La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
የረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች
የዝሁር ሰላትን እንዲ ባማረ መልኩ ሰግደው ተመልሰዋል🥰🥰🥰🥰

እዩዋቸው እስኪ አያስቀኑም የኔ ውቦች😍
ኢማንህ ከፍ ሲልና ከአላህ እርዳታ ዉጭ አንድም ነገር ሊሳካ እንደማይችል ሲገባህ ሁሉ ነገርህን ለፈጠረህ አምላክ ለአላህ ትሠጣለህ። የማትችለውንም የምትችለውንም ሁሉ አንድም ሳታስቀር ታስረክበዋለህ። ገር ነገር ጭምር ሊገራልህ የሚችለው አላህ ሲያገራልህ ብቻ ነውና።

ኢላሂ ጉዳያችን ሁሉ አንተው አግራልን!
ኡስታዝ አህመድ አደም አላህ እጅህን ይባርክልህ!

ከእውቀት የሆኑ መፃህፍትን ስታስነብበን ቆይተሃል!!
ይኸው አሁንም ኡስታዛችን የሰማይ መስኮት በሚል ርእስ የተዘጋጀውን የአስርቱን የመጨረሻ የረመዷን ቀናት፣ ኢዕቲካፍንና ለይለተል ቀድርን አስመልክቶ ሰፋ ያለ እውቀት የሚያስጨብጥ መፅሀፍ ለንባብ አብቅቷል!!

መፅሀፉ በስእሉ ላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ይገኛል!!

የአንብብ ትውልድ ሆይ አንብብ!!!
አሏህ ሱበሀነሁ ወተዓላ በተከበረው ቃሉ እንድህ ይላል፦
۞ وَسَارِعُوا إِلَىٰ مَغْفِرَةٍ مِّن رَّبِّكُمْ وَجَنَّةٍ عَرْضُهَا السَّمَاوَاتُ وَالْأَرْضُ أُعِدَّتْ لِلْمُتَّقِينَ
ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡
(ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 133)

ዛሬ በማያልቀው ገዘባችን ለመልካም ስራ እንሽቀዳደም ።።።።።
Channel photo removed
💎ለሌሎች መልካም በመሆንህ ከአንተ ነገር ላይ ምንም አይቀንስም፡፡
🍂ለሌላቸው ሠዎች ካለህ ላይ ቆንጥረህ በመለገስህ ከአንተ ሀብት ላይ ምንም አይቀንስም እጥፍ ድርብ አርጎ ይዞልህ ይመጣል እንጂ፡፡
🍂ምንጊዜም ለሌሎች መልካም ነገሮችን በሰራህ ቁጥር መልካም እና ውብ ነገሮች ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡አትጠራጠር
በነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጊዜ በተደጋጋሚ አስካሪ መጠጥ እየጠጣ እርሳቸው ፊት በመቅረብ ቅጣት የሚፈጸምበት ሰው ነበር። አንድ ዕለትም እንዲሁ ጠጥቶ በመገኘቱ ግርፋት ፈርደውበት ቅጣቱ ተፈጸመበት። እዚያ ከነበሩ ባልደረቦቻቸው የተወሰኑት “አላህ ያዋርድህ…!” ወዘተ. እያሉ ተራገሙ። ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ግን በዚህ አባባላቸው አልተደሰቱም። በመሆኑም፣ “በጓደኛችሁ ላይ ሰይጣንን አታግዙ፤ ከዚያ ይልቅ ‘አላህ ይማርህ፣ አላህ ቅናቻን (መመራትን) ይስጥህ’ ብላችሁ ዱዓእ (ጸሎት) አድርጉለት” በማለት ገሰጿቸው።
ሶደቃ
~
ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦
"ወንጀሎችህ ከበዙ ሶደቃ አብዛ። ወንጀሎችን ታጠፋለችና።"
📚 [ሸርሑል አርበዒነ ነውዊያህ፡ 361]
=
ረመዷን ያልተቀየረ መቸ ነዉ የሚቀየረዉ ??
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

📣 ትላቅ የዳዕዋ ፕሮግራም ↩️↩️


ጉራጌ ዞን በጉቴ መስጅድ እና በገርቢቻ መስጅድ ነገ የጁመአ እለት በሱና ኡስታዞቻን ደምቀው ይውላሉ


ነገ ጁመአ ቀን 06_08_14 ከጁመዓ ሶላት ከመሰገዱ በፊት ተጀምሮ ቀኑን ሙሉ ዳእዋ ይደረጋል ።

እዛ የሚሄዱ ኡስታዞች

👉ኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዙሁሏህ

👉ኡስታዝ አብዱ ናስር ሀፊዙሁሏህ

እንዲሁም ሌሎችም ኡስታዞች ይገኛሉ ሸር አድርጉት
⇛የደስታ ማግኛ መንገዶች ብዙ ናቸው። ከሁለም የሚልቀው ግን የእናት አባት ዱዓ ነው።

⇛ደስታችሁ ይበዛ ዘንድ ዱዓቸውን ፈልጉ። √በተለይ በዚህ በተከበረ ወር…!
➡️ጀግኖች የሰለፍ እንስቶች💎

💎(የዐቂዳን ጉዳይ ከሂወት አስበልጠው የሚያዩ)

➤የታላቁ ሰለፍ (አሲም ኢብኑ ዐሊይ) ሁለት ሴት ልጆቹ ደብዳቤ ፅፈው ወደርሱ ላኩለት ፡

➤ደብዳቤው እንዲህ ይላል ፡- አባታችን ሆይ ! ሙእተሲም የተባለው መንግስት ኢማሙ አህመድን (ቁርአን ፍጡር ነው እንዲል አስገድዶት ስላልተቀበለውና ቁርአን ፍጡር ነው ስላላለለት እንዳሰረውና በጅራፍ እንደገረፈው ዜናው ደርሶናልናልና) ፡ ይህ መንግስት (ሙእተሲም) ልክ እንደ ኢማሙ አህመድ ቁርአን ፍጡር ነው እንድትል ካስገደደህ አላህን ፍራ እንዳትቀበለው ! እሺ እንዳትለው ! ፈፅሞ ቁርአን ፍጡር ነው እንዳትልለት !

➤ከዚያም እንዲህ አሉ፡- በአላህ ስም እንምላለን ! አንተ ቁርአን ፍጡር ነው ብለሃል የሚለው ዜና ከሚመጣልን ቁርአን ፍጡር አይደለም በማለትህ ቢገድልህና የሞትህ ዜና ቢመጣልን ይሻለናል ፡፡

ምንጭ፡- ተህዚቡል ከማል ( 514-13 )
ያንን ቀን ( አኺራን ) እንፍራ

በጣም አጭር ማስታወሻ
ዑመር ኢብኑልኸጧብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦ "ከሰማይ 'እናንተ ሰዎች ሆይ! ሁላችሁም ሙሉ ለሙሉ ጀነት ትገባላችሁ አንድ ሰው ሲቀር' የሚል ተጣሪ ቢጣራ ያ አንዱ ሰው እኔ እንዳልሆነ እሰጋለሁ፡፡"
(አልሒልያህ፡ 1/73)