La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ፍጠኑ ረመዷን እየፈጠነ ነው።
ቁርአናችሁን፣ ዱዓችሁን፣ ሶላታችሁን፣ ዚክራችሁን፣ ሶደቃችሁን፣ መልካም ሥራዎቻችሁን ሁሉ ወጥራችሁ ያዙ።

ረመዷን መጥቶ ያሰባችሁ ሳይሳካ ከሄደ በርግጥ ከሠራችሁ።
የማያልፍ መስሎ ሲቃይ ቢደራረብ
ጠላት ቢዘረጋም የጥላቻ መረብ
ሰው ግን አይጎዳህም
ገፍቶ አይጥልህም
አይቀንስብህም
አይጨምርልህም
በሰው ተንኮል ሴራ ምንም አትሸበር
በፈጣሪ ፀጋ ተሸሸግ በአምላክ ስር
«የቲምን አደራ»

የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነ
ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን✌️ያሉት፣

ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣

የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።
💦💦💦💦💦💦💦💦


ኑርአህመድ


https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
ምስጢሩ

አንቺ እየከሳሽ እኔ መፋፋቴ
አንቺ አኅንብሰሽ እኔ መቃናቴ
ተርቦ አንጀትሽ ጠግቤ መብለቴ
ባዶ እግርሽን ሆነሽ እኔ መጫማቴ
አንቺ አፊሽ ደርቆ እኔ መጠጣቴ
አንቺ ሳትማሪ ተምሬ ማወቄ
ልፋትሽ ተረስቶ እኔ መደነቄ
ዕውቀትና ክብሬ ስጦታ ውበቴ
ሽልመት ማዓረጌ መልኬ ደም ግባቴ
የእኔ እኮ አይደለም የአንቺ ነው እማ እናቴ
እኔ ባርያው ነኝ ፣ ጥሎ እንደማይጥለኝም እርግጠኛ ነኝ።
ይገርማል!
ይገርማል ሰው ሁሉ እራሱን አልቆ
ጌታውን ሲያረክስ፣
አኼራን ረስቶ ከታች ከላይ ሲሮጥ
ዱኒያን ሊያግበሰብስ፣
ያለ አቅሙ ሲኮፈስ ፤ ከላይ ሲንጠራራ፣
በሰው ለመወደድ ፤ የማይሆን ሲሰራ ....፤
ይገርማል ....፤
ከመሞት ላያመልጥ ፤ ላይረዳው ልጅ ሀብቱ፣
ይገርማል ሰው ሞኙ ፤ ጌታ ያዘዘውን ስራውን መርሳቱ!!
"የሚቆጠሩ ቀናት/ አያመን መዕዱዳት" አላቸው አላህ። እውነትም የሚቆጠሩ ጥቂት ቀናት።
ሄዱ እኮ በረቢ።

ረመዷን 13
#ሰለፍ ነኝ ማለት ቀላል ነው
ነገር ግን የሰለፎች ስራ ስሰራ ነው
እውነተኛ ሰለፍነትህ ሚረጋገጠው
የተመቸህ መርጠህ
ያልተመቸህ ትተህ
ሰለፊይ ነኝ ብለህ
ታወራ ይሆናል ከሀዲስ ተጋጭተህ
ረመዳን ቀን 13
Sadat
ቀብር አምልኮ
ፋና ቲቪ
ሶስት ዱዓዎች
ኡስታስ ሳዳት ከማል ((ከፊዘሁሏህ))
==
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/2430
የቁርዐን ተፍሲር
@Quran_Tefsir
🌙ረመዷን 13

▒▒▒ ያኔ ~ አልቅስ ▒▒▒

👉 በነፍስህና በስሜትህ ተበልጠህ
ለትናንሽም ሆነ ለትላልቅ ወንጀሎች
በቀላሉ እጅ የሰጠህ ቀን።

👉 መልካም ነገርን እያየህ ከመሥራት
ስትሰንፍ ፣ መጥፎን ደግሞ መጥፎነቱን
እያወቅክ ስትዳፈር።

👉 ለሙዚቃ ፣ ለድራማና ለፊልም
ውስጥህ ሲነካ ፡ ለቁርዓን ልብህ
ሲደነደን።

👉 ለዱኒያና ለጥቅሞቿ ስትሮጥ
እንቅልፍ ስታጣ ለአኺራህ ግድ የለሽ
ስትሆን።

👉 ሶላትህ ትርጉም ስታጣብህ ፣
ሩኩዕና ሱጁድ ጎንበስ ቀና ስፖርታዊ
እንቅስቃሴ ብቻ ሲሆንብህ።

👉 ከዒባዳህ ጥፍጥና ስታጣ በአምልኮ
ተግባርህ እርካታን ከተነፈግክ።

👉 ጊዜህን ባልረባ ነገር ስትጨርስ ፡
ኸይር ሳትጨምር ቀን አልፎ ቀን ከተተካ።

👉 የተውባ በር ሁሌም ክፍት ሆኖ
ሳለ ለመግባት ድፍረት ስታጣ።

👉 የዓለማዊው ሕይወት ፍጻሜ መቃረቡን ስታውቅ በበቂ አለመዘጋጀትህን ስትረዳ።

@sineislam @sineislam ☀️
የረጲ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ሙስሊም ተማሪዎች
የዝሁር ሰላትን እንዲ ባማረ መልኩ ሰግደው ተመልሰዋል🥰🥰🥰🥰

እዩዋቸው እስኪ አያስቀኑም የኔ ውቦች😍
ኢማንህ ከፍ ሲልና ከአላህ እርዳታ ዉጭ አንድም ነገር ሊሳካ እንደማይችል ሲገባህ ሁሉ ነገርህን ለፈጠረህ አምላክ ለአላህ ትሠጣለህ። የማትችለውንም የምትችለውንም ሁሉ አንድም ሳታስቀር ታስረክበዋለህ። ገር ነገር ጭምር ሊገራልህ የሚችለው አላህ ሲያገራልህ ብቻ ነውና።

ኢላሂ ጉዳያችን ሁሉ አንተው አግራልን!