La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ሶላት የ ል ብ መድኃኒት፣ የስኬት መሰላል ነው። የሰው ልጅ የእድገቱና የስነ ምግባሩ ሚዛን ሶላት ነው። ሶላቱ የተስተካከለ እንደሆን ሕይወቱ ሰመሯል። በአሏህ(ሱ.ወ) መንገድ ሕይወታቸው ከሚሰምራለቸው ሙዕሚሞች መካከል ያድርገን!

አሚን 🤲
#የፈጅርንሶላት_በመስጂድ
የምንፆመው ምግብ እና መጠጥ ብቻ አይደለም። በደል፣ ተንኮል፣ ዉሸት፣ ሀሜት፣ ክህደት፣ ስርቆት፣ ቅጥፈት፣ መጥፎ ንግግር ፣ የሀሰት ምስክርነት፣ ማታለል፣ የዉሸት መሃላ፣ ጥላቻ፣ ጎሚ፣ በቀል፣ ስካር፣ ... እነኚህን እና የመሳሰሉትን ካልፆምን ፆማችን ትክክል ሊሆን አይችልም።
“ሴት“

አልሀምዱሊላሂ ልጀምር በስሙ፣
ሴት ልጅን ለሰጠን ሀምድ ይግባው ረሂሙ፣

በሁሉም ዘርፍ ላይ ናት የተዋጣላት፣
ቢወራስ አያልቅም የእሷኮ ማንነት፣

ነች እኮ ወድ እናት አምሳያ የሌላት፣
ደሞ በእህትነት ለወንድሟ ምትሞት፣

እንደው ምን ልበላት ቃላት አጣሁላት፣
ጀሊሉ በቁድራው በጀነት ይካሳት፣

ሚስትም ትሆናለች የባል ተፈቃሪ፣
በጦርነት ላይም ምን ባትሆን ወራሪ፣

ወንዱን ታጅባለች ከጎን አባሻሪ፣
ተወዳጇ ሴት ልጅ አባቷን አክባሪ፣

ኧረ ማነው እስቲ ቦታዋን ሚተካ፣
አልፎ ተረማምዶ ነው ክብሯን ሚነካ፣

ነች እኮ ክብር ያላት የቤተሰብ ዋርካ፣
አላህ ይዘንላት ይሙላት በበረካ።

ልክ እንደ ዓኢሻ በእውቀት የተካቡ፣
አሉ በዘመኑም በኢማን ያበቡ፣

በኒቃብ በሂጃብ እጅግ የተዋቡ፣
ሚናቸው አያልቅም ቢከተብ ኪታቡ፣

ልምከርሽ እህቴ ምን ብዙ ባልቀራ፣
ካየሁ ከሰማሁት በጥቂቱ ላውራ፣

በዲን በክብርሽ ላይ አደራ አደራ፣
ከአላህ እንዳይገጥምሽ የስቃይ መከራ፣

እንዳይታለዪ ዘመኑ ባመጣሽ፣
ገዜ እንዳታጠፊ ምንም በማይጠቀምሽ፣

አልፎ ተገልብጦ አንቺን በሚጎዳሽ፣
እንዳትሸወጂ አደራ ልበልሽ፣

እኔም በዚው ላብቃ ግጥሙም ሳይንዛዛ፣
ራህማኑ ይክፈልሽ ሚያምረውን ጀዛ።

ኑርአህመድ

https://t.me/httpsLatahzen
‼️ዘርን ለገበሬ

ዘርን ለገበሬ ብያለሁ አምርሬ፣
ላይጠቅመኝ ሊጎዳኝ ብዬ ዘሬ ዘሬ፣

ሀገሬ ባሌ ነው ኦሮሞ ነው ዘሬ፣
እኔ ጉራጌ ነኝ ምኖረው ጉንችሬ፣
እኔ ሀደሬ ነኝ የሆንኩኝ ሀረሬ፣

ሌላም ሌላም ቢሆን ትቻለሁ አምርሬ፣
ምን ሊጠቅመኝ ነው ለዘር መቆርቆሬ፣
አደም የማን ዘር ነው እላለሁ ደፍሬ፣
ከዛ ሇላ ያለው ነው የሱ ጅማሬ፣

እስቲ ልጠይቅህ አምጣ ስልጤም ትግሬ፣

ከዛ ቅደዳቸው ውጋቸው በጩቤ፣
ሚወጣቸው ደም ነው ዋነኛ ታሳቤ፣
ደሙን ቀላቅዬ ልለየው አስቤ፣
ጭራሹን አይሆንም አይታሰብ ከቶ፣
እስካልተነቀስከው የዘርህን ታቶ፣

ሙስሊሞች አንድ ነን በተውሂዱ ገመድ፣
ምስጋና ይገባው ለጌታችን ሰመድ፣
አንድ ላደረገን በሀቂቃው መንገድ፣

እኛ እንሰግዳለን ሁለም በአንድ መሰጊድ፣
ዘሩን አንጠይቅም ከጎናችን ሚሰግድ፣

ነቢ አስጠንቅቀዋል እኛ እንድንዋደድ፣
ከጥንቧ እራቁ አንድ ሁኑ በተውሂድ፣
ጀሊል እኛን ያርገን በተውሂድ ሚዋደድ።



ኑርአህመድ🖊🖊https://t.me/httpsLatahzen
ረመዳን 1 ፣
ረመዳን 2 ፣
ረመዳን 3 ፣
ረመዳን 4 ፣
ረመዳን 5 ፣
ረመዳን 6 ፣
ረመዳን 7 ፣
ረመዳን 8 ፣
ረመዳን 9፣
ረመዳን 10፣
ረመዳን 11፣
ረመዳን 12፣
ላይመለሱ ሄደዋል!
መልካም ከነበሩ ጨምርባቸው ፣
ካልነበሩ እንደገና ጀምር
ኑርአህመድ

#ውድድሩ ከተሰጠህ ግዜ ጋ ነው።
እባክህ አምላኬ ስጠኝ አንድ ነገር
ጠላቴን ገበሬ እኔን አርገኝ ምድር
ዘጠኝ ወር በጋውን ረግጦኝ ረግጦኝ
ሲለው መፀዳጃ ሲለው ግጦሽ አርጎኝ
ክረምት ሲመጣ ጥቅም ከኔ ሲሻ
ያለምንም እዝነት አርሶ በማረሻ
ይህን ሁሉ ነገር በደሉን እረስቶ
መብቀሉን ሲጠብቅ ቡቃያውን ዘርቶ
የመፃኢ እድሉ በኔላይ ሲወሰን
አላበቅልም ብዬ አላስብ በቀልን
በተገላቢጦሽ አንዷን ሺ አድርጌ
የነገ ተስፋውን ልስጠው አሳድጌ
ከክፋት በጎነት መሻሉን እንዲያውቀው
ከኔ በበቀለው እርሀቡን ይግደለው
የመግፋት ትርጉሙ ማሳደግ መሆኑን
በተግባር ላሳየው ማንም ያላየውን
የበደለው በደል ሁሌ እንዲፀፅተው
በበደሉ ፋንታ እዝነትን ላሳየው
የትግስትን ፍሬ ፍቅር ከኔ እንዲማር
ጠላቴ ገበሬ እኔ ልሁን ምድር

🖊🖊ኑር https://t.me/httpsLatahzen
ኢላሂ
==========
⇛ ካንተ ተነጥለው የሚኖሩት ኑሮ የሰቀቀን መሆኑን በዚህ ታላቅ ወር አሳውቀህናል…፡፡
⇛ ሁሌም በሀሳብም ሆነ በተግባር ካንተ ጋር ከተሳሰሩት አድርገን።
⇛አንተን ማውሳትን ሱሳችን አድርግልን፣
⇛ ሥምህ ከምላሳችን ፣ ልቅናህ ከልቦናችን አይነጠል፡፡
⇛ ዘወትር እናመሰግንህ ዘንድ አንቃን!
አፍጡር ላይ የሚባል

ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ الْعُرُوْقُ وَثَبَتَ اْلأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ.

‘ዘሐበዝዘመኡ ውበተልለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል አጅሩ ኢንሻአህ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِيْ
, አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሐለሁ፡
ፍጠኑ ረመዷን እየፈጠነ ነው።
ቁርአናችሁን፣ ዱዓችሁን፣ ሶላታችሁን፣ ዚክራችሁን፣ ሶደቃችሁን፣ መልካም ሥራዎቻችሁን ሁሉ ወጥራችሁ ያዙ።

ረመዷን መጥቶ ያሰባችሁ ሳይሳካ ከሄደ በርግጥ ከሠራችሁ።
የማያልፍ መስሎ ሲቃይ ቢደራረብ
ጠላት ቢዘረጋም የጥላቻ መረብ
ሰው ግን አይጎዳህም
ገፍቶ አይጥልህም
አይቀንስብህም
አይጨምርልህም
በሰው ተንኮል ሴራ ምንም አትሸበር
በፈጣሪ ፀጋ ተሸሸግ በአምላክ ስር
«የቲምን አደራ»

የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነ
ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን✌️ያሉት፣

ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣

የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።
💦💦💦💦💦💦💦💦


ኑርአህመድ


https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
ምስጢሩ

አንቺ እየከሳሽ እኔ መፋፋቴ
አንቺ አኅንብሰሽ እኔ መቃናቴ
ተርቦ አንጀትሽ ጠግቤ መብለቴ
ባዶ እግርሽን ሆነሽ እኔ መጫማቴ
አንቺ አፊሽ ደርቆ እኔ መጠጣቴ
አንቺ ሳትማሪ ተምሬ ማወቄ
ልፋትሽ ተረስቶ እኔ መደነቄ
ዕውቀትና ክብሬ ስጦታ ውበቴ
ሽልመት ማዓረጌ መልኬ ደም ግባቴ
የእኔ እኮ አይደለም የአንቺ ነው እማ እናቴ
እኔ ባርያው ነኝ ፣ ጥሎ እንደማይጥለኝም እርግጠኛ ነኝ።
ይገርማል!
ይገርማል ሰው ሁሉ እራሱን አልቆ
ጌታውን ሲያረክስ፣
አኼራን ረስቶ ከታች ከላይ ሲሮጥ
ዱኒያን ሊያግበሰብስ፣
ያለ አቅሙ ሲኮፈስ ፤ ከላይ ሲንጠራራ፣
በሰው ለመወደድ ፤ የማይሆን ሲሰራ ....፤
ይገርማል ....፤
ከመሞት ላያመልጥ ፤ ላይረዳው ልጅ ሀብቱ፣
ይገርማል ሰው ሞኙ ፤ ጌታ ያዘዘውን ስራውን መርሳቱ!!
"የሚቆጠሩ ቀናት/ አያመን መዕዱዳት" አላቸው አላህ። እውነትም የሚቆጠሩ ጥቂት ቀናት።
ሄዱ እኮ በረቢ።

ረመዷን 13
#ሰለፍ ነኝ ማለት ቀላል ነው
ነገር ግን የሰለፎች ስራ ስሰራ ነው
እውነተኛ ሰለፍነትህ ሚረጋገጠው
የተመቸህ መርጠህ
ያልተመቸህ ትተህ
ሰለፊይ ነኝ ብለህ
ታወራ ይሆናል ከሀዲስ ተጋጭተህ
ረመዳን ቀን 13
Sadat
ቀብር አምልኮ
ፋና ቲቪ
ሶስት ዱዓዎች
ኡስታስ ሳዳት ከማል ((ከፊዘሁሏህ))
==
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem/2430
የቁርዐን ተፍሲር
@Quran_Tefsir