La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ
# አልሀምዱ ሊላህ
# Alhamdu lilahe
ለሀይማኖታዊ መብቱ ሚታገልለት ህዝባዊ መጅሊስ የተነፈገው ትውልድ
በሰላማዊ መንገድ አንድነቱን ጠብቆ የሀይማኖቴን መብት መብቴን አትንኩብኝ
ብሎ የሚጠይቅ ታዳጊ ትውልድ ማየት በጣም ደስ ይላል አልሀምዱ ሊላህ
በ1990ዎቹ የአዲስ አበባ
ትምህርት ቤቶች የሰላት
ችግር ስለነበር የመጅሊሱ መሪ
ችግሩን ሊፈቱ ሄደው
«የመጣችሁት ለትምህርት
ነው፤ ሰላታችሁን ቤታችሁ
ሰብስባችሁ ስገዱ» የሚል
ፈተዋ ሰጥተው ነበር።
ዘንድሮስ?
ይህ ትውልድ ፍም እሳት ነው
በነካቹን ቁጥር እንጠነክራለን
🔹ሰላትን አደራ!🔹


ወደ አላህ መሸሻ:
አጅር ያለው ጉርሻ:
የሩህ መናፈሻ:
የመንፈስ ማደሻ:
ጎዶሎን መካሻ:
ወደ አላህ ማልቀሻ:
ለሌላ ዒባዳ ቀልብን ማነሳሻ:
🍀@Nur4843🍀
ቀልብህ እንዲራራ:
እንዳይሆን መራራ:
በሀራም በረራ:
ከፉጃሮች ተራ:
እኔም በዚው ላብቃ ብዙ ሳላወራ:
ወንድሜ ልምከርህ ሰላትን አደራ!!
ምን ቢበዛብህም የችግር መከራ:
ባንተ ላይ ቢዘንብም ባንተም ቢያባራ:
በትግስት ጠብቅ የፀሀዩዋን ጮራ:
ምንም ብትዘገይ አትቀር ተቀርቅራ።


ኢንሻአላህ
«አላህን ከሚያስረሳ ሀብት ጀነትን ሚያስናፍቅ ድህነት ይሻላል።»
ሙእሚን በዱንያ ለነገ አያውቅም:
ሀሳቡ ሌላ ነው በርካሽ አይወድቅም:

«––––––––––––––»

ዛሬ ላይ የሰጠው ነገ የትስ ሄዶ:
ቃሉን አያፈርስም ፅፉል ያኔ ማዶ:

«––––––––––––––––»

ሊስትሮም ወዛደር ቢበላም ነግዶ
ሁሌም አመስጋኝ ነው ለፈጣሪው ሰግዶ።
"ትልቁ ፈተና
ተሸራተህ
በሀቅ ላይ ያለህ ሲመስልህ ነው"
ሁሌም ታገስ፣በርታ፣ፅና

🌿የፀና ሰው ቀና🌿
🌿የበረታ ረታ🌿
🌿የዘራም አፈራ🌿
🌿የታገሰ ነገሰ🌿
🌿የጠነከረ ከበረ🌿
ዝቅ ስትል ከፍ የሚያደርገው ጌታ ይመስገን፤ አልሀምዱሊሏህ

#የፈጅርንሶላት በመስጂድ
ሃገር ውስጥ ያለነውን ሰላት አትስገዱ ብሎ ከልክሎ ሲ ያበቃ ባህር ማዶ ያሉትን ኑና ስገዱ ማለት እንዴት ነው ነገሩ⁉️
"የኢኽላስ ኢባዳ"

ስራን ለአላህ ማጥራት፣
ከልብ የእውነት፣
ሪያእ የሌለባት፣
ሱምዓም የማይቀርባት፣
ኡጅብም የማይደፍራት፣
ዱንያ ማታታልላት፣
ለአላህ ያለች ፅድት፣
ሽርክ ሆነ ቢድዓ ከቶ የማይቀርባት፣
ምታስገባ ጀነት የምታርቅ ከእሳት፣
የኢኽላስ ኢባዳ የዝች አይነቷ ናት፣
ደግሞ ትንሽ ላውጋ የኢኽላስ ባልተቤት፣
እሱ ባልተቤት ነው የውዲቷ ጀነት፣
ስራውን ደባቂ አላህን አዋቂ፣
እጅግ ተጠንቃቂ፣
ልቡም የሚጠላ መሆንን ታዋቂ፣
በኢባዳ ላይም ዘውታሪ ዘላቂ፣
ነው እኮ አልቃሻ፣
ወርዶ ከትከሻ፣
አብዝቶ ሚኮንን መባልን በሻሻ፣
ነው የኢማን ዋሻ የተቅዋ መንገሻ፣
ቀን በፆም ይውላል፣
ሌሊቱን ይቆማል፣
ጌታውን አብዝቶ ከልቡ ይፈራል፣
ጀነትን ከጅሏል ፣
እሳትንም ፈርቷል፣
በእሳት ፍራቻም ሌት ቀኑን ያለቅሳል፣
በስራው ማይኮራ፣
አልፎ እንደው ሚፈራ፣
አሳነስኩኝ ብሎ ከሚገባው ስፍራ፣
ደስታው የቀነሰ ሀዘኑም ከራራ፣
ሳቅን ማያበዛ ያልሆነ ሞዛዛ፣
ሁሌም የሚለምን የጌታውን ጀዛ፣
ዱንያንም የናቀ ተቅዋው የረቀቀ፣
ከሸህዋ የራቀ ጀነት የናፈቀ፣
ወንድሙን መካሪ፣
ባለ ውድ ባህሪ፣
ስለርሱ ባወጋ ደርሼ አልጨርሰው፣
በአጭሩ ይህ ነው የዛ ውድ ባህሪው፣
አላህ ውለታውን አብዝቶ የሰጠው፣
ያራህማን አድርገን የሱ አይነት አምሳያው።
ምን ጊዜም ኢስላም በሌለበት ስልጣኔ ማለት ያለ ሩህ ህይወት እንደማለት ነው። ተመልከት ዛሬ ላይ በጣም ሰልጥነዋል እየሰለጠንን ነው የሚባሉ ሀገራት በዘረኝነት እየተፋጩ ስታይ ወላሂ ከምንም በላይ ጌታህን አመስግን ምክንያቱም ኢስላም ለሁሉም ልኩን የሰጠ፣ ጥመብን ከንፁ የለየ፣ የሚጠቅምን ሁሉ የፈቀደ፣የሚጎዳ የተባለን በሙሉ የከለከለ ምርጥ እምነት ነው። አሁንም አመስግን የዚ እምነት ተከታይ ላደረገህ ጌታ።

الحمد لله
በተናደድህ ሰዓት የምትናገረው እወቅ
ንዴቱ ሲለቅህ የተናገርከው ስትጠየቅ
ወላሂ እንዲ አላልኩም ነበር ብለህ ከምትዘባርቅ
መጀመሪያ ራስህን አስጠንቅቅ
"አንድ አንድ ወንጀሎች ህግ የማይዳኛቸው አሉ ነገር ግን ጊዜ በራሱ ፍርድ ይሰጣል።"
#ሙስሊም_መሆን_መታደል_ነው!!

#የፈለገ ያህል ብትሳሳት/ብትወነጅል
ሰላት መስገድን አታቁም፣ ኸይር ስራ ከመስራት አትቦዝን ትንሽም ትልቅም ቢሆንም፣ አላህን ለምን፣ ኢስቲግፋር ማድረግን አብዛ በአላህና በአንተ መካከል ያለውን በር በፍፁም እንዲዘጋ አትፍቀድለት‼️

#መቼም ቢሆን ከአላህ እዝነትም ተስፋ አትቁረጥ 🚫

አላህ እንዲህ ይላል
{ ﻗُﻞْ ﻳَﺎ ﻋِﺒَﺎﺩِﻱَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺃَﺳْﺮَﻓُﻮﺍ ﻋَﻠَﻰ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﻻ ﺗَﻘْﻨَﻄُﻮﺍ ﻣِﻦ ﺭَّﺣْﻤَﺔِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﺇِﻥَّ ﺍﻟﻠَّﻪَ ﻳَﻐْﻔِﺮُ ﺍﻟﺬُّﻧُﻮﺏَ ﺟَﻤِﻴﻌًﺎ ﺇِﻧَّﻪُ ﻫُﻮَ ﺍﻟْﻐَﻔُﻮﺭُ ﺍﻟﺮَّﺣِﻴﻢُ}

#በላቸው «እናንተ በነፍሶቻችሁ ላይ ድንበር ያለፋችሁ ባሮቼ ሆይ, ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ አላህ ኃጢኣቶችን በመላ ይምራልና ፡፡ እነሆ እርሱ መሓሪው አዛኙ ነውና ፡፡"

➩ [አዙመር 53]
ጊዜህ አይገዝግዝህ

ወንድሜዋ ንቃ:
ልክ እንደ ጥበቃ:
እድሜህ ሳታበቃ:
ስንፈቱ አያጥቃ:

ጊዜ እኮ ወርቅ ነው:
ልክ እንደሚባለው:
በኛው በሀበሻ እንደሚተረተው:
ግን ምን ዋጋ አለው:
ተጠቃሚ የለው:
አላህ ካላደለው:
የሚጠቀምበት አቅለኛ ብቻ ነው:
ኢማሙ ሻፊእይ አሉ እንደሚባለው:
ጊዜ እንደ ሰይፍ ነው:
ሳይቆርጥህ ቁረጠው።

ይህን ትርፍ ጊዜ:
አታጥፋው በአባዜ:
አትሁን ፈዛዜ:
ሓላ አታገኘውም አልፎ ይሄ ግዜ:

ከልብህ አድምጠኝ:
በጊዜህ አትሞኝ:
ካለፈህ አታገኝ:

ደግሞ አትሰላች ደካማ አትሁን:
እሩቅ ህልምን አልም ማያስተኛህ ዛሬን።
🛑ዳሩል ፊትና🛑

በዱንያ መኖርህ:
ሀብት መንበሽበሽህ:
ድሎት ቢበዛብህ:
ኒእማ እንዳይመስልህ:
🌺🌺🌺🌺🌺
የዱንያ ሀያት:
የፊትና ጊዜ ናት:
አትታለልባት:
ድሎት ብትል ክፋት:
ሁሏም ለፊትና ናት:
🌺🌺🌺🌺🌺
ይህን ተገንዝበህ:
ራስን አዘጋጅተህ:
🌺🌺🌺🌺🌺
ተፈተን ፈተና:
ውጤት ከጅልና።
🌺🌺🌺🌺🌺
♣️ድንቄም ዘመናዊ♣️

የእርድና ትግል በፋራዎች አንግል:
ዝመና መስሏቸው ለሆኑት ጅላጅል:

ቀዉሌን አድርሱልኝ ዘማኝ ለሚመስል:
ከሴቷ ልጀምር ከገባችው ገደል:

አይታ ትገባለች ከአደባባይ ወጥታ:
ሰብአዊ ያልሆኑ ከእንስሳት ተርታ:

አራዳ ነን ብለው ሚያሰሙ ኡኡታ:
እሷም እግረ መንገድ ድምፃቸውን ሰምታ:

ማስተጋባት ያዘች የነሱን ኡኡታ:
በድምፅ አይምሰልህ በተግባሯ ሰርታ:

መውጣት ጀምራለች ራሷን አራቁታ:
ሽቶና ዶደራንት በራሷ ላይ ነፍታ:

ትፈናጠዛለች ታስሮ እንደ ተፈታ:
መግባቷስ መች ቀረ ከአጅነቢ እይታ:

ትሞላፈጣለች ለመለከፍ ሽታ:
ፊቷ ላይ ለቅልቃ የቀለም ጋጋታ:

ወንድ ተብየውም አራዳ ነኝ ባዩ:
መባልን ከጅሎ ነው እኮ አማላዩ:

ፀጉሩን አበላልጦ ሲኪኒውን ለብሶ:
እሷን ለማማለል አቅዶ ጠንስሶ:

ራሱን ገምቶ ተመስሎ አረዳ:
ቢያውቅማ ነበር ሞኛ ሞኝ ገዳዳ:

ድንቄም ነሽ አራዳ:

አራዳማ እሱ ነው ያ የሱና አንበሳ:
አጅነቢ ለማየት አይኑን ማያነሳ:

ቆፍጠን ያለ ጀግና ያልሆነ ኮሳሳ:
ሱሪ ያሳጠረ ፂሙን ማያነሳ:

ሴቷም አራዳ ነች ያች የሱና ጀግና:
በሰለፎች መንገድ በሀቅ ላይ ሆና:

እንደዛች ኮሽኳሺት የማትቀር መና:
በኒቃብ ተዉባ በሂጃቧ ዘምና:

በአላህ በሩሱሉ አረጋግጣ አምና:
በቁርአን በሀዲስ ነች የምትቃና:

ይህን ካልኩ ይበቃል እንደው ለናሙና:
እርድና ይሄ ነው የሁለት ሀገር ጀና።


Be dgmie yetlkek