La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
መመሪያው በዓላማ 5.3 ሥር የተቀመጡት ትክክለኛ ሕገ መንግስታዊ ናቸዉ።ነገር ግን ዓላማውን ለመተግበር የተደነገጉ ድንጋጌዎች ሁሉም ከዓላማው እጅጉኑ ተፃራሪ ናቸዉ።

በመመሪያዉ ክፍል ሁለት ሥር ሂጃብን ይፈቅድና ኒቃብን ይከለክላል። ይህ አገላለፅ በራሱ ችግር አለበት። በመጀመሪያ ደረጃ ሂጃብ ማለት የቱ ነው? ይህቺ ወንዶችን የሚያደጓት ጥምጣም ዓይነት ነች ሂጃብ? ወይስ ጅልባብ የሚባለዉ? አልያስ ዋጂብነቱ በከፊል ዑለሞች የሚታወቀው ኒቃብ? የቱ ነው? ትምህርት ሚኒስቴር በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ይህ ይቻላል፤ይኸኛው ደግሞ አይቻልም ማለት ይችላልን? ሃይማኖቱን የመተርጎም ሥልጣን የመንግስት ወይስ የሃይማኖቱ ምሁራን? መመሪያው አለባበስ በሚል ርዕስ ሥር "የክርስትና እምነት ተከታይ መነኮሳት እና ካህናት እንዲሁም የእስልምና እምነት ተከታይ ሼኾች ብቻ በትምህርት ተቋማት ቆብ ሊያደርጉ ወይም ሻሽ ሊጠመጥሙ ይችላሉ።" ይላል።

ለመሆኑ ማን ነው መነኮሳት፥ ካህናት እና ሼኮች እንደ ሆኑ የሚለየዉ? ትምህርት ሚኒስቴር በምን መልኩ እና መመዘኛ ይህ ሊል ይሁን? ይህስ በሕገ መንግስት አንቀፅ 11(3) "መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም። ሃይማኖትም በመንግስ ጉዳይ ጣልቃ አይገባም።" የሚለውን አይጥስምን?

መመሪያው "በትምህርት ተቋማት ጊቢ በምንም መልኩ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታዮች በቡድን የአምልኮ ሥርዓት መፈፀም አይችልም" ይላል።

ህገ መንግስቱ "ማንኛውም ሰዉ የማሰብ፣የኅሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለው።ይህ መብት ማንኛዉም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱን እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣የመከታተል ፣የመተግበር ፣የማስተማር ወይም የመግለፅ መብትን ያትታል።"ይላል። ስለሆነም የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሕገ መንግስቱ በመግለፅ የሚቃረን በመሆኑ በመኾኑ ተፈፃሚነት አይኖረውም። ይህ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችውን ዓለም አቀፍ ሕጎች በቀጥታ የሚቃረን ነው።

ለአብነት በዩኔስኮ የሰብአዊ መብት ስምምነት ላይ :- "እያንዳንዱ ሰዉ የሀሳብ፣የኅሊና እና የሃይማኖት ነፃነት መብት አለው።ይህም መብት ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ፣ነፃነትን ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኅብረት በይፋ ወይም በግል ኾኖ ሃይማኖቱን ወይም እምነቱ የማስተማር፣በተግባር ለመግለፅ፣የማምለክ እና የማክበር ነፃነትን ይጨምራል።"ይላል። ታዲያ ትምህርት ሚኒስቴር ይህን የዩኒስኮን ዓለም አቀፍ ስምምነት የሚጥስ መመሪያ እንዴት አዘጋጀ?

በኢትዮጲያ ሕገ መንግሥት መሠረት ማንም አካል ስላሰኝው ብቻ የአንዱን ሃይማኖት ተግባር ማገድ እንደ ማይችል ተገልጿል።ሕገ መንግስቱ በአንቀፅ 27(5) ላይ "ሃይማኖትን እና እምነትን የመግለፅ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብ ደኅንነት፣ ሰላም፣ ጤና ፣ ትምህርት፣ የሕዝብ የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች፣ነፃነቶች እና መንግስት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል።" ይላሉ።

ነገር ግን መመሪያው በድፍኑ የተከለከሉት ሃይማኖታዊ ድርጊቶች በሕገ መንግስቱ እንደ ተጠቀሰው አደገኛ ሁኔታ ስለመፍጠራቸዉ የቀረበ ነገር የለም።ገና ለገና ይሆናሉ ተብለው ሳይሆን ፈጥረው ሲገኙ ብቻ ነው።ይህም ቢሆን ዝም ተብሎ በአንድ መሥሪያ ቤት ፍላጎት ብቻ የሚሆን ሳይሆን በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 13(2) ላይ እንደ ተገለፀው ከዓለም አቀፍ መርሆች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም ይኖርበታል።

በዮኔስኮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነድ አንቀፅ 29(2) እንዲህ ይላል፦

"እያንዳንዱ ሰዉ በመብቶቹ ፣በነፃነቶቹ በሚጠቀምበት ጊዜ የሚታገደው የሌሎችን መብቶች እና ነፃነቶች በሚገባ ለማስከበር ብቻ በተደነገጉ ሕጎች እና የግብረ ገብነት፣ የጠቅላላውን የሕዝብ ፀጥታ እና ደኅንነት በዴሞክራሲያዊ ፣ማኅበራዊ ኑሮ ትክክለኛ የኾነዉ ተፈላጊ ጉዳይ ለማርካት በተወሰነው ብቻ ነው።"

በመግቢያችን እንደገለፃነው ሕገ መንግስቱ መተርጎም ያለበት በማብራሪያው እና በወቅቱ ሲፀድቅ በነበረዉ ቃለ ጉባኤ አማካኝነት መኾን ይኖርበታል። ሃይማኖታዊ ተግባራት ላይ የሚጣል እገዳን በሚመለከት ለምሳሌ በ1948 በወጣው ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 እንዲህ ተቀምጧል፦

"የሕዝብን መልካም ጠባይ ወይም ፀጥታን ወይም ፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግስት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች በሕግ የሃይማኖታቸው ሥርዓት አክብረው በነፃ ለመፈፀም አይከለክሉም።" ይላል። ይህ ገደብ ሕገመንግስቱ የነበረ መሆኑን ያስገነዝበናል።

እንደዚሁም በአላማው ስር በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 27(5) ሥር የተገለጹ ገደቦችን በሕግ አግባብ ገደብ ለመጣል መሟላት ያለበት ጉዳይ የተባለው ገደብ ህጋዊ (Legitimate) ያሁኑ ሕገመንግስት ውስጥ በግልጽ የተቀመጡ የኃብረተሰቡ ውስጥ ጥቅሞች ለማስጠበቅ "አድሏዊነትነው የሚያስከትል መሆን የለበትም" ከሚለው የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ማብራሪያ አንጻር ስንመለከተው መመሪያው አድሏዊ ውጤትን የሚያስከትል ነው።

ምንም እንኳ መመሪያው አንቀጽ 5·2 "አድሎን የማስወገድ አላማ አለኝ" ቢልም ዝርዝር ድንጋጌዎች ስንመለከት በአንድ ኃይማኖት በኢስላም ላይ ያነጣጠሩ ሆነው እናገኛቸዋለን። ከዚህም በላይ ሊነጻጸሩ የማይችሉ ነገሮች በአንድ ላይ መጨፍለቅ በራሱ አድሎዊ ነው።

ስለዚህ ጠቅላላ መመሪያው በሃይማኖት ላይ እንደተደረገ ገደብ ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች በተለይ( Iccpr) ቅድመ ሁኔታዎች ጋር የማይጣጣም ነው።

መመሪያ ረቂቅ ከሕገመንግስቱ ጋር በግለጽ ይጋጫል። ስለ ገደብ የሚያወሳውን የአገራችንን ሕገመንግስት አንቀጽ 27(5) በሕግ አተረጓጐም መሠረት የልዩ ሁኔታ (Exception) ሲሆን እንደነዚህ ያሉት የልዩ ሁኔታ አንቀጾች መተርጎም ያለባቸው በጠባቡ እና እና በጥብቅ ሁኔታ መሆን አለበት።
Untitled Project 4
🎙 للشيخ بندر بليلة

ጣፍጭ የቲላዋ ግብዣ!

አሳ በህይወት ለመኖር ውሀ እንደ ሚያስፈልገው ሁሉ ቀልባችን ህያው ይሆን ዘንድ ቁርአን ያስፈልገዋል!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Canadian Prime Minister Justin Trudeau


የእስልምናን ፍኖት እጋርዳለሁ ብለህ ከመጋጋጥ ይልቅ አምነህ ተቀብለህ ተገቢውን ድጋፍ ብታደርግ ነው የሚያዋጣው። ላይሳካልህ ነገር የምታተርፈው ነገር ሙስሊሞችን ማጠናከርና ራስህን ማስገመት ብቻ ነው። እስልምናን ለማስቆም መሞከር የጸሐይን ብርሃን በመዳፍህ ሸፍነህ ምድርን ጨለማ ለማድረግ እንደመሞከር ነው። አይደለም መዳፍህን ሙሉ ሰውነትህን ዘርግተህ ብትዘረር የጸሐይን ጮራ መሸፈን እንደማትችለው ሁሉ፤ ሶላትን አይደለም ት/ቤት ውስጥ መኖሪያ ቤታችሁ ውስጥም አትሰግዱም ብለህ ብታዝ ሙስሊሞችን ይባስ ታጠናክራቸዋለህ እንጂ ቅዠትህ ዕውን አይሆንም።


እንኳን አንተ ከአንተ በላይ ሴኪዩላር ነን ብለው ቃሉን ራሱ ያስተማሩህ ሃገራት መሪዎች እንዲህ እጅ ሰጥተው በሰላም ሙስሊሙ ጋር እየኖሩ ነው። የአንተ ግን የመሃይምነት ጥግ በሃገሪቱ ከግማሽ በላይ ከሆነ ህዝብ ጋር በህልውናው መጥተህ ቀይ መስመር ታልፋለህ። ተመከር ወዳጄ የማትጨርሰውን ጉዞ አትጀምር፤ ወደ ኋላም መመለስ፣ ወደፊትም መገስገስ በማትችልበት ወጥመድ ገብተህ መካከል ላይ ሰምጠህ ትቀራለህ።
||
አንድ ሰው ጭንቀትና ትካዜ አጋጥሞት ይህንን ዱዓእ ካደረገ አላህ ያስወግድለታል ብለዋል ነቢያችን ﷺ። እናም ሐፍዙት።


«اللهم إني عبدك، ابن عبدك، ابن أمتك، ناصيتي بيدك، ماضٍ فيَّ حكمك، عدلٌ فيَّ قضاؤك، أسألك بكل اسمٍ هو لك، سميتَ به نفسَك، أو علَّمتَه أحدًا من خلقك، أو أنزلتَه في كتابك، أو استأثرتَ به في علم الغيب عندك؛ أن تجعل القرآنَ ربيع قلبي، ونور صدري، وجلاء حزني، وذهاب همِّي»
«ቀጣዩን ትውልድ ልክ እንደኛ "ታገሱ! አርፈህ ትምህርትህን ተማር!" ምናምን እያልን የምናሳድግ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል። ልጆቻችንን "በዲንህ ጉዳይ ለመሞት ዝግጁ ሁን፤ ቤት ተመልሰህ እንዳትመጣ!" እያልን ነው የምንመክራቸው። መብታችንን ከማክበር ውጭ ምንም ምርጫ የላችሁም። ትንታግ የሆነ ትውልድ እየመጣ ነው። ሁለተኛ ዜግነት ደህና ሰንብት።»

© ዶ/ር ቃልኪዳን ሐሰን (Kh Abate) ከጂማ ዩኒቨርስቲ
ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ
# አልሀምዱ ሊላህ
# Alhamdu lilahe
ለሀይማኖታዊ መብቱ ሚታገልለት ህዝባዊ መጅሊስ የተነፈገው ትውልድ
በሰላማዊ መንገድ አንድነቱን ጠብቆ የሀይማኖቴን መብት መብቴን አትንኩብኝ
ብሎ የሚጠይቅ ታዳጊ ትውልድ ማየት በጣም ደስ ይላል አልሀምዱ ሊላህ
በ1990ዎቹ የአዲስ አበባ
ትምህርት ቤቶች የሰላት
ችግር ስለነበር የመጅሊሱ መሪ
ችግሩን ሊፈቱ ሄደው
«የመጣችሁት ለትምህርት
ነው፤ ሰላታችሁን ቤታችሁ
ሰብስባችሁ ስገዱ» የሚል
ፈተዋ ሰጥተው ነበር።
ዘንድሮስ?
ይህ ትውልድ ፍም እሳት ነው
በነካቹን ቁጥር እንጠነክራለን
🔹ሰላትን አደራ!🔹


ወደ አላህ መሸሻ:
አጅር ያለው ጉርሻ:
የሩህ መናፈሻ:
የመንፈስ ማደሻ:
ጎዶሎን መካሻ:
ወደ አላህ ማልቀሻ:
ለሌላ ዒባዳ ቀልብን ማነሳሻ:
🍀@Nur4843🍀
ቀልብህ እንዲራራ:
እንዳይሆን መራራ:
በሀራም በረራ:
ከፉጃሮች ተራ:
እኔም በዚው ላብቃ ብዙ ሳላወራ:
ወንድሜ ልምከርህ ሰላትን አደራ!!
ምን ቢበዛብህም የችግር መከራ:
ባንተ ላይ ቢዘንብም ባንተም ቢያባራ:
በትግስት ጠብቅ የፀሀዩዋን ጮራ:
ምንም ብትዘገይ አትቀር ተቀርቅራ።


ኢንሻአላህ
«አላህን ከሚያስረሳ ሀብት ጀነትን ሚያስናፍቅ ድህነት ይሻላል።»
ሙእሚን በዱንያ ለነገ አያውቅም:
ሀሳቡ ሌላ ነው በርካሽ አይወድቅም:

«––––––––––––––»

ዛሬ ላይ የሰጠው ነገ የትስ ሄዶ:
ቃሉን አያፈርስም ፅፉል ያኔ ማዶ:

«––––––––––––––––»

ሊስትሮም ወዛደር ቢበላም ነግዶ
ሁሌም አመስጋኝ ነው ለፈጣሪው ሰግዶ።
"ትልቁ ፈተና
ተሸራተህ
በሀቅ ላይ ያለህ ሲመስልህ ነው"
ሁሌም ታገስ፣በርታ፣ፅና

🌿የፀና ሰው ቀና🌿
🌿የበረታ ረታ🌿
🌿የዘራም አፈራ🌿
🌿የታገሰ ነገሰ🌿
🌿የጠነከረ ከበረ🌿
ዝቅ ስትል ከፍ የሚያደርገው ጌታ ይመስገን፤ አልሀምዱሊሏህ

#የፈጅርንሶላት በመስጂድ
ሃገር ውስጥ ያለነውን ሰላት አትስገዱ ብሎ ከልክሎ ሲ ያበቃ ባህር ማዶ ያሉትን ኑና ስገዱ ማለት እንዴት ነው ነገሩ⁉️
"የኢኽላስ ኢባዳ"

ስራን ለአላህ ማጥራት፣
ከልብ የእውነት፣
ሪያእ የሌለባት፣
ሱምዓም የማይቀርባት፣
ኡጅብም የማይደፍራት፣
ዱንያ ማታታልላት፣
ለአላህ ያለች ፅድት፣
ሽርክ ሆነ ቢድዓ ከቶ የማይቀርባት፣
ምታስገባ ጀነት የምታርቅ ከእሳት፣
የኢኽላስ ኢባዳ የዝች አይነቷ ናት፣
ደግሞ ትንሽ ላውጋ የኢኽላስ ባልተቤት፣
እሱ ባልተቤት ነው የውዲቷ ጀነት፣
ስራውን ደባቂ አላህን አዋቂ፣
እጅግ ተጠንቃቂ፣
ልቡም የሚጠላ መሆንን ታዋቂ፣
በኢባዳ ላይም ዘውታሪ ዘላቂ፣
ነው እኮ አልቃሻ፣
ወርዶ ከትከሻ፣
አብዝቶ ሚኮንን መባልን በሻሻ፣
ነው የኢማን ዋሻ የተቅዋ መንገሻ፣
ቀን በፆም ይውላል፣
ሌሊቱን ይቆማል፣
ጌታውን አብዝቶ ከልቡ ይፈራል፣
ጀነትን ከጅሏል ፣
እሳትንም ፈርቷል፣
በእሳት ፍራቻም ሌት ቀኑን ያለቅሳል፣
በስራው ማይኮራ፣
አልፎ እንደው ሚፈራ፣
አሳነስኩኝ ብሎ ከሚገባው ስፍራ፣
ደስታው የቀነሰ ሀዘኑም ከራራ፣
ሳቅን ማያበዛ ያልሆነ ሞዛዛ፣
ሁሌም የሚለምን የጌታውን ጀዛ፣
ዱንያንም የናቀ ተቅዋው የረቀቀ፣
ከሸህዋ የራቀ ጀነት የናፈቀ፣
ወንድሙን መካሪ፣
ባለ ውድ ባህሪ፣
ስለርሱ ባወጋ ደርሼ አልጨርሰው፣
በአጭሩ ይህ ነው የዛ ውድ ባህሪው፣
አላህ ውለታውን አብዝቶ የሰጠው፣
ያራህማን አድርገን የሱ አይነት አምሳያው።
ምን ጊዜም ኢስላም በሌለበት ስልጣኔ ማለት ያለ ሩህ ህይወት እንደማለት ነው። ተመልከት ዛሬ ላይ በጣም ሰልጥነዋል እየሰለጠንን ነው የሚባሉ ሀገራት በዘረኝነት እየተፋጩ ስታይ ወላሂ ከምንም በላይ ጌታህን አመስግን ምክንያቱም ኢስላም ለሁሉም ልኩን የሰጠ፣ ጥመብን ከንፁ የለየ፣ የሚጠቅምን ሁሉ የፈቀደ፣የሚጎዳ የተባለን በሙሉ የከለከለ ምርጥ እምነት ነው። አሁንም አመስግን የዚ እምነት ተከታይ ላደረገህ ጌታ።

الحمد لله