La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
La tehzen
ረመዷን ሱሑር (7) *** ከትናንት ወድያ ኮልፌ ላይ ሦስት ሰዎችን ቀበርን። በረመዷን ወር፣ በእዝነቱ ቀናት ዉስጥ ነዉና የሞቱት ኸይረኞች ይሆናሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይገርመኛል ኮልፌ ገበያዋ ሁሌም ክፍት ነው። በረመዷንም ከረመዷን ዉጭም። ክረምትም በጋም። ጠዋትም ማታም። ከሟቾቹ መካከል ሁለት የረመዷን ቀናትን የፆመ አለ። በሦስተኛው ቀን ላይ ድንገት ተያዘና በቃህ ተባለ። አጀል ማለት እንዲህ…
ከአላህ ዉዴታ ቀጥሎ በጥሩ ወንድሞችና እህቶች ስንወደድና ለኛ የማይገባ የሆነ ቦታና ክብር ሲስጠን ከፍተኛ የሆነ የደስታ ስሜት ይሰማናል። የዚህ ሁሉ ዉለታ ባለቤቱ አላህ ነው። መጥፎነታችንን ሰትሮ መልካምነታችንን ላሳየልን ጌታ ትልቅ ምስጋና ይገባው።
በአላህ መንገድ የተዋወቅን ወዳጆቼ ሁሉ ስለናንተ ማሰቡ ብቻ ሁሉ ብዙ ደስ ይላል ።
ታላቅ የረመዳን የዳዕዋ ፕሮግራም‼️

1) የተውሒድ ትሩፋትና አንገብጋቢነት
በኡስታዝ ተውፊቅ ራህመቶ
2) ረመዳንና ተቅዋ
በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

የፊታችን እሁድ ሚያዝያ 2፣ 2014 አለም ባንክ ስልጤ ሰፈር በሚገኘው አዒሻ መስጂድ ከ ጠዋቱ 3:00 ጀምሮ

ለወንዶችም ለሴቶችም ከነ ቤተሰቦዎ ተጋብዘዋል!


🎙ልዩ የሙሐደራ ፕሮግራም በራህማ መስጂድ

🌴 ረመዷን የድል ወር
💺 በሸይኽ አብዱሰላም አንዋር
____

🌴 ኢስላማዊ ቤተሰብ
💺 በኡስታዝ አብዱልካፊ ሙሐመድ

አድራሻ፦ ራህማ መስጂድ(አየር ጤና ቻይና ካምፕ ወደ ጀሞ3 በሚያቋርጠው መንገድ አዋሽ ዳቦ ጋ!)


🔻ልዩ የሙሐደራ መድረክ

✂️ሊያመልጦ የማይገባ ወሳኝ ፕሮግራም

ርዕስ፦ ይህች ናት ዱንያ‼️

📌በኡስታዝ ሙሐመድ አረቦ ሻፊ (ሐፊዘሁላህ)

📎የፊታችን እሁድ ሚያዝያ02-2014 አስር ሰላት እንደተጠናቀቀ

✂️አድራሻ፦ ሎሚ ሜዳ ኹበይብ መስጂድ

ለበለጠ መረጃ፦ 0932982730/ 0923623124


Shre shre shre
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እናንተ ሶላት ለማሰቆም ስትሞክሩ አቁመው የነበሩ ይጀምራል!!
ከቻላችህ ከትምህርት ቤት ፎርፈው ሺሻ ቤት እና መጠጥ ቤት የሚገባውን
ትውልድ አድኑት!!
# መስገድ#ወንጀል#አይደለም !!
በሰላት አንደራደርም! በአዲስ አበባ የሚገኙ ሙስሊም ተማሪዎች ድምፃቸውን
ማሰማት ጀምረዋል::
መብታቸንን በጨዋ ደንብ ጠይቀናል:: በስመ ሴኪዩላሪዝም በእስልምና ላይ
እየተቃጣ ያለውን ጥቃት እንቃወማለን ብለዋል:: በጉዳዩ ላይ ያለውን መረጃ
ወደናንተ እየተከታተልን የምናደርስ ይሆናል::
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠ/ም/ቤት
የሥራ አመራር ቦርድ
በወቅታዊ የሙስሊሙ ጉዳይ ላይ የተሰጠ የአቋም መግለጫ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው
ሀገራችን ኢትዮጵያ የለውጥ ሂደት ውስጥ ከገባችበት ያለፉት ጥቂት ዓመታት
ወዲህ ከስሞ የነበረው የኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ተማሪዎች “ሶላት አትስገዱ”
እና “ሂጃብ አውልቁ” መከራ ያገረሸ ይመስላል፡፡ አልፎ አልፎ ብቅ ሲል የነበረውና
አሁን ባልንበት ሳምንት ደግሞ በታቀደ እና ይፋዊ በሆነ መልኩ ተማሪዎቻችንን
የማንገላታት ኢ-ሕገ-መንግስታዊ ዘመቻ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን
ከትምህርት ገበታ የማራቅ ከጎደፈው ታሪካችን የቀጠለ ሴራ ነው፡፡ የደረሱን
ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት እና በመገናኛ ብዙኃን በሰፊው እየተሰራጭ
እንደሚገኘው ተማሪዎቻችንን ለህገ-ወጥ እንግልት የመዳረጉ ተግባር በተለይ
በአዲስ አበባና ዙሪያ ባሉ ትምህርት ቤቶች እንደተፈፀመ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የዘመናት የተቋም ባለቤትነት ጥያቄያቸው የተሳካ
ምላሽ እንዲያገኝ ህጋዊ መሰረት ያላቸው ልዩ ልዩ ተግባራትን እያከናወኑ ባሉበት
ተጨባጭ ሁኔታ እንዲሁም የተከበረው የረመዷን ወር ፆም እየተፆመ ባለበት
ጊዜ ተማሪዎቻችን በዘመቻ መልክ በሚፈፀም ኢህገ–መንግስታዊ ድርጊት
ለእንግልት መዳረጋቸው አስደንግጦናል፡፡ ዘመቻው የጀመርነውን የተቋም ግንባታ
ሂደት ትኩረት ለማስቀየር የተደረገ አንደኛው ሙከራ መሆኑን ለመረዳት ችለናል፡፡
መሰል የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ፈተናዎች በዘላቂነት ሊፈቱ የሚችሉት
ጠንካራ ተቋማት ሲኖሩን መሆኑን እናምናለን፡፡ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የመብት
ጥሰት ሲደረግብን ፈጥኖ በመድረስ ፈጣን ምላሽ በመስጠት ፊት አውራሪ
የነበሩት በዳዕዋ እንቅስቃሴ የሚታወቁ እና ከፍተኛ የህዝብ ውዴታ እና አክብሮት
ያተረፉ ኡስታዞቻችን ነበሩ፡፡ ይህም የሆነበት በስም ብቻ ከኢትዮጵያዊያን
ሙስሊሞች ጋር የሚታወቁት ግብራቸው ሙስሊሙን ተፃርሮ በመቆም
የምናውቃቸው “ተቋሞቻችን” ሚና ቢስ የነበሩ መሆናቸው አሁንም ከአእምሯችን
ያልጠፋ የኖርነው እውነታ ነው፡፡ በእርግጥ ሰፊው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም
በቁጭት የሚያውቅላቸው አንድ አሉታዊ ሚና ነበራቸው፡፡ ተማሪዎች ከትምህርት
ገበታቸው እንዲፈናቀሉ ለማድረግ በሚጎነጎኑ እና በሚፈፀሙ ሴራዎች መጅሊስ
“ለትምህርት እንጂ ለሶላት አልናክናቸውም” እና “ሂጃባቸውን ከትምህርት ቤት
ግቢ ሲወጡ መልበስ ይችላሉ” በማለት ሙስሊሞች አንገት እንድንደፋ እጅግ
አስፀያፊ ክፋት በወገናቸው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ላይ ሲሰሩ በከረሙት
አፍራሽ ሚናቸው ይታወሳሉ፡፡
ከዚህ በተቃራኒ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ተማሪዎች በህጃብ እና ስላት ሰበብ
ከትምህርት ገበታቸው በግፍ መታገዳቸው እንደተሰማ ፈጣን ምላሽ የተገኘው
እንደከዚህ ቀደሙ ከግለሰቦች ሳይሆን ወኪላቸው ከሆነው ተቋማቸው መሆኑን
አይተናል፡፡ በዚህ ረገድ የአዲስ አበባ መጅሊስ ሊመሰገን ይገባዋል፡፡ የመጅሊሱ
አመራሮች ችግር መፈጠሩ እንደተሰማ በፍጥነት ችግሩ በተከሰተበት የለሚ ኮራ
ጮራ ትምህርት ቤት ድረስ በመገኘት የጉዳዩ ተጠሪዎች መሆናቸውን
በሚያሳምን አግባብ ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ጋር ግንኙነት
በመፍጠር የተማሪዎቻችን ችግር የቅርብ ተጋሪ መሆናቸውን አስመስክረዋል፡፡
ይህ ተቋምን ያማከለ የችግር አፈታት አመርቂ ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል
ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ለተጀመረው የተቋም ግንባታ ሂደት እያሳዩት ያለውን
ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የተለመደውን ጥሪያችንን እያቀረብን
ተማሪዎቻችን የሃይማኖት እና መንግስት እንዲሁም የሃይማኖት እና የትምህርት
ሥርዓት መለያየት ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌን የማይጥሰው የሶላት እና የሂጃብ
አለባበስ ስርዓታቸውን እንደከዚህ ቀደሙ እንዲፈፅሙ የምንደግፋቸው መሆኑን
በይፋ እናሳውቃለን፡፡
የተማሪዎቻችን የሶላት እና የሂጃብ መልበስ ሃይማኖታዊ ተግባር የሃይማኖት እና
መንግስት መለያየት ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌን አይጥስም፡፡ መንግስት
በሃይማኖት ጉዳይ፤ ሃይማኖት በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገቡ
የሚደነግገው የሴኩላሪዝም መርህ ተማሪዎቻችን ሶላት ከመስገዳቸው እና
ሂጃብ ከመልበሳቸው ጋር የሚቃረንበት አንዳችም ሁኔታ የለም፡፡ እንስት
ተማሪዎቻችን እስላማዊ የአለባበስ ሥርዓታቸውን ጠብቀው ወደ ትምህርት
ገበታቸው መምጣታቸው እና ከትምህርት ሰዓት ውጭ ለጥቂት ደቂቃዎች ግዴታ
የሆነባቸውን ሶላት በአንድ የትምህርት ቤቱ ኮርነር መስገዳቸው ሕገ-መንግስቱ
ሃይማኖትን በነፃነት እንዲያምኑ እና የሌላውን መብት ሳይነኩ እንዲተገብሩ
ያጎናፀፋቸው መብት መሆኑ ሊታወስ ይገባዋል፡፡
የትምህርት እና ሃይማኖት መለያየት መገለጫው የሥርዓተ-ትምህርቱ ሴኩላር
መሆን እንጂ የተማሪው ሴኩላር መሆን አይደለም፡፡ ሶላት እና ሂጃብ በሙስሊሙ
ላይ ግዴታዎች ናቸው፡፡ ሶላት መስገድ እና ሂጃብ መልበስ የትምህርት ስርዓተን
የሚያውክም አይደለም የስርዓቱን ሴኩላርነት መጣስ መገለጫ አድርጎ መሳል
ፍፁም ስህተት ነው፡፡ በእርግጥም በሴኩላሪዝም ሽፋን ህገ መንግስቱ
ያጎናፀፈንን መሰረታዊ የሃይማኖት መብት በጉልበት እና ያለ ተጠያቂነት የመጣስ
ተግባር አድርገን ነው የምንረዳው፡፡ ይህ ድርጊት በተደጋጋሚ ላለፉት አሰርት
ዓመታት ኢትዮጵያዊያን ሙስሊም ተማሪዎችን ብቻ በነጠለ መልኩ መፈፀሙ
ይህንን አረዳዳችንን የበለጠ ያጠናክራል፡፡
የሀገራቸን ሕገ-መንግስት ዜጎችን እኩል እውቅና ይሰጣል፡፡ የዜጎች ያልተሸራረፈ
እኩል ተጠቃሚነት መረጋገጥ እንዳለበት ያውጃል፡፡ በሰንካላ የሴኩላሪዝም
ግንዛቤ ሽፋን ሙስሊም ተማሪዎች ትምህርታቸውን በተረጋጋ ሁኔታ
እንዳይከታተሉ በየጊዜው የሚፈጠሩ የጥቂት ኃላፊነት የጎደላቸው የትምህርት
አስተዳዳሪዎች ትንኮሳዎች ዳግም በማያንሰራረበት መልኩ ሊቀረፉ ይገባል፡
እነዚህ አካላት በእስላም ላይ ባላቸው የግል ጥላቻ የተነሳ ሴኩላሪዝምን እንደ
ሽፋን በመጠቀም በሙስሊሙ ላይ በፈፅሙት ግፍ በህግ ሊጠየቁ ይገባል።
ባጠቃላይ ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቆመው አሁን እየታየ ያለው
ተማሪዎችን የማዋከብ ተግባር ዋና አላማ ሙስሊሙን ከተቋማዊ ጥያቄ ትኩረት
አቅጣጫ በማስቀየር ሙስሊሙ ሁሌም ተረጋግቶ ከትናንሽ ዜግነታዊ መብት
ጥያቄ እንዳይወጣ የተሸረበ ተንኮል እንደሆነ እናምናለን። በመሆኑም እንደ ሁነኛ
መፍትሔ የኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ተቋማት ጅምር አበረታች የመፍትሄ
አማራጮችን የመደገፍ ሂደት ተጠናከሮ መቀጠል እንደሚገባው እናምናለን፡፡
ይህም እንዲሳካ የጀመርነው የተቋም ግንባታ እና ባለቤት የመሆን ያላሰለሰ
ሂደት ከህዝባችን በምናገኘው ድጋፍ ዳር የምናደርሰው ይሆናል፡፡
በሌላ በኩል ባለፉት አመታት በሙስሊሙ ወሳኝ ድርሻ ትግል የመጣውን
አገራዊ ለውጥ ተከትሎ አሁን ብቅ ብቅ ማለት የጀመሩትን ሙስሊሙን
በተለመደው ትንኮሳዎች መብቶቹን የመደፍጠጥ አፍራሽ ተግባር ለአንዴና
ለመጨረሻ ጊዜ እንዳከተመ ብዙዎቻችን የተሳሳተ ግምት ነበረን። ሆኖም
እንዳለመታደል አሁንም ሙስሊሙን እንደሁለተኛ ዜጋ አድርጎ የመቁጠር አባዜ
እንደቀጠለ መሆኑን ሰሞኑን ያየነው የመጅሊስ ጥያቄ እና የተማሪዎች ጉዳይ
በቂ ማሳያ መሆናቸውን መገንዘብ ይቻላል። የትምህርት ስርዓታችን
ተማሪዎቻችንን ከሃይማኖት የማራቅም ሆነ የመነጠል ተልዕኮ ሊኖረው
አይገባም፡፡
ስለሆነም መንግስት ለሙስሊሙ ጥያቄ በአፋጣኝ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ፣
በሂጃብ እና ሶላት ምክንያት የሚደርሰውን ትንኮሳ በአስቸኳይ እንዲያስቆምልን፣
በተማሪዎቻችን ላይ በደረሰው መጉላላት የተሳተፉት አካላት በሙሉ በህግ ፊት
ተጠያቂ እንዲሆኑ አጥብቀን እንጠይቃለን።
የተቋማዊ ጥያቄያችን በተሟላ መልኩ ምላሽ አግኝቶ የዜግነት መብቶቸችን
(በነፃነት መማርን ጨምሮ) በዘለቄታው እንዲከበሩ እስከመጨረሻው
እንታገላለን!
አላሁ አክበር!
ረመዷን 07/1443 ዓሂ
መጋቢት 30/2014 ዓል
ትዕዛዙ ከላይ በመዋቅር ተናበው ነው። ምሳ ሰዓት ላይ ወጥተው መስገድ እንዳይችሉ ነው ይህ አዋጅ የወረደው። ወጥቶ መስገድን ከከለከሉ እዛው ግቢ ውስጥ በጀማዓህ መስገድ ነው። አንድትም ሶላት ከወቅቷ ማለፍ የለባትም። እንዳውም እዛው ውስጥ ላይ ያመቻቹላችሁ።