La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
Forwarded from Deleted Account
(( #ግጥም ))

((በሐጂ ሙሐመድ ወሌ (ረሒመሁላህ))

ዛሬማ ምን አለ ቢሰግዱ ቢፆሙ፣
ይቸግራል እንጂ አላህ ፊት ሲቆሙ።
ዛሬማ ምን አለ ቢጠጡ ቢሰክሩ፣
ይቸግራል እንጂ ሙተው ሲቀበሩ።
ዛሬማ ማን አለ የሚያጋልጥህ፣
ከቀብር ስትገባ ይታያል ጉድህ።
ዛሬማ ማን አለ የሚጋልጥሽ፣
ከቀብር ስትገቢ ይታያል ጉድሽ።

[[ ሐጂ ሙሐመድ ወሌ (ረሒመሁላህ) }}
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በለሚ ኩራ እድገት ጮራ ትምህርት ቤት "ሶላት ለምን ሰገዳችሁ ?" በሚል
የታሰሩ ተማሪዎችን "ይፈቱልን "ብለው በጠየቁ ወላጆች ላይ የተኩስ ሩምታ
መከፈቱን እና ወላጆችም ላይ ድብደባ መድረሱ ታወቀ

በለሚ ኩራ እድገት ጮራ ትምህርት ቤት ሶላት ለምን ሰገዳችሁ ተብለው ያለ
አግባብ የታሰሩባቸውን ልጆቻቸውን ፍቱልን ብለው የሄዱ ወላጆች ላይ ከፖሊስ
የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸዋል። በርካታ ወላጆች ተደብድበው መታሰራቸው
ታውቋል
ተማሪዎቹ ከግቢያቸው ውጭም ሆነ በትምህርት ቤት ግቢ እንዳይሰግዱ
ተደርገዋል::
https://t.me/islam_in_school
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በለሚ ኩራ እድገት ጮራ ትምህርት ቤት "ሶላት ለምን ሰገዳችሁ ?" በሚል
የታሰሩ ተማሪዎችን "ይፈቱልን "ብለው በጠየቁ ወላጆች ላይ የተኩስ ሩምታ
መከፈቱን እና ወላጆችም ላይ ድብደባ መድረሱ ታወቀ

በለሚ ኩራ እድገት ጮራ ትምህርት ቤት ሶላት ለምን ሰገዳችሁ ተብለው ያለ
አግባብ የታሰሩባቸውን ልጆቻቸውን ፍቱልን ብለው የሄዱ ወላጆች ላይ ከፖሊስ
የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸዋል። በርካታ ወላጆች ተደብድበው መታሰራቸው
ታውቋል
ተማሪዎቹ ከግቢያቸው ውጭም ሆነ በትምህርት ቤት ግቢ እንዳይሰግዱ
ተደርገዋል::
https://t.me/islam_in_school
https://t.me/islam_in_school
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መስገድ የሚያሳስርበት ጊዜ ላይ ደርሰናል ህፃናትን ለምን ሰገድክ ብሎ ማሰር
በታዳጊው ስነልቦና ላይ ሊፈጥር የሚችለው ጫና ከባድ ነው
-እድገት ጮራ ትምህርት ቤት
-ትምህርት ቢሮ
-ለሚኩራ ክፍለከተማ
ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድ ያዳርሱ
https://t.me/islam_in_school
https://t.me/islam_in_school
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
(3)ከረመዷን ጋር ተያያዥ የሆኑ ፈታዋ በዛዱል መዓድ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም@ዛዱል መዓድ
ሁለቱ ምስክርነቶች
ኢብኑ/ሙነወር
ሁለቱ ሸሃዳዎች
--
በወለቴ ሑነይን መስጂድ የቀረበ
Forwarded from Deleted Account
أَفَحَسِبْتُمْ أَنَّمَا خَلَقْنَاكُمْ عَبَثًا وَأَنَّكُمْ إِلَيْنَا لَا تُرْجَعُونَ

[ ሱረቱ አል-ሙእሚኑን - 115 ]
«የፈጠርናችሁ ለከንቱ መኾኑን እናንተም ወደኛ የማትመለሱ መኾናችሁን ጠረጠራችሁን» (ለከንቱ የፈጠርናችሁ መሰላችሁን)
Forwarded from Deleted Account
#ታጥቦ ጭቃ አንሁን*
*أعمال تفسد ثواب الصوم*
አንድ ፆመኛ ሰው በመፆሙ ምክንያት ወንጀሉ ይሰረዝለታል ዳሩ ግን ከእነዚህ ወንጀሎች ካልተጠነቀቀ ታጥቦ ጭቃ ነው ሚሆነው :—
— መዋሸት በቃላትም ሆነ በተግባር
— ክህደት በቃልም ሆነ በተግባር
— ቀጠሮን አለማክበር
— ሀሜት ሰው ሲታማ ጆሮ ሰጥቶ ማድመጥ
— ነገር ማዋሰድ (ሰዎችን ማጣላት)
— ማታለል ፣ማጭበርበር
— ሙዚቃ ማድመጥ ፣ መልእክቱ ምንም ያህል ሸጋ ቢሆንም በሙዚቃ መሣሪያ ከታጀበ የሸይጣን ድምጽ ነው ተጠንቀቀው
— የተቃራኒ ፆታን ስሜት የሚቀሰቅሱ ነገራትን መተግበር
— በሰው ማፌዝ፣ ማላገጥ፣ መጠቃቀስ
— መሳደብ ፣ ማንጓጠጥ
— መራገም ፣ ሰውንም ሆነ እንስሳን ወይም ንብረትን ከመራገም ተቆጠብ
— ከሰው ጋር መጋጨት ፣ መጣላት
— የሰውን ክብርና ንብረት መንካት

*በሆዳችን ብቻ ሳይሆን በመላው አካላችን የምንጾም አላህ ያድርገን !
Forwarded from Deleted Account
🛑 ተራዊህ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች

📌 ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን

📌 ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን

📌 ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን

📌 ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን

📌 ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን

📌 ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን

📌 በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "አሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል

📌 መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል

📌 ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል

📌 የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን

📌 ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል

📌 ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን

📌 ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን

📌 ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን

📌 በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "አሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን

📌 ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን

📌 የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም

📌 ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታና ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊህን ሳንሰለች እንስገድ።

አላህ ያግራልን
#ሱብሀነክ
#ጥበቃህ_አልተለየኝም__!!
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
መጥፎነቴ ገዝፎብኝ፤
በሰወች የሀሳብ ሚዛን፡
ክፋቴ ከመጠን አልፎ፤
ተሰምቶ በአለም እንደ አዛን፡
ሁሉም በአይን ጫፍ አይቶኝ፤
በመኖሬ አጥቼ ለዛን፡
መላ ቅጡ ጠፍቶብኝ፤
የመፈጠር ጣዕሙ፡
ድንግርግር ምርር ብሎኝ፤
ጠፍቶኝ የመኖር ትርጉሙ፡
ችግር መከራ ወሮኝ፤
ጉስቁልናውም ህመሙ፡
የሀሳብ ረጂም መንገድ፤
ውጣ ውረዱ ድካሙ፡
ምን እንደሆነ ሳላውቀው፤
ማጣፈጫ ቅመሙ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
እጂግ ብዙ ዳከርኩኝ በጣም በብዙ አመፅኩኝ፡
በስሜት ባለማወቅ ብዙ ወንጀልን ፈፀምኩኝ፡
የመፈጠሬን አላማ እኔ ብዘነጋውም፡
የአምላክነትህን እዝነት በፍፁም አላጣሁም፡
በሽተኛ ነው ብሎ የሰው ዘር ቢፀየፈኝም፡
መጥፎ መገለጫወችን ቀምሞ ቢጭንብኝም፡
ያለስሜ ስም ሰጥቶ በግፍ ቢያንቋሽሸኝም፡
በሌለሁበት ዋሽቶ እጂግ ብዙ ቢለኝም፡
እኔ እየወነጀልኩህ፤
አንተ መች አዋረድከኝ፡
ሰወች ጠላት ሲሆኑኝ፤
አምላኬ አንተ መች ተውከኝ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
በተደጋጋሚ ደፍሬህ፤
ከእዝነትህ መች አራቅከኝ፡
አምፀኸኛልና እኔ አላውቅህም መች አልከኝ፡
ተመለስ እና ወደኔ፤
ተውበት አድርግ እንጂ ያልከኝ፡
የበደልኩህን ቆጥረህ፤
እስረኛ መች አደረከኝ፡
መመሪያህን እየጣስኩ
እያመፅኩህ መች ተውከኝ፡
ባሪያዬ ብለህ በመጥራት
ይበልጥ ነው ያቀረብከኝ፡
እኔን ፍራ ብለህ ገስፀህ፤
ብዙ ፀጋ ነው ያደልከኝ፡
እመነኝ ጀነት አለህ፤
ብለህ ነው የነገርከኝ፡
ጥራት ይገባህ ላንተ፤
እኔን ስላከበርከኝ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የቀረቡኝ ሲርቁ ያበላኋቸው ሲበሉኝ፡
ትላንት የረዳኋቸው ዛሬ ላይ ሲያታልሉኝ፡
መልካም ያደረኩላቸው በሌለ ስንት ሲሉኝ፡
ወዳጆች የነበሩ ሁሉ ተከርብተው ሲጠሉኝ፡
ከገደል ያወጣኋቸው፤
ወደ ገደል ሲገፉኝ፡
በእዝነት የዳበስኳቸው፤
እሾህ ጨብጠው ሲያቅፉኝ፡
አብሮ አደግ ጓደኞቼ፤
ኮርተው በንቀት ሲያልፉኝ፡
ሚስጥሬን የነገርኳቸው፤
እቀደዱ ሲሰፉኝ፡
ያመንኳቸው ሁሉ ጓደኞች፤
በቅፅበት ውሳኔ ሲያኮርፉኝ፡
እየተከረባበቱ በወጥመድ ሲማጎ ሲጠልፉኝ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
ወንድምም ሆነ ዘመድ ሞኝ ነህ ብሎ ቢለኝም፡
ጠላት በሩቅ እየሳቀ በበደል ቢወርፈኝም፡
ከፈጠርከኝ ጀምሮ፤
ባሳለፍኳቸው አመታት፡
ጥበቃህ አልተለየኝም፤
ለሰከንድ እንኳን ሰአታት፡
አንተን ማመኔ ብቻ፤
ለኔ ሆኖኛል ብርታት፡
የእውነትም አምላክ ነህና፤
የሚሆኑልህ ሰማዕታት፡
አንድ ብቸኛ ጌታ የአለማት ሁሉ ፈጣሪ፡
የፈለገውን አድራጊ የፈለገውን ሰሪ፡
የፈለገውን ቀጥቶ የፈለገውን መሀሪ፡
ሁሉንም ነገር አጥፍቶ ከኋላ ብቻውን ቀሪ፡
ሞተ የማይባል ጌታ የዘላለም ዘውታሪ፡
ድካም እንቅልፍ የማያውቅ ህያውና ታታሪ፡
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
የሰውነት ቅርፅ የሰጠኸኝን፤
የተዋበ አድርጎ መልኬን፡
ሙሉ አካልን ለግሶኝ፤
አንድም ሳይቀንስ ልኬን፡
በብርሀን የቀየረልኝን፤
ያንን ጨለማ ታሪኬን፡
ከአርሹ በላይ ያለውን፤
መገዛት አልተውም አምላኬን፡
ያለማንነቴ እየዘለፈ ማንም ምንም ቢያወራ፡
ብቻየን እንኳን ብቀር በምድረ-በዳ ጠራራ፡
ቃል እገባለሁ ወላሒ እኔ አንተን ብቻ ልጣራ፡
አንድነትህን እያዜምኩ በማንም ላላጋራ፡
ፈፅሞ እኔ ላልተወው የፈጠርክብኝን አላማ፡
ማንም ቢለፈልፍብኝ ማንም ድምፅ ቢያሰማ፡
ከናፍሮቼ ቢዘጉ እጀ ቢታሰር በካስማ፡
ቃል ገብቻለሁ በአንተ ፊት፤
ካንተ ውጭ ሌላ ላልሰማ፡
በመጨረሻው ነብይ፤
በሙሀመድ አበል ፋጢማ፡
በዚያ በጣፋጭ ቅመም፤
በላከው ለአለም ረህማ፡
በመካው የቀትር ፀሀይ፤
በመድና ላይ ጨረቃ፡
መልካምነቱ በአላም፤
ተጉዞ በማያበቃ፡
በተነገረ ቁጥር፤
ፍቅሩ የሚያሲዝ ሲቃ፡
በርሱ መንገድ ከመጓዝ፤
በፅሞ እኔ አልቦዝንም፡
አንተን አንድ አምላክ አምኘ፤
በፍፁም እኔማ አላዝንም፡
ስህተቴን እያስተካከልኩ፤
እስክሞት አመልክሀለሁ፡
አንተን በማምለኬ ላይ፤
ፅናትን እማፀናለሁ፡
አምላኬ በመሆንህ፤
ከልቤ ደስተኛ ነኝ፡
ግና በወንጀል ተለውሻለሁ
በዕዝነትህ ከዕሳት አድነኝ፡
የጀነት ነህ ብለህ አስደሳኝ፤
በስራዬ ሳይሆን በዕዝነትህ፡
ከዱንያ መከራም አውጣኝ፤
ጠብቀኝ በበረከትህ፡
እወድሀለሁ አምላኬ
የምገልፅበት ቃል የለኝም፡
በባርነቴ አምኛለሁ፤
ለማንም ግድ አይሰጠኝም፡
የሰወች ወቀሳ ትችን፤
ምንም አይሰማኝም፡
አንተን ባላወቅኩበት ዘመን፤
ብዙ ጥፋቶችን ብመኝም፡
በመሀይምነት ታውሬ፤
ግዙፍ ስህተት ብቀኝም፡
ወንጀለኛ ሆኘ እንኳን፤
ጥበቃህ አልተለየኝም፡
#አምላኬ______እወድለሁ
〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️〰️
✍️በኑረዲን
Audio
۞ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡

وَأَوْفُوا بِعَهْدِ اللَّهِ إِذَا عَاهَدتُّمْ وَلَا تَنقُضُوا الْأَيْمَانَ بَعْدَ تَوْكِيدِهَا وَقَدْ جَعَلْتُمُ اللَّهَ عَلَيْكُمْ كَفِيلًا ۚ إِنَّ اللَّهَ يَعْلَمُ مَا تَفْعَلُونَ

ቃል ኪዳንም በገባችሁ ጊዜ በአላህ ቃል ኪዳን ሙሉ፡፡ መሓሎቻችሁንም ከአጠነከራችኋት በኋላ አላህን በእናንተ ላይ በእርግጥ መስካሪ ያደረጋችሁ ስትኾኑ አታፍርሱ፡፡ አላህ የምትሠሩትን ሁሉ ያውቃልና፡፡🤍
#أذكار_المساء
أَعُوذُ بِاللَّهِ مِنَ الشَّيطَانِ الرَّجِيمِ
﴿اللَّهُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ هُوَ الْحَيُّ الْقَيُّومُ لاَ تَأْخُذُهُ سِنَةٌ وَلاَ نَوْمٌ لَّهُ مَا فِي السَّمَوَاتِ وَمَا فِي الأَرْضِ مَن ذَا الَّذِي يَشْفَعُ عِنْدَهُ إِلاَّ بِإِذْنِهِ يَعْلَمُ مَا بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَمَا خَلْفَهُمْ وَلاَ يُحِيطُونَ بِشَيْءٍ مِّنْ عِلْمِهِ إِلاَّ بِمَا شَاء وَسِعَ كُرْسِيُّهُ السَّمَوَاتِ وَالْأَرْضَ وَلاَ يَؤُودُهُ حِفْظُهُمَا وَهُوَ الْعَلِيُّ الْعَظِيمُ﴾.
🍃🌻
ረመዷን
(5)
**
ሰዎች ድምፃችንን ይሰማሉ፣ አንተ ግን ዉስጣችንን ትሰማለህ።
የልባችንን ለቅሶ የምትሰማ፣ የዉስጣችን መሻት የምታውቅ አምላካችን ሆይ! በፆመ አንጀታችን ለመንንህ፣ በደረቅ ጎሮሮኣችን ተማፀንንህ። መሻታችንን ሁሉ ሙላልን፣ ሓጃችንን ሁሉ ፈጽምልን፣ የምንፈልገዉን ሁሉ ስጠን።
ያ ረብ!
ረመዷን
(5)
***
እንግዳ የሚበዛበት ቤት አላህ የሚወደው ቤት ነው ይላሉ።
ለትንሽ ትልቁ ልድሃ ሀብታም ሚከፈትን ቤት የሰዉም ሆነ የመላእክት ዱዓ አይለየዉም። የአላህ ችሮታም አይጎድልበትም።
እንግዳ እቤት ሲገባ በረከትና የአላህ እዝነት አብሮት ይገባል።
እንግዳው ብዙ ችሮታዎችን ይዞ ይመጣል፣ ወንጀልም አጥቦ ይሄዳል።
"በአላህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳዉን ያክብር።" ብለዋል የአላህ መልዕክተኛ ሶ.ዐ.ወ።

ፆመኛን ያስፈጠረ የሱን ያህል እኩል ምንዳ ያገኛል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
(4)ከረመዷን ጋር ተያያዥ የሆኑ ፈታዋ በዛዱል መዓድ በኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም @እድል መዓድ
ረመዷን
(5)
****
አንድ አባት ስልክ ጠጋኝ ዘንድ ሄዱና "ስልኬ ተበላሽቷል ሥራልኝ።" አሉት።
ጠጋኙም "አረ ይሠራል ችግር የለበትም።" አላቸው።
"ታድያ ልጆቼ ለምን አይደዉሉልኝም?" ።
ብለው ጠየቁት።
ስልካቸው መሥራት አለመሥራቱን የሚያውቁት ልጆቻቸው ቶሎ ቶሎ ሲደዉሉላቸው ነው። ሲቆዩ ጊዜ የተበላሸ መሠላቸው።
እንዲህ እንዳይጠራጠሩ ለወላጆቻችሁ ሳትሰለቹ ደዉሉላቸው።
ረመዷን በልጅ ወላጅ ትዝታ ዉስጥ ትልቅ ቦታ አለው። ቤተሰብ ቢኖረዉም ዛሬም ድረስ እናቱ ደዉላ የምትቀሰቅሰው በድምጿ የሚነቃ ሰው አውቃለሁ።
አላህ ሆይ በልጅነታችን ወላጆቻችን በመልካም ሁኔታ አሳድገዉናል፣ እዝነትህ አይለያቸው።
ጾም ነፍስን ለመቆጣጠርና አቅጣጫ ለማሳየት ግዙፉ መንገድ ነው። ነፍስ ወደ አላህ የሚደረገው ጉዞ ላይ መሰናክል የምትሆነው ክፉ ስትሆን ነው። በባሕሪዋ ደግሞ ደስ የሚላትን ማድረግና ግዴታ ከተደረጉባት ተግባራት መሸሽ ትመርጣለች። ይህን ባሕሪዋን ለማረም ደግሞ ጾም ምርጡ አምልኮ ነው። በዚህ መንገድ መጠቀም የፈለግን እንደሆነ በጾሙ ክፍለ ጊዜ አብዛኛውን በእንቅልፍ ልናሳልፈው አይገባም። ስናፈጥርም የምንወስዳቸውን ምግቦችና መጠጦች ማመጣጠን ይኖርብናል። የምግብ ዓይነታዎችንም ማብዛት ተገቢ አይደለም። አንድ ወይም ሁለት ዓይነት በቂያችን ነው።
አል-ሐሊሚይ እንዲህ ይላሉ፦ ‹‹ሐላል ስለሆነ ብቻ ለአንድ ሰው አብዝቶ መመገቡ ትክክል አይደለም። ምግብ በብዛቱ ሰውነቱን ይከብደዋል፤ ወደ እንቅልፍ ይገፋዋል፤ አምልኮ ይከለክለዋል። ስለዚህ ረሐቡን በሚያስረሳ ሁኔታ ይመገብ። የሚመገብበትን ዓላማም በአምልኮ ለመበርታትና ለመጠናከር ይሁን።›› ሹዐብ አል-ኢማን አልበይሀቂ 5/22

ከምግብና ከመጠጥ ከመጾም በተጨማሪ ከማይጠቅሙ ንግግሮች እንዲሁም ከሳቅም ጭምር መጾም ይገባናል። ‹‹ምላስህን ያዝ!›› መፈክራች ሆኖ ከአላስፈላጊና ካልተፈቀዱልን ነገሮች ሁሉ መራቅ ይገባናል።

ጥቂት የረመዷን ቀናት
ረመዷን
(6)
የማያውቁ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ ንገሯቸው፡፡ ሶላት በአንድ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ የትም በምንም ሁኔታ ዉስጥም ቢሆን መስገድ ይኖርበታል፡፡ ያለ ሶላት ፆምም ትርጉም የለዉም፡፡

ሶላት - ለመልካም ሥነምግባር
ሶላት - ዓላማ ላለው ትውልድ
ሶላት - መልካም ዜጋ ለማፍራት
ያለ ሶላት ሕይወት የለንም፡፡
ልጆቻችንን ሶላት አትከልክሉ፡፡
አምና፣ ካቻ-አምና የሰሑርና የፊጥር ማዕድ ላይ የነበሩ፣ ዘንድሮ ግን የሌሉ ወዳጆችና የቤተሰብ አባላት ይኖራሉ። የዘንድሮውንም ጀምረው ሳይጨርሱ ወደ ማይቀረው አገር የሄዱ አይጠፉም። እኛ ያገኘነውን ዕድል አላገኙምና ዱዓ እናድርግላቸው፣ ኢስቲጝፋር እንስደድላቸው፣ ሶደቃ እናውጣላቸው... በኸይራት እናስባቸው።