La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
አፍጡር ላይ የሚባል

ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ الْعُرُوْقُ وَثَبَتَ اْلأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ.

‘ዘሐበዝዘመኡ ውበተልለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል አጅሩ ኢንሻአህ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِيْ
, አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሐለሁ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
ኢብኑል ቀይም - ረሂመሁላሁ ተአላ እንዲህ ይላል :-

"ፆመኛ ማለት አካላቱ ከወንጀል
ምላሱ ከውሸትና ከመጥፎ ንግግር ከውሽት ምስክርነት
ሆዱ ከምግብና ከመጠጥ
ብልቱ ከዝሙት የፆመ ነው
ከተናገረ ፆሙን የሚጠፋ ንግግር አይናገርም ከሰራም ፆሙን የሚያበላሽ ነገር አይሰራም "

📚አል ዋቢሉ ሰይብ ገፅ ( 43 )
https://t.me/httpsLatahzen
Channel photo removed
ما حكم متابعة الإمام في التراويح بالمصحف ؟ لفضيلة الشيخ الدكتور…
◉ቁርአን ይዞ ኢማምን መከታተል
------------------------------------------
➜ኢማሙን በተራዊህ ሰላት ሲያሰግድ በቁርአን መከታተል ፍርዱ ምንድን ነው ?

◎ما حكم متابعة الامام في التراويح في المصحف?

◁◦ لا يجوز. ابداً عليك ان تنصت. لا تتابعه ابداً.
إنما عليك أن تنصت للقراءة ولا تقرأ معه.

لا تتابع معه في المصحف ولا تقرأ معه اثناء قراءته. كل ذلك مخالفٌ بل يعني يخشى ان لا تصح صلاتك.

لانه يجب عليك الانصات وجوباً. يجب عليك ومتابعة الامام بالانصات◦
▬▭▬▭▬▭▬▭▬▭▬▬


🎙فضيلة الشيخ د.صالح السحيمي
📨 ፆመኛው ማን ነው ?


📌 ﻗـﺎﻝ ﺍﺑﻦ ﺍﻟﻘﻴِّﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍﻟﻠﻪ :

« ﻭﺍﻟﺼَّﺎﺋﻢ ﻫﻮ ﺍﻟَّﺬﻱ ﺻﺎﻣﺖ ﺟﻮﺍﺭﺣﻪ ﻋﻦ ﺍﻵﺛﺎﻡ, ﻭﻟﺴﺎﻧﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﻜﺬﺏ ﻭﺍﻟﻔﺤﺶ ﻭﻗﻮﻝ ﺍﻟﺰُّﻭﺭ, ﻭﺑﻄﻨﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ﻭﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ, ﻭﻓﺮﺟﻪ ﻋﻦ ﺍﻟﺮَّﻓَﺚ ؛

«ፆመኛ ማለት አካሎቹን ከሀጢአት የጸዱ፤ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤ ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።

ﻓﺈﻥْ ﺗﻜﻠَّﻢ ﻟﻢ ﻳﺘﻜﻠَّﻢ ﺑﻤﺎ ﻳﺠﺮﺡ ﺻﻮﻣﻪ, ﻭﺇﻥ ﻓﻌﻞ ﻟﻢ ﻳﻔﻌﻞ ﻣﺎ ﻳﻔﺴﺪﺻﻮﻣﻪ,

ፆመኛ ከተናገረ:– ፆሙን በማይጎዳ ስራ ከሰራ ጾሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል።

ﻓﻴﺨﺮﺝ ﻛﻼﻣﻪ ﻛﻠُّﻪ ﻧﺎﻓﻌًﺎ ﺻﺎﻟﺤًﺎ, ﻭﻛﺬﻟﻚ ﺃﻋﻤﺎﻟﻪ, ﻓﻬﻲ ﺑﻤﻨﺰﻟﺔ ﺍﻟﺮَّﺍﺋﺤﺔ ﺍﻟَّﺘﻲ ﻳﺸﻤُّﻬﺎ ﻣﻦ ﺟﺎﻟﺲ ﺣﺎﻣﻞ ﺍﻟﻤﺴﻚ،

ፆመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው።

ﻛﺬﻟﻚ ﻣﻦ ﺟﺎﻟﺲ ﺍﻟﺼَّﺎﺋﻢ ﺍﻧﺘﻔﻊ ﺑﻤﺠﺎﻟﺴﺘﻪ, ﻭﺃَﻣِﻦ ﻓﻴﻬﺎ ﻣﻦ ﺍﻟﺰُّﻭﺭ ﻭﺍﻟﻜﺬﺏ ﻭﺍﻟﻔﺠﻮﺭ ﻭﺍﻟﻈُّﻠﻢ,

ከፆመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመትን እና በደልን ሁሉ ሰላም ይሆናል።

ﻫﺬﺍ ﻫﻮ ﺍﻟﺼَّﻮﻡ ﺍﻟﻤﺸﺮﻭﻉ ﻻ ﻣﺠﺮَّﺩ ﺍﻹﻣﺴﺎﻙ ﻋﻦ ﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ﻭﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ ... ؛

ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ፆም ማለት ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ፆም አይባልም።

ﻓﺎﻟﺼَّﻮﻡ ﻫﻮ ﺻﻮﻡ ﺍﻟﺠﻮﺍﺭﺡ ﻋﻦ ﺍﻵﺛﺎﻡ, ﻭﺻﻮﻡ ﺍﻟﺒﻄﻦ ﻋﻦ ﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏﻭﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ؛

ፆም ማለት አካላትን ከሀጢአት እና ሆድን ከምግብና መጠጥ በመታቀብ መፆም ነወ።

ﻓﻜﻤﺎ ﺃﻥَّ ﺍﻟﻄَّﻌﺎﻡ ﻭﺍﻟﺸَّﺮﺍﺏ ﻳﻘﻄﻌﻪ ﻭﻳﻔﺴﺪﻩ, ﻓﻬﻜﺬﺍ ﺍﻵﺛﺎﻡ ﺗﻘﻄﻊ ﺛﻮﺍﺑَﻪ, ﻭﺗﻔﺴﺪُ ﺛﻤﺮﺗَﻪ, ﻓﺘُﺼَﻴِّﺮﻩ ﺑﻤﻨﺰﻟﺔ ﻣﻦ ﻟﻢ ﻳﺼُﻢ ».

ምግብና መጠጥ ፆምን እንደሚያጠፋ ሁሉ ሀጢአትም የፆምን ምንዳ ያጠፋል፣ ውጤቱን ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ፆም እንዳልጾመ ተደርጎ ይታሰባል።

📜 [ ﺍﻟﻮﺍﺑﻞ ﺍﻟﺼَّﻴِّﺐ ص(31 ، 32 ) ]



┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄
ሼር 👇JoiN👇 & Share
https://t.me/httpsLatahzen
ما تيسر من سورة المائدة _ تــلاوة بديعة _ القارئ عبدالله بصفر
مجموعات تلاوات خاشعة
ቁርአን የአላህ ስጦታ‼️

ቁርአንን በማስተንተን ከማንበብ የበለጠ ለቀልብ የሚጠቅም ነገር የለም!

♦️ቆንጆ የምሽት ግብዣ
01 የረመዷን ምክር በሸይኽ ሐሰን ገላው (1443)
የረመዷን ምክር 01

በሸይኽ ሐሰን ገላው ሃፊዞሁሏህ
02 የረመዷን ምክር, በወንድም ሰዓድ ዓብዱል’ለጢፍ ሃፊዞሁሏህ (1443)
የረመዷን ምክር 02

በወንድም ሰዓድ ዓብዱል`ለጢፍ ሃፊዞሁሏህ
ፆመኛ ሊጠነቀቃቸው የሚገቡ ከፊል ነገሮች

① ሀሜት፣ውሸት ፣ነገረኝነት እና ማንኛውንም አሉባልታ ወሬዎች
ፆመኛ የሆነ ሰው እነዚህን ሊጠነቀቅ ይገባዋል እነዚህን ነገሮች ካልተጠነቀቀ እየተራበ እና እየተጠማ ያለው በከንቱ ነው ማለት ነው ።
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ በለዋል
"የውሸት ንግግርን እና በእሱ መስራትን ያልተወ ሰው ምግብ እና ፆም በመተዎ ለአላህ ጉዳይ የለውም" [ቡኻሪ 6057]

② ውዱ በሚያደርግ ግዜ በአፍንጫው ውሃ ሲያስገባ(እስቲንሻቅ ሲያደርግ) በደንብ አለመሳብ
የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም "ፀመኛ የሆንክ ግዜ ሲቀር በአፍንጫህ በደንብ ውሀን ሳብ" ብለዋል [ሱነን አቢ ዳውድ 2366]
ከዚህ ሐዲሥ እንደምንረዳው ውሃን የውዱ ግዜ በአፍንጫ በደንብ ወደ ውስጥ በመሳብ ማስገባት ሱና ነው ግን የፆም ግዜ ክልክል ነው ምክያቱም በደንብ ውሃውን ከሳብን ወደ ጉሮሯችን መግባቱ ስለማይቀር ነው በፆም ግዜ የተከለከለው።

③ አብዛሀኛውን ወይን ብዙውን የቀን ክፍል መተኛት ለፆመኛ ጥሩ አይደለም ምክኒያቱም ውድ የሆነውን ግዜ ያለምንም ኢባዳ እንዲያልፍ ያደርግበታል (እንቅልፍም ኢባዳ አይደል ላላችሁኝ አዎ ግን መባል የያዘው ሁሉም በልክ ይሁን ነው)
ታላቁ ዐሊም ኢብኑ ዑሠይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
"ለፆመኛ በሶላት፣አላህን በማውሳት(በዚክር)፣በዱአና ቁራኣን በመቅራት (ግዜውን ሊያሳልፍ) ይገባዋል። ሰው በፆመ ግዜ ነፍሱን በተለያየ ኢባዳ ካላመዳት ይህ ለሱ ይገራለትል። (ግን በተቃራኒው ነፍሱን)
በስንፍና እና ረፍት(እንቅልፍ) በማብዛት
ከሆነስ ያላመዳት እሄንኑ ስንፍናውን እንጅ ሌላን አይለምድም (ሁኔታው እንዲህ ከሆነች) የፆመ ግዜ በእርሱ ላይ መልካም ስራ እና ዒባዳዎች ይከብዱበታል" [መጅሙኡል ፈታዋ ወረሳኢል 19/171]

④ በራሱ ላይ ስሜቱን የማይተማመን ሰው ሚስቱን መሳም ይህም በፆም ሰአት ሊጠነቀቁት የሚገባ አደጋ ነው።
ኢብኑ አብዲል በር (ረሂመሁላህ)
"ሚስቱን ከመሳም የተነሳ ፆም የሚያበላሽ ነገር የሚመጣበት ለሆነ ሰው መሳምን(ይፈቀዳል) ያለ (ዐሊም) አንድንም አላውቅ" ይላሉ [አት-ተምሂድ 5/114]
ስለዚህ በራሱ ላይ ስሜቱን የማይተማመን ሰው ከንደዚህ አይነት ድርጊት እራሱን ሊቆጥብ ይገባዋል
አላህ ፆማቸውን ከተቀበላቸው ያድርገን

⑤ ፉጡርን ማዘግየት ብዙ ሰዎች ፀሀይ ተገባ በሗላ ፉጡርን የሚያዘገዩ አሉ አንዳዶች አዛንኳ እየተደረገ ከሶላት በሗላ ካልሆነ እንጅ የማያፈጥሩ አሉ ይህ ስህተት ነው። ፀሃይ መግባቱ ከተረጋገጠ ፉጥርን ማቻኮል ሱና ነው። ነቢዩ(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ "ሰዎች ፉጡርን እስካቻኮሉ ድረስ ከመልካም ነገር አይወገዱም" 【ቡኻሪና ሙስሊም】
🍂 ጃቢር ቢን አብደላህ እንዳስተላለፈው ረሱላችን ﷺ ጂብሪል ዓለይሂ ሰላም መጣኝና እንዲህ አለኝ ይሉናል: -

👉የፈለግከውን ያህል እድሜ ኑር ሟች ነክ፤የፈለግከውን ውደድ ትለየዋለህ፤የፈለግከውን ስራ ስራ ትመነዳበታለህ።
▪️እወቅ!! የአማኝ ልቅናው የሌሊት ሰላት መስገዱ ነው።የአማኝ ክብሩ ደግሞ ከሰዎች መብቃቃቱ ነው።

📚(ሶሂሁል ጃምዕ 73)
የወረቀት ብር ኖት ዘካ
~~~
በጥንት መን ሰዎች ግብይት የሚፈፅሙት እቃን በእቃ በመለዋወጥ ነበር። የልውውጥ ገበያ ለአጠቃቀም አስቸጋሪ በመሆኑ የተነሳ ቀስ በቀስ እየቀዘቀዘ ሄዶ አንዳንድ እቃዎችን (ለምሳሌ በሃገራችን አሞሌ ጨው) እንደመገበያያ ገንዘብ በመጠቃቀም ተተካ። ይሁን እንጂ እነዚህ እቃዎች ለአያያዝ አስቸጋሪ በመሆናቸው የተነሳ ሰዎች ወደ ሌሎች አማራጮች ማማተር ይጀምራሉ። በዚህም የተነሳ ነበር ወርቅና ብር ለመገበያያነት መዋል የጀመሩት። ወርቅና ብር ታዲያ በጊዜ ሂደት በአንጣሪዎች አማካኝነት ተመሳሳይ መጠንና ክብደት እንዲይዙ ተደርገው ለአስተማማኝነታቸው ማህተም ዲዛይን ተደርጎባቸው መዘጋጀት ያዙ። እነዚህን ገንዘቦች ለደህንነታቸው በመስጋት ገንዘብ መንዛሪዎችና አንጥረኞች ዘንድ በማስቀመጥ መተማመኛ ደረሰኞችን በምትካቸው ይቀበሉ ነበር። ሰዎች በነዚህ ድርጅቶች ላይ ያላቸው እምነት በጨመረ ቁጥር ደርሰኞቹ በግብይት ላይ ለክፍያ መዋል ያዙ።
የወረቀት ብር ኖት ታሪካዊ አነሳሱ በዚህ መልኩ ነበር። በጊዜው እነዚህ ከገንዘብ መንዛሪ ድርጅቶች የሚመጡ ወረቀቶች ሰውየው በነዚህ የግል ድርጅቶች ዘንድ ወርቅ/ ብር እንዳስቀመጠ በመግለፅ ወረቀቱን የተቀበለ ሰው ሄዶ ወርቁን/ ብሩን መውሰድ እንደሚችል ከመጠቆም ባለፈ ኦፊሴላዊ ይዘትም ሆነ የህግ ከለላ አልነበራቸውም። አገልግሎታቸው በሰፋ ቁጥር ግን በጊዜ ሂደት መንግስታት የህግ ሽፋን ሊሰጡ ግድ ብሏቸዋል። በዚህን ጊዜ የታወቀ ተመን በመስጠት ላምጪው እንዲከፈል አስገዳጅ ህግ ወጣ። የማተሙ/ የማሳተሙ ኃላፊነትም የመንግስታት ሆነ። ይህ ነገር የተጀመረው በ1833 እንደሆነ ድርሳናት ይጠቁማሉ። (ዘመኑ በሙሉ እንደ ጎርጎሮሳውያን አቆጣጠር ነው።)
መንግስታት ካላቸው ተቀማጭ የወርቅ መጠን በላይ እነዚህን የወረቀት መገበያያዎች ገበያ ላይ ሲያቀርቡ ጊዜ ግን በነባሩ የወርቅ መገበያያ ላይ ፈተና ተደቀነ። በዚህን ጊዜ የወረቀት መገበያያዎችን ወደ ወርቅ ከመቀየር የሚከለክል ህግ መውጣት ያዘ። በዚህ ረገድ ቀዳሚዋ ብሪታኒያ ስትሆን ይህ የሆነውም በ1931 ነበር። አሜሪካ በ1934 ተከተለቻት። የክልከላው ተግባራዊነት ግን ድንበር ተሻጋሪ ሳይሆን በሃገራቱ ውስጥ የተገደበ ነበር። ሃገራት ከሃገራት ጋር ሲገበያዩ ግን የወረቀት ብሩን ወደ ወርቅ የመቀየር ውላቸውን ይጠብቁ ነበር። ከ1971 ጀምሮ ግን የወርቅ መጠን እያነሰ ስለመጣ አሜሪካ ይህንኛውን አሰራር ጭምር አቆመች። የመጨረሻው ወርቅን ለግብይት ተመን የመጠቀም አሰራር በዚህ መልኩ ተዘጋ።
የወረቀት ብር ኖት እነዚህን ታሪካዊ ለውጦች በማሳለፉ የተነሳ ምንነቱን በመግለፅ ላይ የኢስላም ምሁራን እይታቸው ሊለያይ ችሏል። የብዙሃን ዑለማዎችን አቋም ብቻ ሳሰፍር የወረቀት ብር ማለት እራሱን የቻለ የተለየ መገበያያ ገንዘብ ሲሆን ወርቅና ብርን (ሲልቨር) የሚመለከቱ ህጎች ይመለከቱታል። የየሃገራቱ የወረቀት ኖት እራሱን የቻለ አንዱ ከሌላው የሚለይ ገንዘብ ነው። ለማሳጠር ስል ለዚህ ትርጓሜ የሚውሉ አጋዥ መረጃዎችን አልጠቅስም።
እነዚህ የወረቀት ብር ኖት ሲጀመሩ አካባቢ ዘካ ይወጅብባቸዋል ወይስ አይወጅብባቸውም በሚለው ላይ በኢስላም ምሁራን መካከል ውዝግብ ተከስቶ ነበር። የልዩነቱ መነሻ ለዚህ ገንዘብ ምንነት የተሰጡ ትርጓሜዎች መለያየት ነበር። ነገር ግን ይሄ መገበያያ በከፍተኛ መጠን በመስፋፋቱና የወርቅና የብርን ቦታ በመተካቱ የተነሳ ውዝግቡ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ከስሟል። ስለዚህ ትኩረታችን ይህ የወረቀት ብር ኖት ለዘካ መጠን በሚደርስበት መነሻ ተመን (ኒሷብ) ላይ ይገደባል ማለት ነው።
የወረቀት ብር ኖት ዘካ የሚወጅብበት መነሻው ተመን (ኒሷብ) ስንት ነው? በዚህ ላይ ሶስት የተለያዩ ሃሳቦች ተሰንዝረዋል።

አንደኛ:– የወረቀት መገበያያ ኖት መነሻ የዘካ ተመን የብር (ሲልቨር፣ ፊዷ) ኒሷብ ነው ያሉ አሉ። ይህም 200 ዲርሃም ማለትም 595 ግራም ነው።
ሁለተኛ:– ኒሷቡ የወርቅ ኒሷብ ማለትም 20 ዲናር ውይም 85 ግራም ነው ያሉም አሉ።
ሶስተኛ:– መነሻው መጠን ከወርቅና ከብር መነሻ ተመኖች ዝቅ ያለው ነው ያሉም አሉ።

ከሶስቱ ሃሳቦች ውስጥ ሶስተኛው ሚዛን የሚደፋ እንደሆነ በርካታ ዑለማዎች ደምድመዋል። መነሻቸውም:–
1ኛ፦ ድሃዎቹን የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋል።
2ኛ፦ ለዘካ አውጪውም ከውዝግብ ቀጠና ለመውጣት፣ ከተጠያቂነት ስጋት ለመትረፍ ይበልጥ ሰላማዊ ነው።
3ኛ፦ የመጀምሪያዎቹን ሁለት አቋሞች ያንፀባረቁ ምሁራን የሚያቀርቧቸውን መርጃዎችና ትንታኔዎች አንፃራዊ በሆነ መልኩ የተሻለ የሚያቀራርብ ነው።
4ኛ፦ ለዚህ የወረቀት መገበያያ ኖት የዘካ ተመን ከወርቅና ከብር (ሲልቨር) አንዱን መጠቀም ግድ ከሆነ ከሁለት አንዱ ቀድሞ የደረሰውን ኒሷብ በምን አሳማኝ መነሻ ልንዘለው እንችላለን? እንደሚታወቀው የብር (ሲልቨር) ኒሷብ ዛሬም በነብዩ ﷺ ዘመን ከነበረው አይቀየርም። ዛሬም እንደ ጥንቱ 200 ዲርሃም ማለትም 595 ግራም ብር ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግድ ይለዋል።
ይህ አቋም የሰዑዲያ የታላላቅ ዑለማእ ምክር ቤት፣ የእውቀታዊ ምርምር ቋሚ ኮሚቴ (ለጅነተ ዳኢማህ)፣ በራቢጦተል ዓለሚል ኢስላሚ ስር ያለው ቀራረል መጅመዒል ፊቅሂይ እና የሌሎችም ምርጫ ነው።

የዘንድሮ የወረቀት ብር ዘካ መነሻ (ሂሳብ) ስንት ነው?
````````
`````````
የሚችል ሰው
ወቅታዊን የወርቅና የብር ዋጋ አጣርቶ በራሱ ማስላት ይችላል። በኔ በኩል በተወሰኑ ወንድሞች አማካኝነት ለማጣራት እንደሞከርኩት ወቅታዊ (የ 2014) ወርቅ የሚሸጥበት ዋጋ በግራም ከ 3800 እስከ 4,500 ብር ነው። የብር መሸጫ ዋጋ ደግሞ ከ 120 እስከ 150 ብር ነው። ስለዚህ፡
[ሀ] የወርቅ ዘካ ኒሷብ የሆነውን 20 ዲናር (85 ግራም) በወቅቱ ዋጋ 3,800 ብር ስናባዛው 323,000 ብር ሲሆን
[ለ] የብር ዘካ ኒሷብ ደግሞ 200 ዲርሃም (595 ግራም) በወቅቱ ዋጋ 120 ብር ሲባዛ 71,400 ብር ይሆናል። ስለዚህ ከሁለቱ ኒሷቦች የብሩ ስለሚያንስ ከላይ በቀረበው 3ኛው አቋም መሰረት ለዚህ አመት (1443 ሂጅሪያ) ይህንን መጠን 71,400 መነሻ እናደርጋለን ማለት ነው። እናም 71,400 ብር እና የበለጠ አመት የቆየ ብር ያለው ሰው ዘካ ማውጣት ግድ ይለዋል ማለት ነው። ስለሆነም ለዘካ መጠን የደረሰ ገንዘብ ኖሮት አመት ከቆየ የገንዘቡን የ1/10ኛውን እሩብ ማለትም 2.5% ዘካ ያወጣል ማለት ነው። ስሌቱን ግልፅ ለማድረግ ጥቂት ምሳሌዎችን ልስጥ፦

1– አመት የዞረ 300,000 ብር ያለው ሰው የ 300,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 300,000 x 0.025=7,500 ብር
2– አመት የዞረ 450,000 ብር ያለው ሰው የ 450,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 450,000 x 0.025=11,250 ብር
3– አመት የዞረ 5 ሚሊዮን ብር ያለው ሰው የ 5,000,000ን 2.5% ያወጣል፡፡ 5,000,000 x 0.025=125,000 ብር ይሆናል ማለት ነው። ወይም ደግሞ አጠቃላይ ገንዘቡን ለ40 ቢያካፍለው ማውጣት ያለበትን የዘካ መጠን ይሰጠዋል። የቀረቡትን ምሳሌዎች ለ40 ቢያካፈል ተመሳሳይ መጠን ያገኛል።

ማሳሰቢያ፦
~
በብሄራዊ ባንክ በኩል የሚወጣውን የወርቅና የብር ዋጋ ያልተጠቀምኩት ህዝብ የሚገባያይበት ትክክለኛ ዋጋ ነው ብየ ስላላመንኩበት ነው። ወሏሁ አዕለም።
(ረመዳን 15/1442፣ ሚያዚያ 20/ 2013)
https://t.me/IbnuMunewor