La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
በረመዳን ውስጥ በሳምንት ቁርኣንን ለማኽተም 🌹
✔️ፈጅር ላይ 20 ገፅ
✔️ዙህር 15 ገፅ
✔️ዐስር ላይ 12 ገፅ
✔️መግሪብ ላይ 13 ገፅ
✔️ዒሻእ ላይ 14 ገፅ
✔️ስሑር ላይ 12 ገፅ


«وفقنا الله وإياكم لما يحب ويرضى ..»🍃🌷
ተራዊሕ - 1

ወሩ የሑፋዞች ነው። የአላህን ቃል በማንበብ ወሩን ሙሉ በረመዷን ምሽቶች ላይ ይነግሳሉ። ሰማይ ምድሩን በማራኪ ድምፆቻቸው ያዉዳሉ። ሰዎች የአላህን ቃል ይወዱ ዘንድ ሰበብ ይሆናሉ። ምንኛ ታደሉ በረቢ።

ሑፋዞች ልዩ የአላህ ሰዎች ናቸው። አላህ ከሰዎች አስበልጦ ሰዎች ፊት አቆማቸው። የሚሕራብ ንጉሶች አደረጋቸው። ይህም በርግጥ የአላህ ችሮታ ነው። እሱም ችሮታዉን ለሻው ሰው ይሠጣል። "የኽተሱ ቢረህመቲሂ መን የሻኡ።"
ልጅህን ቁርአን ስታስተምረው ፣ በተራው ቁርኣን ደግሞ ልጅህን ያስተምርልሃል።

#የቁርኣን ወር


https://t.me/httpsLatahzen
ረመዷን -1
ሱሑር -1

አላህ ሐያታችንን አርዝሞ በርሱ ፍቃድ ተመልሰናል። ያለ ሰው ሲገናኝ የሞተ ግን በቃው። በዲን ላይ ቆይቶ ዳግም መገናኘት ትልቅ መታደል ነው።
አላህ ሆይ አምና ከኛ ጋር ለፆሙት ዘንድሮ ግን ለሌሉ ወንድም እህቶች ሁሉ ምህረትህን ለግስ።

https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from La tehzen
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ
...

ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ላተህዘኖች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም #ላተህዘኖች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ የተወሰኑ ቤቶች ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ ፓኬጅ #1000 ብር
ግማሽ ፓኬጅ #500 ብር
ሩብ ፓኬጅ #250 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
🔺ዱቄት 🔺ሩዝ
🔺የሾርባ እህል 🔺ቴምር እና ዘይት


አድራሻ ካራቆሬ
ስልክ ቁጥር
📞 0938619117 ይደውሉልን
📞 0937442278
ወይም👇👇
''
@mamepro or @Oufeyret


Join us 👇👇👇
https://t.me/resulinn

https://t.me/resulinn

የየቲሞችን እንባ ተባብረን እናብስላቸው
እንታደጋቸው


ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➡️በምናፈጥር ጊዜ የሚባል ዱአ

ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ
♦️ጥም ተወገደ፣ ጉሮሮዎችም (የደም ስሮች) ረጠቡ፣ በአሏህ ፍቃድ አጅሩም ፀደቀ።"
📚 ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678)
La tehzen
ረመዷን -1 ሱሑር -1 አላህ ሐያታችንን አርዝሞ በርሱ ፍቃድ ተመልሰናል። ያለ ሰው ሲገናኝ የሞተ ግን በቃው። በዲን ላይ ቆይቶ ዳግም መገናኘት ትልቅ መታደል ነው። አላህ ሆይ አምና ከኛ ጋር ለፆሙት ዘንድሮ ግን ለሌሉ ወንድም እህቶች ሁሉ ምህረትህን ለግስ። https://t.me/httpsLatahzen
ረመዷን (2)
ሰሐር፣ ሰሑር እና ሱሑር
**
'ሰሐር' ከእውነተኛው ንጋት (ሱብሒ ሶላት መግቢያ ምልክት) በፊት ወደ ሌሊቱ መጨረሻ አካባቢ የሚገኝ ጊዜ ነው።
በዚህ ጊዜ የሚበላ ምግብ/መጠጥ 'ሰሑር' ይባላል።
የመመገብ/መጠጣት ሁኔታው ደግሞ 'ሱሑር' ይባላል።

'ሰሑር' ለፆም መያዣ ተብሎ የሚበላ ቀለል ያለ ምግብ ወይም የሚጠጣ ዉሃ ነው።
ሰሑርን መመገብ ነቢያዊ ፈለግ ነው። እርሳቸው እንድንጠቀም መክረዋል። የሰሑር ዓላማው የሚበላና የሚጠጣ ነገር በማግበስበስ፣ ሆድን መወጠርና ማጨናነቅ አይደለም። ወይም ደግሞ በተለምዶ ከረመዷን ዉጭ ቀን ላይ ይመገቡ የነበረዉን ምግብ ወደ ሌሊት ጊዜ ማዞር አይደለም። እንዲያማ ከሆነ ፆም ዓላማዉን ይስታል።

ሰሑር በረከትና ምንዳ አለው። በፆም ላይ ያበረታል። ሰሑር ጉንጭ ዉሃ ሊሆን ይችላል። ጥቂት የተምር ፍሬዎች ሊሆን ይችላል። አንድ እና ሁለት ጉርሻ ምግብ ሊሆን ይችላል።

ሱሑርን እኛ ሙስሊሞች ብቻ ነን ያለን። በዚህም ከሌሎች ሃይማኖቶች ፆም እንለያለን።

https://t.me/httpsLatahzen
እናንተ ጿሚዎች ሆይ

በሱሁር በረካ አለው ተነስታችሁ የበላችሁ ላልተነሱ ጓደኞቻችሁ ደውሉላቸው ።
ቀጥታ ስርጪት ከአዲስ አበባ/ወለቴ
በኡስታዝ አቡል ዓባስ ጀምሯል
➴➴➴

https://t.me/abuhuzeyfaabdilbasete?livestream=3edfab14b7125736a9

.
◾️ሰለፎችና ቁርአን በረመዷን ውስጥ


ረመዷን ውስጥ ቀደምት የዲን ሊቃውንቶቻችን ትኩረት ከሚሰጧቸውና በብዛት ይፈፅሟቸው ከነበሩ ታላላቅ ኢባዳዎች ውስጥ አንዱና ዋናው በሶላትም ሆነ ከሶላት ውጪ ቁርአንን አብዝቶ መቅራትን ነበር። እነዚህ ቀደምቶቻችንና ሞዴሎቻችን ከቁርአን ጋር የነበራቸው ግኑኝነትና ቁርኝነት እጅግኑ የገዘፈና የጠበቀ ነበር። ከዚህም የተነሳ ቁርአንን በአግባቡ ቀርተው፣ ተረድተው፣ ተግብረውና ህይወታቸው ሙሉ ለሙሉ ከቁርአን ጋር በማቆራኘትና በማገናኘት የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ፈፅመው ወደ ማይቀረው ሀገር ተሻግረዋል። ይህንን እውነታ ከሚያሳዩን ነገሮች ውስጥ፦

↪️ ኢማሙ ዙህርይ (رحمه الله تعالى)

👉 ይህ ታላቅ ኢማም ረመዷን ውስጥ በዋናነት ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባ ኢባዳ አስመልክቶ እንዲህ አለ፦【ረመዷን ማለት ቁርአንን በብዛት የማንበብያና ምስኪኖችን የመመገቢያ ወር ብቻ ነው።】ይል ነበር።

↪️ ኢማሙ ማሊክ (رحمه الله تعالى)

👉 ረመዷንን በቁርአን ከሚያሳልፋ ኢማሞች ውስጥ አንዱ ናቸው። ከዚህም የተነሳ ልክ ረመዷን ሲቃረብ፦ 【የሀዲስ ቂርአትና የኢልም ሀለቃቸውን በማቆም ቁርአንን ከሙስሀፋ (ከመፅሀፋ) ይዘው ወደ መቅራት ይዛወሩ እንደነበረ ተወስቷል።】

↪️ ኢማሙ ቀታዳ (رحمه الله تعالى)

👉 ረመዷን ውስጥም ሆነ ከረመዷን ውጪ ቁርአንን በብዛት ከሚያነቡት ተርታ የሚመደቡ ታላቅ ኢማም ናቸው። 【ከዚህም የተነሳ በሁሉም ወራቶች ቁርአንን በየ ሰባት ሰባት ቀን ያኸትሙ ነበር። ረመዷን ውስጥ ደሞ በየ ሶስት ሶስት ቀኑ ያኸትሙ ነበረ። የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ሌሊቶች ላይ ደሞ በየቀኑ ቁርአንን ያኸትሙ ነበር።

↪️ ኢብራሂም አንነኸእዩ (رحمه الله تعالى)

👉 ይህ ታላቅ ኢማም፦ 【በረመዷን ውስጥ በየ ሶስት ሶስት ቀን ቁርአንን ያኸትም ነበር። አሽረል አዋኺር (የረመዷን የመጨረሻ አስርት ቀናት) ውስጥ በየ ሁለት ሁለት ቀን ያኸትም ነበር።】

↪️ ኢማም አል አስወድ (رحمه الله تعالى)

👉 ይህ ታላቅ አሊም በአመቱ ውስጥ ባሉ ወራቶች ባጠቃላይ፦ 【በየ ሁለት ሁለት ቀን ቁርአንን ያኸትም ነበር።】

📚 لطائف المعارف (ص:٣١٨)

http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
http://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
ረመዷን መጣላችሁ
በሚል ርእስ ወንድማችን አቡ መርየም ሳዳት ከማል ቀጥታ ከሁዘይፋ መስጂድ








ገባ ገባ በሉ ባረከሏሁ ፊኩም

https://t.me/SadatKemalAbuMeryem?livestream
የቴሌግራም live ሊንክ⤴️⤴️⤴️⤴️
~[ተውበት]በማንኛውም ጌዜ ወደ አላህ መመለስ እና ከሰራናቸው ወንጀሎች መፀፀታችንን አላህ የሚወደው ተግባር ነው

በተለየ መልኩ ደግሞ እኛን አላህ ወዶን ለዚህ ታላቅ የተውበት የእዝነት ወር አድርሶናል

~እስኪ ቆም ብለህ አስታውስ ከምታውቃቸው ሰወች ውስጥ የዛሬ አመት አብሮህ የነበር
አሁን ግን በሂወት የሌለ የለምን? በእርግጥም አለ
ታዳ አንተስ የዛሬ አመት ድረስ ከሱ ላለመሆንህ ምን ማስረጃ አለህ ?

እናማ ማለት የፈለኩት በዚህ ታላቅ ወር ከሌላ በተለየ መልኩ ተውበታችን ተቀባይነት የሚኖረው ወር በመሆኑም የተውበት መስፈርቶችን አሞልተን ጉዞ ወደ ተውበት........

https://t.me/htt_asselfya
https://t.me/htt_asselfya



https://t.me/httpsLatahzen
በረመዳን በብዛት የሚፈፀሙ ስህተቶች

① ሶላት ሳይሰግዱ መፆም፣
② ሌሊቱን በጫት ካሳለፉ በኋላ ሱሑርን አስቀድሞ በመመገብ ፈጅር
ሳይሰግዱ መተኛት፣
③ ቀኑን በእንቅልፍ፣ ሌሊቱን በተከታታይ ፊልም/ ሙሰልሰላት ማሳለፍ፣
④ ረመዳንን ጠብቆ መንዙማና ነሺዳ እየለቀቁ ሰዎችን ከቁርኣን ማዘናጋት፣
⑤ ተራዊሕን በንቃት እየሰገዱ ፈጅር ሶላትን በእንቅልፍ ማሳለፍ፣
⑥ ተራዊሕ ላይ በየ አራቱ ረከዐ መሐል የቢድዐና የሺርክ እንጉርጉሮዎችን
ማስገባት፣
⑦ የተራዊሕ ኢማሞች ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑት ዱዓእ የበለጠ ትኩረትና
ጊዜ መስጠት፣
⑧ መግሪብ ሶላት ሲጠናቀቅ አሳፋሪ በሆነ መልኩ ለፊጥራ መጣደፍ
(ሰጋጆችን የሚያቋርጥ፣ የሰው ጫማ የሚያቀያይር፣…ብዙ ነው)
⑨ ሌሊት ላይ "ተሰሐሩ " እያሉ በእስፒከር መጮህ፣
(10) የሱሑር ጊዜ ሳያልቅ ለጥንቃቄ በሚል ቀድሞ አዛን ማድረግ፣
(11) ሱሑር ላይ "ነወይቱ ሰውመ ገዲን" እያሉ በቃል መነየት፣
(12) እያንቀላፉ ተራዊሕ መስገድ፣
(13) ልጆች "እንፁም" ሲሉ ማበረታታት ሲገባ መከልከል፣ "ውሃ
አያፈጥርም፣ ተደብቀህ ብላና ትፆማለህ" እያሉ መዋሸትና ውሸት
ማለማመድ፣
(14) ሴቶች በተጋነነ የምግብ ዝግጅት ሰፊ ጊዜያቸውን ማቃጠል፣
(15) ሴቶች ሽቶ ተቀብቶ ለተራዊሕ መውጣት፣
(16) በተራዊሕ ወቅት የሴቶችና የወንዶች አላስፈላጊ መዝረክረክ፣
(17) ሃሜት፣
(18) ፊጥራ ላይ ከመጠን በላይ መመገብ፣
(19) ቀኑን በካርታ፣ በዳማ፣ ወዘተ ማሳለፍ፣
(20) ሙዚቃ ማዳመጥ፣
(21) የሰው ስራ የሚሰሩ ተቀጣሪዎች ጧት በሰዓት አለመግባት (አማና
መጠበቅ፣ ቃልን ማክበር ግድ ይላል። ግዴታ ያልሆኑ ዒባዳዎች ተፅእኖ
የሚያሳድሩብን ከሆነ መተው ወይም መቀነስ ነው)፣
(22) በተለይ በስራ ቦታዎች ላይ በመንዙማና በነሺዳ ማሳለፍ (መሆን
ያለበት ከተመቼ ቁርአን መቅራት፣ ካልሆነ ዚክር ማድረግ ወይም ደዕዋ
ማዳመጥ፣ ካልሆነ ዝምታ ይሻላል።)
(23) ለይለተል ቀድርን ለማየት ሰማይ ሰማይ እያንጋጠጡ መጠበቅ
(የሚታይ ነገር የለም)፣
(24) አንዳንድ አካባቢዎች ዒሻን በጣም በማዘግየት ሰው ጀማዐ ላይ
እንዳይካፈል እንቅፋት መሆን፣
(25) አንዳንድ አካባቢዎች መስጂድ ውስጥ ጫት ይዞ ገብቶ መቃም፣
(26) አንዳንድ አካባቢዎች "ተርቲብ" ብለው ንፍሮ፣ ቆሎና መሰል
ምግቦችን ወደ መስጂድ እንዲያቀርቡ ሰዎችን ማዘዝ፣ ወዘተ

By Ibnu munewor

↷ ⇣🌹⇣↷
https://t.me/httpsLatahzen
መንገደኛ እና ፆም፡-

♦️መንገደኛ ፆምን መፍታት ስለተፈቀደለት ካልፆመ ከጉዞው መልስ ያልፆማቸውን ቀናት ቀዳእ ማውጣት ይኖርበታል፡፡ ይህን በተመለከተ አላህ እንዲህ ብሏል፦
فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ ٱلشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍۢ فَعِدَّةٌۭ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ
 البقرة ١٨٥

“ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው፡፡ በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነም ሰው ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን (በልኩ) መጾም አለበት”፡፡አል-በቀራህ 185

ነብዩም (ﷺ) በጉዞ ላይ ስለመፆም ሲጠየቁ “ከፈለግክ ፁም ካስፈለገክም ፍታ” ብለዋል፡፡ እሳቸውም ወደ መካ ጉዞ ላይ ሳሉ ፆም ላይ ቆይተው ኹደይድ የሚባል ስፍራ ሲደርሱ ፆማቸውን ፈተው ሰሃቦችም እንዲፈቱ አዘዋል፡፡ ፆምን መፍታት የሚፈቀድበት የጉዞ መጠን ሰላትን ማሳጠር በሚፈቀድበት የጉዞ መጠን ሲሆን እሱም ሰማንያ ኪሎ ሜትር ርቀት ነው፡፡ እንዲሁም ፆምን መፍታት የሚፈቀድበት የጉዞ አይነት የኃጢአት ጉዞ ወይም ፆምን ለማፍረስ ብቻ የታቀደበት ጉዞ መሆን የለበትም፡፡

መንገደኛ ቢፆም ፆሙ ተቀባይነት ይኖረዋል፡፡ አነስ እንዲህ ብለዋል፦
“ከነቢዩ(ﷺ) ጋር ጐዞ ላይ ስንሆን ከመካከላችን የሚፆምና የሚፈታ ቢኖርም የፆመው የፈታውን የፈታውም የፆመውን አያነውርም ነበር”
📚አል ቡኻሪ (1947)

መንገደኛ ሲፆም የሚጐዳ ወይም ፆም የሚከብደው ከሆነ ግን ባይፆም ይመረጣል:: ምክንያቱም ነቢያችን (ﷺ) አንድ ሰው በጉዞ ላይ ሳለ በመፆሙ ስለተጎዳ አቅራቢያው ያሉ ሰዎች ከፀሐይ ሲጠልሉት ተመልክተው
“ጉዞ ላይ መፆም ከመልካም ስራ አይደለም” ብለዋል፡፡
📚አል ቡኻሪ (1946)

↷ ⇣🌹⇣↷
https://t.me/httpsLatahzen
አፍጡር ላይ የሚባል

ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ الْعُرُوْقُ وَثَبَتَ اْلأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ.

‘ዘሐበዝዘመኡ ውበተልለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል አጅሩ ኢንሻአህ

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِيْ
, አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሐለሁ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
ኢብኑል ቀይም - ረሂመሁላሁ ተአላ እንዲህ ይላል :-

"ፆመኛ ማለት አካላቱ ከወንጀል
ምላሱ ከውሸትና ከመጥፎ ንግግር ከውሽት ምስክርነት
ሆዱ ከምግብና ከመጠጥ
ብልቱ ከዝሙት የፆመ ነው
ከተናገረ ፆሙን የሚጠፋ ንግግር አይናገርም ከሰራም ፆሙን የሚያበላሽ ነገር አይሰራም "

📚አል ዋቢሉ ሰይብ ገፅ ( 43 )
https://t.me/httpsLatahzen
Channel photo removed