La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
Forwarded from La tehzen
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ
...

ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ላተህዘኖች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም #ላተህዘኖች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ የተወሰኑ ቤቶች ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ ፓኬጅ #1000 ብር
ግማሽ ፓኬጅ #500 ብር
ሩብ ፓኬጅ #250 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
🔺ዱቄት 🔺ሩዝ
🔺የሾርባ እህል 🔺ቴምር እና ዘይት


አድራሻ ካራቆሬ
ስልክ ቁጥር
📞 0938619117 ይደውሉልን
📞 0937442278
ወይም👇👇
''
@mamepro or @Oufeyret


Join us 👇👇👇
https://t.me/resulinn

https://t.me/resulinn

የየቲሞችን እንባ ተባብረን እናብስላቸው
እንታደጋቸው


ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም
ደስ የሚል ንግግር

ሶደቃ በውብ ቋንቋ ሲገለፅ!

«ስትሞት ኃብትህን ካንተ ጋር ይዘህ መሄድ አትችልም። ነገርግን ቀድሞህ እንዲሄድ ማድረግ ትችላለህ!»


የነየትንም ንያችንን እናስገባ
ያልነየትንም እንነይት እህቶቼ ወንድሞቼ በአቅማችን ለኸይር ስራ እንሽቀዳዳም
⤵️እህቴ ሆይ ንቂ !
〰️〰️〰️〰️〰️

ፈገግታ እያበዛ በአስመሳይ ጥርሱ
ወደድኩሽ እያለ በቅቤምላሱ
ፍቅር ሲገልፅልሽ ቃላትን ቀምሞ
አመመኝ እያለ ሲነግርሽ ደጋግሞ
እዳትሸወጂ ብልጥ ሁኚ አደራ
ያቺ ያልሆነን ሰው በፍፁም አታፍቅሪ
በሀሳብ መንምነሽ ከቱ እዳትቀሪ
ከኔ አያልፍም ብለሽ ምኑን ሳታቂ የፍቅር አባዜ ጠልፎሽ እዳትወርቂ
ደግሜ ልገርሽእህቴሆይ ንቂ
ከድህ አይነት ነገር በጭራሽ ራቂ
ለምኑም ለምኑም አትጨናነቂ
አላህ ባለጊዜ ይሆናል እወቂ

ያንን ቀን በተስፋ ከጌታሽ ጠብቂ
"ሰደቃ የአላህን ቁጣ ያበርዳር ሰደቃን ስጡ( ረሱሉ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

ተናፋቂው የእዝነቱ ወር ሊደርስ ጥቂት ቀናቶች ነው የቀሩት ታዲያ እርስዎ ምን አስበዋል ምንስ ነይተዋል እንግዲያውስ ካሎት ላይ የበኩልወን እንዲያካፍሉ አማናወን ይወጡ ዘንድ #ላተህዘን የየቲሞች ልማትና መርጃ ማህበራት ጥሪውን ያስተላልፋል
አወን አንድም የቲም ሳያፈጥር እንዳያድር የበኩላችንን እንወጣ እያለን ነው ስለዚህ ትሪውን እንቀበለው ዘንድ በ አላህ ስም እንጠይቃለን

#ለአንድ ቤተሰብ
- ሙሊ ፓኬጅ 1000 ብር
-ግማሽ ፓኬጅ 500
- እሩብ ፓኬጅ 250
እንዲሁም የንያወትን
በአይነት መደገፍ ለምትፈልጉ
🔵ዱቄት
🔵ዘይት
🔵ቴምር
🔵የሾርባ እህል
🔵ሩዝ

ለበለጠ መረጃ

0937442278
0938619117 ይደውሉ

@mamepro👈 @Oufeyret👈 ንያወን በዚህ ያሳውቁን

ደግነት ለራስ ነው መልካምነት መልሶ ይከፍላል


https://t.me/resulinn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①③

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
🌟ታላቁ ወር ....🌟


ወደ አላህ ለመቅረብ በዚክር በኢባዳ
በኢኽላሱ መጠን ሊበዛልን ምንዳ
ታላቁ ወር መጣ ኸይርን መሸመቻ
የአጅር ሀሰናት ካዝናን ማካበቻ።
🌟🌟🌟
እንግዲህ የአላህ ቤት በኸልቁ ተዋቢ
መጣልሽ ረመዳን በድምፆች አብቢ።
⭐️⭐️⭐️
ምላስም ለዘበች ከወሬ ከሀሜት
ከተራ ዛዛታ የማይረቡ ቃላት
ከከንቱ ንግግር ከቀልድ ና ውሸት
ተጠመደች እና በዚክር በቂርዓት።
🌟🌟🌟
ባማረ ቅላፄ ድምጿ ሊስተጋባ
ወደ አላህ በመቅረብ ሊረጥብ ነው ቀልቧ።

በአመፅ በገፍላ የተረሱ ለይሎች
ደረሰ ረመዳን ብድግ አሉ ጎኖች
ሀጃ ገጠማቸው እዝነቱ ጠራቸው
ከእንቅልፍ አባንኖ ለይል አቆማቸው።

ቀልብም ይመርባት ተጊጣ ተውባ
በመልካም ስራዎች ወደ አላህ ቀርባ
ሰኪናን አግኝታ ተቅዋን ደርባ።
⭐️⭐️⭐️
በወርሃ ረመዳን ሁሉም ነገር ያምራል
ከወንጀል ከባጢል ከተማው ይፀዳል
ሼጧን አሳሳቹ ከኛ ይታሰራል
ከሰዎች ልብ ላይ ውስወሳው ይርቃል
በሙዐዚን ጥሪ ሀገሩ ይደምቃል
ጀሀነም ተዘግቶ ጀነት ይከፈታል
የራህመት እጆቹን አላህ ይዘረጋል
በስቲግፋር ሰደቃ ቁጣው ይወገዳል
ከወር ሁሉ መርጦ አላህ አልቆታል።
🌟🌟🌟
ፈድሉና ራህመቱ ኒዕማው እና ፀጋው
በወርሃ ረመዳን ሰፊና ጥልቅ ነው።

በዚህ በረመዳን ፆመኞች በሙሉ
በተሟላ ኒያ አላህን ካሰቡ
ሽርክና ቢድዓ ክልክላት ከራቁ
በተውሂድ ተጉዘው ሱናን ከጠበቁ
በሆድ ብቻ ሳይሆን በአካል ከፆሙ
ረያን አላቸው ምነኛ ታደሉ።
⭐️⭐️⭐️
ማንም አይገባትም ይችን የጀነት በር
ሳይታክት ቢታገል ወይም ደግሞ ቢጥር
ማንም ይሁን ማንም ከፆመኞች በቀር
አላህ ይወፍቀን ይጠብቀን ከሸር
ግዴታ መሆኑ በዚሁ ታላቅ ወር
መፆሙ ለአላህ ተቅዋ እንዲኖር።
🌟🌟🌟
ከዚሁ እንንቃ ሴቶች እባካቹ
ሳንቡሳ ስጠብሱ ሾርባውን ጥዳቹ
ከምግቡ ብዛት ብፌ ደርድራቹ
ምግብን በማብሰል አይለቅ ጊዜያቹ
ሳትጠቀሙበት ወሩ እንዳያልፋቹ
ወሩ እኮ አይደለም የምግብ የመጠጥ
ቤቶችን የማስዋብ በውዶች ጌጣጌጥ
ከዚህም ከዚያም በስራ መራወጥ።
🌟🌟🌟
አጥብቀን እንያዝ የነብዩን ሱና
ጥርት ባለው መንገድ በሰለፎች ፋና
ተውሂድ እንዲሰምር ህይወት እንዲቃና።
⭐️⭐️⭐️
ምስጋና ይገባህ ወሮችን ለፈጠርክ
በተለይ ረመዳን ለኛ ስላደረክ
ውለታህ ብዙ ነው ተነግሮ አያልቅም
ለፀጋህ መግለጫ አጥቻለው አቅም
አንተን ማወደሻ ቃላትን አላውቅም
ቃላት ቢሰካኩ ለክብርህ አይበቃም።

አድርሰን ያረቢ አግራልን ኢባዳ
ነጃ እንድንባል ከቁጭቱ ዕዳ።
◾️የማይሰግድ ሰው ፃም በተመለከተ


♦️የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ተቀባይነት አለውን?

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሸይኽ መሀመድ ሷሊህ አልኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

↪️ የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ምንም ሊጠቅመው አይችልም። አላህ ዘንድም ተቀባይነት አያገኝም። ቢፃም እራሱ እስካልሰገደ ድረስ ነገ አላህ ፊት ከመጠየቅ አይድንም። አንድ ሰው እስካልሰገደ ድረስ ፃም አለብህና ፁም አይባልም። ምክንያቱም የማይሰግድ ሰው እንደ የሁድና ነሷራ አምሳያ ነው። ታዳ የአይሁድና የነሳራ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ረመዷንን ቢፃም ይፈይደዋልን? ፃሙንስ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛልን? በጭራሽ ሊሆን አይችልም። ይህም ሰው ልክ እንደነሱ አምሳያ ነው። ባይሆን አንድ ሰው ሶላትን የማይሰግድ ሆኖ ሲፃም ካየነው፦ መጀመርያ ከመፃምህ በፊት ወደ አላህ ተውበት አድርግ፣ ሶላትህንም ጀምር ከዛ በኋላ ፁም ብለን እንመክረዋለን። በመፀፀት ወደ አላህ የተመለሰ ሰው አላህ ተውበቱን ይቀበለዋልና።
☞⇄①, ለአላህ ቅርብ መሆን ትፈልጋለህ?

☞አንድ ባሪያ አላህ ዘንድ የበለጠ ቅርብ የሚሆነው ስጂድ ላይ ሲሆን ነው። ያኔ ዱአ አብዙ
(ረሱል ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⇄ ②የሀጅን አጂር(ምንዳ) ትፈልጋለህ?

☞በረመዳን ኡምራ ሀጂን ወይም ከኔ ጋር ሀጂን ማረግን ይስተካከላል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞③ ⇄በጀነት ቤት ትፈልጋለህ?

☞ለአላህ ብሎ መስጂዲን የገነባ አላህ በጀነት ቤት ይገነባለታል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞④⇄የአላህን ውደታ ማግኘት ትፈልጋለህ,?

☞አላህ አንዲትንም ጉርሻ ጎርሶ በሱዋ የሚያመሰግን ፣ባሪያ ይወዳል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑤።።ዱአህ ተቀባይነት እንዲኖረው ትፈልጋለህ?

☞በአዛን እንዲሁም በኢቃም መካከል የሚደርግ ዱአ አይመለስም።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑥።። አንድ አመት ሙሉ የፆም አጂር(ምንዳ) እንዲፃፍልህ(እንዲመዘገብልህ) ትፈልጋለህን?

☞ከያንዳንዱ ወር 3 ቀን መፆም አመት ሙሉ ከመፆም ጋር ይስተካከላል ።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞ ⑦, ልክ እንደተራራ የገዘፈ አጂር ትፈልጋለህ?

☞ጂናዛ(አስክሬን) ላይ ሰግዶ ለሸኘ ሰው ለርሱ #ቂረጣን አለው እስከሚቀበር ድርስ።
ለሸኛ ሰው ሁለት ቂረጣን አለው።ቂረጣን ምድነው ተብለው ሲጠየቁ ፣ልክ እደ ትልቅ ተራራ ነው ብለዋል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑧⇄ ጀነት ከረሱል ቅርብ(ጎረቤት) መሆን ትፈልጋለህ?

☞እኔና የቲምን የሚከባከብ ሰው እድህ ነን ሲሉ
መጠቆሚያና የመሀል ጣታቸውን አሳዩ ።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑨።። ለሊት ሙሉ መቆምን አጂር ትፈልጋለህ?

☞ኢሻን በጀመአ የሰገደ ግማሽ ለሊትን ቆሞ እንደሰገደ ይቆጠርለታል።ሱቢሂን በጀመአ የጨመረ ለሊቱን ሙሉ እንደሰገደ ይቆጠርለታል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞ ⑩።።, በቁርአን ውስጥ የቁረአንን 1/3 መቅራት
ትፈልጋለህ?

☞ቁርአንን 1/3 ትስተካከላለች፣ሱረቱል ኢህላስ፣
ወይም በአጭሩ "ቁልሁወላሁ አሀድ" የሚለውን ሱራ 3 ግዜ ከቀራ ቁርዓንን እንዳከተመ(ሙሉውን እንደቀራ ይቆጠርለታል)።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱላሏህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም።

☞⑪።።።,የጥሩ ስራህን ሚዛን ከበድ ማድርግ ትፈልጋለህ?

☞ሁለት ንግግሮች ናቸው።
ለምላስ የቀለሉ አራህማን ዘንድ የተወደዱ ሚዛን ላይ የከበዱ
1ኛ—ሱብሀነላህ ወቢሀምዲሂ
2ኛ— ሱብሀነላህ አልአዚም።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂም)

☞⑫ ።።ርዝቅህ እንዲሰፋ እድሜህ እንዲረዝም
ትፈልጋለህ?

☞እርዚቁ እድሰፋለት እድሜው እንዲረዝም የፈለገ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል ።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

⇡☞⑬።።። አላህ አንተን መገናኘትን ትፈልጋለህ?

☞አላህን መገናኘትን የወደደ፣አላህም እሱን መገናኘትን ይወድለታል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞ ⑭።። አላህ እንዲጠብቅህ ትፈልጋለህን?

☞ሱብሂን ሰላት የሰገደ ሰው እሱ በአላህ ጥበቃ ስር ነው።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

⑮15, አላህ ባንተ ላይ ሰለዋት እንዲያወርድልህ ትፈልጋለህ?

☞በኔላይ(በረሱል ሰዐወ) ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ ፣አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርዳል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱህ ውድ እህት ወንድሞቼ እኳን ለተከበረው ወር ረመዷን አደረሳችሁ አሏህ እነዚህን የቀሩትን ጥቂት ቀናት በሰላም አድርሶ በትክክል ፆመው ከሚጠቀሙት ነገ የፍርዱ ቀን ከሚመሰክርላቸው ባሮቹ ያድርገን አሚን በማወቅም ሆነ ባለማወቅ አስቀይሜያችሁ ወይም የሰው ልጅ ከምላስ ወለምታ የፀዳ አይደለምና አስቤውም ሆነ ሳላስበው በምላሴ አንስቻችሁ ይሆናል እና ለአሏህ ብላችሁ አፉ በሉኝ እኔ ለአሏህ ብዬ አፉ ብያለሁ
Forwarded from Deleted Account
🌷አስደሳች ዜና🌷

ታላቅ የሙሓደራ ዝግጅት

➨በኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
ርዕስ➬ሁለቱ ሸሀዳዎች
➨በኡስታዝ አቡል አባስ (ናስር)
ርዕስ➬የረመዳን ጥሩ አጋጣሚዎች
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እሁድ መጋቢት 25 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ
አድራሻ ሁነይን መስጅድ ወለቴ ሀረር ደቦ ቤት አከባቢ ድልድይ አጣገብ።
ለሴቶችም ቦታ አዘጋጅተናል

አይደለም መቅረት ማርፈድ አይገባም

አዘጋጅ የሁነይን መስጅድ ወጣቶች ጃማዓ

https://t.me/httpsLatahzen

https://t.me/httpsLatahzen
#ጀነት መግባት ትፈልጋለህ!

🍃የአላህ መልእተኛ (ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:
"የጀነት በሮች ዘወትር ሰኞ እና ሀሙስ ቀን ይከፈታሉ፤ አላህም በነዚህ ቀኖች በሱ ምንንም ያላጋሩ ባሮቹን ሁሉ ይምራል በመካከላቸው ጠብ (ቅራኔ) ያለባቸው ሁለት ሰወች ሲቀሩ ፤ እነዚህን ሁለት ሰዎች በመካከላቸው ያለውን ቅራኔ እስከሚያስወግዱ (እስከሚስማሙ) ድረስ ተዋቸው (ጠብቋቸው) ይባላሉ።
Forwarded from Deleted Account
# ስታሳዝን
ይህች አንጀት የምትበላ ህፃን # ኢልሀም_ንጉስ ትባላለች!የ7ተኛ ክፍል ጎበዝ
ተማሪ ነበረች!ድንገት
መድከምና ማዞር ሲጀምራት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ለምርመራ ትሄዳለች!!
በሚያሳዝን ሁኔታ የ13ዓመቷ # ኢልሀም የአጥንት መቅኔዋ ደም ማምረት
እንዳቆመና በአስቸኳይ ወደ
ውጪ ሄዳ መታከም እንዳለባት ይነገራታል
# ለ3ወራትም ያለማቆረጥ በማህፀኗ ደም ፈሷታል
አባት ትቷት ሄዶ እናትም ለአመታት በስደት አጎንብሳ ብቻዋን እየተሰቃየች
አሳድጋት ደረሰችልኝ ስትል
# ሞት ቀድሞ ልጇን ሊነጥቅባት ነው
ስለልጇ ብላ ሌላ ህይወት ሳትመኝ በስደት # ተንከራታ ሰው ቤት ደክማ
ለአመታት የሰራችበትን ጨርሳ ዛሬ ልመና ወጥታለች
ምስኪኗ ኢልሀምም ህመሙ ስለባሰባት ትምህርቷን አቋርጣ አልጋ ላይ
ቀርታለች
እናት ሰአዳ # በቸኛ_ልጇ እንድትድንላት ከ2,000,000 (2ሚሊዮን) ብር በላይ
ያስፈልግሻል ተብላለች
ህመሙ ብሶባት አፏ መቁሰል የጀመረውን የአይኔ ማረፊያ መፅናኛዬን
# እባካችሁ_አድኑልኝ ትላለች
የምንችል # በገንዘብ ካልቻልን # በፀሎትና # በሼር
# እናግዛት ለህፃን # ኢልሀም # እንድረስላት
# አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፡-
1000444871176-ሰአዳ አብራር(እናት)
# ስልክ፡-
0910346090-ሰአዳ አብራር(እናት)
0912121942-ውብሸት ተካ
0913559189-ሄኖክ ፍቃዱ
0921058425-ኤደን ተክሉ
"ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድ ያዳርሱ ለኸይር ሰበብ እንሁን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①③

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ