La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
»“ረመዷን የኸይር ወር”«

√→ እንደሚታወቀው ይህ ወር የፃም ወር ነው የበረካ የራህመት የእዝነትም ጭምር
√→ከራህመቱ ከበረካው ከእዝነቱ እናገኝና ትክክለኛ ፇሚ እንሆን ዘንድ
√↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
√→ሆዳችን ከምግብ ከመጠጥ እንደሚፃም ሁላ ሌሎችንም አካላቶቻችን ሊፃሙና አላህ ሊፈሩ ግድ ይላል
√→ብልታችን ከሀራም ከዚና ሊፃም ይገባል ያለበለዛ የሆዳችን መራብ ብቻ ዋጋ የለውም
√→አይኖቻችን አጅነብይ ከማየትና ሀራም ከመመልከት ሊፃምና ሊቆጠብ ይገባዋል
√→እጆቻችን የማትፈቀድልንን ሴት እና ወንድ ከመጨበጥና በጃችን አላህ ከማመፅ ልንርቅ ይገባል
√→አፋችን ከተለያዩ ፃምን ከሚያበላሹ ወይም ምንዳን ከሚቀንሱ ነገራቶች ለምሳሌ ሰውን ከማማት፣ ከመሳደብ፣ ከመዋሸት እና ከሌሎች ሊፃም ግድ ይለዋል
√→በአጠቃላይ ሁለመናችን ፃመኛ ሊሆን ይገባል

መክንያቱም የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ
{من لم يدع قول الزور والعمل به فليس لله حاجة أن يدع طعامه وشرابه}
(አንድ ሰው አፀያፊ ንግግርና በሱ መስራትን እስካልተው ምግብና መጠጥ በመተዉ ብቻ አላህ ምንም ጉዳይ የለውም )
በሌላ ሀዲሳቸው
{فكم من صائم ليس من صومه إلا الجوع والعطش}
(ስንትና ስንት ፃመኞች አሉ ነገር ግን ከፃማቸው ረሀብና ጥማት እንጂ ሌላ የማያገኙ) ይላሉ

https://t.me/httpsLatahzen

√→ስለዚህ ፃማችን ሀራም ከተደረጉ ነገራቶች በመጠበቅ በመልካም ስራ ልናስጌጠው ይገባል
→ቁርአን በመቅራት
→ሰደቃ በመስጠት
→ሶላቶችን በማብዛት
→ዚክሮችን በማለት
→አልቅሰን ወደ አላህ በመመለስና ለስከዛሬው ጥፋታችን መሀርታውን በመለመን
→የተቸገረን በመርዳት
→ሰዎችን በማስፈጠር እና በመሳሰሉት ኢባዶዎች ላይ በመጠንከር ልክ ረመዷን ሲወጣ አዲስ እንደተወለደ ልጅ ንፁህ ልንሆን ይገባል
→ወንጀላችን ታጥቦ
→ልባችን በኸይር ተሞልቶ
→ተስፋችን ለምልሞ
→አቂዳችን ጠንክሮ
→ኢማናችን ጨምሮ
→ከአላህ ውድ ባሮች እንሆን ዘንድ የዛሬው ጥረታችንና ልፋታችን ወሳኝ ስለሆነ በኢባዳ ላይ እንበርታ እላሉሁ
اللهم أعنى على ذكرك وشكرك وحسن عبادتك
اللهم تقبل قيامنا وصيامنا وسائر أعمالنا
ربنا آتنا في الدنيا حسنة وفي الآخرت حسنة وقنا عذاب النار
ረመዳን ታላቁ ወር
Sadat
ረመዳን ታላቁ ወር
ረመዳንን እንዴት እናሳልፍ
Sadat
ረመዳንን እንዴት እናሳልፍ?
ረመዳን ለነማን
Sadat
አዲስ ሙሐደራ
ረመዳን ለነማን?
🌙የረመዷን ሌባዎች አውቀው ይጠንቀቁ‼️

✍️1ኛው ሌባ;
🖥️ቴሌቬዥን‼️
ሙስሊሞች አንገብጋቢ በሆነው የረመዷን ወር ላይ መስራት ያለባቸውን ዒባዳ ሰርተው እንዳይጠቀሙ በተለያዩ ተከታታይ ፕሮግራሞች እና አሉ ባልታ ዜናዎች ጊዜያቸውን ይሰርቃቸዋል። አውቀን እንጠንቀቀው‼️

✍️2ኛው ሌባ;
🏪የገበያ ማዕከል‼️
አስፈላጊና አስገዳጅ የሆነ ጉዳይ ካለ በፍጥነት ሸምቶ መመለስ እንጂ ገበያ ቦታ ላይ ያለ ሀጃ በመመላለስ ውዱ የረመዷን ወቅታችሁ እንዳትሰረቁ ተጠንቀቁ።

✍️3ኛው ሌባ;
🌌መቃዠት (ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ ማባከን)‼️
ይህም ክፉ ከሆኑ የረመዷን ሌባዎች አንዱ ነው። እረፍት አድርገህ ተኸጁድ በነሻጣ እንዳትሰግድ እና ቀንህም ያለ ቂርኣት እና አዝካር በድብርት እንዲያልፍ ያደርገዋል። በመሆኑም ውዱ የረመዷን ወቅትህን እንደይሰርቅብህ ተጠንቀቀው።

✍️4ኛው ሌባ;
ኩሽና‼️
ይህ ሌባ ለየት ባለ መልኩ በብዛት የሚያጠቃው ሴቶችን ነው። ረመዷን የዒባዳ ወር መሆኑን ይዘነጋና የምግብ ዐይነት ማተራመሻ ወር በማስመሰል ሴቶች የተለያዩ የምግብ ዐይነቶች በማዘጋጀት ስራ ላይ ተጠምደው አብዘሃኛው ሰዓታቸው ማድ ቤት እንዲያልፍ ያደርጉታል። በመሆኑም ቀን በስራ ውለው ማታ እየደከማቸው መስራት ያለባቸውን ዒባዳ እንዳይሰሩ ይሆናሉ። ይህንን ተረድተው የወቅታቸው ሌባ የሆነውን ኩሽና ሊጠነቀቁት ይገባቸዋል።

5ኛው ሌባ;
📲ስልክ‼️
ረዥም ሰዓት መደዋወል፤ ምንም ፋኢዳ የሌለው የአሉ ተባለ ወሬ ማውራትና መከታተል እንዲሁም በማይመለከት ጉዳዮች በማሰብና በማሰላሰል ጊዜ እንዲባክን የሚያደርገው ዋነኛው ሌባ ስልክ ነው። አውቀን እንጠንቀቀው።

✍️6ኛው ሌባ;
🥨ስስታምነት‼️
ድሃዎችንና ምስኪኖችን በመንከባከብ እንዲሁም ለየት ባለ መልኩ በተከበረው የረመዷን ወር ሰደቃ በማድረግ የሚገኘውን ምንዳ እና ከእሳት መጠበቅ እንዳይኖር በማድረግ ምንዳን የሚሰርቅ ክፉ ሌባ ነው። እኛም ክፋቱን አውቀን እንጠንቀቀው።

✍️7ኛው ሌባ;
አላህን ከማውሳት ነፃ የሆነ ሸንጎ‼️
ይህም የቂያማ ቀን ባለቤቱን የሚፀፀትበት የሆነ በዱንያም ላይ በተለይ በውዱ የረመዷን ወር ላይ ወቅቱን የሚሰርቅ የሆነ ሌባ ነው።

✍️8ኛው ሌባ;
ረዥም የሆነ እንቅልፍ‼️
በረመዷን ወር አስፈላጊ ከሆነው በላይ እንቅልፍ ማብዛት በቀንም ይሁን በሌሊት ከሚፈፀሙ ዒባዳዎች የሚያዘናጋ፣ ድብርትና ድካምን በማውረስ የረመዷን ወቅት የሚሰርቅ ሌባ ነው።

✍️9ኛው ሌባ;
የመገናኛ ብዙሃን (ሚዲያ)‼️
ይህ በጣም የከፋና አደገኛ ሌባ ነው። የትኛውም የሚዲያ ስርጭት አላህን ለሚያስወደድ ነገር ካልተጠቀምንበት ወቅታችንን ከሚሰርቁን ሌቦች ዋነኛው ይሆናል።


🌙ለተከበረው የረመዷን ወር አላህ በሰላም ያድርሰንና ከተጠቃሚዎች ያድርገን🤲🏽

✍️ሐምዱ ቋንጤ
ከፉርቃን ሰማይ ስር
https://t.me/joinchat/AAAAAENJn9-WekBJmow0AQ

ያልተጠቀሱ ሌባዎች ካሉ ለመጠቆም
👇🏽👇🏽👇🏽
http://telegram.me/hamdquante_bot
La tehzen
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ ... ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር..... ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች…………… እኔ…
የየቲምን እንባ ማበስ የአንድ ሰዉ ብቻ ሐላፊነት አይደለም!
የእናትን እንባ ማበስ የግለሰብ ሐላፊነት አይደለም!
ጎዳና የወጣዉ የአባቴን እንባ ማበስ የብቻዬ ሐላፊነት አይደለም!

እህቴና ወንድሞቼ በዝናብና በብርድ እየተቀጠቀጡ እኔ እንዴት አስችሎኝ እቀመጣለዉ...?

ልጇን በጉያዋ ይዛ ተቀምጣ የሰዉን አይን እያየች እንዴት ባላየ አልፋለዉ...?

ዉድ ወገኖች የጀመርነዉ ስራና የያዝነዉ ቀጠሮ እንደቀልድ ሊታይ አይገባም.. ማንም ትኩረት የነፈገዉን ነገር ነዉ ዛሬ ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ የተፈለገዉ..
ያለንን እንነይት even ከአንድ ብር ጀምሮ በስልካችን እንላክ!
የናንተ ትንሽ ተጠራቅሞ ነዉ ከአላህ በታች የዛ የ የቲሙ እንባ የሚታበሰዉ...የእናቴ ለቅሶ የሚያበቃዉ!

ስለዚህ አሕለል ኸይሮች እዚሁ ግሩፕ ላይ ያለንን እንነይት...ሊላህ ብላቹ!!
ባንችል እንኳን አቅሙ ላላቸዉ ሼር እናድርግ!!!

Join &share👆👆
Forwarded from La tehzen
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ
...

ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ላተህዘኖች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም #ላተህዘኖች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ የተወሰኑ ቤቶች ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ ፓኬጅ #1000 ብር
ግማሽ ፓኬጅ #500 ብር
ሩብ ፓኬጅ #250 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
🔺ዱቄት 🔺ሩዝ
🔺የሾርባ እህል 🔺ቴምር እና ዘይት


አድራሻ ካራቆሬ
ስልክ ቁጥር
📞 0938619117 ይደውሉልን
📞 0937442278
ወይም👇👇
''
@mamepro or @Oufeyret


Join us 👇👇👇
https://t.me/resulinn

https://t.me/resulinn

የየቲሞችን እንባ ተባብረን እናብስላቸው
እንታደጋቸው


ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም
ደስ የሚል ንግግር

ሶደቃ በውብ ቋንቋ ሲገለፅ!

«ስትሞት ኃብትህን ካንተ ጋር ይዘህ መሄድ አትችልም። ነገርግን ቀድሞህ እንዲሄድ ማድረግ ትችላለህ!»


የነየትንም ንያችንን እናስገባ
ያልነየትንም እንነይት እህቶቼ ወንድሞቼ በአቅማችን ለኸይር ስራ እንሽቀዳዳም
⤵️እህቴ ሆይ ንቂ !
〰️〰️〰️〰️〰️

ፈገግታ እያበዛ በአስመሳይ ጥርሱ
ወደድኩሽ እያለ በቅቤምላሱ
ፍቅር ሲገልፅልሽ ቃላትን ቀምሞ
አመመኝ እያለ ሲነግርሽ ደጋግሞ
እዳትሸወጂ ብልጥ ሁኚ አደራ
ያቺ ያልሆነን ሰው በፍፁም አታፍቅሪ
በሀሳብ መንምነሽ ከቱ እዳትቀሪ
ከኔ አያልፍም ብለሽ ምኑን ሳታቂ የፍቅር አባዜ ጠልፎሽ እዳትወርቂ
ደግሜ ልገርሽእህቴሆይ ንቂ
ከድህ አይነት ነገር በጭራሽ ራቂ
ለምኑም ለምኑም አትጨናነቂ
አላህ ባለጊዜ ይሆናል እወቂ

ያንን ቀን በተስፋ ከጌታሽ ጠብቂ
"ሰደቃ የአላህን ቁጣ ያበርዳር ሰደቃን ስጡ( ረሱሉ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

ተናፋቂው የእዝነቱ ወር ሊደርስ ጥቂት ቀናቶች ነው የቀሩት ታዲያ እርስዎ ምን አስበዋል ምንስ ነይተዋል እንግዲያውስ ካሎት ላይ የበኩልወን እንዲያካፍሉ አማናወን ይወጡ ዘንድ #ላተህዘን የየቲሞች ልማትና መርጃ ማህበራት ጥሪውን ያስተላልፋል
አወን አንድም የቲም ሳያፈጥር እንዳያድር የበኩላችንን እንወጣ እያለን ነው ስለዚህ ትሪውን እንቀበለው ዘንድ በ አላህ ስም እንጠይቃለን

#ለአንድ ቤተሰብ
- ሙሊ ፓኬጅ 1000 ብር
-ግማሽ ፓኬጅ 500
- እሩብ ፓኬጅ 250
እንዲሁም የንያወትን
በአይነት መደገፍ ለምትፈልጉ
🔵ዱቄት
🔵ዘይት
🔵ቴምር
🔵የሾርባ እህል
🔵ሩዝ

ለበለጠ መረጃ

0937442278
0938619117 ይደውሉ

@mamepro👈 @Oufeyret👈 ንያወን በዚህ ያሳውቁን

ደግነት ለራስ ነው መልካምነት መልሶ ይከፍላል


https://t.me/resulinn
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①③

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
🌟ታላቁ ወር ....🌟


ወደ አላህ ለመቅረብ በዚክር በኢባዳ
በኢኽላሱ መጠን ሊበዛልን ምንዳ
ታላቁ ወር መጣ ኸይርን መሸመቻ
የአጅር ሀሰናት ካዝናን ማካበቻ።
🌟🌟🌟
እንግዲህ የአላህ ቤት በኸልቁ ተዋቢ
መጣልሽ ረመዳን በድምፆች አብቢ።
⭐️⭐️⭐️
ምላስም ለዘበች ከወሬ ከሀሜት
ከተራ ዛዛታ የማይረቡ ቃላት
ከከንቱ ንግግር ከቀልድ ና ውሸት
ተጠመደች እና በዚክር በቂርዓት።
🌟🌟🌟
ባማረ ቅላፄ ድምጿ ሊስተጋባ
ወደ አላህ በመቅረብ ሊረጥብ ነው ቀልቧ።

በአመፅ በገፍላ የተረሱ ለይሎች
ደረሰ ረመዳን ብድግ አሉ ጎኖች
ሀጃ ገጠማቸው እዝነቱ ጠራቸው
ከእንቅልፍ አባንኖ ለይል አቆማቸው።

ቀልብም ይመርባት ተጊጣ ተውባ
በመልካም ስራዎች ወደ አላህ ቀርባ
ሰኪናን አግኝታ ተቅዋን ደርባ።
⭐️⭐️⭐️
በወርሃ ረመዳን ሁሉም ነገር ያምራል
ከወንጀል ከባጢል ከተማው ይፀዳል
ሼጧን አሳሳቹ ከኛ ይታሰራል
ከሰዎች ልብ ላይ ውስወሳው ይርቃል
በሙዐዚን ጥሪ ሀገሩ ይደምቃል
ጀሀነም ተዘግቶ ጀነት ይከፈታል
የራህመት እጆቹን አላህ ይዘረጋል
በስቲግፋር ሰደቃ ቁጣው ይወገዳል
ከወር ሁሉ መርጦ አላህ አልቆታል።
🌟🌟🌟
ፈድሉና ራህመቱ ኒዕማው እና ፀጋው
በወርሃ ረመዳን ሰፊና ጥልቅ ነው።

በዚህ በረመዳን ፆመኞች በሙሉ
በተሟላ ኒያ አላህን ካሰቡ
ሽርክና ቢድዓ ክልክላት ከራቁ
በተውሂድ ተጉዘው ሱናን ከጠበቁ
በሆድ ብቻ ሳይሆን በአካል ከፆሙ
ረያን አላቸው ምነኛ ታደሉ።
⭐️⭐️⭐️
ማንም አይገባትም ይችን የጀነት በር
ሳይታክት ቢታገል ወይም ደግሞ ቢጥር
ማንም ይሁን ማንም ከፆመኞች በቀር
አላህ ይወፍቀን ይጠብቀን ከሸር
ግዴታ መሆኑ በዚሁ ታላቅ ወር
መፆሙ ለአላህ ተቅዋ እንዲኖር።
🌟🌟🌟
ከዚሁ እንንቃ ሴቶች እባካቹ
ሳንቡሳ ስጠብሱ ሾርባውን ጥዳቹ
ከምግቡ ብዛት ብፌ ደርድራቹ
ምግብን በማብሰል አይለቅ ጊዜያቹ
ሳትጠቀሙበት ወሩ እንዳያልፋቹ
ወሩ እኮ አይደለም የምግብ የመጠጥ
ቤቶችን የማስዋብ በውዶች ጌጣጌጥ
ከዚህም ከዚያም በስራ መራወጥ።
🌟🌟🌟
አጥብቀን እንያዝ የነብዩን ሱና
ጥርት ባለው መንገድ በሰለፎች ፋና
ተውሂድ እንዲሰምር ህይወት እንዲቃና።
⭐️⭐️⭐️
ምስጋና ይገባህ ወሮችን ለፈጠርክ
በተለይ ረመዳን ለኛ ስላደረክ
ውለታህ ብዙ ነው ተነግሮ አያልቅም
ለፀጋህ መግለጫ አጥቻለው አቅም
አንተን ማወደሻ ቃላትን አላውቅም
ቃላት ቢሰካኩ ለክብርህ አይበቃም።

አድርሰን ያረቢ አግራልን ኢባዳ
ነጃ እንድንባል ከቁጭቱ ዕዳ።
◾️የማይሰግድ ሰው ፃም በተመለከተ


♦️የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ተቀባይነት አለውን?

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሸይኽ መሀመድ ሷሊህ አልኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

↪️ የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ምንም ሊጠቅመው አይችልም። አላህ ዘንድም ተቀባይነት አያገኝም። ቢፃም እራሱ እስካልሰገደ ድረስ ነገ አላህ ፊት ከመጠየቅ አይድንም። አንድ ሰው እስካልሰገደ ድረስ ፃም አለብህና ፁም አይባልም። ምክንያቱም የማይሰግድ ሰው እንደ የሁድና ነሷራ አምሳያ ነው። ታዳ የአይሁድና የነሳራ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ረመዷንን ቢፃም ይፈይደዋልን? ፃሙንስ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛልን? በጭራሽ ሊሆን አይችልም። ይህም ሰው ልክ እንደነሱ አምሳያ ነው። ባይሆን አንድ ሰው ሶላትን የማይሰግድ ሆኖ ሲፃም ካየነው፦ መጀመርያ ከመፃምህ በፊት ወደ አላህ ተውበት አድርግ፣ ሶላትህንም ጀምር ከዛ በኋላ ፁም ብለን እንመክረዋለን። በመፀፀት ወደ አላህ የተመለሰ ሰው አላህ ተውበቱን ይቀበለዋልና።
☞⇄①, ለአላህ ቅርብ መሆን ትፈልጋለህ?

☞አንድ ባሪያ አላህ ዘንድ የበለጠ ቅርብ የሚሆነው ስጂድ ላይ ሲሆን ነው። ያኔ ዱአ አብዙ
(ረሱል ሱለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⇄ ②የሀጅን አጂር(ምንዳ) ትፈልጋለህ?

☞በረመዳን ኡምራ ሀጂን ወይም ከኔ ጋር ሀጂን ማረግን ይስተካከላል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞③ ⇄በጀነት ቤት ትፈልጋለህ?

☞ለአላህ ብሎ መስጂዲን የገነባ አላህ በጀነት ቤት ይገነባለታል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞④⇄የአላህን ውደታ ማግኘት ትፈልጋለህ,?

☞አላህ አንዲትንም ጉርሻ ጎርሶ በሱዋ የሚያመሰግን ፣ባሪያ ይወዳል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑤።።ዱአህ ተቀባይነት እንዲኖረው ትፈልጋለህ?

☞በአዛን እንዲሁም በኢቃም መካከል የሚደርግ ዱአ አይመለስም።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑥።። አንድ አመት ሙሉ የፆም አጂር(ምንዳ) እንዲፃፍልህ(እንዲመዘገብልህ) ትፈልጋለህን?

☞ከያንዳንዱ ወር 3 ቀን መፆም አመት ሙሉ ከመፆም ጋር ይስተካከላል ።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞ ⑦, ልክ እንደተራራ የገዘፈ አጂር ትፈልጋለህ?

☞ጂናዛ(አስክሬን) ላይ ሰግዶ ለሸኘ ሰው ለርሱ #ቂረጣን አለው እስከሚቀበር ድርስ።
ለሸኛ ሰው ሁለት ቂረጣን አለው።ቂረጣን ምድነው ተብለው ሲጠየቁ ፣ልክ እደ ትልቅ ተራራ ነው ብለዋል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑧⇄ ጀነት ከረሱል ቅርብ(ጎረቤት) መሆን ትፈልጋለህ?

☞እኔና የቲምን የሚከባከብ ሰው እድህ ነን ሲሉ
መጠቆሚያና የመሀል ጣታቸውን አሳዩ ።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞⑨።። ለሊት ሙሉ መቆምን አጂር ትፈልጋለህ?

☞ኢሻን በጀመአ የሰገደ ግማሽ ለሊትን ቆሞ እንደሰገደ ይቆጠርለታል።ሱቢሂን በጀመአ የጨመረ ለሊቱን ሙሉ እንደሰገደ ይቆጠርለታል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞ ⑩።።, በቁርአን ውስጥ የቁረአንን 1/3 መቅራት
ትፈልጋለህ?

☞ቁርአንን 1/3 ትስተካከላለች፣ሱረቱል ኢህላስ፣
ወይም በአጭሩ "ቁልሁወላሁ አሀድ" የሚለውን ሱራ 3 ግዜ ከቀራ ቁርዓንን እንዳከተመ(ሙሉውን እንደቀራ ይቆጠርለታል)።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)
ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያረሱላሏህ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም።

☞⑪።።።,የጥሩ ስራህን ሚዛን ከበድ ማድርግ ትፈልጋለህ?

☞ሁለት ንግግሮች ናቸው።
ለምላስ የቀለሉ አራህማን ዘንድ የተወደዱ ሚዛን ላይ የከበዱ
1ኛ—ሱብሀነላህ ወቢሀምዲሂ
2ኛ— ሱብሀነላህ አልአዚም።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂም)

☞⑫ ።።ርዝቅህ እንዲሰፋ እድሜህ እንዲረዝም
ትፈልጋለህ?

☞እርዚቁ እድሰፋለት እድሜው እንዲረዝም የፈለገ ሰው ዝምድናውን ይቀጥል ።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

⇡☞⑬።።። አላህ አንተን መገናኘትን ትፈልጋለህ?

☞አላህን መገናኘትን የወደደ፣አላህም እሱን መገናኘትን ይወድለታል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

☞ ⑭።። አላህ እንዲጠብቅህ ትፈልጋለህን?

☞ሱብሂን ሰላት የሰገደ ሰው እሱ በአላህ ጥበቃ ስር ነው።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)

⑮15, አላህ ባንተ ላይ ሰለዋት እንዲያወርድልህ ትፈልጋለህ?

☞በኔላይ(በረሱል ሰዐወ) ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ ፣አላህ በእርሱ ላይ አስር ሰለዋት ያወርዳል።
(ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰላም)