La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
>>> አፈውቱ . . . <<<


አፍህን አዳልጦት እሱም አፉ ገድፎ
የፍቅራችሁ ፀዳል ከራማው ተገፎ
ቂም በቀል ይዛችሁ የምትቋሰሉ
ፍቅር ሰላም ይሁን አውፍ ተባባሉ::
አፈውቱ ... አፈውቱ
ተዉ አንሁን ከንቱ ! ...
ዘመን ጉልበት ሰጥቶት ክንዱን አበርትቶ
አቅመ ቢስ ደካማን በግፍ አንገላቶ
ዘርፎ!... ነጥቆ!... ሰቅሎ!...
አስሮ!... ገርፎ!... ገሎ!...
በድንቁርናው ልክ ስንቱን አመሳቅሎ
ወገን የበደለን ያን ጭንጋፍ ሙትቻ
የዘመን እንቅፋት የሰው አራሙቻ
ክስረቱን ቆጥራችሁ ግፉን በርብራችሁ
እጥፉን ልትከፍሉት ደግሞ በተራችሁ
ሰይፍ የምታፋጩ ጎራዴ የምትስሉ
ግዴላችሁም ተውት ይቅር ተባባሉ
በፍቅር ወስፈንጥር ጥላቻን ግደሉ! . . .
አፈውቱ ... አፈውቱ...
በሉ አፈውቱሊላ (ህ)
እንረስ በደቦ፣
ባንድ ማእድ እንብላ::
ደግሞም ያንን ርካሽ
ጉማጅ የሰው ብጣሽ! ...
ዘር ቀለም ሃይማኖት ስር እየመዘዘ
የፍቅርን ሰንሰለት እየገዘገዘ
ያብሮነትን ዋርካ እየመዘመዘ
የአድባሩን ሸንጎ ባፉ እየመረዘ
ሃቅና ቅጥፈትን ባንድ እየበረዘ
ሲዳክር ሲባዝን ለክስረት ሲለፋ
ሽቅቡን ሲወጣው ተያይዞ ሊጠፋ ...
አይታችሁ ብትበግኑ ውስጣችሁ ቢቃጠል
በነፍጥ አታድርጉት አውድሙት በቅጠል!...
ምግባሩን ነው እንጂ ተውት የሱን ገላ
ርካሽ ነው ርካሽን በርካሽ 'ሚበላ
ይሁን እድል ስጡት ይቁረስ አንድ እንጀራ
ደንዳናው ልቦናው በፍቅር ቢገራ ...
የከበደው ሰማይ ያ የቂም ደመና
ያልፋል በይቅርታ ሳያደርገን መና . . .
ይቅር በል!
ይቅር በይ!
በቃ አፈውቱሊላ (ህ)
አይርከስ
አይፍረስ
የጎጇችን ባላ::


https://t.me/httpsLatahzen
#አንድ_እውነት_እናውራ__!!
----------------------------------
አብዛሀኛውን ህዝቡ በሽርክ እየጋዬ፡
በአድስ መጤ ቢድዐ እየተሰቃዬ፡
ሞት እየቀደመው ተውሒድ ሳይረዳ፡
ቀብር እየገባ ሳያውቅ ሸሀዳ፡
የፊትና ሰንሰለት አረቂ ስትቀዳ፡
ደግሞም እየዋሸህ እያልክ ሚሪንዳ፡
ይህ ይዘገንናል ለዘመድ ለባዳ፡
-------------------//----------------
ጂን እያመለከ አንበሶና ጨንገር፡
እየኖርን እያለ በእንድህ አይነት ሀገር፡
በራሒሎ በጭራቅ በአድባሩ በቆሌው፡
በሰራን በሾናት እንድሁ በጭሌው፡
ሽርክን እምነት ይዞ ህዝቡ ተውሒድ ትቶ፡
ቢዲዐ ሲከተል ሱናውን ዘንግቶ፡
ባጢል ላይ ሲፀና እውነትን ረስቶ፡
ተውሒድ ካላስቀደምን ይህንን እያየን፡
ከኢኽዋን ከአህባሽ ለምን ተለያየን?
-----------------------------=-------------
የተለየንበት ከነዚህ ቡድኖች፡
ከጥመት ጥርቅም ከቢዲአ ጋኖች፡
በተውሒድ በሱና ስለማይጣሩ፡
በማያውቁት ነገር ስለሚናገሩ፡
በእምነት ሲዋሹ አሏህን ሳይፈሩ፡
ከሀቁ ጎዳና ሲለቁ ከፈሩ፡
በዚህ አይደለም ወይ የተለያየነው፡
ጩኸቱ በዛሳ ኪነት ያገነነው፡
አልገባኝም እኔ ሚስጥሩ ምንድን ነው!?
---------------------///--------------------
በነዚህ ምክነያት ከነርሱ ብንርቅ፡
ይህ የነርሱ መንገድ ላንተ ከሆነ ብርቅ፡
አሏህ ይድረስልህ እኔ ምን ላድርግህ፡
ለፊትና አትፈልገኝ እኔም አልፈልግህ፡
-------------------------------------------
እየተመለከ መርሳ አባገትዬ፡
ምን ተቆጥሮ ያልቃል በጥቅሳ አባዬ፡
ደገር አማን አምባ በቃሉ ገትዬ፡
ድረሱልኝ ሲባል ቦረናው ደግዬ፡
ድምፅ ከፍ አድርገው እያሰሙ ለቅሶ፡
ጋቻ ተዘጋጅቶ እጣን ተጫጭሶ፡
ባንቱ መጀን ሲባል አብሬትና አልከሶ፡
ተውሒዱ ሲረሳ የድኑ ምሰሶ፡
በሀገራችን ውስጥ እያለ ይህ ክስተት፡
አንተ ነጋ መሸ ከጨመርክ ስህተት፡
በአሏህ ንገረኝ እኔ ምን ላድርግህ፡
አንተም አትፈልገኝ እኔም አልፈልግህ፡
-----------------------------------------
መማር ከተሳነህ ከትላንት ዛሬ፡
ፊትና ከናፈቀህ ከተጠማህ ወሬ፡
ህዝብህን ተመልከት ሒድና ቃጥባሬ፡
በሚዲያው አለም አታብዛ ዝማሬ፡
ሰኞ ቀን ነብዩን ህዝቡ እያመለከ፡
ማክሰኞ ኑርሁሴን ብሎ እየሰበከ፡
እሮብ ለአብዶዬ እያረደ ዶሮ፡
ይህንን ዘግናኝ ሽርክ እየሰማ ጆሮ፡
ተውሒድ ተዘንግቷል ጉድ አየን ዘንድሮ፡
ከሰውነት ወጥተን ባስተሳሰባችን ሆነናል ዝንጀሮ፡
#አዎ___!
ሽርክ ግልፅ ሆኖ ተውሒድ ከተረሳ፡
እውነቱን ልንገርህ ሆነናል እንሰሳ፡
-------------------///--------------------
ሀሙስ ኸሚስ ብሎ ሰው ተሰብስቦ፡
መስፈርት አብጅቶ አምሮና ተውቦ፡
ሽርክ ለመፈፀም ተዘጋጅቶ ቀርቦ፡
ለዚህ አይነቱ ህዝብ አታዝንም ወይ አቦ!!?
ቅዳሜ በኸድር እየተመጀነ፡
ይሔ ክብር መስሎት እየተጀነነ፡
ይሔው ባገራችን ቢድዐው ገነነ፡
ህዝቡ ዛሬም ይላል እሁድን ለቁጥቡ፡
አድሩስ አትጨርሱ ቡናውን ቆጥቡ፡
በሁሉም ቀናቶች ሙታን ሲመለኩ፡
እምነቶች ጠቅላላ በሽርክ ሲለኩ፡
የአሏህ አምላክነት ፈፅሞ ሲረሳ፡
ምን እየሰራህ ነው የመንሀጅ ደረሳ፡
የተውሒዱ ሞተር የሱናው አንበሳ፡
በእውቀት ታነፅና ተውሒድ በል ተነሳ፡
ለደዕዋ ተዘጋጅ በል ጡሌህን አንሳ፡
እውነት ሰለፍያን አንተ ከተረዳህ፡
ቃል ገብቷል ፈጣሪ ጀነት ሊመነዳህ፡
-------------------------------------------
#ግና_ወዳጄ ሆይ___!!
ይሔ ሽርክ እያለ በሀገራችን ወሎ፡
ዛፍ እያመለከ ህዝቡ ተኮልኩሎ፡
እያስተናገደ ወጣት ተመልምሎ፡
እንደ ግመል መንጋ ሲሔድ ተግተልትሎ፡
በደቡብ በሰሜን በምዕራብ በምስራቅ፡
ዶሮና ፍየል በግ ሰው ሲያመልክ ጭራቅ፡
በሀበሻ ምድር ባለንባት ሀገር፡
እጅግ ያሳስባል የተውሒዱ ነገር፡
በሁሉም ክልሎች ሽርክ አለ በአቻ፡
በደቡብ ቃጥ ባሬ ኦሮሚያ ኢሬቻ፡
አድባርና ቆሌ አለልህ በአማራ፡
ከደጋ እስከቆላ ብሎም ካራማራ፡
ሽርክ በጣም ገዝፏል ተሻገር ኤርትራ፡
ሀቅን ለመናገር አትሁን አይናፋር፡
እጅግ ብዙ ነገር ሽርክ አለ በአፋር፡
-----------------------------------------
መወከል ራሒሎ ሾናትና ጨሌ፡
ተውሒድ ላይ አተኩር ሽርክ አለ ሱማሌ፡
እንደ ምግብ መጠጥ ቀርቦ የሚበላ፡
እጅግ ዘግናኝ ክስተት ሽርክ አለ ጋንቤላ፡
ነገ በምንተዋት በዚህች ጠፊ አለም፡
ያልተሰራ ወንጀል ያላየነው የለም፡
ሒድና ተመልከት በጎጃም በጎንደር፡
ለጅን የሚገበር አለ ብዙ ጊደር፡
ብዙ ነገር አለ በሙታኖች ቀብር፡
ያዩናል እያሉ ይከፍላሉ ግብር፡
አላፊና አግዳሚው ይጥላል ብዙ ብር፡
---------------------------------------------
ጫት ቢከለከልም በቤት ወይ በኪራይ፡
ያልተከለከለ ሽርክ አለ በትግራይ፡
በሙሉ ሀበሻ ሽርኩ ተጥለቅልቋል፡
ዳኢው ይህን ትቶ ተራ ነገር ናፍቋል፡
ምን እንደሁ አላውቅም ከተውሒድ ርቋል፡
በኔ ይሁን አለም ፉክክር ላይ ወድቋል፡
ጯሒና አጨብጫቢ ቲፎዞ አብጅቶ፡
የተውሒድ ስብከቱን እርግፍ አርጎ ትቶ፡
የሌለ አድስ ነገር ያመጣል ጎትቶ፡
#ጉድ__!!
ከዚያ እኔን ካልመሰልክ ብሎ ይከስሀል፡
በማታውቀው ነገር፤
ባልሰማኸው ክስተት ይመስለኛል ብሎ ረድ ይሰጥሀል!?
#ጉድ_ነው_!!
ተዘዋውረህ ብታይ ሔህ ወደ ሀረር፡
የሽርክ የቢዲአ አለ ብዙ ጨረር፡
ይህ ሁሉ መከራ እያለ በሀገርህ፡
ከሽርክ ማስጠንቀቅ ቢሆን ንግግርህ፡
ቁጭት ውስጥህ አድሮ ዋልጌነት ቢመርህ፡
በደቡብም ብትዘምት በስልጤ ጉራጌ፡
ሙታን የሚጣራ ብዙ አለ ባለጌ፡
ስራ የማይሰራ ሰነፍና ዋልጌ፡
ይህን ሁሉ ነገር እየተመለከትክ ባይንህ በብረቱ፡
ምነው ከሽርክ ይልቅ ከሱና ሰዎች ላይ ክንዶችህ በረቱ!?
#ያ_አሏህ_በጤናህ_ነው!?
አዎ ከተውሒድ ውጭ ከሆነ ርዕስህ፡
በየትኛው ዳኛ በምን እንክሰስህ፡
አውሬ አይደለን እኛ መቸስ አንነክስህ!?
ወይም በሬ አይደለህ በመጥመድ አናርስህ፡
ይልቅ ተውሒድ ስበክ ፍራላት ለነፍስህ፡
ማንንም አትጎዳም ተጠንቀቅ ለራስህ፡
በሁለቱም ሀገር እንድመች ትራስህ፡
------------------///------------------
ይልቁን ተመከር ጥመትህን ልቀቅ፡
ተገሰፅ ወገኔ እባክህ ተጠንቀቅ፡
ዛሬ ባወራኸው ነገ ከመሳቀቅ፡
ከመጥፎ ዘመቻህ አሁኑ ተላቀቅ፡
በቁርአን በሀዲስ ተፈተሽ ተመርመር፡
ከዛም አንድ እንሁን በሀቅ እንጣመር፡
ዱንያችን ይሳካ አኸይራችን ይመር፡
ችግርም ይልቀቀን ሪዝቁም ይደመር፡
ሱና ላይ በመፅናት ህይወታችን ይስመር፡
--------------------//-------------------------
ሽርክና ቢዲዐን ገድለነው ይቀበር፡
ከኛ ላይ ይነሳ የጠላቶች ቀንበር፡
የመሰለኝ ወሬ ይዘጋ ይሔ በር፡
መረጃ ቢዳኘን መች ይመጣ ነበር:
ቁርአንና ሀድስ ብናበጅ ድንበር፡
ስለዚህ አሁንም ሁላችን እንንቃ፡
ተባብረን እንዝጋው የፊትናውን ሳንቃ፡
ውሸቱ ቅጥፈቱ እዚሁ ላይ ያብቃ፡
ፊትና ቀስቃሽ ሸፍጥን ብለን በቃ በቃ፡
በርሶ መንገድ

በርሶ የቀን ውሎ ቀኑን ቢወጥነው
በፈገግታዎ ልክ ሳቁን ቢመጥነው
ባንቱ ውብ ባህሪ ክፋቱን ቢፍቀው
በእዝነቶ ብርሃን ነፍሱን ቢያደምቀው።
የአማኝ ባህሪ ባንቱ ግብር ቢኳል
ሀሉም በታደለ የጀነትን አስኳል።

#Share #Share

https://t.me/httpsLatahzen
Audio
📚ሱረቱል ሙልክ📚

🎧 ተጋበዙልኝ 🎧
በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️

1) አንድ ግዜ ለማክተም፥

~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16 መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20 ገጽ መቅራት!!
||


ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

አላህ ያግዘን።
#ነብያችን (ﷺ)በ3 ነገሮች ያልተጠቀመ ሰው ከአላህ ራህመት የወጣ ሰው ነው ብለዋል!!!

☞1 "ረመዷን መቶ/ደርሶ/ ራሱን ወደ ኸይር ስራ ያልመለሰ ሰው::
☞2 "የኔ ስም ሲነሳ ሶለዋት የማያወርድ ሰው::
☞3 "እናትና አባቱ በህይወት እያሉ ያልተጠቀመባቸው ሰው ናቸው ብለዋል"ረሱል"(ﷺ)
""የዚህ ተላቅ እንግዳ መምጣት ምክንያት,,,,,
☞1" ሾይጧን ይታሰራል
☞ 2" የጀሀነም በሮች ይዘጋጋሉ
☞ 3 የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ:: ይሉናል ረሱል (ﷺ)::
በዘህ በረመዷን ወር:,
☞1 "በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት # አላህ ለባሮቹ ራህመት
የሚያወርድበት ነው::
☞2 "በመካከለኛዎቹ 10 "ቀናት አላህ ባሮቹን የሚምርበት ነው።
☞3 "በመጨረሻዎቹ 10 ቀናት ደግሞ" አላህ(ሱ ወ) ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ የሚያወጣበት ነው።
ይሉናል"ነብይና መሀመድ (ﷺ)

ያ አላህ እውነትም በዚህ ወር
ያልተጠቀመ ከአላህ እዝነት የወጣ ነው" «አላህ ይጠብቀን!!»
እና"፥እናም እህት ወንድሞቻችን የ11 ወር ወንጀል ተጠራርጎ
ገደል በሚገባበት በዚህ ታላቅ ወር ሁላችንም ለዒባዳ መነሳሳት ለኸይር ስራ መሽቀዳደም ይኖርብናል።በዚህ ወር አላህ ጋ ያለንን ግንኙነት ካላስተካከልን መቸም አናስተካክልም። አላህ በዚህ ታላቅ ወር ደርሰው ከሚጠቀሙት ያድርገን!! አሚን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①①

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
እኔና ጊዜ
.......
ካቻምና በረረ
ታሪክ ሆኖ ቀረ
ኣምናም ተከተለ
ከህልም ዓለም ዋለ
ትናንት ነጎደ
ዛሬም ተራመደ
ሣልደርስበት ሮጬ
ሣልይዘው ጨብጬ

ጨለማው ይነጋል
ብርሃኑም ይመሻል
በጋ ክረምት ያልፋል
ቀን ቀንን ይወልዳል
ከዕድሜዬ ቆርሦ
ከነፍሴ ቀንሦ

ይሮጣል ዘመኑ
ይቀየራል ቀኑ
እኔ ግን ተኝቼ
መሞቴን ረስቼ
አኺራን ዘንግቼ

ቀናቶቹ ሄዱ
ፈጠኑ ነጎዱ
ኅጢአቴ በዝቶ
ወንጀሌ በርክቶ

ቀናቶች በረሩ
ህልሜን ሊያሣጥሩ

ቀናቶች አለቁ
ከኔ እየነጠቁ
አምላኬን ሣልፈራ
ለነፍሴ ሣልሠራ
ኢማኔ ሣይጨምር
ውሎዬ ሣይሰምር
ሣይከደን ጥርሴ
ሣያርፍ ምላሴ

https://t.me/httpsLatahzen
......ረመዳን.....



የወር ሁሉ ንጉስ የኢስላም ስጦታ
መጣልን ረመዳን የሙስሊሞችደስታ
ፁመን ልናሳልፍ በአላህ ችሮታ
እጅጉን ተቃርበን ወደ አለማት ጌታ
አላህ ከጅሎልን ዘንድሮን ወፈቀን
ድጋሚ ውዱን ወር ለማየትም በቃን
እስኪ እናሳልፈው በፆም በኢባዳ
በዘካ በሰላት በሀምድ በሰደቃ
ከአላህ ጋር እንሁን በእያንዳንዷ ቅፅበት
ለከርሞ እንዲያደርሰን ከልብ በመመኘት
ታላቁ ወር መጧል ብስራት ዜና ይዞ
መንገድን ሊያመቻች ለጀነቱ ጉዞ
ሸይጣንን አባሮ ከምድር አፈር ላይ
ወደአላህ ሊያቃርብ በዲናችን ጉዳይ
ከአላህ አስተሳስሮ እጅግም አቃርቦ
ቶሎ ያልቅብናል ሳንጨብጠው ቀርቦ
ህልም ይመስለናል የረመዳን ማብቃት
ወር ሲፈጥን ስናይ ልክ እንደ ሳምንታት
ታዲያ አንዘናጋ እያየነው እስኪያልቅ
እንጠባበቀው ቆመን በተጠንቀቅ
ተጠቃሚ እንሁን በታላቁ ወር ውስጥ
ካለፉት ጊዜያት በደረጃ እንድንበልጥ
ከልብ ተመልሰን ወደ አለማት ጌታ
ረመዳንን እንፁም በጤና በደስታ
የተቸገሩትን ሳንዘነጋ ላፍታ
ተግባራችን ሆኖ ዘካናእርዳታ
ለሌለው አካፍለን ያለንን በደስታ
ከአላህ ምንዳን ሽተን እናግኝ እርካታ
ረመዳን ተባለ በአራት ፊደላት
መቼ ይገልፁታል ሺ የሆኑ ቃላት!!

°°°°°°°°°❤️
°°°°°°°°°°°°°❤️
°°°°°°°°°❤️
°°°°°°°°°°°°°❤️


https://t.me/httpsLatahzen
ባችሉም እንኳን ባታለብሱን
🍕🍕ቁራሽ ከአፋችን ባታጐርሱን🍕🍕
👳👳የአባትነት ፍቅር ባትለግሱን👳👳
👉👉እሱ ይበቃናል ስዳብሱን👈👈
🤝🤝እሱ ያጠግበናል ስዘይሩን🤝🤝
🗣🗣ኑ... አብረን ጀነት እንግባ
🗣🗣ኑ...አብረን ልቦናችንን እናረጋጋ
እንዴት ይሆናል ብለው እያሰቡ ይሆናል ለሱም ቀላል ነገር ነው
👉ትንሽ ጊዜ
👉 አዛኝ ልብ እና ፍላጎት ብቻ
ያኔ አብረን የቲሞችን እንዘይራለን ምንም ባናደርግላቸው በርቱ ብለን ጭንቅላታቸውን ዳበስ ዳበስ ስናደርጋቸው ያረቢ... ደስታቸውን ሳሉት ሳቃቸውን አስቡት ንፁህ ፈገግታ እንሰጣቸዋለን ያኔ ሙሉ ናቸው ከምንም በላይወገን አለኝ ብለው ያምናሉ የሆዳቸውን ያወሩናል ፊታቸው በደስታ ይፈካል እና ውዶቼ ይሄን ያክል ደስታ ማግኘትን ማን ይጠላል እኛ ላተህዘኖች ደግሞ እድሉን አመቻችተን እንካቹ ብለናል ተቀላቀሉን 🙏🙏🙏https://t.me/resulinn
https://t.me/resulinn



ለበጎነት ሁሌም፣ መስፈርት የለውም!

ላተህዘን የየቲሞች የልማትና መረዳጃ ተቋም
ምን ያደርግልኛል ⁉️

ሀብቱ ቢትረፈረፍ አካሉ ቢያምር
ምን ያደርግልኛል የጃሂል አጋር ።
አቂዳ ከሌለው ካላማረ እምነቱ
ምን ያደርግልኛል ሀብትና ንብረቱ።
በጫት ሱስ ተለክፎ ጠዋት ማታ እያበደ
ስለድኑ እማያውቅ የሆነ ወንበደ

ምን ያደርግልኛል በሱስ የተመታ
አሏሁ መውጁዱን ቢላ ሚካን የሚል ጠዋት ማታ ።
በል እዛው ተቀመጥ እንዳትደርስ ከደጀ
እንዳንተ ያለውን እኔ አልፈልገውም ተመለስ ወዳጀ።
አራዳነት መስሎህ ጉንጭህን ወጥረህ
የሱናውን ጀግና ፋራ ነው ትላለህ ።
አልገባህም እንጅ ፋራውማ አንተ ነህ።


ቁጭብለህ ቁማር ቤት ወሬ ታበጃለህ
ትዳር ያሉህ ጊዜ ሴቶች ትመርጣለህ
አንተ የት እንዳለህ መች ታውቀዋለህ
በወንድነት ብቻ ሴት ትጠይቃለህ አለህ
ሰውን አሰዳቢ ምኑ ባለየነህ


ረውዳ‼️‼️‼️

ወንድን አሰዳቢ የወንዶች አልጫ
ለራስህ የማኮን የሆንክ ሞላጫ።



✒️ bint baba
بسم الله
🌴የቲሞችን መንከባከብ🌴


አንድ ግለሠብ የአሏህ መልክተኛ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም
ዘንድ በመምጣት ቀልቤ ደነዘዘ ርሕራሔም የሚባል ነገር
በማጣት ደረቀ መላ ይንገሩኝ ሲል ስሞታውን ያሰማል ።
የአሏህም መልክተኛ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ((ቀልብህ
እንዲለሰልስ የተገራም እንዲሆን ፣ ያሰብከው እና
ያቀድከው ጉዳይህ ተሳክቶ ማየትን ትወዳለህን ?! ))
አሉት ግለሠቡም እንዴታ አንቱ የአላህ መልክተኛ በሚገባ
ነው እንጂ !!)) በማለት ይመልስላቸዋል ።
(( እንግዲያውስ የቲሞችን ራራላቸው ፣ ጸጉራቸውንም
አባብሳቸው ፣ ከምትመገበውም ምግብ በማቋደስ
አብላቸው ያኔ ቀልብህ ይርሳል ፣ ይለሰልሳልም ፣
ያሰብከውም ይሳካልሃል !! )) ሲሉ መለሱለት ።
[ በይሐቂይ ሹዕቡል ኢማን ውስጥ 7 ሐዲስ ቁጥር 330
ላይ ዘግበውታል ። ሃይሰሚይም ሙጀመዕ አዝዘዋኢድ
ውስጥ 8/160 አልባኒም ሠሒሑል ጃሚዕ 80 ላይ
ሰሒሕ መሆኑን አረጋግጠውታል ። ]
ከሰለፎቻችን መካከል አንዱ የሚከተለውን የራሱን ታሪክ
ያወገናል ።
(( በመጀመሪያዎቹ የሕይወት ዘመኔ በኃጢአት ውስጥ
የተጨመላለቅሁ ሰው ነበርኩ ። አስካሪ መጠጥ
በመጠጣት እና ሌሎችንም ኃጢአቶች በመተግበር
ሕይወቴን ያመሰቃቀልኩ ወንጀለኛ ሰው ነበርኩ ። ከዕለታት
በአንዱ ቀን አንድ የቲም ልጅ አገኘሁና ተንከባከብኩት ።
ወደ ቤቴ ወስጄው ከገላ መታጠቢያ ክፍሌ በማስገባት
ገላውን እጥብ አድርጌ ጽዱ አደረግሁት ፤ በማደግ
ተንጨፍርሮ የነበረውን ጸጉሩንም አስተካክዬ አሳመርኩት ፤
ያደጉ ጥፍሮቹንም ቆርጬ አስተካከልኳቸው ፣ አዲስም
ልብስ አልብሼው ልክ አንድ አባት ለልጁ እንደሚያደርገው
ሁሉ በደንብ ተንከባክቤ አብልቼ አጠጥቼ ሸኘሁት ። የዚያ
ቀን ማታ ተኝቼ የሚገርም ህልም አየሁ ። ቂያማ ቆሞ
ተመለከትኩ ፤ አሏህ ሊተሳሰበኝ ስሜ ለፍርድ ሲጠራም
ተሰማኝ ። ሒሳቤንም ስተሳሰብ ከጥፋት ፣ ወንጀመልና
ኃጢአት በስተቀር ምንም ደግ ስራ ሊገኝልኝ አልቻልኩም ።
መዝገቤ ወደ ጀሃነም እትድሄድ ብቻ የሚያደርግ የውርደት
ምዘግብ ነበር ። መልአክቶችም መጥተው እየጎተቱኝ ወደ
ጀሃነም ይነዱኝ ጀመር እኔም ተሸማቅቄ በስራዬ ክፋት
የውረደትን ማቅ ተከናንቤ ሳግ እየተናነቀኝ ወደ ጀሃነም
በሃፍረት መጓዜን ቀጠልኩ ። ወደ ጀሃነም አፋፍ ልደርስ
አካባቢ ያ የተንከባከብኩ የቲም ልጅ ተንደርድሮ
በመምጣት ከፊት ለፊቴ ቆሞ መንገድ ዘጋብኝ ። ((እናንተ
የጌታዬ መልአክቶች ሆይ ይህን ደግ ሰው ወደ ጀሃነም
ፈጽሞ አትውሰዱት ይልቅ ለኔ በዋስትና ስጡኝ ጌታዬ ዘንድ
ሄጄ አማልደዋለሁ አሏህን በሽምግልና ቅጣቱን በማንሳት
እንዲምረው እኔ እማጸንለታሁ !! ይህ ደግ ሰው በደስታና
በሙሉ ውዴታ ተንከባክቦ እንደልጁ ያሰማመረኝ ሰው ነው
። እባካችሁ ለኔ በዋስትና ስጡኝ)) ብሎ በሚማጸናቸው
ወቅት መልአክቱ (( እኛ ይህን እንድናደርግ ፈጽሞ
አልታዘዝንም … )) ብለው ንግግራቸውን ሳይጨርሱ ከወደ
አሏህ ዘንድ (( ይህን ሰው ወደ ጀሃነም መንዳቱን ተዉት !!
በዚህ የቲም ልጅ ሽምግልናና ምልጃ ምሬዋለሁ !! ))
የሚል ድምፅ ተሰማ ። ከእንቅልፌም ደንግጬ ተነሳው
ከዚያች ዕለት ጀምሮ ተውባ በማድረግ ወደ አሏህ በንሰሃ
ተመለስኩ ። ባገኘሁት አቅም በሙሉ ከዚያ ወዲህ
የቲሞችን ከመርዳት አልተወገድኩም ። )) ሲል ተናግሯል።
ይህም ሰው ኋላ ከታላላቅ ሙሐዲሶችና ዛሂዶች አንዱ
ለመሆን በቅቷል ።


https://t.me/httpsLatahzen
ማነው አላማውን አሸናፊ ለማድረግ ግምባር ቀደም ተሰላፊ ነኝ በማለት አሻራውን የሚያስቀምጥ ?
የአላህ መልእክተኛ ረሱል ሰለሏህ አለይሂ ወሰለም 3 ነገሮችን (እውነት በመሆናቸው) እምልባቸዋለሁ ብለው ከተናገሩት መካከል አንዱ:-
"የአንድ ባሪያ ገንዘብ ሰደቃ በመስጠቱ አይቀንስም" ማለታቸው ነው።
[ኢማሙ አህመድ እና ቲርሚዚይ ዘግበውታል]
እናም ሰደቃ በመስጠታችን ገንዘባችን አይቀነስብንም ።

https://t.me/resulinn
ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ፡፡

"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንድመጸውትና ከደጋጐቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ"፡፡

https://t.me/resulinn
ያ ረብ ! ይኸው ስተኛም አንተን አምኜ ተጋደምኩ፣ አንተን ይዤ ተኛሁ፣ ላንተ ሁለመናዬን ሰጥቼ ለሽሽሽ አልኩ።

አላህ ረመዷንን ደርሰው ከሚፆሙት ያድርገን!
◾️የማይሰግድ ሰው ፃም በተመለከተ


♦️የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ተቀባይነት አለውን?

ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ሸይኽ መሀመድ ሷሊህ አልኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

↪️ የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ምንም ሊጠቅመው አይችልም። አላህ ዘንድም ተቀባይነት አያገኝም። ቢፃም እራሱ እስካልሰገደ ድረስ ነገ አላህ ፊት ከመጠየቅ አይድንም። አንድ ሰው እስካልሰገደ ድረስ ፃም አለብህና ፁም አይባልም። ምክንያቱም የማይሰግድ ሰው እንደ የሁድና ነሷራ አምሳያ ነው። ታዳ የአይሁድና የነሳራ እምነት ተከታይ የሆነ ሰው ረመዷንን ቢፃም ይፈይደዋልን? ፃሙንስ አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያገኛልን? በጭራሽ ሊሆን አይችልም። ይህም ሰው ልክ እንደነሱ አምሳያ ነው። ባይሆን አንድ ሰው ሶላትን የማይሰግድ ሆኖ ሲፃም ካየነው፦ መጀመርያ ከመፃምህ በፊት ወደ አላህ ተውበት አድርግ፣ ሶላትህንም ጀምር ከዛ በኋላ ፁም ብለን እንመክረዋለን። በመፀፀት ወደ አላህ የተመለሰ ሰው አላህ ተውበቱን ይቀበለዋልና።

📚 【مجموع الفتاوى(ج20 ص87)】
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①②

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ
...

ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ላተህዘኖች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም #ላተህዘኖች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ የተወሰኑ ቤቶች ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ ፓኬጅ #1000 ብር
ግማሽ ፓኬጅ #500 ብር
ሩብ ፓኬጅ #250 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
🔺ዱቄት 🔺ሩዝ
🔺የሾርባ እህል 🔺ቴምር እና ዘይት


አድራሻ ካራቆሬ
ስልክ ቁጥር
📞 0938619117 ይደውሉልን
📞 0937442278
ወይም👇👇
''
@mamepro or @Oufeyret


Join us 👇👇👇
https://t.me/resulinn

https://t.me/resulinn

የየቲሞችን እንባ ተባብረን እናብስላቸው
እንታደጋቸው


ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም
»“ረመዷን የኸይር ወር”«

√→ እንደሚታወቀው ይህ ወር የፃም ወር ነው የበረካ የራህመት የእዝነትም ጭምር
√→ከራህመቱ ከበረካው ከእዝነቱ እናገኝና ትክክለኛ ፇሚ እንሆን ዘንድ
√↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓↓
√→ሆዳችን ከምግብ ከመጠጥ እንደሚፃም ሁላ ሌሎችንም አካላቶቻችን ሊፃሙና አላህ ሊፈሩ ግድ ይላል
√→ብልታችን ከሀራም ከዚና ሊፃም ይገባል ያለበለዛ የሆዳችን መራብ ብቻ ዋጋ የለውም
√→አይኖቻችን አጅነብይ ከማየትና ሀራም ከመመልከት ሊፃምና ሊቆጠብ ይገባዋል
√→እጆቻችን የማትፈቀድልንን ሴት እና ወንድ ከመጨበጥና በጃችን አላህ ከማመፅ ልንርቅ ይገባል
√→አፋችን ከተለያዩ ፃምን ከሚያበላሹ ወይም ምንዳን ከሚቀንሱ ነገራቶች ለምሳሌ ሰውን ከማማት፣ ከመሳደብ፣ ከመዋሸት እና ከሌሎች ሊፃም ግድ ይለዋል
√→በአጠቃላይ ሁለመናችን ፃመኛ ሊሆን ይገባል

መክንያቱም የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ይላሉ
{من لم يدع قول الزور والعمل به فليس لله حاجة أن يدع طعامه وشرابه}
(አንድ ሰው አፀያፊ ንግግርና በሱ መስራትን እስካልተው ምግብና መጠጥ በመተዉ ብቻ አላህ ምንም ጉዳይ የለውም )
በሌላ ሀዲሳቸው
{فكم من صائم ليس من صومه إلا الجوع والعطش}
(ስንትና ስንት ፃመኞች አሉ ነገር ግን ከፃማቸው ረሀብና ጥማት እንጂ ሌላ የማያገኙ) ይላሉ

https://t.me/httpsLatahzen

√→ስለዚህ ፃማችን ሀራም ከተደረጉ ነገራቶች በመጠበቅ በመልካም ስራ ልናስጌጠው ይገባል
→ቁርአን በመቅራት
→ሰደቃ በመስጠት
→ሶላቶችን በማብዛት
→ዚክሮችን በማለት
→አልቅሰን ወደ አላህ በመመለስና ለስከዛሬው ጥፋታችን መሀርታውን በመለመን
→የተቸገረን በመርዳት
→ሰዎችን በማስፈጠር እና በመሳሰሉት ኢባዶዎች ላይ በመጠንከር ልክ ረመዷን ሲወጣ አዲስ እንደተወለደ ልጅ ንፁህ ልንሆን ይገባል
→ወንጀላችን ታጥቦ
→ልባችን በኸይር ተሞልቶ
→ተስፋችን ለምልሞ
→አቂዳችን ጠንክሮ
→ኢማናችን ጨምሮ
→ከአላህ ውድ ባሮች እንሆን ዘንድ የዛሬው ጥረታችንና ልፋታችን ወሳኝ ስለሆነ በኢባዳ ላይ እንበርታ እላሉሁ
اللهم أعنى على ذكرك وشكرك وحسن عبادتك
اللهم تقبل قيامنا وصيامنا وسائر أعمالنا
ربنا آتنا في الدنيا حسنة وفي الآخرت حسنة وقنا عذاب النار