La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
((በአላህ ተመካ))

////

በቆላ በደጋ፣ ከወንድ ከሴቱ
ሁሉንም አዩሁ ከልጅ ከወጣቱ
ልሙት ይሰንጥቀኝ በጌታው ስም ምሎ
ላልከዳህ ላልከዳሽ ሲኖር ተዋውሎ
አንድ ቀን ይርቃል ተበደልኩኝ ብሎ
እናማ …
በስጋ በነፍሱ እዬተፈተነ፣አድሮ ከሚጠፋው ከፍጡራን ሁሉ
ሲያምኑት የማይከዳ፣
ሊያምኑት የሚበቃ፣ አንድ አላህ ብቻ ነው የሚገኝ በቃሉ
# ከፍያለሁ !
______
ለምፈልገዉ ሰዉ ልቤ ለከጀለዉ:
መዉደዴ ለኔ'ጅ ለሱ 'ማይታየዉ::
ዉለታ ሆኖበት የመዉደዴ ዋጋ:
ምላሹን ሊሰጠኝ ቢጀምር ፍለጋ::
ብየ ከጀልኩና ለልቤ ነግሬ:
ቀድሜ ከፈልኩኝ ቀብድ ለችግሬ::

___
# በዘሀራ ሰይድ
[[~ፅናትሽ_ማረከኝ ]]


➻የዱንያ ጌጣጌጥ ከቶ ሳያታልሽ
የዘመኑ ክፋት ወላፈን ሳይነካሽ
የአሏህን ትእዛዝ ከፊትሽ አድርገሽ
በነፃነት ካባ በሂጃብ የተዋብሽ!!

{{~አንቺ ውዷ እህቴ ፅናትሽ ማረከኝ}}

➻የውስጥ ጥንካሬሽ ተስፋ አጎናፀፈኝ
ምን እንኳን ቢጠሩሽ ሁሉም በየደጁ
ገበያ አውጥተው ሊሸጡሽ ቢያውጁ!!

➻ውድ ነኝ አልሻቸው አይደለሁ ዚቲቶ
ማንም መንገደኛ በሾለ ምላሱ በውሸት አግባብቶ
በወረደ ዋጋ ሚገዛኝ አስማምቶ!

{{~እኮ እኔ አይደለሁም ድሪቶ ዚቲቶ}}

➻Join Sher👇
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
ዓይንን (አጅነቢይ) ያልተፈቀደችለትን ሴት ከማየት መጠበቁ ከዝሙት ለመጠበቅ ፍቱን መድኃኒት ነው። ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 4 (ዚና) ዝሙት ነው። ኢስላም ምንኛ ያማርና ቀጥ ያለ ዲን ነው!! ከጎጂ ነገሮች ከመከሰታቸው በፊት መጠበቅን ያደረገለት የሆነው ዲን። የላቀው! አምላካችን አላህ (ተባረከወተዓላ) የሰው ልጆችን ከብልግና እንዲጠበቁ ወደ ብልግና ከመድረሳቸው በፊት በርቀቱ አስጠንቅቋል! ወደዛ ነገር…
ዓይንሽን (አጅነቢይ) ባዕድ የሆነን ወንድ ከማየት መከልከልሽ ከዝሙት ለመጠበቅ ፍቱን መድኃኒት ነው።
ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 5 (ዚና) ዝሙት ነው።

በአሁን ጊዜ በተለየ መልኩ ዝሙት እጅግ በጣም የተንሰራፋበት ጊዜ ነው፣ እንደሚታወቀው እስልምና ለአደጋዎች ሁሉ ቅድመ መከላከያ አድርጓል፣ በመሆኑም ከዚህ ከባድ የሆነ ወንጀል ዓይንን ሀራም ነገር ከማየት መስበር/ (አጅነቢይ) ባዕድ የሆነን ተቃራኒ ፆታን ከመመልከት ዓይንን መከልከልን አላህ በሴቱም በወንዱም ደንግጓል፣ ከዚህ ፅሁፌ በፊት ባስቀደምኩት ፅሁፌ ላይ ወንዶችን በተመለከተ የመጣውን የቁርኣን አንቀፅ በመጥቀስ ማብራሪያዎችን አሳልፌያለሁ፣ አሁን ደግሞ ሴቶችን በተመለከተ የመጣውን የቁርኣን አንቀፅ ለማየት እንሞክራለን፣ አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:–
﴿وَقُل لِلمُؤمِناتِ يَغضُضنَ مِن أَبصارِهِنَّ وَيَحفَظنَ فُروجَهُنَّ وَلا يُبدينَ زينَتَهُنَّ إِلّا ما ظَهَرَ مِنها وَليَضرِبنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلى جُيوبِهِنَّ وَلا يُبدينَ زينَتَهُنَّ إِلّا لِبُعولَتِهِنَّ أَو آبائِهِنَّ أَو آباءِ بُعولَتِهِنَّ أَو أَبنائِهِنَّ أَو أَبناءِ بُعولَتِهِنَّ أَو إِخوانِهِنَّ أَو بَني إِخوانِهِنَّ أَو بَني أَخَواتِهِنَّ أَو نِسائِهِنَّ أَو ما مَلَكَت أَيمانُهُنَّ أَوِ التّابِعينَ غَيرِ أُولِي الإِربَةِ مِنَ الرِّجالِ أَوِ الطِّفلِ الَّذينَ لَم يَظهَروا عَلى عَوراتِ النِّساءِ وَلا يَضرِبنَ بِأَرجُلِهِنَّ لِيُعلَمَ ما يُخفينَ مِن زينَتِهِنَّ وَتوبوا إِلَى اللَّهِ جَميعًا أَيُّهَ المُؤمِنونَ لَعَلَّكُم تُفلِحونَ﴾ النور ٣١
“ለምእመናትም ንገራቸው:– ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፣ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፣ ጌጣቸውንም ከርሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለፁ፣ ጉፍታዎቻችውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፣ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው፣ ወይም ለአባቶቻቸው፣ ወይም ለባሎቻቸው አባቶች፣ (ውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው፣ ወይም ለአባቶቻቸው፣ ወይም ለባሎቻቸው አባቶች፣ ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው፣ ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች፣ ወይም ለወንድሞቻቸው፣ ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች፣ ወይም ለእህቶቻቸው ወንድ ልጆች፣ ወይም ለ(ሙስሊም) ሴቶቻቸው፣ እጆቻቸው ለያዘችው (ባሪያ)፣ ወይም ከወንዶች ለሴቶች ጉዳይ የሌላቸው ለሆኑ ተከታዮች፣ ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ ላይ ለላወቁ (አካለ መጠን ላልደረሱ) ህፃኖች ለሆኑ፣ ካልሆነ በስተቀር አይግለፁ፣ ከጌጣቸውም የሚሸፍኑት ይታወቅ ዘንድ በእግሮቻቸው (መሬትን) አይምቱ፣ ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተፀፀቱ።” አንኑር 31

ይህ ከአላህ ዘንድ ለአማኝ ሴቶች የተሰጠ ትእዛዝ ነው፣ ከነቢዩﷺ በፊት ከነበሩ መሀይማንና (ሙሽሪክ) አጋሪ ሴቶች መለያ ነው፣ በመሆኑም አላህ (ተባረከወተዓላ) እንዲከለከሉ ያዘዛቸውን ከተቃረኑና ከተራቆቱ፣ እንዲሁም የለበሱት ልብስ እንዲታይላቸው መሬትን በእግራቸው እየመቱና በዘመናዊ የባለጌዎች ጫማ እያስጮሁ የሚሄዱ ከሆነ በቀደምት መሀይማን (ሙሽሪክ) ሴቶች ተመሳስለዋል ማለት ነው።
በአሁን ጊዜ ሰለጠንን ብለው የተጣበቀ ልብስ ለብሰው አንገታቸውና ጆሮ ጌጣቸውን እያሳዩ፣ ቀሚሳቸውን እስከ ቅልጥማቸው ግማሽ ድረስ አሳጥረው መሬቱን በእግራቸውና በጫማቸው እያስጮሁ የሚሄዱ ሙስሊም ሴቶች፣ የቀደምት መሀይማን (ሙሽሪክ) ሴቶችን ተግባር እየፈፀሙ እንደሆነ ይህ የቁርኣን አንቀፅ በግልፅ አስረጂ ነው። ይህ የድሮ የኋላ ቀር ሰዎች ባህሪ ከሆነ ታዲያ የቱጋ ነው ስልጣኔሽ??
እውነት ነው ውሸት ነው የሚለው እንዳለ ሆኖ፣ ሳይንስ በሚናገረው እንኳን "በድሮ ኋላ ቀር ጊዜ አልያም በዲንጋይ ዘመን የሰው ልጅ ራቆቱን ያለ ልብስ ይኖር እንደነበረና እየሰለጠነ ሲመጣ ቅጠልና ብጣሽ ጨርቅ መልበስ እንደጀመረና በደንብ ሲሰለጥን ደግሞ ሙሉ አካሉን የሚሸፍንለትን ልብስ መልበስ እንደጀመረ ነው የሚጠቀሰው" ታዲያ የአሁኑ የአንቺው ስልጣኔ የቱጋ ነው??? መልሱን ለናንተው ትቼዋለሁ።
“ለምእመናት ንገራቸው:– ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ…” ማለቱ:– አላህ ከባሎቻቸው ውጪ እይታን ሀራም ካደረገባቸው ነገር ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ! ማለት ነው። ለዚህም ነው ብዙ የኢስላም ሊቃውንቶች ሴቶች ወደ (አጅነቢይ) ባእድ ወንዶች በስሜትም ሆነ ያለ ስሜት ማየቱ ሀራም ነው የሚሉት፣ የሚከተለውንም ሀዲስ ለተጨማሪ ማስረጃነት ተጠቅመዋል:–

ከኡሙ ሰለማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ተይዞ እንዲህ አለች:
{እኔና መይሙና የአላህ መልእክተኛﷺ ዘንድ ነበርን፣ ኢብኑ ኡሚ መክቱም ወደ ነቢዩ ﷺ ገባ፣ ይህ የሆነው በሂጃብ ከታዘዝን በኋላ ነበር፣ የአላህ መልእክተኛﷺ “ከሱ ተሸፈኑ” አሉን፣ የአላህ መልእክተኛ ሆይ እሱ እውርና የማያያን የማያውቀን አይደለምን? አልኳቸው፣ የአላህ መልእክተኛﷺ “እናንተ እውሮች ናችሁን? እያያችሁት አይደለም፣” አሉ።} አቡዳውድና ትርሚዚይ የዘገቡት ሲሆን ትርሚዚይ ሀዲሱን ሀሰንም ሶሂህም ነው ብለውታል።
እህቴ ሆይ! ዓይንሽን አታቅበዝብዢው፣ በዓይንሽ እየተጋረፍሽ እራስሽንም ወንዶችንም ከከባድ ፊትናና ዝሙት ላይ ከመጣል ተጠንቀቂ ተሸፋፍነሽ ኒቃብ እንኳን የለበሽ ብትሆኚ አጅነቢይ ወንድ ማየት ሀራም እንደሚሆንብሽ ያሳለፍነው የቁርኣን አንቀፅና ሀዲስ ግልፅ የሆኑ አስረጂዎች ናቸው፣ ዓይንሽን ያልተፈቀደልሽን አጅነቢይ ወንድ ከማየት ከልክያት! ይህ ብሊትሽን ለመጠበቅና ያለ ቦታው ከማራከስና ኢስላም ውድ ያደረገውን ገላሽን ያልሆነ ቦታ ላይ በሀራም አውጥተሽ ከመጣል የሚያግድሽ ጠንካራ የሆነ አጥር ነውና ተጠንቀቂ
===በአላህ ፈቃድ!===ይቀጥላል…

Nurahemd Muhammed

share and join ማድረግ እንዳይረሱ 👆👆
https://t.me/httpsLatahzen
የመጨረሻ ክፈል ዝሙት

ሁላችሁም ሼር እንድታረጉ በአላህ ስም እጠይቃለሁ

አላህ (ተባረከ ወተዓላ) ያይኛል ይሰማኛል ብሎ በልብ ውስጥ እምነትን ማስቀመጥ ከዝሙት ለመጠበቅ ሌላው ፍቱን መድኃኒት ነው።

ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 6 (ዚና) ዝሙት ነው።

እንደሚታወቀው ዝሙት በዚህን ዘመን ላይ እንደከባድና አውዳሚ፣ ዘርን የሚያበላሽና የሰው ልጆችን መልካም ስነ–ምግባር የሚያበላሽ ወንጀል እንደሆነ ሊታወቅና ሊታመን ቀርቶ፣ በተቃራኒው እንደ ሀላል እየታየና ሀላሉ የኒካህ ጋብቻ እንደ ሀራምና ኋላ ቀርነት እየታየ ነው ታዲያ ከዝሙት የመራቂያና የመጠንቀቂያ መፍትሄዎችንና መድኃኒቶችን በሚገባ መጠቀም ግዴታ ነው!
አላህ (ሱብሃነሁወተዓላ) በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነን ወንጀልን መዳፈር እንደሌለብን ሲያስጠነቅቀን የትኛውም ቦታ ላይ ብንሆን እንደሚያየን በተለያዩ የቁርኣን አንቀፆች ነግሮናል: ከነዚያም ውስጥ የሚከተለውን አንቀፅ መመልከት ይቻላል:–
﴿إِنَّهُ يَعلَمُ الجَهرَ مِنَ القَولِ وَيَعلَمُ ما تَكتُمونَ﴾
“እርሱ ከንግግር ጩሀትን ያውቃል። የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል።” አል አንቢያእ 110
ይህ አንድ ሰው በምላሱ በሚናገረው ከሆነና በልቡ ውስጥ የደበቀውን ሸር ሁሉ የሚያውቅ ከሆነ በግልፅ በአካሉ ሀራም ነገር ሲሰራ፣ እንደ ዝሙት ያለ ፀያፍ ብልግና ሲሰራ አላህ ከላይ እንደሚያየው ጠንቅቆ ካወቀና ካመነ ከዝሙትም ሆነ ከሌሎች ወንጀሎች ሊቆጠብ ፍቱን መድኃኒት ይሆነዋል።
የትኛውንም መልካም ስራችንን ስንሰራ አላህ እንደሚያየን አድርገን እንድንሰራ ነቢዩ ﷺ በሶሂህ ሀዲሳቸው ተናግረዋል: ኢህሳን ማለት “አላህን ልክ እንደምታየው አድርገህ እንድታመልከው ነው፣ አንተ ባታየው እንኳን እርሱ ያይሃል” ብለዋል።
ይህ እንግዲህ መልካም ስራችንን ስንሰራ አሳምረን እንድንሰራና ከመጥፎ ነገሮችም እንድንጠነቀቅ የሚያደርገን ሐዲስ ነው። በሌላ ሐዲሳቸው የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከወንጀል እንድንጠነቀቅም እንደሚከተለው ተናግረዋል:– “በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነህ አላህን ፍራ!…።” ብለዋል።
አዎ! የትኛውም ቦታ ላይ ያለ ሰው ነፍሲያውና ሸይጧን ማንም የሚያውቅህና የሚያይህ ሰው የለም፣ ይህ ቦታ እኮ ጨለማ ነው ብለው ወደ ወንጀል ሲጎተጉቱት፣ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረ፣ የምራመድበትን እግሬን የፈጠረ፣ አለምን ሁሉ የፈጠረ፣ አካሌን ሁሉ የፈጠረ፣ ጨለማና ብርሃንን የፈጠረው አላህ ያይኝ የለም እንዴ? ብሎ ሊመልስና ሊመለስ ይገበዋል!!
ይህ ከሆነ በድብቅ ከ(አጅነቢይ) ባእድ ተቃራኒ ፆታዎች ጋር በየ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወደ ዋናው ዝሙት የሚያዳርሱ ፅሁፎችን መፃፃፍ ይቀራል፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተቃራኒ ፆታዎችን ፎቶዎችንም በድብቅ እያዩ መመሳሳጥ ይቀራል፣ በድብቅ ተቃራኒ ፆታን ማየት ይቀራል፣ ሰዎች በሌሉበት ገጠመኝ ተቃራኒ ፆታዎች ቢገናኙ እንኳን ወደ ሀራም የሚያዳርሳቸውን ነገር ሁሉ ይርቃሉ፣ ምክንያቱም ማንም ባያያቸው እንኳን አንድ ከባድ የሆነ የሚፈሩትና የሚያመልኩት ከደም ስራቸው የበለጠ ቅርብ የሆነው አምላካቸው አላህ እንደሚያያቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ እርሱንም በሚገባ ይፈሩታል፣ ከማንም በላይ ያፍሩታል! ለነፍሲያቸውና ለሸይጧንም ጨለማ ቦታ ላይ "ጨለማ እኮ ነው ማንም አያይህም/ሽም" ሲሉት፣ ጨለማን የፈጠረው አላህ ያይኛል ብለው መልስ በመስጠት ከሀራም ይቆጠባሉ።
ሀያሉ!! አምላካቸው አላህ እንደሚያያቸው በልባቸው ውስጥ እምነትን ካሳደሩ፣ በተከበረውና በተለይ መልኩ የ(ተውበት) ወደ አላህ ተፀፅቶ የመመለሻ ወር በሆነው የረመዷን ወር ላይም ከቤተሰባቸው በተራዊህ አሳበው ወጥተው ተደብቀው ጨለማንና የተለያዩ ድብቅ ቦታዎችን ተገን በማድረግ ዝሙት ከመፈፀም ይቆጠባሉ
አዎ! ከቤተሰብ ብትደበቅም/ብትደበቂም አላህ ያይሃል/ያይሻል! ከፍጡራን በጠቅላላ ተደብቀህ/ሽ ወንጀልን ብትሰራም/ብትሰሪም ለትንሽ ጊዜ ተውበት አድርገህ/ሽ ወደ አላህ ቶሎ እንደምትመለስ/ሽ ቢታገስህ/ሽ ነው እንጂ፣ አላህ የምትደበቃቸው/የምትደበቂያቸው ሰዎች ፊትም ያጋልጥሃል/ሻል፣ የዛኔ አኼራ አዱኒያህ/ሽ ምስቅልቅሉ ይወጣል
ከሁሉ በላይ ትልቁ ፀጋ አላህ ያይኛል ይሰማኛል ብሎ ከሀራም ነገሮች መጠንቀቅና ባእድ የሆኑ ተቃራኒ ፆታዎችን ከማየትም አይንን ሰበር ማድረግ ነው!!! ስለ ሰዎች ከመጨነቅህ/ሽ በፊት ስለ አላህ ተጨነቅ/ቂ!! ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ቢያወሩትም በቃ አበቃለት/ላት ተባለሸ/ች ብለው ይተውታል፣ የአላህ ቅጣትና ቁጣ ግን ለቀጣዩም ዘላለማዊ አለም የሚቆይ ነው
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! አላህን ፍሩ የኒካህ መንገዶችን ቀላል አድርጉ!! ዝሙትን ከሞትና ከእሳት በላይ ፍሩት! ራቁት ተጠንቀቁት
﴿وَلا تَقْرَبُوا الزِّنَى إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلاً﴾ الإسراء ٣٢
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ ፀያፍ/(ብልግና ነውና)፡ መንገድነቱም ከፋ!" [ኢስራእ: 32]
===ተፈፀመ ፡፡
Nurahemd Muhammed


https://t.me/httpsLatahzen

share share
((በአላህ ተመካ))

////

በቆላ በደጋ፣ ከወንድ ከሴቱ
ሁሉንም አዩሁ ከልጅ ከወጣቱ
ልሙት ይሰንጥቀኝ በጌታው ስም ምሎ
ላልከዳህ ላልከዳሽ ሲኖር ተዋውሎ
አንድ ቀን ይርቃል ተበደልኩኝ ብሎ
እናማ …
በስጋ በነፍሱ እዬተፈተነ፣አድሮ ከሚጠፋው ከፍጡራን ሁሉ
ሲያምኑት የማይከዳ፣
ሊያምኑት የሚበቃ፣ አንድ አላህ ብቻ ነው የሚገኝ በቃሉ


https://t.me/httpsLatahzen
ጁምአ ነነነነነነው
*****

አንዳንድ ቀን አለ
ቃል ሳይናገሩ በአይን የሚያግባባ
ከራህመት አውድማ ጎትቶ ሚያስገባ
የመዳንን ጥሪ ልቆ ሚያስተጋባ
አንዳንድ ቀን አለ
በቀናት መሀከል ተማግሮ የቆመ
ከወፎች ቅላፄ ዜማ የቀመመ
በብርሃን ጣቶቹ መንገድ የጠቆመ
ከሙት ሰልፍ አውጥቶ ህልው የሚዘራ
ወደ ፅድቅ ደጃፍ ኡመት የሚጣራ
አንድ አንድ ቀን አለ
እንደ ጁምዐ ያለ



https://t.me/httpsLatahzen
«አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሒ ወበረካቱሁ እንዴት ናችህ ያጀምአ ወንድሜ በጣም ታሟል ኩላሊቱና ጉበቱ መታጠብ አለበት ተብለን በጣም ተቸግረናል በገንዘብም በዱአም በፓስትም እህት ወንድሞች አንዲረዱን ለመጠየቅ ነው እንድታግዙኝ እፈልጋለሁ ሁለት ኩላሊቱ ከጥቅም ውጪ ነው ጉበቱ ባይረስ አለበት ሳንባው ውሀ ቋጥሯል ተብለን በጣም ፈተና ላይ ነን በሳምንት 3ግዜ እየታጠበ ነው በወር 36ሺ ነው ምናወጣው አላህ በሚያቀው አቅሙ የለንምና ለአላህ ብላችሁ ለወንድሜን ድረሱለት አላህ ያለው ነው ሚሆነው ግን የሰውልጅ ተስፋ አይቆርጥምና ሰበቡን ለማድረስ ነው ካርድም የሚሸጥ አለ የታተመ ልታወሩኝ ከፈለጋችሁ 0919325101 ደውሉልኝ።» የምትችሉ ሁሉ ተባበሯቸው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①∅

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
«የታለች ልእልቷ »!!

➻ውብ ፅጌሬዳ የፈካሽ አበባ
በጥሩ መአዛ በውዴታሽ ልግባ
የጌታሽ ፍራቻ አሣምሮሽ የኖርሽ
እሡን ለማስደሠት ሲሆን ጥረትሽ
ሁሌ ትደምቂያለሽ እንዳበባ ፈክተሽ!!

➻መልክና ቁንጅና በማይጠቅመው ቤትሽ
ስትሞሸሪ አንቺ በጀነት ውስጥ ገብተሽ
ጥንቁቅ እና ትሁት በድምር ላይ ሆነሽ
አሣልፊው በቃ ምንዳውን ከጅለሽ!!

➻የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፉ እኮ አንቺ ነሽ
ትዛዙንም ስሚ ክልከላውን እራቂ
የአሄራን ህይወት እንዲያምር ሠንቂ
እሳት እንዳገቢ በጣም ተጠንቀቂ!!

➻እውነት ነው ይመጣል ልብወለድ አይደለም
ተነግሮናል እና ልብ በይ እህት አለም
ለሚያልፍ ኑሮ ለዚች አጭር ጊዜ
ምነው ባንኳትን እንደው እንዳአባዜ
በዱኒያ ነገር ባይበዛ ትካዜ!!

➤Join sher👇
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
🕌አላህ ቃል የገባቸው
4⃣ ነገሮች
ማወቅ ያለብህ እናም መቼም ልንረሳው የማይገባ

🔶 ያመሰገናችሁኝ
ከሆንእጨምርላችዋለው

🔶 አስታውሱኝ
አስስታውሳችውዋለው

🔶 ለምኑኝ እሰጣችዋለው

🔶 አላህን አንዳቸውንም
አይቀጣም መሀርታውን
እስከ ፈለገ ድረስ
ሌላውም ሰው ይውቅ ዘንድ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ሼር ያርጉ
.
.

https://t.me/httpsLatahzen

nur
ኢላሂ

ይቅር በለኝ ልልህ ቆሜ ባፈርኩህ ሰአት
ሲናገሩ ሰማሁ የአንተን ግዙፍነት
ወንጀሉ ያሳፈረዉ ባርያህ እጅ አንስቶ
ማረኝ ሊልህ አፍሮ ማረኝ ሊልህ ፈርቶ
ከደጅህ ላይ ቆሞ ብትመለከተው
አንተም መቅጣት አፋረህ ይቅርታን ሸለምከው
ኢላሂ ......


https://t.me/httpsLatahzen
የካሜራ ነገር
Sadat
⤴️⤴️ የካሜራ ነገር


🎤Bustaze Sadat Kemal
Abu Meryem
(
#حفظ_الله)

⤴️⤴️ የካሜራ ነገር
ሰላት ኡምራ፣ ዱኣ፣ ሰደቃ፣ ሰርግ፣ ሚዜ፣ ምርቃት !!

ጭራሽ ደግሞ ሌላ ጉድ ልንገራቹ፦በፎቶ ሾፕ ፎቶ መነካካት ፎቶ ሾፕ የሚባል ሶፍት ዌር አለ አላህ አሳምሮ ነው አይደል የፈጠረን ነው እንጂ ፎቶ ቤት ያሉ ሰዎች ምን ያደርጋሉ ፎቶ ያነሱህና እንዳለ በቃ ቡጉር አትቀር ምን አትቀር ሙልጭ አድርጎ በሶፍት ዌሩ አጥፍተውት የተወለወለ ሌላ ሰው ያስመስሉሃል¡! በዚህም የተነሳ የብዙ ሰዎች ትዳር እየተናጋ ነው! በተለይ ውጪ ሃገርና እዚህ ሃገር ያሉ ሲተዋወቁ ፎቶሽን ላኪልኝ ፎቶህን ላክልኝ ይባባሉና የ50 ሽማግሌ የ25¡¡ አመት ጎረምሳ ሆኖ ቁጭ ይላል!ሴቷም እንደዛው! አላሁል ሙስታዓን!! ከዛ ልክ ወደ ትዳር ከገቡ በኃላ አረ እኔ እንዲህ አልመሰልሽኝም ነበር ፎቶ የላክሽው ትዝ አይልሽም?? ምናም ይባባላሉ¡! ሹፍ ጨዋታ አስለን ለትዳር በፎቶ አይደለም!

https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
የእናትህን አምሳያ አታገኝም!
ልጅ እያለህ ታመህ ወደ ሀኪምቤት ትሄድ ነበር። ሀኪሙ "ምን ይሰማሃል?" ብሎ ሲጠይቅህ ፡ መልስ መስጠቱን ትተህ የእናትህን ዓይን ትመለከታለህ፤ መልስ እንድትሰጥልህ። ምክንያቱም ላንተ የሚሰማህ የህመም ስሜት ለርሷም እንደሚሰማት እርግጠኛ ነህና!
እናም ወላሂ
የርሷን ዓይነት አታገኝም!!!
=~~~
"""እማመቅረዜ""""

አይኖችሽ ከሰማይ ይመሳሰላሉ፣
እምቅ ዝናብ አዝለው ጸሀይ ያወጣሉ፣
ሰማይና ልብሽ ሁለቱ አንድ ናቸው፣
ሺህ ጊዜ ተሰብረው ጠባሳም የላቸው፣
እንደ ሀምሌ ሰማይ ውስጥሽ ብዙ እምባ አለ፣
ብቻሽን ማልቀሻ ጓዳ በማጣትሽ ውስጥሽ፣ የታጀለ
ባለ ብዙ ሀዘን ባለ ሺህ መከራ፣
የልብሽ ፍጥረቱ ላዘን የተሰራ፣
እማ የኔ መቅረዝ የደስታዬ ባህር፣
የመጽናናቴ ምንጭ ዛሬን የመሻገር፣
ሰው ያላየው ጥበብ ቢኖርሽ ነው እንጂ፣
ከሀዘን ባህር ውስጥ ደስታን የምትቀጂ፣
     ┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄👇

https://t.me/umuzefa123456
*ጠያቂ ነኝ እኔ*

ያስቀየምኩት ካለ፣በስካሁን ቆይታ
ያስከፋሁት ካለ፣በእኔ ልቡ ደምታ
በአላህ ስም በሉኝ፣ከልባቹ ይቅርታ

ደካማ ፍጡር ነኝ፣በስራዬም ዘንጊ
በማላቀዉ ነገር፣የሰዉ ስሜት ወጊ
ይሆናል ባላልኩት፣ጭራሽ ባልገመትኩት
ጎድቼ ይሆናል፣የአንዳቹሁን ስሜት
ግና አዉቄዉ ባይሆንም፣ክፋትም አስቤ
ይቅር በሉኝ እና፣ይሰብሰብ ሃሳቤ

ለአላህ ብዬ፣ሁሉን እወዳለው
ወላሂ፣ከልቤ፣አፍ ብያቹሃለሁ

ቅርም ያሰኘሁት፣በምሰራዉ ስራ
ያበገንኩት ካለ፣ሊነግረኝ የፈራ
አዉፍ እንድትሉኝ፣እላለዉ አደራ
ማንን እንዳስቆጣዉ፣ከቶ አላዉቅ እኔ
እንዲያዉ በደፈና፣ይቅር በሉኝና ይረፍልኝ ጎኔ።



ኑርhttps://t.me/httpsLatahzen
>>> አፈውቱ . . . <<<


አፍህን አዳልጦት እሱም አፉ ገድፎ
የፍቅራችሁ ፀዳል ከራማው ተገፎ
ቂም በቀል ይዛችሁ የምትቋሰሉ
ፍቅር ሰላም ይሁን አውፍ ተባባሉ::
አፈውቱ ... አፈውቱ
ተዉ አንሁን ከንቱ ! ...
ዘመን ጉልበት ሰጥቶት ክንዱን አበርትቶ
አቅመ ቢስ ደካማን በግፍ አንገላቶ
ዘርፎ!... ነጥቆ!... ሰቅሎ!...
አስሮ!... ገርፎ!... ገሎ!...
በድንቁርናው ልክ ስንቱን አመሳቅሎ
ወገን የበደለን ያን ጭንጋፍ ሙትቻ
የዘመን እንቅፋት የሰው አራሙቻ
ክስረቱን ቆጥራችሁ ግፉን በርብራችሁ
እጥፉን ልትከፍሉት ደግሞ በተራችሁ
ሰይፍ የምታፋጩ ጎራዴ የምትስሉ
ግዴላችሁም ተውት ይቅር ተባባሉ
በፍቅር ወስፈንጥር ጥላቻን ግደሉ! . . .
አፈውቱ ... አፈውቱ...
በሉ አፈውቱሊላ (ህ)
እንረስ በደቦ፣
ባንድ ማእድ እንብላ::
ደግሞም ያንን ርካሽ
ጉማጅ የሰው ብጣሽ! ...
ዘር ቀለም ሃይማኖት ስር እየመዘዘ
የፍቅርን ሰንሰለት እየገዘገዘ
ያብሮነትን ዋርካ እየመዘመዘ
የአድባሩን ሸንጎ ባፉ እየመረዘ
ሃቅና ቅጥፈትን ባንድ እየበረዘ
ሲዳክር ሲባዝን ለክስረት ሲለፋ
ሽቅቡን ሲወጣው ተያይዞ ሊጠፋ ...
አይታችሁ ብትበግኑ ውስጣችሁ ቢቃጠል
በነፍጥ አታድርጉት አውድሙት በቅጠል!...
ምግባሩን ነው እንጂ ተውት የሱን ገላ
ርካሽ ነው ርካሽን በርካሽ 'ሚበላ
ይሁን እድል ስጡት ይቁረስ አንድ እንጀራ
ደንዳናው ልቦናው በፍቅር ቢገራ ...
የከበደው ሰማይ ያ የቂም ደመና
ያልፋል በይቅርታ ሳያደርገን መና . . .
ይቅር በል!
ይቅር በይ!
በቃ አፈውቱሊላ (ህ)
አይርከስ
አይፍረስ
የጎጇችን ባላ::


https://t.me/httpsLatahzen