La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ለምን ይሄ ሁሉ ትርምስ ?

በአላህ የትነት ላይ “ከዐርሹ በላይ ነው፣ “ኣይ ሁሉም ቦታ ነው እና ጭራሽ የትም አይደለም የሚሉ እጅግ የተራራቁ አቋሞች ተንፀባርቀዋል። ልዩነቶቹ የተካረሩ የሆኑበት ሰበብ ርአሱ መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ የተነሳ ነው። ግን ሸሪዐው ገላጋይ መፍትሄ ባይኖረው ነወይ ይህን በሚያከል ጉዳይ ላይ ልዩነት የተከሰተው? በጭራሽ! ስለ ሽንት ቤት አጠቃቀም ዝርዝርመመሪያ ያሰቀመጠ ሃይማኖት፣ ይህን በሚያከል ትልቅ ጉዳይ የማያሻማ መልስ አይኖረውም ብሎ _ማሰብ ኢስላምንም፣ቁርኣንንም፣ ነብያችንንም ፣ ሶሐቦችንም ያላግባብ መጠርጠር ነው። አላህ (ዛሬ ሃይማታችሁን ሞላሁላችሁ) ካለ አስራ አራት ክፍለ ዘመናት አለፉ። ነብዩም [ሌሊቱ እንደ ቀኑ ግልፅ የሆነ ጎዳና ላይ ነው የተውኳችሁ) ማለታቸው ይሰመርበት። (ኢብኑ ማጃህ 43] [ኣልሙስተድረከ ሓኪምቁ 331

ስለዚህ ሃይማኖቱም ሙሉ፣ ጉዳዩም ግልፅ ነው ማለት ነው። (ከዐርሹ በላይ ገፅ 10)

አ/አ አንዋር መስጂድ አጠገብ አት ተውባህ መክተባ ያገኙታል ይግዙ ፣ ለወዳጅ ዘመድዎ ስጦታ ያበርክቱ
https://t.me/Umu_Meryem/4096
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑤

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ⑥

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
በአርሽ ጥላ ስር የሚጠለሉ 7 አይነት ሰዎች
አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
خُطْبَةُ الْجُمُعَةِ
የጁሙዓ ኹጥባ

سَبْعَةٌ يُظِلُّهُمُ اللهُ في ظِلِّهِ يَوْمَ لاَ ظِلَّ إلاَّ ظِلُّهُ
ሰባት አይነት ሰዎችን ከአሏህ (ከ"አርሽ") ጥላ ዉጭ ሌላ ጥላ በሌለበት ቀን በጥላዉ ያጠልላቸዋል።

🕌 ደሴ አል-አዝሐር መስጂድ

📅 يوم الجمعة 24 رجب 1443 الموافق 25/02/2022

🎙አቡ ረይስ ሙሀመድ ኢብኑ ኢማም
🌿🌿አንተ ወጣት ሆይ ንቃ🌿🌿 !!!


ከአጅነቢዮች ያለክ ግንኙነት በሰፋ ቁጥር ወደ መጥፎ የምታመራበት መንገድ ይገዝፋል፡፡...ከአጅነቢዮች ያለህን ግንኙነት በቀነስክ ቁጥር ወደ "ፋሂሻ " የምታመራበት መንገድ ይጠባል፡፡
☞በደውልም ይሁን በፅሁፍ ከአጅነቢይ ሰው ማውራት ካዘወተርክ ..ልብክ ላይ ኒፋቅ በቅሎ ወደ አላስፈላጊ እርከን ትሸጋገራለህ ...በአይናችን እያየን ..በጆሯችን እየሰማን ነው .. የት ይደርሳሉ የተባሉ ወንዶች ከሴቶች ባላቸው "ዐላቃ" የተነሳ ነው ውርደትን የሚከናነቡት °° #አንቺም ቢሆን እንደሱ ከወንዶች ጋር ያለሽ ቅርርቦሽ ለከት ሊኖረው ይገባል ...አለዚያ ውርደትሽ እሩቅ አይደለም .. ውስጥ አዋቂው አላህ ሁሉንም እያየ ዝም ያለሽ ምናልባት ትመለሺ ይሆናል ብሎ እንጂ አለዚያ በአይ ጨረፍታ አንችን የመያዝ ችሎታ አጥቶ አይደለም፡፡

#ኸልዋ ወደ መጥፎ ነገር ከሚመሩ ነገራቶች ዋነኛው ነው ..በታክስ ..በመንገድ ..በቤት #በየትኛውም አጋጣሚ አንድ ወንድ እና አንድ ሴት ብቻቸውን ከሆኑ ..ሸይጧን ሶስተኛቸው ነው ፡፡ ®__ሸይጧን ሶስተኛው ከሆነ አካል ላይ መልካም ነገር አይፈጠርም .. ፡፡

☞በተለይ ዲን ተገንዝቧዋል ከሚባል አካል ይህን ቆሻሻ ተግባር መመልከት ልብ ያደማል ...ወንገኔ ሆይ ንቃ ተደብቀህ ብሰራው ውስጥ አዋቂው አላህ አደባባይ ያወጣብሃል .. ችላ ሲልህ አላህ እያዘናጋህ መሆኑን አትዘንጋ ፡፡

አላህ እኔንም ቤተሰቦቼን ወዳጆቼን ..ሁሉንም ሙስሊም አካል ከዚህ አስነዋሪ ስራ ይሰውረን ፡፡
https://t.me/httpsLatahzen
_አሚን_

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድ
አንተ እፈር እንጂ እኔ አንገት አልደፋም
******

ዕጣ ክፍሌን በሞጣ አስፍ
ህይወቴን ከአንተ ጋር፣ በአንድነት አጣምሮት
ያለ አንዳች ክፋት፣ በጎ ሳልም ኖሬ
ምን አጊኝቶህ ይሆን፣ ያስጨከነህ ዛሬ

ደራሼ የምልህ፣ ቅርብ ጎረቤቴ
ደጋፊዬ ያልኩህ፣ አበርታች ጉልበቴ
መልካሙን ምሻልህ፣ የህይወቴ አጋር
ምን ሸይጣን አክፍቶህ፣ አደረሰህ ’ኔ ጋር

አንድ ነገድ ሆነን፣ አንድ ሀገር ተወልደን
አንድ ቋንቋ አውርተን፣ ከአንድ ወንዝ ቀድተን
እልፍ ዘመን ኖረን፣ በሰላም አንድ ላይ
ምን አስበህ ይሆን፣ የከፋህ በእኔ ላይ

እኮ ለምን በእኔ! ይሄንን አደረክ?
እኮ ለምን ዛሬ! ከሰውነት ወረድክ?

ያዘው ቢሉኝ እሳት፣ ቤተ መቅደሱን
ለማዳን ስሯሯጥ፣ ለማጥፋት ጭሱን
አንተ የእኔን ንብረት፣ የቻልከውን ዘርፈኽ፣ በእሳት አንድደህ
በኾታ በልልታ፣ በጭፈራ አነጋህ፣ ሰውነትኸን ክደህ

ለይተህ ማጥቃትን፣ ሙስሊም በመሆኔ
እንዴት ግን አስቻለህ፣ እሳት መስደድ በእኔ
አላህን ማምለኬ፣ ላንተ ሆኖ ጥፋት
ከአውሬ ብሶ ታየ፣ የልቦናህ ክፋት

አዎ!
ህመሙ ከባድ ነው፣ ያደረስከው ጉዳት
ጠባሳው አይሽርም፣ ወገኔ ነው ባሉት፣ ባመኑት መከዳት
አፀፋን መመለስ፣ የሚያስችል ጉልበት፣ አቅም ቢኖረኝም
እምነቴ ቂም በቀል፣ ጎሜና ጥላቻን፣ አላስተማረኝም!

የትላንት በደልህ፣ ማንን እንዳስቆጣ
በል እየው ተመልከት፣ ከምሽግህ ውጣ
ብቸኛ ነው ብለህ፣ የመዘዝክብኝ ጦር
እህት ወንድሞቼን፣ ተመልክተህ እፈር

አንተ ቅርቤ ሆነህ፣ እያወከኝ እኔን
ሀዘን ስታወርሰኝ፣ ስትነጥቀኝ ቀኔን
ሳያዩኝ ሳያውቁኝ፣ ስቸገር ሚረዱኝ
ሙስሊም ወንድም እህት፣ እልፍ አዕላፎች አሉኝ

ተመልከት በርሜሉን፣ ምን እንደ ተሞላ
ገንዘብ እንዳይመስልህ፣ ፍቅር ነው ጠቅላላ
እኔን ቀና አርገው፣ አንተን ሊያሳፍሩ
ብር እየለገሱ፣ ፍቅር ነው የጨመሩ

የሚሰጠው አ’ቶ፣ ምርኩዙን የቸረ
አለ በታሪኬ፣ ደምቆ የሰፈረ
ገቢዋን ልትለግስ፣ ምትቸረችር ቡና
ተመልከተው ፍቅሯን፣ በኢስላም የፀና
መጓጓዣ ሳይክል፣ ይቅርብኝ ለምኔ
ያለውንም እየው፣ አስቀደሞ ለእኔ

ሊስትሮ በመሆን፣ ጫማ እየጠረጉ፣ ብር ያሰባሰቡ
ጀግኖቼን ተመልከት፣ ዝቅ ብለው ውለው፣ ከፍ ያለ የከሰቡ
የጆሮ ጉትቻ፣ ሳታስቀር የአንገቷን
የእጇንም አንባር፣ የጣት ቀለበቷን
አራግፋ የሰጠችኝ፣ ለኔ ፍፁም አዝና
እህቴን ተመልከት፣ ታሪኬናትና
ባዶ ሲሆንበት፣ ሲዳብሰው ኪሱን
አውልቆ የቸረኝ፣ አለ ወርቅ ጥርሱን
በመስጂዶች ሁሉ፣ በመንገድ ላይ ሳይቀር፣ በገበያም ቦታ
አዝኖልኝ ከልቡ፣ ሰብስቦ ሲቸረኝ፣ ተመልከት ውዴታ
በየ ክፍለ ሀገሩ፣ በየ ከተሞቹ፣ በየ አህጉራቱ
ፍቅርን ሲያድሉኝ፣ ተስፋን ሲመግብኝ፣ አስተውል በብርቱ
ከዓለም ጫፍ እስከጫፍ፣ መበደሌን ሰምተው
የቻሉትን ሁሉ፣ ያለስስት ሰጥተው
ከጎኔ የቆሙን፣ ወንድም እህቶቼን፣ በእፍረት ተመልከት
ማንን እንዳስቆጣህ፣ ማንን እንደነካህ፣ አስተውል በጥልቀት
ሀገርን የሚያፈርስ፣ ኃላ ቀር ክፋትን፣ ሰርተህ በጨለማ
ሀገሩን ሚወደው፣ ፍቅር ዘርቶ ዋለ፣ ስልጡን ሙስሊም ዑማ

አዎ!
ህመሙ ከባድ ነው፣ ያደረስከው ጉዳት
ጠባሳው አይሽርም፣ ወገኔ ነው ባሉት፣ ባመኑት መከዳት
አፀፋን መመለስ፣ የሚያስችል ጉልበት፣ አቅም ቢኖረንም
ኢስላም ቂም በቀልን፣ ጎሜና ጥላቻን፣ አላስተማረንም!።


https://t.me/httpsLatahzen

ከሥርህ ተቀምጦ ነገር ሚያነፈንፍ
ታሪክህን ደልዞ ታሪኩን የሚፅፍ
ቢሞላም በምድር ከአፅናፍ እስካፅናፍ
እጅ ሳትሰጥ ጀግን ለእውነት ተሰለፍ
ታሪክህን ሰርተህ ታሪክ ሁነህ እለፍ
ታሪክህ ቢደለዝ ቢሰረዝ ከስር መሰረቱ
ከስር ስርህ ሄደው ሴራም ቢዶልቱ
መውጣቱ አይቀርም ሲገለፅ እውነቱ
የእጅህ አሻራ የያኔው የጥንት የጠዋቱ
ታሪክ በሌለበት ታሪክ እንድትሰራ
እውነትን ተጋፈጥ እውነትን አትፍራ
ቢሰል ነው እንጂ ከቶ አይበጠስም
እውነተኛ ታሪክ በሀሰት አይፈርስም
ታሪክህ ቢቀበር አንተ አትወቀስም
ፅልመቱ ተገፎ ብርሀን እንዲጎላ
ታሪክህን አትርሳ ታሪክን አትጥላ
እውነትን ቀብረሀት ህርሟንም አትብላ
መውጣቷ አይቀርም መቃብር ፈንቅላ
ታሪክን አጉድፈህ እንዳትሆን የታሪክ አተላ።

Semira Aman

https://t.me/httpsLatahzen
🦋💌 ልብን በሀሴት የምትሞላ ግጥም
ተጋበዙልኝ ውዶች 🦋💌

🌙❤️🌙 ተናፋቂው ጀነት! 🌙❤️🌙


አላህ ያዘጋጀው ለሷሊህ ባሮቹ
ነቢን ለታዘዙ ለአመሥጋኞቹ
አላህ ያዘዘውን ለመስራት ሚሮጡ
ከተከለከሉት ምንም ለማይመርጡ
በሱ መንገድ ኖረው በሀቅ ለሞቱ
ቆመው ለለመኑት በስውር ሌሊቱ
ፊርደውስን ወፍቀን ሲሉ ለጠየቁ
መዋቧን ገምተው በወርቅና በእንቁ
አይን አይቶት የማያውቅ እጅጉን ያማረ
ለጆሮም አዲስ ነው ጥንት ያልተነገረ
በወንዝ እና ጅረት በማር እና ወተት
በብርዝ ና በወይን በተዋቡ እፅዋት
ደምቆ ና ተውቦ እስከ ጥግ ድረስ
የአላህ ባሮችን ሰብስቦ የሚያነግስ
ጭንቀትና ጥበት ሀሳብ የሌለበት
ትካዜ እና ድብርት የማይሰማበት
ረሀብ የሌለበት ሁልጊዜ እርካታ
ልብን የሚሞላ በሳቅ እና ደስታ
ጀነት የተባለ እፁብ ድንቅ ቦታ
ለሙእሚኖች ሆነ ተገቢ ስጦታ
አላህን ተገዝተው እሡን ከታዘዙ
ያላንዳች ማመንታት መንገዱን ለያዙ
🌹ተናፋቂ ሆነ በልቦቻችን ውስጥ
እርጋታና ደስታን አብዝቶ የሚሰጥ!!🌹

Nur

Join and Give us comment

https://t.me/httpsLatahzen
📌በእውቀት ላይ ትኩረት እናድርግ!!
የእውቀት ደረጃው የላቀ ነው!!📌

ታላቁ ዓሊም ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል-ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:

ኢማሙ አህመድ (ረሂመሁላህ) አንዲህ ብለዋል:- "ኒያው ለተስተካከለችለት ሰው እውቀትን አንዳች ነገር አይወዳደረውም!። የኒያ መስተካከል ሲባል እንዴት ነው ተብለው? ተጠየቁ፣ መሃይምነትን ከራሱና ከሌሎች ማስወገድን መነየቱ ነው።" አሉ።

ምክንያቱም ልክ አንተው ላይ በመሰረቱ መሃይመነት እንደነበረብህ ሁሉ በሌሎች ላይም የመሃይምነት መሰረቱ ስላለ ነው። መሃይምነትን ከዚህ ማህበረሰብ ለማስወገድ ብለህ ከተማርክ፣ የአላህን ዲን ከሚያሰራጩ በአላህ ዲን ላይ ከሚታገሉ ሰዎች ሆነሃል። [ኪታቡል ዒልም 23]

እውቀት ያለው ሰው በፊትና ጊዜ ንፋስ እንደሚያወዛውዘው ዛፍ ከመሆን ይልቅ ቆም ብሎ ነገሮችን በማስረጃ ይፈትሻል!።
ትክክለኛ እውቀት ያለው ሰው ፊትናዎች በተከሰቱ ቁጥር ጎርፍ ጠራርጎ እንደሚወስደው ግሳንግስ አይሆንም!።

እውቀት ያለው ሰው በተለያዩ ፈተናዎች ጊዜ ለራሱ ሀቅ ላይ ፀንቶ ሌሎችንም እንዲፀኑ በተሰጠው እውቀት ጥረት ያደርጋል!።

እውቀት ያለውና በእውቀቱ በትክክል የተገበረ ሰው ደረጃ የላቀ ነው!። የጥልቅ እውቀት ባለ ቤት የሆነው አምላካችን አላህ እንዲህ ብሏል:-

قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ

«እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?፣ በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው፡፡»
አዝ-ዙመር 9

በተቻለን መጠን በጊዜያችን በአግባቡ እንጠቀም!፣ እውቀትን ከትክክለኛ ሱኒይ ዓሊሞች እንቅሰም። እውቀት ማግኛ መንገዶች ብዙ ናቸው (ተመቻችተዋል!)፣ ነገር ግን እውቀት የሚፈልጉ ሰዎች በጣም አንሰዋል።

ስለ እውቀት ቢወራ በቀላሉ የሚያልቅ አይደለም!፣ በዚህ ርእስ ብቻ የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንቶች የተለያዩ ሙጀለድ፣ሙጀለድ የሚሆኑ ኪታቦችን ፅፈዋል። ለምሳሌ ያህል:- ጃሚዕ በያኒል ዒልሚ ወፈድሊሂ: ኢብኑ ዐብዱልበር። ኪታቡል ዒልም ሸይኽ ሙሀመድ ኢብኑ ሷሊህ አል-ዑሰይሚን። ፈድሉል ዒልም ሸይኽ ረስላን…
አላህ ጠቃሚ እውቀትን ይወፍቀን።
➬➬➬➬
https://t.me/httpsLatahzen
احرص على ما ينفعك
➲በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ!!
➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬➬

➠‟ክፍል˝አንድ[⓵]

بسم الله الرحمن الرحيم
‟ምስጋና ለዓለማት ጌታ ለአላህ ይገባው ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ
የሌለ መሆኑን ሙሐመድም የአላህ አገልጋዩና መልክተኛው መሆናቸውን
በእርግጠኝነት እመሰክራለሁ የአላህ ሶላትና ሰላምታ በሙሐመድ በቤተሰቦቻቸው
እና በአጠቃላይ በባልደረቦቻቸው ላይ ይስፈን፡፡
የክብር ባለቤት የሆንከው አላህ ሆይ! ጠቃሚ የሆነውን ትምህርት አስተምረን
ባስተማርከንም ትምህርት ተጠቃሚዎች አድርገን ከእውቀት ላይ እውቀትን
ጨምርልን የተማርነውን ትምህርት ለእኛ ማስረጃ እንጅ በእኛ ላይ ማስረጃ
አታድርግብን‼️

➲ከዚህ በመቀጠል
የተከበራችሁ ወንድሞቸ ሆይ!ዛሬ የምንነጋገረው ነብዩ صلى الله عليه وسلم በተናገሩት አንድ ቃል
ዙሪያ ነው፡፡ እርሱም፡-
⬅️„احرص على ما ينفعك واستعن بالله"
♻️“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ እገዛንም ከአላህ ብቻ ፈልግ፡፡”
📚(ሙስሊም፡2664)

➠ ‟ይህ ንግግራቸው የተወሰደው ከሚከተለው ኢማም ሙስሊም ከዘገቡት አቡሁረይራ
رضي الله عنه
ካስተላለፉት ትክክለኛ
ሐዲስ ውስጥ ነው፡፡
⬅️"المؤمن القوي خير وأحب إلى الله من المؤمن الضعيف ، وفي كل خير ، احرص
على ما ينفعك واستعن بالله ولا تعجز ، وإن أصابك شيء ، فلا تقل لو أني فعلت
كان كذا وكذا ، ولكن قل قدر الله وما شاء فعل، فإن لو تفتح عمل الشيطان"
“ከአላህ ዘንድ ጠንካራው አማኝ ከደካማው አማኝ የተሻለና በጣም ተወዳጅ ነው
ከሁሉም ዘንድ ግን መልካም አለ በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ እገዛንም
ከአላህ ብቻ ፈልግ ደካማ አትሁን አንድ ነገር ከገጠመህ ይህን ብሰራ ኖሮ እንዲህ
እንዲህ ..... ይሆን ነበር ብለህ የቁጭት ንግግር አትናገር ነገር ግን “አላህ የፈለገውን ሰሪ
ነው አላህ የወሰነው ደግሞ ተፈጻሚ ይሆናል” በል “ለው” (ወይኔ!) ያለችው
(የቁጭት ቃል) ለሰይጣን ተግባር በር ትከፍታለች፡፡”
📚(ሙስሊም፡2664)

➲ ‟የእውቀት ባለቤቶች ግልጽ እንዳደረጉት ይህ ሐዲስ ከረሡል صلى الله عليه وسلم አጠቃላይ
ንግግራቸው መካከል ሲሆን በውስጡ በርካታ ጠቃሚና መሰረታዊ ነገሮችን ሰብስቦ
ይዟል፡፡
በዚህ ሰዓት በሚከተለው የነብዩ صلى الله عليه وسلم ንግግር ላይ ትንታኔ በመስጠት ብቻ
እንቆያለን፡፡

እርሱም ፡- ➴➴
⬅️"احرص على ما ينفعك واستعن بالله"
🔺“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ፤ እገዛንም ከአላህ ብቻ ፈልግ፡፡”
📚(ሙስሊም፡2664)

ይህ የነብዩ صلى الله عليه وسلم ቃል የሰው ልጅ ለዱንያውም ይሁን ለአኼራው እድለኛ
የሚሆንበት ሁለት ታላላቅና ጠንካራ መሰረቶችን ያቀፈ ሐዲስ ነው፡፡

➮አንደኛው፡- “በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ” የሚለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ቃል ነው፡፡
ይህ የረሡል صلى الله عليه وسلم ቃል የሰው ልጅ ለዱንያውም ይሁን ለአኼራው በሚጠቅመው ነገር
ላይ ሰበብ ነገሮችን ማስገኘት እንዳለበት እና በእርሱም ላይ ተነሳሽነቱ ሊኖረው
እንደሚገባ የሚጠቁም ነው፡፡

➮ሁለተኛው፡- “በአላህ ታገዝ፡፡ የሚለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ንግግር ነው፡፡ በዚህ ንግግራቸው
ውስጥ ደግሞ ሰበብ በሆኑ ነገሮች ብቻ መደገፍ በቂ እንዳልሆነ ይልቁንም አንድ ሰው
ሰበብ ነገሮችን ለማስገኘት ሲንቀሳቀስ የአላህን እገዛ በተሟላ ሁኔታ መፈለግ እና
በእርሱ ብቻ መመካት እንዳለበት የሚያሳስብ ሐዲስ ነው፡፡
“በሚጠቅምህ ነገር ላይ ፍላጎቱ ይኑርህ” በሚለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ንግግር ደግሞ ጠቃሚ
ለሆኑ የዱንያ ጉዳዮች መንቀሳቀስ እንደታዘዝን ሁሉ ጠቃሚ በሆኑ የአኼራ ጉዳዮችም
መንቀሳቀስ እንዳለብን የሚያስረዳ ነው፡፡
🔺ስለዚህ ይህ ሐዲስ በዱንያውም ይሁን በዲኑ
ጥቅም ለሚያስገኙ ነገሮች ሁሉ ፍላጎቱ ኖሮት መንቀሳቀስ እንዳለበት ያስረዳል ማለት
ነው፡፡ ይህን ፍላጎቱን ተፈጻሚ ለማድረግ ደግሞ ትክክለኛ እና ቀጥ ያሉ መንገዶችን
ወይም ሰበቦችን መፈጸም በዚህ መካከል ወደሚፈልገው ታላቅ አላማው ለመድረስ
ከፍተኛ የነፍስ ትግልና የአላህ እገዛ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ ምክንያቱም ብልሃትም
ይሁን ሐይል የአላህ እንጅ የማንም አይደለም አላህ የሻው ይሆናል አላህ ያልሻው
ደግሞ አይሆንም፡፡

➻ኢንሻአሏህ
ይቀጥላል........

🖊ኑር

🔺አንብብ ማንበብ የተሻለ ሰዉ ያደርጋል የመረዳት ችሎታህ ይጨምራል‼️
___
https://t.me/httpsLatahzen
መንዙማ መፀሀፍ.pdf
2.5 MB
┈••✿❒ 📚 መንዙማ 📚❒✿••┈
[እውነታዎቹ ፣ አደጋዎቹ እና መዘዞቹ ]

ኡስታዝ ሳዳት ከማል
አልበያን_ጀምዒያ፣_ሱሪና_የተብዲዕ_ህግጋት.pdf
2 MB
┈••✿❒ 📚 አልበያን 📚❒✿••┈
[ጀምዒያ፣ ሱሪና የተብዲዕ ህግጋት]

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
ተውሂድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ.pdf
102.7 MB
📚 ተውሒድ የሁለት ሃገር 📚
የስኬት ቁልፍ

ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር
የረሳነው መስታዎት
~~
°
አካህ ተውቦ
ገፅታህ አብቦ
ሰውነትህ ደምቆ
መልክህ አሸብርቆ

መደነቅ ያማረው፣
መኮፈስ ያጓጓው፣
መስታወት ያሰኘው፣
‘እየኝ’ ያለህ ’ለታ፣
እፍኝ አፈር ዘግነህ ተመልከት በጌታ!!
ተመልከት በአላህ!
ተመልከት በቃሉ
ቋንቋ ብሄር ሰጥቶ ቢያግባባህ ጀሊሉ
ዘር እየመነዘርክ ትጎራለህ አሉ!

ወንድማለም!
እስኪ
ተመልከት ከጭቃው፣ ተመልከት ከምድሩ
አንተን አንተን ይላል፣
ዘመድ ከዘመዱ ሰውም ከ አፈሩ!

መልክህ ረጋፊ ነው፣
ቀለምህ ጠፊ ነው፣
ቋንቋህ አላፊ ነው፣
ብሄርህ ትርፍ ነው፣
አካልህ ፈራሽ ነው፣
ዋናው ማንነትህ አፈር ነው ጭቃ ነው።


ወንድሜ!
እስኪ አትንጠራራ
አትደርስም ተራራ!
እስኪ አትንገዳገድ
ምድር ላትሰረጉድ
አፈር ነህ ያ’ፈር ልጅ
የግም ጭቃ ውላጅ!

አፈር ነው መነሻህ
አፈር ነው መድረሻህ
አፈር መጀመሪያህ አፈር መጨረሻህ
ነገም ከ አፈር ነው ዳግም ’ምትወጣ
እንደተበተነ እንደ መንጋ አንበጣ!!

ከጭቃ ተሰርቶ፣
ከጭቃ ተነስቶ፣
በቆሻሻ መውጫ ሁለት ጊዜ ወጥቶ፣
መሬት አይንካኝ ሲል
በኩራት ሲፏልል፣
በትእቢት ሲሸልል፣
አይደንቅም ወይ ከቶ!!
አይ የሰው ልጅ!!

(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሃሴ 29/2011)
እስኪዘጋ ድረስ…
===========

ነግቷል ክፈቱልኝ!
መሽቷል ኑ ዝጉልኝ!
ለማይባል ሀገር፤ ሳለሁ ተሰልፌ፣
በቀናት ዝርዝር ዉስጥ፤ ቀን ጉዴን ታቅፌ፣
አለሁኝ እያልኩኝ፤
እንደሌሎች ሁሉ፤ ይደርሳል ማለፌ።
መካካድ ሲወደስ፤ መማማል ሲደራ፤
መታመን ሲነወር፤ መናጠቅ ሲያኮራ፣
አማኝ እየካደ፤ ሲሄድ ፊቱን ዞሮ…
ሀቅ ተሸርጥጦ፤ ስንቱ ናላዉ ዞሮ፣
እኔንም ተጋብቶኝ፤ ያለም ትርፍራፊ፣
ባንዱ ላይ ገንኜ፤ ስልሰዉ በጥፊ…
ለካ እራሴዉ ነኝ፤ የኔ ራሴ አጥፊ።
ማቅለል እየቻልኩኝ፤ የሚታለፍ ነገር፣
በጄ እየሸረብኩ፤ እየፈተልኩ ሳከር…
ነግቷል ክፈቱልኝ!
መሽቷል ኑ ዝጉልኝ፤
ለማይባል ሀገር፣ ወረፋ ስጠብቅ፤ ቆሜ ተሰልፌ…
ቀብር ጋደም ስል፤ ሰሌኔን አንጥፌ፣
ምስጥ ይልሰኝ ጀመር፤ የጄ የመዳፌ፤

ኑር
https://t.me/httpsLatahzen
⇠الحياء زينة المرأة وجمالها
👑ልዕልቷ👑
#የሀያዕ ብቻ ሣይሆን የኢማን እና የተቅዋም ንግስት ሁኚ ሀያዕ ሀያዕ ሊሆን የሚችለው የኢማን እና የተቅዋ ልብስን ሲለብስ ነው እና!
https://t.me/httpsLatahzen
🎊🦋 ይቺን አጂብ የምታስብል ታሪክ ተጋበዙልኝ🎊🦋

❤️የባህሩ ሰውየ እና ሞት❤️

በአንድ ወቅት አንድ ባህር ላይ የሚሰራ ሰው ይኖር ነበር! ከዛም ስለ ቅርብ ህይወቱ የሚያውቅ አንድ ተሳፋሪ እንዲህ አለው!

ሰውየው፣ አባትህ የት ነው የሞተው?
የባህሩ ሰው፣ ባህር ላይ ሲሰራ
ሰውየው፣ አያትህስ?
የባህሩ ሰው፣ ባህር ላይ ሲሰራ
ሰውየው፣ በንዴት አየጮኸ "ባህር ሁለቱንም አሳጥቶህ አሁንም ባህር ላይ እንዴት ትሰራለህ" አለው?
የባህሩ ሰው፣ ፈገግ አለና "እስኪ አንተ አባትህ የት ላይ ነው የሞተው "አለው?
ሰውየው፣ አልጋ ላይ
የባህሩ ሰው፣ አያትህስ?
ሰውየው፣ አልጋ ላይ ነው የሞተው
የባህሩ ሰው፣ ከሞቱ በዃላ እንዴት አልጋ ላይ ትተኛለህ? አለው
ሰውየው፣ ዝም አለና መንገዳቸውን ቀጠሉ!!!

❤️ዋናው ሀሳቡ ምንድን ነው፣ አንድን ነገር ለመስራት ባሰብክ ጊዜ በአላህ ላይ ተወኩል አድርግ ፣ ህይወት ቢያጨናንቅህ ከአዋቂ ሰዎች መላ ጠይቅ!

በአላህ ላይ ተወኩል አድርገህ ስራህን ከሰራህ ኢንሻ አላህ አላህ ይረዝቅሃል፣ ወፍ በንስሮች መካከል ሆና አላህ እንደሚረዝቃት፣እርቧት ወጣ ጠግባ እንደምትመለስ አስታውስ!!❤️

ተቀላቀሉን👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
🌙🦋 ብቸኝነት ለሚሰማቹ ወዳጆቼ
በሙሉ ይችን ግጥም ተጋበዙልኝ!!🌙🦋

❤️ አላህ ይበቃሃል!! ❤️


የሰው ልጅ ቢሸሽህ ከቶ ምን ቢርቅህ
ጭንቀትን ተካፋይ ሰዎች ቢጠፉብህ
አለም ጠባብ ሆና እንባ ብታስነባህ
ዱንያ ፈታኝ ሆና ሞትን ብታስመኝህ
በሰዎች ተከበህ ሰዎች ቢናፍቁህ
የበታች አድራጊ ስሜቶች ቢሰሙህ
ያኔ...... ታስባለህ ብቸኛ እንደሆንክ
ሁሌ ማይተውህን አላህን ዘንግተክ
በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ትዘዋወራለህ
እድለቢስ ሰው ነኝ ብለህ ታስባለህ
አንዴ አድምጠኝ እማ እስኪ ልጠይቅህ
ወደ ዱንያ ፈጥሮህ ማን ነበር ያመጣህ
እስከ ዛሬ እለትስ ማን ነበር ያኖረህ
አይብህን ሸፍኖ ያበላህ ያጠጣህ
አንዱ ጌታ እኮ ነው ህይወትን የሰጠህ
በፈለገው ሰአት ይችላል ሊነጥቅህ
ስለዚህ ወገኔ አንድ እሱ ይበቃሃል
ባላሰብከው መንገድ እልፍ ይረዝቅሃል
ለሰው ሳትጨነቅ ለፍጡር ውዴታ
በአላህ ተብቃቃ በአለማት ጌታ
አላህ ከወደደህ አላህ ካቀረበህ
ፍጡራን ቢጠሉህ ከቶ አይግረምህ
ምክንያቱም እሱ ሁሉን አዋቂ ነው
ብቻህን ማየተውህ አዛኝ ፈጣሪ ነው
እሱን አታስከፋ ለፍጡራን ደስታ
በኢባዳዎች ላይ ሁሌም ተበራታ
ወላሂ በቂህ ነው የአለማቱ ጌታ
ሁሌም የማይተውህ ሳይዘነጋ ላፍታ!!

Nur

ተቀላቀሉን👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
🛑 አንድ ጊዜ ቻቱን አቁሙና ይችን
ጠቃሚ አጭር ታሪክ ተጋበዙልኝ!🛑

🦋ከእለታት አንድ ቀን አንድ ህፃን ልጅ አያቱን እንዲህ ይላታል "አያቴ! ሁሉም ነገር ያስጠላል፣ ትምህርት፣ቤተሰብ፣ችግር፣የጤና መቃወስ፣ከጓደኛ ጋር መጣላት፣ድህነት ብቻ ሁሉም ያስጠላል!!"🛑አላት።

ከዛም አያትየው ኬክ እየጋገሩ ነበር እና ቀና ብለው እንዲህ አሉት"ኬክ ትወዳለህ?"ልጁም አዎን እወዳለሁ አላት። እሷም ጥያቄዋን እንዲህ ስትል ቀጠለች
" ዘይት መጠጣት ትወዳለህ? ልጁም "አይ"
እሺ" ጥሬ እንቁላል መብላትስ?" ልጁም "በጣም ያስጠላል እሱም" አላት፣
እሺ "ዱቄት መቃምስ አለችው?" "ኧረ ደስ አይልም"ሲል መለሰ ልጁ

ከዛም አያትየው እንዲህ አሉት"አየህ አደል ልጄ እንዚህ የሚያስጠሉ ያልካቸው ነገሮች አንድ ላይ ተደባልቀው ነው ጣፋጭ ኬክ መስራት የሚችሉት ፣ህይወትም እንደዚህ ናት መራራ እና የሚያስጠሉ የሚመስሉ ነገሮች አንድ ላይ በስርአት ሲቀናጁ ውጤታቸው ያማረ ይሆናል፣ ስለዚህ ሁሉም ነገሮች አንድ ላይ በትክክለኛው መንገድ እና ሰአት መስተካከል አለባቸው!!!🦋

🦋ስለዚህ መልእክቱ ምንድን ነው ወገኔ ትምህርት አሊያም ስራ ወይም ትዳር አስጠላኝ አትበል ሁሉንም በትክክለኛው መንገድ እና ሰአት ከአላህ ጋር ለማስኬድ ሞክር🦋

ተቀላቀሉን👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen