La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
በፍጡር መማል
~~~~
በፍጡር መማል ከሺርክ ነው የሚመደበው። እንደ አካባቢውና ባህሉ በተለያዩ ፍጡሮች የሚምሉ ሰዎች አሉ። ለምሳሌ ያክል፦
1. “አባቴን”፣ “እናቴ ትሙት” እያለ የሚምሉ አሉ። ነብዩ ﷺ ግን {አዋጅ! አላህ፡ በአባቶቻችሁ እንዳትምሉ ይከለክላችኋል። የሚምል በአላህ ይማል። ያለበለዚያ ዝም ይበል} ይላሉ። [ቡኻሪ፡ 6108፣ ሙስሊም፡ 4346]
2. “ሸሆቹን”፣ “ሸህ እከሌን”፣ “ሐጂ እንትናን” እያለ የሚምል አለ። ነብዩ ﷺ ግን በሸይኽ ቀርቶ {አንዳችሁ በመሲሑ (በዒሳ) ቢምል አደጋ ላይ ወድቋል። መሲሕ ግን ከአባቶቻችሁ የበለጠ ነው} ይላሉ። [አልሙሰነፍ፡ 12278]
3. “እንዲህ ካደረግኩኝ እኔ ክርስቲያን ነኝ!” እያለ የሚምል አለ። ነብያችን ﷺ ግን {ከኢስላም ውጭ ባለ ሃይማኖት መሀላ የማለ (ለምሳሌ 'ይህን ካደረግኩ እኔ ክርስቲያን ነኝ!' ያለ) እንዳለው ሆኗል (ከኢስላም ወጥቷል)!} ይላሉ። [ቡኻሪ፡ 1363፣ ሙስሊም፡ 315]
4. በከዕባ የሚምሉም አሉ። ነብያችን ﷺ ግን ከዚህ ተግባር ከልክለዋል። [ሶሒሑ ነሳኢይ፡ 3782]
5. “ነቢን” የሚሉ፣ በዶሪሕ (በመቃብር) የሚምሉም ብዙ ናቸው። ውዱ ነብይ ﷺ ግን {በአባቶቻችሁ፤ በእናቶቻችሁና ያለአግባብ ሰዎች ለአላህ ብጤዎች ወይም አቻዎች አድርገው በሚይዟቸው አትማሉ። በአላህ እንጂ አትማሉ። እውነተኞች ሆናችሁ እንጂ አትማሉ} ይላሉ። [ሶሒሑል ጃሚዕ፡ 7249]
6. “የልጅነቴ አበባ ይርገፍ”፣ “ከፊትህ ይነጥለኝ”፣ “የናቴን አጥንት”፣ “የናቴን ቀን ይስጠኝ” እያሉ የሚምሉ ሞልተዋል። ድንጋይ በእጁ በመምታት፣ ጠመንጃ በመራመድ፣ ቆቲ (የአበጋር ብትር) በመራመድ የሚምልም አለ። ታማኙ ነብይ ﷺ ግን {ከአላህ ሌላ ባለ ነገር የሚማል መሀላ ሁሉ ሺርክ ነው} ይላሉ። [አሶሒሐህ፡ 2042] በሌላ ሐዲሣቸውም {ከአላህ ሌላ ባለ የማለ በርግጥም ክዷል ወይም አጋርቷል} ይላሉ። [ኢርዋእ፡ 2561]

እዚህም እዚያም እንደዋዛ የምንሰማቸው ወጣ ያሉ መሃላዎች አደጋቸው ምን ያክል የከፋ እንደሆነ ተመልከቱ። ነገሩ ምን ያክል ከባድ እንደሆነ ከሶሐቦች ንግግር መረዳት እንችላለን። ዐብዱላህ ብኑ መስዑድ ረዲየላሁ ዐንሁ “እውነት ተናግሬ ከአላህ ሌላ ባለ ከምምል ውሸት ተናግሬ በአላህ ብምል እመርጣለሁ” ይላሉ። [ኢርዋእ፡ 2562] ኢብኑ ዐባስም እንዲሁ “አንድ ጊዜ ከአላህ ሌላ ባለ ምዬ እውነት ከምናገር መቶ ጊዜ በአላህ እየማልኩ ብወነጅል እመርጣለሁ” ይላሉ። [ሸርሑ ሙስሊም፣ነወዊይ፡ 11/105] ሱብሓነላህ! ሺርክ ምን ያክል አደገኛ ጥፋት ቢሆን ነው እንዲህ አይነት አስፈሪ ነገር የሚናገሩት?!
♦️ሱፍያነ ሰውሪይ ረሂመሁላህ እንዲህ ይላአሉ:-

"ላኢላሀ ኢለላህ ከሚለው ቃል የበለጠ የሰይጣንን ወገበ የሚቆርጥ የለም"

[ሲየር አእላሚ ኑበላእ (7/260)]
♦️ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይምያህ (ረሂመሁላሁ)

"ለሸሪአ ተፃራሪ የሆነን ሸይኽ የወደደ ከሱጋር ይሆናል ሸይኹ እሳት ቢገባም ከሱጋር (አብሮ ይገባል)"

[መጅሙኡል ፈታዋ (315)]
↪️የረመዳን ወር በመቃረቡ ምክንያት ምን ትመክራላችሁ⁉️

🎙ሸይኽ ዶ/ር ሷሊሕ ኢብኑ ፈዉዛን አል ፈዉዛን ሐፊዘሁሏሁ


♦️አንድ ሙሰሊም አላህ ለረመዳን ወር እንዳያደርሰዉ እና አድርሶትም ፆሙ ላይ ሰግደቱ ላይ እና ሌሎች አምልኮዎች ላይ አላህ እንዲያግዘዉ አላህን መለመን አለበት።

🔺ምክንያቱም ይህ ወር በአንድ ሙሰሊም ህይወት ዕድል ነዉ።ረሱል /እንዲህ አሉ:-ረመዳንን አምኖ እና ምንዳዉን ከአሏህ ከጅሎ የፆመ ያለፈዉ ወንጀሉ ይማርለታል።

♦️ረመዳንን አምኖ እና ምንዳዉን ከአላህ ከጅሎ የሰገደ ያለፈዉ ወንጀሉ ይማርለታል።

🔻ሰለዚህ ይህ ወር ላይመለሰ የሚችል ዕድል ነዉ።

♦️ሙሰሊም የሆነ ሰዉ ረመዳን ሲመጣ ይደሰታል፣ተሰፋም ያደርጋል በደሰታ ነዉ የሚቀበለዉ፣እድሉን
በደንብ በአላህ ትዕዛዝ ላይ ነዉ
ሚያሳልፈዉ።

🔺ሌቱን በመቆም፣ቀኑን በመፃም ቁርዓን በመቅራት እና አላህን በማሰታወሰ ነዉ የሚያሳልፈዉ።
ትልቅ ዕድል ነዉ።

♦️ነገር ግን አንዳንዶቹ ግን ሙሰሊሞችን ለማዘናጋት ረመዳን ሲደርሰ አዘናጊ ፕሮግራሞችን
ፊልሞችን፣ዝባዝንኬዎችን፣ዉድድሮችን የሚያዘጋጁ አሉ።

🔻እነዚህ የሸይጣን ወታደሮች ናቸዉ። ሸይጣን ነዉ ለዚህ ተግባር ያዘጋጃቸዉ።

♦️አንድ ሙሰሊም የሆነ ሰዉ ደግሞ ከነዚህ ሰዎች እና ከተግባሮቻቸዉ መጠንቀቅ አለበት።

🔺ረመዳን የፈንጥዝያ፣የጨዋታ የፊልም፣የዉድድር ወር አይደለም።🖊

↷ ⇣🌹⇣↷
📌ማንቂያ!!!

#ሙቅ ውሃ "በየቦታው ስለ ማፍሰስ"


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


#ሸይኽ ኢብን ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ ፡
ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ #ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ በመፍራት ነው !

መልስ፡-

"አዎን! 👉 #ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ እንዲነቃ ለማድረግ ነው

" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም #በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ ነበር ።

#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን ያዝከው "አለው
#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ

#የሚቀራው ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን ስላላወቀ ነው" አለው

#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው(እንዲያነቃው)"

#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ (ረሂምሁሏህ) እንዲህ አሉ ፡-

"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ አይደፋም ምክንያቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች!!

ምናልባትም #በጂኖች አለም ወይም #በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።

📌ስለዚህ አንድ ሰው #የሞቀን ውሃ መድፋት ከፈለገ #በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር እስኪሆን ያብርደው ከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ፣ ከፈለገ መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ!
፟፟======================================================
#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች በዚህ ሰበብ ችግር ውስጥ ይገባሉ !
ውሸትን የደዕዋ መሳሪያ ከማድረግ መጠንቀቅ
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
ወንድሜ ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቅ! ሙብተዲዕ ነው ብለህ በምታምነው ሰው ላይ እንኳ ፈፅሞ አትዋሽ። ደዕዋ ላይ የተሰማራህ ስትሆን ደግሞ ይበልጥ ጥንቃቄ ይኑርህ። የዳዒያህ ውሸታም አደጋው ከሌሎች ውሸታሞች የከፋ ነው።
1- ውሸት ልፋቱን ከንቱ ያደርጋል። ለደዕዋ እየለፋ ዞሮ በየመሀሉ ሆነ ብሎ ውሸትን የሚሰነቅር ከሆነ እየፈጩ ጥሬ ነው የሚሆው።
2- ውሸት መቋጫ የሌለው ድርብርብ ወንጀል ላይ ይጥላል። በተለይ ውሸቱ በደዕዋው ላይ የሚንፀባረቅ ከሆነ (ለምሳሌ፦ ሰዎችን ዋሽቶ የሚወነጅል ቢሆን) ያ ውሸቱ ባሳደረው ጥፋት ሁሉ ተጠያቂ ይሆናል። በሱ ውሸት የተነሳ ደዕዋ ቢደናቀፍ፣ የሰዎች ስም ቢጎድፍ፣ ሰዎች ለኢስላም ወይም ለደዕዋው ያላቸው እይታ ቢበላሽ፣ ሰዎች ከኸይር ቢርቁ፣ በቀጥታ በራሱ ውሸችም ይሁን በሱ የውሸት ውንጀላ በተሸወዱ ሰዎችም ይሁን በየትኛውም መልኩ ሌሎች ላይ ጉዳት ቢደርስ የውሸቱ ጠንሳሽ ላይ ድርብርብ ወንጀል አለበት።
3- የውሸት ፀያፍነት ሰዎች ዘንድ ቀልሎ እንዲታይ ያደርጋል። ሸይኽ ወይም ኡስታዝ እከሌ እንዲህ የሚዋሸው ጉዳዩ ያን ያህል ከባድ ባይሆን ነው የሚል ሸፋፋ ሂሳብ የሚሰራ ሊያጋጥም ይችላል።
4- ውሸታም ሌሎች የዳዕዋ ሰዎችን ያስንቃል። የጥፋት አንጃዎች ዘንድ መሳለቂያ ያደርጋል። የዑለማእ፣ የዱዓት መናቅ ደግሞ ትምህርታቸው ተቀባይነት እንዲያጣ ያደርጋል።
5- ውሸታም ለሌሎች ክፉ ምሳሌ ይሆናል። አስተማሪው ሲዋሽ የተመለከተ ሰው ነፍሲያ በጎተጎተው ቁጥር ያለምንም ጥንቃቄ ሊዋሽ ይችላል። ውሸታም አስተማሪ ውሸታም ተማሪዎችን ያፈራል። ይሄ ደግሞ አጠቃላይ ደዕዋው ላይ ከባድ ጉዳት ነው የሚያደርሰው። ምክንያቱም የተቀየመውን ሁሉ በረድና ተሕዚር ስም ዋሽቶ ለማጠልሸች የማይመለስ መንጋ ይተካልና።
ወንድሜ ሆይ! አስተውል! ተውሒድ በሺርክ፣ ሱና በቢድዐ፣ እውነት በሀሰት አይታገዝም። ዲንን ለማስተማር ብለህ አታዋሽ። ዲንህ የውሸትን እርዳታ የሚፈልግ አይደለምና። አጥፊን ለማስጠንቀቅ ብለህ አትዋሽ። ሳትዋሽ ከአጥፊ ማስጠንቀቅ ካልቻልክ ከምታለማው የምታጠፋው ይበዛልና ይቅርብህ። አትሸወድ! የበደለኛን በደል በሌላ በደል አስቆማለሁ ማለት አጥፎቶ መጥፋት ነው። ተያይዞ ገደል! የትም ቦታ ቢሆን ፍትህ መጠበቅ አለበት። አላህ እንዳስፈላጊነቱ ከሀ*ዲዎችን ከፍ ስል በመሳሪያ ዝቅ ሲል በደዕዋ እንድንዋጋቸው አዞናል። ከመሆኑም ጋር ፍትህ እንዳናዛባ አሳስቦናል። ይሄውና አደራው፦
(یَـٰۤأَیُّهَا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ كُونُوا۟ قَوَّ ٰ⁠مِینَ لِلَّهِ شُهَدَاۤءَ بِٱلۡقِسۡطِۖ وَلَا یَجۡرِمَنَّكُمۡ شَنَـَٔانُ قَوۡمٍ عَلَىٰۤ أَلَّا تَعۡدِلُوا۟ۚ ٱعۡدِلُوا۟ هُوَ أَقۡرَبُ لِلتَّقۡوَىٰۖ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَۚ إِنَّ ٱللَّهَ خَبِیرُۢ بِمَا تَعۡمَلُونَ)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ሁኑ፡፡ ህዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ (ማስተካከል) ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው፡፡" [አልማኢዳህ፡ 8]
እወቅ! ውሸት ተራ መስሊሞችም ላይ ቢሆን ፀያፍ ከመሆኑ ጋር ነገር ግን የሙስሊም መሪዎችና ዑለማዎች ላይ ሲሆን ክብደቱ ይጨምራል። ምክንያቱም በተራ ሙስሊሞች ላይ ከመዋሸት የከፋ ውጤት ያስከትላልና። ውሸቱ በአላህና በነብዩ ﷺ ላይ ሲሆን ደግሞ የበለጠ አደገኛ ይሆናል። የአንድን ሙስሊም ክብር የሚያጠለሽ ውሸት ተሻጋሪ ጉዳት ከሌለው ውሸት የከፋ ነው። በህዝብ ላይ፣ በደዕዋ ላይ ጉዳት የሚያስከትል ውሸት ደግሞ በግለሰብ ላይ ጉዳት ከሚያደርሰው ውሸት የከፋ ነው። ስለዚህ በጣም መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
እና እልሃለሁ! ለሱና እከላከላለሁ ብለህ አትዋሽ! ቢድዐን እዋጋለሁ ብለህ አትዋሽ። ያለበለዚያ ይበልጥ ቆሻሻ ጥፋት ውስጥ እየተነከርክ ነው። ሸይኽ ረቢዕ - ሐፊዘሁላህ - እንዲህ ይላሉ፦
الكذب أخبث من البدع يا إخوان والكذَّاب أخبث عند أهل السنة من المبتدع المبتدع يروى عنه, رَوَوْا عن القدرية رَوَوْا عن المرجئة ورَوَوْا عن غيرهم من أصناف أهل البدع ما لم تكن بدعة كفرية ما لم يكن كذابا. لو كان ينتمي إلى أهل السنة كذَّاب فهو عندهم أحط من أهل البدع .
ومن هنا عقد ابن عدي-رحمه الله- في كتابه "الكامل" حوالي تسعة وعشرين باباً للكذَّابين([1]) وبابًا واحداً لأهل البدع .
وقَبِل أهل السنة رواية أهل البدع الصادقين غير الدعاة .
"ውሸት ከቢድዐ ይበልጥ ቆሻሻ ነው፣ ወንድሞች። ውሸታም የሱና ሰዎች ዘንድ ከሙብተዲዕ የከፋ ቆሻሻ ነው። ሙብተዲዕ ከሱ ይዘገባል። (የሐዲሥ ምሁራን) ከቀደሪያ ዘግበዋል። ከሙርጂአ ዘግበዋል። ከሌሎች የቢድዐ አራማጅ አይነቶችም እንዲሁ። ይህም ቢድዐው ክህደት የሚደርስ እስካልሆነና ዋሾ እስካልሆነ ድረስ ነው። ይሁን እንጂ አንድ ውሸታም እራሱን ወደ አህለ ሱና የሚያስጠጋ ቢሆን እንኳ እሱ እነሱ ዘንድ ከቢድዐ ሰዎች በታች ናቸው። ለዚህም ነው ኢብኑ ዐዲይ - ረሒመሁላህ - አልካሚል በተሰኘው ኪታባቸው ውስጥ ሙሸታሞችን በተመለከተ ሃያ ዘጠኝ ርእሶችን ሲሰጡ፣ የቢድዐ ሰዎችን በተመለከተ ግን አንድ ርዕስ ብቻ መስጠታቸው።"

ልብ በሉ! ውሸትና ውሸታሞች ፀያፍ የሚሆኑበትን ገፅ አጉልተው ለማሳየት እንጂ ይህን ማለታቸው እንዳጠቃላይ ቢድዐውን እንደ ኢስላም መቃረቢያ አድርጎ የሚቆጥረው ሙብተዲዕ የከፋ ወንጀለኛ መሆኑ የሚያከራክር አይደለም።
ፅሁፌን የምቋጨው በተከታዩ የነብዩ ﷺ ሐዲሥ ነው፦
"وإيّاكم والكذِبَ، فإنّ الكَذِبَ يَهْدِي إلَى الفُجُورِ، وإِنّ الفُجُورَ يَهْدِي إِلَى النّارِ وَمَا يزَالُ العبْدُ يَكْذِبُ وَيَتَحَرّى الكَذِبَ حَتّى يُكْتَبَ عِنْدَ الله كَذّابا".
"ውሸትን አደራችሁን (ተጠንቀቁ)። ውሸት ወደ አመፅ ይመራልና። አመፅ ደግሞ ወደ እሳት ይመራል። አንድ ሰው ከመዋሸትና ውሸት ላይ ከማተኮር አይወገድም አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ እስከሚመዘገብ ድረስ!" [ቡኻሪና ሙስሊም]
==
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor

ወደ ዋናው ፔጅ ገብቶ ለማንበብ
ከ4 ወር በፊት አካባቢ የተፖሰተ

https://t.me/IbnuMunewor/2457
Audio
ስለ ረመዷን ወሳኝ ትምህርት
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

የትምህርቱ ርዕስ፦➴➴➴
አህዋሉሰለፍ ፊረመዷን (የሰለፎች ሁኔታ በተከበረው የረመዳን ወር ውስጥ)

📚ክፍል አንድ

የትምህርቱ አቅራቢ፦➴➴➴
🎙ኡስታዝ ሙሐመድ አህመድ ሙነወር [ኢብኑ ሙነወር] አላህ ይጠብቀው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

በረመዷን ዙሪያ የሰለፎቻችንን ሁኔታ መዳሰስ ለምን አስፈለገ‼️
ያስፈለገበት ምክንያትማ

❶ኛ .ለእያንዳንዱ ስራችን ሞደላችን (ምሳሌያችን) ነብዩ ሙሐመድ ﷺ ናቸው። የሳቸውን ተግባራት ደግሞ በስነ_ስርዓት ወደኛ ያስተላለፉልን ሰለፎቻችን በመሆናቸው የነሱን አህዋል (ሁኔታ) ማየቱ ተገቢ ነው።
አላህ እንዲህ ይላል፦
لَّقَدْ كَانَ لَكُمْ فِي رَسُولِ اللَّهِ أُسْوَةٌ حَسَنَةٌ لِّمَن كَانَ يَرْجُو اللَّهَ وَالْيَوْمَ الْآخِرَ وَذَكَرَ اللَّهَ كَثِيرًا
ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ፡፡
(ሱረቱ አል- አሕዛብ - 21)

❷ኛ .ሌላኛው ያስፈለገበት ምክንያት እኛ ልክ ሰለፎቻችን እንዳመኑበት አይነት ካመንን እንደነሱ አውቀን ከተገበርን ቅናቻውን መንገድ እንመራለንና
አላህ እንዲህ ብሏል፦
فَإِنْ آمَنُوا بِمِثْلِ مَا آمَنتُم بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوا ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ ۖ
በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡
( አል-በቀራህ - 137)

አላህ በሰለፎቻችን አይነት ተግባር ሰርተን የምንጠቀምበት ችሎት ይለግሰን !!
አጠቃላይ ወሳኝ ምክር
ወንድም ሳዳት ከማል
የኛን ተውት የነብያቶቹን ግን አንተውም።
#ሳዳት_ሀፊዞሁሏህ__

➻የመጀመሪያ የሳዳት ከማል ሙሐደራ 01
➻በጉራጌ ዞን በአክሊል ወረዳ በዘነበነር ቀበሌ
➻ወደ ዋናው የሳዳት ከማል ፔጅ ለመቀላቀል

https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
4/7/2014
=ሰዉ በነፈሰበት አትንፈስ አቋም ይኑርህ ሰው ስለተቃወመ አትቃወም ሰው ስለወደደህ አትውደድ ሰው ስለሄደ አትሂድ ሰው ስለቆመ አትቁም
~~
∬በእውነት ሜዳ ላይ ብቻ ተጫወት እውነት በመናገርህ የምታጣው እና የሚርቅህ ብቸኛው ሰው ውሸታም እና አስመሳይ ሰው ነው
አወዛጋቢ ቀን ይመጣል

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወደፊት ስለሚመጣው የኡማው መከፋፈል እንዲህ ብለዋል ።
“« سيأتي على الناس زمان سنوات خداعات: يصدق فيها الكاذب ويكذب فيها الصادق، ويؤتمن فيها الخائن ويخون فيها الأمين، وينطق فيها الرويبضة. قيل يا رسول الله وما الرويبضة؟ قال: الرجل التافه ينطق في أمر العامة »”

” በሰዎች ዘንድ አወዛጋቢ ዘመናት ይመጣሉ ፡፡ ሐሰተኛው እውነተኛ እውተኛው ሐሰተኛ የሚባልበት ፣ ከሓዲው ታማኝ ታማኙ ከሐዲ የሚረግበት ፣ ሩወይቢዳዎች የሚናገሩበት ፡፡ የአላህ መልእክተኛ ሆይ ሩወይቢዳዎች እነማናቸው (ተብለው ተጠየቁ) እሳቸውም ‹‹ ዝቃጭ የሆነ ሰው ነው ግን ስለ ኡማው ጥቅል ጉዳዮች ያወራል›› ሲሉ መለሱ
[4]. أخرجه ابن ماجة ( 4042 ) و الحاكم ( 4 / 465 ، 512 ) و أحمد ( 2 / 291
ቆይታ ከዑለሞች ድንቅ ንግግሮች ጋር

" አኽላቅ ሲበላሽ ዐቂዳ ይበላሻል
ዐቂዳ በተበላሸ ግዜ ሙስሊሞች ከጌታቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ይቋረጣል
በዚህን ግዜ ደካማ ህዝቦች ይሆናሉ "
[ ኢብኑ ዑሰይሚን (ረሂመሁላህ) ]
ትክክል ናቸው

☞ ዛሬ ላይ ማንም ሚጫወትብን ቁጥራችን አንሶ አይደለም በአኽላቃችንና በዐቂዳችን መበላሸት ምክንያት ደካሞች ሆነን እንጂ ፤ ስለዚህ የዚህ ኡሙ ጥንካሬ እንዲመለስ የኡማው ዐቂዳ መስተካከል አለበት አኸላቃችንንም ልናሳምር ይገባል።

ይህን የምታስተካክሉት አንተ፣ አንቺ ናችሁ።
ስናስተካክልም ከትክክለኛ አቋም ጋር ።

ጥቅላዊ ምክሬ እንደ ወድማዊነት

ሰለፎች ተግባርን እንጂ ወሬን አያበዙም ስለዚህ ወንድሜ እህቴ አፍ ለከፈተ ሁሉ መልስ አትስጡ ። ተዋቸው ።

እኛ እውነት መንሃጀ ሰለፍን ተከታይ ከሆን ጊዜያችንን ኢልም በመፈለግ ማሳለፍ አለብን ። ወሬውን ለወሬኛ ተውሏቸው። እንደፈለጉ ይሁኑ ።

የሀቅ ሰዎች ሆይ በማንም ላይ ድንበር አንለፍ ። የፈለጉትን ይበሉ የፈለጉትን ያድርጉን ፣ ወንድሞቼ አኸላቃችንን ልናሳምር ግድ ይለናል ። አለበለዚያ የማንም መሳለቂያ ነው የምንሆነው ፣
ሰሜታችንን ትተን ወደ ትክክለኛው መንገድ ወደ ሰለፎች መጓዝ ።

ዋናው አላማችን የነብዪ ጉርብትና ለማገኘት ነው አይደል እንግዲያውስ እነሱ የሰሩት ብቻ ስራ በቂህ ነው ።

አብሽሩ ሰለፍይ ወንድሞቼና እህቶቼ ባይተዋርነት እንዳይሰማችሁ ።

ለአላህ ብዬ እወዳችኋለሁ ።


https://t.me/httpsLatahzen
ማይጨበጥ ደስታ

ለማይያዝ ህይወት ራስን ማንከራተት:
በሀራሙ ፍቅር ከዲኑ መጣላት:

በዝቷል በዘመኑ የሸይጣን ሰራዊት:
ለሀራም ለዝሙት አንተን ሚጎተጉት:

የወንዱ ልክስክስ የሴት ክብር ሊያረክስ:
ከሴቷ እጭን ስር እንዲው ሚልከሰከስ:

ያን መጪውን አለም እርግፍ አርጎ ረስቶ:
በሀራም ስሜቱን ለማርካት ጓጉቶ:
ከአላህ ይጣላል አኼራውን ረስቶ:

እሷም ክብሯን ጥላ ይወደኛል ብላ:
በጓሮ የመጣን ላስተናግደው ብላ:
መግባቷስ መች ቀረ ማይወጡበት በላ:

እህቴ አትሸወጅ አይምሰልሽ ኸይር:
ከወደደሽ ይምጣ በፊተኛው በር።
🖊@Nur4843

https://t.me/httpsnurutewhide
እነዚህ ሰዎች ድምበር አላፊ ተዛላፊዎች እንጂ ሌላ አይደሉም የምንለው በምክንያት ነው።

ሀቂቃ ከነዚህ ሰዎች ምን እንማር?

በዚህ መልኩ የተወሰኑ የሱና ሰዎች የሚጠሉ ጭፍኖች ልታፈሩ ትችላላችሁ ከዚህ ውጪ ግን አላህን ብትፈሩ ምንኛ በታደላችሁ ነበር።

አላህ አሳምሮ ሰው አድርጎ የፈጠረው አካል ውሻ ብሎ መሳደብ ሁክሙ ምንድ ነው? እመለስበታለሁ ኢንሻአላህ
የኔማ ኡስታዞች!

እውቀት እና አደብን አላህ ያደላቸዉ
ለሰዉ ትችት ስድብ ቦታም የሌላቸዉ

ለህዝቡ መንቃት ሰበብ ያረጋቸዉ
የተዉሒድ አርበኛ የሽርክ ጠላት ናቸዉ

ፈልቅቀው ያወጡኝ ከኢኽዋኖች ኮተት
ከቢድዓዉም ሰፈር ከነሺዳው ቅዠት

ዲኑንም ለመርዳት ብዙ ይለፋሉ
ንፁ ፍሬዎችን ደምቀው ያፈራሉ

አቤት ማማራቸዉ በሱና አሸብርቀዉ
በአንድ ሲለፉ ሲተጉ አሸብርቀዉ

እንዲህ ነዉ አንድነት ከሆነማ ላይቀር
አላህ ይወፍቃቸዉ እድሜ ከጤና ጋር

አሉ ብዙ ጀግኖች በሰሜን በደቡብ
ባህር ማዶም አሉ ኢልምን የጠገቡ በደንብ

አቤት ማማራቸዉ በሱና አሸብርቀዉ
በአንድ ሲለፉ ሲተጉ አሸብርቀዉ

እንዲህ ነዉ አንድነት ከሆነማ ላይቀር
አላህ ይወፍቃቸዉ እርሜ ከጤና ጋር

በነሱ አንድነት ጠላት አይኑ ይቀላል
ተባብረው ሲሰሩ ሁሌ ይቃጠላል

ምን ማድረግ አንችል የጥመት አናጃዎች
በሰለፍዮች ላይ የመሬት ውስጥ መሰሪ እባቦች

ቅናት ምቀኝነት ውስጣቹ ተቀብሯል
ትብብር ስታዩማ ገንፍሎ ይወጣል

ጀግኖናቻችንንም አላህ ያቆይልን
በሱና አኑሮ በዚው ላይ ያጽናልን

🖊 Umu Nuh
ሙእሚን በዱንያ ለነገ አያውቅም:
ሀሳቡ ሌላ ነው በርካሽ አይወድቅም:

«––––––––––––––»

ዛሬ ላይ የሰጠው ነገ የትስ ሄዶ:
ቃሉን አያፈርስም ፅፉል ያኔ ማዶ:

«––––––––––––––––»

ሊስትሮም ወዛደር ቢበላም ነግዶ
ሁሌም አመስጋኝ ነው ለፈጣሪው ሰግዶ።

https://t.me/httpNurahemd
ማይጨበጥ ደስታ

ለማይያዝ ህይወት ራስን ማንከራተት:
በሀራሙ ፍቅር ከዲኑ መጣላት:

በዝቷል በዘመኑ የሸይጣን ሰራዊት:
ለሀራም ለዝሙት አንተን ሚጎተጉት:

የወንዱ ልክስክስ የሴት ክብር ሊያረክስ:
ከሴቷ እጭን ስር እንዲው ሚልከሰከስ:

ያን መጪውን አለም እርግፍ አርጎ ረስቶ:
በሀራም ስሜቱን ለማርካት ጓጉቶ:
ከአላህ ይጣላል አኼራውን ረስቶ:

እሷም ክብሯን ጥላ ይወደኛል ብላ:
በጓሮ የመጣን ላስተናግደው ብላ:
መግባቷስ መች ቀረ ማይወጡበት በላ:

እህቴ አትሸወጅ አይምሰልሽ ኸይር:
ከወደደሽ ይምጣ በፊተኛው በር።

🖌ኑርአህመድ
🔶የጊዜን ደረጃ በቃላት ማብራራት ትንሽ ይዳግታል። ብዙዎች የጊዜን ውድነት ዘንግተዋል በውስጡ ብዙ ከጭንቅ የሚያድኑ ነገሮችን መሸመት እንደሚችሉ ረስተዋል። አደራ‼️ ከነዚህ ሰዎች እንዳትሆን ነፍስህን ተቆጣጥረህ ጊዜህን በሚጠቅምህ ነገር ሙላው።🔶

https://t.me/httpsLatahzen