La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
«የቲምን አደራ»

የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን✌️ያሉት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።
💦💦💦💦💦💦💦💦


ኑርአህመድ


https://t.me/httpsLatahzen
☆ዲን ያላትን ምረጥ☆

ዲን ያላትን ምረጥ የተሞላች በእውቀት፣
ዝም ብላ የማትሮጥ ወደየ ሞቀበት፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ሜካፕና ሽቶ የማይነካት ኮተት፣
ዲኗን ምታከብር ምትወድህ የእውነት፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ቤተሰቧን ሁላ ወዳጅና አክባሪ፣
ረጋ ሰከን ያለች ባለ ድንቅ ባህሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ድንቅ አመለ ሸጋ የሆነች ታታሪ፣
ለሀቅ ለእውነት ታጋይ ተቆርቋሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የተሳፈረች ናት በተውሂዱ ጋሪ፣
የማትለብስ የነሱን የሀራም አክራሪ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የምትለብሰው ኒቃብ ካልሆነ ነው ጅልባብ፣
የማያታልላት የጓደኛ እባብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እጅግ የምታምር ያለች ሰብ ረገብ፣
የማትለይህ ናት ሁሌ ካንተ አጠገብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በዒባዳስ ቢሆን ምታበረታታህ ምታስርልህ ወገብ፣
የዝች አይነቷ ሁብ ይግባ ከሁሉም ቀልብ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
የዝች አይነት ያየ ያሳየኝ አደራ፣
እሷኑ አግብቼ በደስታ ልኑራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ከሷ ጋር ይሆናል ህይወቴ የደራ፣
ሰምታ እህቴ አለች ስለዚህ ሲወራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እኔ ምፈልገው በእውቀት ያበራ፣
እኔን የሚወደኝ ሀራም ማያይ ተራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
አጅነቢ ማትቀርበው አላህን ሚፈራ፣
እኔን ሚያስቀራኝ እጅጉን የቀራ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
እኔን እና ዲኑን እጅግ ያፈቀረ፣
ሸሪአ ሚመራው በዲን የታሰረ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
ስለመልኩስ ቢሆን እጅጉን ያማረ፣
ፂሙን የማይላጭ ሱሪ ያልዘረረ፣
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
በሱና ተውቦ ህይወቱን የኖረ፣
እሱንስ ካገኘሁ ህይወቴ ሰመረ፣
የዚ አይነቱን ይስጠኝ ካገባሁ ካልቀረ።
🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱🌱
🖊ኑርአህመድ





https://t.me/httpsLatahzen
“ሴት“

አልሀምዱሊላሂ ልጀምር በስሙ፣
ሴት ልጅን ለሰጠን ሀምድ ይግባው ረሂሙ፣

በሁሉም ዘርፍ ላይ ናት የተዋጣላት፣
ቢወራስ አያልቅም የእሷኮ ማንነት፣

ነች እኮ ወድ እናት አምሳያ የሌላት፣
ደሞ በእህትነት ለወንድሟ ምትሞት፣

እንደው ምን ልበላት ቃላት አጣሁላት፣
ጀሊሉ በቁድራው በጀነት ይካሳት፣

ሚስትም ትሆናለች የባል ተፈቃሪ፣
በጦርነት ላይም ምን ባትሆን ወራሪ፣

ወንዱን ታጅባለች ከጎን አባሻሪ፣
ተወዳጇ ሴት ልጅ አባቷን አክባሪ፣

ኧረ ማነው እስቲ ቦታዋን ሚተካ፣
አልፎ ተረማምዶ ነው ክብሯን ሚነካ፣

ነች እኮ ክብር ያላት የቤተሰብ ዋርካ፣
አላህ ይዘንላት ይሙላት በበረካ።

ልክ እንደ ዓኢሻ በእውቀት የተካቡ፣
አሉ በዘመኑም በኢማን ያበቡ፣

በኒቃብ በሂጃብ እጅግ የተዋቡ፣
ሚናቸው አያልቅም ቢከተብ ኪታቡ፣

ልምከርሽ እህቴ ምን ብዙ ባልቀራ፣
ካየሁ ከሰማሁት በጥቂቱ ላውራ፣

በዲን በክብርሽ ላይ አደራ አደራ፣
ከአላህ እንዳይገጥምሽ የስቃይ መከራ፣

እንዳይታለዪ ዘመኑ ባመጣሽ፣
ገዜ እንዳታጠፊ ምንም በማይጠቀምሽ፣

አልፎ ተገልብጦ አንቺን በሚጎዳሽ፣
እንዳትሸወጂ አደራ ልበልሽ፣

እኔም በዚው ላብቃ ግጥሙም ሳይንዛዛ፣
ራህማኑ ይክፈልሽ ሚያምረውን ጀዛ።

ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
#ይሔ_ነው_ባል_ማለት__!!
-----------------------------------
የትዳርን ትርጉም ያወቀ ጠንቅቆ፡
ደግነት የሞላው ከክፋት ተላቆ፡
መጥፎን አስወግዶ በበጎነት ደምቆ፡
በፍቅር የሚኖር ቤቱ የደመቀ፡
ሚስቱን ከማስከፋት የተጠነቀቀ፡
በጥብጦ የጠጣ የፍቅርን ጭማቂ፡
ውድ ባለቤቱን ዘወትር ናፋቂ፡
ሙሉ እንቅስቃሴው ለሚስቱ የሚመች፡
ለርሷ ምንም ቢሆን ሁሌም የማይሰለች፡
----------------------------------------------
የሱና ጠበቃ የተውሒድ ሰባኪ፡
ከቢዲዐ ከሽርክ የሌለው ንክኪ
በውቀት የተካነ እጂጉን የነቃ፡
የመዘሀበል ሀቅ የሱና ጠበቃ፡
ፀባዩ ማራኪ እጂግ የረቀቀ፡
ንግግሩ ቁጥብ ኢልሙ የመጠቀ፡
በመልካም ትውስታ ስሙ የገነነው፡
የመንሐጅ ጠበቃ ባል ማለት እሱ ነው፡፡
~~~~
ጭቅጭቅ ንዝንዝ ፈፅሞ የማይወድ፡
ቆፍጣናና ጀግና በቃ ይሔ ነው ወንድ፡
ፈጣን እና አስታዋይ እጂጉን ቀልጣፋ፡
ግሩም-መልከ ቀና አቋመ-ዘንጣፋ፡
ሚስቱ ካይኑ ስትርቅ ቅናት የሚይዘው፡
እውነተኛ ፍቅር የሚወዘውዘው፡
-------------------------------------------
(አልቃሻ!? ሚስኪን ሲያሳዝን!?)
ሚስቱ ስትናፍቀው የሚፈሰው እንባው፡
ያሳለፈው ጊዜ ሆዱን እያባባው፡
በቃ ይህ ነው ለኔ ባልነት የገባው፡
ከቤት እስኪመጣ ከስራ ቆይቶ፡
ሲቃ የሚይዘው ናፍቆቱ በርክቶ፡
ስለርሷ እሚጨነቅ ሁሉን ነገር ትቶ፡
በሆነ አጋጣሚ ከጠፋች ከጎኑ፡
የትዳር አጋሩ የመውደድ ልሳኑ፡
በልቶና ጠጥቶ ምንም የማይመስለው፡
የትዳር አጋሩ ናፍቆት እያየለው፡
ሁሌም የፍቅር ሰው መውደድ የተጠማ፡
መልክና ቁመናው ውብ ማራኪ ዞማ፡
--------------------------------------------
የባልነት መስፈርት ሸርጡ የተሟላ፡
ቃሉ እማይታጠፍ ከገባ መሀላ፡
ከሚስቱ በስተቀር የማያስብ ሌላ፡
ጀግና መልከ-መልካም ገራገር ሸበላ፡
---------------------------------------------
ህዝቦቹ ባንድ ድምፅ የመሰከሩለት፡
መልካም ሰው ነህ አንተስ ብለው ያዜሙለት፡
የሰውነት ሚዛን ይሔ ነው ባል ማለት፡
----------------------------------------------
#ኑር_
----------------------------------------------
https://t.me/httpsLatahzen
የውዱ ነብይ{ﷺ}ምክር
(ትዳርን ላሰቡ ሰዎች)!

➀ ነብይ{ﷺ}እንዲህ አሉ:-
ድንግሎችን አግቡ እነሱ{ድንግሎች} አንደበታቸው እጅጉን ጣፍጭ እና በጥቂት የሚደሰቱ ናቸው።
ምንጭ:-(ሶሒሁል ጃሚዕ)

⓶ ጃቢር ኢብኑ አብደላህ እንዲህ አሉ:-ረሱል ''አገባህ''? አሉኝ አዎን አልዃቸው ቢክራ ወይስ ሰይብ አሉኝ ''ሰይባ''አልዃቸው ከዚያም ቢክራ አታገባም ነበርን የምታጫውታት የምታጫውትህ የምትሆነዋን አሉት።

⓷ ኢማሙ አህለሱና ወልጀምዓ አሕመድ ብን ሀንበል (ረሒመሁላሁ ተዓላ) እንዲህ ይላሉ:-
ቢክር ድንግል የሆነችዋን አግባ።
ምንጭ:-አል ኣዳቡ ሸርዒያ(204-2)

ኢስሃቅ ኢብኑ ሀሳን እንዲህ አሉ:-ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሃንበል ስለ ትዳር አማከርኩትና እንዲህ ሲል መከረኝ ቢክራ{ድንግል} የሆነችዋን አግባ እናት የሌላትን{እናቷ የሞተችባት}ለማግባት ጉጉት ይኑርህ።

ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ:-
ልጃገረድ ድንግል የሆነችን ማግባት በላጭ ነው ምክንያቱም እሷ ከሱ በፊት ወደ ሞከረቻቸውና ወዳየቻቸው ወደ ቀመሰቻቸው ወንዶች አትጓጓም ከሱ በፊት በማንም ላይ በአንድም ሰው ላይ ልቧ አይንጠለጠልም።ምክንያቱም ከወንዶች ለመጀመሪያ ጊዜ እሷን የሚገናኛት ይህ ወንድ ነው ብዙ ትንጠለጠልበታለች። ለነዚህ ምክንያቶች ቢክርን ማግባት በላጭ ነው።
الشرح الممتع (١٢_١٥)

አደራህን #ዲን_ያላት_አግባ!

ኢብኑ ዑሰይሚን እንዲህ አሉ:-
#እወቅ! አንተ የነብይ{ﷺ} ምክር ሰምተህ (ዲን ያላትን መርጠህ ካገባህ) ቆንጆ ያልሆነችውን አላህ ቆንጆ ያደርግልሃል።
ምንጭ:-(ሸርሁ ሙስሊም)

ግልፅ ነው ወንዶች መልክ መልክ እያልክ እድሜህን ለምን ትፈጃለህ ዲን ያላትን ምረጥ ውበቱን ቤትህ ውስጥ ታገኘዋለክ

➲ የአላህ ነብይ{ﷺ}እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር:-
ጌታዬ አላህ ሆይ የመሸበቻ ጊዜዬ ከመድረሱ በፊት እንድሸብት ከምታደርገኝ ሚስት በአንተ እጠበቃለሁኝ።
ምንጭ:-አስ ሶሒሀህ-3137-

ይሔን ዱዓ ስንቶቻችን ነን በዱዓችን ውስጥ የምናስገባው #ራሳችንን_እንፈትሽ

➲ ሙሃመድ ኢብኑ ሁሰይን እንዲህ በማለት ዱዓ ያደርጉ ነበር:-
ጌታዬ አላህ ሆይ! ሳያት የምታስደስተኝ ሳዛት የምትታዘዘኝ ስርቅ{ክብሬንና ክብሯን እና ገንዘቤን}የምትጠብቅልኝ የሆነችዋን ሚስት ስጠኝ።
ምንጭ:-በህጀቱል መጃሊስ{183}📚📚📚📚📚📚📚📚
La tehzen
➧ከተውሂድ አርማዎች ➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ክፍል ሰባት ➛➛➛➛➛➛ ➧የተውሂድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➲ሰባተኛው፡- በዚህ ዓለምም ይሁን በወዲያኛው ዓለም በዘውታሪነትና በቀጣይነት በትክክል የሚያስተሳስር እርሱ ብቻ ነው፡፡ እንደተውሒድ በሰው ልጆች መካከል እርስ በርስ የሚያስተሳስር አንድም ነገር የለም፡፡ ምክንያቱም ተውሒድ በኢማን ባለቤቶች መካከል በዚህ ዓለምም…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➭ክፍል ዘጠኝ

➧የተውሂድ ምንነትና እውነታ
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➲አንደኛው ተውሒድ አር'ሩቡብያ፡ አላህ በመፍጠርም ፣ ሲሳይ በመስጠትም ፣ ሁሉን ተቆጣጣሪ በመሆኑም ፣ ጸጋን በመስጠቱና ሁሉን በማገለባበጡ ብቸኛ መሆኑንና በእነዚህ ነገሮች ምንም አይነት ተጋሪ የሌለው መሆኑን አምኖ ብቸኛ ማድረግ ማለት ነው፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጾቹ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ قُلِ اللَّهُ ۚ

“የሰማያትና የምድር ጌታ ማን ነው?” በላቸው፡፡ “አላህ ነው” በል፡፡ አር ረዕድ (16)

قُل لِّمَنِ الْأَرْضُ وَمَن فِيهَا إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ ◆سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَذَكَّرُونَ ◆قُلْ مَن رَّبُّ السَّمَاوَاتِ السَّبْعِ وَرَبُّ الْعَرْشِ الْعَظِيمِ ◆سَيَقُولُونَ لِلَّهِ ۚ قُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ◆قُلْ مَن بِيَدِهِ مَلَكُوتُ كُلِّ شَيْءٍ وَهُوَ يُجِيرُ وَلَا يُجَارُ عَلَيْهِ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

➲“ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የማን ነው? የምታውቁ ብትሆኑ (ንገሩኝ)” በላቸው፡፡ “በእርግጥ የአላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “ታዲያ አትገሰጹምን?” በላቸው፡፡“የሰባቱ ሰማያት ጌታና የታላቁ ዐርሽ ጌታ ማን ነው?”በላቸው፡፡ “በእርግጥ አላህ ነው” ይሉሃል፡፡ “እንግዲያ አትፈሩትምን?” በላቸው፡፡ “የነገሩ ሁሉ ግዛት በእጁ የሆነ እርሱ የሚጠብቅ በእርሱ ላይ የማይጠበቅ ማን ነው?የምታውቁ እንደሆናችሁ (መልሱልኝ) በላቸው፡፡ አል ሙእሚኑን፡(84__88)

▪️ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ ۖ فَتَبَارَكَ اللَّهُ رَبُّ الْعَالَمِينَ

“ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፡፡የዓለማትም ጌታ አላህ ላቀ፡፡” ጋፊር፡64

➧ሁለተኛው ክፍል፡ ተውሒዱል አስማእ ወስ'ሲፋት በቁርኣን በሐዲስ በመጡ መልካም ስሞቹና ከፍተኛ የሆኑ መገለጫዎች አላህን ብቸኛ ማድረግ ማለት ነው፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጾቹ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️اللَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ

“አላህ ከእርሱ ሌላ አምላክ የለም፡፡ ለእርሱ መልካሞች የሆኑ ስሞች አሉት፡፡”
ጦሃ፡(8)
قُلِ ادْعُوا اللَّهَ أَوِ ادْعُوا الرَّحْمَٰنَ ۖ أَيًّا مَّا تَدْعُوا فَلَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ

➧አላህን ጥሩ ወይም አር'ረሕማንን ጥሩ ፤ (ከሁለቱ) ማንኛውንም ብትጠሩ (መልካም ነው)፡፡ ለእርሱ መልካም ስሞች አሉትና” አል ኢስራእ (110)

▪️هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ عَالِمُ الْغَيْبِ وَالشَّهَادَةِ ۖ هُوَ الرَّحْمَٰنُ الرَّحِيمُ ◆هُوَ اللَّهُ الَّذِي لَا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ الْمَلِكُ الْقُدُّوسُ السَّلَامُ الْمُؤْمِنُ الْمُهَيْمِنُ الْعَزِيزُ الْجَبَّارُ الْمُتَكَبِّرُ ۚ سُبْحَانَ اللَّهِ عَمَّا يُشْرِكُونَ ◆هُوَ اللَّهُ الْخَالِقُ الْبَارِئُ الْمُصَوِّرُ ۖ لَهُ الْأَسْمَاءُ الْحُسْنَىٰ ۚ يُسَبِّحُ لَهُ مَا فِي السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ ۖ وَهُوَ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ

➧እርሱ አላህ ነው ፤ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ ፤ ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ የሆነ ነው፡፡ እርሱ እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ ነው፡፡ እርሱ አላህ ነው፡፡ ያ ከእርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለ ፤ ንጉሱ ከጉድለት ሁሉ የጠራው ፣ የሰላም ባለቤቱ ፣ ጸጥታን ሰጭው ፣ ባሮቹን ጠባቂው ፣ አሸናፊው ፣ ሃያሉ ፣ ኩሩው ነው፡፡ አላህ ከሚያጋሩት ሁሉ ጠራ፡፡ እርሱ አላህ ፈጣሪው (ከኢምንት) አስገኚው ፣ ቅርጽን አሳማሪው ነው፡፡ ለእርሱ መልካሞች ስሞች አሉት፡፡ በሰማያትና በምድርም ያለው ሁሉ ለእርሱ ያሞግሳል፡፡ እርሱም አሸናፊና ጥበበኛም ነው፡፡”ሐሽር፡(22__24)





✍️ኢንሻአላህ ይቀጥላል

ኑርአህመድ
【አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል】

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ ን
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
🔹ሰላትን አደራ!🔹


ወደ አላህ መሸሻ:
አጅር ያለው ጉርሻ:
የሩህ መናፈሻ:
የመንፈስ ማደሻ:
ጎዶሎን መካሻ:
ወደ አላህ ማልቀሻ:
ለሌላ ዒባዳ ቀልብን ማነሳሻ:
🍀
ቀልብህ እንዲራራ:
እንዳይሆን መራራ:
በሀራም በረራ:
ከፉጃሮች ተራ:
እኔም በዚው ላብቃ ብዙ ሳላወራ:
ወንድሜ ልምከርህ ሰላትን አደራ!!
ኑርአህመድ
📖እውቀትን ላወቀ📖

እውቀት ብርሀን ነው:
የእውነት ለተረዳው:
ኻሊቁ ላቃናው:
ለሀቁ ላገራው።

የሰው ልጅ ህይወቱ:
ያለ እውቀት ነው ከንቱ:

በተለይ ለሙስሊም:
ለሱ እንደ እውቀት የለም:
ዱንያዊቷም አለም:
መዝርያ ለዘላለም:

እንደሆነች አውቆ:
ከሀራም እርቆ:
ለእውቀት ተጨንቆ:
ለመቅራት ተዋድቆ:
ምርጥ ሀሳብ ሰንቆ:

እንደዚህ ነው ማወቅ:
ራስህን አርገህ ዝቅ:
ለአኼራህ ሰንቅ:
ከእሳት ለመጠንቀቅ:
በጀነት ለመላቅ:
ዝምምም ብሎ ማወቅ:

ወንድሜ አስተውለው:
ኡስታዝህስ ማነው:
ያ ሀቅ የተማረው?
አቂዳው የነፃው?
ከሽርክ ቢድዓው:
አብዝቶ የራቀው?
ወይንስ ሌላኛው ነው?
ቅጠል የሚበላው:
ስሜት ያታለለው:
በምርቃና ሲለው:
ኻሊቅ ሚሰራራው:
ኧረ የትኛው ነው?
አስተውለህ ምረጠው!?
ሗላ ላይ እንዳቶን ከልብ የሚቆጨው።

ከዚም በመቀጠል:
ኒያ ነው ሚከተል:

ኒያን ያሳመረ:
ሀሳቡ ሰመረ:
ካልተጭበረበረ:
ከነፈ በረረ በእውቀት አበረ:

አላህ እውቀት ይስጠን:
ብለን ዱዓ አድርገን:
እሱም ተቀብሎን:
በእውቀት አልቆን:
ከእሳቱ አርቆን:
ጀነት አስገብቶን:
በፊርደውስ አኑሮን:
የሱን ፊት ያሳየን።

ጌታችን ሆይ አሚን

ኑርአህመድ
Forwarded from Deleted Account
ከእሳት ለመጠበቅ!

....ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿اتَّقُوا النّارَ ولو بشِقَّةِ تَمْرَةٍ، فمَن لَمْ يَجِدْ شِقَّةَ تَمْرَةٍ فَبِكَلِمَةٍ طَيِّبَةٍ﴾

“በግማሽ ቴምርም ቢሆን የጀሃነምን እሳት ተከላከሉ። ግማሽ ቴምር ማታገኙ እንኳ ቢሆን መልካም በመናገር ተከላከሉ።” 📚 ቡኻሪ ዘግበውታል: 3595

┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄
https://t.me/httpsLatahzen
Audio
ቁረአን የልብ ብረሀን
➱➱➱➱➱➱➱➱➱

ከቁርአን በላይ ጣፋጭ የለም!

➲ቀርኣንን ማዳመጥ
የነብዩ (ﷺ)ሱና ነው!!

ቀርኣንን ማዳመጥ
የመቅራት አንድ አካል ነው
!!

ምርጥ ቲላዋ ተጋበዙልኝ!
ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ፡-
~~
1. “እኔ ሰው ነኝ፡፡ እስታለሁ፣ አገኛለሁ፡፡ ስለዚህ እይታየን ተመልከቱ፡፡ ቁርኣንና ሱንና ጋር የገጠመውን በሙሉ ያዙት፡፡ ቁርኣንና ሱንና ጋር ያልገጠመውን ተውት፡፡”
2. “ከነብዩ ﷺ በስተቀር ንግግሩ የሚያዝለት ወይም የሚመለስበት ያልሆነ አንድም የለም፡፡”
3. “ከነብዩ ﷺ በኋላ ከንግግሩ የሚያዝና የሚተው ያልሆነ አንድም የለም፡፡ ነብዩ ﷺ ሲቀሩ፡፡
አሳሳቢ ትዝብት ለሁላችን!
~
ሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልአባኒ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፦

"እኔ እያዘንኩ የማስተውለው ነገር ቢኖር ዛሬ ሰዎች በመጀመሪያው ነገር ላይ ማለትም በእውቀት ላይ ሲያተኩሩ አያለሁ። ነገር ግን ሌላውን ጉዳይ ትኩረት ይነፍጉታል። እርሱም የስነ ምግባር ጉዳይ ነው። ነብዩ (ﷺ) {እኔ የተላክኩት መልካም ስነ-ምግባራትን እንዳሟላ ነው} በማለት ደዕዋቸውን እንዳለ በመልካም ስነ ምግባር ላይ ሊገድቡት እስከሚደርሱ ይቀርባሉ። ይህ የሆነው መልካም ስነ-ምግባራት ለመልእክተኛው (ﷺ) ደዕዋ መሰረታዊ ክፍል ስለሆኑ ነው።
እውነታው እኔ በእውቀት ፍለጋ ጅማሮ ላይ ሳለሁ አላህ - 0ዘ ወጀለ - የጠራ ወደ ሆነው ተውሒድ ሲመራኝ ኢስላማዊው ዓለም ከዚህ ተውሒድ ርቆ እንደሚኖር ስገነዘብ፣ የኢስላማዊው ዓለም ችግር ከላኢላሀ ኢለላህ ትክክለኛ ግንዛቤ መራቃቸው ብቻ ይመስለኝ ነበር።
ነገር ግን ከዚህ መሰረታዊ ችግር ማለትም ከተውሒድ ከመራቃቸው ጋር የሚደረብ ሌላ ችግር እንዳለ ከጊዜ ጋር እየተገለፀልኝ መጣሁ። ይሄውም አብዛኞቻቸው መናኛ በሆነ መጠን ካልሆነ በስተቀር ትክክለኛውን የኢስላም ስነ ምግባራት የማይላበሱ መሆናቸው ነው።"

ምንጭ፦ [ፈታዋ ጁዳ ፡ 34]
አድሰ -ተከታታይ- ፁሁፍ
➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩➩

☞︎︎︎ ክፍል ➨⓵

➲"ፆምን የሚመለከቱ ሰባ【70】ጠቃሚ ነጥቦች !!

"የፆም ትሩፋት ጥቅሞች ስርዓቶችና ሱናዎች ህጎች ፆምን የሚያበላሹ ነገሮች ሴቶችን የሚመለከቱ የፆም ህጎች !!

➽ ምስጋና ሁሉ ለአላህ የተገባ ነዉ እናመሰግነዋለን እገዛዉንም ምህረቱንም እንጠይቀዋለን ከነፍሶቻችን ክፋትና ከስራዎቻችን መጥፎ በአላህ እንጠበቃለን አላህ ቅኑን መንገድ የመራዉ ሊያጠመዉ የሚችል የለም አላህ ያጠመመዉ ደግሞ ትክክለኛዉን መንገድ ሊመራዉ የሚችል አካል የለም ከአላህ በስተቀር ሌላ በእዉነት የሚመለክ አምላክ አለመኖሩን
እሱ አጋር የሌለዉ አንድ አምላክ መሆኑን እመሰክራለሁ ሙሐመድصلى الله عليه وسلم የአላህ አገልጋይና መልዕክተኛ መሆናቸዉን እመሰክራለሁ፡፡

➭"አላህ ብዬ መልካም ነገሮችን ባዘሉ ወራት ምክንያት ለባሮቹ ወደር የለሽ ፀጋን ለግሷል በነኚህ ወራት መልካም ስራዎች ምንዳቸዉ ይነባበራል ወንጀሎች ይታበሳሉ ደረጃዎች ይጨምራሉ !!

➽"ከነኝህ መልካም ነገሮችን ካዘሉ ወራት መካከል ትልቅ ግምት የሚሰጠዉ ( አላሁ ሱበሀነሁ ታአላ) በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገዉ የረመዷን ወር አንዱ ነዉ ግዴታ ስላደረገዉም ያመሰግኑት ዘንድ አመላክቷል ይህ የረመደን ኢባዳ ደረጃዉ ከፍ ያለ ስለሆነ ከዚህ ወር ጋር ትስስርነት የፆም ህጎችን ፣ ያላቸዉን ህጎች መማር ግዴታ ይሆናል ይህ መልዕክት ስርዓቶችን እና ሱናዎችን ጠቅለል ባለ መልኩ አቅፎ የያዘ መልዕክት ነዉ !!

📌"ፆም ማለት ምንዲን ነዉ‼️

❶. ፆም በቋንቋ ደረጃ መከልከል ማለት ሲሆን ግን እንደ ኢስላም ህግ ሌሊቱ ከመንጋቱ በፊት ለመፆም ኒያ( ሀሣብ) በማድረግ አላህን በማምለክ አላማ ጠዋት ሁለተኛዉ ጎህ ከቀደደበት (ከወጣበት) ጀምሮ እስከ ፀሐይ መጥለቅ ድረስ ፆምን ከሚያበላሽ ነገር መከልከል ነዉ፡፡

📌"የፆም ህግ(ብይን) ‼️

❷. የረመዷን ወር መፆም ግዴታ ለመሆኑና ምንም ምክንያት የሌለዉ ሰዉ በረመዷን ወር ካፈጠረ በርግጥ ትልቅ ወንጀል የፈፀመ ለመሆኑ ሙስሊሞች ተስማምተዋል፡፡


📌"የፆም ትሩፋት ‼️

❸. ከፆም ትሩፋቶች መካከል አላህ ፆምን ለራሱ መርጦ በሱ የተነባበረን ምንዳ የሚከፍል ፣ የፆመኛ ዱዓ የማይመለስ ፆመኛ ሰዉ ሁለት ደስታዎችን ማግኘቱ ፆም ለባሪያ የቂያማ ቀን መሸምገሉ የፆመኛ ሰዉ አፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽታ የበለጠ መዓዛ ያለው መሆኑ ፆም ከገሀነም እሳት የሚጠብቅ መከላከያ ምሽግ እና ጋሻ መሆኑ፣ ጂሃድ ላይ አንድ ቀን የፆመ በዚህ ቀን ምክንያት አላህ ፊቱን ከሳት የሰባ ዓመት ያህል የሚያርቀዉ መሆኑ ፣ በገነት ዉስጥ ከፆመኞች በስተቀር ማንም ሊገባበት የማይችል የሆነ ረይያን የሚባል በር መኖሩ ፡፡ (እነኝህ ለምሳሌ ያህል የቀረቡ የረመዷን ትሩፋቶች ናቸዉ፡፡

➽"የረመዷን ፆም ከኢስላም ማዕዘናት አንዱ ነዉ፡፡ ቁርዓን የወረደበት ወር ነዉ የተላቀች ሌሊት ከአንድ ሺህ ወራት የምትበልጥ የምትገኝበት ነዉ የረመዷን ወር ሲገባ የሰማይ(የጀነት) በሮች ይከፈታሉ፡፡ የገሀነም በሮች ይዘጋሉ ሰይጣኖችም በሰንሰለት ይታሰራሉ(ይቀፈደዳሉ)፡፡ የረመዷን ፆም እንዴ አሥር ወሮች ይቆጠራል።


📌"የፆም ጥቅሞች(ፋዒዳዎች) ‼️

❹ .ፆም ከተቅዋ(አላህን ከመፍራት) ጋር የተሳሰሩ ብዙ ጥቅሞችን ያዘለ ነዉ ፆም ሰይጣንን ለማሸነፍ ስሜትን ለመስበር የሰዉነትን ክፍል ለመቆጣጠር መንገድ ነዉ፡፡ ከመጥፎ ስሜትና ወንጀል የመራቅ ፍላጎትን ያዳብራል እንዲሁም ከስርዓቶች እና ከቃል ኪዳን ጋር መላመድን ያስተምራል ይህ ወር የሙስሊሞች አንድነት የሚጀምርበት ወር ለመሆኑ አዋጅ ጥቆማ አለበት፡፡

➧"ይህን ለማብራራት አንድ በጎ ስራ አላህ ዘንድ አሥር እጥፍ ምንዳ አለዉ ፡፡ ) የረመዷን ፆም በአስር ወሮች ይቆጠራል ስድስት የሸዋል ቀናት ደግሞ በሁለት ወሮች ይቆጠራሉ ድምራቸዉ 12 ወራት (አንድ ዓመት) ይሆናል፡፡ በዚህ ዓይነት ፆሙ በየዓመቱ ከተደጋገመ ዕድሜ ልክ እንደመፆም ይቆጠራል ማለት ነዉ፡፡ አላሁ አዕለም)ተርጓሚው !!

📌የፆም ስርዓቶችና ሱናዎች ‼️

❺. ግዴታ ወይም ተወዳጅ የሆነ አለ እሱም፡-ለኩለ ሌሊት ምግብ ግምት መስጠትና ማዘግየት ፊጥር ማፋጠን ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል !!
ولا يزال الناس بخير ما عجلوا الفطر» (رواه الترمذي)
(ሰዎች በጎ ነገር ከመፈፀም አይወገዱም ፆማቸዉን ወቅቱ እንደገባ በአስቸኳይ እስካቆሙ (እስካፋጠሩ) ድረስ ፡፡ ረሱል صلى الله عليه وسلم ከመስገዳቸዉ በፊት በተምር እሸት ያፈጥሩ ነበር ይህን ካላገኙ በደረቅ ተምሮች ይህን ካላገኙ በዉሃ ያፈጥሩ ነበር፡፡ ካፈጠሩ በኋላ➘

كان رسول الله صلى الله عليه وسلم، إذا أفطر قال: «ذهب الظمأ وابتلت العروق، وثبت الأجر إن شاء الله سنن ابی داود حديث حسن
የአላህ መልእክተኛ በሚያፈጥሩ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡- «ጥማቱ ሄደ ጅማቶችም ራሱ፣ በአላህ ፍቃድም ምንዳዉ ፀና »፡፡📚(አቡዳውድ የዘገቡት ሐዲስ) #ተገቢ ያልሆኑ መጥፎ ነገሮችንና ወንጀሎችን መራቅ መልካም ነገሮች እንዲወገዱና እንዲጠፉ መጥፎ እንዲስፋፋና እንዲከሰት ከሚያደርጉት ጥቂቶቹ (ለምሳሌ) ፡- አፈ ታሪክ ተረቶች ሙሰልሰሎች ፣ ድራማ ፣ኳስ ጨዋታ ከጥቅም ያገለለ የሆነ ስብሰባ እና መንገዶች ላይ በመዝናናት ጊዜን ማባከን ወዘተ ናቸዉ፡፡ ምግብ መቀነስ ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል።➘
ما ملأ آدمي وعاء شرا من بطن. بحسب ابن آدم أكلات يقمن صلبه، فإن كان لا محالة فث لطعامه وثلث لشرابه وث لنفسيه» (رواه الترمذي)
የአደም ልጅ ከዕቃዎች ሁሉ እንደ ሆድ ያለ መጥፎ ዕቃ አይሞላም ፡፡ የተወሰኑ ጉርሻዎች ይበቁታል፡፡ የግድ መጨመር ካለበት ሆዱን ለሶስት ይክፈለው አንድ ሶስተኛውን ለምግብ አንድ ሶስተኛውን ለመጠጥ አንድ ሶስተኛውን መተንፈሻ፡፡📚(ቲርሚዚ የዘገቡት)




ኢንሻ አሏህ◉◉◉◉ይቀጥላል

📚ዝግጅት :-ሸይኽ አቡዘር ሀሰን ኢማም
«حَفِظَهُ اللَّهُ»

【አንብብብ ❗️ማንበብ የተሻለ ሰዉ ያደርጋል !!



https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሴት ልጅ ከፊቷ ፀጉር ከበቀለባት ማስወገድ እንዴት ይታያል??
በተለይ ቀድሞ ቀመስ ላይ ቀድሞ ቀመስ ማለት የከንፈራችን የላይኛዉ ማለት ነዉ
እንደዚሁ የእጇን ፀጉር የእግሯን ፀጉር ለባሏ ለመዋብ አስባ ብታስወግደዉ እንዴት ይታያል??
መልስ
የእጅ ላይ የእግር ላይ እንደዚሁ በሌላ ቦታ የሚወጡ ፀጉሮችን ማስወገድ የሚከለክል ነገር የለም
የፊት ፀጉር ማስወገድ በሚለዉ ተፍሲል አለዉ ፊቱዋን የሚረብሽ አዛ የሚያደርግ ከሆነ ብታስወግደዉ ችግር የለዉም። የቅንድብ ፀጉር ማስወገድ ረሱል ይሄን የፈፀመ ረግመዋል ከትላልቅ ወንጀሎች ነዉ። ሁሉንም አስወግዳ የሆነ ነገር ብታደርግበት እንኳ መቀባት ይመስል ከፊል መሀይም ሴቶች እንደሚፈፅሙት አመፀኞች ወይም የተወሰነዉን እንኳ ቅኖድብ ማስወገድ ይሄ ሁሉ የተከለከለ ነዉ ያገዘችም የተረገመች ናትያስወገደችዉ በመቁረጥ ይሁን በመንጨት ይሁን በመላጨት ወይም በማስወገጃ ነገሮች የቅንድብን ፀጉር ማስወገድ በማንኛዉ ሁኖታ ክልከላዉ ብርቱ (ጠንካራ)የሆነ ክልከላ ነዉ
👇👇👇
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ተዉሂዲን ተማር አስተምር ‼️

↪️ሸይኽ ሷሊህ አል- ፈውዛን((ሃፊዘሁሏህ))

➧እንዲህ አሉ:-

ቡዙዎቹ ሰዎች ተውሂድ ምን ማለት ነው ተብለው ቢጠየቁ መመለስ የማይችሉትን ተውሂዲ ተማር!!

✍️ምክኒያቱም ሰዎች የተውሂድን ትርጉም እና በውስጡ ለማለት የተፈለገበትን ነገር አያውቁም!!

✍️ተውሂድ እሱ ከፍ ያለው ጌታችንን አላህን በዓምልኮ ብቸኛ ማዲረግና መነጠል ሲሆነ ሽይኽ መሃመዲ ዓብዱል-ወሃብ አላህ ይዘንላቸውና እንዳሉት ተውሂድ ማለት የሚገባውን አምልኮ ተገቢውን አምልኮ(ዒባዳን) በመስጠት አላህን ብቻውን መነጠል መሆኑን እወቅ!!

✍️ተውሂድ ማለት በጌትነቱ፤ነገራቶችን ሁሉ ፈጣሪ መሆኑ፤ሲሳይን ሰጭ መሆኑ፤የሚገል፤ሂያው የሚያዲረግ የሚለው ብቻውን በቂ እና ተውሂድ አይደለም ይህ ተውሂደል-አረቡቡያ(በጌትነቱ ማመን) ሲሆን በዚህ የተውሂድ ዘርፍ በፊት የነበሩ ጃሂሎች ያምኑና ያርጋግጡ ነበር በጌትነቱ አልካዱም !!

✍️ነገር ግን ከአላህ ጋር ሌላ ነገርን በመገዛታቸውና አምልኮን ለሌላ አካል በመስጠታቸው ምክኒያት ሙሽሪኮችና እሳት(ጀሃነብ)ውስጥ ዝንታለም ዘወታሪ የማይወጡ የሆኑት ከነሡ(ከሙሽሪኮቹ) ከመሞታቸው በፊት ወደ አላህ ቶብተው በመመለስ ተውሂድን ወይም አምልኮን ለአላህ ብቻ አጥብቀው የያዙት ሲቀሩ!!
Forwarded from Deleted Account
ጉድና ጉድ ክፍል①
=======^======
እግዚአብሄር :– እኔ ሰው አይደለሁም።( ሆሴዕ 11:9 )
ኢየሱስ :– እኔ ሰው ነኝ።(ዮሐንስ ወንጌል 8:40 )

( ትንቢተ ሆሴዕ 11:9 ) እኔ እግዚአብሔር አምላክ ነኝ
እንጂ #ሰው_አይደለሁምና

ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሰው ነኝ ይላል

(የዮሐንስ ወንጌል 8:40 ) ነገር ግን አሁን ከእግዚአብሔር
የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን #ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ::

ነገር ግን ነገር ግን........
ኢየሱስ ሰው ነኝ አምላክ አይደለሁም እያለ እየተማፀናቹ እናንተ ግን አይ ኢየሱስ አምላክ ነህ፣ ጌታ ነህ፣ ፈጣሪ ነህ ወዘተ..... ብላችሁ የምታመልኩት ከሆነ ይህን መልዕክት በአንደበቱና በግልፅ አስቀምጦላቹሃል፣

የማቴዎስ ወንጌል 7 ፣ 21 በሰማያት ያለውን የአባቴን ፈቃድ የሚያደርግ እንጂ፥ #ጌታ_ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ #የሚለኝ_ሁሉ_መንግሥተ_ሰማያት_የሚገባ_አይደለም

22 በዚያ ቀን ብዙዎች። ጌታ ሆይ፥ ጌታ ሆይ፥ በስምህ ትንቢት አልተናገርንምን፥ በስምህስ አጋንንትን አላወጣንምን፥ በስምህስ ብዙ ተአምራትን አላደረግንምን? ይሉኛል።

23 የዚያን ጊዜም። #ከቶ_አላወቅኋችሁም#እናንተ_ዓመፀኞች#ከእኔ_ራቁ_ብዬ_እመሰክርባቸዋለሁ

ስለዚህ ኢየሱስን ምትወዱት ከሆነ ቃሉንና ምክሩን ስሙ! ከፊቴ ጥፉ አላውቃችሁም እላቹሃለው እያላቹ ነው።

በወንጌል ካላፈሩ እስኪ ሼር አድርጉት
ይህ 100% ከመፅሀፍ ቅዱስ ከ (ወንጌል) ስለወጣ ሁሉም #ክርስቲያን #ሼር ያድርገው።

📱 “እየሱስ ክርስቶስ እጅግ የተከበረ የፈጣሪ መልእክተኛ”
 ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄ ̄
💥1•
“የምትሰሙትም ቃል የላከኝ የኣብ ነው እንጂ የኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 14:24)

የማን ነው ኣለ?
••••• የላከኝ የኣብ√

በዚህ ጥቅስ መሰረት ወልድ( እየሱስ) የኣብ መልእክተኛ ነው።

💥 2•
“እኔ ከራሴ ኣንዳች ላደርግ ኣይቻለኝም እንደሰማሁ እፈርዳሎ ፍርዴም ቅን ነው የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን ኣልሻምና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:30)

የማን ፈቃድ ኣለ?
••••• የላከኝን√
ማነው የላከው?

እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ኣምላክን የሚልክ ደግሞ ማነው?
ኣምላክ ይልካል ወይስ ይላካል?

💥 3•
“ቃሌን የሚሰማ የላከኝም የሚያምን የዘላለም ሂወት ኣለው”( የዬሐንስ ወንጌል 5:24)

ማንን የሚያምን ኣለ?
••••••• የላከኝን√
ማነው የላከው?

💥 4•
“ኢየሱስም ጮኸ እንዲህም ኣለ በኔ የሚያምን በላከኝ ማመኑ ነው እንጂ በኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ ወንጌል 12:44)

በኢየሱስ ማመን በማን ማመን ነው?
•••••• በላከው√
ማነው የላከው?

💥 5•
“እኔ ከራሴ ኣልተናገርሁምና ነገር ግን የላከኝ ኣብ እርሱ የምለውን የምናገረውንም ትእዛዝ ሰጠኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 12:49)

እዚህ ላይ ደግሞ ” የላከኝ ኣብ” በማለት የኣብ መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ተናግርዋል።

💥6•
“የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 8:26)

ኢየሱስን የላከ እውነተኛው ማነው?

💥 7•
“የላከኝም ኣብ ሰለኔ ይመሰክራል”( የዬሐንስ ወንጌል 8:18)

ማን ኣለ?
••••• የላከኝ ኣብ√

💥8•
“ስለዚህ ኢየሱስ መለሰ እንዲህም ኣላቸው ትምህርቴስ ከላከኝ ነው እንጂ ከኔ ኣይደለም”( የዬሐንስ 7:16)

ትምህርቱ ከማን ነው?•••••ከላከው√
ማነው የላከው?

💥 9•
“እኔም በራሴ ኣልመጣሁም ነገር ግን እናንተ የማታውቁት የላከኝ እውነተኛ ነው”( የዬሐንስ ወንጌል 7:28)

ኢየሱስን የላከ የማይታወቅ እውነተኛው ማነው?

💥 10•
“እኔንም የጣለ የላከኝም ይጥላል”( ሉቃስ ወንጌል 10:16)

የላከኝን? ማነው የላከው?

💥11•
“ከእስራኤል ቤት ለጠፉት በጎች በቀር ኣልተላክሁም ኣለ”( ማቴዎስ 15:34)

ወደ እስራኤል መልእክተኛ ኣድርጎ የላከው ማነው?

💥12•
“ኣንተም እንደላክኸኝ ኣመኑ”( የዬሐንስ ወንጌል 17:8)

ማነው የላከው?

💥13•
“ይህ የማደርገው ስራ ኣብ እንደላከኝ ስለኔ ይመሰክራልና”( የዬሐንስ ወንጌል 5:36)

ኣብ እንደላከኝ በማለት መልእክተኛ መሆኑን በግልፅ ይናገራል።

💥14•
“የላከኝ ኣብም እርሱ ስለኔ መስክሮዋል”( የዬሐንስ ወንጌል 5:37)

ምን ያደረገኝ ኣብ?
•••••••• የላከኝ√

💥15•
“እኔ ከእግዚኣብሄር ወጥቼ መጥቻለሁና እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ ኣልመጣሁም”( የዬሐንስ ወንጌል 8:42)

ከእግዚኣብሄር የተላከ መልእክተኛ መሆኑን ይነግረናል።

💥16•
“ባሪያ ከጌታው ኣይበልጥም መልእክተኛም ከላከው ኣይበልጥም”
( የዬሐንስ ወንጌል 13:16)
መልእክተኛው ማነው? ላኪውስ ማነው?

💥17•
“ኣብ እንደላከኝ እኔ ደግሞ እልካችኃለሁኝ”( የዬሐንስ ወንጌል 20:21)

ኣብ እንደላከኝ በማለት የኣብ መልእክተኛ እንደሆነ በግልፅ ነግሮናል።

==============∞
ስለዚህ እራሱ አምላክ መሆኑን የነገረንን ጌታ አላህን እናምልክ

إنَّنِي أنا اللهُ لآ إلَٰه إلّآ أنَاْ فَاعْبُدنِي وَأَقِمِ الصَّلَوٰة لِذِكْرِي
እኔ አላህ ነኝ ። ከእኔ ውጪ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም።ተገዛኝ።ሰላትንም(በእርሷ) እኔን ለማስታወስ ስገድ።ሱረቱ ጣሃ አንቀፅ 14
ሼር ሼር ሼር👇👇
https://t.me/Pointing_to_the_True_Religion
https://t.me/Pointing_to_the_True_Religion
እኛ ብንሆን ኖሮስ!
~
ለኢማሙ አሕመድ የሆነ ሰው ስም ተነሳላቸው።
* "እኔ ስለሱ መልካምን እንጂ አላውቅም" አሉ።
* "አንተ በሱ ላይ የምትናገረው እሱ ባንተ ላይ ከሚናገረው ይለያል" አላቸው አንዱ። (በክፉ ያነሳሀል ማለቱ ነው።)
* ፈገግ ብለው "እኔ ስለሱ መልካምን እንጂ አላውቅም። ስለሚናገረው እሱ ያውቃል። የማላውቀውን እንድናገር ነው የምትፈልገው?" አሉ።
ቀጥለውም እንዲህ አሉ፦
"ሳሊምን አላህ ይዘንላቸው። (ሳሊም የኢብኑ ዑመር ረዲየላሁ ዐንሁ ልጅ ናቸው።) አንዴ ግመላቸው የሌላን ሰው ግመል ገፋች። ሰውየው በዚህን ጊዜ ለሳሊም 'ክፉ ሽማግሌ ትመስለኛለህ!' አላቸው። 'አልራቅክም!' አሉት። (ልክ ነህ! እያሉት ነው። ኢማሙ አሕመድም ለራሳቸው ተመሳሳይ ነገር መጠቀማቸው ነው።)
ምንጭ፦ አልወረዕ ሊልመርወዚ፡ 197]

* እስኪ እራሳችንን በሳሊም ቦታ አድርገን እናስብ። ምን ይሆን ነበር ምላሻችን? አላሁል ሙስተዓን!
* እስኪ እራሳችንን በኢማሙ አሕመድ ቦታ አድርገን እናስብ። ምን ይሆን ነበር ምላሻችን? አላህ ይድረስልን
……… ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች ………
===========================
በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊት እንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው? እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?! ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን? ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:–

① ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ መፈፀም ማለት ነው። አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት ዘንግቷል።
② ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ቀጥታ ሊያቆም ይገባል።
③ ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡ በኋላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።
④ በወንጀሉ መፀፀት፦ ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የሐቂቃ አይደለም። ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል። ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ። እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።
⑤ ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን። ይህም ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።
⑥ ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ ይገባል። ያን ማድረግ ካልቻለ ዱዓእ ሊያደርግለት እንዲሁም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል።
📌ማንቂያ!!!

#ሙቅ ውሃ "በየቦታው ስለ ማፍሰስ"


👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆


#ሸይኽ ኢብን ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ ፡
ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ #ቢስሚላህ እንላለንን፣ ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ በመፍራት ነው !

መልስ፡-

"አዎን! 👉 #ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ እንዲነቃ ለማድረግ ነው

" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም #በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ ነበር ።

#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ "ለምን ያዝከው "አለው
#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ

#የሚቀራው ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን ስላላወቀ ነው" አለው

#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው(እንዲያነቃው)"

#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ (ረሂምሁሏህ) እንዲህ አሉ ፡-

"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ አይደፋም ምክንያቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች!!

ምናልባትም #በጂኖች አለም ወይም #በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።

📌ስለዚህ አንድ ሰው #የሞቀን ውሃ መድፋት ከፈለገ #በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዘው የማያስቸግር እስኪሆን ያብርደው ከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ፣ ከፈለገ መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ!
፟፟======================================================
#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች በዚህ ሰበብ ችግር ውስጥ ይገባሉ !