La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram

   የሕያ ቢን أبي كثير እንዲህ ይል ነበር……

"አንድ ሰው ላይ ሁለት ነገሮች ካየህ ከጀርባቸው ከእነርሱ የበለጠ ኸይር እንደሚኖረው ዕወቅ;
1ኛው, ምላሱን የሚቆጣጠር ሲሆን
2ኛው, ሰላቱን የሚጠባበቅ ከሆነ"
      /ابن أبي الدنيا في الصمت ٥٦٤/

Ibnu muhammed
https://t.me/httpsLatahzen
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ያጀምዓ እንዴት ናችሁ
ዛሬ ማለትም 9/04/2017 ከምሽቱ 3:00 ሹራ ስለሚኖረን ኸይር ስራ መስራት ሚፈልግ በሀሳብም፣በጉልበት፣በገንዘብ፣በአልባሳት እንዲሁም አባል ሆኖ ከኛጋመስራት ሚፈልግ አብረን ሹራ እንድናረግ አልያም በወስጥ እንድታናግሩን እንደ አላህ ፍቃድ የቻለዉን ያክል ሰበብያውን እንድናደርስ ዘንድ የ ላታህዘን አሚሮች በአላህ ስም እንጠይቃለን🙏
አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
ሹራ የሚደረግበት ግሩፕ:-https://t.me/Latahezn
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
#በአላህ ፍቃድ ስለ ተወደዱ ጾሞች ትንሽ ነገር እተዋወሳለን
#ክፍል,1
እነዚህ የጾም ዓይነቶች ለአላህ ምስጋና ይገባወና ምንዳን ማብዛት ለፈለገ ሰው ቁጥራቸዉ በጣም ብዙ ሲሆኑ ከነሱም መካከል ፦

#1.አንድ ቀን መጾም አንድ ቀን መፈሰክ፦ ይህ ጾም የነብዩላህ ዳውድ(ዐ.ሰ) ጾም ሲባል እሱም ከግዴታ ጾሞች ቡኋላ በጣም በላጩ ነው። ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአብደላህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፦

قال النبي(صلى لله عليه وسلم)، لعبد لله بن عمرو: "صم يومآ، وأفطر يومآ، وذللك صيام داود (عليه السلام)، وهو أعدل الصيام"

"አንድ ቀን ጹሙ አንድ ቀን ፈስክ ይህ የዳዉድ ጾም ሲሆን ይህ ፍትሀዊ ጾም ነው።(ቡኻሪ ቁጥር 1976፣ ሙስሊም በቁጥር ላይ 1159 ዘግቦታል)

#2.አያመ-ል-ቢይድን (ከየወሩ 13ኛ፣14ኛና 15ኛ ቀኖች) መጾም ፦
عن أبو هريرة رضي لله عنه قل:أوصاني خليلي بثلاث: "صيام ثلاثة أيام من كل شهر، وركعتي الضحى، وأن أوتر قبل أن أنام"
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) "ወዳጅ በሶስት ነገሮች መከሩኝ (በማለት) ከየወሩ ሶስት ቀን መጾም፣ ሁለት ረከአ የዱሀ ሶላት መስገድና ከእንቅልፉ በፊት የዊትር ሶላት መስገድ" (ቡኻሪ በቁጥር 1981 ሙስሊም በቁጥር 1981 ዘግበዉታል)"

#3.ሰኞና ሀሙስ መጾም ፦ የሰኞ ጾም ከሀሙሱ በጣም የጠበቀ ተጠይቀዉ ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል፦


"ذاك يوم ولدت فيه، ويوم بعثت - أو أنزل علي_ فيه"
"ያ ቀን እኔ የተወለድኩበትና በመልዕክት የተላኩበት ወይም በእኔ ላይ ቁርዓን የወረደበት ቀን ነው። ብለዋል። (ሙስሊም 1162)


#በሌላ ዘገባ የረሱል ( ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ወዳጅ እና የወዳጃቸዉ ልጅ ኡሳማ ቢን ዘይድ (ረ.ዐ) "እርስዎ ሽማግሌ ነዎት ለምን የሰኞና የሀሙስ ቀንን ይጾማሉ?" ተብለዉ ሲጠየቁ " የአላህ መልክተኛ ሰኞና ሀሙስን ይጾሙ ነበር ለምን እንደሚጾሙ ሲጠየቁም "የአላህ ባሮች ስራ ሰኞና ሀሙስ ወደ ጌታቸዉ ዘንድ ትቀርባለች"።(አቡ ዳዉድ 2436) ያሉ ስለሆነ የኔ ስራ እኔ ጾመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ።"ብለዋል።
(ቲርሚዝ በቁጥር 747 ዘግበውታል)
ክፍል,2 ይቀጥላል

https://t.me/Latahezn
አቡ የህያ ሱሀይብ ኢብኑ ሲናን (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተከታዩን ተናግረዋል፦"የሙእሚን ጉዳይ እጅግ የሚደንቅ ነው። ሁለ ነገሩ ኸይር (ሰናይ) ነው ።እንጂ ለማንም (የተሰጠ) አይደለም። አስደሳች ነገር ከገጠመዉ ለአላህ ምስጋና (ሹክር) ያደርሳል፤መልካም ይሆንለታል። ጉዳት ካገኘውም (አስከፊ ነገር ከገጠመዉም) ትዕግስት (ሶብር) ያደርጋል፤ ይህም ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"
አልሀምዱሊላህ☺️🙏

(ሙስሊም አንደዘገቡት)
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from لاتحزن
#የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ መናገራቸዉ ተወስትዋል፦

((والله في عون العبد ماكان العبد في عون أخيه))

"ባሪያው ወንድሙን መርዳት እስካላቆመ ድረስ አላህ ባርያዉን ከመርዳት አይቆጠብም።"

https://t.me/httpsLatahzen
ሌሎችን እርዳ
መልሰው ሊረዱህ እንደማይችሉ
       ብታውቅ እንኳን !