La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ማብዛትን ታሳቢ አድርገዉ አለመለገስ
አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል:-

"ማብዛትንም የምትፈልግ ኾነህ:(በረከትን) ከትለግስ።"( አል-ሙደሲር 6)
#አንድ ሙስሊም ሰደቃ ሲሰጥ በአጸፋዉ ከሰዉ የበዛ በረከትን ማግኘትን ፈልጎ መሆን የለበትም።የሚመፀዉተዉ ገንዘብ 💵💵 የቱንም ያህል ቢበዛምየተሰጠዉ የአላህን ዉዴታ ለማግኘት እስከሆነ ድረስ ሌላ አላማ አንግቦ ሰደቃን መስጠት የለበትም። በርግጥ ገንዘቡን ነገ በጣም በሚፈልግበት ጊዜ እፈፊቱ ላይ ያገኘዋል።
# ሆኖም ግን መፅዋቹ ሰደቃዉን ተቀባይነት ይኑረው አይኑረው ባላወቀበት አግባብ ዉስጥ የበዛ ችሮታን አገኛለሁ ብሎ መለገስ የለበትም። ከዚህ ይልቅ ሰደቃው ተቀባይነት እንዲያገኝ በመተናነስና የሆነ ነገርን በመጉደሌ አላህ ባይቀበለኝስ በሚል መስጋት አለበት ። ከዚህም በላይ ሰደቃውን ከሰጠ በኋላ ኢስቲግፋር ማድረግ ወይም የአላህን ማህረት መለመን አለበት።
#ምጽዋቱ ለተገቢዉ ሰዉ መሰጠት አለበት

#ምጽዋት ሲሰጥ ከግምት ውስጥ ሊገቡ ከሚገቡ መስፈርቶች መካከል አንዱ ምጽቱን ለሚገባ እና ይበልጥ ተገቢ ለሆነ ሰው መስጠት ነው። ለምጽዋት ይበልጥ ተገቢ ከሆኑ ሰዎች መካከል ደግሞ የቅርብ ዘመዶችን በግንባር ቀደምነትይጠቀሳሉ።
# ከዚህም በተጨማሪ ለቅርብ ዘመዶች የሚሰጥ ሰደቃ ዝምድናንም ያጠናክራል።
ይህን አስመልክቶ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ)
እንዲህ ብለዋል:-

"ምፅዋት ለሚስኪኑ ሰደቃ ነው። (ሰደቃዉ) ለዝምድና ባለቤት በሚሆንበት ጊዜ ግን (ፋይዳው) መንታ (ጣምራ) ነወ። (እርሱም)ሰደቃና ዘምድናን ናቸው።"(አህመድና ቲርሚዚ የዘገብት)


#ከዚያም ሰደቃው እንደ ሁኔታው ይበልጥ አሳሳቢ ጉዳይ ያለበትና ሲበዛ ፈላጊ ለሆነ ሰዉ ይሰጣል።
#ሙሲባ (አደጋ)

የሰዉ ልጅ ሲሞት ሁለት ሙሲባ (አደጋ)ይወርድበታል። አንደኛው በፀሐይ በብርድ የሰበሰበው እድሜ ልኩን የደከመበት ገንዘቡንና አንጡራ ሀብቱን ጥሎ ይሄዳል። ከርሱ ጋር የሚቀበር ምንም ነገር የለም በጆሮው ላይ የሚደረገው ጥጥ እና የተገነዘበት ከፈን ሲቀር ። ንብረቱን ትቶ ቀብር ይገባል።
#ሁለተኛው አደጋ (ሙሲባ ) ትቶ በሄደው ገንዘብና ንብረት ላይ አላህ (ሱ.ወ) ፊት በገንዘቡ ይጠየቅበታል። ለዚህም ነው አላህ እንዲህ የሚለዉ

"አንዳችሁንም ሞት ሳይመጣውና ጌታዬ ሆይ! እንደመጸውትና ከደጋጎቹም ሰዎች እንድኾን ወደ ጥቂት ጊዜ ብታቆየኝ ኖሮ እመኛለሁ ከማለቱ በፊት ከሰጠናችሁ ሲሳይ ለግሱ።"(አል-ሙናፊቁን 63:10)
#"ከሰጠኋችሁ ጸጋ ሞት ሳይመጣባችሁ ለግሱ ነው" ያለው ጌታችን አላህ (ሱ.ወ) ዝንጉ የሆነው የሰዉ ልጅ ግን ሞት። በሚመጣበት ጊዜ "ጌታዬ ሆይ! ትንሽ ጊዜ ብትሰጠኝ ሰደቃን አደርግ ነበር ሐጅንም እፈጽም ነበር" ይላል። ከንቱ ምኞት ይመኛል። ግን አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ሲል ጥያቄውን ውድቅ ያደርግበታል:-
"ማንኛይቱም ነፍስ የሞት ጊዜዋ በመጣበት ጊዜ አላህ በፍጹም አያቆያትም።
አላህ በምትሰሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው።"(አል-ሙናፊቁን 63:11)


"ከተወሰነች ጊዜ ምንም መዘግየት የለም እኔም የምትሰሩትን ዉስጠ አዋቂ ነኝ" ይላል። ወንድሞች እህቶቼ! አራዳ ወይም ብልጥ ሰው ማለት ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ መልካም ነገርን ያስቀደመ ሰው ነው።
#በሰደቃ መመፃደቅ:- ማለት ለጋሹ እራሱን መልካም ሰው አድርጎ ሲመለከትና ከሰጣቸው ሰዎች ምስጋናን ሲጠብቅ የሚስተዋል ባህሪ ነው። አልያም ደግሞ ከለገሳቸው ሰዎች በምላሹ አገልግሎትን (ኺድማን) ሲፈልግና የሰራውን መልካም ነገር እያነሳ በሰዎች መካከል ተረጂዎችን በጉራው ማሸማቀቁ ነው።
በዱንያ ላይ የሰራነውን ምንም ነገር ከሰዎች ሳይሆን ከሀያሉና ከአዛኙ ከአላህ (ሱ.ወ) የምናገኝ ያርገን አሚን🤲🤲
# በሰደቃችን - የዘነጋናቸው - ሰዎች

#እንደሚታወቀዉ የሰዉ ልጅ ባህሪ ይለያያል። ገሚሱ እያለዉ የሚጠይቅ፣ ከፊሉ ሳይኖረውና ቸግሮት የሚጠይቅ ሲሆን ሌላው ደግሞ ቢቸግረዉም ቢጠመዉም ቢርበዉም ቢያመውም ለማንም አልናገርም ብሎ አንገቱን ደፋቶ የሚቀመጥ ነው። ስለዚህ አሁን የምናየው የተዘነጉ ሰዎች ባህሪ ነው። እንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ባህሪያቸው በጥቂቱ እንደሚከተለው፦

1/ ባላቸዉ ነገር ተብቃቅተውና ካላቸው ጋር ተመሳስለው ይኖራሉ። ቢርባቸውም ቢጠማቸዉም ቢያማቸዉን ማንም ሰው አያውቅባቸዉም።

2/ ሰዉን ቸገረኝ ብለው መጠየቅ የሚያሳፋራቸዉ፣ ቢናገሩም የማይሳካላቸዉ ናቸው።

3/ በመብቃቃታቸው እና በቁጥብነታቸው የተነሳ እንደውም ሰዉ የተሞላላቸው እና የደላቸው ሀብታሞች አድርጎ ይቆጥራቸዋል፤ አላዋቂዉ።


#በጣም የሚገርመዉ ዉስጠ ዐዋቂው ጥበበኛው ጌታ ስለ ባህሪያቸው ነግሮናል። ሰዉን ቢለምኑ እንኳን ችክ የማይሉ፣ ከናካቴው የማይጠይቁ ሰምች በሰደቃ ሊዘነጉ አይገባም። በዚህ አጋጣሚ ሊታወቅ የሚገባዉ መሰረታዊ ነገር ቢኖር የሚለምን ሰዉ ሰው ሁሉ ችግርተኛ እንዳልሆነና የዛኑ ያህል ደግሞ የማይለምን ሰዉ ሁሉ ድሎተኛ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል። ለዚህም ነው እንደነዚህ ሰዎች ሀብታሞች ቢመስሉም በሰደቃ እንዳይዘነጉ ቁርኣንና ሐዲሥም ያስታወሱን።
ወንድሞቻችን አል-ፋቲሁን ጀምዓም ስለነርሱ ባህሪ በነሺዳ እንዲህ ገልጸውልን፦

ሐያእ አድርጎ የሰው ፊት ፈርቶ
ቤቱ ተቀምጦ "ሚበላው ጠፋቶ
ሞቱን ሚጠብቅ ስንት ሰው አለ
ከሰው ላይሻል በአላህ የ...ማ...ለ
ይሄ ነው ድሀ የረሕማን ባሪያ
ይሄ ነው ድሀ የረሕማን ባሪያ
#በሰደቃ ማስከፋት ማለት ደግሞ ተለጋሾችን በንግግር ማስከፋት አልያም ደግሞ በሰዎች ፊት ልግስናውን ማዉራቱ ነዉ።
#አላህ (ሱ.ወ) ለምፅዋት ሕግና ሥርዓትን ከደነገገባቸው ምክንያቶች መካከል አንዱ ተመጽዋቶችን ከዚህ አይነቱ ዳፋ ለመታደግና ክብራቸዉን ለማስጠበቅ ነዉ። አንደሚታወቀዉ ኢስላማዊዉ ሕግ የሰዉን ልጅ ሰብአዊ ማንነቱንና ተፈጥሯዊ ፍላጎቱን እንጂ ዉጫዊ ማንነቱን እና የሀብት ደረጃዉን ከግምት ዉስጥ አያስገባም። ስለዚህ መጽዋቹ የተመጽዋቹን ክብር መጠበቅ አለበት፤ መክንያቱም የሰዉ ልጅ ከአላህ ዘንድ ደረጃ የሚሰጠዉ በሥራው መልካመሰነትና በልቦናዉ ንጽሕና እንጂ በሌላ አይደለምና። ይህንንም በማሰሸመልከት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦


"አላህ መልካችሁንና የሰዉነት ቅርፃችሁን አይመለከትም፤ ነገር ግን እሱ የሚመለከተዉ ልቦነሠችሁን እና ሰራችሁን ነው።"


# ከላይ የተዘረዘሩ ነጥቦች የሰደቃን ተቀባይነት የሚያረጋግጡና በተቃረሠኒዉ ደግሞ ካለሰተሞሉ ሰደቃነሸ የመመየሠመክኑ ነገረሸቸሰ መሆናቸው መገንዘብ አለብን፤ መክንያቱም ለግሰነ መና እነሰዳንሆን መጠንቀቅ ግድ የሰላልና።
Channel photo removed
Channel photo updated
# ስንቶቻችን ነን የመስጠትን ዋጋ ምናቀዉ?

# አብዛኞቻችን መስጠትን የምንረዳበት መንገድ የተሳሳተ ነው። እኛ ሰዎች ሰዉን ለመርዳት እንደ መስፈርት ከምንወስድባቸው ነገሮች በዋናኘት የሚጠቀሰዉ መጀመሪያ አኔ ሳይኖረኝ ሌላውን እንዴት አረዳለው፣ ካለን ነገር ግማሹን እንኳን ለመስጠት እንዴት ይሄ ለሰዉ ይሰጣል ከሰጠውማ በደንብ ነው እያልን በትናንሽ ነገሮች የኸይር ስራ በሮችን እንዘጋለን ። ነገር ግን ይህ አስተሳሰብ አሁንም ቢሆን በአላህ መንገድ ተጉዘን ኸይር ስራዎችን እንዳንሰራ እያደረገን ነዉ።" አንድ ሰው ሰውን ለመርዳት ሰዉ መሆን በቂ ነው ።" ኸይር ስራን ለመስራት ግዴታ ከምንበላው፣ ከምንለብሰው መትረፋ የለበትም ካለችን ላይ መስጠትን ብንለምድ አንድም እናት የልጇን መራብ እያየች አታለቅስም፣ አንድም አባት ልጆቹ ሚጠይቁትን እንደ አባት ባለሟሟላቱ እያሰበ አያዝንም ነበር። አንድም ሕፃን ጓደኞቹ ትምህርት ቤት ሲሄዱ እቤት ኩጭ ብሎ አይተክዝም ነበር። እስኪ ስንቶቻችን ነን የነዚ ሰዎች ህመም ሚሰማ እንዴትስ ነው ከንደዚህ ዓይነት የሰቀቀን ህይወት የምናወጣቸው ? ብለን አስበን እናቃለን ? ሁላችንም ራሳችንን እንፈትሽ። ካለን ነገር አካፍለን የመስጠትን ዋጋ ብናዉቃት ምናለ ምናለ ለኔ ቀርቶብኝ ለወንድሜ በሰጠሁ እስከምንል ድረስ ነው። እኛ አንድ ስንሰጥ አላህ (ሱ.ወ) እጥፍ አርጎ ይመልስልናል ዛሬ ካለን ላይ የሰጠናት ነገር ምን አልባት አንድ ቀን ተመልሳ ትመጣለች ። ከሁሉም ግን የአንድ እናት ምርቃት ነፍስ ታድሳለች ምነው ደጋግሜ እየሰጠዉ በኖሩክ ያሰኛል። ብቻ በመስጠት ውስጥ ሰላም፣ በመስጠት ዉስጥ ደስታ ሌላውና ትልቁ በመስጠት ውስጥ ራሳችንን እናገኛለን ለካ ከኔም የባሰ አለ እንድንል ያረገናል። የቲሞችን ወገናችን እናቶችን ከጉናችሁ ብለን አብረናቸው ልንሆን ይገባል። አላህ የምንሰጠውን ከልባችን የምንሰጥ ያርገን።
Bint mohammed
#ባሏ የሞተባት የ የቲሞቹ እናት

# በአላም ላይ ብዙ አይነት ስቃዮች ይኖራሉ። የቲም ልጆቿን ይዛ እንደምትሰቃይ እናት ግን ማንም አይሰቃይም።


አላህ (ሱ.ወ) ይህንንም አይቶ ትልቁን ትዕግስት ሰቷቸዋል።


#የ የቲሞቹ እናት ስቃይ "ሀ" ብሎ የሚጀምረዉ ባሏን የልጆቿን አባት በሞት ከተለየቸበት ሰዓት ይጀምራል። አባት ሩሁ ስትወጣ ወዳጅ ጠላት ዘመድ አዝማድ ሁሉ ተሰባስቦ ወደ ማትቀርበት አለም ተሰባስበዉ ይሸኙታል።

እንዲያ ሲሰባሰቡ ምናለ በሰዎች ብዛት የ የቲሞችን አባት ነፍስ መመለስ ቢቻል ያስብላል።


#እንዲያም ሆኖ እናትና ልጆች ግን እንግልታቸዉን አይቀንስም። ልጆች የማሳደግ ኃላፊነት የማስተማር የማልበስ የማጠጣት ኃላፊነት ከ አላህ በታች በ እናት ላይ ይወድቃል። አተዋቸዉ ነገር ከጉያዋ የወጡ ልጆቿ ናቸዉ።

ግዴታ ከሰው እኩል አርጋ ማሳደግ አለባት። እናት ናትና ልጆችዋ ምንም እንዲሰማቸው እንዲጎልባቸዉ አትፈልግም። ለ ልጆችዋ ብላ የሰዉ ፊት አይታ የስንቱን ስድብ ግልምጫ ቻል አርጋ ክፍተት ለመሙላት ትጥራለች።

የስዋ ህልም ልጆችዋ ናቸዉና ህልማቸዉን ለማሳካት የተሻለ ት/ት ቤት ምንም እንዳይ ጎልባቸው አርጋ ታሳድጋቸዋለች። በ አላህ መንገድ ታንፀዉ ታላላቆቻቸውን አክብረዉ ለታናኖሻቸዉም አዛኝ ሆነው እንዲያድጉ የበኩልዋን ትጥራለች።

የቲምነት ተሰምቷቸዉ አንገታቸዉን እንዳይደፉም አናትም አባትም ሆና ታሳድጋቸዋለች።ይሄ ሁሉ ስትለፋ ግን አንድ ዘመድ ወዳጅ ነኝ ባይ አይመጣም ሞችን እንደሸኙ ላይመለሱ በዛዉ ይቀራሉ።
እ እ እ እ እንዴት ናቹ ምን ጉደላቹ አይዝዋቹ አብሽሩ ባይ እንኳን ይጠፋል። ያኔ ሌላ ሀዘን😔😔😔😔

#ሰዉ እያለ የልጆችዋ መራብ ዉስጧን ይነካታል። ትላንት እሷ ለጋሽ ሆና እያለ ዛሬ ከሰዉ መከጀልዋ ቢሰማትም ልጆችዋን ስትል ግን ሁሉንም ማለፍ እንዳለባት ታምናለች። በዚህች ምድር ላይ ስትኖር ትልቁ ተስፋዎቿ ልጆቿ ናቸው።

#አልገባን አለ እንጂ እንደዚህች እናት ቻይ እንደዚህች እናት ኢማነኛ እንደዚህች እናት ባላት ነገር አመስግና አዳሪ የለችም።ምን ቢከፋት ምን ብታጣ ችግሯን ከ ልጆቿ ጋር ማለፋ የምትፈልግ ምርጥ እናት ነች።😍


#መርዳት ባንችል እንኳን ምናለ ጊዚያችንን እኛን ማይመጥኑን ቦታ ከምንዉል እነሱን በመዘየር ብናሳልፍ ትንሽም ብትሆን ያለችንን አካፍለን አብረናቸዉ ስቀን ሰዉ እንዳላቸዉ አሳይተናቸዉ ብንመለስ መቼም ቢሆን ጥሎ ማይጥለንን ዱዓቸዉን ተቀብለን እንመለስ ነበር።


# እህት ወንድሞቼ ይሄን ምታነብ ሁሉ ምን አልባት ይህችን እናት ከልባችን ልብ አላልናትም ይሆናል።

ግን እንደስዋ ሰዉነትዋ ክሰል እስኪመስል ድረስ ልጆችዋን ለማሳደግ የስቃይን የእንግልትን ጥግ የሚያይ የለም።

# እንደዉ ለማስታወስ ያክል እንጂ እንበል ካልንማ ፅፈንም አዉርተንም አንጨርስም ።


#አላህ (ሱ.ወ) ለናቶቻችንም ለየቲም ወንድም እህቶቻችን ሀዘን አርቆ ደስታን ያሳያቸው።ችግርን አባሮ በረካ ይግባላቸው።

ባነበብነው ምንጠቀም አላህ ያርገን.......... አሚንንንንን



Bint Mohammed

https://t.me/httpsLatahzen
#ማንም ስላለዉ ወይም ሞልቶ ስለተረፈዉ አደለም ሚሰጠው። ግን እሱ ጠግቦ አድሮ ወንድሙ ሲራብ ማየት ማንስ ያስችለዋል?????

የወንድሙ ችግር የኔም ነው ብሎ ከሱ የባሰም እንዳለ በማሰብ ያለዉን አካፍሎ ጌታውን አመስግኖ ያድራል።

#ሙዕሚን ማለት ይሄ ነው

#ማንኛውንም እርዳታ መስጠት ምትፈልጉ ኸይር ፈላጊዎች ካላችሁ ወይም አብሮ መስራት ምትፈልጉ በዚ ስልክ ያናግሩን +251945064709
ኑርአህመድ
+251937849354
ራቢያ ሙሀመድ
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳንሰህ አትመልከት ፤ወንድምህን

በብሩህ ፈገግታ መገናኘት ቢሆን እንኳን"
ነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)
# ስንት አይነት ለጋሽ አለ


1 /ከ አላህ (ሱ.ወ) አገኘዋለዉ ብሎ ሚነይት


# ሚስኪኖችን በመንከባከብና በመርዳት የሰራውን በጎ ተግባር ከሰዎች ሙገሳና አድናቆትን ሳይሻ ከብቸኛው ጌታ ከጠየቁት ማይከለክል መልካም ነገር ለሰሩት ምንዳዉን እጥፍ ድርብ አርጎ ሚከፍለዉ ከ (ዐ.ሱ.ወ) ብቻ ሚጠብቅ ለርሱም ሚያገለግል ነው።




2/ ታዋቂ ለመሆን

# አሁን ያለንበት ጊዜ የተደፉን አንገት ቀና አርጌ እንዴት ላስደስት ሳይሆን ምን አርጌ ታዋቂ ልሁን ሚለዉ ነው ያሳሰበን።
ጊዜው ካመጣቸው ነገሮች አንዱ social mdia ነው። Tik tok you tube የመሳሰሉት ናቸዉ።

ይሄን ያህል ሰጠው ይሄን ያህል ልሰጥ ነው እያሉ በ አላህ ዘንድ ሳይሆን በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን ቀን ከሌት ሳይሉ ይተጋሉ። በሰሩት ልክ አላህ ሳይሆን የሰው ልጅ የሚከፍላቸው ይመስላል።

#የሰው ልጅ ሆኖ followe ለመሰብሰብ በነኚህ ሰዎች መነገድ ግን አይከብድም ?????🤔 ሆኖም ግን ለመልካም ነገር ምንጠቀም እንዳለን ሁሉ ለመጥፎ ነገር ሚጠቀምም አይጠፋም።


3/ ሰው ሲሰጥ ብቻ የሚሰጥ
#የሚሰጠዉ ነገር ለዛ ሰዉ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ፈፅሞ ማያዉቅ።
#ለኛ ትንሽ ነው ብለን የምንሰጠው ነገር የእውነት ለዛ ሰው ምን ያህል ትልቅ አንደሆነ የምናውቀው ከልባችን ስንሰጥ ነው።

#ለምሣሌ፦ የርሀብን ሥሜት የምናውቀው ቤታችን ውስጥ አደለም ምግብ የምግብ ስም የማይነሳበት ደረጃ ደርሶ ስንራብ ነዉ።

#የ ችግርን ሥሜት ምናዉቀው ዓጊኝቶ ማጣትን ስናይ ነዉ።

# የህመምን ስሜት ምናዉቀው ታሞ መዳንን ስናይ ነው።

#እንደዉ ለቁጥር ያክል እነዚህን አልን እንጂ ሁሉም የሚሰድቅበት ምክኒያት አለው። ከሰጠን አይቀር ግን አላህ (ሱ.ወ) በሚያዘን መንገድ ብንሰጥ ይበልጥ ተጠቃሚዎች እንሆናለን።


"አንብብ በዚያ (ሁሉን)በፈጠረዉ ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳንሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘት እንኳን" ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)




https://t.me/httpsLatahzen


Bint Mohammed
#ለምን ግን አመስጋኝ መሆን ተሳነን??????????

የ ሰው ልጅ ሆንን ና ዝቅ ብለን ኖረን ካላየን ያለንበትን አናመሰግንም ።

#ያለንበት ህይወት ምንም ይሁን ምን አልሀምዱሊላህ ማለት ነው።አመስጋኝ ባርያ በሆንን ቁጥር አላህ (ሱ.ወ) ካለን ላይ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይሰጠናል።

#እስኪ ለማስተዋል እንሞክር በአሁኑ ጊዜ እኛ በቀን 3 ከዚያ በላይ እየበላን በቀን አንዴ በልቶ ማደር የከበደዉ ስንት አለ??????


#አኛ ልብስ ተርፎ ሞልቶን ምን እንደምናረገው ግራ ይገባናል
ግን ሙሉ ሰውነቱን በቅጡ ሚሸፍንለት ልብስ ያጣ ስንት አለ?????


#ከዚ ሁሉ ሚገርመው ባንድ ሀገር ላይ ሁለት ሦስት ቦታ ላይ መኖሪያ ቤት ያለን ስንኖር ሌላው ማደሪያ ጎኑን ማሳረፍያ የሌለው ህዝብ ስንት አለ?????

#እንደሀቁ ከሆነማ እነዚህን ሁሉ እያየን

እናመሰግን ነበር ።

#ግን የሁላችንም አይን ዱንያ ላይ ብቻ ሆኖ የራሳችን እንጂ ሌላው አይታየንም ማንንስ አይተን እናመስግን አመስጋኝ ባሪያም ምንሆነው ከኛ በታች ያሉ ሰዎችን ዝቅ ብለን ኑሯቸውን ውሎአቸውን ስንመለከት አላህ (ሱ.ወ) የሰውን ልጅ ለማስተማር የሚጠቀምበት መንገድ እናይበታለን።

#እኛ እነሱን አይተን ከኔ የባሰም አለ አነሱም ሌላውን አይተው እንደዛው ሁሉም ያለበትን ደረጃ እያየ ምንያክል ደስተኛ እና እድለኛ እንደሆንን እንረዳ ነበር።

#አሁንም ቢሆን ለማመስገን ጊዜው አረፈደም። አላህ (ሱ.ወ) በሰጠን እያንዳንዱ ነገር ምን ያክል እድለኛ ደስተኛ እንደሆንን እያሰብን እናመስግን።
ምሥጋና የራህመት በር ነው ስናመሰግን ካለን ላይ ይጨመርልናል በቻልነው አቅም ባለን ነገር አልሀምዱሊላህ ብለን እንደር

አመስግነው ከሚያድሩት ባሪያ አላህ ያርገን🤲🤲🤲



"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from لاتحزن
አንድ ሙስሊም በሙስሊም ወንድሙ (ወይም እህቱ) ላይ ያለው ግዴታ በእስልምና አስተምህሮ ላይ የተመሰረተ እና ርህራሄን፣ ድጋፍን እና ሃላፊነትን ያጎላል። አንዳንድ ቁልፍ ነጥቦች እነኚሁና፡

1. ወንድማማችነት እና አንድነት፡- ሙስሊሞች በእምነት ወንድም እና እህቶች ተደርገው ይቆጠራሉ (ቁርኣን 49፡10)። ይህ ትስስር በማህበረሰቡ ውስጥ አንድነትን እና አንድነትን ያበረታታል.

2. መደገፍና መረዳዳት፡- ሙስሊም ወገኖቻቸውን በችግር ጊዜ በስሜታዊ ድጋፍ፣ በገንዘብና በአካላዊ እርዳታ መርዳት የሙስሊም ግዴታ ነው።

3. የበጎ ማበረታቻ፡- ሙስሊሞች እርስበርስ በመከባበርና ገንቢ በሆነ መልኩ በጎ ተግባርን (አማር ቢል መዓሩፍ) እንዲሰሩ መበረታታት እና ጥፋትን (ነሂ አኒል ሙንከር) ተስፋ ማድረግ አለባቸው።

4. ይቅርታና ትዕግስት፡- እስልምና ይቅርታንና ትዕግስትን አስፈላጊነት ያስተምራል። ሙስሊሞች የሌሎችን ስህተት በመመልከት ደግነትን ለመለማመድ መጣር አለባቸው።

5. መተማመንን እና ሚስጥራዊነትን መጠበቅ፡ መተማመን በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ ነው። ሙስሊሞች መተማመንን ማክበር እና የአንዱን ሚስጥር በአክብሮት መያዝ አለባቸው።

6.  የታመሙትን መጎብኘት እና የቀብር ስነስርአት ላይ መገኘት፡- ሙስሊሞች የታመሙትን እንዲጎበኙ እና በቀብር ሰላትና በቀብር ስነስርአት ላይ በመሳተፍ በአስቸጋሪ ጊዜያት ርህራሄ እና አጋርነት እንዲያሳዩ ይበረታታሉ።

7. እርስ በርስ መጸለይ፡- አንዱ ለሌላው ዱዓ ማድረግ (ልመና) ደጋፊ ማህበረሰቡን ማፍራት ትልቅ ድርሻ ነው።

8. ሰላምን ማስፋፋት፡- ሙስሊሞች በሙስሊም ወገኖቻችን መካከል ሰላምና እርቅ እንዲሰፍን፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በማጠቃለያው አንድ ሙስሊም ለሙስሊም ወገኖቹ ያለው ግዴታ ማህበረሰቡን የሚያጠናክር እና የተስማማ ማህበረሰብን የሚያጎለብቱ ደጋፊ ፣ሩህሩህ እና ስነ ምግባራዊ ባህሪያትን ያጠቃልላል።

   የሕያ ቢን أبي كثير እንዲህ ይል ነበር……

"አንድ ሰው ላይ ሁለት ነገሮች ካየህ ከጀርባቸው ከእነርሱ የበለጠ ኸይር እንደሚኖረው ዕወቅ;
1ኛው, ምላሱን የሚቆጣጠር ሲሆን
2ኛው, ሰላቱን የሚጠባበቅ ከሆነ"
      /ابن أبي الدنيا في الصمت ٥٦٤/

Ibnu muhammed
https://t.me/httpsLatahzen
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ያጀምዓ እንዴት ናችሁ
ዛሬ ማለትም 9/04/2017 ከምሽቱ 3:00 ሹራ ስለሚኖረን ኸይር ስራ መስራት ሚፈልግ በሀሳብም፣በጉልበት፣በገንዘብ፣በአልባሳት እንዲሁም አባል ሆኖ ከኛጋመስራት ሚፈልግ አብረን ሹራ እንድናረግ አልያም በወስጥ እንድታናግሩን እንደ አላህ ፍቃድ የቻለዉን ያክል ሰበብያውን እንድናደርስ ዘንድ የ ላታህዘን አሚሮች በአላህ ስም እንጠይቃለን🙏
አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
ሹራ የሚደረግበት ግሩፕ:-https://t.me/Latahezn
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
#በአላህ ፍቃድ ስለ ተወደዱ ጾሞች ትንሽ ነገር እተዋወሳለን
#ክፍል,1
እነዚህ የጾም ዓይነቶች ለአላህ ምስጋና ይገባወና ምንዳን ማብዛት ለፈለገ ሰው ቁጥራቸዉ በጣም ብዙ ሲሆኑ ከነሱም መካከል ፦

#1.አንድ ቀን መጾም አንድ ቀን መፈሰክ፦ ይህ ጾም የነብዩላህ ዳውድ(ዐ.ሰ) ጾም ሲባል እሱም ከግዴታ ጾሞች ቡኋላ በጣም በላጩ ነው። ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአብደላህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፦

قال النبي(صلى لله عليه وسلم)، لعبد لله بن عمرو: "صم يومآ، وأفطر يومآ، وذللك صيام داود (عليه السلام)، وهو أعدل الصيام"

"አንድ ቀን ጹሙ አንድ ቀን ፈስክ ይህ የዳዉድ ጾም ሲሆን ይህ ፍትሀዊ ጾም ነው።(ቡኻሪ ቁጥር 1976፣ ሙስሊም በቁጥር ላይ 1159 ዘግቦታል)

#2.አያመ-ል-ቢይድን (ከየወሩ 13ኛ፣14ኛና 15ኛ ቀኖች) መጾም ፦
عن أبو هريرة رضي لله عنه قل:أوصاني خليلي بثلاث: "صيام ثلاثة أيام من كل شهر، وركعتي الضحى، وأن أوتر قبل أن أنام"
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) "ወዳጅ በሶስት ነገሮች መከሩኝ (በማለት) ከየወሩ ሶስት ቀን መጾም፣ ሁለት ረከአ የዱሀ ሶላት መስገድና ከእንቅልፉ በፊት የዊትር ሶላት መስገድ" (ቡኻሪ በቁጥር 1981 ሙስሊም በቁጥር 1981 ዘግበዉታል)"

#3.ሰኞና ሀሙስ መጾም ፦ የሰኞ ጾም ከሀሙሱ በጣም የጠበቀ ተጠይቀዉ ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል፦


"ذاك يوم ولدت فيه، ويوم بعثت - أو أنزل علي_ فيه"
"ያ ቀን እኔ የተወለድኩበትና በመልዕክት የተላኩበት ወይም በእኔ ላይ ቁርዓን የወረደበት ቀን ነው። ብለዋል። (ሙስሊም 1162)


#በሌላ ዘገባ የረሱል ( ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ወዳጅ እና የወዳጃቸዉ ልጅ ኡሳማ ቢን ዘይድ (ረ.ዐ) "እርስዎ ሽማግሌ ነዎት ለምን የሰኞና የሀሙስ ቀንን ይጾማሉ?" ተብለዉ ሲጠየቁ " የአላህ መልክተኛ ሰኞና ሀሙስን ይጾሙ ነበር ለምን እንደሚጾሙ ሲጠየቁም "የአላህ ባሮች ስራ ሰኞና ሀሙስ ወደ ጌታቸዉ ዘንድ ትቀርባለች"።(አቡ ዳዉድ 2436) ያሉ ስለሆነ የኔ ስራ እኔ ጾመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ።"ብለዋል።
(ቲርሚዝ በቁጥር 747 ዘግበውታል)
ክፍል,2 ይቀጥላል

https://t.me/Latahezn
አቡ የህያ ሱሀይብ ኢብኑ ሲናን (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተከታዩን ተናግረዋል፦"የሙእሚን ጉዳይ እጅግ የሚደንቅ ነው። ሁለ ነገሩ ኸይር (ሰናይ) ነው ።እንጂ ለማንም (የተሰጠ) አይደለም። አስደሳች ነገር ከገጠመዉ ለአላህ ምስጋና (ሹክር) ያደርሳል፤መልካም ይሆንለታል። ጉዳት ካገኘውም (አስከፊ ነገር ከገጠመዉም) ትዕግስት (ሶብር) ያደርጋል፤ ይህም ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"
አልሀምዱሊላህ☺️🙏

(ሙስሊም አንደዘገቡት)
https://t.me/httpsLatahzen