La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
▣አቡ ሁረይራ ረድየሏሁ ዐንሁ ▣
┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

ክፍል 1⃣
❒❒🌹❒❒

" አቡ ሁረይራ ለሙስሊሙ ህብረተሰብ (ኡምማ ከ 5374 በላይ ሐዲሶችን ጠብቆ አቆይቷል።" (የታሪክ ሊቃውንት)

ዐን አቢ ሁረይረተ ረድየሏሁ ዐንሁ ቃለ፣ ቃለ ረሱሉሏሂ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም...."

በዚህ ሀረግ አማካኝነት ከኢስላም የመጀመርያ ታሪክ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሙስሊሞች አቡ ሁረይራ የሚለውን ስም ሊለምዱት ችለዋል። በንግግሮችና በትምህርቶች፤ በጁምአ ኹጥባወችና በአውደ ጥናቶች፤ በሐዲስ፤ በፊቂህና በታሪክ መጽሐፍት አቡ ሁረይራ የሚለው ስም በዚህ መልኩ ይጠቀሳል።



በእሳቸው አስደናቂ ጥረቶች አማካኝነት በሺወች የሚቆጠሩ ሐዲሶች (የረሱል ሰ.ዐ.ወ ንግግሮች) ለቀጣዩ ትውልድ ተላልፏል። በሐዲስ ዘጋቢወች መዝገብ ውስጥ የእሳቸው ስም ዝርዝር ግንባር ቀደም ነው። ከእሳቸው ቀጥሎ አብደላህ ኢብን ዑመር ረ.ዐ፣ አነስ ኢብን ማሊክ ረ.ዐ፤ ኡሙል ሙእሚን አዒሻ ረ.ዐ፣ ጃቢር ኢብን ዐብደላህና አቡ ሰኢድ አልኹድሪይ ረ.ዐንሁም ከአንድ ሺህ በላይ የሚሆኑ ሐዲሶችን እና ገቢር እንቅስቃሴዎች ለትውልድ አስተላልፈዋል።

አቡ ሁረይራ እስልምናን የተቀበሉት እሳቸው የሚገኙበት ደውስ የተባለው ነገድ መሪ በሆነው ጡፈይል ኢብን ዐምር አማካኝነት ነው። የደውስ ጎሣ አባላት ይኖሩ የነበሩት በደቡብ ዐረቢያ የቀይ ባህር ዳርቻን ተከትሎ ባለው ክልል ውስጥ ነው። ጡፈይል ነብዩን ሰ.ዐ.ወ ከተገናኘና በእሳቸው ተልዕኮ የመጀመርያ አመታት ውስጥ ሙስሊም ከሆነ በኋላ ወደመኖሪያ ሰፈሩ በተመለሰ ጊዜ ጥሪውን ከተቀበሉት የመጀመሪያወቹ ሰወች አቡ ሁረይራ አንዱ ነበሩ። በድሮ እምነታቸው ላይ ለረጅም ጊዜ ችክ ብለው እንደቆዩት አብዛኞቹ የደውስ ተወላጆች አልነበሩም።



ጡፈይል በድጋሚ መካ በሄደ ጊዜ አቡ ሁረይራም ረ.ዐ ተከተሉ። እዚያም የተከበሩትን ነብይ ሰ.ዐ.ወ የማግኘት ክብርና ዕድልን ተጎናፀፉ። ረሱል ሰ.ዐ.ወ "ስምህ ማነው? ሲሉ ጠየቁት እሳቸውም "ዐብዲሸምስ-የፀሀይ ባርያ ብለው መለሱ። ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከዚህ ይልቅ ዐብዱረህማን ብትባልስ አሉት።
"እሺ የአላህ መልእክተኛ ዐብዱረህማን ይሁንልኝ" በማለት መለሱ።

ይሁንና አብዱረህማን ይበልጥ የሚታወቁት "አቡ ሁረይራ" በሚለው ቅፅል ስም ነው። የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም "የድመት አባት" ማለት ሲሆን ስያሜውን ያገኙት ድመቶችን ይወዱና ከልጅነታቸው ጀምሮ አጫዋች ድመት ያረቡ ስለነበር ነው።



አቡ ሁረይራ ለበርካታ ዓመታት የቆዩት በጢሀማህ ሲሆን ከሂጅራ በኋላ በሰባተኛው ዓመት መጀመሪያ ላይ ነበር ከሌሎች የጎሣቸው አባላት ጋር ሁነው መዲና የገቡት። በዚያ ጊዜ ነብዩ ሰ.ዐ.ወ ወደ ኸይበር ዘመቻ ሂደው ነበር። አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ምግብና ሌሎች መሰረታዊ ቁሳቁሶች ስላልነበሯቸው ከ "አህለስ ሱፋህ" ሰወች ጋር ተቀላቀሉ ማረፊያቸውንም መስጊድ አደረጉ። ልጅም ሚስትም አልነበራቸውም።

ይሁንና ከሙሽሪክነት (አጋሪነት) ያልተላቀቀችው እናታቸው አብራቸው ነበረች።

አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ምግብና ሌሎች መሰረታዊ ቁሳቁሶች ስላልነበሯቸው ከ "አህለስ ሱፋህ" ሰወች ጋር ተቀላቀሉ ማረፊያቸውንም መስጊድ አደረጉ። ልጅም ሚስትም አልነበራቸውም።ይሁንና ከሙሽሪክነት (አጋሪነት) ያልተላቀቀችው እናታቸው አብራቸው ነበረች። እናታቸው ሙስሊም እንድትሆን በፅኑ ይመኙና ዱአ ያደርጉላት የነበረ ቢሆንም ማንገራገሯ አልቀረም።

አንድ ቀን በአንድ አላህ ብቻ እንድታምንና የአላህንም ነብይ እንድትከተል ሲመክሯት ስለነብዩ አንዳንድ ቃላትን ተናገረች። አቡ ሁረይራ እጅግ አዘኑ። ዐይናቸው እንባ እንዳቀረረ ወደ ረሱል ሰ.ዐ.ወ ሄዱ። ረሱልም " አንተ አቡ ሁረይራ ለመሆኑ ምን ያስለቅሳል?" አሉዋቸው። እናቴ እናቴ ኢስላምን እንድትቀበል ከመገፋፋት ወደ ኋላ ብየ አላውቅም። እሷ ግን ሁልጊዜ በንቀት ትቃወመኛለች። ዛሬም እንደገና ብነግራት የማልወዳቸውን ቃላቶች ከእርሷ ሰማሁ። የአቡ ሁረይራ እናት ልብ ኢስላምን ለመቀበል እንዲገራ ሁሉን ማድረግ ለሚችለው አላህ ሱ.ወን ይለምኑልኝ ሲል አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ረሱልን ሰ.ዐ.ወ ተማፀኑ



ረሱል ሰ.ዐ.ወ የአቡ ሁረይራን ጥያቄ በመቀበል ዱአ አደረጉላት። ከዚያ በኋላ ስለሆነው አቡ ሁረይራ ረ.ዐ ሲናገሩ "ወደ ቤት ስሄድ በሩ ተዘግቶ አገኘሁት። የሚቀዳና የሚፈስ ውሀ ድምፅ ሰማሁ። ወደቤት ለመግባት ስሞክር እናቴ "አንተ አቡ ሁረይራ እዛው ቆይ" አለችኝ። ከዚያ ልብሷን ከለበሰች በኋላ ግባ አለችኝ ገባሁ "ከአላህ በስተቀር በሀቅ የሚገዙት ሌላ አምላክ እንደሌለ እመሰክራለሁ፤ ሙሀመድ የእሱ አገልጋይና መልእክተኛ መሆኑንም እመሰክራለሁ" በማለት ቃሏን ሰጠች።

ቀደም ብየ በሀዘንና እያለቀስኩ እንደሄድኩት ሁሉ አሁን ደግሞ የደስታ እንባ እያፈሰስኩ ወደ ነብዩ ሙሀመድ ሰ.ዐ.ወ ተመልሸ ሄድኩና "የአላህ መልእክተኛ ሆይ፣ የምስራች ዜና አለኝ። አላህ ሱ.ወ የርሰወን ዱአ ተቀብሎ የአቡ ሁረይራን እናት ወደ ኢስላም መርቷታል አልኳቸው።

አቡሁረይራ ረ.ዐ ነቢዩን ሰ.ዐ.ወ ሲበዛ ወደዷቸው። ውለታ ለመክፈልም ፈለጉ። የፀኃይን ጨረር ሁሉ የያዘ የሚመስላቸውን የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ፊት ማየትና ንግግራቸውን ማዳመጥ በጭራሽ ሰልችቷቸው አያውቅም ነበር። ላገኙት መልካም ዕድል ዘወትር አላህን ያወድሱትና ለራሳቸው "አቡ ሁረይራን ወደ ኢስላም ለመራው አምላክ ምስጋና ይገባው። ለአቡ ሁረይራ የነብዩን ሰ.ዐ.ወ ጓደኝነት እንዲያገኝ ለረዳው አምላክ ምስጋና ይድረሰው" ይሉ ነበር።



አቡ ሁረይራ ረ.ዐ መዲና ከደረሱበት ወቅት ጀምሮ እውቀት ለመሰብሰብ ልባቸውን ክፍት አድርገው ነበር። የረሱል ሰ.ዐ.ወ ታዋቂ ጓደኛ ዘይድ ኢብኑ ሳቢት ረ.ዐ የሚከተለውን ተናግረዋል፦ አቡ ሁረይራ እኔና ሌላ ጓደኛየ መስጊድ ውስጥ ዱአ እያደረግን ሳለን ረሱል ሰ.ዐ.ወ መጡ
ኢንሻአላህ ይቀጥላል
የአሏህ መልእክተኛﷺ እንድህ ብለዋል ‹‹አሏህን መገናኘት የወደደ ሰው አሏህም ሊያገየው ይወዳል›› (ቡኻሪ)
ከሱ ዉጭ ሌላ መድሃኒት እንደማያውቅ ሰው ዱዓህን ወጥረህ ያዝ። ዱዓ ዱዓ ዱዓ ...
በሰው ለሰው ግንኙነቶች ዉስጥ የመጀመርያዎቹ መስተጋብሮች እውነተኛ አቋሞች ሳይሆኑ ግልብ ስሜቶቹ ናቸው።
እውነተኛ ማንንቶች የሚንፀባረቁት ከጊዜ በኋላ ነው። መረጋጋትና መስከን ይበጃል።
ጓደኛ ይኑርህ
~~
በቀናው መንግድላይ የሚተባበርህ
ሚስጥስርህንአውቆ ዱዐ
እሚያረግልህ

በችግርህ ጊዜ የሚሆን ከጎንህ
ደስታህ አስደስቶት የሚደሰትልህ

ከሀራም ነገሮች የሚከለክልህ
ከሺርክ ከቢድዐ አንስቶ የሚያዞርህ

በተውሂድ በሱና አንተን የሚያንጵህ
ምንም ነገር አድርግ የማይጠረጥርህ

አስመሳይ ያልሆነ ጓደኛ ይኑርህ

(ኢብኑ ሙሀመድ ) ግንቦት 13 2014
"ጭንቀ ጥብብ ሲልህ ሁሌም
ይህን የቁርዐን አያ አስታውስ
💎ኒቃቢስቷ እንስት አንቺ ነሽ አንደኛ !!!

➸ተውሂድን አጥብቃ ሱናን አሣምራ
ከዘፈን እርቃ ቁርአን የምትቀራ!!

➸ጥብቅ የሆነችው ሀያእ ተከናንባ
ለዲኗ ምተጋ እውቀትን ተላብሳ!!

➸ቁጣዋ አስደንጋጭ ልክ እንደ አንበሳ
ካሉባልታ ወሬ ከአጉል ጨዋታ!!

➸አትፈልግም እሷ ማይረባ ዛዛት
እንቁ ፅጌሬዳ .የኢስላም አበባ!!

➸በእንዳንቺ አይነቱ ዲናችን ያብባ
ትውልድን ፍጠሪ ምንም ሳትፈሪ!

➸ባለሽበት ፅኚ በዚሁ ጠንክሪ

የፈላስፋ ወሬ መቼም እንዳትፈሪ!!

➸ነፃነት የሰጠሽ ዲንሽን አክብሪ
ለአለም ስኬት አንቺ ነሽ ተጠሪ
እናት ነሽ እና ልጆችን መካሪ!!

ኑር
[[ክብር ነው ሴትነት]]
<==================>
የዚህች ምድርውበት ግርማ ነሽ የጀነት፡
የፍትህ ፍርድ ነው የሚጣፍጥ እውነት፡
በለቅሶ ዝቅ አይልም አይገንም በኪነት፡
የተፈጥሮ ቃል ነው ሚዛን ነው ሴትነት፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;//;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ሴትነት………!!!
ሰዋዊ ሴትነት ሴትነት ሰውነት
ደግነት አብሳሪ የበጎነት ስምረት
ጀግንነት ሴትነት ሴትነት ጀግንነት
የሰውነት ኪሎ ውበት ለወንድነት፡
የሴት ስም አታጥፉ ክብር ነው ሴትነት፡
ከልቤ ውስጥ ያለው ይሔ ነው የኔ እውነት፡
የማንነት ሚስጥር የእናትነት ፀጋ፡
የመኖሬ ሰበብ የስትንፋሴ ዋጋ፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;///;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ሴትነት!!
የጌታችን ፀጋ ውበት ነች ስጦታ፡
ሞገስ የተቸረች በሀያሉ ጌታ፡
መግባቢያ ቃል፣
ጥሩ ነገር ግሩም ሀረግ፡
የኛ ግርማ ፤
የወንድ አልቦ ጌጥ ማዕረግ፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;//;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ሴትነት………
ሰው የምታክም በእርሷ ህመም ፡
በሴት ክብሯ አፍሳ ደም ፡
እርሷ ቅኔ ፤
ነችና ለኔ፤
እዚህ የመድረሴ ወኔ፡
አንድም ቀን ሣልል ወይኔ፡
ድንቅ ህብረ ቃል ሰም እና ወርቅ፡
ሙሉ ማንነት ትርጉመ ጥልቅ፡
ሴትነት ነው ፍቸ ረቂቅ፡
ደግነቷ ወሰን የልሽ ከሁሉ አልፎ የሚርቅ፡
ለማንም በጎ አድራጊ፡
ሁከትን አረጋጊ፡
ሰውነትን አረጋጊ፡
የትልቅ ታሪክ ባለቤት የውበት አንፀባራቂ፡
እናት በሚል ሶስት ፊደል አለማችንን አድማቂ፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;//;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
እናትነት…………!!!
የችግር ቀን ቀን ሲጎድል~መሸሸጊያ፡
የሁሉም ቤት መግቢያ መውጫ መናኸሪያ፡
የግርማ ልክ ሞገስ መሆን ~መታፈሪያ፡
ሚዛን መሆን የልኬት ምንጭ~መሰፈርያ፡
እናትነት ነው ለኔ ሰው የመሆን መጀመሪያ፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;///;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
እናት………
እርሷ ሴንተር ምስራቅ ዋልታ፡
የማትነጥፍ በጧት ማታ፡
ፀሀይ መውጫ~ውብ ማለዳ፡
ሰቆቃን ቻይ ፅኑ ግድግዳ፡
ጅማሬ ቃል የእውቀት ጮራ፡
የወንድነት ውብ አሻራ፡
የመጥፎነት ክኒን ጂራፍ፡
የደግነት ትልቅ በራፍ፡
የዕውቀት እና የእውነት ደጃፍ ፡
የሰውነት የእዝነት ጓዳ…!!
ለሁሉ አዛኝ ነጎድጓዳ፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;//;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ሴትነት………
ማንነቱን ለሚጠረጥር፡
የደግነት ትልቅ ሚስጥር፡
ሚስጥረ ቁልፍ~መግቢያ ጀነት
መንፈስ አዳሽ የሀሴት ጅረት፡
አርቆ አሣቢ ለሌሎች ኑረት፡
መጀመሪያ የሰውነት ፍንጭ፡
የደስታ የሣቃችን ምንጭ፡
የደግነት ድርብርብ፡
ማር አምራች ሁሌም ነች ንብ፡
የጥሩነት መስፈሪያ ጥግ~የሰው ልኬት፡
የእዝነት ካብ ተደራራቢ ብሎኬት፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;///;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ሴትነት………
የሰውነት መለኪያ ሴትነት፡
ማንም የሚመሰክረው እውነት፡
ደግነት አብሳሪ የበጎነት ጥምረት
ጀግንነት ሴት መሆን ሴትነት ጀግንነት
የሰውነት ግራም ውበት ለወንድነት፡
የወንዲነታችን ጂማሮ፡
ህጋችን የተፈጥሮ፡
ይህች ነች ማለት ሴትነት፡
የማይካድ ገሀድ እውነት፡
የማትረሣ ለቅፅበት፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;//;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;
ሴትነት!!!
ወንድ ሆይ አድምጠኝ ተከበር አትርከስ፡
ሴት ብለህ አትማ ሴት ብለህ አትውቀስ፡
የአንተ ማንነት ነች እድገትህ ሲታወስ፡
ጠጠር ሆነህ አንተ ተራራን አትክሰስ፡
አንተ ብናኝ ነህ እናት ነች ተራራ፡
እርሷ ነች ሚስጥሯ የሰውነት አውራ፡
ከበሮ ቢመታ ቢጎሰም ዳንኪራ፡
የእምሮ መዝገብ ተገልጦ ቢቀራ፡
ማንም አይቃረብ ከሴትነት ተራ፡
’"""""""""""""""""""""""""""""""""""""""""
ባለንበት ዘመን ቢመሰከር እውነት፡
መግለጫ ቃላቶች ሁሌ እማጠፉለት፡
የረቀቀ ቋንቋ የማይገኝለት፡
የሰውነት ሚስጥር ክብር ነው ሴትነት፡
;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;;///

Join&share
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
Channel name was changed to «NUR»
ምዕራፍ الأنبياء 21:88

فَاسْتَجَبْنَا لَهُ وَنَجَّيْنَاهُ مِنَ الْغَمِّ ۚ وَكَذَٰلِكَ نُنجِي الْمُؤْمِنِينَ

ለርሱም ጥሪውን ተቀበልነው፡፡ ከጭንቅም አዳነው፡፡ እንደዚሁም ምእመናንን እናድናለን፡፡
ሞትን አታስቀርም
✿----------<•••★•••>--------


ለመኖር ብትለፋ ለዱኒያ ብትደክም

ልፋትህ ተሳክቶ ስኬት ቢገጥምህም
🍃
ሀብት ዝና ክብር ስልጣን ቢኖርህም

ሁል ጊዜ በፌሽታ ኑሮን ብታጣጥም
🍃
በዚህ ሁሉ መሐል.......

አንድ እውነት አለ ወደድክም ጠላህም

ቀጠሮህ ይደርሳል መሞትህ አይቀርም

ምንም ያክል ድከም ሞትን አታስቀርም‼️
https://t.me/httpsLatahzen
አሏህ ሱብሐነሁ ወተዓላ ሲናገር ፦

نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ الْقَصَصِ بِمَا أَوْحَيْنَا إِلَيْكَ هَٰذَا الْقُرْآنَ

እኛ ይህንን ቁርኣን ወደ አንተ በማውረዳችን በጣም መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፡፡
【ዩሱፍ ③ 】

እያንዳንዱ ታሪክ አንድ ጊዜ ከሰማኸው እንደገና ለመስማት ይደብርሃል ። ከቁርኣን ታሪኮች በስተቀር !! እርሱ ግን ከአንድ ሺህ አራት መቶ ዓመታት በፊት ጀምሮ እየደመቀ ፤ እየተሻለ ፤ እያማረ እና መማሪያ እየሆነ መጥቷል ።
የወደደ ግድግዳ አፍርሶም ይመጣል።
የጠላህ በር ገንጥሎም ይወጣል።
አላህ የምትወዱና የምትወደዱ ያርጋችሁ።
ሁሉ ነገር አበቃለት ብለን ተስፋ በቆረጥንበት ሰዓት እንደገና እንደአዲስ የሚያስጀምረን አላህ ነው። አላህ ያውቃል እኛ አናውቅም።
አሁንም አላህን ያዙ።
በሰው ላይ አይቼ የጠላሁትን ነዉር በኔ ላይ አታሳየኝ።
ያ ረብ።
👉 የሶለዋት አስፈላጊነት
በነብዩ – ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም – ላይ ሶለዋት ማውረድ ተቆጥረው የማይዘለቁ ቱሩፋቶችና ጥቅሞች አሉት ። በመሆኑም አላህ ለአማኞች በርሳቸው ላይ ሶለዋት እንዲያወርዱ እንዲህ ሲል አዟቸዋል :–
« إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا»
الأحزاب ( 56 )
" አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ" ፡፡
ዐብዱላሂ ኢብኑ ዐምር ኢብኑል ዓስ ባስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል :–
- وعنْ عبداللَّه بن عمرو بن العاص، رضي اللَّه عنْهُمَا أنَّهُ سمِع رسُول اللَّه ﷺ يقُولُ : 
” مَنْ صلَّى عليَّ صلاَةً، صلَّى اللَّه علَيّهِ بِهَا عشْرًا "
 رواهُ مسلم
" በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶለዋት ያወረደ ሰው አላህ በሱ ላይ አስር ጊዜ ያወርድለታል "
– ዐብዱላሂ አብኑ መስዑድ – ረዲየላሁ ዐንሁ – የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል: –
- وعن ابن مسْعُودٍ  أنَّ رسُول اللَّهِ ﷺ قَالَ :
" أَوْلى النَّاسِ بِي يوْمَ الْقِيامةِ أَكْثَرُهُم عَليَّ صَلاَةً "
 رواه الترمذي وقال: حديثٌ حسنٌ.
" የቂያማ ቀን በኔ ላይ በላጭ የሆነ ሰው በኔ ላይ በብዛት ሶለዋት የሚያወርድ ነው "
– አውስ ኢብኑ አውስ – ረዲየላሁ ዐንሁ – የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል ይላል : –
- وعن أوس بن أوسٍ،  قَالَ : قالَ رسولُ اللَّه ﷺ : 
" إنَّ مِن أَفْضلِ أيَّامِكُمْ يَوْمَ الجُمُعةِ، فَأَكْثِرُوا عليَّ مِنَ الصلاةِ فِيهِ، فإنَّ صَلاتَكُمْ معْرُوضَةٌ علَيَّ
 فقالوا : يَا رسول اللَّه، وكَيْفَ تُعرضُ صلاتُنَا عليْكَ وقدْ أرَمْتَ ؟
قال : يقولُ : بَلِيتَ،
قالَ : إنَّ اللَّه حَرم عَلَى الأرْضِ أجْساد الأنْبِياءِ ". رواهُ أَبُو داود بإسنادٍ صحيحِ .
" ከቀኖቻችሁ ሁሉ በላጩ የጁሙዐ ቀን ነው ። በኔ ላይ ሶለዋት አብዙ ( በዚህ ቀን ) የናንተ ሶለዋት ወደኔ ይቀርባልና
የአላህ መልእክተኛ ሆይ ሶለዋታችን እንዴት ወዳንተ ይቀርባል በርግጥ አፈር ሆነህ ሳለህ አሏቸው?
አላህ በአፈር ( በመሬት) ላይ የነብያቶችን ሰውነት እርም አድርጓል " ።
እነዚህና የመሳሰሉ ኑሱሶች በነብዩ ላይ ሶለዋት እንድናወርድ የሚገፋፉን ናቸው ። በመሆኑም የዱንያም የአኼራም ጉዳያችን አላህ እንዲበቃን ሶለዋት በታላቁ ነብይ ላይ እናውርድ እናብዛ
በተለይ የጁሙዓ ለሊትና ቀን በከንቱ ሊያልፈን አይገባም ። አላህ ተጠቃሚ ያድርገን ።
በፍርድ ቤት ክስ ጥፋትን ማመንና መፀፀት ቅጣትን ያቃልላል። አጥፍቻለሁ ብሎ አላህ ፊት መናዘዝ ወንጀልን ያስምራል። አላጎደልኩም ብላችሁ አታስቡ። አጥፍቻለሁ ብላችሁ አምላካችሁ ፊት ቅረቡ።

ሰባሐል ኸይር ወዳጆቼ
ከፊታችን ያለ ሁሉ የኛ ላይሆን ይችላል። ከኋላችን የሚከተለን ያስፈልገን ይሆናል። የሚሸሽን ኮከብ አታባርሩ። የማይፈልጋችሁን አትከተሉ። ግራቀኝ እያያችሁ ተጓዙ። ቆምብላችሁም ጠብቁ። ማንያውቃል ቀጥላ የምትወጣው ጨረቃ ያንተ ልትሆን ትችላለች።
Channel name was changed to «La tehzen»