La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
<ሸኙት በእልቅሻ>
👋👋👋👋👋👋
ሸኙት በእልቅሻ፣
ያን የራህመት ዋሻ፣
የስህተት ማበሻ፣
ከወንጀል መሸሻ፣
🔸🔸🔹🔸🔸
አልፈዋል ሳምንታት፣
እሱ የጀመረበት፣
ቀርቧል ሊሰናበት፣
ቀናት ነው የቀሩት፣
ትውስታ ይሆናል ለተጠቀሙበት፣
በዚያ በአኼራው ቤት፣
🔸🔸🔹🔸🔸
ደግሞ ለፈዘዙት፣
ነው የእግር እሳት፣
ምንስ ሊፈይዳት፣
ቁጭት አይመልሳት፣
🔸🔸🔹🔸🔸
ይህንን ፈዘውት፣
ቀጣይ ለማይደርሱት፣
ነው የእሳትም እሳት፣
ከነሱስ አታድርገን ረሂም ባንተ ራህመት፣
🔸🔸🔸🔹🔸🔸🔸

ያራህማን አድርገን ቀጣይ ከሚደርሱት፣
ምን መድረሱን ብቻ ከሚጠቀሙበት፣
ቀኑን ከመፆም ጋር ሌቱን ከማይተኙት፣
አንተን ለማስደሰት የእውነት ከሚለፋት፣
ተቀብለሀቸው ጀነት ሚመነዱት፣
አድርገን ከነሱ ወዱድ ባንተ እዝነት።
➡️የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ።

🌙ከዚክሮች ሁሉ በላጩ 👉 لا إله إلا الله ነው
🌙ከዱአዎች ሁሉ በላጩ 👉 الحمد لله ነው

📚(ቲርሚዚ ዘግቦታል)
"لا تستوحشوا طريق الحق لقلة سالكيه"

【ትክክለኛን መንገድ ጥቂት ሰዎች ስለሚከተሉት ብለህ አትተወው (ብቸኛ አታድርገው)】
"إذا مدحك الرجل بما ليس فيك، فلا تأمنه أن يذمك بما ليس فيك".

『አንድ ሰው አንተ በሌለህበት ነገር ቢያሞግስህ አንተ በሌለህበት ነገር ላይም ሲወቅስህ አትመነው』
ፆመን ውለን ስናበቃ ያለ አጅር ባዶዋችን እንዳንገባ እንጠንቀቅ!!
———
በዚህን ጊዜ አላህ ያዘነለት ሰው ሲቀር የብዙ ሰዎችን ተግባርና ምላስ ስናይ ፆም ማለት:– በቃ ከምግብና ከሚጠጡ ነገሮች መታቀብ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ከባድ የሆነ አደጋ ነው!። አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:-

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ وَالْجَهْلَ، فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ ".
صحيح البخاري وغيره

“(ፆመኛ ሆኖ) በውሸት መናገርን ያልተወ፣ በውዳቂ ነገር መስራትን ያልተወ ሰው፣ በአላዋቂነትና በሞኛሞኝነት በሰዎችም ሆነ በራሱ ላይ ድንበር ማለፍን (ቂላቂል መሆንን) ካልተወ ምግብና የሚጠጣ ነገር በመተው ለአላህ ግድ የለውም።” [ቡኻሪና ሌሎችም ዘግበውታል።]

ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«ፆመኛ ማለት አካሎቹ ከሀጢአት የጸዱ፤ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤ ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።

ፆመኛ ከተናገረ፣ ፆሙን በማይጎዳ መልኩ ይናገራል፣ ስራ ከሰራ ፆሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል። ፆመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው!!። ከፆመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመት እና በደል ከመሰሉ ነገሮች ሁሉ ሰላም ይሆናል። ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ፆም ማለት። ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ፆም አይባልም።

ፆም ማለት አካላትን ከሀጢአት፣ ሆድን ከምግብና ከሚጠጣ ነገር በመታቀብ መፆም ነው። ምግብና የሚጠጣ ነገር ፆምን እንደሚያበላሽ ሁሉ ሀጢአትም የፆምን ምንዳ ያበላሻል፣ ውጤቱንም ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ፆም እንዳልፆመ ተደርጎ ይታሰባል።» [አልዋቢሉ አስ-ሶይብ 31-32]
La tehzen
#ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ #ክፍል1 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 የሰሙድ ህዝቦች ከሁድ ህዝቦች በኋላ የመጡ ሲሆኑ በጣም ትዕቢተኛ እና ኩራተኛ ናቸው። በሳውዲ ዐረቢያ ምድር በሂጃዝ እና በተቡክ መሀከል የሚገኝውን ግዙፍ ተራራ በመፈልፈል ከዘመኑ ጋር የማይመጣጠን ውብ ውብ... ህንፃዎችን ሰርተው ነበር የሚኖሩት።በጣም ትላልቅ ናቸው አሁን ያለው ትውልድ በጉልበትም ሆነ በግዝፈት…
#የነቢዩሏ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታረክ

#ክፍል2

ይህን ባዩ ግዜ አይኖቻቸው ፈጠጠ፣ አንደበታቸው ደረቀ፣ምላሶቻቸው ተሳሰሩ።ሳሊህም ዐ ሰ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ግመል የአላህ ተዐምር ናት።

ታይዋታላችሁ፤ ትዳስሷታላችሁም እናንተ ዘንድም ትኖራለች።
ባስቀመጣችሁት መስፈርት መሰረት ትልቅ እና እርጉዝ ሴት ግመል እንደመሆኗ መጠን ካሁን በኋላ ውሀችሁንም ለጋራ ነው ምትጠጡት።

አንድ ቀን ግመሊቱ ስትጠጣ ቀጣይ ቀን እናንተ ትጠጣላችሁ። ምክንያቱም መጀመርያ ያስቀመጣችሁት መስፈርት ይህ ነው'ና።

ነገር ግን ይህችን ግመል አንዳችሁ በመጥፎ ከተተናኮላችኋት የአላህ ፈጣኑ ቅጣት ይወርድባችኋል" በማለት አስረዳቸው።

ከዚያም ህዝቡ ለሳሊህ ዐ ሰ ያለው አመለካከት 100% ተቀየረ።ሁሉም ከማንም በላይ ሳሊህን ያከብር ጀመረ።ብዙ ሺህ ሰውም የሳሊህ ተከታይ ሆነ።

ይህ ያሳሰባቸው የከተማይቱ ሹማምንት አንድ ቀን ተሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲወያዩ ውለው በመጨረሻም ግመሊቱን በመግደል ተስማሙ።

ይህ የተወሰነውም በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው ነበር።አጋጣሚ እዛው መጠጥ ቤት ሳሉ የመጠጥ ጥማቸው ሳይቋረጥም ከመጠጡ ቤት ጓዳ "መጠጥ አልቋል" የሚል መርዶ ደረሳቸው።

ሹመንቱም፦"ለምንድነው በርከት አድርጋችሁ ማትሰሩት" ብለው ሲጮሁባቸው
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት፦

"ዛሬ ውሀ የግመሊቱ ተራ ስለሆነ ውሀ የለም'ና ብዙ መስራት አልቻንም" ብላ መለሰችላቸው።

ከመሀከላቸውም አንድ ቀዳር ኢብን ሳሊፍ ኢብን ጁንደዕ የተባለ አመፀኛ ከመሰል ጓደኛው ጋር ተነሳ'ና ግመሏን ሊገድል ጉዞ ጀመረ።

በጉዞ ላይ ሳሉም ሌላ ሰባት ሰዎችን መንገድ ላይ በመቀላቀል ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።

ውሀው ዘንድም ደረሱ'ና በያዙት ሰይፍ ገደሏት።ከአጠገቧ ግልገሏ ነበር'ና ግልገሏንም አሳድደው በትልቅ ተራራ ላይ ይዘውት ገደሉት።ከሙጅሪምነታቸው የተነሳ የግመሊቱን ስጋ ቀኑኑ ተከፋፈሉት።

ሳሊህም ዐ ሰ ይህን በተመለከተ ግዜ፦"አሁን የጌታችሁን ቅጣት ተጠባበቁ።

የጌታችሁ ቅጣት ከመውረዱም በፊት ስጋውን ተሎ ተሎ በልታችሁ ጨርሱ" አላቸው።

ህዝቡም፦"አንተ ምን ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት እያልክ ትዝትብናለህ! እስቲ አምጣ ቅጣት ምትለውን" ሲሉት

ሳሊህም፦"በዚህ 3 ቀን ውስጥ የጌታችሁ ቅጣት እናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።ለዚህም ማረጋገጫ ዛሬ ፊታችሁ ብጫ ይሆናል።

ነገ ደሞ ቀይ ይሆናል።ከነገ ወዲያ ደግሞ ጥቁር ይሆንና ትጠፋላችሁ ይህም ሀሰት የሌለው ዛቻ ነው" አላቸው።

እነዚህ የሀፅያትን ፅዋ ጠጥተው የማይጠግቡ ህዝቦችም ሳሊህን ዐ ሰ ለመግደል ወስነው ዝግጅታቸውን አጠናቀው ሳለ፣

በመጀመርያ ግመሏን በገደሉት ዘጠኙ ሰዎች ላይ እቤት ተደረመሰባቸው፣

አሁን የአመፀኞቹ ህዝቦች ፊታቸው መቀያየር ጀምሯል።ሀሉም የፊቱ ብጫ መሆን አስፈርቶት እርስ በርስ ይተያያል።

ሁለተኛው ቀን ደርሶ በነጋታው ሰዉ ሲነቃ ሁሉም ፊቱ ደም መስሏል።በድንጋጤ የሞቱትም ብዙ ነበሩ።ያን ቀን በትካዜ እና በፍራቻ ካሳለፉ በኋላ የማይደርስ የለም'ና ሶስተኛዋ ቀን መጣች።

ፊቶቻቸውን ጥቁረት ወረረው፣ተስፋም ቆረጡ ሁሉም በመሰባሰብ ከፈናቸውን ለብሰው ሽቶ ተቀብተው ሞታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ።

ልክ ፀሀይ ጀንበሯን ተሻግራ ብቅ ማለት ስትጀመር ከወደ ሰማይ በኩል እንደመብረቅ ያለ፣

ከፍተኛ ድምፅ ያለው ነገር መጣ።ምድርም በሀል መንቀጥቀጥ ጀመረች...ጂብሪልም በከፍተኛ ድምፁ ጮኸባቸው።

ያን ግዜ ልቦቻቸው ከደረታቸው መበጣጠስ ጀመረ።አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ያፈጣሉ...

መቅሰፍቱ ከየት በኩል እንኳን እንደመጣ ማወቅ እየተሳናቸው ነፍሶቻቸው ወደ ሰውነታቸው ዳግም ላትመለስ ተነጠለቻቸው።

የከተማይቱ ህዝብ ሁሉም በያሉበት በድን ሁነው ሲሞቱ አንዲት ሴት ብቻ ቀረች ስሟም ከልባ ቢንት ሰለቅ ይባላል።

ለሳሊህ ዐ ሰ ከፍተኛ ጥላቻ ሲኖታት የክህደትን ዘውድ ከራሷ አኑራለች።

ይህን ስትመለከት እግሬ አውጭኝ ብላ ከሀገሩ ሸሸች። ብዙ ከተጓዘችም በኋላ አንድ የዐረብ ነገድ የሚኖሩበትን መንደር ደረሰችና የሆነውን ሁሉ ነገረቻቸው።

በመጨረሻም ውሀ እንዲያጠጧት ጠይቃ ልክ ውሀውን ስትቀምሰው ነፍሷ የሙታንን መንደር ተቀላቀለች።

ሳሊህ ዐለይሂሰላም ወደ ሌላ ቦታ ተሰደደ ሷሊህ እና ከሱጋ ያመኑት ሰወች ወደ ተከበረቺው ወደ ተባረከቺው ፊለስጢን ሀገር ተሰደደ፡፡

ከዚያንም በረምላ ከተማ መኖር ጀመረ፡፡ ቆይቶም ሷሊህ ዐለይሂሰለም በ58 አመታቸው በዛው በረምላ ከተማ የዚህችን አለም ጣጣ አጠናቅቀው ነፍሳቸውን ለጌታቸው አስረከቡ።


......❀━┅┉┈#ተፈፀመ┈┉┅━❀

በነገራችን ላይ ረሱላችን (ሰዐወ) አንድ ቀን ለተቡክ ዘመቻ ባልደረቦቻቸውን ይዘው በመሄድ ላይ ሳሉ የሳሊህ ህዝቦች የጠፉበትን ከተማ ደረሱ።

ማንም አይኖርበትም..የተወሰኑ ሶሃቦች በሷሊህ ከተማ ውስጥ
ከሚገኙ ምንጮች ውስጥ ሊቀዱ ሄዱ፣ የተወሰኑት፣ ደግሞ መገልገያ እቃወችን አመጡ፥

የአሏህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መገልገያ መሰረያወቹ እንዲሰበሩ እና የተቀዳም ውሃ እንዲደፋ አዘዙ፡፡

ከዚያ ውሃ የተሰረው ምግብ ሁሉ እንድደፋ አዘዙ፦ከዚያም ነቢያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦

"ይህችን ከተማ ስትገቡ እያለቀሳችሁ ፣መልቀስ እንኳዋ ባትችሉ ለማልቀስ የዳዳቹህ ሁናቹህ እንጂ ዝም ብላችሁ እንዳትገቡ።

እኔ በነሱ የወረደው በላእ እናንተን እንዲያገኝብኝ አልፈልግም" አሏቸው።ፊዳከ አቢ ወ ኡም ወነፍሲ ወደሚ ወዒርዲ ያ ረሱሉላህ

በዚያ አከባቢም ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለባልደረቦቻቸው አሳይዋቸው።ግመሏም የወጣችበትን እና የተገደለችበትንም ቦታ ወስደው አሳይዋቸው።

ምንጮቻችን፦
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
صحيح مسلم
صحيح البخاري
-------------------------------
ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። 👇
https://t.me/httpsLatahzen
የአዞ እምባ እንዳይሆን እንጠንቀቅ!!

ረመዷን ተጋመሰ ሊሄድብን ነው አዎ የብዙዎቻችን ጭንቀት ነው ነገር ግን የእያንዳንዳችን ውሎ ሄደብን ሳይሆን በሄደልን ነው የሚመስለው ያ ከሆነ ደግሞ ጩኸታችን ከአንገት በላይ ነው እምባችን የአዞ እምባ ነው ከራሴ ጀምሮ የተግባር ሰዎች እንጂ የማስመሰል ሰዎች አንሁን

አዎ ረመዷን ላይመለስ እያኮበኮበ ነው ነገር ግን አሁንም ከተጠቀምንባቸው በቂ ጊዜያቶች አሉን ከጩኸት በፊት ተግባር ይቀደም ለኔም ለናንተም ከኢኽላስጋ የተቆራኘ ተግባር አሏህ ይወፍቀን።
» እህቴ ሆይ!
።።።ሳትፈልጊና ሳትመርጪው አካልሽ
በከፈን ከመገነዙ በፊት፣
በፍላጎትና ምርጫሽ በጅልባብ በኒቃብ ሸፍኚው።።።
بسم الله الرحمن الحيم

حجابک أيتها المسلمه
#ሙስሊሟ_ሴት_ሆይ_ሂጃብሽን_አደራ!!!

ምስጋና ለአላህ ይገባው ፡፡ በእርሱ እመካለሁ ፣ ወደእርሱ ተጸጽቼ እመለሳለሁ ፡፡
ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑን ፣ ሙሐመድ صلى الله عليه وسلم የአላህ
አገልጋይና መልክተኛ መሆናቸውን ፣ እስከ እለተ ሞታቸው ድረስ ህዝብን በትክክል
የመከሩና የተሰጣቸውን አደራ በአግባቡ የተወጡ መሆናቸውን ፤ መልካም ነገር ኖሮ
የተውት ፣ መጥፎ ነገር ኖሮ ያላስጠነቀቁት አንድም ነገር የለም ብየ በእርግጠኝነት
እመሰክራለሁ፡፡ በእርሳቸው ፣ በቤተሰቦቻቸውና በባልደረቦቻቸው ላይ የአላህ ሶላትና
ሰላምታ ይስፈን፡፡
አላህን በመፍራት ላይ ነፍሴንም እናንተንም አደራ እላለሁ ፤ አላህን የፈራ ሰው
ከክፉ ነገር ይጠበቃል ፤ መልካም ለሆነው ጎዳና አላህ ይመራዋል፡፡
ከዚህ በመቀጠል፡
የተከበርሽ እህቴ ሆይ! ጊዜሽን በኢማን ፣ በዒልም ፣ አላህን በመታዘዝና በበጎ ስራ
እንዲያሳልፍልሽ ፤ አካልሽን በሂጃብ እንዲሸፍንልሽ አላህን እማጸንልሻለሁ፡፡ ይህ
ለአንች በእርሱ ተጠቃሚ እንድትሆኝ ከአላህ ተስፋ በማድረግ የማቀርብልሽ ስጦታ
ነው፡፡ እርሱም በማንኛውም ቦታ የምትከበሪበት ፤ ደረጃሽ ከፍ የሚልበት የሒጃብ ጉዳይ
ነው፡፡ ፡
የተከበርሽው እህቴ ሆይ! አላህ ወደትክክለኛው ጎዳና በምመራት በእኛ ላይ የዋለውን
ታላቅ ጸጋ በቅድሚያ ልትገነዘቢ ይገባል፡፡ ኢስላም ለባሮቹ የወደደው ያለምንም ጉድለት
ያሟላው ከእርሱ ውጭ የማይቀበለው የሆነ ዲን ነው፡፡
አላህ በተከበረው ቁርኣን የሚከተለውን ተናግሯል፡
إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ ۗ
አላህ ዘንድ (የተወደደ) ሃይማኖት ኢስላም ብቻ ነው፡፡” አል ዒምራን/ዓያ ፡1️⃣9️⃣

وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلَامِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِي الْآخِرَةِ مِنَ الْخَاسِرِينَ
``ከኢስላም ሌላ ሃይማኖትን የሚፈልግ ሰው ፈጽሞ ከርሱ ተቀባይ የለውም፡፡
እርሱም በመጨረሻይቱ ዓለም ከከሳሪዎቹ ነው፡፡” አል ዒምራን/ ዓያ 8️⃣5️⃣


ኢንሻ አሏህ





إعداد:
الشيخ عبدالرزاق بن عبدالمحسن البدر
#የኪታቡ_አዘጋጅ_ሸይኽ_ዓብድረዛቅ_ቢን_ዓብድል_ሙሕሲን_አል_በድር ናቸው📝
"مهما تصورت ببالك فالله بخلاف ذلك"

『ምንም በአዕምሮህ ብትስል ብታንሰላስል አንተ የሳልከውና ያሰብከው አሏህን አይመስል』
አንድ ሰው ምቾት በቀነሰ ቁጥር ስሜቱ ይደክማል። ስሜት በደከመ ቁጥር ደሞ ወንጀልን ይቀንሳል።

በተቃራኒው

አንድ ሰው ምቾት ባበዛ ቁጥር ስሜቱ ይጨምራል። ስሜቱ በጨመረ ቁጥር ወንጀልን በቀላሉ ይዳፈራል።
▪️አቡሁረይራ ረደየሏሁ አንሁ እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል:–

➲ፆመኛ ሁለት ደስታዎች አሉት።
➧ሲያፈጥር ይደሰታል
➧ከጌታው ጋር ሲገናኝም በመፆሙ
ደስ ይለዋል።
عبدُ اللهِ بنُ مَسعود رضيَ الله عنه قالَ: "ما كُنتُ أظنُّ أنَّ أحَدًا مِنَّا يُحِبُّ المال حتى أَنزَلَ اللهُ تبَارَكَ وتعالى: ﴿مِنْكُمْ مَنْ يُرِيدُ الدُّنيا﴾


ዓብዱሏህ ብን መስዑድ እንዲህ አሉ፦『ከእኛ መካከል አንድም ቢሆን ገንዘብን የሚወድ አለ ብዪ አላስብም ነበር የአሏህ ይህን ንግግር እስኪያወርድ ድረስ 【ከእናንተ መካከል ዱንያን የሚወድም አለ】

አሏህ አሏህ አሏህ።።።።
(ይህን ወንድ ካገኘሽ ያ ሰላም
… …አንቺ ታውቅያለሽ ምን ማድረግ እንዳለብሽ)😍😍

تزوجي رجلا

إذا حاورته وجدته حكيما
وإذا غضب عنك كان حليما
وإذا ظفر برزق كان كريما
وإذا أصابك شيء ينزعج أكثر مما تنزعج أنت عليك.
وإذا وعدك أوفى
ولو كان الوعد عظيما.

ስታዋይው ጥበበኛ ሆኖ ምታገኚውን
ባንቺ ላይ ሲቆጣብሽ ጥበበኛ የሆነውን
ሲሳይን ሲሰጥ ለጋሽ የሆነውን
የሆነ ነገር ሲገጥምሽ አንቺ ከምትጨነቂው በላይ እርሱ የሚጨነቅ
ቃል ከገባልሽ የሚሞላ የሆነውን
የገባው ቃል ትልቅ ቢሆን እንኳን።
الله غني عن العالمين ، الله لا يحتاج لشيء من خلقه ، الله لا يتشرف بشيء من خلقه ، لا تصح العبادة الا بعد معرفة المعبود.


『አሏህ ከዓለማት የተብቃቃ ነው አሏህ ከአንዱም ፍጡሩ አይፈልግም አሏህ በአንድም ፍጡሩ ልቅናን አያገኝም እርሱ ጅማሬ በሌለው መኖሩ የላቀ ነውና አምልኮ አትበቃም የሚገዙትን ጌታ ካወቁ ቡሀሏ ቢሆን እንጂ』
​​​​
«እህቴ ሆይ!»
እዉቀት ለሠዉ ልጅ ብርሀን ነዉ።
እዉቀት ለመቅሰም ወደ ኃላ ማለት አይገባንም እስልምና እምነታችን በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ዲን (ሀይማኖት ) ነዉ እና
ውሃ ለዓሣ የሚያስፈልገውን ያህል
ለሴት ልጅ ዐይን አፋርነትና እና ቁጥብነት እጅግ ያስፈልጓታል
ለወንድ ልጅ ደግሞ ቆፍጣናነት እና ቆራጥነት እጅጉን ያስፈልገዋል
وَلَقَدْ ذَرَأْنَا لِجَهَنَّمَ كَثِيرًا مِّنَ الْجِنِّ وَالْإِنسِ ۖ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا ۚ أُولَـٰئِكَ كَالْأَنْعَامِ بَلْ هُمْ أَضَلُّ ۚ أُولَـٰئِكَ هُمُ الْغَافِلُونَ

[ ሱረቱ አል-አዕራፍ - 179 ]
ከጋኔንም ከሰዎችም ብዙዎችን ለገሀነም በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ለእነርሱ በርሳቸው የማያውቁባቸው ልቦች አሏቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማያዩባቸው ዓይኖች አሉዋቸው፡፡ ለእነሱም በሳቸው የማይሰሙባቸው ጆሮዎች አሉዋቸው፡፡ እነዚያ እንደ እንስሳዎች ናቸው፡፡ ይልቁንም እነርሱ በጣም የተሳሳቱ ናቸው፡፡ እነዚያ ዘንጊዎቹ እነርሱ ናቸው፤
በበድር ዕለት ያጋጠሙ አንዳንድ ክስተቶች

1-    አል-በራዕ ኢብኑ ዓዚብ (ረ.ዐ) እና ኢብን ዑመር (ረ.ዐ) ወደቤታቸው እንዲመለሱ መደረጋቸው፡-
ሙስሊሞች የአቡ ሱፍያን ቅፍለት ያለበት ቦታ ለመድረስ ከመዲና ወጥተው ‘ቡዩት አስ-ሱቅያ’ የተባለው ሥፍራ ደርሰዋል፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አብረዋቸው የወጡትን ባልደረቦቻቸውን ሁኔታ ሲገመግሙ ሁለት ወጣቶች ዕድሜያቸው ለውጊያ ያልደረሰ ሆኖ በመገኘቱ እንዲመለሱ አዘዟቸው፡፡ እነርሱም አል-በራእ ኢብኑ ዓዚብ (ረ.ዐ) እና ኢብኑ ዑመር (ረ.ዐ) ናቸው፡፡ ሁለቱ ወጣቶች ከሙስሊሞች ጋር በመሆን ለመዋጋት በጥሩ ንያ (እሳቤ) ነበር ከቤታቸው የወጡት፡፡

2-   የአንድ ከሃዲን (አጋሪን) እርዳታ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) አልተቀበሉም፡-
ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ብላለች፡- “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ በድር እያመሩ እያለ ‘ሃራቱል-ወብራህ’ የተባለ ሥፍራ ሲደርሱ አንድ በውጊያ ብቃቱና በጀግንነቱ የታወቀ ሰው አገኛቸው፡፡ ባልደረቦቻቸው ይህን ሰው ሲያዩት በጣም ተደሰቱ፡፡ ሰውየው የአላህን መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “ከእርስዎ ጋር ሆኜ ለመዋጋትና ምርኮ ለማግኘት ነው የመጣሁት” አላቸው፡፡ የአላህ ነቢይ (ሰ.ዐ.ወ) “በአላህና በመልዕክተኛው አምነሃልን?” አሉት፡፡ “አላመንኩም” አለ ሰውዬው፡፡ “እንደዚያ ከሆነ ወደመጣህበት ተመለስ፡፡ እኔ አጋሪ ከሆነ ሰው እርዳታ አልፈልግም” አሉት፡፡ ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጉዟቸውን ቀጥለው ‘አሽ-ሸጀራህ’ የተባለ ሥፍራ ሲደርሱ ያ ሰው ደረሰባቸውና መጀመሪያ የተናገረውን ነገር ደገመላቸው፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) መጀመሪያ የሰጡትን መልስ ደገሙለት፡፡ ሰውዬው ተመለሰ፡፡ ይሁን እንጂ እንደገና ‘አል-በዒዳ’ የተባለ ሥፍራ ሲደርሱ ተከትሏቸው በመምጣት መጀመሪያ ላይ ያቀረበላቸውን ጥያቄ ጠየቃቸው፡፡ ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ) እንደመጀመሪው ሁሉ “በአላህና በመልዕክተኛው አምነሃልን?” አሉት፡፡ ሰውዬው በዚህ ጊዜ “አዎን” አለ፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “እንደዚያ ከሆነ (ከኛ ጋር) ወደፊት ቀጥል” አሉት፡፡

3-  የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የባልደረቦቻቸውን ችግር መካፈላቸው፡-
ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፡- “በበድር ዕለት አንድን ግመል ለሦስት ሆነን ነበር የምንጋልበው፡፡ አቡ ሉባባህ (ረ.ዐ)፣ ዐሊ ኢብን አቡ ጣሊብ (ረ.ዐ) እና የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ግመል በተራ ይጋልቡ ነበር፡፡ ሁለቱ ሰዎች ነቢዩን (ሰ.ዐ.ወ) እኛ በእግራችን እንሄዳለን እርስዎ ይጋልቡ” ሲሏቸው እርሳቸው (ሰ.ዐ.ወ) ግን “እናንተ ከእኔ አትጠነክሩም ምንዳን ከአላህ ለማግኘት ደግሞ ከእናንተ ያነሰ ፍላጎት የለኝም?” ይሏቸው ነበር፡፡”
ዱንያ እና አኺራ

ይህንን ጎዶሎና ሞት የሚከተለውን የዱንያ ህይወት ለመግፋት የሚደከመው ድካም ፣ የሚከፈለው መስዋእትነት የከበደና የበዛ ነው ።
ድካም ፣ በሽታ ፣ እንግልት የሌለበትን ዘላለማዊ ደስታ ያለበትን የጀነት ህይወት ለማግኘት ግን እንቅልፋችን ረዝሟል ፣ ጉልበታችን ዝሏል ።

ጀነት ውስጥ አይን ተመልክቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅና በልቦናችን ውል ብሎ የማያውቅ ፀጋና አስደሳች ነገር አለ ።

ጀነት ውስጥ የማይቋረጥ ፀጋና ደስታ አለ አቃጣይ ሙቀትም ሆነ አንጥቃጭ ብርድ የለም ። የጀነት ሰዎች ጭንቀትም ሆነ ረብሻን አያውቁም ።

ከምንም በላይ ፈጣሪያቸውን አሏህን ያያሉ !!!

መልካም ስራዎችን በመስራትና ሐራም ነገችን በመራቅ ለጀነት እንሽቀዳደም


ወንድሞቼና እህቶቼ ፣

የዱንያ ህይወት የሽንትና የሰገራ ህይወት ነውና አያታለን ። ጠፊ ነውና አይሸንግለን !
የቂያማ ምልክቶች
• ግብረ ሰዶም
• ሰዎች ስለሌሎች አያት ቅድመ አያት ክፋት እና ቂም ማውራት
• ልብሶች አብዛኛውን የሰውነት ክፍል የሚያሳዩ መሆናቸው
• በሰማይ ላይ ብዙም ከዋክብት አይኖሩም
• ትላልቅ ህንፃዎች መብዛት
• የደጃል መምጣት
• የኢማም አህመድ መምጣት
• የኢሳ አለይሂሰላም መውረድ
• የእጁጅ እና መእጁጅ መምጣት
• ፀሀይ በገባች መውጣት( የይቅርታ በር በተዘጋ ጊዜ)
• ከመሬት ውስጥ አንዲት ፍጡር መውጣት እና ትክክለኛ አማኞችላይ ምልክት ማድረጓ
• ለ40 ቀናት ጉም መነሳት እና በዛምክንያትም እውነተኛ አማኞች ምንም እውቀትም ሆነ ስሜት ሳይሰማቸው መሞት
• ከባድ እሳት መነሳት በዛም ብዙ ነገሮች መውደም
• የካአባ መፍረስ
• ቁርአን ከሰውም ልብ ከወረቀትላይ መነሳት
• የጡሩንባ መነፋት በመጀመርያው እንስሳዎች አና ሰዎች መሞት
• በሁለተኛው ሲነፋ የአላህ ፍጥረት በሙሉ እንደገና ይነሳሉ ለፍርድ በአረፈት መሬት ላይ ይሰበሰባሉ
• ፀሀይ ወደ ምድር በጣም ትቀርባለች
• ነብዩ ሙሀመድ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰም እንዳሉት" ይህንን ዜና ለአንድ ሰውያደረሰ ( ያስተላለፈ) በፍረዱ ቀን ጀነት ላይ ቦታ ይዘጋጅለታል
• ይህንን መልእክት በስልካችሁ contact ላይ ላሉ ሙስሊሞች በሙሉ ላኩ ይህን መልእክት ችላ ካልከው(ሽው) የረሱልን ንግግር አስታውስ)ሺ)

"ላኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሀነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነ ዟሊሚን"

አላህ ሁላችንንም ወደሱ ይመልሰን