لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا ۚ لَهَا مَا كَسَبَتْ وَعَلَيْهَا مَا اكْتَسَبَتْ ۗ رَبَّنَا لَا تُؤَاخِذْنَا إِن نَّسِينَا أَوْ أَخْطَأْنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تَحْمِلْ عَلَيْنَا إِصْرًا كَمَا حَمَلْتَهُ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِنَا ۚ رَبَّنَا وَلَا تُحَمِّلْنَا مَا لَا طَاقَةَ لَنَا بِهِ ۖ وَاعْفُ عَنَّا وَاغْفِرْ لَنَا وَارْحَمْنَا ۚ أَنتَ مَوْلَانَا فَانصُرْنَا عَلَى الْقَوْمِ الْكَافِرِينَ
[ አል-በቀራህ - 286 ]
አላህ ነፍስን ከችሎታዋ በላይ አያስገድዳትም፡፡ ለርስዋ የሠራችው አላት፡፡ በርስዋም ላይ ያፈራችው (ኀጢአት) አለባት፡፡ (በሉ)፡- ጌታችን ሆይ! ብንረሳ ወይም ብንስት አትያዘን፤ (አትቅጣን)፡፡ ጌታችን ሆይ! ከባድ ሸክምን ከእኛ በፊት በነበሩት ላይ እንደጫንከው በእኛ ላይ አትጫንብን፡፡ ጌታችን ሆይ! ለኛም በርሱ ችሎታ የሌለንን ነገር አታሸክመን፡፡ ከእኛም ይቅርታ አድርግ ለእኛም ምሕረት አድርግ፡፡ እዘንልንም፤ ዋቢያችን አንተ ነህና፡፡ በከሓዲዎች ሕዝቦች ላይም እርዳን፡፡

➪ኢማሙ አህመድ ተጠየቁ፡
ጥያቄ፦ መልካም ስነምግባር ማለት ምን ማለት ነው ?
መልስ፦ መልካም ስነምግባር ማለት ከሰወች የሚደርስብህን አዛ መቻል ማለት ነው።
☞︎︎︎ ሹዕቡል ኢማን (7726)

☞ከጓደኛ ምርጡ ማነው? ተብለው ሲጠየቁ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ በማለት መለሱ "አላህን እንድትፈራ የሚያስታውስህ መልካም ሲሰራ ስታየው ተግባሩን የምትከተል ለችግርህ
ስትጠራው የሚደርስልህ ነው አሉ
አላህ ጥሩ ጥሩ ጓደኞችን ያብዛልን።
ስትጠራው የሚደርስልህ ነው አሉ
አላህ ጥሩ ጥሩ ጓደኞችን ያብዛልን።
#ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ
#ክፍል1
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
የሰሙድ ህዝቦች ከሁድ ህዝቦች በኋላ የመጡ ሲሆኑ በጣም ትዕቢተኛ እና ኩራተኛ ናቸው።
በሳውዲ ዐረቢያ ምድር በሂጃዝ እና በተቡክ መሀከል የሚገኝውን ግዙፍ ተራራ በመፈልፈል ከዘመኑ ጋር የማይመጣጠን ውብ ውብ... ህንፃዎችን ሰርተው ነበር የሚኖሩት።በጣም ትላልቅ ናቸው አሁን ያለው ትውልድ በጉልበትም ሆነ በግዝፈት ከነሱ አይስተካከልም።
ምንም እንኳን ድንጋያማ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ቢሆኑም አላህ ምድራቸውን ለቡቃያ ምቹ አድርጓት የምንጮቹንም ብዛት ለጉድ አድርጎታል።
ግዜው ከአባቶቻቸው የወረሱርትን የጣኦት አምልኮ አጧጡፈው የያዙበት ዘመን ነበር።
በዱንያ ሰክረው...አላህን ረስተው...በወንጀል ተጨማልቀው ሳለ አላሁ ሱብሀነሁ ወተዓላ ሳሊህ ኢብን ዑበይድ ኢብን ሂሻም ኢብን.....ዓድ ኢብን ኣርም ኢብን ሳም ኢብን ኑህ (ዐ ሰ) የተባለን መልካም ነቢይ ከመሀከላቸው ላከላቸው።
ሳሊህ ዐ ሰ በነቢይነት ከመመረጣቸው በፊት ህዝቡ ዘንድ በምልካም ስነ ምግባራቸው የሚታወቁ፣ከከበርቴ ቤተሰብ የተወለዱ፣ከዚያም አልፎ ሰዎች ለፍርድ ሚያስቸግር ክርክር ሲገጥማቸው እሳቸው ጋር የሚሄዱ ምርጥ የአላህ ባርያ ናቸው።
ወደፊት ሀገሪቷን በንግስና ያስተዳድሯታል ተብሎም ይገመት ነበር።
በንዲህ አይነት ሁኔታ ላይ ሳለ ሳሊህ ዐ ሰ የጌታቸውን ተልዕኮ እንደተቀበሉ በትኩስነቱ፦" ወገኖቼ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ ከእርሱ ሌላ ለእናንተ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ ከዓድም በኋላ ምትኮች ባደረጋችሁና በምድሪቱም ላይ ባስቀመጣችሁ ጊዜ አስታውሱ፡፡ ከሜዳዎቿ (ሸክላ) ሕንጻዎችን ትገነባላችሁ፡፡ ከተራራዎችም ቤቶችን ትጠርባላችሁ፡፡ ስለዚህ የአላህን ጸጋዎች አስታውሱ፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ኾናችሁ አታበላሹ" በማለት ጥሪውን አስተጋባ።
ይህን በሰሙ ግዜ ትዕቢታቸው አናታቸው ላይ ወጣ...ኩራታቸው ገነፈለ...የከተማይቱ መሳፍንትም፦"አንተ ሳሊህ! ቆይ አንተ ከኛ በምን ተሽለህ ነው አላህ መልዕክተኛ አድርጎ ሊመርጥህ የቻለው? ይልቁኑ አማልክቶቻችን በመጥፎ አይን ሳያዩህ አልቀሩም'ና አብደሀል" አሉት።
ከዚያም እንደተለመደው ሳሊህ(ዐ ሰ) የድሆች እና ምስኪኖች ተከታይ ይበራከቱለት ጀመር።ይሁን እንጂ በለፀጋዎች እና ጉልበተኞቹ ዝም ማለትን አልመረጡም'ና ምእመናኑ ዘንድ በመሄድ፦"እናንተ ባመናችሁት ነገር እኛ ክደናል" በማለት ይሳለቁባቸው ነበር።
ከዛላችሁ እነዚህ አመፀኛ ህዝቦች አንደ ቀን የሳሊህን ዐ ሰ ጥሪ ለማስቆም እና ተከታዮቹን ከሱ ለማራቅ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሊመካከሩ አንድ ቦታ ተሰበሰቡ።
ብዙ ከመከሩ በኋላ በመጨረሻም ሳሊህን (ዐ ሰ) ያለ ተከታይ ብቻውን ለማስቀረት አንድ መፍትሄ አገኙ።
እሱም፦"ሳሊህን የሚከተል ከአማልክቱ በኩል የማይድንን በሽታ ይይዘዋል።ከሳሊህም የሚርቅ ከነዚህ ነገሮች የተጠበቀ ይሆናል" በማለት ከተማይቷን ቀወጧት።
ነገር ግን ትክክለኛይቱ የዳዕዋ ጥሪ መንገዷን ይዛ ቀጥላለች።በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ አንድ ቀን ሳሊህ ዐ ሰ ጥሪያቸውን በህዝብ ፊት ሲያደርሱ ህዝቡም፦"አንተ ሳሊህ እውን አንተ ነቢይ ከሆንክ ማረጋገጫ ይሆነን ዘንድ እስቲ ተዐምር አምጣልን" አሉት።
የከተማይቱ ሹማምንት እና የተከበሩ ሰዎች በቦታው ነበሩ።የማይችለውን ነገር በመጠየቅ እንዳደናገሩት በማሰብ የማላገጥን ሳቅ ይስቁበትም ጀመር።(ወላሂ ነቢያቶች አላህ ምንዳቸውን ከፍ ያድርግላቸው።በገዛ ሀገራቸው ይሳቀቃሉ)
ከመሳፍንቱ መሀክል አንዱ ቆመ'ና፦"አንተ ሳሊህ ተዐምር ማሳየት እችላለሁ የምትል ከሆነ የተዐምሩን አይነት እኛ ነን ምንመርጠው ያንተ ስራ እኛ የመረጥነውን ተዐምር መተግበር ብቻ ነው" አሉት
እኛ እያየን ከዚህ ተራራ ውስጥ በግዝፈቷ አቻ የሌላት የአስር ወር እርጉዝ የሆነች፣መልኳም ቀይ የሆነ፣ከግዝፈቷ የተነሳ የከተማይቱ ይዝብ እና እንስሳት የሚጠጡትን ውሀ በአንዴው መጠጣት የምትችል ትልቅ ግመል አውጣልን"አሉት።
ነቢዩላህ ሳሊህም (ዐ ሰ) ህዝቡ ሁሉ ተዐምሩን አይተው በማመን ከጀሀነም ይድኑ ዘንድ የከተማይቱ ሰው ሁሉ እንዲሰበሰብ አዘዙ'ና ሁሉም ተሰበሰቡ።
ከዚያም ሳሊህ (ዐ ሰ) ለጌታቸው ሱጁድ በመውረድ ጌታቸውን ይማፀኑ ጀመር።አላህም የሱን መልዕክተኞች በህዝባቸው ፊት አያሳፍራቸውም'ና ተራራው በጣም መንቀጥቀጥ ጀመረ።
ህዝቡ ሁሉ አይኑን ተራራው ላይ ተክሏል።ካሁን አሁን ምን ሊከሰት ነው በማለት እርስ በርስ ይተያያሉ።
በዚህ ሁኔታ ላይ ሳሉ ተራራው ከፍተኛ ጩኸት ካስተጋባ በኋላ በጣም በመሰንጠቅ ከመሀከሉ ህዝቡ በጠየቀው መልኩ ትልቅ እና እርጉዝ ቀይ ግመል ወጣች።
በአላህ ፍቃድ ክፍል ሁለት ነገ
ይ
ቀ
ጥ
ላ
ል...........
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ምንጮቻችን፦
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
صحيح مسلم
صحيح البخاري
---------------------------------
ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ቻናሉን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ።

#لا_اله_إلا_الله
ኢማም ኢብኑ ሀጀር አላህ ይዘንላቸው
ዛሬ በተውሂዳችሁ ላይ ታገሉ
ነገሩኮ ከአላህ ቅጣት እሱ እንጂ ምንም አያድንም
አንድም ተናጋሪ ያማረ ንግግር አልተናገረም ከላኢላሀ ኢለላህ የበለጠ 🌺
📔كلمة_الإخلاص ١٧١/١👉ምንጭ

«ولاَتَـــقْـــــرَبُـــــواالــزِنــــــىا»
«ዝሙትን እንዳትቀርቡት»
ሙሉውን አንብቡት አስተማሪ ታሪክ ነው
ጌታችን አላህ ሱብሀነሁ ወተአላ በተከበረው ቃሉ "ولاتقربواالزنى"
ዝሙትን እንዳትቀርቡት ይላል።"ኢስራእ 32" ልብ በሉ እንዳትሰሩት ሳይሆን እንዳትቀርቡት ነው ያለው አላህ እኛ ለራሳችን ከምናውቀው በላይ እሱ ለኛ ያውቅልናል። የሰው ልጅ ማንም ይሁን ማን ፊትናን በራሱ ላይ መተማመን አይችልም ለዚህ ነው ጌታችን አላህ ዝሙትን ከሩቁ የከለከለን። የቀደምቶቻችንን አንድ ድንቅ ታሪክ ላጫውታችሁ።
በመካ ከተማ የምትኖር አንዲት እጅግ መልከመልካም የሆነች ሴት ነበረች ባልም አላት።ከእለታት አንድ ቀን ራሷን በመስታወት ታይና በመልኳ በጣም ተደነቀች ለባሏም አንድ ጥያቄን ጠየቀችው ይህን የመሰለ የሚያምር ፊት አይቶ የማይፈተን ወንድ ያለ ይመስልሀል አለችው ባሏም እጅግ ሞኛ ሞኝ ነበርና አው ያንቺን መልክ አይቶ የማይፈተን አንድ ሰው አውቃለሁ ስሙም ኡበይድ ኢብኑ ኡመይር የሚባል አላህን ፈሪና አሊም የሆነ ሰው ነው በማለት ነገራት እሷም ፍቀድልኝ እና ይህን ሰውዬ ልፈትነው ብላ ለባሏ ጥያቄ አቀረበች ባሏም እንደነገርኳቹ በሚስቱ ቅናት የማይሰማው(ደዩስ) ነበርና ፈቀደላት እሷም ወደተባለው ሸይኽ ሄደች ከዚያም ልክ ፈትዋ እንደሚጠይቅ ሰው ሁና ቀረበች ሸይኹም ፈቀደላት እሷ ግን ሰው ባለበት የሚጠየቅ ጥያቄ አደለም ለብቻህ ላናግርህ አለችው ሸይኹም ተቀብለው ከመስጊዱ ወደ አንዱ ጥግ በመውሰድ ጥያቄሽ ምንድን ነው አሏት እሷም መሽኮርመሙን እና ለማማለል መሞከሩን ተያያዘችው እሱም አልበቃ ብሏት ኒቃቧን ከፍታ ፊቷን ለማሳየትና እሱን ለመፈተን ሞከረች ከዛም አልፋ እኔ በአንተ ተፈትኛለሁ ወድጀሀለው እና መላ በለኝ አለችው እሱ ግን አላህን ፈሪ ነበርና መጥፎ ነገር ከማሰብ ይልቅ አንድ ነገር ተናገራት
አንቺ የአላህ ባሪያ ሆይ አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ በአላህ ይሁንብሽ እውነቱን ትነግሪኛለሽ አላት እሷም በሀሳቡ ተስማማች ከዚያም የሚከተሉትን ጥያዎች ይጠይቃት ጀመር
– በዚህ ሰአት መለከል መውት ነፍስሽን ሊወስድ መጥቶ ቢሆንና ይህን ነገር በሀራም ፈፅመሽ መሞትን ትመርጪ ነበር አላት እሷም በፍፁም ብላ መለሰች
–በዚህ ሰአት ቀብር ውስጥ ሰዎች አየከተቱሽ ቢሆን እና ከዛ በፊት ይህን ነገር ፈፅመሽ ቢሆን ትመርጪ ነበር ሲላት እሷም በጭራሽ አለች
–አሁንም አስከትሎ በዚህ ሰአት ሰዎች አላህ ፊት ቆመው ኪታባቸውን እየተሰጡ ቢሆን እና የአንቺ ኪታብ በቀኝ ይሁን በግራ የሚሰጥሽ በማታውቂበት ሰአት ይህን ነገር ፈፅመሽ ኪታብሽ ላይ እንዲመዘገብ ትመርጪ ነበር ሲላት የሷም መልስ በፍፁም ነበር
አስከትሎም የተለያዩ ገሳጭ የሆኑ ጥያቄዎችን ጠየቃት ከዚያም እጅግ በጣም ደንግጣ ወደ ቤቷ ተመለሰች።
ያሞኙ ባሏም እንዴት ነው ተሳካልሽ ብሎ ጠየቃት እሷም እኔም አንተም የማንረባ ሰዎች ነን የሚል መልስ ሰጠችው።
ከዚያን ቀን በሗላ ይቺ ሴት አላህን በማምለክ ላይ በጣም መጠመድ ጀመረች።
ባሏም ከሰዎች ጋር ሲያወራ ያ ኡበይድ ኢብኑ ኡመይር ሚስቴን አበላሸብኝ ሌላ ጊዜ ወደ አልጋ ሰትመጣ በጣም ተውባና አጊጣ ትመጣ ነበር ከዛ በሗላ ግን በሰላትና በፆም ተጠምዳለች ይል ነበር።
📚ኢማሙል ጀውዚ
ዘሚል ሀዋ በሚለው ኪታባቸው ላይ አስፍረውታል።
ስለዚ ወንድሞች እና እህቶች ወደ ዚና ከሚወስዱ ነገሮች ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል አላህ ራቁ ብሎናል እና ከሩቁ ልንሸሸው ይገባል አጅነቢን አትኩሮ ከመመልከት ጀምሮ ራሳችንን ልንጠብቅ ይገባል አላህ ከሀራም በሙሉ ተጠብቀው ወደ ሀላሉ ትዳር የሚገቡ ያድርገን የገቡትንም ያፅናልን።

ለይለተልቀድር ለሴቶች‼️
==============
✍ለይለተል ቀድር ለሰጋጆች ብቻ አይደለችም የወር አበባ ደም ላይ፣ የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶችም፣ የዚች ለሊት ትሩፋት አያልፋቸውም፡፡
||
✔️ባይሆን እህተቶችየ በዚክርና መሰል ዒባዳዎች ልትበራቱ ይገባል፣ ይህን የሚጠቁም ሀሳብም ከመልካም ሰለፎቻችን ተገኝቷል፣ በዚያች ለሊት ዱዓእ ማብዛት ጥሩ ነው፡፡
እንዳውም ሱፍያኑ ሠውሪ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-
«በለሊቷ ከሶላት ይልቅ ዱዓእ እኔ ዘንድ የተወደደ ነው» ይላሉ፡፡

ሞልታ የነበረችው ጨረቃ እየጎደለች ሄዳ ከጨረቃዋ ማለቅ ጋር ረመዷንም ያልቃል። ደጋጎቹ የረመዷን ቀናት በጎደሉ ቁጥር በዒባዳ ብርታታቸው ያይል ነበር።
ረመዷን ዉድድር ነው። እኛ ደግሞ ለዉድድር የተለቀቅን ባሮቹ ነን። ትንፋሽ ሰብስቦ ፍፃሜን ለማሳመር መታገል አሁን ነው ወዳጄ።
ረመዷን 17
ይህ ቀን ታላቁን የበድር ጦርነት ያስታዉሰናል።
# እንደ በድር ድል ይሳካላችሁ።

ከሸይኹ'ል አልባኒ ረሒመሁሏህ ገጠመኞች መካከል…
⇛ከዕለታት አንድ ቀን ሸይኹል አልባኒ በታመሙበት ግዜ አንድ ሐኪም ሊያክማቸው ወደ እርሳቸው ሔደ…ሐኪሙ ደሞ ፂም አልነበረውም። ለ ሸይኹ ህክምና ከጨረሳ ብኃላ ሊወጣ ሲል«ያ ሸይኽ ዱዓ አድርጉልኝ» አላቸው…።
⇛ሸይኹል አልባኒም አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉት፦"
"جمَّلك الله بما جمَّل به الرجال"
"አሏህ ወንዶችን ባስዋበበት(ፂም) ያስውብህ" ብለው መለሱለት።
📚 انظر [ دروس ومواقف وعبر 96 ]
(ፂም ለሌለው ወንድ ከዚህ በላይ ምን ትልቅ ዱዓ አለ!?)

⇛ታላቁ ሸኽ ሷሊህ አል_ፈውዛን እንድህ ይላሉ፦
📌የሰለፎችን አካሄድ ከሚፃረሩ አካላት ማስጠንቀቅ የሙስሊሞችን አንድነት ከመጠበቅ እንጂ አንድነትን ከመከፋፈል አይቆጠርም።
📚አል_አጅዊበቱል ሙፊዳ 157
[الأجوبة المفيدة (١٥٧)]

⇛ከረመዳን አንፃር ቁርኣንን እያዩ መቅራቱ(ነዞር) ወይንስ እየሐፈዙ መቅራቱ የቱ ነው የተሻለው?
•=================•
ﺍﻷﻭﻟﻰ ﺃﻥ ﻳﻘﺮﺃ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ ﻛﻠﻪ ﻧﻈﺮﺍً، ﻭﺃﻥ ﻳﺤﺎﻓﻆ ﻋﻠﻰ ﻣﺎ ﺣﻔﻈﻪ ﻋﻦ ﻇﻬﺮ ﻗﻠﺐ ﻟﺌﻼ ﻳﻨﺴﺎﻩ…
⇛በላጩ ቁርኣንን በሙሉ እያየ መቅራቱ ነው።የ ሐፈዘውን ደሞ እንዳይረሳ ሊከታተልም ይገባል።
📚ﺍﻟﺸﻴﺦ ﺍﺑﻦ ﻋﺜﻴﻤﻴﻦ ﻣﻦ ﻓﺘﺎﻭﻯ ﻧﻮﺭ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﺪﺭ

<ሸኙት በእልቅሻ>
👋👋👋👋👋👋
ሸኙት በእልቅሻ፣
ያን የራህመት ዋሻ፣
የስህተት ማበሻ፣
ከወንጀል መሸሻ፣
🔸🔸🔹🔸🔸
አልፈዋል ሳምንታት፣
እሱ የጀመረበት፣
ቀርቧል ሊሰናበት፣
ቀናት ነው የቀሩት፣
ትውስታ ይሆናል ለተጠቀሙበት፣
በዚያ በአኼራው ቤት፣
🔸🔸🔹🔸🔸
ደግሞ ለፈዘዙት፣
ነው የእግር እሳት፣
ምንስ ሊፈይዳት፣
ቁጭት አይመልሳት፣
🔸🔸🔹🔸🔸
ይህንን ፈዘውት፣
ቀጣይ ለማይደርሱት፣
ነው የእሳትም እሳት፣
ከነሱስ አታድርገን ረሂም ባንተ ራህመት፣
🔸🔸🔸🔹🔸🔸🔸
ያራህማን አድርገን ቀጣይ ከሚደርሱት፣
ምን መድረሱን ብቻ ከሚጠቀሙበት፣
ቀኑን ከመፆም ጋር ሌቱን ከማይተኙት፣
አንተን ለማስደሰት የእውነት ከሚለፋት፣
ተቀብለሀቸው ጀነት ሚመነዱት፣
አድርገን ከነሱ ወዱድ ባንተ እዝነት።
👋👋👋👋👋👋
ሸኙት በእልቅሻ፣
ያን የራህመት ዋሻ፣
የስህተት ማበሻ፣
ከወንጀል መሸሻ፣
🔸🔸🔹🔸🔸
አልፈዋል ሳምንታት፣
እሱ የጀመረበት፣
ቀርቧል ሊሰናበት፣
ቀናት ነው የቀሩት፣
ትውስታ ይሆናል ለተጠቀሙበት፣
በዚያ በአኼራው ቤት፣
🔸🔸🔹🔸🔸
ደግሞ ለፈዘዙት፣
ነው የእግር እሳት፣
ምንስ ሊፈይዳት፣
ቁጭት አይመልሳት፣
🔸🔸🔹🔸🔸
ይህንን ፈዘውት፣
ቀጣይ ለማይደርሱት፣
ነው የእሳትም እሳት፣
ከነሱስ አታድርገን ረሂም ባንተ ራህመት፣
🔸🔸🔸🔹🔸🔸🔸
ያራህማን አድርገን ቀጣይ ከሚደርሱት፣
ምን መድረሱን ብቻ ከሚጠቀሙበት፣
ቀኑን ከመፆም ጋር ሌቱን ከማይተኙት፣
አንተን ለማስደሰት የእውነት ከሚለፋት፣
ተቀብለሀቸው ጀነት ሚመነዱት፣
አድርገን ከነሱ ወዱድ ባንተ እዝነት።
➡️የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ።
🌙ከዚክሮች ሁሉ በላጩ 👉 لا إله إلا الله ነው
🌙ከዱአዎች ሁሉ በላጩ 👉 الحمد لله ነው
📚(ቲርሚዚ ዘግቦታል)
🌙ከዚክሮች ሁሉ በላጩ 👉 لا إله إلا الله ነው
🌙ከዱአዎች ሁሉ በላጩ 👉 الحمد لله ነው
📚(ቲርሚዚ ዘግቦታል)
"لا تستوحشوا طريق الحق لقلة سالكيه"
【ትክክለኛን መንገድ ጥቂት ሰዎች ስለሚከተሉት ብለህ አትተወው (ብቸኛ አታድርገው)】

"إذا مدحك الرجل بما ليس فيك، فلا تأمنه أن يذمك بما ليس فيك".
『አንድ ሰው አንተ በሌለህበት ነገር ቢያሞግስህ አንተ በሌለህበት ነገር ላይም ሲወቅስህ አትመነው』

ፆመን ውለን ስናበቃ ያለ አጅር ባዶዋችን እንዳንገባ እንጠንቀቅ!!
———
በዚህን ጊዜ አላህ ያዘነለት ሰው ሲቀር የብዙ ሰዎችን ተግባርና ምላስ ስናይ ፆም ማለት:– በቃ ከምግብና ከሚጠጡ ነገሮች መታቀብ ብቻ ይመስላቸዋል። ይህ ከባድ የሆነ አደጋ ነው!። አቢ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል አለ:-
عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : " مَنْ لَمْ يَدَعْ قَوْلَ الزُّورِ وَالْعَمَلَ بِهِ وَالْجَهْلَ، فَلَيْسَ لِلَّهِ حَاجَةٌ أَنْ يَدَعَ طَعَامَهُ وَشَرَابَهُ ".
صحيح البخاري وغيره
“(ፆመኛ ሆኖ) በውሸት መናገርን ያልተወ፣ በውዳቂ ነገር መስራትን ያልተወ ሰው፣ በአላዋቂነትና በሞኛሞኝነት በሰዎችም ሆነ በራሱ ላይ ድንበር ማለፍን (ቂላቂል መሆንን) ካልተወ ምግብና የሚጠጣ ነገር በመተው ለአላህ ግድ የለውም።” [ቡኻሪና ሌሎችም ዘግበውታል።]
ኢብኑ'ል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ አሉ:-
«ፆመኛ ማለት አካሎቹ ከሀጢአት የጸዱ፤ ምላሱን ከአሉባልታ፣ ከውሸት እና ከአጸያፊ ንግግር የጠበቀ፤ ሆዱን ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ብልቱን (በቀን ክፍለ ጊዜ) ከግብረ ስጋ ግንኙነት የጠበቀ ነው።
ፆመኛ ከተናገረ፣ ፆሙን በማይጎዳ መልኩ ይናገራል፣ ስራ ከሰራ ፆሙን በማያበላሽበት መልኩ ይሰራል። ፆመኛ ጠቃሚና ቁምነገር ያለው ንግግር እና ስራ ሲሰራ ምሳሌው ልክ ከሽቶ ተሸካሚ ሰው ጋር ተቀምጦ መልካም ሽታ እንደሚያገኝ ሰው ነው!!። ከፆመኛ ጋር የተቀመጠም ሰው መልካም ነገርን እንጂ ሌላ አያገኝም። ከተለያዩ መጥፎ ነገሮች እንደ ቅጥፈት፣ ውሸት፣ ጥመት እና በደል ከመሰሉ ነገሮች ሁሉ ሰላም ይሆናል። ይህ ነው ትክክለኛና ህጋዊ ፆም ማለት። ከምግብና መጠጥ ብቻ መታቀብ ፆም አይባልም።
ፆም ማለት አካላትን ከሀጢአት፣ ሆድን ከምግብና ከሚጠጣ ነገር በመታቀብ መፆም ነው። ምግብና የሚጠጣ ነገር ፆምን እንደሚያበላሽ ሁሉ ሀጢአትም የፆምን ምንዳ ያበላሻል፣ ውጤቱንም ያበላሻል። በዚህም ምክንያት ልክ ፆም እንዳልፆመ ተደርጎ ይታሰባል።» [አልዋቢሉ አስ-ሶይብ 31-32]

La tehzen
#ነብዩሏህ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታሪክ #ክፍል1 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 የሰሙድ ህዝቦች ከሁድ ህዝቦች በኋላ የመጡ ሲሆኑ በጣም ትዕቢተኛ እና ኩራተኛ ናቸው። በሳውዲ ዐረቢያ ምድር በሂጃዝ እና በተቡክ መሀከል የሚገኝውን ግዙፍ ተራራ በመፈልፈል ከዘመኑ ጋር የማይመጣጠን ውብ ውብ... ህንፃዎችን ሰርተው ነበር የሚኖሩት።በጣም ትላልቅ ናቸው አሁን ያለው ትውልድ በጉልበትም ሆነ በግዝፈት…
#የነቢዩሏ_ሷሊህ_ዐለይሂ_ሰላም_ታረክ
#ክፍል2
ይህን ባዩ ግዜ አይኖቻቸው ፈጠጠ፣ አንደበታቸው ደረቀ፣ምላሶቻቸው ተሳሰሩ።ሳሊህም ዐ ሰ፦"ህዝቦቼ ሆይ! ይህች ግመል የአላህ ተዐምር ናት።
ታይዋታላችሁ፤ ትዳስሷታላችሁም እናንተ ዘንድም ትኖራለች።
ባስቀመጣችሁት መስፈርት መሰረት ትልቅ እና እርጉዝ ሴት ግመል እንደመሆኗ መጠን ካሁን በኋላ ውሀችሁንም ለጋራ ነው ምትጠጡት።
አንድ ቀን ግመሊቱ ስትጠጣ ቀጣይ ቀን እናንተ ትጠጣላችሁ። ምክንያቱም መጀመርያ ያስቀመጣችሁት መስፈርት ይህ ነው'ና።
ነገር ግን ይህችን ግመል አንዳችሁ በመጥፎ ከተተናኮላችኋት የአላህ ፈጣኑ ቅጣት ይወርድባችኋል" በማለት አስረዳቸው።
ከዚያም ህዝቡ ለሳሊህ ዐ ሰ ያለው አመለካከት 100% ተቀየረ።ሁሉም ከማንም በላይ ሳሊህን ያከብር ጀመረ።ብዙ ሺህ ሰውም የሳሊህ ተከታይ ሆነ።
ይህ ያሳሰባቸው የከተማይቱ ሹማምንት አንድ ቀን ተሰብስበው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሲወያዩ ውለው በመጨረሻም ግመሊቱን በመግደል ተስማሙ።
ይህ የተወሰነውም በአንድ መጠጥ ቤት ውስጥ ሆነው ነበር።አጋጣሚ እዛው መጠጥ ቤት ሳሉ የመጠጥ ጥማቸው ሳይቋረጥም ከመጠጡ ቤት ጓዳ "መጠጥ አልቋል" የሚል መርዶ ደረሳቸው።
ሹመንቱም፦"ለምንድነው በርከት አድርጋችሁ ማትሰሩት" ብለው ሲጮሁባቸው
የመጠጥ ቤቱ ባለቤት፦
"ዛሬ ውሀ የግመሊቱ ተራ ስለሆነ ውሀ የለም'ና ብዙ መስራት አልቻንም" ብላ መለሰችላቸው።
ከመሀከላቸውም አንድ ቀዳር ኢብን ሳሊፍ ኢብን ጁንደዕ የተባለ አመፀኛ ከመሰል ጓደኛው ጋር ተነሳ'ና ግመሏን ሊገድል ጉዞ ጀመረ።
በጉዞ ላይ ሳሉም ሌላ ሰባት ሰዎችን መንገድ ላይ በመቀላቀል ዘጠኝ ሁነው ግመሏ ውሀ የምትጠጣበት ስፍራ ደረሱ።
ውሀው ዘንድም ደረሱ'ና በያዙት ሰይፍ ገደሏት።ከአጠገቧ ግልገሏ ነበር'ና ግልገሏንም አሳድደው በትልቅ ተራራ ላይ ይዘውት ገደሉት።ከሙጅሪምነታቸው የተነሳ የግመሊቱን ስጋ ቀኑኑ ተከፋፈሉት።
ሳሊህም ዐ ሰ ይህን በተመለከተ ግዜ፦"አሁን የጌታችሁን ቅጣት ተጠባበቁ።
የጌታችሁ ቅጣት ከመውረዱም በፊት ስጋውን ተሎ ተሎ በልታችሁ ጨርሱ" አላቸው።
ህዝቡም፦"አንተ ምን ዝም ብለህ ቅጣት ቅጣት እያልክ ትዝትብናለህ! እስቲ አምጣ ቅጣት ምትለውን" ሲሉት
ሳሊህም፦"በዚህ 3 ቀን ውስጥ የጌታችሁ ቅጣት እናንተ ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።ለዚህም ማረጋገጫ ዛሬ ፊታችሁ ብጫ ይሆናል።
ነገ ደሞ ቀይ ይሆናል።ከነገ ወዲያ ደግሞ ጥቁር ይሆንና ትጠፋላችሁ ይህም ሀሰት የሌለው ዛቻ ነው" አላቸው።
እነዚህ የሀፅያትን ፅዋ ጠጥተው የማይጠግቡ ህዝቦችም ሳሊህን ዐ ሰ ለመግደል ወስነው ዝግጅታቸውን አጠናቀው ሳለ፣
በመጀመርያ ግመሏን በገደሉት ዘጠኙ ሰዎች ላይ እቤት ተደረመሰባቸው፣
አሁን የአመፀኞቹ ህዝቦች ፊታቸው መቀያየር ጀምሯል።ሀሉም የፊቱ ብጫ መሆን አስፈርቶት እርስ በርስ ይተያያል።
ሁለተኛው ቀን ደርሶ በነጋታው ሰዉ ሲነቃ ሁሉም ፊቱ ደም መስሏል።በድንጋጤ የሞቱትም ብዙ ነበሩ።ያን ቀን በትካዜ እና በፍራቻ ካሳለፉ በኋላ የማይደርስ የለም'ና ሶስተኛዋ ቀን መጣች።
ፊቶቻቸውን ጥቁረት ወረረው፣ተስፋም ቆረጡ ሁሉም በመሰባሰብ ከፈናቸውን ለብሰው ሽቶ ተቀብተው ሞታቸውን መጠባበቅ ጀመሩ።
ልክ ፀሀይ ጀንበሯን ተሻግራ ብቅ ማለት ስትጀመር ከወደ ሰማይ በኩል እንደመብረቅ ያለ፣
ከፍተኛ ድምፅ ያለው ነገር መጣ።ምድርም በሀል መንቀጥቀጥ ጀመረች...ጂብሪልም በከፍተኛ ድምፁ ጮኸባቸው።
ያን ግዜ ልቦቻቸው ከደረታቸው መበጣጠስ ጀመረ።አይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ያፈጣሉ...
መቅሰፍቱ ከየት በኩል እንኳን እንደመጣ ማወቅ እየተሳናቸው ነፍሶቻቸው ወደ ሰውነታቸው ዳግም ላትመለስ ተነጠለቻቸው።
የከተማይቱ ህዝብ ሁሉም በያሉበት በድን ሁነው ሲሞቱ አንዲት ሴት ብቻ ቀረች ስሟም ከልባ ቢንት ሰለቅ ይባላል።
ለሳሊህ ዐ ሰ ከፍተኛ ጥላቻ ሲኖታት የክህደትን ዘውድ ከራሷ አኑራለች።
ይህን ስትመለከት እግሬ አውጭኝ ብላ ከሀገሩ ሸሸች። ብዙ ከተጓዘችም በኋላ አንድ የዐረብ ነገድ የሚኖሩበትን መንደር ደረሰችና የሆነውን ሁሉ ነገረቻቸው።
በመጨረሻም ውሀ እንዲያጠጧት ጠይቃ ልክ ውሀውን ስትቀምሰው ነፍሷ የሙታንን መንደር ተቀላቀለች።
ሳሊህ ዐለይሂሰላም ወደ ሌላ ቦታ ተሰደደ ሷሊህ እና ከሱጋ ያመኑት ሰወች ወደ ተከበረቺው ወደ ተባረከቺው ፊለስጢን ሀገር ተሰደደ፡፡
ከዚያንም በረምላ ከተማ መኖር ጀመረ፡፡ ቆይቶም ሷሊህ ዐለይሂሰለም በ58 አመታቸው በዛው በረምላ ከተማ የዚህችን አለም ጣጣ አጠናቅቀው ነፍሳቸውን ለጌታቸው አስረከቡ።
......❀━┅┉┈#ተፈፀመ┈┉┅━❀
በነገራችን ላይ ረሱላችን (ሰዐወ) አንድ ቀን ለተቡክ ዘመቻ ባልደረቦቻቸውን ይዘው በመሄድ ላይ ሳሉ የሳሊህ ህዝቦች የጠፉበትን ከተማ ደረሱ።
ማንም አይኖርበትም..የተወሰኑ ሶሃቦች በሷሊህ ከተማ ውስጥ
ከሚገኙ ምንጮች ውስጥ ሊቀዱ ሄዱ፣ የተወሰኑት፣ ደግሞ መገልገያ እቃወችን አመጡ፥
የአሏህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መገልገያ መሰረያወቹ እንዲሰበሩ እና የተቀዳም ውሃ እንዲደፋ አዘዙ፡፡
ከዚያ ውሃ የተሰረው ምግብ ሁሉ እንድደፋ አዘዙ፦ከዚያም ነቢያችን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ፦
"ይህችን ከተማ ስትገቡ እያለቀሳችሁ ፣መልቀስ እንኳዋ ባትችሉ ለማልቀስ የዳዳቹህ ሁናቹህ እንጂ ዝም ብላችሁ እንዳትገቡ።
እኔ በነሱ የወረደው በላእ እናንተን እንዲያገኝብኝ አልፈልግም" አሏቸው።ፊዳከ አቢ ወ ኡም ወነፍሲ ወደሚ ወዒርዲ ያ ረሱሉላህ
በዚያ አከባቢም ያሉ ነገሮችን ሁሉ ለባልደረቦቻቸው አሳይዋቸው።ግመሏም የወጣችበትን እና የተገደለችበትንም ቦታ ወስደው አሳይዋቸው።
〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
ምንጮቻችን፦
القرءان الكريم
ﺍﻟﺒﺪﺍﻳﺔ ﻭﺍﻟﻨﻬﺎﻳﺔ /ﺍﻟﺠﺰﺀ ﺍﻷﻭﻝ /
صحيح مسلم
صحيح البخاري
-------------------------------
ሌሎች የነብያት፣ የሰሃቦች ታሪክ ና የተለያዪ ትምህርታዊ ፅሁፉች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶ ከስር ሊንኩን በመክፈት ግሩፑን ይቀላቀሉ እርሶ ጋር እንዲቀመጥ አይፍቀዱ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ። 👇
https://t.me/httpsLatahzen

Telegram
La tehzen
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
ቁርዓን96:1
"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret