La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Canadian Prime Minister Justin Trudeau


የእስልምናን ፍኖት እጋርዳለሁ ብለህ ከመጋጋጥ ይልቅ አምነህ ተቀብለህ ተገቢውን ድጋፍ ብታደርግ ነው የሚያዋጣው። ላይሳካልህ ነገር የምታተርፈው ነገር ሙስሊሞችን ማጠናከርና ራስህን ማስገመት ብቻ ነው። እስልምናን ለማስቆም መሞከር የጸሐይን ብርሃን በመዳፍህ ሸፍነህ ምድርን ጨለማ ለማድረግ እንደመሞከር ነው። አይደለም መዳፍህን ሙሉ ሰውነትህን ዘርግተህ ብትዘረር የጸሐይን ጮራ መሸፈን እንደማትችለው ሁሉ፤ ሶላትን አይደለም ት/ቤት ውስጥ መኖሪያ ቤታችሁ ውስጥም አትሰግዱም ብለህ ብታዝ ሙስሊሞችን ይባስ ታጠናክራቸዋለህ እንጂ ቅዠትህ ዕውን አይሆንም።


እንኳን አንተ ከአንተ በላይ ሴኪዩላር ነን ብለው ቃሉን ራሱ ያስተማሩህ ሃገራት መሪዎች እንዲህ እጅ ሰጥተው በሰላም ሙስሊሙ ጋር እየኖሩ ነው። የአንተ ግን የመሃይምነት ጥግ በሃገሪቱ ከግማሽ በላይ ከሆነ ህዝብ ጋር በህልውናው መጥተህ ቀይ መስመር ታልፋለህ። ተመከር ወዳጄ የማትጨርሰውን ጉዞ አትጀምር፤ ወደ ኋላም መመለስ፣ ወደፊትም መገስገስ በማትችልበት ወጥመድ ገብተህ መካከል ላይ ሰምጠህ ትቀራለህ።
||
አንድ ሰው ጭንቀትና ትካዜ አጋጥሞት ይህንን ዱዓእ ካደረገ አላህ ያስወግድለታል ብለዋል ነቢያችን ﷺ። እናም ሐፍዙት።


«اللهم إني عبدك، ابن عبدك، ابن أمتك، ناصيتي بيدك، ماضٍ فيَّ حكمك، عدلٌ فيَّ قضاؤك، أسألك بكل اسمٍ هو لك، سميتَ به نفسَك، أو علَّمتَه أحدًا من خلقك، أو أنزلتَه في كتابك، أو استأثرتَ به في علم الغيب عندك؛ أن تجعل القرآنَ ربيع قلبي، ونور صدري، وجلاء حزني، وذهاب همِّي»
«ቀጣዩን ትውልድ ልክ እንደኛ "ታገሱ! አርፈህ ትምህርትህን ተማር!" ምናምን እያልን የምናሳድግ መስሏችሁ ከሆነ ተሳስታችኋል። ልጆቻችንን "በዲንህ ጉዳይ ለመሞት ዝግጁ ሁን፤ ቤት ተመልሰህ እንዳትመጣ!" እያልን ነው የምንመክራቸው። መብታችንን ከማክበር ውጭ ምንም ምርጫ የላችሁም። ትንታግ የሆነ ትውልድ እየመጣ ነው። ሁለተኛ ዜግነት ደህና ሰንብት።»

© ዶ/ር ቃልኪዳን ሐሰን (Kh Abate) ከጂማ ዩኒቨርስቲ
ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ
# አልሀምዱ ሊላህ
# Alhamdu lilahe
ለሀይማኖታዊ መብቱ ሚታገልለት ህዝባዊ መጅሊስ የተነፈገው ትውልድ
በሰላማዊ መንገድ አንድነቱን ጠብቆ የሀይማኖቴን መብት መብቴን አትንኩብኝ
ብሎ የሚጠይቅ ታዳጊ ትውልድ ማየት በጣም ደስ ይላል አልሀምዱ ሊላህ
በ1990ዎቹ የአዲስ አበባ
ትምህርት ቤቶች የሰላት
ችግር ስለነበር የመጅሊሱ መሪ
ችግሩን ሊፈቱ ሄደው
«የመጣችሁት ለትምህርት
ነው፤ ሰላታችሁን ቤታችሁ
ሰብስባችሁ ስገዱ» የሚል
ፈተዋ ሰጥተው ነበር።
ዘንድሮስ?
ይህ ትውልድ ፍም እሳት ነው
በነካቹን ቁጥር እንጠነክራለን
🔹ሰላትን አደራ!🔹


ወደ አላህ መሸሻ:
አጅር ያለው ጉርሻ:
የሩህ መናፈሻ:
የመንፈስ ማደሻ:
ጎዶሎን መካሻ:
ወደ አላህ ማልቀሻ:
ለሌላ ዒባዳ ቀልብን ማነሳሻ:
🍀@Nur4843🍀
ቀልብህ እንዲራራ:
እንዳይሆን መራራ:
በሀራም በረራ:
ከፉጃሮች ተራ:
እኔም በዚው ላብቃ ብዙ ሳላወራ:
ወንድሜ ልምከርህ ሰላትን አደራ!!
ምን ቢበዛብህም የችግር መከራ:
ባንተ ላይ ቢዘንብም ባንተም ቢያባራ:
በትግስት ጠብቅ የፀሀዩዋን ጮራ:
ምንም ብትዘገይ አትቀር ተቀርቅራ።


ኢንሻአላህ
«አላህን ከሚያስረሳ ሀብት ጀነትን ሚያስናፍቅ ድህነት ይሻላል።»
ሙእሚን በዱንያ ለነገ አያውቅም:
ሀሳቡ ሌላ ነው በርካሽ አይወድቅም:

«––––––––––––––»

ዛሬ ላይ የሰጠው ነገ የትስ ሄዶ:
ቃሉን አያፈርስም ፅፉል ያኔ ማዶ:

«––––––––––––––––»

ሊስትሮም ወዛደር ቢበላም ነግዶ
ሁሌም አመስጋኝ ነው ለፈጣሪው ሰግዶ።
"ትልቁ ፈተና
ተሸራተህ
በሀቅ ላይ ያለህ ሲመስልህ ነው"
ሁሌም ታገስ፣በርታ፣ፅና

🌿የፀና ሰው ቀና🌿
🌿የበረታ ረታ🌿
🌿የዘራም አፈራ🌿
🌿የታገሰ ነገሰ🌿
🌿የጠነከረ ከበረ🌿
ዝቅ ስትል ከፍ የሚያደርገው ጌታ ይመስገን፤ አልሀምዱሊሏህ

#የፈጅርንሶላት በመስጂድ
ሃገር ውስጥ ያለነውን ሰላት አትስገዱ ብሎ ከልክሎ ሲ ያበቃ ባህር ማዶ ያሉትን ኑና ስገዱ ማለት እንዴት ነው ነገሩ⁉️
"የኢኽላስ ኢባዳ"

ስራን ለአላህ ማጥራት፣
ከልብ የእውነት፣
ሪያእ የሌለባት፣
ሱምዓም የማይቀርባት፣
ኡጅብም የማይደፍራት፣
ዱንያ ማታታልላት፣
ለአላህ ያለች ፅድት፣
ሽርክ ሆነ ቢድዓ ከቶ የማይቀርባት፣
ምታስገባ ጀነት የምታርቅ ከእሳት፣
የኢኽላስ ኢባዳ የዝች አይነቷ ናት፣
ደግሞ ትንሽ ላውጋ የኢኽላስ ባልተቤት፣
እሱ ባልተቤት ነው የውዲቷ ጀነት፣
ስራውን ደባቂ አላህን አዋቂ፣
እጅግ ተጠንቃቂ፣
ልቡም የሚጠላ መሆንን ታዋቂ፣
በኢባዳ ላይም ዘውታሪ ዘላቂ፣
ነው እኮ አልቃሻ፣
ወርዶ ከትከሻ፣
አብዝቶ ሚኮንን መባልን በሻሻ፣
ነው የኢማን ዋሻ የተቅዋ መንገሻ፣
ቀን በፆም ይውላል፣
ሌሊቱን ይቆማል፣
ጌታውን አብዝቶ ከልቡ ይፈራል፣
ጀነትን ከጅሏል ፣
እሳትንም ፈርቷል፣
በእሳት ፍራቻም ሌት ቀኑን ያለቅሳል፣
በስራው ማይኮራ፣
አልፎ እንደው ሚፈራ፣
አሳነስኩኝ ብሎ ከሚገባው ስፍራ፣
ደስታው የቀነሰ ሀዘኑም ከራራ፣
ሳቅን ማያበዛ ያልሆነ ሞዛዛ፣
ሁሌም የሚለምን የጌታውን ጀዛ፣
ዱንያንም የናቀ ተቅዋው የረቀቀ፣
ከሸህዋ የራቀ ጀነት የናፈቀ፣
ወንድሙን መካሪ፣
ባለ ውድ ባህሪ፣
ስለርሱ ባወጋ ደርሼ አልጨርሰው፣
በአጭሩ ይህ ነው የዛ ውድ ባህሪው፣
አላህ ውለታውን አብዝቶ የሰጠው፣
ያራህማን አድርገን የሱ አይነት አምሳያው።
ምን ጊዜም ኢስላም በሌለበት ስልጣኔ ማለት ያለ ሩህ ህይወት እንደማለት ነው። ተመልከት ዛሬ ላይ በጣም ሰልጥነዋል እየሰለጠንን ነው የሚባሉ ሀገራት በዘረኝነት እየተፋጩ ስታይ ወላሂ ከምንም በላይ ጌታህን አመስግን ምክንያቱም ኢስላም ለሁሉም ልኩን የሰጠ፣ ጥመብን ከንፁ የለየ፣ የሚጠቅምን ሁሉ የፈቀደ፣የሚጎዳ የተባለን በሙሉ የከለከለ ምርጥ እምነት ነው። አሁንም አመስግን የዚ እምነት ተከታይ ላደረገህ ጌታ።

الحمد لله
በተናደድህ ሰዓት የምትናገረው እወቅ
ንዴቱ ሲለቅህ የተናገርከው ስትጠየቅ
ወላሂ እንዲ አላልኩም ነበር ብለህ ከምትዘባርቅ
መጀመሪያ ራስህን አስጠንቅቅ
"አንድ አንድ ወንጀሎች ህግ የማይዳኛቸው አሉ ነገር ግን ጊዜ በራሱ ፍርድ ይሰጣል።"