La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ኤፕሪል ዘፉል
Sadat
April 1 የውሸታሞች ቀን

"በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁሏህ"
ፈገግ የሚያሰኘኝ ሐዲሥ‼️
====================
✍️ የሐዲሡ አስተላላፊ ግንባር ቀደም የሐዲሥ ዘጋቢ የሆነው የነቢያችን ﷺ ባልደረባ አቡ ሁረይራህ ነው። አላህ ሥራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦
" بيْنَما نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ النبيِّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ، إذْ جَاءَهُ رَجُلٌ فَقَالَ: يا رَسولَ اللَّهِ هَلَكْتُ."
«ነቢያችን ﷺ ዘንድ ተቀምጠን ሳለን ድንገት አንድ ሰው መጣና "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጠፋሁ! (የሚያጠፋ ወንጀል ላይ ወደቅኩ!)" አላቸው።»
እርሳቸውም፦
قَالَ: ما لَكَ؟
«ምን ሆንክ? (ምን አገኘህ?)» አሉት።

እርሱም፦
قَالَ: وقَعْتُ علَى امْرَأَتي وأَنَا صَائِمٌ،
«ጾመኛ ሆኘ ሳለሁ ባለቤቴ ላይ ወደቅኩ! (ባለቤቴ ጋር ግንኙነት አደረግን!)» አላቸው።

እርሳቸውም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ፦

فَقَالَ رَسولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ: هلْ تَجِدُ رَقَبَةً تُعْتِقُهَا؟
«ነጻ የምታወጣው ባሪያ ታገኛለህን?» አሉት።

እርሱም፦
قَالَ: لَا،
"ኧረ! በጭራሽ! (አላገኝም!)" አለ።

እርሳቸውም፦
قَالَ: فَهلْ تَسْتَطِيعُ أنْ تَصُومَ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ،
«ሁለት ወራትን በተከታታይ መጾም ትችላለህን?»አሉት።
(አንድ ወር አላስችለው ብሎ ጭራሽ ሁለት ወርi)

እርሱም፦
قَالَ: لَا،
"ኧረ! በጭራሽ! (አልችልም!)" አለ።

እርሳቸውም፦
فَقَالَ: فَهلْ تَجِدُ إطْعَامَ سِتِّينَ مِسْكِينًا.

«ስድሳ (60) ሚስኪኖችን የምትመግበው ታገኛለህን?» አሉት።

እርሱም፦
قَالَ: لَا،
"ኧረ! በጭራሽ! (አላገኝም!)" አለ።

فَمَكَثَ النبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ، فَبيْنَا نَحْنُ علَى ذلكَ أُتِيَ النبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ بعَرَقٍ فِيهَا تَمْرٌ
ነቢዩ ﷺ በዚህ ሁኔታ ላይ ትንሽ እንደቆዩ ተምር ያለበት ዘንቢል ይዞላቸው ተመጣ።

እንዲህ አሉ፦

قَالَ: أيْنَ السَّائِلُ؟
«(የቅድሙ) ጠያቂ የት አለ?» አሉ።

እርሱም፦
فَقَالَ: أنَا،
"እኔ ነኝ!" አለ።

እርሳቸውም፦

قَالَ: خُذْهَا، فَتَصَدَّقْ به!
ያንን የተመጣላቸውን በተምር የተሞላ ዘንቢል "(እንካ!) ይህቺን ያዝና ሶደቃ ስጥ!" አሉት።

(ፈገግ የሚያሰኘኝ ነገር እዚህ ጋር ነው።)
እርሱም፦

فَقَالَ الرَّجُلُ: أعَلَى أفْقَرَ مِنِّي يا رَسولَ اللَّهِ؟ فَوَاللَّهِ ما بيْنَ لَابَتَيْهَا - يُرِيدُ الحَرَّتَيْنِ - أهْلُ بَيْتٍ أفْقَرُ مِن أهْلِ بَيْتِي،
«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ከኔ የበለጠ እጅግ በጣም ድሃ ማን አለና ነው (ለሌላ የምሰድቀው)? በአላህ ይሁንብኝ! (በመዲና) ተራሮች መካከል ከኔ የበለጠ እጅግ በጣም ድሃ የለም!» አላቸው።

فَضَحِكَ النبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ حتَّى بَدَتْ أنْيَابُهُ، ثُمَّ قَالَ: أطْعِمْهُ أهْلَكَ.
ውዱና አዛኙ ነቢይም ረሱሉ-ል-ሁዳ ቀንጣጤዎቻቸው እስኪታዩ ድረስ ሳቁና "እሺ! ቤተሰብህን መግበው!" አሉት።

ተመልከቱ እስኪ አቦ እኚህን የእዝነት ነብይ‼️
ይህን የእዝነትና ልስላሴ እምነት‼️
ወንጀል ሠርቶ ተጨናንቆ ቢሄድ ጭራሽ እንደ መልካም ሠሪ ስጦታ ተሰጥቶት ተመለሰ።
አጂብ'ኮ ነው ዲናችን! ምንኛ ያማረ አዛኝ የሆነ አምላክ ባሮች ነን! ምንኛ የእዝነትና ርኅራሄ እምነት ተከታዮች ነን! ለአማኞች ርኅሩኅ የሆነ ነቢይ ተከታዮች ነን!

ከዚህ ሐዲሥ ከምንማራቸው ቁም ነገሮች፦
1) በረመዿን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ይህ አይነት ወንጀል ላይ የወደቀ ሰው፤
ከላይ ሐዲሡ ላይ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሠረት፤ መጀመሪያ ነጻ የሚያወጣው ባሪያ ካለ ያወጣል፣ ያንን ካላገኘ ሁለት ወራትን በተከታታይ ይጾማል፣ ይህን ካልቻለ ስድሳ ሚስኪኖችን እስኪጠግቡ ይመግባል።
.
2) ከፋራ ለማውጣት የተቸገረን ሰው መርዳት እንደሚገባ፣
.
3) በመገረም ወቅት በዚህ ልክ መሳቅ እንደሚቻል፣
.
4) የወዱ ነቢይ ﷺ የማስተማር ጥበብ፣ እዝነትና ርኅራሄ፣
.
5) የሚማረውም ግለሰብ አደብና የዲናችን ገርነት፣
.
6) በወንጀል መጸጸትና እንዲህ አይነት ማካካሻ የሚያስፈልገውን ወንጀል ከመደበቅ ይልቅ መፍትሄውን አዋቂዎችን መጠየቅ እንደሚገባ እንማራለን።

ወንጀል ሠርተህ ውስጥህን ከከፋህና ደስተኛ ካልሆንክ፣ ይህ የኢማን መኖርህ ምልክት ነው።
You know the guilt after committing a sin?
Don't ever lose that, its a sign of Imaan. ባይሆን ቶሎ ወደ ጌታህ ተመለስ። ሸይጧን አላህ አይምርህም እያለ ተስፋ አስቆርጦ እስከ መጨረሻው አላማውን እንዳይፈጽምብህ ተጠንቀቅ።

አላህ ረመዿን በሰላም ደርሰው ከሚጠቀሙበት ባሮቹ ያድርገን።
||
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
======
ዕለተ ጁሙዓህ ሸዕባን 29, 1443 H.C
April 01, 2022 G.C
||
t.me/MuradTadesse
ከአርሹ በላይ የሚለው መፅሃፍ የመጀመሪያው ዙር መጥቷል እጄ ገብቷል

ማገኘት የምትችሉት
ቦታ ደሴ አራዳ ሰላም ህንፃ ግራውንድ 33 ቁጥር መምጣት ትችላላችሁ!
0933519871
0921119899
ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ
@JemalEndro
ከጁመዓ በሇላ ነው እጄ የገባው ያዘገየሁባችሁ አፍወን
0933519871

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/11426
አንዲት እናት ወደ አንድ ሸይኽ ፈትዋ ለመጠየቅ ትመጣና ለሸይኹ
" ሸይኽ ሆይ የልጆቼ እንቅልፍ በጣም ከባድ ነው ፣ ለፈጅር ሰላት እነሱን መቀስቀስ ደከመኝና ምንድነው መፍትሄው? " በማለት ጠየቀች ።
๏ ሸይኹም " ሙቀት መቆጣጠሪያው ተቃጥሎ እሳት ቢተፋ ኖሮ ምን ታደርጊ ነበር? " አላት
๏ እናት " እቀሰቅሳቹኋለሁ " አለች
๏ ሸይኹ " ግንኮ እንቅልፋቸው ከባድ ነው " አላት
๏ እናት " በአላህ ይሁንብኝ አንገታቸውን እየጎተትኩ ቢሆንም እቀሰቅሳቸዋለሁ " አለች
๏ ሸይኹ " ይህን የምታደርጊው ከዱንያ እሳት ልታድኚያቸው ነው ፣ ልክ እንደዛውም ከአኺራ እሳት ለማዳን ቀስቅሺያቸው " አላት ።

(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ)
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ጠብቁ ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች ፣ ኀይለኞች የሆኑ መላእክት አልሉ ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም ፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ ፡፡" [ተህሪም 6]

------------------
═ •⊰✿ (🌺) ✿⊱• ══
⇓ ⇓ ⇓

⇩ አላህ ሆይ ሀያሉ 👏

አደገኛ ማእበል መጥቶ ፥
ባህሩ ሲናወጥ በርትቶ ፥
በመርከቧ ዉስጥ ያሉ ፥
ተሳፋሪዎች በሙሉ ፥
እባክህ አዉጣን ይላሉ ፥
አላህዬ ሆይ ሀያሉ ።
ግመል ነጅዉ ከነ እቃዉ ፥
ጭልጥ ባለዉ በበርሃዉ ፥
ጥፍት ሲልበት ደብዛዉ ፥
ባለበት ሆኖ ይጣራል ፥
አላህ ሆይ!አላህ ሆይ! ይላል ፥
አደጋዉ ደርሶ በድንገት ፥
ተጠቂዉ ሲርድ በፍርሃት ፥
ይላል አላህ ሆይ አድነኝ ፥
ከቶ ያላንተ ማን አለኝ? ፥
ሲዘጋባቸዉ መግቢያዉ በር ፥
ሲርቅ የሚሹት ነገር ፥
ሰዎች አምርረዉ ይጮሀሉ ፥
አላህ ሆይ ድረስ እያሉ ፥
ተስፋ ህልማቸዉ ሲሟጠጥ ፥
እቅድ ትልማቸዉ ሲቀልጥ ፥
አላህ ሆይ እያሉ ፥
የሱን እርዳታ ይሻሉ ፥
ሰፌዋ ምድር ጠባብህ ፥
ጭንቅ ስትል ነፍስህ ፥
በሙሉ ልብህ ጥራዉ ፥
አላህ ሆይ ድረስልኝ በለዉ ፥
እርዳታዉ እጅግ ፈጣን ነዉ ።

══ •⊰✿ (🌼) ✿⊱• ══
قصتان في مراعاة مشاعر الزوجات
فضيلة الشيخ الداعية / وهبان بن مرشد المودعي حفظه الله تعالى
#ወድጀሀለሁና_አግባኝ__!!

በ አላህ ስም እጠይቀሃለው ወድጄኃለው እና አግባኝ" ብላ ጠየቀችው እሱም አገባት… !!

ግን ከተዋደዱ ነው

ከማይወዱት ጋር ኑሮ አባጨጓሬ ነው


ከማይወዱት ጋር አይደለም ትዳር አዳርም ይሰለቻል።

#ለዚህም_ነዉ___!!

ፍቅር የሌለው ትዳር አሰልች የሁለት ሰወች ስብሰባ ነው የምልህ.............


በጥቅሉ በደንብ አድምጡት እያፈገገ ሰርፆ የሚገባ የታላቅ አሊም ምክር ነው።

በሸይኽ ወህባን ኢብኑ ሙርሽድ አል-መውደዒ (ሀፊዞሁሏህ)

--------------------
https://t.me/httpsLatahzen
◼️ስሑር መብላት ያለው ጥቅም


💦የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

ስሁር መብላት በረካ አለውና እንዳትተውት። አንድ ጉንጭ ውሃም ቢሆን (ሌላ ባየገኝ እንኳ) አትተውት። አላህና መላኢካዎች ስሁር በሚመገቡ ሰዎች ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ።
📚أخرجه أحمد وابن أبي شيبة

የአላህ መልእክተኛ በሌላ ሀዲስ፦ (ስሁር ብሉ። ስሁር መብላት በረካ አለውና) ብለዋል።
📚البخاري (1923)، ومسلم (1095).

♦️ በየቀኑ ስሁር (ሌሊት ተነስተን) በመብላት የመልእክተኛውን ሱና ህያው በማድረግ ትልቅ ምንዳና አጅር ማግኘትን እንዳንዘነጋ።
بسْـــــــــــــــــــمِ اللّهِ الرَّحْمَنِ الرَّحِيْم​
قال النبي صلى الله عليه وسلم:
تسحروا فإن في السحور بركة .
البخاري ١٩٢٣ ومسلم ١٠٩٥

#የአሏህ_መልእክተኛ_አሉ
💡
#እሰሩ_ማሰር_ትልቅ_በረካ_አለው
#ቡኻሪ_እና_ሙስሊም
💡💡💡💡
#የረመዷን ፆም ኒያ ምን ይሆን ?

نَوَيْتُ صَوْمَ غَدٍ عَنْ أَدَا ءِ فَرْضِ رَمَضَانَ هَذِهِ السَّنَةِ إِيْمَانًا وَاحْتِسَابًا لِلَّهِ تَعَالَى

#አማረኛውን_
#ግዴታ_የሆነብኝን_የረመዷንን
#የዚህን_አመት_ነገን_ፆመኛ_ነኝ
🔉 ረመዳንና ተቅዋ
➬➬➬➬➬➬➬➧

ረመዳን የምህረት፣ የእዝነት፣ የቁርኣን፣ የሶላት የሰደቃ፣ የዚያራ፣ የዚክርና ባጠቃላይ የመልካም ስራ ወር ሲሆን ይህን ሁሉ አጠቃሎ የሚዘው ተቅዋ ነው። ለዚህ ነው ረመዳንን አላህ የደነገገው ለተቅዋ ( አላህን ለመፍራት) መሆኑን በተከበረው ቃሉ እንዲህ ብሎ የነገረን፦
"يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُتِبَ عَلَيْكُمُ الصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ"
(البقرة 183)
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ ጾም በነዚያ ከናንተ በፊት በነበሩት (ሕዝቦች) ላይ እንደ ተጻፈ በናንተም ላይ ተጻፈ (ተደነገገ) ልትጠነቀቁ ይከጀላልና"

➩ ተቅዋን ዓልይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ – ረዲየላሁ ዐንሁ –እንዲህ ብለው ገልፀውታል:–
التقوى هو "العمل بالتنزيل والقناعة بالقليل والإستعداد ليوم الرحيل" أو كما قال
ተቅዋ ማለት:–
"አላህ ባወረደው መስራት, በጥቂቱ መብቃቃት, ለመጨረሻው ቀን መሰናዳት"
➲ እነዚህ ጥቂት ቃላቶች የያዙት እምቅ መልእክት የዚህ ወር መደንገግ ሚስጢር ናቸው።

↪️ በንግግራችንም፣ በስራችንም በማንኛውም ሁኔታችን አላህን መፍራት እንዳለብን ይጠቁማል። ይህ ወር አላህን የምንፈራበት እንጂ የምናምፅበት መሆን የለበትም። ከፆማችን የሚፈለገው ተቅዋ ነው። ይህ ከሌለ ፆማች የጥያቄ ምልክት ውስጥ ነው የሚሆነው። በተለይ ወጣቶች አላህን ልንፈራ ይገባል። ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የረመዳንን ወር የአመፅ ወር ያደርጉትል። በተራዊሕ ስም ከቤት ወጥተው አላህን ወደ ማመፅ ይሄዳሉ። ይህ ትልቅ ኪሳራ ነው ልንጠነቀቅ ይገባል።
አላህ ረመዳንን አግኝቶ ወንጀሉ ከሚማርለት ባሪያው ያድርገን
#ረመዳን_1 🌙

إِنَّا أَنزَلْنَاهُ فِي لَيْلَةِ الْقَدْرِ
እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ ሌሊት አወረድነው፡፡

(ሱረቱል ቀድር 97:1)
ከሁለት ቀናት በፊት በአውቶቢስ ተራ ሳልፍ ስልኬ ላይ ያስቀረሁት ፎቶ!


ረመዿን → የቁርኣን ወር

اللهم اجعل القران العظيم ربيع قلوبنا ونور صدورنا وجلاء أحزاننا وهمومنا ومغفره لذنوبنا اللهم أمين!🤲🤲🤲
በረመዳን ውስጥ በሳምንት ቁርኣንን ለማኽተም 🌹
✔️ፈጅር ላይ 20 ገፅ
✔️ዙህር 15 ገፅ
✔️ዐስር ላይ 12 ገፅ
✔️መግሪብ ላይ 13 ገፅ
✔️ዒሻእ ላይ 14 ገፅ
✔️ስሑር ላይ 12 ገፅ


«وفقنا الله وإياكم لما يحب ويرضى ..»🍃🌷
ተራዊሕ - 1

ወሩ የሑፋዞች ነው። የአላህን ቃል በማንበብ ወሩን ሙሉ በረመዷን ምሽቶች ላይ ይነግሳሉ። ሰማይ ምድሩን በማራኪ ድምፆቻቸው ያዉዳሉ። ሰዎች የአላህን ቃል ይወዱ ዘንድ ሰበብ ይሆናሉ። ምንኛ ታደሉ በረቢ።

ሑፋዞች ልዩ የአላህ ሰዎች ናቸው። አላህ ከሰዎች አስበልጦ ሰዎች ፊት አቆማቸው። የሚሕራብ ንጉሶች አደረጋቸው። ይህም በርግጥ የአላህ ችሮታ ነው። እሱም ችሮታዉን ለሻው ሰው ይሠጣል። "የኽተሱ ቢረህመቲሂ መን የሻኡ።"
ልጅህን ቁርአን ስታስተምረው ፣ በተራው ቁርኣን ደግሞ ልጅህን ያስተምርልሃል።

#የቁርኣን ወር


https://t.me/httpsLatahzen
ረመዷን -1
ሱሑር -1

አላህ ሐያታችንን አርዝሞ በርሱ ፍቃድ ተመልሰናል። ያለ ሰው ሲገናኝ የሞተ ግን በቃው። በዲን ላይ ቆይቶ ዳግም መገናኘት ትልቅ መታደል ነው።
አላህ ሆይ አምና ከኛ ጋር ለፆሙት ዘንድሮ ግን ለሌሉ ወንድም እህቶች ሁሉ ምህረትህን ለግስ።

https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from La tehzen
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ
...

ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ላተህዘኖች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም #ላተህዘኖች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ የተወሰኑ ቤቶች ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ ፓኬጅ #1000 ብር
ግማሽ ፓኬጅ #500 ብር
ሩብ ፓኬጅ #250 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
🔺ዱቄት 🔺ሩዝ
🔺የሾርባ እህል 🔺ቴምር እና ዘይት


አድራሻ ካራቆሬ
ስልክ ቁጥር
📞 0938619117 ይደውሉልን
📞 0937442278
ወይም👇👇
''
@mamepro or @Oufeyret


Join us 👇👇👇
https://t.me/resulinn

https://t.me/resulinn

የየቲሞችን እንባ ተባብረን እናብስላቸው
እንታደጋቸው


ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
➡️በምናፈጥር ጊዜ የሚባል ዱአ

ﺫﻫﺐ ﺍﻟﻈﻤﺄ ﻭ ﺍﺑﺘﻠﺖِ ﺍﻟﻌﺮﻭﻕ ﻭﺛﺒﺖ ﺍﻷﺟﺮ ﺇﻥ ﺷﺎﺀ ﺍﻟﻠﻪ
♦️ጥም ተወገደ፣ ጉሮሮዎችም (የደም ስሮች) ረጠቡ፣ በአሏህ ፍቃድ አጅሩም ፀደቀ።"
📚 ﺻﺤﻴﺢ ﺍﻟﺠﺎمع) [(4678)
La tehzen
ረመዷን -1 ሱሑር -1 አላህ ሐያታችንን አርዝሞ በርሱ ፍቃድ ተመልሰናል። ያለ ሰው ሲገናኝ የሞተ ግን በቃው። በዲን ላይ ቆይቶ ዳግም መገናኘት ትልቅ መታደል ነው። አላህ ሆይ አምና ከኛ ጋር ለፆሙት ዘንድሮ ግን ለሌሉ ወንድም እህቶች ሁሉ ምህረትህን ለግስ። https://t.me/httpsLatahzen
ረመዷን (2)
ሰሐር፣ ሰሑር እና ሱሑር
**
'ሰሐር' ከእውነተኛው ንጋት (ሱብሒ ሶላት መግቢያ ምልክት) በፊት ወደ ሌሊቱ መጨረሻ አካባቢ የሚገኝ ጊዜ ነው።
በዚህ ጊዜ የሚበላ ምግብ/መጠጥ 'ሰሑር' ይባላል።
የመመገብ/መጠጣት ሁኔታው ደግሞ 'ሱሑር' ይባላል።

'ሰሑር' ለፆም መያዣ ተብሎ የሚበላ ቀለል ያለ ምግብ ወይም የሚጠጣ ዉሃ ነው።
ሰሑርን መመገብ ነቢያዊ ፈለግ ነው። እርሳቸው እንድንጠቀም መክረዋል። የሰሑር ዓላማው የሚበላና የሚጠጣ ነገር በማግበስበስ፣ ሆድን መወጠርና ማጨናነቅ አይደለም። ወይም ደግሞ በተለምዶ ከረመዷን ዉጭ ቀን ላይ ይመገቡ የነበረዉን ምግብ ወደ ሌሊት ጊዜ ማዞር አይደለም። እንዲያማ ከሆነ ፆም ዓላማዉን ይስታል።

ሰሑር በረከትና ምንዳ አለው። በፆም ላይ ያበረታል። ሰሑር ጉንጭ ዉሃ ሊሆን ይችላል። ጥቂት የተምር ፍሬዎች ሊሆን ይችላል። አንድ እና ሁለት ጉርሻ ምግብ ሊሆን ይችላል።

ሱሑርን እኛ ሙስሊሞች ብቻ ነን ያለን። በዚህም ከሌሎች ሃይማኖቶች ፆም እንለያለን።

https://t.me/httpsLatahzen
እናንተ ጿሚዎች ሆይ

በሱሁር በረካ አለው ተነስታችሁ የበላችሁ ላልተነሱ ጓደኞቻችሁ ደውሉላቸው ።