La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
የመጨረሻ ክፈል ዝሙት

ሁላችሁም ሼር እንድታረጉ በአላህ ስም እጠይቃለሁ

አላህ (ተባረከ ወተዓላ) ያይኛል ይሰማኛል ብሎ በልብ ውስጥ እምነትን ማስቀመጥ ከዝሙት ለመጠበቅ ሌላው ፍቱን መድኃኒት ነው።

ከከባባድ ወንጀሎች ክፍል 6 (ዚና) ዝሙት ነው።

እንደሚታወቀው ዝሙት በዚህን ዘመን ላይ እንደከባድና አውዳሚ፣ ዘርን የሚያበላሽና የሰው ልጆችን መልካም ስነ–ምግባር የሚያበላሽ ወንጀል እንደሆነ ሊታወቅና ሊታመን ቀርቶ፣ በተቃራኒው እንደ ሀላል እየታየና ሀላሉ የኒካህ ጋብቻ እንደ ሀራምና ኋላ ቀርነት እየታየ ነው ታዲያ ከዝሙት የመራቂያና የመጠንቀቂያ መፍትሄዎችንና መድኃኒቶችን በሚገባ መጠቀም ግዴታ ነው!
አላህ (ሱብሃነሁወተዓላ) በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነን ወንጀልን መዳፈር እንደሌለብን ሲያስጠነቅቀን የትኛውም ቦታ ላይ ብንሆን እንደሚያየን በተለያዩ የቁርኣን አንቀፆች ነግሮናል: ከነዚያም ውስጥ የሚከተለውን አንቀፅ መመልከት ይቻላል:–
﴿إِنَّهُ يَعلَمُ الجَهرَ مِنَ القَولِ وَيَعلَمُ ما تَكتُمونَ﴾
“እርሱ ከንግግር ጩሀትን ያውቃል። የምትደብቁትንም ሁሉ ያውቃል።” አል አንቢያእ 110
ይህ አንድ ሰው በምላሱ በሚናገረው ከሆነና በልቡ ውስጥ የደበቀውን ሸር ሁሉ የሚያውቅ ከሆነ በግልፅ በአካሉ ሀራም ነገር ሲሰራ፣ እንደ ዝሙት ያለ ፀያፍ ብልግና ሲሰራ አላህ ከላይ እንደሚያየው ጠንቅቆ ካወቀና ካመነ ከዝሙትም ሆነ ከሌሎች ወንጀሎች ሊቆጠብ ፍቱን መድኃኒት ይሆነዋል።
የትኛውንም መልካም ስራችንን ስንሰራ አላህ እንደሚያየን አድርገን እንድንሰራ ነቢዩ ﷺ በሶሂህ ሀዲሳቸው ተናግረዋል: ኢህሳን ማለት “አላህን ልክ እንደምታየው አድርገህ እንድታመልከው ነው፣ አንተ ባታየው እንኳን እርሱ ያይሃል” ብለዋል።
ይህ እንግዲህ መልካም ስራችንን ስንሰራ አሳምረን እንድንሰራና ከመጥፎ ነገሮችም እንድንጠነቀቅ የሚያደርገን ሐዲስ ነው። በሌላ ሐዲሳቸው የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከወንጀል እንድንጠነቀቅም እንደሚከተለው ተናግረዋል:– “በየትኛውም ቦታ ላይ ሆነህ አላህን ፍራ!…።” ብለዋል።
አዎ! የትኛውም ቦታ ላይ ያለ ሰው ነፍሲያውና ሸይጧን ማንም የሚያውቅህና የሚያይህ ሰው የለም፣ ይህ ቦታ እኮ ጨለማ ነው ብለው ወደ ወንጀል ሲጎተጉቱት፣ ሰዎችን ሁሉ የፈጠረ፣ የምራመድበትን እግሬን የፈጠረ፣ አለምን ሁሉ የፈጠረ፣ አካሌን ሁሉ የፈጠረ፣ ጨለማና ብርሃንን የፈጠረው አላህ ያይኝ የለም እንዴ? ብሎ ሊመልስና ሊመለስ ይገበዋል!!
ይህ ከሆነ በድብቅ ከ(አጅነቢይ) ባእድ ተቃራኒ ፆታዎች ጋር በየ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወደ ዋናው ዝሙት የሚያዳርሱ ፅሁፎችን መፃፃፍ ይቀራል፣ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ የተቃራኒ ፆታዎችን ፎቶዎችንም በድብቅ እያዩ መመሳሳጥ ይቀራል፣ በድብቅ ተቃራኒ ፆታን ማየት ይቀራል፣ ሰዎች በሌሉበት ገጠመኝ ተቃራኒ ፆታዎች ቢገናኙ እንኳን ወደ ሀራም የሚያዳርሳቸውን ነገር ሁሉ ይርቃሉ፣ ምክንያቱም ማንም ባያያቸው እንኳን አንድ ከባድ የሆነ የሚፈሩትና የሚያመልኩት ከደም ስራቸው የበለጠ ቅርብ የሆነው አምላካቸው አላህ እንደሚያያቸው ጠንቅቀው ያውቃሉ፣ እርሱንም በሚገባ ይፈሩታል፣ ከማንም በላይ ያፍሩታል! ለነፍሲያቸውና ለሸይጧንም ጨለማ ቦታ ላይ "ጨለማ እኮ ነው ማንም አያይህም/ሽም" ሲሉት፣ ጨለማን የፈጠረው አላህ ያይኛል ብለው መልስ በመስጠት ከሀራም ይቆጠባሉ።
ሀያሉ!! አምላካቸው አላህ እንደሚያያቸው በልባቸው ውስጥ እምነትን ካሳደሩ፣ በተከበረውና በተለይ መልኩ የ(ተውበት) ወደ አላህ ተፀፅቶ የመመለሻ ወር በሆነው የረመዷን ወር ላይም ከቤተሰባቸው በተራዊህ አሳበው ወጥተው ተደብቀው ጨለማንና የተለያዩ ድብቅ ቦታዎችን ተገን በማድረግ ዝሙት ከመፈፀም ይቆጠባሉ
አዎ! ከቤተሰብ ብትደበቅም/ብትደበቂም አላህ ያይሃል/ያይሻል! ከፍጡራን በጠቅላላ ተደብቀህ/ሽ ወንጀልን ብትሰራም/ብትሰሪም ለትንሽ ጊዜ ተውበት አድርገህ/ሽ ወደ አላህ ቶሎ እንደምትመለስ/ሽ ቢታገስህ/ሽ ነው እንጂ፣ አላህ የምትደበቃቸው/የምትደበቂያቸው ሰዎች ፊትም ያጋልጥሃል/ሻል፣ የዛኔ አኼራ አዱኒያህ/ሽ ምስቅልቅሉ ይወጣል
ከሁሉ በላይ ትልቁ ፀጋ አላህ ያይኛል ይሰማኛል ብሎ ከሀራም ነገሮች መጠንቀቅና ባእድ የሆኑ ተቃራኒ ፆታዎችን ከማየትም አይንን ሰበር ማድረግ ነው!!! ስለ ሰዎች ከመጨነቅህ/ሽ በፊት ስለ አላህ ተጨነቅ/ቂ!! ሰዎች ለተወሰነ ጊዜ ቢያወሩትም በቃ አበቃለት/ላት ተባለሸ/ች ብለው ይተውታል፣ የአላህ ቅጣትና ቁጣ ግን ለቀጣዩም ዘላለማዊ አለም የሚቆይ ነው
እናንተ የአላህ ባሮች ሆይ! አላህን ፍሩ የኒካህ መንገዶችን ቀላል አድርጉ!! ዝሙትን ከሞትና ከእሳት በላይ ፍሩት! ራቁት ተጠንቀቁት
﴿وَلا تَقْرَبُوا الزِّنَى إِنَّهُ كَانَ فَاحِشَةً وَسَاءَ سَبِيلاً﴾ الإسراء ٣٢
"ዝሙትንም አትቅረቡ፡፡ እርሱ በእርግጥ ፀያፍ/(ብልግና ነውና)፡ መንገድነቱም ከፋ!" [ኢስራእ: 32]
===ተፈፀመ ፡፡
Nurahemd Muhammed


https://t.me/httpsLatahzen

share share
((በአላህ ተመካ))

////

በቆላ በደጋ፣ ከወንድ ከሴቱ
ሁሉንም አዩሁ ከልጅ ከወጣቱ
ልሙት ይሰንጥቀኝ በጌታው ስም ምሎ
ላልከዳህ ላልከዳሽ ሲኖር ተዋውሎ
አንድ ቀን ይርቃል ተበደልኩኝ ብሎ
እናማ …
በስጋ በነፍሱ እዬተፈተነ፣አድሮ ከሚጠፋው ከፍጡራን ሁሉ
ሲያምኑት የማይከዳ፣
ሊያምኑት የሚበቃ፣ አንድ አላህ ብቻ ነው የሚገኝ በቃሉ


https://t.me/httpsLatahzen
ጁምአ ነነነነነነው
*****

አንዳንድ ቀን አለ
ቃል ሳይናገሩ በአይን የሚያግባባ
ከራህመት አውድማ ጎትቶ ሚያስገባ
የመዳንን ጥሪ ልቆ ሚያስተጋባ
አንዳንድ ቀን አለ
በቀናት መሀከል ተማግሮ የቆመ
ከወፎች ቅላፄ ዜማ የቀመመ
በብርሃን ጣቶቹ መንገድ የጠቆመ
ከሙት ሰልፍ አውጥቶ ህልው የሚዘራ
ወደ ፅድቅ ደጃፍ ኡመት የሚጣራ
አንድ አንድ ቀን አለ
እንደ ጁምዐ ያለ



https://t.me/httpsLatahzen
«አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላሒ ወበረካቱሁ እንዴት ናችህ ያጀምአ ወንድሜ በጣም ታሟል ኩላሊቱና ጉበቱ መታጠብ አለበት ተብለን በጣም ተቸግረናል በገንዘብም በዱአም በፓስትም እህት ወንድሞች አንዲረዱን ለመጠየቅ ነው እንድታግዙኝ እፈልጋለሁ ሁለት ኩላሊቱ ከጥቅም ውጪ ነው ጉበቱ ባይረስ አለበት ሳንባው ውሀ ቋጥሯል ተብለን በጣም ፈተና ላይ ነን በሳምንት 3ግዜ እየታጠበ ነው በወር 36ሺ ነው ምናወጣው አላህ በሚያቀው አቅሙ የለንምና ለአላህ ብላችሁ ለወንድሜን ድረሱለት አላህ ያለው ነው ሚሆነው ግን የሰውልጅ ተስፋ አይቆርጥምና ሰበቡን ለማድረስ ነው ካርድም የሚሸጥ አለ የታተመ ልታወሩኝ ከፈለጋችሁ 0919325101 ደውሉልኝ።» የምትችሉ ሁሉ ተባበሯቸው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①∅

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
«የታለች ልእልቷ »!!

➻ውብ ፅጌሬዳ የፈካሽ አበባ
በጥሩ መአዛ በውዴታሽ ልግባ
የጌታሽ ፍራቻ አሣምሮሽ የኖርሽ
እሡን ለማስደሠት ሲሆን ጥረትሽ
ሁሌ ትደምቂያለሽ እንዳበባ ፈክተሽ!!

➻መልክና ቁንጅና በማይጠቅመው ቤትሽ
ስትሞሸሪ አንቺ በጀነት ውስጥ ገብተሽ
ጥንቁቅ እና ትሁት በድምር ላይ ሆነሽ
አሣልፊው በቃ ምንዳውን ከጅለሽ!!

➻የሁለት ሀገር ስኬት ቁልፉ እኮ አንቺ ነሽ
ትዛዙንም ስሚ ክልከላውን እራቂ
የአሄራን ህይወት እንዲያምር ሠንቂ
እሳት እንዳገቢ በጣም ተጠንቀቂ!!

➻እውነት ነው ይመጣል ልብወለድ አይደለም
ተነግሮናል እና ልብ በይ እህት አለም
ለሚያልፍ ኑሮ ለዚች አጭር ጊዜ
ምነው ባንኳትን እንደው እንዳአባዜ
በዱኒያ ነገር ባይበዛ ትካዜ!!

➤Join sher👇
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
🕌አላህ ቃል የገባቸው
4⃣ ነገሮች
ማወቅ ያለብህ እናም መቼም ልንረሳው የማይገባ

🔶 ያመሰገናችሁኝ
ከሆንእጨምርላችዋለው

🔶 አስታውሱኝ
አስስታውሳችውዋለው

🔶 ለምኑኝ እሰጣችዋለው

🔶 አላህን አንዳቸውንም
አይቀጣም መሀርታውን
እስከ ፈለገ ድረስ
ሌላውም ሰው ይውቅ ዘንድ ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ሼር ያርጉ
.
.

https://t.me/httpsLatahzen

nur
ኢላሂ

ይቅር በለኝ ልልህ ቆሜ ባፈርኩህ ሰአት
ሲናገሩ ሰማሁ የአንተን ግዙፍነት
ወንጀሉ ያሳፈረዉ ባርያህ እጅ አንስቶ
ማረኝ ሊልህ አፍሮ ማረኝ ሊልህ ፈርቶ
ከደጅህ ላይ ቆሞ ብትመለከተው
አንተም መቅጣት አፋረህ ይቅርታን ሸለምከው
ኢላሂ ......


https://t.me/httpsLatahzen
የካሜራ ነገር
Sadat
⤴️⤴️ የካሜራ ነገር


🎤Bustaze Sadat Kemal
Abu Meryem
(
#حفظ_الله)

⤴️⤴️ የካሜራ ነገር
ሰላት ኡምራ፣ ዱኣ፣ ሰደቃ፣ ሰርግ፣ ሚዜ፣ ምርቃት !!

ጭራሽ ደግሞ ሌላ ጉድ ልንገራቹ፦በፎቶ ሾፕ ፎቶ መነካካት ፎቶ ሾፕ የሚባል ሶፍት ዌር አለ አላህ አሳምሮ ነው አይደል የፈጠረን ነው እንጂ ፎቶ ቤት ያሉ ሰዎች ምን ያደርጋሉ ፎቶ ያነሱህና እንዳለ በቃ ቡጉር አትቀር ምን አትቀር ሙልጭ አድርጎ በሶፍት ዌሩ አጥፍተውት የተወለወለ ሌላ ሰው ያስመስሉሃል¡! በዚህም የተነሳ የብዙ ሰዎች ትዳር እየተናጋ ነው! በተለይ ውጪ ሃገርና እዚህ ሃገር ያሉ ሲተዋወቁ ፎቶሽን ላኪልኝ ፎቶህን ላክልኝ ይባባሉና የ50 ሽማግሌ የ25¡¡ አመት ጎረምሳ ሆኖ ቁጭ ይላል!ሴቷም እንደዛው! አላሁል ሙስታዓን!! ከዛ ልክ ወደ ትዳር ከገቡ በኃላ አረ እኔ እንዲህ አልመሰልሽኝም ነበር ፎቶ የላክሽው ትዝ አይልሽም?? ምናም ይባባላሉ¡! ሹፍ ጨዋታ አስለን ለትዳር በፎቶ አይደለም!

https://t.me/SadatKemalAbuMeryem
የእናትህን አምሳያ አታገኝም!
ልጅ እያለህ ታመህ ወደ ሀኪምቤት ትሄድ ነበር። ሀኪሙ "ምን ይሰማሃል?" ብሎ ሲጠይቅህ ፡ መልስ መስጠቱን ትተህ የእናትህን ዓይን ትመለከታለህ፤ መልስ እንድትሰጥልህ። ምክንያቱም ላንተ የሚሰማህ የህመም ስሜት ለርሷም እንደሚሰማት እርግጠኛ ነህና!
እናም ወላሂ
የርሷን ዓይነት አታገኝም!!!
=~~~
"""እማመቅረዜ""""

አይኖችሽ ከሰማይ ይመሳሰላሉ፣
እምቅ ዝናብ አዝለው ጸሀይ ያወጣሉ፣
ሰማይና ልብሽ ሁለቱ አንድ ናቸው፣
ሺህ ጊዜ ተሰብረው ጠባሳም የላቸው፣
እንደ ሀምሌ ሰማይ ውስጥሽ ብዙ እምባ አለ፣
ብቻሽን ማልቀሻ ጓዳ በማጣትሽ ውስጥሽ፣ የታጀለ
ባለ ብዙ ሀዘን ባለ ሺህ መከራ፣
የልብሽ ፍጥረቱ ላዘን የተሰራ፣
እማ የኔ መቅረዝ የደስታዬ ባህር፣
የመጽናናቴ ምንጭ ዛሬን የመሻገር፣
ሰው ያላየው ጥበብ ቢኖርሽ ነው እንጂ፣
ከሀዘን ባህር ውስጥ ደስታን የምትቀጂ፣
     ┄┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄┄👇

https://t.me/umuzefa123456
*ጠያቂ ነኝ እኔ*

ያስቀየምኩት ካለ፣በስካሁን ቆይታ
ያስከፋሁት ካለ፣በእኔ ልቡ ደምታ
በአላህ ስም በሉኝ፣ከልባቹ ይቅርታ

ደካማ ፍጡር ነኝ፣በስራዬም ዘንጊ
በማላቀዉ ነገር፣የሰዉ ስሜት ወጊ
ይሆናል ባላልኩት፣ጭራሽ ባልገመትኩት
ጎድቼ ይሆናል፣የአንዳቹሁን ስሜት
ግና አዉቄዉ ባይሆንም፣ክፋትም አስቤ
ይቅር በሉኝ እና፣ይሰብሰብ ሃሳቤ

ለአላህ ብዬ፣ሁሉን እወዳለው
ወላሂ፣ከልቤ፣አፍ ብያቹሃለሁ

ቅርም ያሰኘሁት፣በምሰራዉ ስራ
ያበገንኩት ካለ፣ሊነግረኝ የፈራ
አዉፍ እንድትሉኝ፣እላለዉ አደራ
ማንን እንዳስቆጣዉ፣ከቶ አላዉቅ እኔ
እንዲያዉ በደፈና፣ይቅር በሉኝና ይረፍልኝ ጎኔ።



ኑርhttps://t.me/httpsLatahzen
>>> አፈውቱ . . . <<<


አፍህን አዳልጦት እሱም አፉ ገድፎ
የፍቅራችሁ ፀዳል ከራማው ተገፎ
ቂም በቀል ይዛችሁ የምትቋሰሉ
ፍቅር ሰላም ይሁን አውፍ ተባባሉ::
አፈውቱ ... አፈውቱ
ተዉ አንሁን ከንቱ ! ...
ዘመን ጉልበት ሰጥቶት ክንዱን አበርትቶ
አቅመ ቢስ ደካማን በግፍ አንገላቶ
ዘርፎ!... ነጥቆ!... ሰቅሎ!...
አስሮ!... ገርፎ!... ገሎ!...
በድንቁርናው ልክ ስንቱን አመሳቅሎ
ወገን የበደለን ያን ጭንጋፍ ሙትቻ
የዘመን እንቅፋት የሰው አራሙቻ
ክስረቱን ቆጥራችሁ ግፉን በርብራችሁ
እጥፉን ልትከፍሉት ደግሞ በተራችሁ
ሰይፍ የምታፋጩ ጎራዴ የምትስሉ
ግዴላችሁም ተውት ይቅር ተባባሉ
በፍቅር ወስፈንጥር ጥላቻን ግደሉ! . . .
አፈውቱ ... አፈውቱ...
በሉ አፈውቱሊላ (ህ)
እንረስ በደቦ፣
ባንድ ማእድ እንብላ::
ደግሞም ያንን ርካሽ
ጉማጅ የሰው ብጣሽ! ...
ዘር ቀለም ሃይማኖት ስር እየመዘዘ
የፍቅርን ሰንሰለት እየገዘገዘ
ያብሮነትን ዋርካ እየመዘመዘ
የአድባሩን ሸንጎ ባፉ እየመረዘ
ሃቅና ቅጥፈትን ባንድ እየበረዘ
ሲዳክር ሲባዝን ለክስረት ሲለፋ
ሽቅቡን ሲወጣው ተያይዞ ሊጠፋ ...
አይታችሁ ብትበግኑ ውስጣችሁ ቢቃጠል
በነፍጥ አታድርጉት አውድሙት በቅጠል!...
ምግባሩን ነው እንጂ ተውት የሱን ገላ
ርካሽ ነው ርካሽን በርካሽ 'ሚበላ
ይሁን እድል ስጡት ይቁረስ አንድ እንጀራ
ደንዳናው ልቦናው በፍቅር ቢገራ ...
የከበደው ሰማይ ያ የቂም ደመና
ያልፋል በይቅርታ ሳያደርገን መና . . .
ይቅር በል!
ይቅር በይ!
በቃ አፈውቱሊላ (ህ)
አይርከስ
አይፍረስ
የጎጇችን ባላ::


https://t.me/httpsLatahzen
#አንድ_እውነት_እናውራ__!!
----------------------------------
አብዛሀኛውን ህዝቡ በሽርክ እየጋዬ፡
በአድስ መጤ ቢድዐ እየተሰቃዬ፡
ሞት እየቀደመው ተውሒድ ሳይረዳ፡
ቀብር እየገባ ሳያውቅ ሸሀዳ፡
የፊትና ሰንሰለት አረቂ ስትቀዳ፡
ደግሞም እየዋሸህ እያልክ ሚሪንዳ፡
ይህ ይዘገንናል ለዘመድ ለባዳ፡
-------------------//----------------
ጂን እያመለከ አንበሶና ጨንገር፡
እየኖርን እያለ በእንድህ አይነት ሀገር፡
በራሒሎ በጭራቅ በአድባሩ በቆሌው፡
በሰራን በሾናት እንድሁ በጭሌው፡
ሽርክን እምነት ይዞ ህዝቡ ተውሒድ ትቶ፡
ቢዲዐ ሲከተል ሱናውን ዘንግቶ፡
ባጢል ላይ ሲፀና እውነትን ረስቶ፡
ተውሒድ ካላስቀደምን ይህንን እያየን፡
ከኢኽዋን ከአህባሽ ለምን ተለያየን?
-----------------------------=-------------
የተለየንበት ከነዚህ ቡድኖች፡
ከጥመት ጥርቅም ከቢዲአ ጋኖች፡
በተውሒድ በሱና ስለማይጣሩ፡
በማያውቁት ነገር ስለሚናገሩ፡
በእምነት ሲዋሹ አሏህን ሳይፈሩ፡
ከሀቁ ጎዳና ሲለቁ ከፈሩ፡
በዚህ አይደለም ወይ የተለያየነው፡
ጩኸቱ በዛሳ ኪነት ያገነነው፡
አልገባኝም እኔ ሚስጥሩ ምንድን ነው!?
---------------------///--------------------
በነዚህ ምክነያት ከነርሱ ብንርቅ፡
ይህ የነርሱ መንገድ ላንተ ከሆነ ብርቅ፡
አሏህ ይድረስልህ እኔ ምን ላድርግህ፡
ለፊትና አትፈልገኝ እኔም አልፈልግህ፡
-------------------------------------------
እየተመለከ መርሳ አባገትዬ፡
ምን ተቆጥሮ ያልቃል በጥቅሳ አባዬ፡
ደገር አማን አምባ በቃሉ ገትዬ፡
ድረሱልኝ ሲባል ቦረናው ደግዬ፡
ድምፅ ከፍ አድርገው እያሰሙ ለቅሶ፡
ጋቻ ተዘጋጅቶ እጣን ተጫጭሶ፡
ባንቱ መጀን ሲባል አብሬትና አልከሶ፡
ተውሒዱ ሲረሳ የድኑ ምሰሶ፡
በሀገራችን ውስጥ እያለ ይህ ክስተት፡
አንተ ነጋ መሸ ከጨመርክ ስህተት፡
በአሏህ ንገረኝ እኔ ምን ላድርግህ፡
አንተም አትፈልገኝ እኔም አልፈልግህ፡
-----------------------------------------
መማር ከተሳነህ ከትላንት ዛሬ፡
ፊትና ከናፈቀህ ከተጠማህ ወሬ፡
ህዝብህን ተመልከት ሒድና ቃጥባሬ፡
በሚዲያው አለም አታብዛ ዝማሬ፡
ሰኞ ቀን ነብዩን ህዝቡ እያመለከ፡
ማክሰኞ ኑርሁሴን ብሎ እየሰበከ፡
እሮብ ለአብዶዬ እያረደ ዶሮ፡
ይህንን ዘግናኝ ሽርክ እየሰማ ጆሮ፡
ተውሒድ ተዘንግቷል ጉድ አየን ዘንድሮ፡
ከሰውነት ወጥተን ባስተሳሰባችን ሆነናል ዝንጀሮ፡
#አዎ___!
ሽርክ ግልፅ ሆኖ ተውሒድ ከተረሳ፡
እውነቱን ልንገርህ ሆነናል እንሰሳ፡
-------------------///--------------------
ሀሙስ ኸሚስ ብሎ ሰው ተሰብስቦ፡
መስፈርት አብጅቶ አምሮና ተውቦ፡
ሽርክ ለመፈፀም ተዘጋጅቶ ቀርቦ፡
ለዚህ አይነቱ ህዝብ አታዝንም ወይ አቦ!!?
ቅዳሜ በኸድር እየተመጀነ፡
ይሔ ክብር መስሎት እየተጀነነ፡
ይሔው ባገራችን ቢድዐው ገነነ፡
ህዝቡ ዛሬም ይላል እሁድን ለቁጥቡ፡
አድሩስ አትጨርሱ ቡናውን ቆጥቡ፡
በሁሉም ቀናቶች ሙታን ሲመለኩ፡
እምነቶች ጠቅላላ በሽርክ ሲለኩ፡
የአሏህ አምላክነት ፈፅሞ ሲረሳ፡
ምን እየሰራህ ነው የመንሀጅ ደረሳ፡
የተውሒዱ ሞተር የሱናው አንበሳ፡
በእውቀት ታነፅና ተውሒድ በል ተነሳ፡
ለደዕዋ ተዘጋጅ በል ጡሌህን አንሳ፡
እውነት ሰለፍያን አንተ ከተረዳህ፡
ቃል ገብቷል ፈጣሪ ጀነት ሊመነዳህ፡
-------------------------------------------
#ግና_ወዳጄ ሆይ___!!
ይሔ ሽርክ እያለ በሀገራችን ወሎ፡
ዛፍ እያመለከ ህዝቡ ተኮልኩሎ፡
እያስተናገደ ወጣት ተመልምሎ፡
እንደ ግመል መንጋ ሲሔድ ተግተልትሎ፡
በደቡብ በሰሜን በምዕራብ በምስራቅ፡
ዶሮና ፍየል በግ ሰው ሲያመልክ ጭራቅ፡
በሀበሻ ምድር ባለንባት ሀገር፡
እጅግ ያሳስባል የተውሒዱ ነገር፡
በሁሉም ክልሎች ሽርክ አለ በአቻ፡
በደቡብ ቃጥ ባሬ ኦሮሚያ ኢሬቻ፡
አድባርና ቆሌ አለልህ በአማራ፡
ከደጋ እስከቆላ ብሎም ካራማራ፡
ሽርክ በጣም ገዝፏል ተሻገር ኤርትራ፡
ሀቅን ለመናገር አትሁን አይናፋር፡
እጅግ ብዙ ነገር ሽርክ አለ በአፋር፡
-----------------------------------------
መወከል ራሒሎ ሾናትና ጨሌ፡
ተውሒድ ላይ አተኩር ሽርክ አለ ሱማሌ፡
እንደ ምግብ መጠጥ ቀርቦ የሚበላ፡
እጅግ ዘግናኝ ክስተት ሽርክ አለ ጋንቤላ፡
ነገ በምንተዋት በዚህች ጠፊ አለም፡
ያልተሰራ ወንጀል ያላየነው የለም፡
ሒድና ተመልከት በጎጃም በጎንደር፡
ለጅን የሚገበር አለ ብዙ ጊደር፡
ብዙ ነገር አለ በሙታኖች ቀብር፡
ያዩናል እያሉ ይከፍላሉ ግብር፡
አላፊና አግዳሚው ይጥላል ብዙ ብር፡
---------------------------------------------
ጫት ቢከለከልም በቤት ወይ በኪራይ፡
ያልተከለከለ ሽርክ አለ በትግራይ፡
በሙሉ ሀበሻ ሽርኩ ተጥለቅልቋል፡
ዳኢው ይህን ትቶ ተራ ነገር ናፍቋል፡
ምን እንደሁ አላውቅም ከተውሒድ ርቋል፡
በኔ ይሁን አለም ፉክክር ላይ ወድቋል፡
ጯሒና አጨብጫቢ ቲፎዞ አብጅቶ፡
የተውሒድ ስብከቱን እርግፍ አርጎ ትቶ፡
የሌለ አድስ ነገር ያመጣል ጎትቶ፡
#ጉድ__!!
ከዚያ እኔን ካልመሰልክ ብሎ ይከስሀል፡
በማታውቀው ነገር፤
ባልሰማኸው ክስተት ይመስለኛል ብሎ ረድ ይሰጥሀል!?
#ጉድ_ነው_!!
ተዘዋውረህ ብታይ ሔህ ወደ ሀረር፡
የሽርክ የቢዲአ አለ ብዙ ጨረር፡
ይህ ሁሉ መከራ እያለ በሀገርህ፡
ከሽርክ ማስጠንቀቅ ቢሆን ንግግርህ፡
ቁጭት ውስጥህ አድሮ ዋልጌነት ቢመርህ፡
በደቡብም ብትዘምት በስልጤ ጉራጌ፡
ሙታን የሚጣራ ብዙ አለ ባለጌ፡
ስራ የማይሰራ ሰነፍና ዋልጌ፡
ይህን ሁሉ ነገር እየተመለከትክ ባይንህ በብረቱ፡
ምነው ከሽርክ ይልቅ ከሱና ሰዎች ላይ ክንዶችህ በረቱ!?
#ያ_አሏህ_በጤናህ_ነው!?
አዎ ከተውሒድ ውጭ ከሆነ ርዕስህ፡
በየትኛው ዳኛ በምን እንክሰስህ፡
አውሬ አይደለን እኛ መቸስ አንነክስህ!?
ወይም በሬ አይደለህ በመጥመድ አናርስህ፡
ይልቅ ተውሒድ ስበክ ፍራላት ለነፍስህ፡
ማንንም አትጎዳም ተጠንቀቅ ለራስህ፡
በሁለቱም ሀገር እንድመች ትራስህ፡
------------------///------------------
ይልቁን ተመከር ጥመትህን ልቀቅ፡
ተገሰፅ ወገኔ እባክህ ተጠንቀቅ፡
ዛሬ ባወራኸው ነገ ከመሳቀቅ፡
ከመጥፎ ዘመቻህ አሁኑ ተላቀቅ፡
በቁርአን በሀዲስ ተፈተሽ ተመርመር፡
ከዛም አንድ እንሁን በሀቅ እንጣመር፡
ዱንያችን ይሳካ አኸይራችን ይመር፡
ችግርም ይልቀቀን ሪዝቁም ይደመር፡
ሱና ላይ በመፅናት ህይወታችን ይስመር፡
--------------------//-------------------------
ሽርክና ቢዲዐን ገድለነው ይቀበር፡
ከኛ ላይ ይነሳ የጠላቶች ቀንበር፡
የመሰለኝ ወሬ ይዘጋ ይሔ በር፡
መረጃ ቢዳኘን መች ይመጣ ነበር:
ቁርአንና ሀድስ ብናበጅ ድንበር፡
ስለዚህ አሁንም ሁላችን እንንቃ፡
ተባብረን እንዝጋው የፊትናውን ሳንቃ፡
ውሸቱ ቅጥፈቱ እዚሁ ላይ ያብቃ፡
ፊትና ቀስቃሽ ሸፍጥን ብለን በቃ በቃ፡
በርሶ መንገድ

በርሶ የቀን ውሎ ቀኑን ቢወጥነው
በፈገግታዎ ልክ ሳቁን ቢመጥነው
ባንቱ ውብ ባህሪ ክፋቱን ቢፍቀው
በእዝነቶ ብርሃን ነፍሱን ቢያደምቀው።
የአማኝ ባህሪ ባንቱ ግብር ቢኳል
ሀሉም በታደለ የጀነትን አስኳል።

#Share #Share

https://t.me/httpsLatahzen
Audio
📚ሱረቱል ሙልክ📚

🎧 ተጋበዙልኝ 🎧
በረመዳን ቁርኣንን ለማክተም‼️

1) አንድ ግዜ ለማክተም፥

~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 4 ገጽ መቅራት፣

2) ሁለት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 8 ገጽ መቅራት፣

3) ሶስት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 12 ገጽ መቅራት፣

4) አራት ግዜ ለማክተም፥
~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 16 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ ገጽ 16 መቅራት፣

5) አምስት ግዜ ለማክተም፥
~~~~
ፈጅር (ሱብሒ) ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዝሁር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
አሱር ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
መጝሪብ ላይ 20 ገጽ መቅራት፣
ዒሻእ ላይ 20 ገጽ መቅራት!!
||


ረመዳን የቁርኣን ወር ነው።
ከአምስት ግዜ በላይ ብናከትምም በጣም ተወዳጅ ነው።

ምናልባት ይህ ፕሮግራማችን አንድ ቀን ወይም በሆነ ሰአት ላይ በተለያዬ ምክንያት ቢያልፈን፣
ከሌላኛው ቀን ወይም ግዜ ማካካስ መቻል አለብን።

አላህ ያግዘን።
#ነብያችን (ﷺ)በ3 ነገሮች ያልተጠቀመ ሰው ከአላህ ራህመት የወጣ ሰው ነው ብለዋል!!!

☞1 "ረመዷን መቶ/ደርሶ/ ራሱን ወደ ኸይር ስራ ያልመለሰ ሰው::
☞2 "የኔ ስም ሲነሳ ሶለዋት የማያወርድ ሰው::
☞3 "እናትና አባቱ በህይወት እያሉ ያልተጠቀመባቸው ሰው ናቸው ብለዋል"ረሱል"(ﷺ)
""የዚህ ተላቅ እንግዳ መምጣት ምክንያት,,,,,
☞1" ሾይጧን ይታሰራል
☞ 2" የጀሀነም በሮች ይዘጋጋሉ
☞ 3 የጀነት በሮች ይከፋፈታሉ:: ይሉናል ረሱል (ﷺ)::
በዘህ በረመዷን ወር:,
☞1 "በመጀመሪያዎቹ 10 ቀናት # አላህ ለባሮቹ ራህመት
የሚያወርድበት ነው::
☞2 "በመካከለኛዎቹ 10 "ቀናት አላህ ባሮቹን የሚምርበት ነው።
☞3 "በመጨረሻዎቹ 10 ቀናት ደግሞ" አላህ(ሱ ወ) ባሮቹን ከጀሀነም እሳት ነፃ የሚያወጣበት ነው።
ይሉናል"ነብይና መሀመድ (ﷺ)

ያ አላህ እውነትም በዚህ ወር
ያልተጠቀመ ከአላህ እዝነት የወጣ ነው" «አላህ ይጠብቀን!!»
እና"፥እናም እህት ወንድሞቻችን የ11 ወር ወንጀል ተጠራርጎ
ገደል በሚገባበት በዚህ ታላቅ ወር ሁላችንም ለዒባዳ መነሳሳት ለኸይር ስራ መሽቀዳደም ይኖርብናል።በዚህ ወር አላህ ጋ ያለንን ግንኙነት ካላስተካከልን መቸም አናስተካክልም። አላህ በዚህ ታላቅ ወር ደርሰው ከሚጠቀሙት ያድርገን!! አሚን