La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: 3]👌

#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠዋት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: 4]👌

#ቁርኣን
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አህለን ቢከ ያረመዳን
እንኳን ደና መጣክ ረመዳን....ረመዳንን እንዴት ነው መቀበል ያለብን??

ሸይኽ አብዱ ያሲን መልእክት አላቸው

𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
https://t.me/httpsLatahzen
የሸይኸ ፈውዛን ምክር
العلامة الفوزان
ልብ በሉ አድምጡት_ራሳችንን እንፈትሽ!!?
#እውነት ምን_እየሰራን_ነው!??

በሸይኽ ሳሊህ አልፈውዛን አንደበት(ሀፊዞሁሏህ)
- ሱንዮች አትበታተኑ
-`ጥፋት ካለ_ተመካከሩ
-#ራስ በራሲችሁ ህሜትን_ራቁ
#የወንድማችሁን ስጋ_አትብሉ

↷⇣🌹⇣↶
https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/11140
Audio
AudioLab
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሃፊዘሁላህ
https://t.me/iliyasNassir/3203
Audio
AudioLab
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሃፊዘሁላህ
https://t.me/iliyasNassir/3204
Audio
AudioLab
በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሃፊዘሁላህ
https://t.me/iliyasNassir/3205
ለኢማናችን መድከም መንስኤዎቹ ምንድን ናቸው ?

እምነት ከሌላቸው ሰዎች ጋር ለረዥም ጊዜያቶች መቀመጥ

ይህ ለአንድ ሰው ኢማን መቀነስ ምክንያት ነው፡፡ አማኝ ምንጊዜም በራሱ ደካማ ነው ነገር ግን ከሙስሊም ጓደኞቹ ጋር ጠንካራ ነው፡፡ ሀሰነል በስሪ(አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለው ነበር “ወንድሞቻችን ከቤተሰቦቻችን የበለጠ ለኛ ቅርብ ናቸው፡፡ ቤተሰቦቻችን ይህን አለም ሲያስታውሱን ሙስሊም ወንድሞቻችን ግን አሄራን ነው ሚያስታውሱን” ብለዋል፡፡ ታዲያ የሙስሊሞች ቀረቤታ ከኛ ከራቀን በዱንያ ውዴታ ስካር ውስጥ ገብተን ኢማናችን ባዶ እንደሚሆን ምንም ጥርጥር የለውም፡፡

ሷሊህና አዋቂ ከሆኑ ሰዎች መራቅ

ከደጋግ የአላህ ባሮች ብዙ ትምህርት ይወሰዳል፤ ትምህርት ብቻ ሳይሆን በጎ ተግባርና ጥሩ ባህሪ ይወረሳል፡፡ ይህን ያስለመደ ሰው ከዛ ደግ ሰው የተለየ ጊዜ ኢማኑ እንደሚወርድ አጣራጣሪ አይደለም፡፡ ልበ ደረቅነትና ግድየለሽነት ተያይዘው መምጣታቸው አይቀሬ ነው፡፡ ለዚህም ነው ነብዩ ሙሐመድ(ሰላትና ሰላም በርሰቸውላይ ይሁንና) ሞተው የተቀበሩ ጊዜ ባልደረቦቻቸው “ልባችንን ስንመለከት ትልቅ ለውጥ እንዳመጣን ይታወቀናል” ያሉት፡፡

ከሀዲስና ከቁርዐን መራቅ

የእምነት ምንጭ ከሆኑት ቁርዐንና ሀዲስ ተርቆ ኢማንን ማሰብ ማለት “ወጥ የለም እንጂ እንጀራ ቢኖር እንበላ ነበር” እንደተባለው ተረት ከመሆን በቀር ፋይዳ የለውም፡፡ በአሁኑ ሰዐት የሚታየው ከባድ ችግር አንዱ ይህ ነው፡፡ አዛዡን በአግባቡ ሳናውቅ ወደ ትዕዛዙ መሮጥ ከተያያዝነው ሰነበትን፡፡ ለማለት የፈለኩት እስልምና አላህ ምን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን አላህ ምን እንዳልሆነም ጭምር በቁርዐንና በሀዲስ በሚገባ ተንትኖልናል፤ ግን እኛ እውን አላህን በሚገባ አውቀነዋል ወይ ? ለኢማን መውረድ ዋናው ሰበብ አላህን አለመፍራት ነው፡፡ ጥያቄው አላህን በሚገባ ሳናውቀው እንዴት እንፈራዋለን ነው ? ለዛም ነው እልቅናው ከፍ ያለው ጌታችን አላህ “እኔን የሚፈሩኝ የሚያውቁኝ ብቻ ናቸው” ያለው፡፡ በአሁኑ ሰዐት እኛ የተጠመድነው ከእስልምና በሗላ በተፈበረኩት በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፍልስፍና፣ በሳይኮሎጂ፣ ልብወለድና ጥቅም በሌላቸው መጽሔቶችና ጋዜጣዎች ላይ ነው፤ እነዚህ በራሳቸው በኢማናችን መድከም ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አላቸው፡፡

ወንጀል በተሞላበት አካባቢ መኖር

ዙሪያህን ረጋ ብለህ ቃኘው...አንዱ ጠጪ፣አጫሽና ቃሚ፤ሌላኛው በዘፈንና በፊልም ድንዝዝ ያለ፤ በሌላ በኩል በተቃራኒ ፆታ የተለከፈና አላስፈላጊ ፎቶዎችና ምስሎች ሲያይና ሲያነብ የሚውል፤ ወሬያቸው ሀሜት፣ ሰው መቦጨቅ ወሬ ማመላለስ፤ ዛሬ አርሰናል ማን ገባ ነገ ማን ወጣ....ተገልፆ አያልቅም፤ አንዳንድ አካባቢዎች ይህን ብቻ ያስታውሱሃል፡፡ አንዳንድ አካባቢ ደግሞ ቢዝነስ ብቻ ሚወራበት ቦታ...ስራ፣ ብር፣ ኢንቨስትመንት የመሳሰሉት...እኛ የቤታችን ውጠት ቤታችን ደግሞ የአካባቢያችን ውጤት መሆኑ ጥርጥር የለውም፡፡ ታዲያ በአሁኑ ሰዐት የሙስሊም ቤት ስንገባ ብዙ አሳፋሪ ኮተቶች ማየት የተለመደ ነው፡፡ አሳፋሪ ሙዚቃዎች፣ ፊልሞች፣ የተከለከለ የሴትና የወንድ መቀላቀል...የመሳሰሉት፡፡ በእንደዚህ አካባቢ መኖር ልባችን እንደ እንጨት መድረቁ ጥርጥር የለውም፡፡

ልባችን የርሷ ባሪያ እስክንሆን በዱንያ ስራ መጠመድ

ነብዩ ሙሀመድ(ሰላትና ሰላም በርሰቸውላይ ይሁንና) “የዲናርና የዲርሃም ባሪያ ጠፋ” ማለታቸው በሰሂህ በቡሀሪ ተዘግቧል፡፡ የምትፈልገው ቦታ የሚያደርስህ ስንቅ በቂህ ነው ምክንያቱም ነብዩ መሐመድ(ሰላትና ሰላም በርሰቸውላይ ይሁንና) “የሰው ልጅ አንድ ሸለቆ ወርቅ ቢሰጠው ሌላ ሁለተኛ ይመኛል፤ የሰውን ልጅ ሆድ ሚሞላው አፈር ብቻ ነው” ብለዋልና፡፡ ይህ እውነታ በሁላችንም ላይ አለ፤ ይህን ስል አንድ ቃለ ምልልስ አስታወሰኝ...የአለማችን አንደኛው ሃብታም ተጠየቀ “ያንተ ገንዘብ እኮ አንተንና ካሁን በሗላ ለሚመጡት መቶ ዘሮችህ አንደላቆ ያኖራል፤ ለምን ትሰራህ ?” ሲባል “ሁለተኛው ሀብታም እንዳይደርስብኝ ነው” ብሎ መለሰ፤ ሁለተኛው ሀብታም ተመሳሳይ ጥያቄ ሲጠየቅ እሱም “አንደኛው ሀብታም ላይ ለመድረስ ነው ምሰራው” አለ፡፡ ታዲያ ነብዩ ያሉት እውነታ አልተገለፀላችሁም ? ዱንያ አንስራ የሚል ቃል አልወጣኝም ለማለት የፈለኩት ኪሳችን ላይ እንጂ ልባችን ላይ አደላድለን አናስቀምጣት ነው፡፡

ከብዙ በጥቂቱ የኢማናችን መድከም ሰበቦች ይህን ይመስላሉ፤ ይህን በሽታ እንዴት ማከም እንደምንችል ኢንሻአላህ በሚቀጥለው ክፍል እናቀርበዋለን፡፡

✏️✏️✏️✏️✏️✏️
https://t.me/httpsLatahzen
#አልሀምዱሊላሒ

ሱብሀን የኛ ጌታ ጥበቡ ገራሚ
እጅግ አዛኝ ሆኖ ተመልካችም ሰሚ
ለሰውልጅ በማሰብ ስለሆነ ደካማ የማይችል ልፍስፍስ
ለድካሙ እረፍት እንቅልፍ ፈጠረለት ህሊናው እንዲያድስ።

የጀሊሉ ትዕዛዝ ወቅቷንም ጠብቃ
ይኸው ብቅ ብላለች የማለዳ ጀንበር አማምራ ደማምቃ
የምድር ፍጥረታት ቀሰቀሰችው በብርሃን አሙቃ

#አልሀምዱሊላሒ ህያው ላደረገን ከሞታችን በኋላ ዳግም ላነቃን
ስራችን እንድናስውብ ሌላ እድል ለሰጠን፣
ወደ እሱ ነውና የኛ መሰብሰቢያ መመለሻችን።

በአዝካር በቁርኣን እሱን በማወደስ
ምሽቱን አሳይቶን ለንጋት እንድንደርስ
ላበቃን ጌታችን ምስጋናን በማቅረብ
ውሎአችን እንጀምር አላማን በማንገብ
ለአኼራው ቤታችን ስንቅን ለመሰብሰብ።


መልካም ውሎ 🥀🥀🌴
እስቲዓና፦ማለት የዱኒያም ሆነ የአኽራን ጉዳይ ለማሳካት እገዛ መፈለግ ማለት ሲሆን የዚህም ብዙ ክፍሎች አሉት (1)እገዛ ከአላህ መፈለግ (2)በሚችሉት ነገር ብቻ ከፉጡር እገዛን መፈለግ (3)በሕወት ያለና አጠገቡ ባለ ሰው ግና ደካማ በሆነ ሰው መደገፍ(4)በሟች መታገዝ(5)በጅኖች መታገስ(6)አላህ ዘንድ በሚወደዱ ሥራዎች
(1)እገዛ ከአላህ መፈለግ ፦ይህም ባሪያዉ ጉዳዩን በሙሉ ወደ አላህ በመተናነስ በመቅረብ እርዳታን መጠየቅ ነው፡፡ ይህም ባሪያዉአላህ ብቻዉን የሚፈልገውን እገዛ እንደሚሰጠዉ ሙሉ በሙሉ በማመን መሆን አለበት፡፡አላህ እንዲህ ይላል((ኢያ ከነእቡዱ ወእያ ከነስተኢን))አንተን ብቻ እንገዛለን፤አተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡እብኑል ቀይም እስትዓና በአላህ ላይ ያለንን እርግጠኝነት በሱ ላይ መደገፋችን ያሣያል ብለዋል እገዛ የሚፈልግ ሁሉ ከአላህ ብቻ ይፈልግ እሱ ብቻ ነው የሰዎችን የእገዛ ጥያቄ ለመመለስ አቅም ያለዉ ለዚህ ነውሙሣ(ዐ ሰ)ለህዝቦቹ እንዲ በማለት መልዕክት ያስተላለፈዉ ለአላህ ተገዙ ታገሱም ምድር ለአላህ ናት ፡፡ከባሮች ለሚሻው ያወርሣታል፡፡ምስጉንዋም ፍፃሜ ለጥንቁቆች ናት አላቸው☝️((አል-አዐራፍ 128))
(2) ከሚችሉት ነገር ብቻ ከፉጡራን እገዛ መፈለግ፦እገዛ በተፈቀደ ነገር ከሆነ አላህ እንዲ ይላል በበጎ ነገር አላህን በመፍራት ተረዳዱ፡፡ግን በኃጢአት ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡አላህንም ፍሩ፡፡አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡(አል ማዕዳህ፡2)በሀራም ላይ ከሆነ በሁለቱም (በአጋዥና ተጋዥ )ላይ ሀራም ነው የተወደደ በሆነ ነገር ከሆነ አጋዥ አጅር ያገኝበታል፡፡በአላህ መንገድ ለግሱ፡፡በእጆቻችሁንም(ነፍሶቻችሁን)ወደ ጥፋት አትጣሉ፡፡በጎ ስራንም ስሩ፤አላህ በጎ ሰሪዎችን ይወዳል፡፡(አል በቀራ 195)
(3)በሕይወት ያለና አጠገቡ ባለ ሰው ግና ደካማ በሆነ ሰው መደገፍ፦ይህ ጫወታ ነው ለምሣሌ፡በጣም ደካማ የሆነን ሰው ትልቅ ሸክም አሸክመኝ ብሎ መጠየቅ፡፡ኑርአህመድ
(4)በሟች መታገዝ፦ይህ ክልክል የሆነ የእገዛ አይነት ነው፡፡ድርጊቱም ሽርኩል አክበር (ትልቁ ሽርክ)ነው፡፡አላህ ብቻ ማድረግ የሚችለዉ ነገር ከሞተ ሰው መጠየቅ ትልቅ በደል ነው፡፡ሙታኖች ምንም ማድረግ አይችሉም፡፡የሞቱ ሰዎች ነብያቶች ሆኑ ወሊዮች እንዲሁም ሌላ ተራ ሰው በዚህ ዘርፍ እኩል ናቸዉ፡፡ከነዚህ እገዛ የፈለገ ሰው ሙሽሪክ ነው፡፡☞ልብ በሉ በሀገራችን በተለያዩ ቦታዋች ከሚገኙ አናጅና(ባሌ የሚገኘዉ የሼክ ሁሴን መሥጂድ)፣በገታ(ወሎ የሚገኘው የገታ ሼክ ቀብር)በጉራጌ ዞን የአብሬትናየቃጥባሬ ቀብር በርካታ መሠል ቦታዎች ይኖራሉ፡፡ወደነዚህ ቦታዎች በመሄድ ከነሱ በሆነ ነገር እንዲረዳቸዉ መለመን ትልቁ ሽርክ ነው፡፡ ከእስልምና ያስወጣል፡፡ከሰዉ ሁሉ በላጭ የሆኑት ነብዩ ቀብር በመሄድ እርዳታን መለመን ከትልቁ ሽርክ ነው ታዳ ለነብዩ ሽርክ ከሆነ ለተራ ሰው እንዴት እገዛን እንጠይቃለን እንደዉ ከኛ ዱዐን እገዛን ይፈልጋሉ እንጂ::ኑርአህመድ
ከሰዎችና ከሌሎች ከሚችሉ አካላት እገዝ መጠየቅ የሚፈቅደው ሶስት ነገሮች ሲሟሉ ብቻ ነው ፦ 1 በሕይወት መኖር አለበት 2 በአጠገቡ መኖር አለበት 3የሚችል መሆን አለበት ኑርአህመድ
በማይችል አካል ያለ አንዳች ድብቅ እምነት ድረሱልኝ ማለት ይሄ ጨዋታ ይሆናል፡፡ ለምሣሌ ፦ለአንድ ሰውነቱ የደነዘዘ ሰው፣ ጉድጓድ ዉስጥ እየሰመጠ አድኑኝ ብሎ ጩኸት ማሰማት፡፡ ሰውየዉ ራሱ ፓራለይዝድ ሆኖ ተቀምጧልና ይህ ደካማ የማይችል ሰውመለመን ትርጉም የለውም ማለት ነው፡፡ባጠቃላይ የማይችል አካል ድረሱልኝ ብሎ መለመን፣ እስረኛ ለእስረኛ ከእስር ቤት አዉጣኝ ብሎ እንደ መለመን አይነት ማለት ነው ሟችን የሚለምን እንደዚህ ሰው አይነት ነው፡፡ምክኒያቱም ሰዉየዉ ከእስር እሱን ማዉጣ ቢችል ኖሮ ራሱ በወጣ ነበርና፡፡ ሌላ ምሳሌ፦ባህር ዉስጥ እየሰመጠ ያለ ሰው ሌላ እየሰመጠ ያለዉን ጓደኛዉን አድነኝ ብሎ መለመን ነው፡፡ኑርአህመድ
ኧረ በአላህ ይሁንብን እስቲ ቁጭ ብለን እናስብ ከአላህ ውጭ ያሉ ነገራቶች ምን ብለን ነው ወደነሱ ምንቃረበዉ እነሱ ሁላቸዉም ተሰባስበው አንድ ቁንጫ ሊፈጥሩ አይችሉም አላህ ያለምንም ረዳት ሰማይናምድር በዉስጧም ያሉ ነገራቶች የፈጠረ እሱን ትተን ወዴት የዉመል ቂያማ እነሱ ናቸዉ እንዴ ሚቀሰቅሱን ወይስ አላህ ነው ሱብሀን አላህ ራሳቸዉ ተቀስቅሰዉ የሰሩት ስራ ይሰጣቸዋል እንኳን ሊቀሰቅሱ ይቅርና እና በምን አይነት ሁኔታ ነው ያለነዉ አባታች ፣እናታችን ቀብር ዝየራ ብለዉ ጓዛቸዉ ይዘዉ ሲሄዱ ሚያዝገነዝብላቸዉ ጠፍቶ ሳይሆን ሀቅ ሚቀበል ታጣ አላህ ከዚህ ነገር ያዉጣንኑር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ④

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
#ፍቅርን_ፍቅር_ከሆነ_ሰው_ተማር
በሌሊት ስግደት ከጌታቸው ጋር በሚገናኙበት ጊዜ ቤታቸው ጠባብ ነበረችና ባለቤታቸው ዓኢሻ እግራቸውን ዘርግተው በተኙበት የአላህ መልክተኛ ወደሱጁድ ሲወርዱ እግራቸውን እንዲሰበስቡ የመእመናንን እናት ዓኢሻን ቆንጠጥ ያደርጓቸዋል ረዘም ላለ ሰዓትም በስግደት ላይ ስለሚቆሙ የምእመናን እናት ዓኢሻ እግራቸውን መልሰው ይዘረጉታል።

አንድ ወንድ ሚስቱን የመኪና በር ከፍቶ ሲያሰገባት ሲያይ ለሚስቱ ባለው ክብር ይደነቃል ነገርግን የአላህ መልክተኛ ﷺ 'በኸይበር' ዘመቻ ላይ ሚስታቸውን ሶፍያን በተከበረው ጭናቸው ላይ ቆማ ግመል ላይ እንድትወጣ አድርገዋል ይህ በዘመቻ ወቅት ለሚስታቸው ያላቸውን ክብር ያሳዩበት ነው። ይኽንን ግን አያስተውልም! 

ለሚወዱት ሰው አበባ ወይም ጥሩ ሽታ ያላቸው ተክሎችን መስጠት የምዕራባውያን ፈለግ እንደሆነ አድርገው የሚገመቱ አሉ ነገርግን የአላህ መልክተኛ ﷺ << ለሱ 'ረይሐን' (የተክል አይነት) የተሰጠው ሰው አይመልሰው (ይቀበል) ቀላልና ሽታዋ ውብ ነውና >> ብለዋል ። 🌷
የስጦታ ትንሽ እንደሌለውም እያስተማሩን ነው!

የአላህ መልክተኛ ﷺ ከምእመናኖች እናት ዓኢሻ ጋር ሆነው መጠጣት በፈለጉ ጊዜ ዓኢሻ የጠጡበትን እቃ ይዘው በጠጡበት ቦታ ይጠጡ ነበር ።ይኽ በትዳር ሕይወት ውስጥ ፍቅርን መተማመንን አንደሚጨምር ጥርጥር የለውም ።
ይኽ ታላቅ ነብይ ለሚስት የምናጎርሰው ጉርሻ ራሱ ሰደቃ እንደሆነ ያስተምሩናል ።🍶

የምእመናን እናት ዓኢሻ የአላህ መልክተኛ ﷺ ቤት ውስጥ የሚያደረጉትን ተጠይቀው ' ልብሳቸውን ይሰፉ ፤ ወተት ያልቡ እራሳቸውንም ቤተሰቦቻቸውንም ይረዱ ነበር ' ትላለች። የሴት ስራ ነው ተብሎ የሚተው ነገር እንደሌለም እያስተማሩ ነው።
•••••••••••••••••••••••••••••••••••••
🌹ፍቅርን ፍቅር ከሆነ ሰው ተማር!



🖊ኑርአህመድ
https://t.me/httpsLatahzen
☞ረመዳን እየመጣ ነው ሰማታቹኃል አይደል…እና ወዳጆቼ እስከዛሬ ከነበርንበት ቀልብ እና የኢማን ደረጃ በጣም ከፍ ብለን መልካም ስራን ተላምደን ከወድሁ የዘጋጁተን ልንጠብቀው ግድ ይላል።የኢማን ደረጃችንን ከፍ ለማድረግ ፕሮግራም አውጥተን ብንጠቀም መልካም ነው እላለው፡፡

📄እኔ ለምሳሌ ይህንን ፕሮግራም አውጥቻለው(ከተስማማችሁ መልካም… ምክኒያቱም የሁሉም ሰው የስራ ዘርፍ እና ክፍት ክፍለ ግዜ ይለያያል እና…)

① ማታ አራት ሰዓት እንተኛለን፡፡
② ሌሊት አስር ሰኣት አሊያም ዘጠኝ ሰዓት ተኩል እንነሳለን፡፡ ለኔ ዓይነቱ ደካማ ሰው በአንድ ምሽት ዉስጥ 6 ሰዓት ከተኛ በቂ ነው፡፡
③ ከዉዱእ በኋላ ለሀያ ወይም ለአርባ ደቂቃ ዊትር እንሰግዳለን፡፡ እንደ ከእንቅልፍ አነሳሳችን እና አቅማችን ማድረግ እንችላለን፡፡
④ እስከ አሥራ አንድ ከሩብ ድረስ በኢስቲግፋርና በዚክር እንቆያለን፡፡ ይህ ከንጋት በፊት ያለው ሰዓት እጅግ የተወደደና ዱዓዉም ምላሽ የሚያገኝበት ነው፡፡ በጣም ልንጠቀምበት ይገባል ። ስሜቱም ደስ ይላል። መስገጃችን ላይ ሆነን ወይም ጋደም ብለን ዚክር ዱዓና ኢስቲግፋር እናብዛ።
⑤እስከ አሥራ አንድ ሰዓት ተኩል ሱብሒ እንሰግዳለን፡፡ የሱብሒን ሱንና መርሳት የለብንም፡፡
⑥ከዚያ በኋላ ፀሐይ እስክትወጣ ድረስ ባንተኛ መልካም ነው፡፡ ለዚክርና ዱዓ የሚወደድ ሰዓት ነውና እንድሁም ቁርኣንን ልንቀራበት የሚገባ ሰኣት ነው፡፡
⑦ከዚያ ተነስተን ቤተሰብ እናግዛለን፤ ወደ ት/ት መሄድ ካለብን እንሄዳለን ቤታችንን እናስተካክላለን፤ ለዕለት ዉሏችን መስመር እንሲዛለን፡፡
⑧ምሳ ከበላን ብኃላ የተወሰነ 30_40 ደቂቃ ያክል አረፍ ብንል ይህ አንድም ማታ ላይ ስንሰግድ እንቅልፍ እንዳያሸንፈን ያግዘናል፡፡ የቀይሉላ ሰዓትም ነዉና ሱናዉን አገኘን ማለት ነው፡፡
⑨ከዐስር በኋላ እስከ መግሪብ ባለው ሰኣት ሁሉም እንደ ፕሮግራሙ… በዚህ ሰኣት ክፍት ክፍለ ግዜ ያለው መስጁድ ቁጭ ብሎ የ ዒልም ሀለቃን ቢጣድ ለሱ የተሻለ ነው።
⑩አስራ አንድ ሰኣት ተኩል አከባቢ የማታ ዚክር(አዝካረል_መሳእ) እናድርግ።
⑪ሦስት ሰዓት ላይ እራት ብንበላ፡፡ ጎን ለጎን ኘሮግራሞች ካሉ መርጠን እናስኪድ። ከእራት በኋላ ባናመሽ መልካም ነው፡፡

♻️እናንተስ ምን አሰባቹህ? ይህ እኔ ያሰብኩት ነው(አላህ ኢኽላስን እና በተናገርኩት መተግበርን ይስጠኝና)

“ለናንተም ቢጠቅማቹህ ብየ ነው ያካፈልኳቹህ”

በወንድማችሁ ኢብኑ ሙሀመድ



https://t.me/httpsLatahzen
🖌🖌🔖የአደም ልጅ ሆይ‼️🖌🖌

✏️💦የትላንት ትላንት ምንም አልነበረህም፤ ምንም ሳትይዝ፣ ራቁትህን ነው ይችን ዓለም የተቀላቀልከው፤
🔑 ይሁንና ትላንት ያጣኸውን ዛሬ አግኝተሃል፣ ዛሬ ያጣኸውን ነገ ታገኘዋለህ፣ ሁሉንም ደግሞ የነገ ነገ ታጣዋለህ።

🔑 ባጭሩ አንድ ቀን ሁሉንም ትተህ ትሞታለህ።

✏️💦ከሞትክ በኋላስ?

🔑 ከ3 ቀን በኋላ የጣቶችህ ጥፍሮች መወዳደቅ ይጀምራሉ።
🔑 ከ4 ቀን በኋላ የራስ ቅልህና ሰውነትህ ላይ ያሉ ጸጉሮች በሙሉ ይረግፋሉ።
🔑ከ5 ቀን በኋላ አንጎልህ መርገብ ይጀምራል፣ የሰውነትህ ሥጋ ይጠወልጋል፤ መቀመጫህ፣ ጡትና ኃፍረተ-ስጋህ ይበሰብሳል።
🔑 ከ6 ቀን በኋላ ቆዳህ መሳሳትና ቀስ በቀስም ከአጥንትህ ላይ መለያየት ይጀምራል።
🔑 ከ7 ቀን በኋላ ሆድህ ይቀልጣል፣ መጥፎ ጠረንም ማውጣት (radiate ማድረግ) ይጀምራል።

🔑 ከሞትክ ከ60 ቀን በኋላ መላው የሰውነትህ አካል ወዳልነበር ይለወጥና "አንተ" ማለት "አጥንት" ብቻ ትሆናለህ:-

🖌🌺ታዲያ🌺🖌

🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ትእቢት?
🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ራስ ወዳድነት?

🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ክርክር፣ ጭቅጭቅና ንትርክ?
🔑 ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ ቅናት?

🔑 ለምንስ ይሆን ይሄ ሁሉ ጥላቻ?

🔑 እኮ ለምን ይሆን ይሄ ሁሉ የክፋት ሥራ?

🔑 ጥለህ ለምትሄደው አለም? እስኪ ለሞት ሩብ ጉዳይ እንደቀረው ሰው እንኑር!!
🔑ደሃ ሃብታም እያልክ ሳታደላ፣ የተማረ ያልተማረ ብለህ ሳትለይ፣ መልከ መልካም መልከ ጥፉ ሳትል፣ ባለስልጣን ተራ ሰው ብለህ ሳትመርጥ...እኩል- ተመልከት፣ ሰዎች ዘንድ በሚኖራቸው ደረጃ ሳይሆን አላህ ዘንዳ ሊኖራቸው የሚችል ደረጃ አታውቅምና አስተንትን!!
🔑 አንድ ቀን የሁላችንም ፍጻሜ አንድ ሥፍራ- መቃብር ነውና!። -
🔑 በሰዎች ደስታ ደስ ይበልህ። ራስህንም በዚህ ምድር ብቻ አትለካው፣
🔑 ከዚህ አለም ወዲያ ያለውን ህይወት አስብና ጊዜህ ሳያልቅ ወደ አላህ ተጠጋ!!
አላህ ያግራልን!!
🔄🔄➨➨➧➧



https://t.me/httpsLatahzen