La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)፡ ዐዋቂና ብልህ ሰው ማለት ሥጋዊ ፍላጎቱንና ስሜታዊ ዝንባሌውን ተቆጣጥሮ ከሞት በኋላ ላለው ሕይወቱ የሰራ ነው። ሞኝ ተላላና ደካማ ሰው ማለት ደግሞ ራሱን (ወደ ተከለከሉና አጥፊ ወደሆኑ እኩይ ተግባራት በምትመራው ነፍሱ) ስሜታዊ ዝንባሌ ቁጥጥር ሥር አውሎ የዝንባሌው ተከታይ በመሆን (ምህረትና ጸጋውን ያላንዳች ጥረት) በባዶ ተምኔት ከአላህ የሚጠብቅ ሰው ነው። /ትርሚዚ/
የነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሀዲሶች

sher
ሶላት ከሰገዱ ቡኋላ መስገጃዎ ላይ መቆየት ምን ያህል አጅር እንደሚያስገኝ ያውቃሉ?
✿┈┈┈┈•✶✾✶•┈┈┈┈┈✿
👉👉 የአላህ መልክተኛ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦ "ከእናንተ መካከል አንዳቹ ሶላት የሰገደበት መስገጃው ላይ እስካለ እና ውዱእ እስካላጠፋ ድረስ መላኢካዎች በርሱ ላይ ሰለዋት ያወርዱለታል። "አላህ ሆይ! ወንጀሉን ማረው፣ አላህ ሆይ! እዘንለት።" ይላሉ።"
(ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

👉 ኢብኑ በጣል(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "እጅግ ብዙ ወንጀል ያለበት ያለ ብዙ ልፋት ወንጀሉን አላህ እንዲያራግፍለት የሚፈልግ ሰው ካለ፦ መላኢካዎች እርሱ ላይ የሚያደርጉት ዱዓ እና ኢስቲግፋር ይበዛለት ዘንድ ሶላት ከሰገደ ቡኋላ መስገጃው ላይ በመፅናት እድሉን ይጠቀሙ።
* ዕለተ ጁሙዓ - ሸዕባን 1443 ዓ.ሂ ላይ ደርሰናል፡፡
* ለታላቁና ተወዳጁ ረመዷን 30 ወይም 29 ቀን ቀረው፡፡

* ሸዕባን - ከረመዷን ቀጥሎ ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.) በብዛት የፆሙት ወር ነበር፡፡

* ወሩ የዓመት ሥራዎቻችን አላህ ዘንድ የሚቀርቡበት ወር ነው፡፡

* ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ.)"ለምን እንደሚፆሙት ተጠይቀው በረመዷን እና በረጀብ መካከል ስለሚገኝ ብዙዎች ይዘናጉበታል፣ ፆመኛ ሆኜ ሥራዬ አላህ ዘንድ ቢቀርብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

* ሸዕባን መፆም ለረመዷን ፆም መዘጋጃና አካልንና መንፈስንም ማለማመድ ነው፡፡

* ሸዕባን ላይ ረመዷን በእጅጉ ይናፍቃል፣ ወሬው ሁሉ ስለ ረመዷን ይሆናል፡፡

* አላህ ሆይ ሸዕባንን ባርክልን ለረመዷን በሰላም አድርሰን፡፡
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል ዘጠኝ


አምስተኛው፡ - ሰለፎቹ ባወቁት ለመስራት ተሸቀዳዳሚ ነበሩ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➲ይህን ደረጃ ከሚያብራሩ ነጥቦች መካከል፡ የሰለፎች አስደናቂ ባህሪያቸው ነው፡፡ሰለፎቹ ተግባርን በቋሚነት ለመፈጸም ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡ ከረሡል صلى الله عليه وسلم የሰሙትን ፈጥነው ለመተግባር ይቸኩሉ ነበር፡፡

➭በዚህ ትርጉም ላይ ሰለፎቹ ምን ያክል ባወቁት ለመተግበር ፍላጎቱ እንደነበራቸው ብርቱ ትኩረት እንደሚሰጡ የሚገልጹ በርካታ መረጃዎች መጠዋል፡፡ከዚህ መካከል ቡኻሪና ሙስሊም ላይ ተዘግቦ የሚገኘው ሐዲስ ነው፡፡ የረሡል صلى الله عليه وسلم ልጅ ፋጢማ ረድየላህ አንሃ አገልጋይ ፈልጋ ለአላህ መልእከተኛ ጥያቄ አቀረበች፡፡

▪️የአላህ መልክተኛም صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምላሽ ሰጧት፡- “ለአንች ከአገልጋይ የተሻለውን ልጠቁምሽ?” አሏት፡፡ (ለመተኛት) ወደፍራሽ በተጠጋሽ ጊዜ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ሱብሃን አሏህ ፣ አልሀምዱ ሊላህ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ፤ አሏሁ አክበር ሰላሳ ሶስት ጊዜ በይ” አሏት፡፡ ባለቤቷ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"فما تركتها منذ سمعتها من رسول الله صلى الله عليه وسلم"

“ከረሡል ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቸው አላውቅም” ከመካከላቸው አንዱ “አስቸጋሪ ሌሊት ላይ እንኳ ቢሆን? - ማለትም ሰው በሚዘነጋበት ሰኣት ላይ እንኳ ቢሆን? - ይህን ዚክር ረስቶት አያውቅም?” ፤ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን?!” - ይህ ሌሊት የታወቀ ጦርነት ነው - የሚል ጥያቄ ተጠየቀ፡፡ “በሲፊን ሌሊት እንኳ ቢሆን” በማለት ምላሽ ሰጧል፡፡ ቡኻሪ፡ 5362 ሙስሊም፡2727

➧ዓንበሳህ ብን አቢ ሱፍያን -ረሂመሁሏህ- በሞተበት በሽታ ላይ ሆኖ ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሰማሁ ብላ የሚከተለውን ሐዲስ ነገረችኝ ብሎ ለእኔ አስተላልፎልኛል ይላል ዓምር ብን አውስ፡፡

"من صلى اثنتيني عشرة ركعة في يوم وليلة بني له بهن بيت في الجنة"

▪️“አስራ ሁለት ረከዓዎችን በሌሊትና በቀን የሰገደ ሰው በእነርሱ አማካኝነት በጀነት ቤት ይገነባለታል፡፡” ኡሙ ሀቢባ ረድየላህ አንሃ የሚከተለውን ተናግራለች ፡-
"فما تركتهن منذ سمعتهن من رسول الله"

➧“ከረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰማሁ ጀምሬ (እነዚህን አስራ ሁለት ረከዓዎች) ትቻቸው አላውቅም” አንበሳህ ደግሞ በተመሳሳይ “ከኡሙ ሀቢባ ከሰማሁ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም”ይላል፡፡ ዓምር ብን አውስ ደግሞ “ከአንበሳህ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል፡፡ ኑዕማን ብን ሳሊም ደግሞ “ከዓምር ብን አውስ ከሰማሁበት ጊዜ ጀምሮ ትቻቸው አላውቅም” ይላል፡፡ ሙስሊም፡728

➠ይህ ፍጥነትን እና በቋሚነት መፈጸምን ያጣመረ ታላቅ ወኔ ነው፡፡ ለስራ መፍጠን ፣ቋሚ ደምበኛ ለመሆን መሽቀዳደም፡፡

▪️ቡኻሪ በዘገቡት ሐዲስ አቡሁረይራ ረዲየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"أوصاني خليلي بثلاث لا أدعهن حتى أموت: صوم ثلاث أيام من كل شهر ، وصالة الضحى ، ونوم على وتر"

➲“ወዳጀ እስከምሞት ድረስ የማልተዋቸው በሆኑ ሶስት ነገሮች አደራ አለኝ፡፡ ከየወሩ ሶስትቀናቶችን (እንድጾም) ፣ የዱሃ ሶላት (እንድሰግድ) ፤ ዊትር ሰግጀ እንድተኛ” ቡኻሪ፡1178



ኢንሻአላህ ይቀጥላል



➭ጥሩ ፀሀፊ ባትሆን ጥሩ አንባቢ ሁን ትጠቀማለህ
➲ከተውሂድ አርማዎች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሁለት
➻➻➻➻➻➻

የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች


➧ተውሒድ፡ ከፍተኛ ደረጃና ቦታ የሚሰጠው መሆኑን የሚጠቁሙ በርካታ መለያ ባህሪያትና ትሩፋቶች እንዳሉት እወቅ፡፡ ከእነርሱ መካከል አስሩን እንደሚከተለው እጠቁምሃለሁ፡፡

➲አንደኛ፡- የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደሚጠቁመው እኛ የተፈጠርንበት እና
የተገኘንበት ዋና ዓላማ ለተውሒድና ተውሒድን ለማረጋገጥ ብቻ ነው፡፡


▪️وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

“ጅንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ (ዓላማ) አልፈጠርኳቸውም፡፡” አዝ ዛሪያት፡56

➧“ኢልላ ሊየዕቡዱን” ፡ የሚለው የቁርኣን ቃል ትርጉም “እኔን (በአምልኮት) ብቸኛ ሊያደርጉኝ” ማለት ነው፡፡ በዚህ ዓለም የተፈጠርንበት ዋና ዓላማ ለቀልድና ለጨዋታ ሳይሆን ለተውሒድ ሲባል ነው፡፡

➭አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ልቅ አድርጎ
ሊተወን ሳይሆን እርሱን በብቸኛነት ልንገዛው ፈጠረን ፤ እርሱን በአምልኮ ብቸኛ ልናደርግ አስገኘን፡፡ የተውሒድ ሁኔታ ላቅ ያለ ለመሆኑ ከማስረጃ በኩል በዚህ ይብቃ፡፡

➲ሁለተኛ፡- ተውሒድ የነብያቶችና የሩሡሎች ጥሪ መሽከርከሪያ ምህዋር ነው፡፡ አላህ የላከው ማንኛውም ነብይ የጥሪው ትኩረትና መቆሚያ መሰረቱ ተውሒድ ነው፡፡ ለዚህም በርካታ ማስረጃዎች አሉ፡፡

▪️አላህ በተከበሩት ቁርኣናዊ አንቀጾች የሚከተለውን ተናግሯል፡

وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِي كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطَّاغُوتَ ۖ

➧“በየሕዝቡም ሁሉ ውስጥ “አላህን ተገዙ ፤ ጣዖትንም ራቁ” በማለት መልክተኛን በእርግጥ ልከናል፡፡” አን ነሕል (36)

▪️وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

➧“ከአንተ በፊትም እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና ተገዙኝ በማለት ወደርሱ የምናወርድለት ቢሆን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡” አል አንቢያእ፡(25)

▪️وَاسْأَلْ مَنْ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رُّسُلِنَا أَجَعَلْنَا مِن دُونِ الرَّحْمَٰنِ آلِهَةً يُعْبَدُونَ

➧“ከመልክተኞቻችንም ካንተ በፊት የላክናቸውን (ተከታዮቻቸውን) ከአልረህማን ሌላ የሚገዟቸው የሆኑን አማልክት አድርገን እንደሆነ ጠይቃቸው፡፡” አዝ ዙኽሩፍ (45)

۞ وَاذْكُرْ أَخَا عَادٍ إِذْ أَنذَرَ قَوْمَهُ بِالْأَحْقَافِ وَقَدْ خَلَتِ النُّذُرُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا اللَّهَ إِنِّي أَخَافُ عَلَيْكُمْ عَذَابَ يَوْمٍ عَظِيمٍ

“የዓድንም ወንድም (ሁድን) ሕዝቦቹን በአሕቃፍ ባስጠነቀቀ ጊዜ አውሳላቸው፡፡ በስተፊቱና በስተኋላውም ብዙ አስፈራሪዎች በእርግጥ አልፈዋል፡፡ “ከአላህ በስተቀር አትግገዙ ፣ እኔ በእናንተ ላይ የከባድ ቀንን ቅጣት እፈራላችኋለሁና” በማለት (ባስጠነቀቀ ጊዜ)፡፡ አል አህቃፍ፡21

➲“ኑዙር” ማለት መልክተኞች ማለት ነው፡፡ ከዚህ በፊት የነበሩትም ይሁን ወደኋላ የመጡት መልክተኞች “ከአላህ በቀር አትግገዙ” በሚለው አላማ ላይ አንድ ሆነዋል፡፡

➧ተውሒድ ፡ የነብያቶች እና የሩሡሎች ጥሪ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቦቻቸው ከመልእክተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያደምጡት ቃል የተውሒድን ቃል ነው፡፡ ወደአላህ ጥሪ ሲያደርጉ አንድ ብለው የሚጀምሩት በተውሒድ ነው፡፡



ኢንሻአላህ ይቀጥላል

🖊🖊🖊Nurahemd

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚

🍁ረመዳን ሽህሩን ሙባረክ🍁
==================

★ የረመዳን ወር የትኩረት አቅጣጫዎች★

① ልቦናዎች የሚደብቁትን ሁሉ የሚያየውና የሚያውቀው አላህ ሱ,ወ የኢማናችንን ጥንካሬ በዚህ ፆም ሊፈትነን እንደፈለገ በመገንዘብ ከፋተኛ ትኩረት
መስጠት።
② ረመዳንን ስንፆም በኒያ (አስበንና ወስነን) መሆን አለበት ምክንያቱም ማንኛውም ኢባዳ ያለኒያ ስለማይሆን።
③ ቀኑን በሙሉ በመኝታ ከማሳለፍ መቆጠብ ምክንያቱም ረመዳን የኢባዳ ወር ነው ስለሆነም የቻልነውን ያክል በኢባዳ መበርታት አለብን።
④ቁርአንን ጀሌላው ጊዜ በተሻለ መቅራት አለብን ረመዳን የቁርአን ወር ነው ቁርአን የወረደውም በረመዳን ወር ነው።
⑤ከፈጣሪያችን ከአላህ ጋር ተውባ በማድ ረግ (በመፀፀት) ወደሱ ልንመለስና ልናስደስተው ይገባል።

⑥የረመዳን ሌሊቶችን በመይጠቅሙ ነገሮች ከማሳለፍ መቆጠብ ።
⑦ በረመዳን ወር ዱአ ማድረግና ወደ አላህ መተናነስን ማብዛት።
⑧ አምስት ወቅት ሰላቶችን በጀመአ መሰጊድ መስገድ።
⑨ ምግብን ደግሞ የቀኑን ለማካ ካስ የሚበቃ ያክል አብዝቶ አለመብላት።
【¹⁰】 ሙሉ አካላችንን ከአላህ ትእዛዝ መስጠት ወይም መገዛት አለብን።

በተያያዥ ነጥቦች ላይ ክፍል 3 ይቀጥላል ኢንሻ አላህ።

ኑር አህመድ ሙሀመድ
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሆነ ሰውየ መስጅድ ገባ ሊሰግድ. ከዛ አሰጋጁ. የት ነህ አይተንህ አናቅም አለው ላድሱ ሰውየ አሁን በቅርብ ነው ከዚህ ከገሌ ቤት ቀጥሎ ያለዉን ቤት ገዝቼ ነዉ አለዉ . የገባሁት. አለው. ኢማሙ. ( አሰጋጁ ). ለሰውየው አላህ. ይሁንህ. አለው. ሰውየው ምን ነው ሲለው ከጎንህ ያለው ጎረቤትክ. አላህን አይፈራም አይሰግድም. አደዛዥ እፅ የሚጠቀም ሰካራም ነዉ አለው.
ሰዉየዉ ለምን ቀድማቹሁ አልነገራቹሁኝም አለዉ ይሄ እጣህ ነዉ ያዝ አለዉ ከመስጅድ ወጣ ሲል ሌላኛዉ ሰዉ ጠየቀዉ የእገሌን ቤት ገዝቼ ነዉ ሲለዉ አሏህ ይዘንልህ ጎረቤትህ አስቸጋሪ ነዉ ብሎ ልክ ኢማሙ ያለዉን አለዉ አሱርን ሶላት ከመስጅድ ሰግዶ ሲወጣ ጎረቤቱን ከቤቱ በር ቁጭ ብሎ ይመለከተዋል ልክ እንዳየዉ በፈገግታ አሰላሙአለይኩም ወረህመቱሏሂ ወበረካቱሁ ብሎ ሰላምታ ካቀረበ ቡኋላ ጎረቤቶችህ ይወዱኋል ያወዱሱሀል ብሎ ነገረዉ ከዚያ ላትመለሰኝ አደራ ብሎ ከቤቴ ራት ልጋብዝህ ብሎ ጋበዘዉ ከቤቱ ሲመጣ ማንም የለም እሱ ብቻ ነዉ ከእኔ ዉጭ ሌላ አልጋበዝክም ሲለዉ ይሄ ራት ግብዣ ላንተ ነዉ አንተን ለማክረም ከዚያ ራት ግብዣዉ ካለቀ ቡኋላ ዉድ ስጦታ ሰጠዉ
. . ከዚያ አደዛዥ እፅ የሚጠቀመዉ የማይሰግድ የነበረ ሰዉ ሶላተል ፈጅር በጀመዓ ሰገደ . ኢማሙ ተገረመ. ምን አድርግለት ምን ብለኽው ነው አለው. በመልካም ንግግር ብቻ ነው ያናገርኩት ሌላምን አላዴረኩለትም አለው

እናም. ሰዎችን በሂክማ መጣራት እዳለብን. ነው. የሚያስተምረው. ወላሁ አእለም።
👇👇👇👇
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from Deleted Account
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጧት ዚክር
➱➱➱➱➱➱

وَاذْكُرِ اسْمَ رَبِّكَ بُكْرَةً وَأَصِيلًا

የጌታህን ስም በጧትና በማታ አውሳ!!

https://t.me/httpsnurutewhide
La tehzen
➲ከተውሂድ አርማዎች ➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሁለት ➻➻➻➻➻➻ የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➧ተውሒድ፡ ከፍተኛ ደረጃና ቦታ የሚሰጠው መሆኑን የሚጠቁሙ በርካታ መለያ ባህሪያትና ትሩፋቶች እንዳሉት እወቅ፡፡ ከእነርሱ መካከል አስሩን እንደሚከተለው እጠቁምሃለሁ፡፡ ➲አንደኛ፡- የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደሚጠቁመው እኛ የተፈጠርንበት እና የተገኘንበት ዋና…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል ሶስት
➻➻➻➻➻➻

➲የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች


➧ተውሂድ ፦ የነብያቶች እና የሩሡሎች ጥሪ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቦቻቸው ከመልእክተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያደምጡት ቃል የተውሒድን ቃል ነው፡፡ ወደአላህ ጥሪ ሲያደርጉ አንድ ብለው የሚጀምሩት በተውሒድ ነው፡፡ ምክንያቱም የኢስላም እምነት በእርሱ ላይ ነው የሚመሰረተው፡፡ የእምነቱ ምሳሌ ልክ እንደዛፍ ነው፡፡

➭ዛፍ መሰረትና ቅርንጫፎች እንዳሉት ይታወቃል፡፡ በመሰረቱ ላይ ካልሆነ በቀር ዛፉ ቀጥ ብሎ ሊቆም አይችልም፡፡ ዲኑም በመሰረቱ ላይ ካልሆነ ቀጥ ብሎ ሊቆም አይችልም፡፡ የዲን መሰረቱ ደግሞ ተውሒድ ነው፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፦

▪️ألَمْ تَرَ كَيْفَ ضَرَبَ اللَّهُ مَثَلًا كَلِمَةً طَيِّبَةً كَشَجَرَةٍ طَيِّبَةٍ أَصْلُهَا ثَابِتٌ وَفَرْعُهَا فِي السَّمَاءِ
➧“አላህ መልካምን ቃል ስሯ (በምድር ውስጥ) የተደላደለች ቅርንጫፏም ወደ ሰማይ (የረዘመች) እንደሆነች መልካም ዛፍ አድርጎ ምሳሌን እንዴት እንደገለጸ
አላየኽምን?” ኢብራሒም፡24

➲ዛፍ ስሩ ሲቆረጥ እንደሚሞተው ሁሉ ፣ ዲንም በተውሒድ ላይ ካልቆመ ህይዎት አይኖረውም፡፡ ሰዎችም በእርሱ ተጠቃሚ ሊሆኑ አይችሉም፡፡ ተውሒድ በዲኑ ውስጥ ያለው ቦታ ልክ የዛፉ ስር ለዛፉ መቆሚያ ፣ የቤት መሰረቱ ደግሞ ለህንጻው መቆሚያ እንደሚያገለግለው ማለት ነው፡፡

ተውሒድ፡ የነብያቶችና የሩሡሎች ጥሪ ዋናው መሽከርከሪያ ፣ የመልእክታቸው ትኩረት እንደሆነ ከሚጠቁሙ መረጃዎች መካከል የሚከተለው የነብዩ صلى الله عليه وسلم ትክክለኛሐዲስ ይገኛል፡-

▪️"ألأنبياء إخوة من عالت ، وأمهاتهم شتى ، ودينهم واحد"

➧“ነብያቶች ከአንድ አባት ፣ ከተለያዩ እናቶች የሆኑ ወንድማማቾች ናቸው፡፡ዲናቸው አንድ ነው፡፡” ሙስሊም 2365

➠በአባት አንድ ናቸው ማለት በተውሒድ አንድ ናቸው ፣ ሁሉም በተመሳሳይ ወደአላህ ተውሒድ ነው ጥሪ የሚያደርጉት ማለት ነው፡፡ እናቶቻቸው የተለያዩ ናቸው ማለት ደግሞ ህግና መመሪያቸው የተለያዩ ናቸው ማለት ነው፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️ لِكُلٍّ جَعَلْنَا مِنكُمْ شِرْعَةً وَمِنْهَاجًا ۚ

“ከእናንተ ለሁሉም ህግንና መንገድን አደረግን፡፡” አል ማኢዳህ፡48

➲ሶስተኛ፡- ተውሒድ ለአካለ መጠን በደረሱ ሰዎች ላይ የመጀመሪያው ግዴታ መሆኑ ነው፡፡ ወደዚህ እምነት ለመግባት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው መጀመሪያ ግዴታ የሚሆንበት ተውሒድ ነው፡፡ወደአላህ ጥሪ ማድረግ የፈለገ ማንኛውም ሰው ጥሪው የሚጀምረው በተውሒድ ነው፡፡

ይህን የሚጠቁሙ በርካታ መረጃዎች አሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል የሚከተለው የረሡል صلى الله عليه وسلم ሐዲስ ይገኝበታል፡-

▪️"أمرت أن أقاتل الناس حتى يشهدوا أن لا إله إلا الله"
“ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም ብለው እስኪመሰክሩ ድረስ ሰዎችን ልጋደል ታዝዣለሁ፡፡” ቡኻሪ፡25 ሙስሊም፡22

▪️ሌላው መረጃ ሙዓዝ ረድየላህ አንሁ ወደየመን ሲላክ ረሡል صلى الله عليه وسلم ያስተላለፉት መልእክት ነው፡፡

▪️إنك تقدم على قوم أهل كتاب ، فليكن أول ما تدعوهم إليه عبادة الله" الحديث

➲“ወደመጽሐፍ ባለቤቶች ትሄዳለህ፡፡ የመጀመሪያው ጥሪህ የአላህ ዒባዳ (አምልኮ) ይሁን፡፡” ቡኻሪ፡ 1458 ሙስሊም፡19 በሌላ ዘገባ፡-

▪️"إنك تقدم على قوم من أهل الكتاب ، فليكن أول ما تدعوهم إلى أن يوحدوا هللا تعالى"

➧“ወደመጽሐፍ ባለቤቶች ትሄዳለህ፡፡ የመጀመሪያው ጥሪህ አላህን (በአምልኮ) ብቸኛ እንዲያደርጉ ይሁን፡፡” ቡኻሪ፡7373 በሌላ ዘገባ፡-
▪️"إنك ستأتي قوما أهل الكتاب ، فإذا جئتهم ، فادعهم إلى أن يشهدوا أن لا إله إلا الله ، وأن محمدا رسول الله"

“ወደመጽሐፍ ባለቤቶች ትሄዳለህ ፤ያገኘሀቸው ጊዜ ከአላሀ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑን ፤ሙሀመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን እንዲመሰክሩ ጥሪ አድርግላቸው፡፡” ቡኻሪ፡ 1496 ሙስሊም፡19



ኢንሻአላህ ይቀጥላል


【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚
La tehzen
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል ዘጠኝ አምስተኛው፡ - ሰለፎቹ ባወቁት ለመስራት ተሸቀዳዳሚ ነበሩ ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➲ይህን ደረጃ ከሚያብራሩ ነጥቦች መካከል፡ የሰለፎች አስደናቂ ባህሪያቸው ነው፡፡ሰለፎቹ ተግባርን በቋሚነት ለመፈጸም ይሽቀዳደሙ ነበር፡፡ ከረሡል صلى الله عليه وسلم የሰሙትን ፈጥነው ለመተግባር ይቸኩሉ ነበር፡፡…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➛ክፍል አስር
➭➭➭➭➭➭➭

➧ረሡል የዚህ ተመሳሳይ ለአቡደርዳእ አደራ እንዳሉት እንደሚከተለው ግልጽ አድርጓል፡-“ወዳጀ እስካለሁ ድረስ እንዳልተዋቸው በሶስት ነገሮች አደራ ብሎኛል” ከዚያም ከላይ የተዘረዘሩ ሶስት ነገሮችን አወሳ፡፡ ሙስሊም፡722

➠እድሜው አነስተኛ የሆነው ዑመር ብን አቢ ሰለማህ ረድየላህ አንሁ የዚህ ተመሳሳይ ተናግሯል፡- “ረሡል ተንከባክበው የሚያሳድጉኝ ትንሽ ልጅ ነበርኩ፡፡ እጀ በየማዕዱ ከዚያም ከዚህም ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምክር መከሩኝ፡፡

▪️"يا غلام! سم الله، وكل بيمينك، وكل مما يليك"
“አንተ ልጅ ሆይ! ቢስሚላህ ብለህ ብላ ፣ በቀኝህ እጅህ ብላ ፣ የፊት የፊትህን ብላ፡፡”

ቡኻሪ ደግሞ የሚከተለውን ጨምረዋል፡-

"فما زالت تلك طعمتي بعد"

“ከዚያ በኋላ አመጋገቤ (እንደመከሩኝ) ከመሆን አልተወገደም” ቡኻሪ፡5376 ሙስሊም፡2022 በህጻንነቴ ይህን ምክር ከመከሩኝ ጀምሮ ማለቱ ነው፡፡

➧ልጆች በተደጋጋሚ - አንድ ጊዜ ፣ ሁለት ጊዜ ፣ ሶስት ጊዜ - ሲምመከሩ ምክርን አይቀበሉም፡፡ ይህ ትንሽ ሶሃባ ግን በአንድ ጊዜ የተመከረውን ምክር ተቀብሎ የሚከተለውን ንግግር መናገሩን አስተውል! “ከዚያ በኋላ አመጋገቤ (እንደመከሩኝ) ከመሆን አልተወገደም”

➲ይህ ፣ ሰለፎቹ በአንድ በኩል ምን ያክል ለመልካም ነገር እንደሚሽቀዳደሙ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ እስከሚሞቱ በአንድ መልካም ስራ ላይ እንዴት እንደሚዘወትሩ ያስረዳል፡፡ የደጋግ ሰለፎችን ታሪክ ብናጠና በዚህ ትርጉም ላይ በርከታ ታሪኮችን ማቅረብ እንችላለን፡፡

▪️ለምሳሌ፡- የሱፍያን አስ'ሰውርይን -ረሂመሁሏህ- ንግግር እንከታተል፡-

▪️"ما بلغني حديث عن رسول الله – صلى الله عليه وسلم – إلا عملت به"

➧“ከረሡል صلى الله عليه وسلم አንድም ሐዲስ አይደርሰኝም በእርሱ የምሰራበት ቢሆን እንጅ፡፡”ዓምር ብን ቀይስ አልመላዒይ - ረሂመሁሏህ - ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️"إذا بلغك الحديث عن رسول الله – صلى الله عليه وسلم – فاعمل به ولو مرة تكن أهله"
“የረሡል ሐዲስ ከደረሰህ አንድ ጊዜ እንኳ ቢሆን በእርሱ ስራ ፣ ከ (ሱና) ባለቤቶች ትሆናለህና፡፡”

➲“አንድ ጊዜ እንኳ ቢሆን በእርሱ ስራ” ማለት ሱናዎችን በተመለከተ ነው፡፡ ፈርድና ዋጅቦችን ግን አንድ ጊዜ መስራቱ ከ (ሱና) ባለቤቶቹ አያደርገውም፡፡

➧ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን የአቢ ኡማማህ ሐዲስ
እንደሚከተለው አስተላልፈዋል፡-

"من قرأ آية الكرسي دبر كل صالة مكتوبة لم يكن بينه وبين الجنة إلا أن يموت"

“ከሶላት በኋላ አየተል ኩርስይ የቀራ ሰው ሞት እንጅ በእርሱ እና በጀነት መካከል ምንም (የሚጋርደው) የለም፡፡” ነሳኢይ ፈልዓመሊ አል የውሚ ወለይላ፡ 100 ሐዲሱን አልባኒ ሶሂህ ብለውታል ሲልሲለቱ አል ሐዲስ አስ ሶሂህ፡972

▪️“ሸይኹል ኢስላም - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን እንደተናገረ ደረሰኝ ይላል የእርሱ ደረሳ የሆነው ኢብን አልቀይም - ረሂመሁሏህ -
"ما تركتها عقيب كل صالة"

“(አየተል ኩርስይን) ከየሶላቱ መጨረሻ አንድም ትቻት አላውቅም፡፡” ዛዱ አል ማኣድ፡ 1/ 285 ከኢማም አህመድ - ረሂመሁሏህ - ደግሞ የሚከተለው ተወርቷል፡-
"ما كتبت حديثا إلا عملت به"

“አንድም ሐዲስ አልጽፍም የምሰራበት ቢሆን እንጅ፡፡” ከዚያም የሚከተለውን ተናገሩ፡-
▪️"حتى إنني سمعت أن النبي صلى الله عليه وسلم احتجم وأعطى الحاجم دينارا فاحتجمت وأعطيت الحاجم دينارا"

➭“ነብዩ صلى الله عليه وسلم ዋግምት ታግመው ላገማቸው አካል አንድ ዲናር መስጠታቸውን ስሰማ ፣እኔም ዋግምት ታገምኩና ለአጋሚው አንድ ዲናር ሰጥቻለሁ፡፡

➲ይህ ነው እንግዲህ ሰለፎች ለመልካም የነበራቸው ጉጉት ፤ በአንድ መልካም ስራ
ላይ የነበራቸው መዘውተር፡፡ አንድን እውቀት ፈጥነው ወደተግባር ይቀይሩታል፡፡ ከዚያም ቋሚ ደንበኛ ይሆናሉ፡፡


➛ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚
La tehzen
➲ከተውሂድ አርማዎች ➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል ሶስት ➻➻➻➻➻➻ ➲የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➧ተውሂድ ፦ የነብያቶች እና የሩሡሎች ጥሪ መሰረት ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ህዝቦቻቸው ከመልእክተኞች ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያደምጡት ቃል የተውሒድን ቃል ነው፡፡ ወደአላህ ጥሪ ሲያደርጉ አንድ ብለው የሚጀምሩት በተውሒድ ነው፡፡ ምክንያቱም የኢስላም እምነት በእርሱ ላይ…
➧ከተውሂድ አርማዎች
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➻ክፍል አራት
➫➫➫➫➫

➲የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች
➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻

➧ተውሒድ፡ ለአካለ መጠን በደረሱ ሰዎች ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ነው፡፡ ሰዎች ወደዚህ ዲን መጀመሪያ የሚገቡት በእርሱ ነው፡፡ የዲኑ መሰረት ተውሒድ ነው ፤ ዲኑ በእርሱ ላይ ይቆማል ፤ በእርሱም ላይ ይጀመራል።

➲አራተኛው፡- ሰላም ለማግኘትም ይሁን በሁለቱ አገር ወደቅኑ ጎዳና ለመመራት
ምክንያቱ ተውሒድ ነው፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

▪️الَّذِينَ آمَنُوا وَلَمْ يَلْبِسُوا إِيمَانَهُم بِظُلْمٍ أُولَٰئِكَ لَهُمُ الْأَمْنُ وَهُم مُّهْتَدُونَ

“እነዚያ ያመኑና እምነታቸውን በበደል ያልቀላቀሉ እነዚያ ለእነርሱ ጸጥታ አላቸው፡፡ እነሱም የተመሩ ናቸው፡፡” አል አንዓም፡82

➠ጸጥታ ወይም ሰላም በአላህ እጅ ነው፡፡አላህ - ሱብሃነሁ ወተዓላ - ዲኑን ፍጹም ለእርሱ ብቻ ለሚያጠሩ የተውሒድ ሰዎች እንጅ ጸጥታን ለማንም አይሰጥም፡፡ከዚህ በላይ የጠቀስነው የቁርኣን አንቀጽ በወረደ ጊዜ ሶሃቦች -ረዲየሏሁ ዓንሁም-በጣም ተጨነቁ፡፡ ወደረሡል صلى الله عليه وسلم በመምጣት የሚከተለውን ጥያቄ አቀረቡ፡-
▪️"يا رسول الله ! أينا لم يظلم نفسه؟"

“የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማንኛችን ነን ነፍሳችንን የማንበድለው?”ይህ ማለት “ከእኛ መካከል አንድም ሰው አይኖርም ፤ ነፍሱን የሚበድል ቢሆን እንጅ” ማለታቸው ነው፡፡ ወይም “እያንዳንዳችን ነፍሳችንን እንበድላለን በመሆኑም ከጸጥታም ይሁን ከመመራትምንም አይነት ድርሻ አይኖረንም” ማለታቸው ነው፡፡
➲ከዚያም ነብዩ صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ምላሽ ሰጡ፡-
"ليس ذاك"
➧“ነገሩ እንደዚያ (እናንተ እንደተገነዘባችሁት) አይደለም”

“በቁርኣን አንቀጹ ላይ የተጠቀሰው በደል ፣ እናንተ የተገነዘባችሁት ዓይነት በደል
አይደለም፡፡” “የዚያ ጥበበኛና ደግ የሆነው ባሪያ - ሉቅማን - የተናገረውን ንግግር አላነበባችሁምን?” አሏቸው፡፡

▪️إِنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ

➲ማጋራት ታላቅ በደል ነውና” ያለውን (አስታውስ)” (ሉቅማን፡ 13)

➧በዚህ አንቀጽ የሚገኘውን “ዙልም” ሽርክ ወይም ማጋራት በሚለው የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم ተርጉመውታል፡፡ ቡኻሪ፡6937

ይህ የቁርኣን አንቀጽ ምንም ሳያጋራ በአላህ ያመነ ሰው በሁለቱም አገር ጸጥታና መመራት እንዳለው ይጠቁመናል፡፡ የተውሒድ ሰው ከሆነ በሁለቱም አገር አላህ ጸጥታን እና መመራትን ይሰጠዋል፡፡ ይህ ደግሞ የተውሒድ ልዩ ገጽታው ነው፡፡

➲አምስተኛው፡- በሌሎች እምነቶች ተቃራኒ እርስ በርስ ከመጋጨትና ከመዋዥቅ ነጻ የሆነ እምነት ነው፡፡
➲ለዚህ ማስረጃው የሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ ነው፡

▪️وَلَوْ كَانَ مِنْ عِندِ غَيْرِ اللَّهِ لَوَجَدُوا فِيهِ اخْتِلَافًا كَثِيرًا
“ከአላህ ሌላ ዘንድ በነበረ ኖሮ በርሱ ውስጥ ብዙን መለያየት ባገኙ ነበር፡፡” አን ኒሳእ፡82

➲ሰዎች በሚፈጥሯቸው እምነቶች ውስጥ በአብዛኛው እርስ በርስ የሚጣረሱና የሚምታቱ ነገሮች ይገኙበታል፡፡ከአላህ ኪታብና ከረሡል صلى الله عليه وسلم ሱና የመነጨ ትክክለኛና ጥልቅ የሆነ እምነት ፣ ሰላማዊ የሆነ ዓቂዳ ከሆነ ግን ከዚህ ሁሉ ነጻ ነው፡፡




ኢንሻአላህ ይቀጥላል
🖊🖊ኑርአህሠድ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
🍁ረመዳን ሽህሩን ሙባረክ🍁② ================== ★ የረመዳን ወር የትኩረት አቅጣጫዎች★ ① ልቦናዎች የሚደብቁትን ሁሉ የሚያየውና የሚያውቀው አላህ ሱ,ወ የኢማናችንን ጥንካሬ በዚህ ፆም ሊፈትነን እንደፈለገ በመገንዘብ ከፋተኛ ትኩረት መስጠት። ② ረመዳንን ስንፆም በኒያ (አስበንና ወስነን) መሆን አለበት ምክንያቱም ማንኛውም ኢባዳ ያለኒያ ስለማይሆን። ③ ቀኑን በሙሉ በመኝታ ከማሳለፍ…
🍁ረመዳን ሸህሩን ሙባረክ🍁

★ የረመዳን ወር አቀባበል★

ታላቁ እንግዳችን የተከበረው የረመዳን ወር ለመቀበል ሁሉም በየፊናው ተፍተፍ እያለ ይገኛል።
ከፊሉ ቤቱን በማፅዳት ፣ሌላው የምግብ አይነቶችን በመሸመት፣ ሌላው ደግሞ ይሩን ትሩፋት ለመጠቀም እቅድ እያወጣ… እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
ለመሆኑ ይህ አያሌ የፈጣሪ ትሩፋትን በውስጡ ይዞ የመጣውን ይህን ወር ለመቀበል ትክክለኛው መንገድ የትኛው ነው?
በወሩ ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን የኢባዳ ወቅቶችን ሁሉ አሟጦ ለመጠቀም ምን ማድረግ ይጠበቅብናል? በነዚ በተከበሩ ጊዜያት ውስጥ በኸይር ነገሮች መሽቀዳደም ያስፈልጋል አላህ እንዲህ ይላል፦"وفي ذلك فليتنافس المتنافسون"

"በዚህም ተሽቀዳዳሚዎች ይሽቀዳደሙ"
በመሆኑም ከዚ በመቀጠል 💦የረመዳንን ወር በተሻለ መንገድ ለመቀበል የሚረዱ ነገሮችን በተወሰነ እናያለን።
1, ዱዓ መዱረግ፦ በፆም በሰላትና በዚክር ላይ እንድንጠነክር አላህ በሙሉ ጤንነትና አቅም ላይ ሆነህ ረመዳንን ወር እንዲያደርስህ ከአሁኑ ዱአ አድርግ አነስ ኢብን ማሊክ ረ,ዐ ነብያችን ሰ,ዐ,ወ የረጀብ ወር ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር ብለዋል "اللهم بارك لنا في رجب وشعبان وبلغنا رمضان"

"አለህ ሆይ ረጀብንና ሻእባንን ባርክልን ረመዳንን አድርሰን"

2,ምስጋና ማቅረብ በረመዳን ወር ከደረስክ ምስጋና አቅርብ ኢማሙ ነወዊይ አል አዝካር በሚለው ኪታባቸው ላይ እንዲ ብለዋል"አንድ አዲስ ፀጋን ያገኘ ወይም አንድ ችግር የተወገደለት ሰው ለአላህ ምስጋና ለማቅረብ ሱጁድ አድርጎ በሚገባው መልኩ ማወደስ ይገባዋል"
3, መደሰት፦ነብያችን ሰ,ዐ,ወ የረመዳን ወር ሲመጣ እንዲህ በማለት ሶሀቦችን ያበስሩ ነበር"جاءكم شهر رمضان مبارك كتب عليكم صيامه فيه تفتح ابواب الجنان وتغلق فيه ابواب الجحيم"

"የተባረከ የረመዳን ወር መጥቶላችሇል እሱን መፆም አላህ በናንተ ላይ ደንግጓል በረመዳን ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ"

4, ንሰሀ መግባት፦የረመዳንን ወር ከወንጀል ሁሉ ለመራቅና ለመፅዳት ወደ ወንጀል ላከመመለስ መወሰንና እውነተኛ ተውበት ማድረግ ና ወደአላህ ለመመለስ ቆርጠን ልንነሳ ይገባናል።

5,ሰለረመዳን መማር፦ሙእሚን አላህን መገዛት ያለበት በእውቀት ላይ ተመስርቶ ነው።አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረጋቸውን ነገሮችና አፈፃፀሙን አለማወቅ ማንኛውንም ሙስሊም ይቅርታ ሊደረግለት የማይችል ጉዳይ ነው። አላህ እንዲ ይላል"فاسائلو اهل الذكر ان كنتم لا تعلمون"
"የማታውቁ ከሆናችሁ የሚያውቁትን ጠይቁ"

ወላሁ ተዐላ አዕለም ።

https://t.me/httpsLatahzen

ኑርአህመድ ሙሀመድ 🖊🖊
#እናት

በሁሉም ጭንቅላት በሁሉም ልቦና
በየአንዳንዱ አእምሮ በየአንዳንዱ ህሊና
አንዲት እንስት አለች አንዲት የሴት ጀግና

እናት
በትንሽ ወረቀት በሰለለ ቡእር
ስለናት በስንኝ ለመጻፍ ስሞክር
ንቀት መስሎ ታየኝ ክብሩዋን የምዳፈር

የማዬን
ተስፋዋን ምኞትዋን ወይስ መልካምነት
ደግነትዋን ፍቅርዋን ወይስ እሩህሩህነት
በስንኝ አስሬ በቃል አትሬ የማሳንስባት
የቱን ልተው የቱን ብዬ
ምኑን ላንሳ ምኑን ጥዬ
ማን ጽፎ እንደጨረሰ ልጨርሰስ ነው ስለምዬ
ቃላት ማሳመሩም ግጥሙም ይቅርባት
ምንም ሳልናገር ዝም ብዬ ልውደዳት
እምዬ የኔ እናት
La tehzen
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➛ክፍል አስር ➭➭➭➭➭➭➭ ➧ረሡል የዚህ ተመሳሳይ ለአቡደርዳእ አደራ እንዳሉት እንደሚከተለው ግልጽ አድርጓል፡-“ወዳጀ እስካለሁ ድረስ እንዳልተዋቸው በሶስት ነገሮች አደራ ብሎኛል” ከዚያም ከላይ የተዘረዘሩ ሶስት ነገሮችን አወሳ፡፡ ሙስሊም፡722 ➠እድሜው አነስተኛ የሆነው ዑመር ብን አቢ ሰለማህ ረድየላህ አንሁ የዚህ ተመሳሳይ…
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል አስራ አንድ
➛➛➛➛➛➛➛

➲ስድስተኛው፡ - ሰለፎች ክልክል ነገሮችን ፈጥነው ይከለከሉ ነበር
ክልክል ነገሮችን በመራቅም በጣም ፈጣንና በአቋማቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፡፡

➤ ይህን አስመልክቶ ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡትን ትክክለኛ ሐዲስ ዑመር ረድየላህ አንሁ አስተላልፏል፡-

▪️"إن الله ينهاكم عن أن تحلفوا بآبائكم "

“በአባቶቻችሁ መማልን አላህ ይከለክላችኋል፡፡” ቡኻሪ፡ 6647 ሙስሊም፡1646

➧በአንዳንድ ዘገባዎች ይህን ሐዲስ ረሡል صلى الله عليه وسلم የተናገሩበት ምክንያት ዑመር ረድየላህ አንሁ
በአባቱ ሲምል ሰምተውት ነው ይባላል፡፡ ከዚህ የምንገነዘበው በአባት መማል በጃሂልያ ጊዜ የለመዱት ተግባር እንደሆነ ነው፡፡ ዑመር ከላይ የተጠቀሰውን ሐዲስ ከረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰማ በኋላ የሚከተለውን ተናገረ፡-

▪️"فوالله ما حلفت بها منذ سمعت النبي صلى الله عليه وسلم ذاكرا ولا آثرا"

➠“ከረሡል صلى الله عليه وسلم ከሰማሁ ጊዜ ጀምሮ ረስቸም ይሁን ሆን ብየ በእርሷ ምየ አላውቅም፡፡” በዚህ ጉዳይ ሰለፎች የነበራቸው ወኔ እንዴት እንደነበር? አሁንም የተወሰነውን
እንጥቀስ፡፡ አንድ ግለሰብ “ነቢን” ብሎ ሲምል ከሰለፎች አንዱ ሰማው፡፡ “ነቢን” ብሎ መማል እንደሌለበት ማስረጃዎችን ደረደረለት፡፡ ከዚያም ሰውየው የሚከተለውን ተናገረ፡-

▪️لن أحلف بالنبي بعد اليوم!

“ከዚህ ቀን በኋላ ፍጹም “ነቢን” ብዬ አልምልም” ይህ የሚያስረዳው አንድ ሰው በምላሱ የለመደው ነገር እንኳ ቢሆን ቁርጠኛ ሆኖ ከተወው ሊተው እንደሚችል ነው፡፡ እስኪ የዑመርን ንግግር እናድምጥ፡-

▪️"والله! ما حلفت بها بعد لا ذاكرا، ولا آثرا"

➧ወሏሂ! ከዚያ በኋላ በእርሷ ሆን ብየም ይሁን ረስቸ (ከአላህ ውጭ በሆነ አካል)
ምየ አላውቅም፡፡”

➳ይህ የሚጠቁመው ሰለፎቹ ትኩረታቸው የጎላ ፣ ለእውቀት ምን ያክል ፍላጎት እንደነበራቸው እንገነዘባለን፡፡በማስጠንቀቂያ መልኩም ይሁን በትዕዛዝ አንድ ሐዲስ ከሰሙ በሚያስገርም ሁኔታ በዚያው ላይ ቀጥ ብለው ይዘወትራሉ፡፡

▪️ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡት የአነስ ረድየላህ አንሁ የሚከተለው ሀድስ አስተላልፏል፡-

➲አነስ ረድየላህ ከአቡጦልሃ ረድየላህ አንሁ ዘንድ አገልጋይ ነበር፡፡ አስካሪ መጠጥ ሀራም ከመደረጉ በፊት ለሶሃቦቹ መጠጥ እየቀዳ ያጠጣቸው ነበር፡፡ከዚያም አንድ ሶሃባ “አስካሪ መጠጥ ሀራም ተደርጓል” የሚል ጥሪ ሲጣራ ሰማ፡፡ ይህን ጉዳይ በጣም የለመዱት ከመሆኑ ጋር ወዲያውኑ መጠጡ እንዲደፋ አዘዙ፡፡ እርሷ ለእነርሱ የመጨረሻ ሆነች፡፡ ቡኻሪ፡1617 አስተላልፈዋል፡-1980

▪️እንደዚሁ በሙስሊም በተዘገበ ሐዲስ ኢብን ዓባስ ረድየላሁ አንሁ የሚከተለውን አስተላልፈዋል፡- የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم ከአንድ ሶሃባ ጣት ላይ ወርቅ ተመለከቱ፡፡ ከጣቱ ላይ በሀይል አውለቀው ጣሉት፡፡ ከዚያም የሚከተለውን ተናገሩ፡-
▪️يعمد أحدكم إلى جمرة من نار فيجعلها في يده"
“አንድ ሰው ፍም እሳት ከእጁ ላይ ማድረግን ያስባልን?”ለዚህ ግለሰብ - ረሡል صلى الله عليه وسلم ወርቁን ከወረወሩት በኋላ “ቀለበትክን ያዝና ተጠቀምበት - ሽጠውና ለቤተሰብህ ተውላቸው - ይህ የሚበቃ ጉዳይ ነው” የሚል ሀሳብ ከጓደኞቹ ቀረበለት፡፡የሰጠውን መልስ ተመልከት፡- “በፍጹም ወሏሂ! የአላህ መልእክተኛ ወርውረው የጣሉትን እስከመጨረሻው አልይዘውም” በማለት ነበር መልስ የሰጣቸው፡፡ ሙስሊም፡2090

➠ከነብዩ صلى الله عليه وسلم የመጣውን ለመያዝ ከነበራቸው ጉጉት የተነሳ የተፈቀደውን ነገር እንኳ ለመያዝ ነፍሳቸው ትጸየፍ ነበር፡፡

➧ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉

🖊🖊ኑርአህመድ
【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚
La tehzen
➧ከተውሂድ አርማዎች ➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭ ➻ክፍል አራት ➫➫➫➫➫ ➲የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻➻ ➧ተውሒድ፡ ለአካለ መጠን በደረሱ ሰዎች ላይ የመጀመሪያው ግዴታ ነው፡፡ ሰዎች ወደዚህ ዲን መጀመሪያ የሚገቡት በእርሱ ነው፡፡ የዲኑ መሰረት ተውሒድ ነው ፤ ዲኑ በእርሱ ላይ ይቆማል ፤ በእርሱም ላይ ይጀመራል። ➲አራተኛው፡- ሰላም ለማግኘትም ይሁን…
➲ከተውሂድ አርማዎች
➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ክፍል አምስት
➛➛➛➛➛➛

➧የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➲ስድሥተኛ፡- ተውሒድ ከሰላማዊ ተፈጥሮ ፣ ከተስተካከለ አቅል ጋር ተስማሚ ነው፡፡ተውሒድ የተፈጥሮ እምነት ነው፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ እምነቱ ላይ ቢተው ከተውሒድ ውጭ ሌላን አይቀበልም፡፡ ምክንያቱም አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደተናገረው ፣ ተውሒድ ከተፈጥሮ ጋር የሚስማማ የሰው ልጅ የተፈጠረበት እምነት ነው፡፡

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

فَأَقِمْ وَجْهَكَ لِلدِّينِ حَنِيفًا ۚ فِطْرَتَ اللَّهِ الَّتِي فَطَرَ النَّاسَ عَلَيْهَا ۚ لَا تَبْدِيلَ لِخَلْقِ اللَّهِ ۚ ذَٰلِكَ الدِّينُ الْقَيِّمُ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَعْلَمُونَ

➧“ወደእውነት ተዘንባይ ሆነህም ፊትህን ለሃይማኖት ቀጥ አድርግ፡፡የአላህንፍጥረት ያችን አላህ ሰዎችን በእርሷ ላይ የፈጠረባትን (ሃይማኖት ያዟት) ፡፡ የአላህን ፍጥረት መለወጥ የለም፡፡ ይህ ቀጥተኛ ሃይማኖት ነው፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያውቁም፡፡” አር ሩም፡30

➧ሽርክ (ማጋራት) ደግሞ ከተፈጥሮው መውጣትና ማዘንበል ነው፡፡ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሰል-ቁድስ አላህ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️"وإني خلقت عبادي حنفاء كلهم ، وإنهم أتتهم الشياطين فاجتالتهم عن دينهم"

“እኔ ባሮቸን ሁሉ በቀጥተኛው መንገድ ላይ ፈጠርኳቸው፡፡ ሰይጣናት ወደነርሱ
በመምጣት ከዲናቸው እንዲዘነበሉ አደረጓቸው፡፡” ሙስሊም፡2865

➧“ኸለቅቱ ዒባዲ ሁነፋእ” ማለት የተፈጥሮ እምነት በሆነው ተውሒድ ላይ ሰዎችን ፈጠርኳቸው ማለት ነው፡፡

➧“ፈአተትሁም አሽሸያጢን ፈጅታለትሁም” ማለት ደግሞ ከዲናቸው ወይም ከተውሒዳቸው እንዲዘነበሉ አደረጓቸው ማለት ነው፡፡

➲በትክክለኛ ዘገባ አቡሁረይራ ረድየላህ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

▪️"ما من مولود إلا يولد على الفطرة ، فأبواه يهودانه ، وينصرانه كما تنتجون البهيمة ، هل تجدون فيها من جدعاء ، حتي تكونوا أنتم تجدعونها؟”وفي رواية: "فأبواه يهودانه ، أو ينصرانه ، أو يمجسانه ، كما تنتج البهيمة بهيمة جمعاء ، هل تحسون فيها من جدعاء؟"

➠“አንድም የሚወለድ የለም በተፈጥሮው (እምነት ላይ ቢሆን) እንጅ ፤ ወላጆቹ አይሁድ ያደርጉታል ፣ ክርስቲያን ያደርጉታል፡፡ እንስሳት ስትወለድ እናንተ ካልቆረጣችኋት በቀር ከሰውነት አካሏ የተቆረጠ አካል ታገኛላችሁ?” ቡኻሪ፡6599

➲በሌላ ዘገባ፡ “ወላጆች አይሁድ ያደርጉታል ወይም ክርስቲያን ያደርጉታል ወይም መጁስ ያደርጉታል፡፡ እንስሳት ምንም እንከን የሌላት ልጅ ትወልዳለች፡፡ ከልጇ አካል ላይ ቆራጣ ታገኛላችሁን?” ቡኻሪ፡ 1359 ሙስሊም፡2658

➲አንዲት እንስሳት ከእናቷ ሆድ ጆሮዋና ጣቶቿ የተሟሉ ሆነው ትወለዳለች፡፡ እግሯ ወይም እጇ ወይም ጆሮዋ ወይም የመሳሰሉት አካሎቿ ከተቆረጠ ይህ ተፈጥሯዊ አይደለም፡፡ ይህ በተሟላ ሁኔታ ከተወለደች በኋላ ሰዎች የሚያደርጉት ነው፡፡ የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم” እናንተ እስከምትቆርጧት ድረስ” በማለት ተናግረዋል፡፡

➭ልክ እንደዚሁ የሰው ልጅ በተፈጥሮ እምነቱ ላይ ነው የሚወለደው፡፡ ክርስቲያን ወይም አይሁድ ወይም መጁስ ወይም በተለያዩ የጥመት አመለካከቶች ተበክሎ
ብናገኘው በወላጆች ወይም በአደገበት አካባቢ ተጽእኖ የተፈጠረ ችግር እንጅ
የተፈጥሮ እምነቱ አይደለም፡፡

▪️وينشأ ناشئ الفتيان منا على ما كان عوده أبوه
➛ወጣቶቻችን ያድጋሉ ታዳጊ ሆነው (በአካባቢው ባህሪ) አባቱ ባስለመደው

➲የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم” ወላጆቹ ሙስሊም ያደርጉታል” የሚል ሳይሆን “ወላጆቹ አይሁድ ወይም ክርስቲያን ወይም መጁስ ያደርጉታል” የሚል ቃል ነው የተናገሩት፡፡



ኢንሻአላህ ይቀጥላል
🖊🖊🖊ኑር አህመድ

【አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል】📚📚📚📚📚

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from ኑሩተውሂድ የግጥም ቻናል
❤️❤️❤️ስንት አየሁ❤️❤️❤️
በሰመመን ስዕል ሁሌ እስልሃለሁ
ከተራማጅ መሃል ኮቴህን እሰማለሁ
ከህዝብ ጫጫታ ድምፅህን እሰርቃለሁ
ከንፁሃን መሀል አንተን አስባለሁ
......... እኔ ስንቱን አየሁ
እንደሚሟሟ ጨው እሳሳልሃለሁ
በእጅ እንደተሰራ ወድቆ እንደሚሰበር እንደ ማሰሮ ጌጥ እንሰፈሰፋለሁ
ድምፅህን ስሰማ ከላይ ተወርውሮ ጆሮዬ እንደገባ የመላክ ምስራች እፈነጥዛለሁ
የከፋህ ሲመስለኝ ድንገተኛ ትዕዛዝ
ሞት እንደመጣበት እደነግጣለሁ
የተደሰትክ ቀን በሳቄ ጋጋታ አንተን እገልፃለሁ እኔስ ስንቱን አየሁ ...........
Forwarded from ኑሩተውሂድ የግጥም ቻናል
የት ነበርኩኝ እኔ⁉️

ኧረ የት ነኝ እኔ:
ቦታው ጠፋኝ ወይኔ:
ተደናገርኩ እኔ:
ተቃጥሎ ዘመኔ:

ጊዜው እረፍዶብኝ:
ገርገራው መጥቶብኝ:
ጌታን ረስቼ እንዲ እንደኳተንኩኝ:
ይኸው እኔን ሊወስድ መለይካው ቀረበኝ:
አሁን ነው የታወቀኝ:
አሁን ነው የነቃሁኝ።

ከማለትህ በፊት:
ወንድም አስብበት:
እህት አቅጂበት:
አታውቂውምና ቀኑን ምትሞቺበት:
ዛሬ ነገ አንበል ደግሞ ለመቶበት።

ኑርአህመድ


https://t.me/httpsnurahemd
#መርህ_አልባ_ጉዞ__!!
--------------------------------

ልብህ ድር አድርቶ ዘወትር ሲከስር
ወይ አልቆነጠጥከው ገብተህ ከጭኑ ስር፡
ሁሌ አቋም ይይዛል በቀን ዘጠኝ አስር፡

የሚሔደው በእውር መመለስ በሌለው፡
ወይ ደስተኛ አይሆን ሸክሙ እንኳን አይቀለው፡
ደግሞ ሁጃ አይጠቅስ እውቀት አላደለው፡

በስሜት በእልህ በውትወታ ጉዞ፡
አንድ ሲናገሩት ወደ አስር ጠምዞ፡
ንፁህ ውሀ ሰጥተህ በአረቂ በርዞ፡

የሰላም ፍችህን በአመፅ ፐውዞ፡
በውስጡ ቂም ቋጥሮ በደልን አርግዞ፡
የሱና ድምፅህን በጥመት መርዞ፡

እርሱ በተረዳው ቃልህን ቀይሮ፡
በእኔ በልጥ ተውሳክ ልቡን አደንቁሮ፡
ነቃሁ ሲል ጨልሟል ጉድ አየሁ ዘንድሮ፡

በቅናት ያበደ በቅባት አይወዛም፡
እውነት የፈለገ ውሸት አያበዛም፡
እውነት ተቀምጦ ውሸትም አይነዛም፡

ያንን ውብ ገለፃ በሸፍጡ መርዞ፡
አደገኛ ትርጉም በርሱስም አስይዞ፡
ሲገርመኝ ሲደንቀኝ አዕምሮዬ ፈዞ፡
ለካ እንድህ ያደርጋል መርህ አልባ ጉዞ፡

ኑር
La tehzen
➲ከተውሂድ አርማዎች ➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➻ክፍል አምስት ➛➛➛➛➛➛ ➧የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ ➲ስድሥተኛ፡- ተውሒድ ከሰላማዊ ተፈጥሮ ፣ ከተስተካከለ አቅል ጋር ተስማሚ ነው፡፡ተውሒድ የተፈጥሮ እምነት ነው፡፡ የሰው ልጅ በተፈጥሮ እምነቱ ላይ ቢተው ከተውሒድ ውጭ ሌላን አይቀበልም፡፡ ምክንያቱም አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንደተናገረው ፣ ተውሒድ ከተፈጥሮ…
➧ከተውሂድ አርማዎች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➛ክፍል ስድስት
➭➭➭➭➭➭➭➭

➧የተውሒድ መለያዎችና ትሩፋቶች
➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱

➲የአላህ መልክተኛ صلى الله عليه وسلم” ወላጆቹ ሙስሊም ያደርጉታል” የሚል ሳይሆን “ወላጆቹ አይሁድ ወይም ክርስቲያን ወይም መጁስ ያደርጉታል” የሚል ቃል ነው የተናገሩት፡፡ ምክንያቱም ያደገው የተወለደው በተፈጥሮ እምነቱ ላይ ነው፡፡

➭ተውሒድ የተፈጥሮ ሐይማኖት ነው፡፡ሽርክ ወይም ማጋራት ፣ ጥመትና ከንቱ አመለካከት ደግሞ የተፈጥሮ እምነትን የሚጋጭ ከተውሒድ ጋር የማይገናኝ ነው፡፡ ተውሐድ ከተስተካከለ ከአዕምሮ ጋር ይስማማል፡፡ ያልተጣመመ ፣ ያልተዘነበለ አዕምሮ ከተውሂድ ውጭ ሌላን አይወድም፤ ተውሒድን እንጅ አይቀበልም፡፡ ከእርሱ ዘንድ ሰላማዊ አዕምሮ ኖሮት ማን ነው በርካታ አማልክትን የሚወድ! ማን ነው ወደ ቁባና የአፈር አምልኮት የሚያዘነብለው!

➲አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

يَا صَاحِبَيِ السِّجْنِ أَأَرْبَابٌ مُّتَفَرِّقُونَ خَيْرٌ أَمِ اللَّهُ الْوَاحِدُ الْقَهَّارُ (39)مَا تَعْبُدُونَ مِن دُونِهِ إِلَّا أَسْمَاءً سَمَّيْتُمُوهَا أَنتُمْ وَآبَاؤُكُم مَّا أَنزَلَ اللَّهُ بِهَا مِن سُلْطَانٍ ۚ(40)

➧“የተለያዩ አምላኮች ይሻላሉን? ወይስ አሸናፊው አንዱ አላህ? “ከእርሱ ሌላ እናንተና አባቶቻችሁ (አማልክት ብላችሁ) የጠራችኋቸውን ስሞች እንጅ አትገዝዙም፡፡ አላህ በእርሷ ምንም አስረጅ አላወረደም፡፡” (ዩሱፍ፡ 39-40)

▪️ዘይድ ብን ዓምር ብን ኑፈይል የተባለው የጃሂልያው የተውሒድ ሰው ከአካባቢው ማህበረሰብ በእምነት በተለየ ጊዜ የሚከተለውን ግጥም ገጥሟል፡-

▪️أربا واحدا أم ألف رب▲ أدين إذا تقسمت الأمور
▪️عزلت اللات والعزى جميعا ▲كذلك يفعل الجلد الصبور
▪️فال عزى أدين ولا ابنتيها ▲ولا صنمي بني عمرو أدير

➴➴አንድ ወይስ አንድ ሽ ጌታ
የተለያዩ ጉዳዮች ሲገጥሙኝ የማምነው (የማታ ማታ)
➴➴ከዑዛም ከላት ከሁሉም ተለየሁ
ልክ እንደዚሁ ይሰራል ታጋሹ ብልሁ
➴➴ዑዛን እስከ ሁለት ልጆቿ በፍጹም አላመልክም
ወደበኒ ዓምር ሁለት ጣዖቶች ፊቴንም አላዞርም

➲ዘይድ ብን ዓምር ብን ኑፈይል ፡ “ፍየልን የፈጠረ ፣ እርሷ የምትጠጣውን ውሃ ከሰማይ ያወረደ ፣ እርሷ የምትመገበውን አትክልት ከምድር ያበቀለ አላህ ሆኖ እያለ እርሷን ስታርዱ ከአላህ ስም ውጭ እንዴት ታነሳላችሁ?” በማለት አላህን በማላቅ ፤ጣዖታትን ዝቅ በማድረግ የመካ ቁረይሾችን እርድ ያነውር ነበር፡፡ ቡኻሪ ፡3826

➧ዓለምን የፈጠረ የሆነው አላህ ከነውርና ከጉድለት የጸዳ ፣ ሙሉ የሆነ ባህሪ ያለው፣ ተናንሰን እና ተዋርደን ልንገዛው የሚገባ መሆኑን ከማወቅ የበለጠ ለአዕምሮ ግልጽና የተብራራ አንድም ነገር የለም፡፡

➲መልክተኞች የመጡት ይህን ጉዳይ ለማሳወቅና ለመዘርዘር ነው፡፡ የተውሒድ
ውበቱና የሽርክ አስቀያሚነቱ በአዕምሮና በተፈጥሮ የተረጋገጠ ህያው የሆነ ልቦና ፣ሰላማዊ የሆነ ዓቅልና ትክክለኛ የሆነ ተፈጥሮ ካለው ሰው ዘንድ በጣም ግልጽ የሆነና የታወቀ ጉዳይ ነው፡፡



ኢንሻአላህ ይቀጥላል
🖊🖊ኑርአህመድ
【አንብብ! ማንበብ የተሻለ ሰው ያደርጋል】

➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴

https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➧የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል አስራ አንድ ➛➛➛➛➛➛➛ ➲ስድስተኛው፡ - ሰለፎች ክልክል ነገሮችን ፈጥነው ይከለከሉ ነበር ክልክል ነገሮችን በመራቅም በጣም ፈጣንና በአቋማቸው ቀጥ ያሉ ነበሩ፡፡ ➤ ይህን አስመልክቶ ቡኻሪና ሙስሊም የዘገቡትን ትክክለኛ ሐዲስ ዑመር ረድየላህ አንሁ አስተላልፏል፡- ▪️"إن الله ينهاكم عن أن تحلفوا…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➭ክፍል አስራ ሁለት

➧ሰባተኛው፡ ተግባር ፣ እውቀት በአዕምሮ ውስጥ ሰርጾ እንዲገባና የጸና ተግባር ከቀረ እውቀትም ይጠፋል፡፡ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️"هتف بالعلم العمل، فإن أجابه وإلا ارتحل"
“እውቀት ለተግባር ጥሪ ያደርጋል ፤ ከተቀበለ (መልካም) ካልተቀበለ ግን ጥሎት ይሄዳል” ዘምሚ መን ላያዕመል ቢዒልሚሂ፡ ገፅ፡ 38 ይህ ማለት እውቀት አይቆይም ይሄዳል ማለቱ ነው፡፡ በእውቀት መስራት ለጽናት ምክንያት ይሆናል፡፡
በዚህ ምክንያት ከሸዕብይ የሚከተለው መቷል፡-

"كنا نستعين على حفظ الحديث بالعمل به"
▪️“ሐዲስን ለመሀፈዝ በተግባር (በሐዲሱ በመስራት) እንታገዝ ነበር” ጃሚዑ በያኒ አል ዒልም፡1/709

➧አቡደርዳእ ረድየላህ አንሁ ደግሞ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

"إنك لن تكون عالما حتى تكون متعلما، ولن تكون متعلما حتى تكون عامال بما
تعلمت"
➧“ተማሪ ካልሆንክ ፍጹም ዓሊም ልትሆን አትችልም ፤ የተማርከውን ወደተግባር
ካልቀየርክ በፍጹም ተማሪ ልትሆን አትችልም፡፡” (ኢቅቲዳዕ ሊልኸጢብ፡ 16,17)

➲በዚህ ትርጉም ላይ በርካታ የሰለፎች ንግግር አለ፡፡ አንድ ሙስሊም የሰለፎችን
ተጨባጭ ህይዎት ከተከታተለ ውብ እና የተባረከ ታሪክ ያገኛል፡፡ ደጋግ ወደሆኑት ባሮቹ አላህ ያስጠጋን!

➲ስምንተኛው፡ - ባወቀው መስራት ፣ ዳዕዋው የበለጠ ተቀባይነት ያለተግባር ከመናገር ይልቅ ለዳእዋው ስኬት ጠቃሚ የሚሆነው በእውቀት መስራቱ ነው፡፡

▪️አላህ ስለሹዓይብ የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️وَمَا أُرِيدُ أَنْ أُخَالِفَكُمْ إِلَىٰ مَا أَنْهَاكُمْ

“ከእርሱ ወደከለከልኳችሁም ነገር ልለያችሁ አልሻም፡፡” ሁድ፡88

▪️ማሊክ ብን ዲናር - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

▪️"إن العالم إذا لم يعمل زلت موعظته عن القلوب كما يزل القطر عن الصفا"

“ዓሊም ባወቀው ካልተገበረ ምክሩ ልክ ከልሙጥ ዲንጋይ ላይ እንደምታርፍ ጠብታ ነው የሚሆነው፡፡ የእርሱ ምክር ከልብ ላይ ትንሸራተታለች፡፡” ኢቅቲዳእ ሊልኸጢብ፡97

➧መእሙን - ረሂመሁሏህ - የሚከተለውን ተናግሯል፡-

▪️"نحن إلى أن نوعظ بالأعمال أحوج من أن نوعظ بالأقوال"

➧“እኛ በንግግር ሰዎችን ከመገሰጽ ይልቅ ፣ በተግባር መገሰጽ በጣም ለእኛ አስፈልጎናል፡፡” ጃሚዑ በያኒ አል ዒልም፡1236 ምክንያቱም የተግባር ቀጣይነት በራሱ ዳዕዋ ነው፡፡ በዚህም ለሰዎች አርአያ ይሆናል፡፡በተግባር የሰዎች ኢማም ይሆናል፡፡

▪️አላህ በተከበረው ቁርኣናዊ አንቀጽ የሚከተለውን ተናግሯል፡

وَاجْعَلْنَا لِلْمُتَّقِينَ إِمَامًا

➛(የአላህ ባሮች) አላህን ለሚፈሩትም መሪ አድርገን” የሚሉት ናቸው፡፡አል ፉርቃን፡74


➧ኢንሻአላህ ይቀጥላል◉◉◉

🖊ኑርአህመድ

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen
La tehzen
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው ➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫ ➭ክፍል አስራ ሁለት ➧ሰባተኛው፡ ተግባር ፣ እውቀት በአዕምሮ ውስጥ ሰርጾ እንዲገባና የጸና ተግባር ከቀረ እውቀትም ይጠፋል፡፡ ዓልይ ረድየላህ አንሁ የሚከተለውን ተናግሯል፡- ▪️"هتف بالعلم العمل، فإن أجابه وإلا ارتحل" “እውቀት ለተግባር ጥሪ ያደርጋል ፤ ከተቀበለ (መልካም) ካልተቀበለ ግን ጥሎት ይሄዳል”…
➲የእውቀት ፍሬው ተግባር ነው
➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭➭

➻ ክፍል አስራ ሶስት
➫➫➫➫➫➫➫➫

➧አንድ ሰው የመልካም ባህሪያት ሁሉ ከእርሱ ላይ ካልተሰባሰቡ ከኢማምነት
ደረጃዎች ሊደርስ አይችልም፡፡ በመልካም ባህሪያቶች ለሰዎች አርአያ ሊሆን ይገባል፡፡

➛የእውቀት አይነቶችን እየሰበሰበ ነገር ግን የተግባር ሰው ካልሆነ ይህ ሰው እርሱ እንዳልተጠቀመ ሁሉ በእውቀቱ ሌሎች ሊጠቀሙ አይችሉም፡፡

ተጽእኖ አሳዳሪ አንድ ታሪክ ላውራ፡-


➲አንድ ጊዜ እድሜያቸው የገፋ ሰው መስጅድ ውስጥ አገኘሁና ዘየርኳቸው፡፡ እኒህ ሽማግሌ አላህን በጣም ይገዙ ነበር፡፡ ሶላትን መስጅድ ውስጥ ሁልጊዜ ይጠባበቃሉ፡፡አሰላሙ ዓለይኩም አልኳቸውና ከሰውየው ጋር ንግግር ጀመርኩ፡፡ “በእናንተ መንደር
እውቀት ፈላጊዎች በብዛት አሉ” አልኳቸው፡፡ “በዚህ በመንደራችን?” አሉኝ። አዎ! አልኳቸው፡፡ “ማሻአላህ የእውቀት ፈላጊዎች በርካታ ናቸው” አልኳቸው፡፡

➧“በዚህ በመንደራችን!” በማለት መልሰው ጠየቁኝ፡፡ የተቃውሞ ይመስላል፡፡ እኔም
“አዎ” አልኳቸው፡፡ ከዚያም “ልጀ ሆይ ከጀመዓ ጋር ሶላትን የማይጠባበቅ ሰው
እውቀት ፈላጊ አይባልም” በማለት መልስ ሰጡኝ፡፡ በዚህ ምክንያት አንዳንድ ሰው ዒልም ፣ ሂፍዝ ፣ እና ዳዕዋ ማድረግን ያበዛል፡፡ ነገር ግን ፈጅር ሶላት ላይ ግን አታገኘውም፡፡ ብዙ ጊዜ ታጣዋለህ፡፡

➧ሶላት ደግሞ ከሸሀደተይን በኋላ የኢስላም ትልቁ ማዕዘን ነው ፣ የቂያማ ቀን መጀመሪያ የምንጠየቅበትም ነው፡፡ ሶላትን ካጠፋ የእውቀት አሻራው የት ላይ ነው ያለው ? የሶሃቦችን ባህሪ ኢብን ዑመር ረድየሏሁ አንሁማ እንደሚከተለው ይናገራል፡

▪️"كنا إذا فقدنا الرجل في الفجر والعشاء أسأنا به الظن"

➲“አንድ ግለሰብ በሱብሂም ይሁን በዒሻ ካጣነው በእርሱ መጥፎን እንጠራጠር ነበር፡፡” ( ጦበራኒይ ፊሙዕጀም አል ከቢር፡12/271 ኢብኑ ኹዘይማ፡ 1405 ኢብኑ ሂባን፡ 2099 ላይ አውርተውታል)

▪️وفي الحديث " إن أثقل صالة على المنافقين صالة الفجر وصالة العشاء"

➧በሐዲስ ረሡል صلى الله عليه وسلم የሚከተለውን ተናግረዋል፡-“በሙናፊቅ ላይ ከሶላት ከባዱ የፈጅርና የዒሻ ሶላት ነው፡፡” ቡኻሪ፡ 757 ሙስሊም 651

➧አሁን ባለንበት ወቅት በብዛት እየተስተዋለ ያለው ችግር የፈጅር ሶላት ላይ ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በዲን እውቀት እየተከራከሩ ያመሻሉ፡፡ ከዚያም የፈጅርን ሶለት ሳይሰግዱ ይተኛሉ፡፡ አንድ ሰው በፈጅር ሂሳብ ቁርኣን እየቀራ ወይም እየሀፈዘ ሌሊትሙሉ ቢያመሽ ማምሸቱ ሀራም ነው የሚሆንበት፡፡ እርሱ ሐጢያተኛ ይሆናል፡፡

➲በዚህ ዘመን በአብዛኛው ውድቅ እየተደረገ ያለው ከሶላቶች ሁሉ በላጭ የሆነው የፈጅር ሶላት ነው፡፡

▪️የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم በሐዲሳቸው የሚከተለውን ተናግረዋል፡-

▪️"أفضل الصلوات عند الله صالة الصبح يوم الجمعة في جماعة"

➧“ከአላህ ዘንድ ከሶላቶች ሁሉ በላጭ ጁሙዓ የፈጅር ሶላትን በጀመዓ መስገድ ነው፡፡” ሂልየቱ አል አውሊያእ፡ 7/207 አልባኒ ሐዲሱን ሶሂህ ብለውታል ሲልሲለቱ አሰ ሶሂህ፡1566

➧የጁሙዓ ቀን የሱብሂ ሶላትን በጀመዓ መስገድ በአብዛኛው እየተዘነጋ የሄደበት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ እስኪ የመስጅድ ኢማሞች ይጠየቁ፡፡ ምክንያቱም (በዓረብ አገሮች) የጁሙዓ ሌሊት የፈቃድ ሌሊት ነው፡፡ የጁሙዓ ሌሊት የወሬ ሌሊት ነው፡፡

➠ሰዎች እስከመጨረሻው ሌሊት ያመሻሉ ፤ ከዚያም የፈጅርን ሶላት ሳይሰግዱ ይተኛሉ፡፡ ከእነርሱ መካከል ጥሩ የሚባለው ዘግይቶና ከዚያም ቅንጭላቱ በእንቅልፍ ናውዞ የሚሰግደው ነው፡፡

➭የመስጅዱ ኢማም “ሱረቱ ሰጅዳ” እና “ሀልአታ” ሱራዎችን በመቅራት የታወቀ ከሆነ ሁለተኛው ረከዓ መጨረሻ ላይ መጠው የሚሰግዱ ሰዎችም አሉ፡፡
ችግሩ ያለው የትንሳኤ ቀን ከእርሱ መጀመሪያ የሚጠየቅበት የሆነው ፈርድ ሶላት ላይ ከሆነ ፣ የእውቀት ፍሬው የት ላይ ነው ያለው? ሶላትን ካጠፋ ሌላውን ማጥፋቱ የሚያጠያይቅ አይደለም፡፡



➧ኢንሻአላህ ክፍል አስራ አራት ይቀጥላል◉◉◉

ኑርአህመድ🖊

【አንብብ በማንበብ ብዙ እውቀት ይገኛል】📚📚📚📚📚


➧ ወ ደ ቻ ና ላ ች ን ይ ቀ ላ ቀ ሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsLatahzen