La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
#ከሀዲስ

1) «ከቀብር ቅጣት ነጃ የወጣ ከዛ ቡሀላ ያለው ገር ይሆንለታል፣ ከቀብር ቅጣት ነጃ ያልወጣ ከዛ ቡሀላ ያለው የበለጥ ይጠናበታል»።
ረሱል (ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📔ሶሒሁል ጃሚዕ (1684)

2) ኢብኑ መስዑድ እንዲህ አሉ፦
«ረሱልን በላጭ የሆነው መልካም ስራ የትኛው ነው ብየ ጠየቅኳቸውና እንዲህ አሉኝ "ሶላትን በወቅቱ መስገድ" ከዛስ አልኳቸው ለወላጆች መልካም መዋል አሉኝ»።
📔ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል

3) «ረሱል የሞቱ ቀን አቡበክር ሲዲቅ ወደርሳቸው መጣና ፊታቸውን ገልጦ ግምባራቸውን ሳማቸው ከዛም እንዲህ አለ"አባቴና እናቴ መስዋት ይሁኑሎትና በህይወትም ሳሉ ሙተውም ምንኛ ውብ ናችሁ»።
ምንጭ:-📔ሶሒሁል ቡኻሪ (3667)
ከኢብኑ #ዑሰይሚን ፈገግ የሚያሰኝ የፈትዋ ጥያቄ

ዶሮ እሽቅድምድም?

ጠያቂ፡- በሐዲሥ፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ታዲያ አንድ ሰው በዶሮ ውድድር ወይም በእርግብ እሽቅድምድም ቢሆን ምን አስተያየት አለህ?

መልስ እነሆ፣ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ወይም ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በጦርነት ውስጥ ስለሚውሉ ነው። ዶሮዎ በላዩ ላይ እንዲጋልቡበት በጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ይፈቀዳል! አለበለዚያ አይሆንም….
አሉት።
ከኢብኑ #ዑሰይሚን ፈገግ የሚያሰኝ የፈትዋ ጥያቄ

ዶሮ እሽቅድምድም?

ጠያቂ፡- በሐዲሥ፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ታዲያ አንድ ሰው በዶሮ ውድድር ወይም በእርግብ እሽቅድምድም ቢሆን ምን አስተያየት አለህ?

መልስ እነሆ፣ ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይኺ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፡- [ከፍላጻ፣ ከእግር ውድድር፣ ወይም ከፈረስ እሽቅድምድም ውጪ ውድድር የለም] ምክንያቱም እነዚህ ነገሮች በጦርነት ውስጥ ስለሚውሉ ነው። ዶሮዎ በላዩ ላይ እንዲጋልቡበት በጦርነት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውል ከሆነ ይፈቀዳል! አለበለዚያ አይሆንም….
አሉት።
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:

لا تكثروا الكلام بغير ذكر الله؛ فإن كثرة الكلام بغير ذكر الله تعالى قسوة للقلب! وإن أبعد الناس من الله تعالى القلب القاسي.
ነብዩ ሰ.ዐ.ወ.እንድህ ይላሉ፦ ንግግርን አታብዙ።
አሏህን ለማውሳትና ለማወደስ ካልሆነ በስተቀር።ለምን ከተባለ፦ ዝክር ያልሆነ ንግግርን ማብዛት ቀልብን ያደርቃታልና።ከአሏህ ረህመት በጣም የራቀ ሰው ማለት ደግሞ ቀልቡ የደረቀበት ሰው ነው። አሏህ ይጠብቀንና‼️

ስለዝህ በተቻለ መጠን መልካም ንግግርን ለመናገር እንሞክር ።አልያም ዝም እንበል።
👉ከተቻለ ሰዎችን ወደ ኢስላም ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ሱና ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ሷላት ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ እውቀት መድረክ ጋብዛቸው

👉ከተቻለ ከሀሜት እንድ ርቁ ምከራቸው

👉ከተቻለ ከውሸት ራቁ በላቸው

👉ከተቻለ ወደ ተውሂድ ጥራቸው

👉ከተቻለ ወደ ዝክር ጥራቸው

👉ከተቻለ እርቅን እንድያሰፍኑ ምከራቸው
👉ከተቻለ ሷደቃ እንድሰጡ አነሳሳቸው

👉ከተቻለ የቲሞችን እንድረዱ አድርጋቸው

👉ከተቻለ ቁርኣንን እንቅራ እናስቀራ

⚠️ከዝህ ውጪ የሆነ ንግግር በሽታ እንጂ የቀልብ ፈውስ አይሰጥህም በደንብ ራቀው‼️

መልካም አዳር‼️

አቡ ሙስሊም ቢን ጋቼኖ
Audio
#የመጨረሻ_ክፍል
•┈┈┈┈•✿❥❥✿•┈┈┈┈•
#የነብዩ_ዩሱፋፍ_(ዐ.ሰ)የህይወት ታሪኩ የመጨረሻ ክፍል ደርሱዋል እስከ ዛሬ ከመጀመሪያው ጀምሮ ስለተከታተላቹን በጣም እናመሰግናለን። ለሌሎችም #ሼር አርጉት እሀንን ጣፋጭ የነቢዩላህ ዩሱፍ (ዐ.ሰ) የህይወት ታሪኩን ከመጀመሪያው ጀምሮ ከላያቹት በዚ ቻናል ማያት ትችላላችሁ ዉድ ye_ le tahzenቤተሰቦቼ 👉

ሁላቹንም ለአላህ ብዬ እወደቹዋለው።

#ሼር_ሼር_ሼር


https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
ማንኛችሁም ሞትን እንዳይመኝ
ቢስሚላህ
አሰላቱ ወሰላሙ ዐላ ረሱሊላህ
አሰላሙዐለይኩም
ውዶች ፣
ሰዎች በእይታቸው ከበድ ያለ ችግር ሲገጥማቸው ምነው በሞትኩት፣ይህንን ሳላይ ብሞት ይሻለኝ ነበር።ሲሉ ይደመጣል።ሌላው ሀገራዊ ብሂል "እልፍ ሲሉ እልፍ ይገኛል
ድሀ ሞኝ ነው ሞትን ይመኛል"
በማለት ዛሬ ከበድ ያለ ችግር ቢገጥምህ ነገ ደግሞ መውጫ ስለሚኖር ተሰፋን አትቁረጥ የተሻለ ነገ ይኖራልና።
ይህን መርሕ ከ 1400 ዓመት በፈት ውዱ ነቢይ
ለ ጓዶቻቸው ሰሐባዎች በተለያዩ ዘገባዎች በገጠማቸው ችግር ሞትን እንዳይመኙ እንዲህ በማለት ያስጠነቅቁ እንደነበር እንረዳለን።ከእነዚህ ዘገባዎች የሚከተለው የቡኻሪ ዘገባ ይጠቀሳል።
حَدَّثَنَا ابْنُ سَلاَمٍ، أَخْبَرَنَا إِسْمَاعِيلُ ابْنُ عُلَيَّةَ، عَنْ عَبْدِ الْعَزِيزِ بْنِ صُهَيْبٍ، عَنْ أَنَسٍ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ لاَ يَتَمَنَّيَنَّ أَحَدٌ مِنْكُمُ الْمَوْتَ لِضُرٍّ نَزَلَ بِهِ، فَإِنْ كَانَ لاَ بُدَّ مُتَمَنِّيًا لِلْمَوْتِ فَلْيَقُلِ اللَّهُمَّ أَحْيِنِي مَا كَانَتِ الْحَيَاةُ خَيْرًا لِي، وَتَوَفَّنِي إِذَا كَانَتِ الْوَفَاةُ خَيْرًا لِي ‏"‌‏.‏ اللبخاري 6351

ከአነስ ቢን ማሊክ በተላለፈው ሀዲስ እንደሚከተለው ማለታቸውን ቡኻሪ ዘግበዋል
"አንዳችሁ በገጠመው ችግር የተነሳ ሞትን አይመኝ።የግድ ሞትን የሚያስመኘው ደረጃ የሚያደርሰው ከሆነ አላህ ሆይ መኖሬ ለኔ የሻለ ከሆነ በህይወት አኑረኝ።መሞቴ ለኔ የተሻለ ከሆነ
ሞትን ግጠመኝ ይበል" በማለት ምርጫውን ለአላህ ይስጥ ዘንድ አስተምረዋል።
ቡኻሪ አረብኛ እንግሊዝኛ መድበል ሀዲስ ቁጥር 6351

ከአቢሁረይራ በተወራ ሀዲስ ደግሞ " .....አንዳችሁ ሞትን እንዳይመኝ መልካም ሰሪ ከሆነ የመልካም ተግባር ኪታቡ እንዲጨምርላት መሆኑ በላጩ ነው።በተቃራኒው አመፀኛ / አጥፊ ከሆነ ደግሞ ተውበት ለማድረግ እድል ያገኛልና" ቡኻሪ ሀዲስ ቁ 5671
በሌላ ዘገባ እድለኛ ሰው ማለት እድሜው የረዘመ ነው ።ማለታቸው ተዘግቧል።
ሁላችንም አላህ ረጅም እድሜና መልካም ስራን እንዲያበዛልን እንለምነው።
እርሱ የባሮቹን ልመና ሰሚ ነው
ወሰለላሁመ ወሰሊም ዐላ ነቢዪና ሙሐመድ
ወሰላም
(سُبْحانَكَ اللَّهُمَّ وَبِحَمْدِكَ، أَشْهَدُ أَنْ لاَ إِلَهَ إِلاَّ أَنْتَ، أَسْتَغْفِرُكَ وَأَتوبُ إِلَيْكَ).
🍃🌻
(بِسْمِ اللَّهِ، تَوَكَّلْتُ عَلَى اللَّهِ، وَلَاَ حَوْلَ وَلَا قُوَّةَ إِلاَّ بِاللَّهِ).
🍃🌻
🛏 እነሆ በፍቃዱ አምሽተን አነጋን
ሌላ ቀን እንድናይ አዲስ እድል ሰጠን።

ከሞት በኋላ ሕይወትን ለለገሰን እኛም ወደ እሱ የምንሰበሰብ የሆነው ጌታ ምስጋና የተገባው ነው።


#አልሀምዱሊላህ

💦በእያንዳንዱ እርምጃ አላህን በሃሳብህ ማቆየትህን አስታውስ።

💦 አላህ በእዝነቱ ጉዳቱን እና ተግዳሮቶቹን ሁሉ ይጠብቅልን።

💦በአካባቢያችሁ መልካም እና ደግነት የተሞላበት አስደሳች እና ሰላማዊ ቀን እንዲኖርዎት ቁርኣን በማንበብ በዚክር ጀምሩ እንዲሁም በውሎዋችሁ ሰላምና መፅናናትን ታገኛላችሁና።

💦ከባድ ቀን ቢያጋጥመህም አላህ የሚፈትንህ ብቻ መሆኑን ተረዳ።

💦አዲስ ቀን የአላህን መንገድ ለመከተል አዲስ እድል ነው ስለዚህ ጊዜህን በአግባቡ ተጠቀም።

💦ውሎ አችሁ የተባረከ አስደሳች እና ማራኪ ተጠቃሚ ምትሆኑበት እንዲሆን እመኛለሁ
" لا تشغلن بعيب غيرك غافلا
عن عيب نفسك إنه عيبان "

የራስህን ነውር ዘንግተህ በሌሎች ነውር አትወጠር
ይህ ማድረግህ ሁለት ነውር ነው።

1ኛ, የራስህን ነውር መዘንጋትህ
2ኛ, የሌሎችን ነውር መከታተልህ
❀ ወላሂ እጅግ በጣም ቀናሁ. . . .
☞ሰብር አድርጋችሁ አንብቡት ትጠቀማላችሁ ኢንሻ አላሁ ተዓላ !
✿መጪው ዘመን የሚል አንድ ደብዳቤ ላይ አንድ የአረብ ሀገሮች
የመኪና ፍጥነት የሚቆጣጠር ትራፊክ ይህንን ታሪክ ዘግቦታል. . .
>ለናንተ ላካፍላችሁ! ትራፊኩ እንዲህ ሲል ታሪኩን ጀመረ:- "
አንዴ የተለመደውን ስራዬን ቆሜ እየሠራሁ እንዳለ አንድ መኪና
እንዲሁ ረጋ ብሎ ሲሄድ ነበር ይህ ሰው መኪናው ተበላሸበትና
ከመኪናው ወቶ ወርዶ ለማስተካከል ልክ እንደወረደ ከሁዋላ
መጣችና አንዲት መኪና ወጣችበት ወደቀ ተገጨ
ይህ ሰው ከባድ የሆነ አወዳደቅን ወደቀ እኛም ሩጠን አነሳነውና
መኪና ላይ ሰቀልነው ይሄን ሰው ይህ ሰው ስናየው ገና ለጋ
~ወጣት ነበር ይህ ልጅ የአላህ ባሪያ መሆኑ ፊቱ ላይ ያስታውቃል
``ፂሙ ፊቱ ያበራል የኢማን ኑር ይታይበት ነበር ልክ አንቡላንስ
>መኪና ላይ ስንጭነው ይህን ወጣት አብረነው ስንሳፈር የኾነ
ቃል ይናገር ነበር የሚለውን ግን መረዳት አልቻልንም ነበር ነገር
ግን መኪና ውስጥ አድርገነው ከጎን እኔና ጉዋደኛዬ ትራፊክ
አብረን ከጎን ሁነን መሄድ ስንጀምር ለየት ያለ የሚያምር ድምፅ
መስማት ጀመርን አላሁ አክበር!!!
❀ይህ ወጣት ቁርዓን እየቀራ ነበር ይህ ወጣት በሚያምር ድምፅ
ቁርዓን እየቀራ ነበር ሱብሀንአላህ! በጣም ይገርማል እንደው
የተመታ እንደዚያ አይመስልህም ደም ልብሱን እንዳለ አካላቱን
አልብሶታል አጥንቱ ደቆ ተሰባብሮዋል ልክ ወጣቱን ስታየው ሞት
አፋፍ ላይ ያለ ነው የሚመስልህ ነገር ግን ይህ ወጣት
በሚያምር ድምፅ ቁርዓንን ይቀራ ነበር ሞት አፋፍ ላይ ያለ
ወጣት! አላሁ አክበር!
ተገርመን በጣም ማየት ጀመርን ትንሽ እንደቆየ ፀጥ አለ!ወደ
ሁዋላ ዞር ብዬ ስመለከተው እጁን ወደ ላይ አድርጎ ሸሀዳ እያለ
ነበር :- " አሽሀዱ አላ ኢላሀ ኢለላህ ወአሽሀዱ አነ ሙሀመደን
ረሱሉላህ" ያ አላህ! ሱሀነክ! ;-( ;-( ;-( ከዛም ፀጥ አለብን
ይህ ወጣት እጁን ሂጄ ነካሁት ደረቱን ዳሰስኩት ምንም
የሚንቀሳቀስ ነገር የለም ይህ ወጣት ዱንያን ለቆ ወጥቶ ነበር
ሱብሀነላህ!
ብዙ አተኩሬ ይህን ወጣት ተመለከትኩት ከአይኔ እንባ መርገፍ
ጀመረ ጉዋደኛዬ እንደው መቆም አልቻለም ለቀቀው ማልቀስ
ጀመረ እንዲህ ብሎ ቁርዓን እየቀራ ሲሞት ሆስፒታልም
እንደደረስን ስለዚህ ወጣት ሁኔታ ያገኘነውን ሰው ሁሉ ስለ
ወጣቱ ነገርናቸው አብዛኛዎቹ በጣም ልባቸው ተነካ እንባቸው
መውረድ ጀመረ አንደኛው ታሪኩን እንደሰማ በጣም ተገረመና
ይሄን የአላህ ባሪያ ሄጄ ግንባሩን ነው የምስመው ብሎ ሳመው
አብዛኛዎቹ በቃ ከዚህ ከአላህ ባሪያ ላይ ሶላተል ጀናዛ
ሳንሰግድበት አንሄድም አሉ::
`
ከዛም ከሆስፒታሉ ሰራተኞች ውስጥ አንዱ ወደ ቤተሰቡ ደወለና
ወንድሙ መጣ:- ወንድሙ ነው ይሄን የሚቀጥለውን ታሪክ
የሚናገረው:- "ወንድሜ ሁሌ ሰኞ ሰኞ አንዲት ገጠር አካባቢ
አያቱ አለች እሷን ሊዘይራት ይመላለስ ነበር:: እዛች አገር
ውስጥ ያሉ ሚስኪኖችን የቲሞችን ባል የሞተባቸውን ሴቶችን
እየሄደ ይረዳቸው ነበር:: ያቺ ከተማ ወንድሜን ታውቀው ነበር::
ለዛች አገር ሰዎች ሁሌ ሰኞ ሰኞ ካሴቶች መፅሐፎችን እየወሰደ
እሱ ነበር የሚሰጣቸው::
ሁሌም ወደዛች ሀገር ሲሄድ መኪናው ውስጥ ሩዝ ስኩዋር
ምናምን ሞልቶ ነበር የሚሄደው ለችግረኞች እዛ ሊበትንላቸው
ማለት ነው:: ከረሜላ እንኩዋን ለዛች ሀገር ሕፃናቶች አይረሳም
ነበር:: ሁሌም ታዲያ ሰዎቹ አንተ የዚህን ያህል ጉዞ
ትመላለሳለህ እንዴ! ብለው ለሚተቹትና ሀሳብ ለሚሰጡት
ሰዎች እንዲህ ብሎ ይመልስላቸው ነበር:- " እኔኮ ወደዝች
ሀገር በመመላለሴ በረጅሙ ጉዞዬ ውስጥ ቁርዓንን ለመሐፈዝና
ቁርዓንን ሙራጃ ለማድረግ ለማስታወስ እጠቀምበታለሁ
የሚጠቅም ሸሪጦችን ሙሀደራ እሰማበታለሁ እንደኛ ሙዚቃ
ከፍቶ አይደለም የሚሄደው ይሄ ሁሉ ጎማዬ የሚሽከረከረው
መሽከርከር ከአላህ ዘንድ አጅር አኝበታለሁ ብዬ አምለናለሁ
ይለን ነበር::
እያለ ወንድምየው ነገረን:: ሱብሀን አላህ!!! ትራፊኩ ምን
ይላል:- ሀያቴ ልክ በማዕበል እንደምትናጥ መርከብ እዛ እዚ
እየዋተትኩ ነበር መዋለል ከሁሉ አቅጣጫ ወሮኝ ነበር አላህ
(ሱ.ወ) ን ከራቁት ውስጥ ነበርኩ ወጣቱን ቀብር ላይ ከተነው
በሰገድንበት ጊዜ እሱ የአኼራን የመጀመሪያን ቀን ሲገናኝ እኔ
የዱንያን የመጀመሪያዬን ቀን ተገናኘሁ ወደ አላሁ (ሱ.ወ)
ተመለስኩ አላሁ (ሱ.ወ) ያሳለፍኩትን ይምረኝ ዘንድ ይህንን
ወጣት አሟሟቱ እንዳሳመረው ሁሉ በኸይር ይወስደኝ ዘንድ
አላሁ(ሱ.ወ) እየተማፀንኩ ቶብቼ ተጸጽቼ የዱንያን
የመጀመሪያዬን ቀን ጀመርኩ ይላል::
" መጪው ዘመን በሚል ርዕስ ላይ ይህ ትራፊክ ነው ታሪኩን
የዘገበው እናቶቼ አባቶቼ እህቶቼ ወንድሞቼ ወላሂ የመጨረሻን
ሸሀዳ ማግኘት ከባድ ነው አሁን ምላሳችን ዚክር ያለመደ ከኾነ
ከቁርዓን ጋር ያልኖርን ከሆነ ያኔ ጣዕረሞት ላይ አይመጣልንም
ወላሂ !!! የቁሉላሁ (ተባረከ ወተዓላ) ፊ ሙህከሚ ተንዚሊህ:
- "አንተ ሰው ሆይ! አንተ ጌታህን (በሞት) እስከምትገናኝ ድረስ
ልፋትን ለፊ ነህ! ተገናኚውም ነህ!" ሱረቱ አል-ኢንሺቃቅ 6
ያ አላህ!!! ያ አረሕማን!!! ያ ዘልጅላሊ ወል ኢክራም!!! ያ
አርሀሙ ራሒሚን!!! አሟሟታችንን አሳምርልን!!! ኑሮአችንን
በኢባዳ ሞታችንን በሸሀዳ አድርግልን!!! አሚን!!! አላሁመ
አሚን!!!
ሼር ያድርጉ ለሌላውም ያስተላልፉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇


https://t.me/httpsLatahzenhttps://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from La tehzen
#ቁርዓኔ
ከአላህ የተላክ ውዱ ደብዳቤዬ፣
መሰረቴ ነህ ሁሌም የልዕልናዬ፣
ፈጥሮካል ኢላሂ እጅጉን ገር አርጎ፣
ሊቀርብክ ላሰበ አኼራን ፈልጎ፣
አትከብድም ሲያነቡህ በጣም ቀላል ነህ፣
እኛው ነን ያከበድንህ ቦታ ሳንሰጥህ፤

#ቁርዓኔ
ታውቃለህ እንደሆንክ የስኬቴ መሰላል፣
ሁሌም ከጎኔ ሁን የፈጣሪዬ ቃል፣
አንተን ስቀርብ ነው ውስጤ ሚረጋጋው፣
ጭንቀቶቼን ትቼ ሰላም የማገኘው፣
በዱንያም በአኼራ ድል የምቀዳጀው፣
ስርቅህ አይደለም እጅግ ስቀርብህ ነው።

#ቁርዓኔ
አንተ ነህ የህይወቴ መመሪያ፣
ሀቅና ባጢሉን አጣርቶ መለያ፤
ምድር ከያዘችው መፅሀፎች መካከል፣
በፍፁም አይገኝም አንተን የሚያክል፤
ካንተ ተፈልጎ የለም የሚታጣ፤
ሁሉን አካተሀል ያለንም ሚመጣ።

#ቁርዓኔ
ህመሜን ምትፈውስ ፍቱን መድሀኒቴ፣
ቁርዓኔ ብቻ ነህ የእድገት መሰረቴ፤
ሰላሙን ተነፍጎ ደስታ የራቀው፣
አንተን ያቅርብና ያድርግ ጓደኛው፤
ምድር ላይ ብቅ ካልህ ሺህ አመታት ቢያልፍም፣
ሁልጊዜ አዲስ ነህ መቼም አትሰለችም።
ቁርኣን…
=================
⇛ከቁርኣን ርቄ ወደ ሶሻል ሚዲያው መመላለስ ካበዛሁ ሰነበትኩ፡፡ የቂያማ ቀን ቁርኣን ከሚከሣቸው ሰው አንዱ እንደሆንኩ አስባለሁ፡፡ አዎን የቂያም ቀን ቁርኣን የዘጉትንና ያኮረፉትን ሰዎች ይከሳል፡፡ አላህ በረሕመቱ ይሁነኝ፡፡

⇨አሁን በመሃል ድንገት የሆነ ስለ ቁርኣን የተፃፈ ጽሑፍ አነበብኩና ከረጅም ጊዜ በኋላ ድንገት ብንን አልኩኝ፡፡ ያነቃኝን አላህ አብዝቶ ይመንዳው፡፡ ለካ ቁርኣንን ረስቼዋለሁ፡፡ በወሬ መሃልም መባነን አንድ ነገር ነው ወዳጆቼ፡፡ ደንዝዞ ከመቅረት አላህ ይጠብቀን፡፡

⇛አላህ ቁርኣንን በረከት፣ ፈውስ፣ ቅናቻ አድርጎ አወረደልን፡፡ እኛ ግን አጠገባችን እያለ ረሳነው፡፡ እርስት አደረግነው …. ወላሂ፡፡

እኛ ግን ምን ዓይነት ሞኞች ነን በአላህ!! በሚጠቅመን ነገር ላይ ትንሽ ብዙ በማይጠቅመን ነገር ላይ ብዙ ሰዓት እናሳልፋለን፡፡

⇛ከኪሣችን ሞባይላችንን አውጥተን፣ ከመደርደርያው ላይ አዉርደን ማንበብ ባንችል እንኳ ቁርኣንን ባገኘንበት አጋጣሚ ሁሉ ዒርፎናችን ሰክተን ለማዳመጥ እንሞክር፡፡ ስንቆምም ሆነ ስንቀመጥ በረከቱን እናትርፍ፡፡ ታክሲ ዉስጥ፣ ወረፋ ስንይዝ፣ እንቅልፍ አልወስድ ሲለን፣ የእግር መንገድ ስንጓዝ … ወዳጃችን እናድርገው፡፡ ትርጉሙን ባናውቅ እንኳ በረከቱ ይተርፈናል እኮ፡፡

ያ ረብ ቁርኣንን አስወድደን፤ ዘወትር ከሚያነቡትም አድርገን፡፡
(اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ أَنْ أَضِلَّ، أَوْ أُضَلَّ، أَوْ أَزِلَّ، أَوْ أُزَلَّ، أَوْ أَظْلِمَ، أَوْ أُظْلَمَ، أَوْ أَجْهَلَ، أَوْ يُجْهَلَ عَلَيَّ).
🍃🌻
🔰🔰የዕለቱ ሀዳስ.............🔰📙
አቡ ሁረይራ [رضي الله عنه‌‎ ] እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ [صلى الله عليه وسلم] እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል፡- “በትንሳኤ ቀን ፍርድ ከሚሰጣቸው ሰዎች የመጀመሪያው የሚሆነው ሰማዕት ሆኖ የሞተ ሰው ነው፡፡ (አላህ ፊት) እንዲቀርብ ይደረግና አላህ የዋለለትን ውለታዎች እንዲያውቅ ያደርገዋል፤ እሱም ያስታውሳቸዋል፡፡ (ኃያሉ አምላክ) “በእነሱ ምን ሠራህባቸው? (ውለታዬን መልሰሃልን?)” ይለዋል፡፡ ሰውየውም “ሰማዕት ሆኜ እስክሰዋ ድረስ በአንተ መንገድ ላይ ተጋደልኩ” ይላል፡፡ አላህም “ዋሽተሃል፤ ደፋር ነው እንድትባል ብቻ ነበር የተዋጋኸው፡፡ እናም እንደዚያ ተብሎልሃል” ይለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ጀሀነም እሳት እስኪጣል ድረስ በፊቱ እየተጎተተ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ ሌላው (ተጠያቂ) (የሃይማኖት) ዕውቀት ያጠና፣ በዕውቀቱም የተገበረና ያስተማረ፣ እንዲሁም ቁርኣንን መቅራት ያዘወትር የነበረ ሰው ይሆናል፡፡ እሱም እንዲቀርብ ይደረግና አላህ የዋለለትን ሁሉ እንዲያውቅ ያደርገዋል፤ እርሱም ያስታውሳቸዋል፡፡ (ኃያሉ አምላክ)፡- “በእነዚህ ምን ሠራህባቸው?” ይለዋል፡፡ እሱም ‹‹(የሃይማኖት) ዕውቀትን ተማርኩ፤ አስተማርኩም፤ ለአንተ ስልም ቁርኣንን አጠናሁ” ይላል፡፡ አላህም “ዋሽተሃል፤ (የሃይማኖት) ዕውቀት ያጠናኸው የተማረ ነው እንድትባል፣ ቁርኣኑንም ያጠናኸው አንባቢ ነው እንድትባል ነበር፤ እንደዚያም ተብሎልህ ነበር” ይለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ጀሀነም እሳት እስከሚጣል ድረስ በፊቱ እየተጎተተ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ (ሌለው ተከሳሽ) አላህ ሃብታም አድርጎት የነበረና ሁሉንም የሃብት ዓይነት ሰጥቶት የነበረ ሰው ይሆናል፡፡ እንዲቀርብ ይደረግና አላህ የዋለለትን ሁሉ ያሳውቀዋል፤ እሱም ያስታውሳቸዋል፡፡ (ኃያሉ አምላክ) “በነዚህ ምን ሠራህባቸው?” ይለዋል፡፡ እሱም “አንተ ገንዘብ እንዲወጣ በምትፈልግበት መንገድ ለአንተ ስል ገንዘብ ከማውጣት አልተቆጠብኩም” ይላል፡፡ አላህም “ዋሽተሃል፤ ያደረግኸው ቸር ነው እንድትባል ብቻ ነበር፡፡ ይህም ደግሞ ተብሎልሃል” ይለዋል፡፡ ከዚያም ወደ ጀሀነም እሳት እስከሚጣል ድረስ በፊቱ እየተጎተተ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡”

📚ሙስሊም፣ነሳኢይ እና ቲርሚዚይ ዘግበውታል📚
ከግዴታ ሶላት በኋላ ዚክርና ዱዓእ ማድረግ ላይ ከጊዜ ጊዜ በጣም እየተዘናጋንበት ያለ ጉዳይ ነው። እንደሚታወቀው ይሄ ጊዜ በጥቂት ጥረት ብዙ ምንዳዎች የሚታፈስበት፣ ምህረት የሚገኝበት፣ ዱዓኦች ይበልጥ ተቀባይነት ከሚያገኙባቸው እጅግ ወሳኝ ጊዜያት ውስጥ አንዱ ነው። ስለዚህ ተገቢ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል፦
ኢብኑ ተይሚያ - ረሒመሁላህ - ደግሞ እንዲህ ይላሉ፦
"ከሰዎች ውስጥ ከሶላት በኋላ ዚክርም ሆነ ዱዓእ ማድረግን የማይወድ አለ። ሶላት እንደተጠናቀቀ እሱም ሌሎች ተከታዮችም ልክ ከአንበሳ እንደሚሸሽ ሆነው ይነሳሉ። ይሄ የሚወደድ አይደለም።" [ጃሚዑል መሳኢል፡ 4/ 316]
.
ኢብኑ በጧል ረሒመሁላህ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦
من كان كثير الذنوب واراد ان يحطها الله عنه بغير تعب، فليغتنم ملازمة مصلاه بعد الصلاة ليستكثر من دعاء الملائكة واستغفارهم له.
ወንጀለ ብዙ የሆነና ያለ ድካም አላህ እንዲያረግፍለት የሚሻ ሰው ከሶላት በኋላ መስገጃ ቦታውን አጥብቆ መያዝን ይጠቀም። መላእክት ለሱ ዱዓእ ማድረጋቸውንና ምህረት መጠየቃቸውን በብዛት ያገኛልና።
[ሸርሑ ሶሒሕ አልቡኻሪ፣ ኢብን በጧል፡ 3/114]
.
በሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሒመሁላህ ስም እንዲህ የሚል መልእክት ሲዘዋወር አይቻለሁ (የሳቸው መሆኑን ማረጋገጥ አልቻልኩም።)፦
الجلوس بعد السلام من الصلاة المكتوبة من أعظم الأوقات التي تنزل فيها رحمة الله عز وجل لا تستعجل بالقيام.
استغفر، سبح الله، واحمده، وهلل وكبر ...
የግዴታ ሶላትን ካሰላመቱ በኋላ መቀመጥ የአላህ - 0ዘ ወጀለ - እዝነት ከሚወረድባቸው ታላላቅ ጊዜያት ውስጥ ነው። ስለዚህ ለመነሳት አትቻኮል። አላህን ምህረትን ጠይቅ (ኢስቲግፋር አድርግ)። ሱብሓነላህ፣ አልሐምዱ ሊላህ፣ ላኢላሀ ኢለላህ፣ አላሁ አክበር፣... በል።
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
➲የተዘረጋው የአላህ ገመድ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➧“የተዘረጋው የአላህ ገመድ” የሚለው ስያሜ ክቡር ለሆነው የአላህ ቁርኣን የተሰጠ ስያሜ ሲሆን ስያሜው በነብዩ صلى الله عليه وسلم ትክክለኛ ሐዲስም ተረጋግጦ ይገኛል፡፡

فقد روى الإمام مسلم في "صحيحه" من حديث زيد بن أرقم رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "ألا وإني تارك فيكم ثقلين : أحدهما كتاب الله عز وجل ، هو حبل الله، من اتبعه كان على الهدى ، ومن تركه كان على ضلالة"

◆በሙስሊም ዘገባ ዘይድ ብን አርቀም رضي الله عنه የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፏል፡-

➠“ንቁ! እኔ በእናንተ ውስጥ ሁለት ታላላቅ ነገሮችን ትቸላችኋለሁ፡፡ አንደኛው የአላህ ኪታብ ነው፡፡ እርሱም የአላህ ገመድ ነው፡፡ እርሱን የተከተለው በቅን ጎዳና ላይ ይሆናል፡፡ እርሱን የተወው ደግሞ በጥመት ላይ ይሆናል፡፡” ሙስሊም፡ (2408)

"وروى الإمام أحمد في "مسنده" من حديث أبي سعيد الخدري رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "كتاب اللّٰه حبل ممدود من السماء إلى الأرض"

◆ኢማም አህመድ በዘገቡት ደግሞ አቡሰዒድ አል'ኹድርይ ረድየሏሁ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

➠“የአላህ መጽሐፍ ከሰማይ ወደምድር የተለቀቀ የአላህ ገመድ ነው፡፡” አህመድ፡11104 ቲርሚዚይ፡3788

وروى ابن أبي شيبة في "مصنفه" من حديث أبي شريح الخزاعي رضي الله عنه أن النبي صَلَى اْللّٰهُ عَلَيْه وَسَلَم قال: "أبشروا أبشروا ، أليس تشهدون أن لا إله إلا الله وأني رسول الله ؟" قالوا : نعم ، قال : "فإن هذا القرآن سبب طرفه بيد الله، وطرفه بأيديكم فتمسكوا به ، فإنكم لن تضلوا ، ولن تهلكوا بعده أبدا"

➧ኢብን አቢ ሸይባ በዘገቡት አቡ'ሹረይህ አል'ኹዛዒይ ረድየሏሁ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

➲“አብሽሩ! አብሽሩ! ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ እንደሌለ ፣ እኔም የአላህ መልክተኛ እንደሆንኩ ትመሰክራላችሁ አይደል?” በማለት ረሡል صلى الله عليه وسلمሶሃቦችን ጠየቁ፡፡ ሶሃቦችም “አዎ!” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ የአላህ መልክተኛም “ይህ ቁርኣን ገመድ ነው፡፡ አንዱ ጫፍ በአላህ እጅ ነው ፤ ሌላኛው ጫፍ ደግሞ በእናንተ እጅ ነው፡፡

እርሱን አጥብቃችሁ ያዙ ፣ ከእርሱ በኋላ ፍጹም አትጠፉም” በማለት ተናገሩ፡፡ ሙሰነፍ ሊብኒ አቢ ሸይባ፡ አልባኒ ሐዲሱን በሙስሊም መስፈርት ሶሂህ ነው ብለውታል አስ ሶሂህ፡

وروى الدارمي عن عبد الله بن مسعود رضي الله عنه أنه قال : "إن هذا الصراط محتضر تحضره الشياطين ينادون يا عبد الله هذا الطريق ، فاعتصموا بحبل الله ، فإن حبل الله القرآن"
አድ ዳሪሚይ በዘገቡት ዓብደሏህ ብን መስዑድ ረድየሏሁ አንሁ የሚከተለውን ሐዲስ አስተላልፈዋል፡-

➳“ይህ (ቀጥተኛ የኢስላም) መንገድ ሰይጣናት ይገኙበታል ፤ (ሰይጣናት) “አንተ የአላህ ባሪያ ሆይ! ቀጥተኛ ያልሆነውን መንገድ ይህ ትክክለኛው መንገድ ነው” እያሉ ጥሪ ያደርጋሉ። የአላህን ገመድ አጥብቃችሁ ያዙ ፤የአላህ ገመድ በእርግጥ ቁርኣን ነው” አድ ዳሪሚይ፡ 3360

➢ኢንሻአላህ
ይቀጥላል





https://t.me/httpsLatahzen
(اللَّهُمَّ اجْعَلْ فِي قَلْبِي نُوراً، وَفِي لِسَانِي نُوراً، وَفِي سَمْعِي نُوراً، وَفِي بَصَرِي نُوراً، وَمِنْ فَوْقِي نُوراً، وَمِنْ تَحْتِي نُوراً، وَعَنْ يَمِينِي نُوراً، وَعَنْ شِمَالِي نُوراً، وَمِنْ أَمَامِي نُوراً، وَمِنْ خَلْفِي نُوراً، وَاجْعَلْ فِي نَفْسِي نُوراً، وَأَعْظِمْ لِي نُوراً، وَعَظِّم لِي نُوراً، وَاجْعَلْ لِي نُوراً، وَاجْعَلْنِي نُوراً، اللَّهُمَّ أَعْطِنِي نُوراً، وَاجْعَلْ فِي عَصَبِي نُوراً، وَفِي لَحْمِي نُوراً، وَفِي دَمِي نُوراً، وَفِي شَعْرِي نُوراً، وَفِي بَشَرِي نُوراً)([اللَّهُمَّ اجْعَلْ لِي نُوراً فِي قَبْرِي... وَنُوراً فِي عِظَامِي])[(وَزِدْنِي نُوراً، وَزِدْنِي نُوراً، وَزِدْنِي نُوراً)][(وَهَبْ لِي نُوراً عَلَى نُورٍ)]
🍃🌻
አንድ ቀን ረሱል (ሰ.ዐ.ወ) ለዐሊይ (ረዐ) እንዲህ አሉት:: አንተ ዐሊይ ሆይ ከመተኛትህ በፊት አምስት ነገሮችን ተግብር፡፡
1,ስትተኛ አራት ሺ ዲናር ሶደቃ ስጥ
2,ቁርዐን አኽትም
3,ለጀነት ዋጋዋን ክፈል
4,ሁለት ሰዎችን አስታርቅ
5,ከዚያም አንድ ጊዜ ሐጅ አድርገህ ተኛ፤
ዐሊይም(ረዐ)እንዲህ በማለት ጠየቁ፦ያ ረሱለላህ ይሄን በአንድ ለሊት እንዴት ማረግ ይቻላል? ብሎ ጠየቃቸው ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) የሚከተለውን ተናገሩ።
1,አራት ጊዜ ሱረቱል ፋቲሀን የቀራ 4000 ዲናር ሰደቃ ከሰጠው ጋር እኩል ነው።
2,ሶስት ጊዜ ሱረቱል ኢኽላስን(ቁል ሁ ወላሁ አሀድ) የቀራ አንድ ጊዜ እንዳኸተመ ይቆጠርለታል።
3,ሶስት ጊዜ ላ ሀውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐሊዩል ዐዚም ያለ የጀነት ዋጋዋን ከፍላል።
4,አስር ጊዜ እስቲግፋር ያረገ ሁለት ሰዎችን እንደ ማስታረቅ ነው።
5,አራት ጊዜ ሸሀዳ ያደረገ አንድ ጊዜ ሀጅ እንዳደረገ ነው።
አስብ ይሄ መልእክት አንተ ጋር ብቻ እንዲቆይ አትፍቀድ ለሌሎችም አጋራ ባንተ ምክንያት ሌላ ሰው አንብቦ ቢጠቀም አንተም የሱ ምንዳ ተካፋይ ነህና።
አላህ ባነበብነው ባስተላለፍነው ተጠቃሚ ያድርገን!
ፈገግ በሉ

የአባት እና የልጅ ወግ

አባት:- ከእኔና ከእናትህ ማንን ነው የምትወደው?

ልጅ:- ሁለታችሁንም

አባት:- አይ አንድኛችንን ብቻ ምረጥ

ልጅ:- ሁለታችሁንም ነዋ የምወደው

አባት:- ቆይ እሽ እኔ ባህር ዳር እናትህ ደግሞ ሀዋሳ ብትሄድ አንተ የት ትሄዳለህ?

ልጅ:- ሀዋሳ

አባት:- አየህ የምትወደው እናትህን ነው ማለት ነው

ልጅ:- አይ እንደዛ እኮ አይደለም

አባት:- እና ምንድን ነው?

ልጅ:- እኔ ሀዋሳን ስለምወዳት ነው

አባት:- እሽ እኔ ሀዋሳ እናትህ ደግሞ ባህር ዳር ብትሄድ ያንተ ምርጫ የት መሄድ ነው?

ልጅ:- ባህር ዳር

አባት:- ለምን

ልጅ:- ቅድም ሀዋሳ ሄጀ ነበራ😄😄😄