La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
አውፍ እንባባል

ጥቂት ቀናት ቀረው ረመዳን ሊገባ
እርስ በርሳችንም ይኑረን ሙሀባ
ነሻጣም ይኑረን እንዳንሆን ጀዝባ

ተውበትንም እናርግ ረመዳን መጥቷል
አሁን ወዲያው ፈጥነን አውፍ እንባባል

በቅድሚያም ከራሴ እኔ እጀምራለው
ላስቀየሙኝን ሰዎች አውፈን ብያለው

አውፍ በዮችን ይወዳል ጌታችሁ
አውፍ በሉኝ እኔን ለአላህ ብለችሁ

ስሙንም እንስቼ እኔ ካማሁት
የሰውነት ክብሩን ከነካሁበት
አውፈን ይበለኝ በጥቂት ቃላት
Audio
ክፍል 6
💍::::::::::ትዳር /ጋብቻ:::: 💍

" ከናንተ መካከል በላጩ ሰው ለሚስቱ መልካም የሆነ ነው"

❥ነብዩ ስለላሁ አለይሂወሰለም ❥
💍 ኒካህ በማሰር ትዳር በመመስረት አላህን ታዘዙ ቃል የገባላችሁን ይሰጣችኋልና....💯💯

💍ጋብቻ በኔ ዘንድ የሚወደድ ተግባር ነው እኔ ለምወደው ነገር ጀርባውን የሰጠ ለኔ ጀርባውን እንደሰጠ ይቆጠራል "🚫
☞❥ብለዋል ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም.

👉 ከራሳችሁ የሆነችን ተጣማሪ ትረኩበት ዘንድ ማድረጉ ከታአምራቶቹ አንዱ ነው።👌

☞❥ 💍 ሚስትህን ውደዳት ጊዜም ሰጥተህ አስደስታት ግማሽ ዲንህን የምትሞላበትን ቀን መቸውም ቢሆን አትዘንጋ እርሷ #ሚስትህ ብቻ ሳትሆን ከአራህማን የተሰጠችህ ንግስናህ ነችና።

☞☞💍 ውዷ እህቴ አንችም ብትሆኝ ባልን ማክበርና መታዘዝና የአላህንና የረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ትዛዝን ከመጠበቅ ይቆጠራልና ለባልሽ መልካም ሁኚ።

❥☞አላህ የባሎችንም ሆነ የሚስቶችን ሀቅ ጠባቂወች ያድርገን... አሚን 🤲🤲

☞☞አላህ መልካምን ትዳር ይወፍቃችሁ.....አሚን

🤲🤲ኧረ አሚን በሉ💍 ከወደዱት #ሼር_ያድርጉ
"ጊዜውን ለአላህ ያላደረገ ከሕይወት ይልቅ ሞት ለሱ የተሻለ ነው።"
ኢብኑል ቀይም
[አዳኡ ወደዋእ፡ 186]
ከረጀብ ወር ጋር የሚያያዙ ደካማ ሐዲሦች
~~~
ከረጀብ ጋር ብዙ መሰረተ ቢስ ቅጥፈቶችና ደካማ ሐዲሦች አሉ። ለምሳሌ ያክል፦
[1ኛ]፡-
رجب شهر الله وشعبان شهري ورمضان شهر أمتي
“ረጀብ የአላህ ወር ነው። ሸዕባን የኔ ወር ነው። ረመዷን ደግሞ የህዝቦቼ ወር ነው።” አልባኒ ደካማ እንደሆነ ገልፀዋል። [አዶዒፋህ፡ 4400]

[2ኛ]፡- ረጀብ ሲገባ እንዲህ ይሉ ነበር፡-
اللهم بارك لنا في رجب وشعبان، وبلغنا رمضان
“አላህ ሆይ! ረጀብንና ሸዕባንን ባርክልን። ረመዷንን አድርሰን።” ነወዊይ በ“አዝካር”፣ ዘሀቢይ በ“ሚዛን” ደካማ እንደሆነ ብይን የሰጡ ሲሆን አልባኒም “ደካማ ነው” ብለዋል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 4395]

[3ኛ]፡-
فضل شهر رجب على الشهور كفضل القرآن على سائر الكلام
“የረጀብ ወር በሌሎች ወራት ላይ ያለው ብልጫ ቁርኣን በሌሎች ንግግሮች ላይ እንዳለው ብልጫ ነው።” ኢብኑ ሐጀር “መሰረተ ቢስ ቅጥፈት ነው ብለዋል።

[4ኛ]፡-
خمس ليال لا ترد فيهن الدعوة أول ليلة من رجب، وليلة النصف من شعبان، وليلة الجمعة، وليلة الفطر، وليلة النحر
“አምስት ሌሊቶች በነሱ ውስጥ የተደረገ ዱዓእ አይመለስም። የመጀመሪያው የረጀብ ሌሊት፣ የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት፣ የጁሙዐ ሌሊት፣ የዒደል ፊጥር ሌሊት እና የዒደል አድሓ ሌሊት ናቸው።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 1452] [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 2852]

[5ኛ]፡-
رجب شهر عظيم يضاعف الله فيه الحسنات، فمن صام يوما من رجب، فكأنما صام سنة، ومن صام منه سبعة أيام، غلقت عنه سبعة أبواب جهنم، ومن صام منه ثمانية أيام، فتحت له ثمانية أبواب الجنة، ومن صام منه عشرة أيام، لم يسأل الله شيئا إلا أعطاه إياه، …
“ረጀብ አላህ መልካም ምንዳዎችን የሚያነባብርበት ታላቅ ወር ነው። ከረጀብ አንድ ወር የፆመ ሰው አመት እንደፆመ ነው። ከሱ ሰባት ቀናትን የፆመ ሰባቱ የጀሀነም በሮች ይዘጉለታል። ከሱ ስምንት ቀናትን የፆመ ስምንቱ የጀነት በሮች ይከፈቱለታል። ከሱ አስር ቀናትን የፆመ አላህን የሆነ ነገር አይጠይቅም፣ እሱኑ የሰጠው ቢሆን እንጂ፣ …” አልባኒ “መሰረተ ቢስ” ብለውታል። [አዶዒፋህ፡ 5413]

[6ኛ]፡-
إن في الجنة نهرا يقال له رجب ماؤه أشد بياضا من اللبن وأحلى من العسل من صام يوما من رجب سقاه الله من ذلك النهر
“በጀነት ውስጥ ረጀብ የሚባል ወንዝ አለ። ውሃው ከወተት የነጣ፣ ከማር የጣፈጠ ነው። ከረጀብ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ ከዚያ ወንዝ ያጠጣዋል።” አልባኒ “መሰረተ ቢስ” ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 1902]

[7ኛ]፡-
صوم أول يوم من رجب كفارة ثلاث سنين، والثاني كفارة سنتين، والثالث كفارة سنة، ثم كل يوم شهرا
“የረጀብን የመጀመሪያ ቀን መፆም የሶስት አመት ወንጀል ያብሳል። ሁለተኛው የሁለት አመት ያብሳል። ሶስተኛው ደግሞ የአመት ያብሳል። ከዚያም እያንዳንዱ ቀን የወር ነው።” አልባኒ ደካማ ብለውታል። [ዶዒፉል ጃሚዕ፡ 3500፣ 5649]

[8ኛ]፡-
لا تغفلوا عن أول جمعة من رجب فإنها ليلة تسميها الملائكة الرغائب
“ከረጀብ የመጀመሪያ ጁሙዐ አትዘናጉ። እርሷ መላእክት ‘አረጋኢብ’ ብለው የሚጠሯት ሌሊት ነች።”
‘ሶላተ ረጋኢብን’ በተመለከተ ነወዊይ እንዲህ ብለዋል፡- “እርሷን የፈጠረን ሰው አላህ ይርገመው! እርሷ አስቀያሚ ቢድዐ ነች!” [ሸርሑ ሙስሊም] በተጨማሪም እሷንና የሸዕባን አጋማሽ ሌሊት ሶላትን አስመልክተው “… ቢድዐና አስቀያሚ ፈጠራዎች ናቸው። በ‘ቁቱል ቁሉብ’፣ ‘ኢሕያእ ዑለሚዲን’ ኪታብ ውስጥ ስለተጠቀሱ ማንም እንዳይሸወድ። እነሱን በሚጠቁመው ሐዲሥም እንዲሁ (እንዳይሸወድ)። ምክንያቱም ሁሉም ውድቅ ነውና” ብለዋል። [አልመጅሙዕ፡ 3/548]

[9ኛ]፡-
أن رسول الله -ﷺ- لم يصم بعد رمضان إلا رجبًا وشعبان
“የአላህ መልእክተኛ ከረመዷን በኋላ ረጀብንና ሸዕባንን እንጂ አልፆሙም።” ኢብኑ ሐጀር በጣም ደካማ ነው ብለውታል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 12]

[10ኛ]፡-
من صلى المغرب في أول ليلة من رجب ثم صلى بعدها عشرين ركعة يقرأ في كل ركعة بفاتحة الكتاب، وقل هو الله أحد مرة، ويسلم فيهن عشر تسليمات، أتدرون ما ثوابه؟ قال: حفظه الله في نفسه وأهله وماله وولده، وأجير من عذاب القبر، وجاز الصراط كالبرق بغير حساب ولا عذاب
“በረጀብ የመጀመሪያ ሌሊት መግሪብን ሰግዶ ከዚያም በእያዳንዷ ረከዐ ፋቲሐንና ቁል ሁላሁ አሐድን አንድ ጊዜ እየቀራ፣ በአስር ተስሊማት እያሰላመተ ሃያ ረከዐ የሰገደ ሰው ምንዳው ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? አላህ በነፍሱም፣ በቤተሰቡም፣ በገንዘቡም፣ በልጁም ይጠብቀዋል። ከቀብር ቅጣትም ይጠበቃል። ሲራጥንም ያለ ሂሳብና ያለ ቅጣት እንደ ብልጭታ ያቋርጧል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/123] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 20]

[11ኛ]፡-
من صام من رجب وصلى فيه أربع ركعات ... لم يمت حتى يرى مقعده من الجنة أو يُرى له
“ከረጀብ ፁሞ፣ በሱ ውስጥ አራት ረከዓዎችን የሰገደ ሰው … በጀነት ውስጥ መቀመጫውን ሳያይ ወይም ሳይታይለት አይሞትም።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/124] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 21]

[12ኛ]፡-
إن شهر رجب شهر عظيم، من صام منه يومًا كتب الله له صوم ألف سنة ...
“የረጀብ ወር ታላቅ ወር ነው። ከሱ አንድ ቀን የፆመ ሰው አላህ አንድ ሺ አመት ፆም ይመዘግብለታል።” ኢብኑል ጀውዚና ኢብኑ ሐጀር መሰረተ ቢስ ቅጥፈት እንደሆነ ገልፀዋል። [አልመውዱዓት፡ 2/206-207] [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 26]

ከረጀብ ጋር የሚያያዙት ዘገባዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም። እነዚህን ለምሳሌ ያክል ይዘን ሌሎቹንም ጭምር በሚመዝን የዓሊሞች ንግግር ልቋጭ:—
1/ አልሓፊዝ ኢብኑ ሐጀር - ረሒመሁላህ - “የረጀብን ወር ልዩ ብልጫም፣ መፆሙን ወይም ከፊሉን በተለየ እንዲፆም፣ ወይም ከሱ ውስጥ የተገደበን ሌሊት በሶላት ማሳለፍን፣… የሚጠቁም ለማስረጃነት የሚበጅ ትክክለኛ ሐዲሥ አልተላለፈም" ብለዋል። [ተብዪኑል ዐጀብ፡ 6 እና 8]
2/ አልሓፊዝ አቡ ዐብዲላህ ሙሐመድ ኢብኑ አቢ በክር አዲመሽቂይ (691 ሂ.) ደግሞ “እያንዳንዱ የረጀብን ፆም እና ከፊል ሌሊቶቹን መስገድን የሚጠቁም ሐዲሥ ውሸት፣ ቅጥፈት ነው” ብለዋል። [አልመናሩል ሙኒፍ፡ 1/96]

ልብ በሉ! በዚህ ወር ውስጥ ፆምና ሶላት አይኑር ለማለት አይደለም። ወሩን ከሌሎቹ ወራት በተለየ መልኩ መያዝ አይገባም ነው አጠቃላይ ጭብጡ።

የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/IbnuMunewor
በአላህ ስም

*🍃 4ቱን እዝነትህን አትንፈጋቸው*

① ሚስትህን
② ልጆችህን
③ ቤተሰብህንና
④ ጓደኞችህን

*🍃 4 ነገሮችን ቀንስ*

① እንቅልፍን
② ምግብን
③ መሰላቸትንና
④ ንግግርን

*🍃 4ቱ ላይ አትጨክንባቸው*

① የቲም ላይ
② ሚስኪን ላይ
③ ድሃ ላይና
④ ህመምተኛ ላይ

*🍃 4 ሰዎችን ቅረባቸው*

① ሙኽሊስ የሆነ ሰው
② ቃሉን ጠባቂ
③ አዛኝንና
④ ታማኝን

*🍃 4 ሰዎችን ራቃቸው*

① ጃሂልን
② ተከራካሪን
③ ቂልንና
④ ባዶን

*🍃 4 ሰዎችን ጓደኛ* አታድርጋቸው

① ውሸታምን
② ሌባን
③ ምቀኛንና
④ ራስወዳድን

*🍃 4 ነገሮችን አትቁረጣቸው*

① ሰላት
② ቁርአን
③ ዚክርንና
④ ዝምድናን

*🍃 በ4ቱ ተዋብባቸው*

① በትእግስት
② በቻይነት
③ በእውቀትና
④ በቅንነት

*🍃 ከ4 ነገሮች በአላህ* ተጠበቅ

① ከትካዜ
② ከሀዘን
③ ከድብርትና
④ ከስስት

*2, ፊትህ እንዲበራ ትፈልጋለህ ?*

®= የሌሊት ሶላት አደራ ፡፡

3, ጤና ትፈልጋለህ ?

_®= ፆምን አጥብቀህ ያዝ ፡፡_

_4, ከጭንቅ ለመዉጣት ትፈልጋለህ ?_

_እሥቲግፋርን እንዳትለቅ ፡፡_

_5, ትካዜን ማሥወገድ ትፈልጋለህ ፡፡_

_ዱአን ሙጭጭ አድርገህ ያዝ ፡፡_

_6, የህይወትን አድካሚ ችግሮች ለማሥወገድ ትፈልጋለህ ?_

_®= "ላሀወላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ " ማለት አብዛ ፡፡_

_7, በረካ ትፈልጋለህ ?_

_®= በነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሠለም ) ላይ ሠለዋት አዉርድ ፡፡_

_8, ዘና ማለት ትፈልጋለህ_ ?

_®= ቁርአንን ረጋ ብለህ በማሥተንተን አንብብ ፡፡_

_9, ያለ ድካም አጅር ትፈልጋለህ ?_

_®=አንብበህ ሥትጨርሥ ለሌሎች ሼር አድርግ_
የሠው ልጅ ከስልጣኔ ጫፍ ላይ ለመድርስ አስተሳሠቡን ብቻ
መለወጥ በቂ ነው ። ነቢዩ ሙሀመድ የአሪቦችን አስተሳሠብ
ለውጠው ነው ከስልጣኔ ጎዳነ ያደሪሡት ። አስተሳሠብ ሲለወጥ
ደግሞ ስልጣኔ መምጣቱ የማይቀር ጉዳይ ነው ።
የሠውን ልጅ አስተሳሠብ ለመለወጥ ደግሞ ከእስልምና
በላይ ምንም ሀይል የለም ።
=መሠልጠን ማለት ፦ እውነተኛውን የአላህን መንገድ እና የነቢዩን ትእዛዝ መከተል ማለት ነው
ስልጣኔ ፦ ለሠው ልጅ የሚጨነቅ -ወደ አንድነት የሚጣር
ለመኸሉቅ ሁሉ የሚያዝን- የዛሬን ላይሆን የነገን ስኬት የሚያስብ ካልሆን ስልጣኔ አይባልም ።
፡ እስልምና ደግሞ አኾላቅ - ሠብር - ውዴታ - ፍቅር
እውነትን እንደ ግብአት ነው የሚጠቀማቸው ። እና ታዲያ የስልጣኔ ማማ ላይ ለመድሪስ - ከእስልምና በላይ ምን አለ? ወደ ስልጣኔ - የሚወስደን በቸኛው መንገድ የእስልምና ደልዲይ በቸ ነው ።
Audio
ክፍል 8
Audio
ክፍል 9
Audio
ክፍል 7
✩.. የአኼራ ስንቅ..✩:
✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩
ጭብጥ ለማትሞላ ለዱኒያ ጓጉቸ፣
ሀብት ለመሰብሰብ ሌት ቀኑን ለፍቸ፣

በአዱኒያ ፍቅር ጥማት ተጎድቸ፣
ከአሏህ እንዳርቅ ኢልቢስን ሰምቸ፣

በወንጀል በአመፅ ልኑር እስከመቸ፣
በአሏህ አንድነት በፍቅሩ ፀንቸ፣

በነብዩ መንገድ በኢስላም በርትቸ፣
ሞቴን ያድርግልኝ ሸሀዳን አግኝቸ፣
✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩✩

JOIN
´´´´´´´ :¨·.·¨: ❀ share
አላህን በማውሳት የነገውን ቤታችን እንገንባ

ኢብኑል ቀይም እንዲህ ይላሉ:—

"የጀነት ደረጃዎች አላህን በማውሳት( በዚክር) ይገነባሉ። የሰውየው ምላስ አላህን ማውሳት ባቆመች ጊዜ መልዐክቶችም ደረጃውን መገንባት ያቆማሉ
( አል—ዋቢሉ ሰይብ

°• https://t.me/httpsLatahzen