La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ወንድሜ ሆይ : ስለ ሴት ከጠየቁህ : በላቸዉ ።
☞ እሷ ነፍስ እንጂ አካል አይደለችም ።
☞ አዋቂ እንጂ መሀይም አይደለችም።
☞ ቅን እንጂ ሞኝ አይደለችም ።
☞ መልካም እንጂ ክፉ አይደለችም ።
☞ አላህ ለአደም የፍጠራት ዉድ ፍጡር ናት ።
☞ የፈጣሪ ሥጦታ እንጂ ምርጫ አይደለችም ።
ቀናን ሀበ ሾቹ


ይሀው ድፍን አለም ሙስሊም የተባለ
በአፍሪካም በኤሺያ ሁሉም ቦታ ያላ
ረሡል መሀመድን አወቅለሁ አለ
ሁሉም ባንድ ጮሁ ምላየትን ተመኙ
አፍቃሪ ነን ብለው ሲጮሁ ተገኙ
በጀነት ጎረቤት ሆነው እንዲገኙ
እስኪ አድምጡኝ አወነት ልንገራቹህ
ሺ ጊዜ ቢድሙ። ሀቢበናን ወዳው
አላይ ታች ቢሉ በሙሀባ አብድው
ፍቃራ ቸውን ቢገልፁ ቃለትን አከብድው
በረሡሉ ፍቅር በረሡል ውዴታ
ማነው ያሚሠላፍ ከሀበሾች ተርታ
ማነው ከልብ ወዳ እኛን ያሚረታ
ማን ነው ያሚበልጠን እኛን ብዝምድና
እምቡጥ ለጋ እያሉ ማን አንደገና
አቅፎ ደግፎ ማን ተንካባከበና
ደርቱ ላይ አርጎ ማንስ አቀፈና
እ። ና። ት።

እናት የሚለዉ ስም ራሡ እኮ የሆነ ደስ የሚል ስሜት ይፈጥራል። እናት ማለት እኮ ሀገር ናት። እናት ማለት እኮ ትዉልድ ናት። እናት ማለት እኮ ህዝብ ናት። እናት እኮ ማህበረሠብ ናት። በዐጠቃላይ እናት ማለት እኮ። ። ። ። ። እናት ናት። የአንድን ነገር ጥሩ ሥብዕና ለመግለፅ እናት ከሚለዉ ቃል በላይ ምን ምርጥ ምሣሌ አለ? እናትነት እኮ ክብር ነዉ። እናትነት እኮ ምሣሌንት ነዉ። እናትነት እኮ ጀግንነት ነው። የእናትነትን ሥሜት የሚያዉቁት እናቶች ብቻ ናቸዉ። እናት ማለት እኮ.......ቃላት የማይገልፇት ልዩ ፍጡር ናት። ጤና እና እድሜ ለእናቶቻችን። ። ። ። ። ። ።
#አይሰጥም_ልቦና__!!
---------------------------------
በአባቶች አደራ በቀደምቶች ምክር፡
ሁላችን በአንድነት አንድ ሀቅ እንዘክር፡
ከቃል የዘለለ በተግባር እንመስክር፡
ቆራርጠን እንጣለው የሽርክን ትብትብ ክር፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
የሸይጧንን ወጥመድ የሸረሪቱን ድር፡
በሱና እናፍርሰው የቢዲዓን ድድር፡
በሀቅ አንቀልድ ይቅርብን ድርድር፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ቆርጠን እንነሳ እንጠንክር እንፅና፡
በነብያት ፈለግ በተውሒድ በሱና፡
የቀደምት አባቶች አደራ ሰጥተዋል፡
የኢስላምን መልዕክት ለኛ አበርክተዋል፡
ብዙ ጭቆናና ብዙ ግፍ ችለዋል፡
ደማቅ አኩሪ ጀብዱ ውብ ታሪክ ሰርተዋል፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ከስህተታችን ቆርጠን እንመለስ፡
ከባጢል ተሰደን ወደ ሀቅ እንፍለስ፡
በሱና ክልል ውስጥ እንበል መለስ ቀለስ፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼
ለልጅ ያስረከቡት የአባቶች አደራ፡
ዘውታሪ የሆነ ከዱንያ እስከ አኸይራ፡
እኛም በምክራቸው ጠንክረን እንፅና፡
አባት ምክር እንጅ አይሰጥም ልቦና፡
⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼⁼


2014 በኑር አህመድ
ኢላሂ

ዱዓችንን ማሳመር ባንችል እንኳ
ሓጃችንን አንተ ታውቃለህ ።

 ምላሣችንን ቢንተባተብም
ሀሳባችንን ትረዳለህ።

አንደበታችን ቢተሳስርም
ምኞታችንን ታውቃለህ ።

የቱን ያህል ብናስመስልም
ውስጣችንን ታነባለህ።

ከኛ ጉዳይ ካንተ የተደበቀ ምን ነገር አለ!
ብናሳይህ ባናሳይህ ምን ይሳንሃል ጌታዬ

ደክሞኛል ደግፈኝ ያ ረቢ
ከፍቶኛል ጠግነኝ ፈጣሪዬ
ሆድ ባሠኝ ዳብሠኛ አካሚዬ!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የቢድዓ መልካም አለውን

💡ቢድዓ መስራት በውስጡ የያዘው ከባድ መልክት

💡ቢድዓ የሚሰሩ ሰዎች ግን ይህን መልእክት አስበውበታል?

💡የዑመር ኢብኑል ኸጣብን ንግግር መረጃ አድርገው የሚያቀርቡ ሰዎች ይህን ሳይሰሙ እንዳታልፉ!

💡ኢማሙ ማሊክ ስለ ቢድዓ ያሉትን ሰምተክ ታውቃለህን?

💡በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ
አስገራሚ ቂሷ❗️

ዒሻእ ሰላት ተሰግዶ ጥቂት ደቂቃዎች እንዳለፉ አንድ ወጣት ከወደ ውጭ በኩል ይጮህና የመስጅዱን ጀማዓ ይጠራል።ሰዉ ግር ብሎ ልጁን ተከትሎ ሲወጣ አንድ እድሜው 20 ማይሞላ ልጅ ባቡር ገጭቶት አካሉን ለሁለት ከፍሎታል (ሱብሀን አላህ) ግን ሩሁ አልወጣችም ሊሞት ጣር ላይ ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከተሰበሰቡት አንዱ ጎንበስ ብሎ የልጁን ጭንቅላት በእግሩ ላይ አስቀመጠው።
"ላ ኢላሀ ኢለላህ በል... ላ ኢላሀ ኢለላህ በል"
ይለውም ጀመር...
ልጁ ሩሁ ልትወጣ ጥድፊያ ላይ ናት ይፈራገጣል...እናም የአላህ ተውፊቅ ሆነና
ልጁ " ላ ኢላሀ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ" እንዳለ ሰውነቱ ቀዘቀዘ ትንፋሹ ዳግም ላይመለስ ተቋረጠ ነፍሱም ወደ ፈጣሪዋ አመራች።
(ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን)

ተባብረው ልጁን ሰዎች ወደሚበዙበት አካባቢ ወሰዱት ቤተሰቡን ለማፈላለግ...
ሌሊቱ ጨለማማ ነበር ፅልመቱ ያስፈራል ብርሀናማ ቦታ ሁነው ልጁን የሚገልፁ ነገሮችን ልብሶቹን በመጠቀም ቤተሰቡን ያፈላልጉ ጀመር...
ድንገት በቦታው ከነበሩት አንዱ የአስክሬኑን እጅ ይዞ ፦"ይህ ልጅ ክርስቲያን ነው አንገቱ ላይ መስቀል ይኸው..." እያለ ጮኸ።
ሁሉም ግራ ተጋባ "ይህ ልጅ በተውሂድ ነው የሞተው ታድያ እኛው በሙስሊሞች መቃብር እንቅበረው ወይስ ለቤተሰቦቹ አስረክበን በክርስቲያኖች መቃብር ይቅበሩት?"
እያሉ ይወያዩ ጀመር..
ቤተስቦቹ ጋ ለመውሰድ ይወስኑና ተሸክመውት በእንባ ወደቤተሰቦቹ ጉዞ ጀመሩ።
ልጁ መስጅድ አካባቢ ስለሞተ አስክሬኑን ያጀቡት ሁሉም ሙስሊሞች ነበሩ።
ተሸክመውት ከአከባቢው ሲደርሱ አባቱም የልጁን ማረፍ ሰምቶ ሲገሰግስ አገኙት አባትየውም ሲያያቸው ተንሰቅስቆ ያለቅስ ጀመር (እንዴት አያልቅስ ተስፋ ይሆነኛል፣ረዳት ይሆነኛል፣መመኪያ ይሆነኛል ብሎ የሚጠብቀው ልጁ ከሰዎች ትከሻ ላይ ተጭኖ ሲመጣለት...)
ልጁን አቅፎ አምርሮ ያለቅሳል...

ይህ ሁሉ ሙስሊም ልጁን ተሸክሞ መምጣቱ ያስገረመው አባት እያለቀሰ ለተሰበሰበው ሰው እንዲህ አላቸው፦
"ይህን ስነግራችሁ በህፍረት ነው...ልጄ እንዲው ቁርአን መስማት ይወዳል። አዎ ልጄ በርግጥ ክርስቲያን ነው ነገር ግን የሙስሊሞችን ቁርአን መስማት ይወዳል።
ዘውትር ክፍሉ ስገባ ኢርፎን/earphone ከጆሮው አያለው...
"ምንድነው ምትሰማው?" ስለው
"ዘፈን ነው"ይለኛል
ከጆሮው ነቅዬ ሳዳምጥ ግን ቁርአን ነው።
በጣምም እቆጣው ነበር
ይሄን መስማት ካልተውክ እገድልሀለሁ እያልኩ ሁሌም አስጠነቅቀውም ነበር...
"ባባ እኔን መግደል አትችልም ቁርአን መስማትም አትከልክለኝ" ይለኝ ነበር..
በቦታው ያሉት ሁሉ እየተያዩ ይለቃቀሱ ነበር።
"ልጅህ እኮ በሸሀዳ ነው የሞተው" ብለው ሲነግሩት...ያ የልጁ መሞት ቅስሙን የሰበረው አባት ያ የልጁን ሬሳ አቅፎ ቁጭ ያለው አባት
እንባውን እያረገፈ ልጁን በስስት እያየ እንዲህ አለ፦
"ልጄ በመሰከረው ነገር እኔም እመሰክራለሁ ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለ ሙሀመድም የ አላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እመስክራለሁ"

ከዚያም ሁሉም ጀማዓ ጀናዛውን ይዘው ወደ ሙስሊሞች መቃብር "ላ ኢላሀ ኢለላህ... ላ ኢላሀ ኢለላህ.... ላ ኢላሀ ኢለላህ" እያሉ አጅበው ወስደው ቀበሩት።
__________________________
ሙስሊም ሆኖ ኖሮ በኩፍር መሞትም አለና ካፊር ሆኖ ኖሮ በተውሂድ መሞትም አለና "አላህ ካቲማችንን ያሳምርልን"
ምንጭ፦ ﻫﻨﺎ ﺃﺑﻨﺎﺀ ﻋﺎﺋﺸﺔ ﺃﻡ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨ
➧መልካም ጓደኛ
➫➫➫➫➫➫

➻ሁለት ውብ የሂወት ኡደቶችን ይለግሰሀል… "አንደኛው እዚህ ዱንያ ላይ ሲሆን" "ሁለተኛው ደግሞ ጀነት ውስጥ ይሆናል"

➧መልካም ጓደኞች «ወደ አሏህ መንገድ… ይጠሩሀል…» «ከጠፋህባቸው… ይፈልጉሀል…» ከተዘናጋህ… አስታውሱሀል»

«…በዱአቸው ውስጥ…ያካቱሀል»
«ልክ እንደ ከዋክብቶች… መርከብህ መንገድ ከሳተች…ይመሩሀል…» «ነገ ከአሏህ አርሽ ስር…ኢንሸአላህ…ይጠብቁሀል…» «ጀነት ውስጥ ፈልገውህ ካጡህ…

➧አሏህን ወደነሱ እንዲቀላቅልህ ይለምኑልሀል» "አሏህ ሶሊሆቹን አድርጎ ከሶሊሆቹ ያወዳጀን ከሶሊሆቹ ጓደኞቻችን አይነጥለን በያሉበት ይጠብቅልን "

#መንቁል

➛ያአላህ ምንኛ መታደል ነው እንደዚህ አይነት ጓደኛ ማገኘት አላህ ይወፍቀን እኛንም መልካሞች ያድርገን!!
ኢላሒ ሰትረን

ኢብኑ አል-ቀይም "በሆነ ወንጀል ሰውን ያነወረ ሰው ያንን ወንጀል ሳይሰራው አይሞትም" ይላሉ።
መሳደብም ሆነ መሳለቅ መልካም አይደለም። ሰውን መሠተር ነው እንጂ ማዋረድ ትርፍ የለው።
...
ዐብደላህ ኢብኑ መስዑድ ደግሞ
"በውሻ ባሾፍ እንኳ ውሻ እንዳልሆን ብዬ እፈራለሁ፡፡"
.
ደጋጎችና ጥንቁቆቹ እንዲህ ናቸው። በሰው ነውር ላይ ሙድ አይዙም፤ አላህ በፈተነው ሰው አያላግጡም፣ በአፈጣጠሩም ሆነ በእንከኑ አያሾፉም፣ ያጠፋውን ቀርበው ይመክሩታል እንጂ አያሙትም፣ አይስቁበትም።
...
ሷሊሖቹ ሰዎች የጠፉት እንዴት እንደጠፉ ሳይሆን ነጃ የወጡት እንዴት ነጃ እንደወጡ ነው ጭንቀታቸው። ዛሬ በሰው ወንጀል የምትስቁ ነገስ እናንተ ላለመሥራታችሁ ምን ዋስትና አላችሁ!!
አላህ ይሠትረን።
▪️ከሰለፎች ውስጥ አንዱ እንዲህ ብሏል።

♦️ሁለት ነገሮች፦
①) ሞትንና
②) አላህ ፊት መቆምን ማስታወስ
የዱንያን ጥፍጥና ቆርጠውልኛል፦

📚 لطائف المعارف [244]
▪️ቢሽር ቢን አልሀሪስ አላህ ይዘንለትና እንዲህ አሉ።

ሰዎች ዘንድ እንድትወሳ ብለህ ምንም አትስራ። መጥፎ ስራህን (ሰዎች እንዳያውቁብህ) እንደምትደብቀው ሁሉ መልካም ስራህንም ደብቅ።

📚 [ سير اعلام النبلاء ]
◾️ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

አንድ ሴት ሸሪአዊ በሆነ መልኩ ሊያጫት ፈልጎ ሊያያት ለሚመጣ ሰው ሜካፓችን መጠቀም አይፈቀድላትም። ምክንያቱም ይህ ነገር ማታለልና የፊት ማጭበርበር ነው።

📚فتاوى نور على الدرب
🟣 ዱንያን መተው ማለት
ብዙ ሰዎች ዱንያን መተው ማለት ደረቅ ነገር መመገብና ሸካራ ነገርን መልበስ ንፅህናን አለመጠበቅ ራስን መጣል አድረገው ይገምታሉ ይህ እይታ ስህተት መሆኑን ታላቁ ታብዕይ ሱፍያን አስሰውርይ እንዲህ ብሎ ይነግረናል : –

قال سفيان الثوري رحمه الله تعالى :
" ليس الزهد بأكل الغليظ، ولبس الخشِن، ولكنّه قِصَر الأمل، وارتقاب الموت".

(سير أعلام النبلاء: ٦/٦٣٠)

" ዙህድ ( ዱንያን መተው ማለት ) ጠንካራ ነገር መብላትና ሸካራ ነገር በመልበስ አይደለም ።
ነገር ግን ዙህድ ማለት ምኞትን ማሳጠርና ሞትን መጠባበቅ ነው " ።
ሲየር አዕላሙ ኑበላእ ( 630 / 6 )
🌺
አቡበክር አስሰዲቅ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ ተናግረዋል፦

"እናንተ ሰዎች ሆይ! የሚከተለውን የቁርኣን አንቀጽ ታነባላችሁ፡-

{ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ اﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮا ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺃَﻧﻔُﺴَﻜُﻢْ ۖ ﻻَ ﻳَﻀُﺮُّﻛُﻢ ﻣَّﻦ ﺿَﻞَّ ﺇِﺫَا اﻫْﺘَﺪَﻳْﺘُﻢ... }

{እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁን (ከእሳት) ያዙ፤ (ጠብቁ)። በተመራችሁ ጊዜ የተሳሳተ ሰው አይጎዳችሁም…}5:105

የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ)፦

{ሰዎች ግፈኛን እየተመለከቱ (ከግፍ ተግባር እንዲቆጠብ) እጁን ካሊያዙት አላህ አጠቃላይ ቅጣት ያወርድባቸዋል ሲሉ አድምጫለሁ}
ቲርሙዚይ ዘግቦታ
ዐብደላህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ ነቢይ እንዲህ ብለዋል፡- ሙስሊም የሚባለው በምላሱና በእጁ ሙስሊሞችን ከመጉዳት የታቀበ (ነፃ የሆነ) ሰው ነው፡፡ ‹‹ሙሃጂር›› (ስደተኛ) የሚባለው ደግሞ አላህ የከለከለውን ነገር ሁሉ የተወ ነው፡፡

(ቡኻሪ ዘግበውታል)
💜 ከምትጠላው ነገር አላህ ሲያድንህ
ሱብሂ/ፈጅር ሰላትን ስለሰገድኩ ነው ፣
ሰደቃ ስለሰጠሁ ነው ፣ ዚክር ማዘውተሬ ነው
ወይም ጥሩ ጥሩ ስለማስብ ነው አትበል‥
⇘ አላህ በእዝነቱ አዳነኝ ብለህ አመስግን ።
 
(فَلَمَّا جَاءَ أَمْرُنَا نَجَّيْنَا صَالِحًا وَالَّذِينَ آمَنُوا مَعَهُ بِرَحْمَةٍ مِنَّا)
" ትዕዛዛችንም በመጣ ጊዜ ሷሊህንና እነዚያን ከሱ ጋር ያመኑትን ከእኛ በሆነው እዝነት አዳን ። "
[ሁድ 66]
💚 ህይወት የፈለገ ያህል ከባድ
ጭንቀተማና አድካሚ ብትሆንም
ሁለት ደስ የሚሉ ጣእምን የሚሰጧት
ነገሮች አሉ ‥ እንሱም
⇘ አላህን ማውሳት እና ለአላህ ብሎ
ከሚወድህ ልብ የሚመጣልህ ዱዓእ ነው ።
አቡ ሙሳ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ሶስት ሰዎች ድርብ ሽልማት ይኖራቸዋል፡-
1) የመጻሐፍቱ ባለቤት (ክርስቲያን ወይም አይሁድ) ሆኖ ሳለ በተላከለት ነቢይ (በኢየሱስ ወይም በሙሴ) ያመነና በሙሐመድ ያመነ፡፡
2) የአላህንና የአሳዳሪውን ሐቅ የሚጠብቅ ባሪያ
3) ሴት ባሪያውን መልካም ስነ ምግባርና ጥሩ ትምህርት ካስተማረ በኋላ ነፃ በማውጣት ያገባ፡፡

(ቡኻሪ ዘግበውታል)
አውፍ እንባባል

ጥቂት ቀናት ቀረው ረመዳን ሊገባ
እርስ በርሳችንም ይኑረን ሙሀባ
ነሻጣም ይኑረን እንዳንሆን ጀዝባ

ተውበትንም እናርግ ረመዳን መጥቷል
አሁን ወዲያው ፈጥነን አውፍ እንባባል

በቅድሚያም ከራሴ እኔ እጀምራለው
ላስቀየሙኝን ሰዎች አውፈን ብያለው

አውፍ በዮችን ይወዳል ጌታችሁ
አውፍ በሉኝ እኔን ለአላህ ብለችሁ

ስሙንም እንስቼ እኔ ካማሁት
የሰውነት ክብሩን ከነካሁበት
አውፈን ይበለኝ በጥቂት ቃላት
Audio
ክፍል 6