La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
# ስንት አይነት ለጋሽ አለ


1 /ከ አላህ (ሱ.ወ) አገኘዋለዉ ብሎ ሚነይት


# ሚስኪኖችን በመንከባከብና በመርዳት የሰራውን በጎ ተግባር ከሰዎች ሙገሳና አድናቆትን ሳይሻ ከብቸኛው ጌታ ከጠየቁት ማይከለክል መልካም ነገር ለሰሩት ምንዳዉን እጥፍ ድርብ አርጎ ሚከፍለዉ ከ (ዐ.ሱ.ወ) ብቻ ሚጠብቅ ለርሱም ሚያገለግል ነው።




2/ ታዋቂ ለመሆን

# አሁን ያለንበት ጊዜ የተደፉን አንገት ቀና አርጌ እንዴት ላስደስት ሳይሆን ምን አርጌ ታዋቂ ልሁን ሚለዉ ነው ያሳሰበን።
ጊዜው ካመጣቸው ነገሮች አንዱ social mdia ነው። Tik tok you tube የመሳሰሉት ናቸዉ።

ይሄን ያህል ሰጠው ይሄን ያህል ልሰጥ ነው እያሉ በ አላህ ዘንድ ሳይሆን በሰዎች ዘንድ ተወዳጅ ለመሆን ቀን ከሌት ሳይሉ ይተጋሉ። በሰሩት ልክ አላህ ሳይሆን የሰው ልጅ የሚከፍላቸው ይመስላል።

#የሰው ልጅ ሆኖ followe ለመሰብሰብ በነኚህ ሰዎች መነገድ ግን አይከብድም ?????🤔 ሆኖም ግን ለመልካም ነገር ምንጠቀም እንዳለን ሁሉ ለመጥፎ ነገር ሚጠቀምም አይጠፋም።


3/ ሰው ሲሰጥ ብቻ የሚሰጥ
#የሚሰጠዉ ነገር ለዛ ሰዉ ምን ያህል ዋጋ እንዳለው ፈፅሞ ማያዉቅ።
#ለኛ ትንሽ ነው ብለን የምንሰጠው ነገር የእውነት ለዛ ሰው ምን ያህል ትልቅ አንደሆነ የምናውቀው ከልባችን ስንሰጥ ነው።

#ለምሣሌ፦ የርሀብን ሥሜት የምናውቀው ቤታችን ውስጥ አደለም ምግብ የምግብ ስም የማይነሳበት ደረጃ ደርሶ ስንራብ ነዉ።

#የ ችግርን ሥሜት ምናዉቀው ዓጊኝቶ ማጣትን ስናይ ነዉ።

# የህመምን ስሜት ምናዉቀው ታሞ መዳንን ስናይ ነው።

#እንደዉ ለቁጥር ያክል እነዚህን አልን እንጂ ሁሉም የሚሰድቅበት ምክኒያት አለው። ከሰጠን አይቀር ግን አላህ (ሱ.ወ) በሚያዘን መንገድ ብንሰጥ ይበልጥ ተጠቃሚዎች እንሆናለን።


"አንብብ በዚያ (ሁሉን)በፈጠረዉ ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳንሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘት እንኳን" ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)




https://t.me/httpsLatahzen


Bint Mohammed
#ለምን ግን አመስጋኝ መሆን ተሳነን??????????

የ ሰው ልጅ ሆንን ና ዝቅ ብለን ኖረን ካላየን ያለንበትን አናመሰግንም ።

#ያለንበት ህይወት ምንም ይሁን ምን አልሀምዱሊላህ ማለት ነው።አመስጋኝ ባርያ በሆንን ቁጥር አላህ (ሱ.ወ) ካለን ላይ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይሰጠናል።

#እስኪ ለማስተዋል እንሞክር በአሁኑ ጊዜ እኛ በቀን 3 ከዚያ በላይ እየበላን በቀን አንዴ በልቶ ማደር የከበደዉ ስንት አለ??????


#አኛ ልብስ ተርፎ ሞልቶን ምን እንደምናረገው ግራ ይገባናል
ግን ሙሉ ሰውነቱን በቅጡ ሚሸፍንለት ልብስ ያጣ ስንት አለ?????


#ከዚ ሁሉ ሚገርመው ባንድ ሀገር ላይ ሁለት ሦስት ቦታ ላይ መኖሪያ ቤት ያለን ስንኖር ሌላው ማደሪያ ጎኑን ማሳረፍያ የሌለው ህዝብ ስንት አለ?????

#እንደሀቁ ከሆነማ እነዚህን ሁሉ እያየን

እናመሰግን ነበር ።

#ግን የሁላችንም አይን ዱንያ ላይ ብቻ ሆኖ የራሳችን እንጂ ሌላው አይታየንም ማንንስ አይተን እናመስግን አመስጋኝ ባሪያም ምንሆነው ከኛ በታች ያሉ ሰዎችን ዝቅ ብለን ኑሯቸውን ውሎአቸውን ስንመለከት አላህ (ሱ.ወ) የሰውን ልጅ ለማስተማር የሚጠቀምበት መንገድ እናይበታለን።

#እኛ እነሱን አይተን ከኔ የባሰም አለ አነሱም ሌላውን አይተው እንደዛው ሁሉም ያለበትን ደረጃ እያየ ምንያክል ደስተኛ እና እድለኛ እንደሆንን እንረዳ ነበር።

#አሁንም ቢሆን ለማመስገን ጊዜው አረፈደም። አላህ (ሱ.ወ) በሰጠን እያንዳንዱ ነገር ምን ያክል እድለኛ ደስተኛ እንደሆንን እያሰብን እናመስግን።
ምሥጋና የራህመት በር ነው ስናመሰግን ካለን ላይ ይጨመርልናል በቻልነው አቅም ባለን ነገር አልሀምዱሊላህ ብለን እንደር

አመስግነው ከሚያድሩት ባሪያ አላህ ያርገን🤲🤲🤲



"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from لاتحزن
አንድ ሙስሊም በሙስሊም ወንድሙ (ወይም እህቱ) ላይ ያለው ግዴታ በእስልምና አስተምህሮ ላይ የተመሰረተ እና ርህራሄን፣ ድጋፍን እና ሃላፊነትን ያጎላል። አንዳንድ ቁልፍ ነጥቦች እነኚሁና፡

1. ወንድማማችነት እና አንድነት፡- ሙስሊሞች በእምነት ወንድም እና እህቶች ተደርገው ይቆጠራሉ (ቁርኣን 49፡10)። ይህ ትስስር በማህበረሰቡ ውስጥ አንድነትን እና አንድነትን ያበረታታል.

2. መደገፍና መረዳዳት፡- ሙስሊም ወገኖቻቸውን በችግር ጊዜ በስሜታዊ ድጋፍ፣ በገንዘብና በአካላዊ እርዳታ መርዳት የሙስሊም ግዴታ ነው።

3. የበጎ ማበረታቻ፡- ሙስሊሞች እርስበርስ በመከባበርና ገንቢ በሆነ መልኩ በጎ ተግባርን (አማር ቢል መዓሩፍ) እንዲሰሩ መበረታታት እና ጥፋትን (ነሂ አኒል ሙንከር) ተስፋ ማድረግ አለባቸው።

4. ይቅርታና ትዕግስት፡- እስልምና ይቅርታንና ትዕግስትን አስፈላጊነት ያስተምራል። ሙስሊሞች የሌሎችን ስህተት በመመልከት ደግነትን ለመለማመድ መጣር አለባቸው።

5. መተማመንን እና ሚስጥራዊነትን መጠበቅ፡ መተማመን በማንኛውም ግንኙነት ውስጥ ወሳኝ ነው። ሙስሊሞች መተማመንን ማክበር እና የአንዱን ሚስጥር በአክብሮት መያዝ አለባቸው።

6.  የታመሙትን መጎብኘት እና የቀብር ስነስርአት ላይ መገኘት፡- ሙስሊሞች የታመሙትን እንዲጎበኙ እና በቀብር ሰላትና በቀብር ስነስርአት ላይ በመሳተፍ በአስቸጋሪ ጊዜያት ርህራሄ እና አጋርነት እንዲያሳዩ ይበረታታሉ።

7. እርስ በርስ መጸለይ፡- አንዱ ለሌላው ዱዓ ማድረግ (ልመና) ደጋፊ ማህበረሰቡን ማፍራት ትልቅ ድርሻ ነው።

8. ሰላምን ማስፋፋት፡- ሙስሊሞች በሙስሊም ወገኖቻችን መካከል ሰላምና እርቅ እንዲሰፍን፣ ግጭቶችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

በማጠቃለያው አንድ ሙስሊም ለሙስሊም ወገኖቹ ያለው ግዴታ ማህበረሰቡን የሚያጠናክር እና የተስማማ ማህበረሰብን የሚያጎለብቱ ደጋፊ ፣ሩህሩህ እና ስነ ምግባራዊ ባህሪያትን ያጠቃልላል።

   የሕያ ቢን أبي كثير እንዲህ ይል ነበር……

"አንድ ሰው ላይ ሁለት ነገሮች ካየህ ከጀርባቸው ከእነርሱ የበለጠ ኸይር እንደሚኖረው ዕወቅ;
1ኛው, ምላሱን የሚቆጣጠር ሲሆን
2ኛው, ሰላቱን የሚጠባበቅ ከሆነ"
      /ابن أبي الدنيا في الصمت ٥٦٤/

Ibnu muhammed
https://t.me/httpsLatahzen
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ያጀምዓ እንዴት ናችሁ
ዛሬ ማለትም 9/04/2017 ከምሽቱ 3:00 ሹራ ስለሚኖረን ኸይር ስራ መስራት ሚፈልግ በሀሳብም፣በጉልበት፣በገንዘብ፣በአልባሳት እንዲሁም አባል ሆኖ ከኛጋመስራት ሚፈልግ አብረን ሹራ እንድናረግ አልያም በወስጥ እንድታናግሩን እንደ አላህ ፍቃድ የቻለዉን ያክል ሰበብያውን እንድናደርስ ዘንድ የ ላታህዘን አሚሮች በአላህ ስም እንጠይቃለን🙏
አሰላሙ አሌይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ።
ሹራ የሚደረግበት ግሩፕ:-https://t.me/Latahezn
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ
#በአላህ ፍቃድ ስለ ተወደዱ ጾሞች ትንሽ ነገር እተዋወሳለን
#ክፍል,1
እነዚህ የጾም ዓይነቶች ለአላህ ምስጋና ይገባወና ምንዳን ማብዛት ለፈለገ ሰው ቁጥራቸዉ በጣም ብዙ ሲሆኑ ከነሱም መካከል ፦

#1.አንድ ቀን መጾም አንድ ቀን መፈሰክ፦ ይህ ጾም የነብዩላህ ዳውድ(ዐ.ሰ) ጾም ሲባል እሱም ከግዴታ ጾሞች ቡኋላ በጣም በላጩ ነው። ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ለአብደላህ ኢብን ዐምር (ረ.ዐ) እንዲህ ብለዋል፦

قال النبي(صلى لله عليه وسلم)، لعبد لله بن عمرو: "صم يومآ، وأفطر يومآ، وذللك صيام داود (عليه السلام)، وهو أعدل الصيام"

"አንድ ቀን ጹሙ አንድ ቀን ፈስክ ይህ የዳዉድ ጾም ሲሆን ይህ ፍትሀዊ ጾም ነው።(ቡኻሪ ቁጥር 1976፣ ሙስሊም በቁጥር ላይ 1159 ዘግቦታል)

#2.አያመ-ል-ቢይድን (ከየወሩ 13ኛ፣14ኛና 15ኛ ቀኖች) መጾም ፦
عن أبو هريرة رضي لله عنه قل:أوصاني خليلي بثلاث: "صيام ثلاثة أيام من كل شهر، وركعتي الضحى، وأن أوتر قبل أن أنام"
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) "ወዳጅ በሶስት ነገሮች መከሩኝ (በማለት) ከየወሩ ሶስት ቀን መጾም፣ ሁለት ረከአ የዱሀ ሶላት መስገድና ከእንቅልፉ በፊት የዊትር ሶላት መስገድ" (ቡኻሪ በቁጥር 1981 ሙስሊም በቁጥር 1981 ዘግበዉታል)"

#3.ሰኞና ሀሙስ መጾም ፦ የሰኞ ጾም ከሀሙሱ በጣም የጠበቀ ተጠይቀዉ ሲመልሱ እንዲህ ብለዋል፦


"ذاك يوم ولدت فيه، ويوم بعثت - أو أنزل علي_ فيه"
"ያ ቀን እኔ የተወለድኩበትና በመልዕክት የተላኩበት ወይም በእኔ ላይ ቁርዓን የወረደበት ቀን ነው። ብለዋል። (ሙስሊም 1162)


#በሌላ ዘገባ የረሱል ( ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ) ወዳጅ እና የወዳጃቸዉ ልጅ ኡሳማ ቢን ዘይድ (ረ.ዐ) "እርስዎ ሽማግሌ ነዎት ለምን የሰኞና የሀሙስ ቀንን ይጾማሉ?" ተብለዉ ሲጠየቁ " የአላህ መልክተኛ ሰኞና ሀሙስን ይጾሙ ነበር ለምን እንደሚጾሙ ሲጠየቁም "የአላህ ባሮች ስራ ሰኞና ሀሙስ ወደ ጌታቸዉ ዘንድ ትቀርባለች"።(አቡ ዳዉድ 2436) ያሉ ስለሆነ የኔ ስራ እኔ ጾመኛ ሆኜ እንዲቀርብልኝ እፈልጋለሁ።"ብለዋል።
(ቲርሚዝ በቁጥር 747 ዘግበውታል)
ክፍል,2 ይቀጥላል

https://t.me/Latahezn
አቡ የህያ ሱሀይብ ኢብኑ ሲናን (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት፦ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ተከታዩን ተናግረዋል፦"የሙእሚን ጉዳይ እጅግ የሚደንቅ ነው። ሁለ ነገሩ ኸይር (ሰናይ) ነው ።እንጂ ለማንም (የተሰጠ) አይደለም። አስደሳች ነገር ከገጠመዉ ለአላህ ምስጋና (ሹክር) ያደርሳል፤መልካም ይሆንለታል። ጉዳት ካገኘውም (አስከፊ ነገር ከገጠመዉም) ትዕግስት (ሶብር) ያደርጋል፤ ይህም ለርሱ መልካም ይሆንለታል።"
አልሀምዱሊላህ☺️🙏

(ሙስሊም አንደዘገቡት)
https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from لاتحزن
#የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ መናገራቸዉ ተወስትዋል፦

((والله في عون العبد ماكان العبد في عون أخيه))

"ባሪያው ወንድሙን መርዳት እስካላቆመ ድረስ አላህ ባርያዉን ከመርዳት አይቆጠብም።"

https://t.me/httpsLatahzen
ሌሎችን እርዳ
መልሰው ሊረዱህ እንደማይችሉ
       ብታውቅ እንኳን !