La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
ሞት ስካር አለው። ጭንቅና ፍርሀቱም የተለየ ነው። አንድ ቀን ከመለከል መውት ጋር ፊት ለፍት መተያየታችን አይቀርም። ምን ይውጠን ይሆን? የዛን ቀን። እንዴት ይሆን? በዛን ሰአት ሁኔታችን። ሞት የሚጀምረው ከታች ከእግር ነው። የሚጠናቀቀው እላይ አይን ላይ ነው። ህመሙ ከታች ከእግር ጫፍ ጀምሮ ሁሉ የሰውነት አካል ወደላይ ያዳርሳል። የዚያ ቀን የመጥፎ ሰሪዎች ስቃይ ደሞ እጅግ የከፋ ነው። ነፍሱ መለከል መውትን ስታይ በድንጋጤ በሁሉ የሰውነት አካል ውስጥ ትበተናለች። ነገር ግን ወዳ ሳይሆን በግዷ እየተፈለቀቀች እንድትወጣ ትደረጋለች።
አላህን የመፍራት ጥቅሞቺ

➊ አላህን በመፍራታቺን የሚገኝው ጥቅም አንዱ ሀጢያታቺንን ይሰርዛል አጂራቺንን ከፍ ያደርጋል ፡፡

አላህ በተከበረ ቃሉ ምን ይለናል ፡

وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يُكَفِّرْ عَنْهُ سَيِّئَاتِهِ وَيُعْظِمْ لَهُ أَجْرًا

አላህንም የሚፈራ ሰው ኀጢኣቶቹን ከእርሱ ይሰረዝለታል፡፡ ምንዳንም ለእርሱ ያተልቅለታል፡፡


➋ አላህ ጉዳዩቺህን (ሀጃህን ) ገር ያደርግልሀል

አላህ የሚፈራ ሰው ነገሮቹ ገር እንደ ሚሆንለት ከተገለፀበት አንቀጰ ውስጥ አንዱ

وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مِنْ أَمْرِهِ يُسْرًا

አላህንም የሚፈራ ሰው ከነገሩ ሁሉ ለርሱ መግራትን ያደርግለታል፡፡


➌ በጨነቀህ ግዜ መውጫ ቀዳዳ ያበጂልሀል ፡፡

አላህ ሱብሀነ ወተአላ ምን ይለናል

وَمَن يَتَّقِ اللَّهَ يَجْعَل لَّهُ مَخْرَجًا

አላህንም የሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፡፡

ጨንቆህ የምትይዘው የምትጨብጠው ስታጣ ያኔ አላህ ይደርስልሀል ፡፡

➍ የአሄራ ሰንቅ ለመያዝ የፈለገ

وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ

ከበጎም ሥራ የምትሠሩትን ሁሉ አላህ ያውቀዋል፡፡ ተሰነቁም፤ ከስንቅም ሁሉ በላጩ ጥንቃቄ (አላህን መፍራት) ነው፡፡ የአእምሮዎችም ባለቤቶች ሆይ! ፍሩኝ፡፡

ከስንቅ ሁሉ ትልቁ ስንቅ አላህን መፍራት ነው ንቁ !!

➎ ጀነትን ያስመነዳል

إِنَّ الْمُتَّقِينَ فِي جَنَّاتٍ وَنَعِيمٍ

አላህን ፈሪዎቹ በእርግጥ በገነቶችና በጸጋ ውስጥ ናቸው፡፡

ሰለዚ ጀነትን የምንፈልግ እህትና ወንድቼ ሆይ, አላህን በመፍራት ላይ አደራ !!!!
La tehzen
#የእጁጅ_ወመእጁጅ 🔷 ክፍል #አስር 🔟 ይሁን እንጂ ይህን ሴራ ኑመይሪድ በድብቅ ተደብቆ እየሰማ ነበር፡፡ ልክ ይህን እንደሰማ በድንጋጤ ራሱን ሳተ፡፡ ከዛም ኑመይሪድ ከነዚህ ህዝቦች ለማምለጥ በፍጥነት ወደ አይጁር ፍቅረኛ በመገስገስ የተከሰተውን በሙሉ ነገራት እና ተነሺ አኔ ጋር እነአይጁር ወዳሉበት እንሽሽ አላት ልጅቶም፦ ምንም ቢሆን ሁናታው አሳዝኖት ብታለቅስም ግን ወገኖቼን ትቼ የትም አልሄድም፡፡…
🔰 #የእጁጅ_ወመእጁጅ

🔷 ክፍል #አስራ_አንድ 1⃣1⃣

ልጂቱም ፦ አይጁር እወድሀለሁ ነገር ግን ቤተሰቦቼን ትቼ ካንተ ጋር መውጣት አልችልም አለችው፡፡
አይጁርም፦ እነዚህ እኮ ወገኖቻችን አይደሉም፡፡ አታለውናል፤ ሸውደውናል ስለዚህ አታከራክሪኝ ሁሉንም ነገር ከዚህ ስንወጣ አስረዳሻለሁ አሁን ሰዐት የለንም ፈጥነን እንሂድ፡፡አሁን የገፀ ምድር ነዋሪያን የጉድጎዱን መሹለኪያ ሊዘጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው እንሂድ በማለት እጅግ ለመናት፡፡
ልጂቱም አይጁር ሂድ አንተ፡፡ እኔ ግን አልሄድም አለችው፡፡
አይጁርም እጮኛውን እና ያን በትዕቢት የተሞላ ጉድጓድ ድጋሚ ላያያቸው ለመጨረሻ ጊዜ ትቶት ወጣ፡፡

ይህን ጊዜም ዙል ቀርነይም፦ ምን ገጠመህ ልጄ!!! ብሎ ሲጠይቀው፤ አይጁርም የተከሰተውን በሙሉ ተረከለት፡፡
ይህን ጊዜ ዙል ቀርነይን አይዞህ ልጄ!!!አንተ የመረጥከውን ወደ ቀጥተኛው መንገድ መምራት አትችልም፡ አላህ ብቻ ነው የሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራው፡፡ ተዋት ወደ ፈለገችበት ትሂድ የአላህን ውሳኔ አክብረውም ውደደውም፡፡
ምናልባትም በዚህ ላንተ ብዙ ኸይር ሊኖረው ይችላል በማለት አፅናናው፡፡ አይጁር በዙል ቀርነይን ምክር ልቡ ከተረጋጋ በኀላ ዙል ቀርነይን ከፍተኛ ብዛት ያለውን እንደ ሬንጅ ያለ ነገር በማስጠጋት እንዲቃጠል አዘዘ፡፡
ህዝቡም በተባለው መሰረት ጉድጓዱ ላይ ሬንጁን በማድረግ ያቃጥሉት ጀመር፡፡ በመቀጠልም ጉድጓዱ ላይ በቀለጠው ሬንጁም ላይ የተሰበሰበዉን የብረታ ብረት ጥርቅም እንዲከምሩ አዘዘ፡፡
ይህ ሬንጁ ላይ የከመሩት የብረታ ብረት መዐትም ልክ እንደ ሬንጁ እየቀለጠ መንቀልቀል ሲጀምር በላዩ ከፍተኛ ብዛት ያለውን እና እንደ ተራራ የተከመረውን የነሀስ ጥርቅም ይከምሩት ጀመር፤ ይህን ጊዜ ነሀሱም እንደ ሬንጁ እና እንደ ብረታ ብረቱ ይቀልጥ ጀመር፡፡
በመቀጠልም ድጋሚ ከፍተኛ ብዛት ያለውን ሬንጅ በማምጣት በቀላጮቹ ላይ ይከምሩትም ጀመር፡፡ በመጨረሻም እንደ ወንዝ ብዛት ያለ የጭቃ ክምር በላዩ ላይ በመመረግ የከርሰ ምድር ነዋሪዎች ዳግም ፀሀይን እንዳይመለከቱ እና እስከ ቂያማ መቃረቢያ ድረስ ላይወጡ አዳፈኗቸው፡፡
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን የእጁጃውያን ሀገር ሰላም ብለው ምድርን ወረረው፡፡ የምታቃጥላቸውንም ፀሀይ አጥፍተው የሰው ልጆችን ገድለው የተቀሩትን ለማሰቃየት ወደ ምድር ሊወጡ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ይሁን እንጂ የጉድጓዱን መሹለኪያ ሲመጡ ዝግ ሆኖ ያገኙትና ሊከፍቱት ሲታገሉም እማይሞከር ሆኖ ያገኙታል
ነገር ግን ያለመታከት ሌት ተቀን ስራቸው ከዚህ ግድብ ጋር መታገል ይሆናል፡፡
ዘዉትር ቀኑን ሙሉ የዚህን ግድብ ግድግዳ ሲቆፍሩ ዉለዉ የሬንጁን ጫፍ ሲደርሱና የተከፈተላቸው መስሏቸው ግር ሲሉ ያኔ በአላህ እገዛ የተገደበው ግድብ የብረት ቅላጭ በላያቸው በመዝነብ ተስፋ ቢስነታቸውን ያሳያቸው ጀመር፡፡
በዚህ ሁኔታ ምድሩ እንዴት ተዘጋብን ??በሚል ጩኸት እና እልህ ያናውጧታል፡፡ ከመካከላቸውም ወገንቼ ምን ያስጮሃችኀል??? አሁን ሰዎች በእኛ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋል፡፡
ይሁን እንጂ እኛም በመጨረሻው ሰዐት የምንወጣበት ቀን ይመጣል፡፡
ያቺ ቀን ደርሳ ከታገትንበት የወጣን ቀን ግን የሰው ልጆችን እስከ መጨረሻው እናጠፋቸዋለን፡፡ ምድር ላይም ምንም አይነት አረንጓዴ ነገር እንዳይቀር አድርገን ምድርን ካወደምን እና ባህሮቻቸውንም ካደረቅን በኀላ የሰማይ ነዋሪያንንም(መላዕክት) እንዳልነበሩ አድርገን እንደመስሳቸዋለን፡፡ይቺ ቀን ስትደርስ ስፍር ቁጥር የሌለን ሁነን ከምድር በመፍለቅ ቤቶቻቸውን እናፈራርስባቸዋል፡፡ የሰው ልጆችን እንገድላቸዋለን፡፡ እንደውም ሰዎች የሚፈሩትን ሞትን ራስን እንገድለዋለን...ሰዎችንም በአጠቃላይ ገድለን የተቀሩተን አገልጋዩቻችን እናደርጋቸዋለን፡፡
ከዚያም ወደ ሰማይ ነዋሪያን ፊታችንን በማዞር የቀስት ናዳዎችን እንለቅባቸዋለን፡፡ በቀስት ናዳዎች የማያልቁ ከሆነ እራሳችን ወጥተን እስከ መጨረሻው ከገደልናቸው በኀላ የተቀሩትንም አገልጋዩቻችን በማድረግ ፍጥረተ አለሙን በብቸኝነት እንቆጣጠረዋለን፡፡አይዟቹ ይህ ቀን ቅርብ ነው፡፡ ተስፋ እንዳትቆርጡ መውጫ ቀዳዳ እስክናገኝ ድረስ በያንዳንዱ ሰከንድ ትግላችንን በማጠናከር እንቀጥላለን በማለት አፅናናቸው፡፡

የእጁጃውያኑ በዚህ ሁኔታ ይዛዛታሉ ለሰው ልጅ ያላቸው ጥላቻ እና ምቀኝነት ከበፊቱ ይልቅ ይብስባቸዋል፡፡ ከንዴት እና ብስጭት ብዛት ልባቸው ተቃጥሎ በማለቅ እንደ ቁራጭ ስጋ ትሆናለች፡፡ በዚህ ሁኔታ የአመፅን ተስፋ ይዘው መውጫ ቀደዳቸውን ለብዙ ሺህ አመታት ከቆፈሩ በኀላ እሱን ትተው ሌላ መውጫ መቆፈር ይጀምራሉ፡፡....

Part ➊➋
ይቀጥላል......
La tehzen
🔰 #የእጁጅ_ወመእጁጅ 🔷 ክፍል #አስራ_አንድ 1⃣1⃣ ልጂቱም ፦ አይጁር እወድሀለሁ ነገር ግን ቤተሰቦቼን ትቼ ካንተ ጋር መውጣት አልችልም አለችው፡፡ አይጁርም፦ እነዚህ እኮ ወገኖቻችን አይደሉም፡፡ አታለውናል፤ ሸውደውናል ስለዚህ አታከራክሪኝ ሁሉንም ነገር ከዚህ ስንወጣ አስረዳሻለሁ አሁን ሰዐት የለንም ፈጥነን እንሂድ፡፡አሁን የገፀ ምድር ነዋሪያን የጉድጎዱን መሹለኪያ ሊዘጉት በመጠባበቅ ላይ ናቸው እንሂድ…
#የእጁጅ_ወመእጁጅ

🔷 ክፍል #አስራ_ሁለት 1⃣2⃣

በዚህ ሁኔታ የአመፅን ተስፋ ሰንቀው መውጫ ጉድጎዳቸውን ለብዙ ሺህ አመታትን ከቆፀሩ በኀላ እሱን ትተው ሌላ መውጫ መቆፈር ይጀምራሉ፡፡
ምንም እንኳን ከቀላጭ ነበልባሉ ሽሽት ሌላ ቦታ ለመቆፈር ቢሞክሩም ምድሪቱን መውጫ ጫፍ ሲቃረቡ እንደ በበፊቱ የቀላጭ ናዳ ይዘንብባቸዋል፡፡ በዚን ጊዜ ለቁጥር የሚያዳግቱ ያእጁጃውያን ለሞት ይዳረጋሉ፡፡ የሞቱትንም በጅምላ በማከማቸት ለምግብነት ያዉሉታል፡፡
ምንም እንኳን በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ያእጁጃውያን በየሰከንዱ የቀላጩ ሰለባ ሁነው ቢሞቱም ብዛታቸው ግን እጅግ ከመጨመሩ የተነሳ ሬሳውን መመገብ አላጠግብ ብሏቸው በረሀብ ይተራመሳሉ፡፡
ገደብ ያለፈው ስግብግብነታቸው እና የተመሳሳይ ዘራቸውን ስጋ በልነታቸውን አቅላቸውን አስቶ ያዋልላቸዋል፡፡
በየቀኑ የሚበሏቸውን የሙታኑን አጥንትም ከቤት መስሪያነት በተጨማሪ ለመቆፈሪያነትም በመገልገል የምድሪቱን ቁፋሮ ጠበቅ አድርገው ይዘዉታል፡፡

ይሁን እንጂ ምድርን በቆፈሩ ቁጥር ከሆዱ የሚወጣው ቀላጭ መኖሪያዎቻቸውን ያጥለቀልቅ ይዞታል፡፡
ዙል ቀርነይን አላህ ባገራለት እውቀት ተጠቅሞ ዘመናዊያን ያልሞከሩትን ኦክስጅን በሌለበት እሳትን በማንቀልቀል ለረጅም ዘመናት የቆየ ብልህ ንጉስ ነው፡፡
አዎ!!!አላህ የፈቀደ እለት እንጂ ለነዚህ ያእጁጃውያን መውጫ የላቸውም፡፡ የጅልነት ተስፋቸው ይህን የቀላጭ ክምር ጥሰው ሳይወጡ በፊት የንዴት ዛቻዎችን እንዲደረደሩ አድርጓቸዋል፡፡ አንዳንድ ያእጁጃውያንም ከረሀብ ብዛት በሺዎች የሚቆጠሩ ያብራክ ክፋይ ልጆቻቸውን አጣጥመው መብላት ይጀምራሉ፡፡ የልጆቻቸውን መብላት ያላጠገባቸው ያእጁጃውያን በዙሪያቸው ያለውን ቋጥኝ እና ተራራዎችንም መብላት ይጀምራሉ፡፡

ዙለል ቀርነይን እና ህዝቦቹ ለዘመናት ያሰቃይዋቸው ህዝቦች ላይ የተሳካ ግድብን በመገደባቸው በደስታ ፈንድንቀዋል፡፡አላህ እስከወሰነው ቀን እስከሚወጡ ድረስ ከያእጁጃውያኑ ተንኮል የተገላገሉ ህዝቦችም ለአላህ ምስጋነሠ ሰላት በመስገድ ደስታቸውን ሙሉ አድርገዋል፡፡
ነገር ግን በመሀላቸው ያለው ዘረ ቅይጥ አይጁር በደስታ እና በሀዘን መካከል ነበር የነበረው
ቀናት ሳምንታትን ሳምንታት ወራትን ወራት አመታትን ታጅበው ጊዜው ይነጉድ ጀመር፡፡ ምድር ሰላማዊ ሆና ህዝቦችዋን ትውልድን በትውልድ መተካቱን ተያይዟቸዋል፡፡
ትውልድ ትውልድን እየተካ ረዥም አመታት ከተቆጠረ በኀላ አላህ ሱብሀነሁ ወተዓላ ኑህን ዐለይሂ ሰላም ወደ ምድር ነዋሪያን ላከው፡፡

Part ➊➌
ይቀጥላል......
አላህ የሠጣችሁን የተረጋጉ እና በጤና የተሞላ ቀኖቻችሁን ዉደዱ። የግድ እኮ በሰርፕራይዝ፣ ብር በማግኘት እና በፌሽታ መሞላት የለባቸዉም።
ይህንንስ ማን አይቶብኝ አትሉም እንዴ።
ዛሬ የገባው ወር ዙልቂዕዳ ይሠኛል። ከተከበሩ አራት የዓመቱ ወራቶች ዉስጥ አንዱ ነው። ቀጥሎ ያለው የተከበረው የሐጅ ወር ነው። ሐጅ ያሰባችሁ አላህ ለታላቁ ምኞታችሁ ያብቃችሁ። አርደልሐረምን ዘይሩልን። ለመዲናው ሙስጦፋ ሰልሙልን። እኛም በአላህ ፈቃድ አንድ ቀን እንደምንመጣ ንገሩልን።
ሶልሏሁ ዐለይሂ ወሰለም።
➲ለሰዎች ሁልጊዜ የደስታ ሰበብ እንጂ ለአንድም ሰው የሀዘን ምንጭ አትሁን ማስደሰት እንኳን ባትችል ማንንም ለመጉዳት አታስብ !!!
በሰው ቀልብ እየተጫወቱ አላህ ጌታ ሆይ ቀልቤን አረጋጋልኝ ብለው ይለምናሉ።
አይታሰብም።
አላህ ሥራችሁን አይመዘግብም መሰላችሁ እንዴ!
እንባ ከዐይናችን እንደሚወድቀው ሁሉ፣ የሆነ ጊዜ ላይ አንዳንድ ሰዎችም ከዐይናችን ዱብ ዱብ ይላሉ። ወሏሁል ሙስተዓን።
አንዱ እኮ ነው ጫት እየቃመ ተርዚናውን የሌለ ቆልሎት ሲጋራ ለኩሶ ሊያጨስ ሲል የሆነች የገጠር ሴትዮ ምን ብትለው ጥሩ ነው ። 😉
.
አይ ልጀ አትድከም እሱን ሁሉ ጎመን እቺን እሳት ታበስለዋለች ብለህ ነው።
ሕይወትን ወደ ዕድሜያችሁ ጨምሩ እንጂ ዕድሜን ወደ ሕይወታችሁ አትጨምሩ። ዕድሜ ከዉብ ሕይወታችሁ ከመስረቁ በፊት ሕይወትን ከዕድሜያችሁ ስረቁ።
ገብቷችኋል አይደል ...።

ጁምዓ ሙባረክ!
😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭


አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84 አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል።
ሁላችንም ይመለከታል ።
ኡበይዱላህ ኢብን ኡመር አንድ ጊዜ
እንዲህ ብለው ነበር “ጀምዐ ሰላት
በተለይ ኢሻና ሱብሂ አምልጦኝ
አያውቅም፡፡ ነገር ግን አንድ ጊዜ ቤቴ
እንግዳ መጣና ከርሱ ቆይቼ ኢሻ ሶላት
አመለጠኝ፡፡ ከቤት ወጣሁ፤ ጀምዐ
ሶላት ለማግኘት ብዬ በስራ ከተማ ላይ
የሚገኙ መስጂዶች በሙሉ ዞርኩ፤
ሁሉም መስጂዶች ተሰግዶ አልቋል፡፡
ሰዎቹ ባጠቃላይ ሰግደው
ወደቤታቸው ሄደዋል፡፡ እኔም ወደ
ቤቴ ተመለስኩና ማሰብ ጀመርኩ፤
ለራሴ እንዲህ አልኩኝ ‘በሀዲስ
በግለሰብ ከሚሰገደው ሰላት በጀምዐ
ሚሰገደው በ 27 ደረጃ ይበልጣል
ተብሎዋል፤ ስለዚህ 27 ጊዜ ኢሻን
ሰላት ብሰግደው በጀምዐ ከሰገዱት ጋር
እኩል ይሆናል’ ብዬ በማሰብ
ኢሻን ሰላት በቤቴ 27 ጊዜ ሰገድኩና
ተኛሁ፡፡ በዛው ቀን ለሊት በህልሜ
ከፈረሰኞች ጋር ፈረስ ውድድር
ስንወዳደር አየሁ፤ ፈረሴ ጠንካራ
ብትሆንም
እንኳ ሌሎቹ ላይ ልደርስባቸው
አልቻልኩም፤ ወደ ዃላ ቀረሁ፡፡ ፈረሴ
ትደርስባቸው ዘንድ እደበድባት
ጀመርኩ፤ ነገር ግን ምንም ለውጥ
ልታመጣልኝ አልቻለችም፡፡ አንደኛው
ፈረሰኛ ወደኔ በመዞር “ፈረስህን
አታሰቃያት እኛ ላይ ልትደርስብን
አትችልም” አለኝ፡፡ እኔም “ለምን?”
ብዬ
ስጠይቀው “ምክንያቱም እኛ ኢሻን
ሶላት በጀምዐ ነው የሰገድነው፤ አንተ
ግን ብቻህን ሰገድከው” በማለት
መለሰልኝ፡፡ ከዚህ ትልቅ ትምህርት
ወሰድኩ፤ በጣምም አዘንኩ፡፡” ይለናል
ኡበይዱላህ፡፡
ሱብሃነላህ!!
እኛ ስንት ሶላት ይሆን ጀምዐ
ያመለጠን?? ስንቶቻችን ይሆን በዚህ
ምክንያት ተፀፅተን የምናውቅ??
“አንድ ሶላት እያወቀ ያሳለፈ 84
አመት
ጀሀነም በር ላይ ስሙ ይፃፋል”
መባሉን ምናስታውስ ስንቶቻችን
ነን??
ዛሬውኑ እንነይት “ኢንሻ አላህ ካሁን
በሗላ አንድም ሶላት ጀምዐ
አያመልጠኝም” ብለን…ለኔም
ለናንተም ሰደቀቱል ጃሪያ ይሆናልና
መልክቱን
ሼር እናድርገው —
ያረብ በሰላት ላይ ጥንካሬና ብርታት ስጠን ከሰይጣን ተንኮል ጠብቀን።
ዋ!! ፈራሁልሽ ነፍሴ 😭😭😭
ውበት የሚደምቀው በአለባበስ ብቻ
ሳይሆን በአስተሳሰብ ጭምር ነው
ውስጣዊ ስሜቶች አይፃፍም፣
ቢፃፍ እንኳ ፍፃሜ የላቸውም ።
የአንዳንድ ነገሮች መሰባበር
ሲሰማህ ትንሽ ራቅ በል።
ንግግር ስሜትህን የመግለጽ አቅም ሲያጥረው ትንሽ ዝም በል።
#ሁሌም_ቢሆን ስለ መልክህ ሳይሆን ስለ መልካምነትህ ተጨነቅ...ከሰው ጋር ሊያዘልቅህ የሚችለው መልክህ ሳይሆን መልካምነትህ ነው
ለምሰራው ጥፋት አታላክ በሰው ላይ፣
ለራስህ ፡ እራስህ አትሁን አታላይ!

ከህሊና ችሎት ማምለጫ ሳይኖረህ
ጣትህን አቀስር በመጥፎ አመልህ!!

@MotivateEthiopia
👉ሁሌም ሐሳቦችህ ልክ ነህ እስከሚያስብሉህ አትጠብቅ፤ እንደዛ ከሆነ ተቀባይነት እስክታገኝ ድረስ ጊዜ ልትፈጅ ነው ማለት ነው! ግን ላንተ ልክ ሆኖ ከተሰማህ ከመሞከር አትቦዝን!!!
👉እኔ ማን እንደሆንክ ታውቃለህ! ይቺ ቃል ክብርን ከምታስጠብቀው በላይ ክብርን የምታስንድ ናት!…መከበር በስራ እና እንደነበርክበት ቦታ እንዳሳለፍከው ጊዜ ፤ እንዲሁም በመልካም ተግባራትህ እንጂ በስም ለመከበር አትሞክር! ማንም ማንንም አያቅምና!!!
👉ከአበቦች ሁሉ በላይ በቁመቷ ለየት ያለች አበባ ፈተናዋ ብዙ ነው፤ እንዴት? በንቦች ለመከበብ ፤ በሌሎች ነፍሳት ለመኖሪያነት በመመረጥ ፤ እንዲሁም በሰዎች በመቆረጥና የራሷ ቁምት እጅግ ከፍ ሲል መቀንጠስ ሚባሉት ነገሮች ይከሰቱባታል!!! ሰውም ከሚኖርበት ማህበረሰብ ጋር መስማማት ካልቻለ እና ካፈነገጠ መኖር ለርሱ ከባድ ይሆንበታል፤ ምንም እንኳ ሰው በሔደበት መንገድ ሳያምኑበት ተከትሎ መሔድ ባይገባም፤ ቢቻል ሐሳብን መግለፅና ጠቀሜታውን አጉልቶ ማሳየት ይገባል፤ ግን የነርሱን እያየን በመልካሙ መንገድ አካሔዳችን ሊመስላቸው ይገባል! ሚኖረው ከሰው ጋር ነውና!!!

@MotivateEthiopia
👉መቸኮል እና ነገርን አለማጣራት መደምደሚያቸው ጥፋት ነው፤ ሁለቱም በስሜት የሚፈጸሙ ድርጊቶችን ያስከትላሉ ያ ደግሞ ኋላ ሚያስቆጩ ሁኔታ ውስጥ ይከተናል! ውሳኔአችን ከምን የመነጨ እንደሆነ ቆም ብለን ማሰብ ይገባናል!!!
👉ገደብ፡ ይሕ ምን ያህል መሔድ እንዳለብን የሚወስነን ነው፤ ገደብ አስፈላጊ ነገር ነው፤ የምንጠይቀው ፤ የምናወራው ፤ የምናስበው ፤ የምንመኘው ፤ የምንፈጽመው ነገር ሁሉ ገደብ ሊኖረው ይገባል፤ ካልሆነ ኑሮአችን ቅጥ ያጣ ፤ ስብዕናችን የተናቀ ፤ ድርጊታችን የጭካኔ መሆኑ የማይቀር ነው!!!

@MotivateEthiopia
🤔 እንዲ ባደርግ...እንዲ ቢሆን...እያልክ ስታሰላስል ጊዜው ይነጉዳል። የሚሻለው እስኪ ልሞክረው ብሎ ቶሎ መሳሳትና እያስተካከሉ መሄድ ነው። ከወደክ አይቀር ቶሎ ውደቅ፤ ግን ስትወድቅ ወደፊት ውደቅ። የ 42 ኪሎ ሜትር ማራቶን በአንድ እርምጃ ነው የሚጀመረው...ፍጥነትህንና ስትራቴጂህን ለመቆጣጠርም እዛው እየሮጥክ ሁኔታዎችን እያየህ አይሻልም? አልጋ ውስጥ ሆነህ እንዲ ባደርግ ከዛ ይሄን ባደርግ ከምትል፤ መጀመሪያ ስራውን ጀምረው ከዛ እያየህ ትጨምርበታለህ። ዳይ ወደ ስራ!

@MotivateEthiopia
መካ
=
ሀሳብ ሰንቄያለሁ ከዚያ ከበረሃ
አንጀት ከሚበላው ከሚያሰኘው ውሃ
የነሱመያ ጣር የነቢላል “አሐድ”
ያብከነክነኛል በትዝታ ንዳድ
በነብይ ዱዐ የሞላሽ በረካ
ሰላማዊት ሀገር ቅድስቲቷ መካ!
-
(ኢብኑ ሙነወር፣ ጳጉሜ 2/2006)