La tehzen
95 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
وحسن الخلق يقوم على أربعة أركان : الصبر ، والعفة ، والشجاعة ، والعدل . ~

『መልካም ባህሪ የሚባለው ነገር በአራት ማዕዘናቶች የቆመ ነው ፦【ትዕግስት፣ ጥብቁነት፣ጀግንነት፣ፍትሀዊነት】
Channel photo updated
ፋና ቲቪ ዶክመንተሪውን ከገፁ አጥፍቶታል። ይህም ዘመቻችን ተፅዕኖ
እንደፈጠረበት ያሳያል። በሌላ በኩል የዶክመንተሪው አላማ የጎንደር
ሙስሊሞችን አጀንዳ ማስረሳት በመሆኑ ሳንታክት ዘመቻችንን እንቀጥል!
ሀቅ ይውጣልሽ ! ሳይወጣም እስሩ እንግልቱ ቀጥሏል !
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በየአድባራቱ የሚካሄደው መሠል የጥላቻ ንግግር ከዚህ በላይ ደም
ላለማፋሰሱ ምንድን ነው ዋስትናችን?"
ጎንደር ከኢትዮጵያ ብዙ መማር ያለባት ነገር አለ!


#የጎንደርጭፍጨፋ
#GondarMassacre
የራሳቸው እንኳ ሰዎች እየታዘቧቸው"
የፋናዎችም ዶክመንተሪ እንደ አምቡላ አስለቃሽ ጭስ ባርቆ ነው እንደ ያጠፉት¿


አምቡላ እንኳ ምናልባት አንድ አምቡላ (አረቄ) አቡልሎ ይሆናል¡ እነዚህ ስንት ቢያቦሉ ነው ሆነ ተብሎ የተቀነባበረ የሴራ ዶክመንተሪ የሚባርቅባቸው¿
ከችግር በኋላም በእርግጥ ምቾት አለ

https://t.me/httpsLatahzen
💫ደስታ ያለው በአላህ እጅ ነው።
አላህ ዘንድ ያለን ነገር ደግሞ አላህን በማመፅ አይገኝም‼️

💫ትክክለኛ ደስታ ከፈለክ ለጌታህ ባርነትህን አረጋግጥ‼️‼️


https://t.me/httpsLatahzen
«يا عَبْدَ اللَّهِ، لا تَكُنْ مِثْلَ فُلانٍ كانَ يَقُومُ اللَّيْلَ، فَتَرَكَ قِيامَ اللَّيْلِ»
«ዐብደላህ ሆይ; እንደ እከሌ እንዳትሆን የለይል ሰላት ይሰግድ ነበር ከዝያም መስገድን ተወ።»
የረሱል ﷺ ማስጠንቀቂያ ነው
https://t.me/httpsLatahzen
ውዱ ወንድሜ የሰው ተከታይ አትሁን

አንድ አንድ ሰወች የሰው ተከታይ መሆንን እንደት ትልቅ ነገር አድርገው ያዩታል

አጅብ
ስማኝ ወንድሜ ስሜትህን መከተልን ተውና ቁርአን ሀድስን ተከተል አውቃለሁ ኡስታዝህን ልትወደው ትችላለህ ግን ስማኝ ሀቢቢ በሱ ሳንባ አትተንፍስ የገባበት ተከትለህ አትግባ።
መንሀጅኮ ቲቸርት አይደለም እንደፈለክ የምቀያይረው !?
እውነት ከሰወች ሳይሆን ከጌታህ ነው የሚመጣውና ፍፅሞ የሰወች ተከታይ አትሁን
ሰወች ስላንተ ብዙ ሊያወሩ ይችላሉ ምንም ቦታ አትስጣቸው
ቢላሂ አለይክ አላህ አእምሮ ሰቶህ እንደት የኡስታዝህ ተከታይ ትሆናለህ? ያም አልበቃህ ብሎ ሰወች ያንተን ኡስታዝ ስላልተከተሉ እንደት ታኮርፋቸዋለህ?

አንተ ቁርአን ሀድስ ነው የምከተለው የምትል ወንድሜ ከስሜት ተከታዮች ብዙ ስድብ ዛቻ ዱላ ሳይቀር ሊመጣብህ ይችላልና ታገስ ጀነት በነዚህ ስሜታቸውን በሚከተሉ ሰወች እጅ ሳትሆን በጌታህ ቁጥጥር ናት ያውም ለምርጥ ባሮቹ ያዘጋጃት ስለዚህ ምንም አያሳስብህ።

https://t.me/httpsLatahzen
ውዷ―እህቴ

ትዕግስትን( ሶብርን) ስንቅሽ!
የአላህ ፍራቻ (ተቅዋ) ልብስሽ!
የአላህን ቃል ቁርዓንን ጓደኛሽ!
ተወኩልን ተስፋሽ አድርገሽ ይዘሽ!
"ዒልምን በመፈለግ ላይ ፅናት ይኑርሽ ።
በአላህ ፍቃድ ለስኬት ትበቂያለሽ!!!

https://t.me/httpsLatahzen
💫ጁማዕ💫

ነቢዩ ﷺ የሚከተለውን ብለዋል፦
"ፀሀይ ከወጣችበት በላጩ ቀን የጁሙአ ቀን ነው በዛች ቀን ነቢዩላህ አደም ተፈጠረ፣ጀነትንም ገባ፣ከጀነትም ወጣ፣ የቂያማ ቀንም በጁሙአ ቀን እንጂ አትቆምም"
[ሙስሊም _ ዘግቦታል]
በጊዜ ወደ መስጅድ መሄድ ነቢዩ ﷺ የሚከተለውን ብለዋል፦

የጁማዕ# ቀን ላይ በእያንዳንዱ መስጅዶች በር ላይ መጀመሪያ የመጣውን መጀመሪያ ላይ ቀጣይ የመጣውን በተርታ የሚመዘግቡ መላኢካዎች አሉ ልክ ኢማሙ ሚንበር ላይ በተቀመጠ ጊዜ መዝገባቸውን ዘግተው ኹጥባ ለማዳመጥ ይመጣሉ። መጀመሪያ ሰአት ላይ የመጣ ሰው ምሳሌው ልክ ግመል ሰደቃ እንዳወጣ ነው፤ከዛ ከብት እንደሰደቀ ነው፤ከዛ ሙክት በግ እንደሰደቀ ነው፣ከዛ ዶሮ እንደሰደቀ ነው፣ ከዛ እንቁላል እንደሰደቀ ነው።"
[ቡኻሪ ዘግቦታል]

فَإِذَا قُضِيَتِ الصَّلَاةُ فَانتَشِرُوا فِي الْأَرْضِ وَابْتَغُوا مِن فَضْلِ اللَّهِ وَاذْكُرُوا اللَّهَ كَثِيرًا لَّعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ
ሶለቲቱም በተፈጸመች ጊዜ በምድር ላይ ተበተኑ፡፡ ከአላህም ችሮታ ፈልጉ፡፡ አላህንም በብዙ አውሱ፡፡ ልትድኑ ይከጀላልና፡፡
وَإِذَا رَأَوْا تِجَارَةً أَوْ لَهْوًا انفَضُّوا إِلَيْهَا وَتَرَكُوكَ قَائِمًا ۚ قُلْ مَا عِندَ اللَّهِ خَيْرٌ مِّنَ اللَّهْوِ وَمِنَ التِّجَارَةِ ۚ وَاللَّهُ خَيْرُ الرَّازِقِينَ
ንግድን ወይም ዛዛታን ባዩ ጊዜም ቆመህ የተዉህ ሲኾኑ ወደእርሷ ይበተናሉ፡፡ አላህ ዘንድ ያለው ዋጋ ከዛዛታም ከንግድም በላጭ ነው፡፡ «አላህም ከሰጪዎቹ ሁሉ ይበልጥ ሲሳይን ሰጭ ነው» በላቸው፡፡
{ጁማዓህ-10-11}

የጁማዕ# ሶላት ሁለት ረካዐዎች ያሉት ፈርድ ሶላት ነው።
አንድ ሰው" ዘግይቶ ቢመጣና ሁለተኛውን ረከዐ ከጀማዓጋር ከሰገደ ቀሪውን አንድ ረከዐ አሟልቶ መስገድ አለበት ። አንድ ሰው" በጣም ዘግይቶ በመድረሱ የጁማዓው ሶላት ሙሉ በሙሉ ያመለጠው እንደሆነ አራት ረከዐዎች ፈርድ የዙሁር ሶላት መስገድ ይኖርበታል። የጁማዓ ሶላት የዙሁር ሶላት ምትክ ናት።

የጁማዕ ቀን ሱናዎች፥- ሻወር መውሰድ
- ንጹህ ልብስ መልበስ- ሽቶ መቀባት
- ሲዋክ _መፋቂያ መጠቀም
- ቁራዕን ማንበብ
ቁርአን እስከ አለም ፍጻሜ ድረስ የሚቆይ ፣
እስከ ዕለተ ሞትህ የምትከተለው ትዕዛዝ ያለበት ፣ ንጽሕናው እንደተጠበቀ የሚዘልቅ መጽሐፍ ነው። ሱረቱል ከህፍን መቅራት በጁማዕ# ቀን የተወደደ ነው

#የጁማዓ ሶላት

ጁማዓ ለመስገድ ወደ መስጅድ የሔደ (የገባ) ሰው" ፀሐይቱ ከእኩል ቀን" ወደ ምዕራብ ትንሽ ካጋደለችበት ጊዜ አንስቶ ኢማሙ ኹጥባ እስከ ሚጀምሩበት ጊዜ ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ የፈለገውን ያህል ነፍል "ሶላት መስገድ ይችላል።
ቢያንስ ሁለት ረካዐ ሱንና መስገድ ግን ይጠበቅበታል።

*ኹጥባ (ምክርን) በፀጥታ ማድመጥ*

ኹጥባ ከተጀመረ በኋላ ሰጋጁ ሕዝብ በፀጥታ ማድመጥ አለበት። አንድ ሰው" ኢማሙ ኹጥባ ሲያደርጉ ከደረሰ ኹጥባውን ለማድመጥ ቁጭ ከማለቱ በፊት ሁለት ረካዐ ነፍል መስገድ ይኖርበታል።

ጀቢር(ረ.ዐ.) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ኹጥባ ስያደርጉ እንደ ሚከተለው " ማለታቸውን ዘግበዋል፦ ማንኛችሁም ኢማሙ ኹጥባህ ስያደርጉ ለጁማዓ የደረሰ ሰው" የግድ ሁለት አጠር ያሉ ረካዐዎች መስገድ አለበት።

በሌላ ሐዲስም ጃቢር (ረ.ዐ)
-አንድ ጊዜ የአላህ መልዕክተኛ (ሰ ዐ ወ) ኹጥባ ስያደርጉ በነበሩበት ጊዜ አንድ ሰው መጣ " ከዛም የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሰግደሀል እንዴ? ሲሉ ጠየቁት ፥ ሰውየውም -አይ ሲል መለሰላቸው! ከዚያም ነብዩ ( ሰ.ዐ.ወ) ተነስና ስገድ አሉት።

(ቡኻሪ -ሙስሊም-አቡዳውድና ቲርሚዚይ ዘግበውታል።)

አንድ አንድ ሰዎች ኢማሙ ኹጥባ ንግግር እያደረጉ ሳለ ሁለት ረካዐዎች ሱንና የሚሰግድ ሰው ካዩ በጣም ይናደዳሉ ፥ ኢማሙን እንደ መናቅ ይቆጥሩታል ፦ይህ አስተሳሰብ ግን ስህተት ነው። ከነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተቀሰመ ልምድ አይደለም።
አቢ ቀታዳህ(ረ.ዐ) የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንደ ሚከተለው መናገራቸውን ገልፀዋል ፦ ማናችሁም ሰው" ወደ መስጅድ ሲገባ ሁለት ረካዐዎች (ተሒይቱል መስጅድ) ሳይሰግድ መቀመጥ የለበትም።
(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።)
*የጁማዓ ሶላት*
የጁማዓ ሶላት ሁለት ረካዐዎች ያሉት ፈርድ ሶላት ነው።
አንድ ሰው" ዘግይቶ ቢመጣና ሁለተኛውን ረከዐ ከጀማዓጋር ከሰገደ ቀሪውን አንድ ረከዐ አሟልቶ መስገድ አለበት ። አንድ ሰው" በጣም ዘግይቶ በመድረሱ የጁማዓው ሶላት ሙሉ በሙሉ ያመለጠው እንደሆነ አራት ረከዐዎች ፈርድ የዙሁር ሶላት መስገድ ይኖርበታል። የጁማዓ ሶላት የዙሁር ሶላት ምትክ ናት።

*ከጁማዓ በኋላ የሚሰገድ ሶላት*
አብደሏህ ኢብኑ ዑመርን ጠቅሰው ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ "ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አብዛኛው ከጁማዓ በኋላ እቤት ገብተው ሁለት ረከዐ ሱና ይሰግዱ ነበር"ብለዋል።
አቡ ሁረይራን ጠቅሰው ሙስሊም አቡ ዳውድና ቲርሚዚ በዘገቡት ሐዲስ ከጁማዓ በኋላ የሚሰገድ አራት(4) ረከዐ ይስገድ" ብለዋል።
ኢብኑ ዑመር ጠቅሰው -አቡ ዳውድ በዘገቡት ሐዲስ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ( መስጅድ ከሰገዱ አራት(4) እቤት ከሰገዱ ሁለት ረከዐ ሱና ነበር የሚሰግዱት" ብለዋል
Audio
♦️አንድ ሰው የውመል ቂያማ ባነሳቸው ፎቶዎች ልክ ይቀጣል።

🎙الشيخ :- صالح الفوزان "حفظه الله"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
حظر الجوال على الشباب مقتطف للشيخ محمد بن عبد الله الإمام

በሰልካችን ምን እየሰራን ነው እህት ወድሞች

እስት ቆም ብለን እናሰበው ይህ ጀዋል በጃችን

ያለው በገዛ ብራችን የመጣነው ሙሲባ ምን

እያረግንበት ነው ያአላህ ያረብ ወላሂ ሲያስፈር
https://t.me/httpsLatahzen
Audio
ጥፍጥ ያለች ግብዣ እንሆ
ለቁርአን ወዳጆች
🌹ሃጅ ለመድርግ ላቃተን ሰዎች #ጁመዓ ለኛ ሃጃቺን ነውና አላህ ከመጣው በላዕ ከሚመጣው በላዕ ሁሉ ነጃህ ብሎን ሃጃቺንሁሉ የሚይወጣበት በሰላት በሰለዋት በኢባዳ ፍክት ፍክትክት ብለን ምናሸበርቅበት ምርጥዬ😍
🤲🤲ጁመዓ ይሁንልን🤲🤲
#Share_Share ለወዳጆህ
Join 👉
https://t.me/httpsLatahzen👈 Join
ልክ እንደዚህች ጎጆ አሁን ላይ መንግስት ስሙ ብቻ ነው ያለው የሚያስብሉ ክስተቶች እያጋጠሙን ነው። ትክክለኛ አሸባሪዎችና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ የጥላቻ ሰባኪዎች እነ ምህረተ አብ አሰፋ ተቀምጠው፤ ሳያጣሩ ንጹሐንን ማሰር ምን ይሉታል?
🌹

💢ከጁመዓ ቀን ሱናዎች

↩️ ‏سنن يوم الجمعة
➊ الغسل
➋ الطيب
➌ السواك
➍ لبس الجميل
➎ قراءة سورة الكهف
➏ التبكير لصلاة الجمعة
➐الإكثار من الدعاء والصلاة على النبي

🔹ገላን መታጠብ
🔹ሽቶ መቀባት
🔹ሲዋክ መጠቀም
🔹ጥሩ ልብስ መልበስ
🔹ሱረቱ ከህፍን መቅራት
🔹በጧት ለጁመዓ ሶላት መጣድ
🔹በነብዩ ﷺ ላይ ዱዓና ሰለዋት ማብዛት

📌((قَالَ رَسُولَ اللَّهِ ﷺ من قرأ سورةَ الكهفِ في يومِ الجمعةِ ، أضاء له من النورِ ما بين الجمُعتَين))
🔺የአላህ መልዕክተኛﷺእንዲህ ብለዋል፦ ((የጁምዓ ቀን ሱረቱል ከህፍን የቀራ ሰው አላህ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል ብርሃንን ያበራለታል))
📚 صحيح الجامع - رقم : (6470