La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram

ሀ እ ስ
ቅ ጅ ጡ

ሀቅ እያወቁ መሸሽ ግፍ ነው
መረጃ ቀርቦልህ አልቀበል ካልክ
ስሜተህ በግሮህ ከሆነ
ለሌላው መጥመም ሰበብያ አትሁን ራስህን ከዞርክ ለሸይጧን በቂ ነው
ለፉክክር ብለህ ያለ ኢኽላስ ምሰራዉ ስራ ታይቶልህ ይቀራል እንጂ ምንዳዉ 0×0 ነዉ

ስለዚህ ወንድም እህቶቼ ለአላህ ብለን ብላቹ የምንሰራው ስራ ኢኽላስ ከሌለዉ ዋጋ የለዉም
አላህ ስራቸዉ ወዶላቸዉ ከሚቀበላቸዉ ያድርገን
አካሄድህ አሳምር

አካሄድህ ጥሩ ከሆነ ለእንቅፋት አትዳረግም

ኡስታዝህ ጠንካራ ከሆነ አትሸራተትም

ኡስታዝህ ካረፈደ ቆይተህ መምጣትህ አይቀርም

እሱ የቀረ እለት መዉደቅህ አይቀርም

መንገድ ከመጀመርህ በፊት መድረሻህን እወቅ

እዉቀት ከመቅሰምህ በፊት ኡስታዝህን ለይተህ እወቅ

ኡስታዝህ በመንሀጁ ጠንካራ ቢሆንም ከእሱ ልጥፍ ከማለት ተጠንቀቅ ራስህን እወቅ

ነጌ እሱን ለማምለክ እዳትዳረግ
ሳታቅ እንዳትጎተት እንደ በግ
የእውነት ወንድምህን ትወደዋለ

💦ወንድሙን የእውነት የሚወድ ከሗላው አያማውም

💦ወንድሙን የእውነት የሚወድ ስህተቱን ለብቻው ይነግረዋል

💦ወንድሙን የእውነት የሚወድ ውድቀቱ ያሳዝነዋል

💦ለወንድሙ አርቆ የሚያስብ በፊቱ እሱን አብዝቶ ከማሞጋገስ ይጠነቀቃል

💦ለወንድሙ አርቆ ሚያስብ በኸይር ያዘዋል ከመጥፎም ይከለክለዋል።

አላህ ለሱ ብለው ተዋደው በአርሹ ጥላ ከሚሰባሰቡት የድርገን☔️
(
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ

«ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡»
[ጦሃ: 132]
Forwarded from La tehzen
«የቲምን አደራ»

የቲምን አደራ አሉን የኛ አወራ፣
ስለዚህም ጉዳይ በጥቂቱ እናውራ፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
አባት የሞተበት ገና በልጅነት፣
እናቲቱም ብትሆን አቅሟ የከዳት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እጅግ ተቸገሩ ማንም በሌለበት፣
በጣሙን ተራቡ የለም ሚጠይቁት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
በቀን አንድ ግዜ እሱንም ካገኙት፣
አንድ ልጅ ነበረ አባት የሞተበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ከእናቱ የሚኖር እሷ አቅም የሌላት፣
ነበር በረመዳን በተራዊህ ሰአት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እናቱን ጠራና እንደዚህም አላት፣
ሰዎች ተመለሱ ከተራዊህ ሰላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
እኛ ሳናፈጥር ይሄሁሉ ሰአት፣
እናቱ ምን ትበል ምን ጉድጓድ ይዋጣት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ለነፍስያ ሳይሆን ለልጇ አሳስቧት፣
ሚበላም ሚጠጣ ምንም ቁራሽ የላት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የዚ አይነትም አለ እይ አንተ ባለሀብት፣
አንተ የምትበላው በቀን 9አይነት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሌላው ይሰቃያል ቁራሽ ዳቦ ጠፍቶት፣
የቲምን በመርዳት አኼራን ገንባበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ነቢ ተናገሩ በዛ ውድ አንደበት፣
የቲምን የረዳ ከሀተይን✌️ያሉት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ካልቻልክም በእጅህ ፀጉሩን እሽለት፣
የነብዩን ትዛዝ ምትተገብርበት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧
ሀብትህንም ቢሆን በረካ ሚያደርጋት፣
ለቸገረው የቲም እጅን በመዘርጋት፣
💧💧💧💧💧💧💧💧💧💧
የአኼራ ቤትን የምታድስበት፣
አላህ ይመድበን የቲም ከሚረዱት።
💦💦💦💦💦💦💦💦


ኑርአህመድ


https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen


ያ ጀማ ይሄ ቻናል የተከፈተበት ምክንያት እናት አባቶቻችን የቲሞችን ለመርዳት እና ለመማማር ነው እና አህባቢ እረመዳን በጣት የሚቆጠሩ ቀኖች ነው የቀሩት ይሄ ወር ደርሳ ከሚፃሙና ከሚጠቀሙበት አላህ ያድርገን
እህባቢ በዚ በረመዳን ብዙ ስራ ይጠበቅብናል በረመዳን አንድ ስራ በእጥፍ በሚቆጠርበት ወር መረዳዳት አለብን '' መልካም ተግባራት ምንንም አሳንሰህ አተመልከት
ወንድምህን በብሩ ፈገግታ መገናኘት አንኳ ''
ነቢዩ (ሶ,ዐ,ወ)

ላታህዘን በሚል ስም የተጀመረ ጀማ አለ

ይሄን ጀመዐ በተለያየ ነገር መርዳት ወይም እንደ አባል ሆኖ መስራት የሚፈልግ ከስር ሚገኘዉ ስልክ ቁጥር ያናግሩን @jafu412
0965187213
ጀዛ ከላህ


(ነ,ሰ,ዐ) የቲሞችን አደራ ብለውናል እና ይሄን ጀማ ትልቅ ደረጃ እንድርሰው በአላህ ፍቃድ እንሯሯጥ
የቴሌግራም የግሩፕ ሊንካችን👇👇👇
https://t.me/resulinn
https://t.me/resulinn
Forwarded from La tehzen
አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱ
እንኳን ለተከበረው ለረመዳን ወር በሰላም አደረሳችሁ
...

ቀኑ በፆምተኞች ኑር ሲያበራ መስጂዶች በምዕመኖቻቸው ተሞልተው ውብ ሲሆኑ የአዛንታው ድምፅ በራሱ ለሀሴት ምግብ ነው ሱብሀነላህ እውነትም ሸይጣን ሚታሰርበት ወር.....

ግና...እነዝያ እናቶች ከሌላው ቀን በተለየ ቀኑ የሚጨልምባቸው፣ ሀዘን የሚወርሳቸው ፣አንገት የሚደፉት ምስኪኖች……………
እኔ ልሳቀቅ እማ.... ስቅቅ ሲሉ ስሁር ሳይበሉ ፁመው የመግሪብ አዛንታን ባልደረሰ ብለው የሚፀልዩ የየቲም እናቶች .......
"እማ አናፈጥርም አዛን እኮ ብሎዋል" የሚሉትን ህፃናት ላለመስማት ጆሮ ዳባ ብላ የምታልፈው ባይሞላላት እኮ ነው እኔ ኩርምት ልበል እማ .......
አንዳንዴማ አንጀታቸውን በመቀነት አስረው ከደቀቀ ፍራሻቸው ኩርምት ማለታቸውን ስታይ መኖር ያስጠላሀል…
ያ....አላህ..... እንዴት ያማል
እናም ውዶቼ ወደ እናንተ ስመለስ ይሄ ሁሉ የሚጠብቀው እኔን አንተን አንቺን ነው።

እናም ውዶች ይህን የተቀደሰ እና ድንቅ የሆነ ሀሳብ ከእናንተ ጋር ለመስራት #ላተህዘኖች ኑ እያሉ ነው ግን ማን አለ በዚህ ሰዓት ጀነትን እንግዛ የሚል የአሄራ ስንቅ ሰንቀው ውሰዱና ምንዳችሁን አፋፉ እያሉ ነው መቼም ወደኃላ የለም
እናም #ላተህዘኖች
#እኔ_እያለው_ሳያፈጥሩ_አያድሩም!"
በሚል መሪ ቃል ከወዲሁ ሽር ጉዱን ተያይዘውታል እንደ ከዚህ በፊቱ ለመነሻ የተወሰኑ ቤቶች ታሳቢ በማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሮዋል።
አልሃምዱሊላህ ሁሌም አንድ ስራ ስናስብ በደስታ የምንጀምረው
#ያንተ
#ያንቺ
#የእርሶ
#የሁላችሁም እገዛ እና ዱአ አብሮን እንደሆነ ስለምናውቅ ነው ሁላቹንም ጀዛከላሁም ኸይረን ከአላህ ጋር የናንተ እገዛ ተጨምሮ ካሰብነው በላይ እንደምናሳካ እርግጠኞች ነን ረመዳኑንም ያማረ የተዋበ እናደርገዋለን ኢንሻላህ……
#ለአንድ_ቤተሰብ
ሙሉ ፓኬጅ #1000 ብር
ግማሽ ፓኬጅ #500 ብር
ሩብ ፓኬጅ #250 ብር
#በአስቤዛ መሸፈን እችላለው ካሉ
🔺ዱቄት 🔺ሩዝ
🔺የሾርባ እህል 🔺ቴምር እና ዘይት


አድራሻ ካራቆሬ
ስልክ ቁጥር
📞 0938619117 ይደውሉልን
📞 0937442278
ወይም👇👇
''
@mamepro or @Oufeyret


Join us 👇👇👇
https://t.me/resulinn

https://t.me/resulinn

የየቲሞችን እንባ ተባብረን እናብስላቸው
እንታደጋቸው


ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም
ረመዷን
(9)

የረመዷን ዉስጥ ሌቦች
***

1)      ቴሌቭዝን ፡- ቻናል ሲቀያይሩ መዋል ማደር፣ ሙሰልሰላትን መከታተል አደገኛ ነገር ነው፣ የሰዉን ፆም ሊያላሽ፣ ምንዳዉንም ሊቀንስ ይችላልና ተጠንቀቁ፡፡
 
2)     ገባ ወጣ ማብዛት ፡- በረመዷን ቤት ወይም መስጊድ ይሻላል፡፡ ለከባድ ሓጃ ካልሆነ መውጣት መልካም አይደለም፡፡  ዐይን ያላሰቡት ነገር ሊያርፍ፣ ጆሮ የማይመችን ነገር ሊሰማ፣ ልቦናም ያልሆነ ነገር ሊጠረጥር ይችላል፡፡
 
3)     ማምሸት ፡- በቁርኣን፣ በዚክር፣ በዱዓ፣ በሶለዋት … ካልሆነ ማምሸት ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡ ጊዜህን ትርጉም በሌለው ነገር እንድታጠፋ ያደርጋል፣ ከኢስቲግፋር፣ ከተራዊሕ እና ተሀጁድ ያዘናጋል፡፡ ስታመሹ ጉዳት ጥቅሙን አስሉ፤ ማለዳ ላይ እንዳትቆጩ
 
4)     ኩሽና ፡- በረመዷን ትልቁ ትኩረታችሁ ምግብ አይሁን፤ ያ ከሆነ የፆም ዓላማው ይሳታል፣ ብዙ ጊዜያችሁንም በማዕድ ቤት አታጥፉ፣ ከምትበሉት በላይ በመሥራትም ምግብን አታባክኑ፤ አላህ አባካኞችን አይወድምና፡፡
 
5)     ስልክ ፡- በስልክ ረጅም ጊዜ ወስዶ ማውራት ንግግርን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ ይመራል፣ ለሀሜትና ለአላስፈላጊ ወሬ ይዳርጋል፡፡ ጊዜና ገንዘብ በከንቱ ይጠፋል፡፡
 
6)     ስስት ፡- የረመዷን ዉስጥ ሶደቃ ምንዳው ከፍ ያለ ነው፡፡ ስስት ምንዳን ያሳጣል፣ በረከትንም  ይነሳል፡፡
 
7)     ያለ ሥራ መቀመጥ ፡- ተማሪ ወይ አስተማሪ ወይ አድማጭ ሁን፤ ከዚህ ዉጭ መሆን ዕድሜን መፍጀት ነው፡፡ ቁጭትን ያስከትላል፣ ፀፀትን ያመጣል፣ አላህ ዘንድም ያስጠይቃል፡፡
 
 
8)     ሶሻል ሚዲያ ፡- ለመልካም ነገር ካልተጠቀምከው ፆምህን ያጎድላል፣ ለመልካምም ቢሆን ረጅም ጊዜህን አትፍጅበት፡፡ ጊዜህን ለቁርኣንና ለዚክር ስጥ፡፡ ዛሬ ላይ ቻት እና ጫት እጅግ ጎጂ ልማዶች ናቸዉና ተጠንቀቅ፡፡

እነኚህን እና መሰል ሌቦችን በረመዷን ዉስጥ ተጠንቀቋቸው፡፡
ወዳጆቼ አንድ ወር ታግሰን መጠቀም እንዴት ያቅተናል!!
ረመዷን
(9)
***
በሚያፈጥሩበትም ሆነ ፆም በሚይዙበት ጊዜ ዱዓ ይወደዳል። ረመዷን ዉስጥ ከልቡ የለመነ ሸዋል ላይ፣ ከሸዋልም በፊት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በርግጠኝነት ዉጤቱን ያያል። በረመዷን በቀንም ይሁን በማታ፣ በአፍጥር ይሁን በሱሑር በማንኛዉም ሰዓት ከዱዓ አትዘናጉ። የፆመ አንጀት ቢማፀን ምላሽ አይነፈገዉም። የረመዷንን ዱዓ ችላ ያለ በርግጥ በራሱ ላይ ሰሰተ። ነፍሱ የምትመኘዉን ነፈገ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የምሽት ስንቅ ለቀልብዎ❤️ [Part: ⑦⑥]👌



#ቁርኣን
🌺ሀቂቃ ዉዴታ🌺

ነቢን አፍቅሪያለሁ:
በፍቅሩ እሞታለሁ:
እሱን በማወደስ እዘፍንለታለሁ:
እሱን እሱን ብዬ ጨርቄንም ጥያለሁ:

እንዲህ የሚል በዝቷል:
በሀገሩም ሞልቷል:

ይሄ እኮ አይደለም ሀቂቃ ዉዴታ:
ተግባር ሲኖረው ነው ሚባለው እውነታ:
ፍቅር እኮ አይደለም ከበሮ በመታ:
ትእዛዙን መፈፅም የዚያን ዉድ አይነታ:

ራስህን አትሸውድ:
ነቢን እንደሚወድ:
ነብዬን ለመውደድ:
ተግባርህ ይዛመድ።

ስራህ:-ሱሪ ቀዳጅ:
ለስሙ ግን ወዳጅ:

ቁርጥህ:-ባላቶኒ:
ለስሙ ግን ሱኒ:

ዉሎህ:-ከሱሰኛ:
ለስሙ ዲነኛ:

ይሄ ሆኖ ሳለ ትላለህ ነኝ ወዳጅ:
ኧረ አላህን ፍራ ማን ያዘህ በግዳጅ:
መሆንን ከፈለግክ የነብዬ ወዳጅ:
ለትእዛዙ ስጥ ሙሉ በሙሉ እጅ።
ታላቁ ነብይ ከፈጅር ሰላት በፊት የምንሰግደውን 2 ረክዓ የሱና ( ግዴታ ያልሆነ ) ሰላትን በተመለከተ

“ خير من الدنيا وما فيها "
“ከዱንያና እሷ ውስጥ ካለው በሙሉ የበለጠ ነው “ብለዋል

ግዴታ ( ዋጅብ ) የሆነ ሰላትማ እንዴት ይገለፅ ይሆን ?!!!

ሰላታችን ከዱንያ ሸቀጦች ብቻ ሳይሆን ከህይወታችንም በላይ ነው - ህይወት ያለ ሰላት ከንቱ እጅግ ከንቱ ናትና !

https://t.me/Muhammedsirage
.......ኢፍጣር

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል “ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ የፆመኛ ሰው የአፍ ጠረን አላህ ዘንድ ከሚስክ ሽቶ በላይ ጣፋጭ ነው።
አላህም እንዲህ ብሏል ‘ምግብ ፣መጠጥና ስሜቱን ለእኔ ብሎ ነው የተወው። የአደም ልጅ ስራ በሙሉ ለራሱ ነው። ፆም ሲቀር!
እርሱ ለእኔ ነው። እርሱን እኔ ነኝ የምመነዳው።”
(ቡኻሪና ሙስሊም)
🛑 ተራዊህ በመስገድ ከሚገኙ ጥቅሞች

📌 ቀኑን በጾም ሌሊቱን በሰላት በማሳለፋችን ከደጋግ የአላህ ባሪያዎች እንመደባለን

📌 ቁርኣን በብዛት በማድመጣችን የአላህን እዝነት እናገኛለን

📌 ተራዊሕ ብዙ ሩኩዕና ሱጁድ ስላለበት ሰፊ የዱዓና የዚክር እድል እናገኛለን

📌 ከወንጀል ርቀን ጊዜያችንን በመልካም ስራ እናሳልፋለን

📌 ዒባዳ ላይ ትዕግስትን እንማራለን

📌 ሰላተል-ለይል እንለማመዳለን

📌 በተደጋጋሚ ከኢማሙና ማእሙሞች ጋር "አሚን" በማለታችን ወንጀላችን ይማራል

📌 መስጂድ ስንሄድና ስንመለስ በእርምጃችን ልክ ወንጀሎች ተራግፈው መልካም ስራዎች ይጻፉልናል

📌 ሰላት እየጠበቀን በምናሳልፋቸው ጊዜያቶች መላኢካዎች ምህረት ይጠይቁልናል

📌 የሙስሊሞችን ጀማዓ በማብዛት ሸይጣንና አጋዦችን እናስቆጫለን

📌 ከመልካም ሰዎች ጋር በመቀላቀላችን መልካም ስራዎቻችን ወደ ሰማይ እንዲወጡና ተቀባይነት እንዲያገኙ እድል ይፈጥራል

📌 ከአልባሌ ነገሮች ለመራቅ ለወጣቱ መልካም አርዓያ እንሆናለን

📌 ካመኑበትና ጥቅሙን ካወቁት ሁሉም ነገር ቀላልና የሚቻል መሆኑን በተጨባጭ እናይበታለን

📌 ቁርኣንን በብዛት በመስማት የአላህን እዝነት እናገኛለን እንዲሁም ብዙ በመስማት ትክክለኛውን የቁርኣን አቀራርም እንማራለን

📌 በቁኑት ዱዓ ወቅት ብዙ እኛ ያላሰብናቸውና መግለጽ የማንችላቸው ነገሮች ዱዓ ተደርጎ "አሚን" በማለታችን ትርፋማ እንሆናለን

📌 ከኢማሙ ጋር እስከሰላቱ ፍጻሜ ድረስ አብረን እየሰገድን ከቆየን ሌሊቱን በሙሉ ሲሰግድ ያደረን ሰው እጅር /ምንዳ እንሸምታለን

📌 የቂያማ ቀን መቆምን ያቀልልናል፥ዱኒያ ላይ ለጌታው ብሎ ረጅም ሰዓት የቆመ የቂያማ ቀን መቆም አይከብደውም

📌 ሰግደን ስንመለስ የውስጥ ደስታና እፎይታና ሌሎችንም የዲንም የዱኒያ በርካታ ጥቅሞችን እናገኛልንና ተራዊህን ሳንሰለች እንስገድ።

አላህ ያግራልን
◼️ስሑር መብላት ያለው ጥቅም


💦የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል።

ስሁር መብላት በረካ አለውና እንዳትተውት። አንድ ጉንጭ ውሃም ቢሆን (ሌላ ባየገኝ እንኳ) አትተውት። አላህና መላኢካዎች ስሁር በሚመገቡ ሰዎች ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ።
📚أخرجه أحمد وابن أبي شيبة

የአላህ መልእክተኛ በሌላ ሀዲስ፦ (ስሁር ብሉ። ስሁር መብላት በረካ አለውና) ብለዋል።
📚البخاري (1923)، ومسلم (1095).

♦️ በየቀኑ ስሁር (ሌሊት ተነስተን) በመብላት የመልእክተኛውን ሱና ህያው በማድረግ ትልቅ ምንዳና አጅር ማግኘትን እንዳንዘነጋ
#በረመዷን_ወር_የተፈፀመው_እጅግ_አስደናቂው_ገድል

ጊዜው ወርሃ ረመዷን ነው የሮም ኢምፓየር አንድትን ሙስሊም ሴት ክብሯን ገፎ ሂጃቧን አራቁቶ ዘብጥያ ያወርዳታል ። ባልተቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ እንዲሉ የሮም መንግስት ይህን ያደረገው በሙስሊሞች ላይ ያለውን ጥላቻና ንቄት ለማሳየት ነበር ።

ያች ጀግና ሴት በጊዜው ለነበረው የአባሲድ ኸሊፋ ሙእተሲም ቢላህ መልእክት ላከች ዋ ! ኢስላማ ! ዋ ሙእተሲማ ! እንደት ሙእተሲም ቢላህ ባለበት የአንድት ሙስሊም ሴት ክብር ይደፈራል ስትል !!
ሙእተሲም ቢላህ ይህንን ሲሰማ ንደቱን መቆጣጠር አልቻለም ። እናም ለሮሙ መሪ ደብዳቤ ላከበት ። ደብዳቤ እንደዚህ ይላል " አንተ የውሻ ልጅ ! ትለቃት እንደሆነ በአስቸኳይ ልቀቃት አለበለዚያ መጀመሪያው ካንተ ጋር መጨረሻው ደግሞ ከእኔ ጋር የሆነን ሰራዊት አዘምትብሃለሁ " አለው ።

የሮሙ መሪ የሚእተሲምን ማስፈራሪያ ችላ በማለት ሴትዮዋን እንደማይለቅ ገለፀ። በዚህ ጊዜ ሙእተሲም ለዚያች ለአንድት ሙስሊም ሴት ክብር ሲል በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሰራዊቱን አሰልፎ በሮም ላይ ዘመተ ። ለአንድት ሙስሊም ሴት ክብር ሲል !!!!
#አሙሪያ ላይ የሮም ሰራዊት ከሙስሊሙ ሰራዊት ተላተመ ። የሮም ጦር ተደመሰሰ ። ያች ጀግና ሙስሊም ሴትም ከሮሞች እጅ ነፃ ወጣች ። የሮም ጦር መሪ ያ ያችን ክብርት ያዋረዳት መሪ ተይዞ ተማርኮ መጣ ። እናም ለዚያች ጀግና ሴት ሙሉ ስልጣኑ ያንቺ ነውና ተበቀይው አሏት ። እርሷ ግን አለች " አውፍ ብየዋለሁ "!!!!! አሏሁ አክበር !

ታላቁ ሙሃዲስ ኢማም አህመድ ኢብኑ ሀምበል ቁርአን የአላህ ቃል አይደለም በል እያለ ብዙ ስቃይ ያደረሰባቸው ሙእተሲም ለአንድት ሙስሊም ሴት ክብር ያደረገውን ባዩ ጊዜ በደስታ በመፈንደቅ " እርሱ ከኔ ጋር ይቅር የተባለ ነው ( ፈሁዎ መእፉውን ኢንዲ ) " አሉ ! ኢማሙ አህመድ ግርፋታቸውን ስቃያቸውን ረሱት ። የርሳቸው ስቃይ ለአላህ ሲባል ነውና !!
ልብወለድ የሚመስል እጅግ አኩሪ ታሪካችን !!

ዛሬ ሙእተሲም ኖሮ ይህ በቢሊዮን የሚቆጠር ሙስሊም ያለበትን የውርደት ኑሮ ቢያይ ምን ይሰማዋል ?!!! ብስጭቱ ብቻ አይገድለውም ??!!
ዛሬ ኡይጉሮችን ፣ ፍልስጤሞችን ፣ ሮሂንጊያዎችን ፣ ሶሪያዎችን ፣ የመኖችን ቢያይ ምን ይሰማዋል ?
ዛሬ እነዚህን ሀሞታቸው የፈሰሰ ሙስሊም ተብየ መሪዎች ቢመለከት ምን ይውጠዋል ?

ፍልስጤሞችም ይላሉ ዋ! ሙእተሲማ !!!

ዋ ! ሙእተሲማ !

ተደራሽ ይሆን ዘንድ ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድዎ ያስተላልፉ ከማይቋረጠው አጅር ተካፋይ ይሁኑ
የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/httpsLatahzen

https://t.me/httpsLatahzen
Forwarded from አቡ ሙዓዝ (Abu muaz) (አቡ ሙዓዝ ሀሰን)
ለደሴ ነጋዴዎች
==========
اَلسَلامُ عَلَيْكُم وَرَحْمَةُ اَللهِ وَبَرَكاتُهُ‎

እንደሚታወቀው ደሴ ውስጥ ሱና ወዳድ የሆኑ ነጋዴዎች አሉ

ይሁን እንጂ የሚያሳዝነው ነገር ከሱና መሻይኾቻቸው ጋር በጥልቅ አይተዋወቁም።

ለምሳሌ የደሴ መሻይኾች አንዳቸውም ኑሯቸውን የሚመሩበት ሲስተም የላቸውም ወሏሂ የወር ገቢ መቶ ብር የሌለው ባለ ቡዙ ልጅ የሆነ ሸይኽ ወይም ዳዒ አለ

ስለዚህ አናንተ የደሴ ሱና ወዳድ ነጋዴዎች ሆይ እባካቹህ ለማንም የጫት ቀርጥ በጉያው ይዞ ለሚዞር ለማኝ እየመዘዛቹህ ብራቹህን አትጨርሱ!!

ለሱና መሻይኾች ደፍረው ለማይለምኑ ቁጥብ ሰለፊይ ማይኾቻቹህና ዳዒዎቻቹህ ስጡ።

እንድትጠቀሙ ነው የጠቆምኳቹህ
የብናኝን ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል።(ኣዝ-ዘልዘላህ)
የብዙ ሰወች የኣንድ ቀን የሻይ ቡና ሂሳብ ተደምሮ በችግር ላይ ላሉ የቲሞችና ለኣቅመ ደካሞች ቢሰጡ ለእነሱ የህልውናችን ጉዳይ ሁሉ ሊታደግ የሚችል ነው።

ሰደቃ ወደ ጀነት መግቢያ ምክንያት ነው።ይህንን ሸይጧን የዘጋብንን በታሰረበት ወር የመልካም በር እኛም መልካም በመስራት እንክፈተው።

🌴🌴ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም 🌴🌴

ወደዚህ መልካም ስራ የሚጠራችኁ።።።ላተህዘንን ቆም ብለን ለጥሪው ምላሽ እንስጥ።

የመልካምነት ትንሽ የለውም። ያለንን በማበርከት ኣጋርነታችን አናሳይ!!

https://t.me/resulinn

https://t.me/httpletehzen
#ያለ_ሶላት_ህይዎት_የለም !!
<~~>
ምን ጠጋ ጠጋ ነው ሶላት መከልከሉ?
የአጴው ስርኣት ናፈቃችሁ ገድሉ?
ሙስሊሙን ጠቅላላ መጨቆን መግደሉ?
ወይ ይለይላችሁ ሙስሊም ይጥፋ በሉ!!
ካልሆነ ሙስሊሙን ያው እንደምታውቁት
በፍፁም የለንም ህይዎት ያለ ሶላት
ምነው የኛ መኖር እንዲህ ከበዳችሁ
በሰላም በተጓዝን ምን ደረስንባችሁ
በስልጣን በወንበር አልተጋራናችሁ
ፖለቲካ አልገባን አልተሻማናችሁ
በሶላት ቀልድ የለም በዚህ አትምጡብን
ሰው ህይዎቱን ካጣ ይጠብቃል ምንን?
ሶላታችን ማለት ይህ ነው ህይዎታችን
ያለ ሶለት ህይዎት የለም እዎቁልን
ያለ ሶላት ህይዎት የለም በእስልምና
በተዋበው እምነት በቀናው ጎዳና
ቀንታችሁ ከሆነ ባንድ እንዝለቅ ኑና
ካልሆነ ምንድን ነው ሲቀኑ ጭቆና!?
ያውም በህይወት ላይ በሶላት ላይ ጫና!?
ኧረ ደግ አይደለም አያምርም በናንተ
ለውጥ መጥቷል ብሎ ላገር ባሰሞተ
ጭቆናን ለማጥፋት ቃል ገብቶ ላተተ
አንገቴን ቀልታችሁ ስጋየን ቦጫጭቁት
ቢሻችሁ ለአሞራ ቢሻችሁ ቅበሩት
በህይወት እስካለሁ ሶላቴን አትንኩት
በፍጹም የለንም እዎቁልን በእውነት
ሶላት ያለ ሂዎት ሂዎት ያለ ሶላት!!


https://t.me/httpsLatahzen
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የረጲ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ወላጆች ተቃውሞ


እንዲህ ጀግና ሁኑ
La tehzen
የብናኝን ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል።(ኣዝ-ዘልዘላህ) የብዙ ሰወች የኣንድ ቀን የሻይ ቡና ሂሳብ ተደምሮ በችግር ላይ ላሉ የቲሞችና ለኣቅመ ደካሞች ቢሰጡ ለእነሱ የህልውናችን ጉዳይ ሁሉ ሊታደግ የሚችል ነው። ሰደቃ ወደ ጀነት መግቢያ ምክንያት ነው።ይህንን ሸይጧን የዘጋብንን በታሰረበት ወር የመልካም በር እኛም መልካም በመስራት እንክፈተው። 🌴🌴ላተህዘን የመረዳጃ ተቋም 🌴🌴 ወደዚህ…
💢ለረጅም ወራት "ያ አላህ ለረመዷን አድርሰን" ስንል ነበር እነሆ በራሕመቱ ለረመዷን አድርሶናል አልሀምዱሊላህ።

አሁን ዱዓችን ሊሆን የሚገባው

"🔷ያረብ መልካም ስራዎችን ወፍቀን አግራልንም ስራችንም ተቀበለን"

በረመዷን ወር ዋና ዋና ከሚባሉ መልካም ስራዎች ውስጥ

↖️/ ፆም (ዋናውና ትልቁ ነው)
↖️/ ሰላት (ፈርዱም ሱናውም)
↖️/ቁርኣን
↖️/ ዱዓ
↖️/ ሰደቃ (ፆመኛን ማስፈጠርም ጭምር)

↙️🔹እነዚህንና ሌሎችንም አላህ የሚወዳቸው ስራዎችን እናብዛ
👉ዋናው ነገር ረመዷንን ማግኘቱ ሳይሆን በርሱ መጠቀሙ ነው።