#ሶላት_እንሰግዳለን!!
-----------//-------------------
መስቀል እሚሸከም እስካለ ጎረቤት፡
ሶላት እንሰግዳለን በየ ትምርት ቤት፡
ልከላከልላት እምነቴን ከሾህ ስር፡
በተውሒዱ ፈረስ ልብረር እንደ ንስር፡
በሁለቱም ሀገር ሁሌም እንዳልከስር፡
--------------------//----------------
ጌታችን ነውና የደነገገልን፡
ሀገር ከሚረበሽ ስግደት ፍቀዱልን፡
ስገዱ ብለዋል እኔ እንደሰገድኩት፡
ምን እያላችሁ ነው እኔ መች አወኩት?
ነብዩ ሙሀመድ ናቸው ያፀደቁት፡
አይገባችሁም እናንተ ልትንቁት፡
አይደለም ለመንቀል እንዳትነቀንቁት፡
የሙስሊሙን አቅም ትዕግስቱን እወቁት፡
--------------------///------------------
ምነው መጨቆኑ ሙስሊም ያገሬ ሰው፡
ለፍቶ ጥሮ ግሮ ሸምኖ እሚለብሰው፡
አያት ቅድመ አያቴ ታርደው በየተራ፡
በደሉ ቢቆጠር ይሞላል ጎተራ፡
ኢስላምን ፅፈዋል በደማቸው ቀለም፡
ግን ለፍትህ እንጂ ለውርደት አይደለም፡
እኔም የነርሱ ልጅ ለእምነቴ እሞታለሁ፡
ተኩሸ ባልገድልም ለመሞት ግን አለሁ፡
ማንም ፕሮፌሰር ኢስላሜን ሲከዳት፡
ውርደታሙ ሁሉ እንዳላይ ሲያወርዳት፡
ደጀን ልሁን እኔ የኢስላሜ እረዳት፡
----------------------//---------------
በሰባቱም አህጉር በሩሲያ አሜሪካ፡
የእምነቴ ጥላት ምን ሴራ ቢያቦካ፡
በፍፁም አይችልም ኢስላሜን ሊነካ፡
------------------//--------------------
ይልቁን እንኑር ባይኖርም ሙሀባ፡
ከጥንት ጀምሮ ምን እንኳን ባይረባ፡
አዳዲስ ህጎችን አታምጡ አትነካኩን፡
ሀገር አታፍርሱ አታድርጓት ብኩን፡
የሙስሊሙን ብቃት አታውቁትም ልኩን፡
------------------//-------------------
#ከጠላቶቻችን_ህግ_ኮርጃችሁ፡
#የእህቴን_ሒጃብ_እንግፈፍ_ካላችሁ፡
#የኢስላም_ጥላቻን_ካጠናከራችሁ፡
#የነጭችን_ሀሳብ_ይዛችሁ_መጥታችሁ፡
#ለነገሩ_ዱሮስ_መች_ጤነኞች_ናችሁ!?
------------------------------------------
የተወለድኩባት የማንነት ክብሬን፡
የአባቶቼን ርስት የምሰጣት ፍቅሬን፡
ዳሩል ሒጅረተይኒ ተወዳጅ ሀገሬን፡
ቀማኛና ሌባ ዘራፊ ከበዛት፡
የፍትኋን ሰንደቅ የነጃሽን ግዛት፡
የአህመድ ኢብራሒምን የሰላሟን አርማ፡
በኢስላም ጠላቶች በመሀይም ኮርማ፡
-------------------//---------------------
እንደት እንኗኗር መብታችን ተገፎ፡
በመንግስት በኩል ሴራው ተደግፎ፡
ለዚህ አድሎ አሰራር እውቅና እየሰጠ፡
በፖለቲካ ስም ሸፍጥ እያሳለጠ፡
ኢስላም ጥላቻውን ደፍሮ ከገለጠ፡
የእኩልነት ወሬው ከተገለበጠ፡
-----------------//------------------
በደሉን ይቀጥል በቃ ይሞክረን፡
ሙስሊሙን ማግለሉን በይፋ ይንገረን፡
#ጴንጤ_እየሰበከ_በፖሊስ_ታጂቦ፡
#እየተጠመቀ_ወታደሩ_ቀርቦ፡
#ተዘርሮ_እያየን_በእዩ_ጩፋ_እርግጫ፡
ሙስሊም ሶላት ሲሰግድ ምንድን ነው መግለጫ፡
ምን አይነት በደል ነው ምን አይነት ግልምጫ፡
ምን አይነት ልሽቀት ነው ምን አይነት ሩጫ፡
የምን ማታለያ ምን አይነት ማምለጫ፡
---------------------//--------------------
ስሙን አሳምሮ ብሎ ብልፅግና፡
ኢስላምን አግልሎ ከሰራ ብልግና፡
አንደራደርም በኢስላም ቀኖና፡
ሞት እስከሚመጣ እንሰግዳለን ገና!!
------------------//-------------------
ኦሮሚያን ሾልኮ ሔዶ እስከ ባሌ፡
በአድስ አበባ ገብቶ በቦሌ፡
ከምፅዋ በር እስከ ኤርታሌ፡
ከመተማ ጫፍ እስከ ሞያሌ፡
ሙስሊሞች አሉ በሀገሪቱ፡
በደል ቢሆንም ዱሮም ስሪቱ፡
----------------//------------------
ጠላት አክሽፈው የገረሰሱ፡
የምነቴን ጠላት የደመሰሱ፡
አሉኝ አበዎች የታሪክ አውራ፡
ለእምነታቸው የሰሩ ስራ፡
የነዚያ ትግል አስተምሮኛል፡
እምነቴን ልቀቅ እኔ መሮኛል፡
በደል ግፋችሁ አንቀጥቅጦኛል፡
-----------------------------------
#እንሰግዳለን___!!
በሁሉም አቅጣጫ ዋልታና ማዕዘን፡
ሶላት እንድንሰግድ አሏህ ነው ያዘዘን፡
አሏሁ አክበር በሚል የነቢላል አዛን፡
ጀግና ልጆች አሏት አስገራሚ ሚዛን፡
የጀግና ልጅ እናት ነችና ኢስላሜ፡
አስጠብቃታለሁ ፈሶ ንፁህ ደሜ፡
የእምነቴ ባንድራ ይተከል በአፅሜ፡
ኢስላም አይደፈር፤
ከህያዋን ተርታ እኔ ልጇ ቁሜ፡
እንኳን በአይን ብሌን አላይም በህልሜ፡
--------------------//----------------
ተወልዶ ከምድርሽ ከለምለምሽ አፈር፡
ጫካ ነው የገባው ያ ጦልሀ ጀዕፈር፡
ኢስላም ያንች ክብር መቼም አይደፈር፡
ዛሬም አሉ ልጆች የዑመር ሰመተር፡
እጂህን አንሳልን መንግስት ተሰተር፡
በኢስላም አትግባ ተጠንቀቅ ተአደብ፡
እየነገርንህ ነው አስቀምጠን ገደብ፡
----------------//----------------------
በአሏህ ይሁንብን ሶላት እንሰግዳለን፡
ግን አመፅ አንሻም ሀገር እንወዳለን፡
ለመንግስታችን ግን ጥሩ ጥያቄ አለን፡
ጴንጤ በፌደራል ታጂቦ ሲዘመር፡
ሙስሊም በመስገዱ ለምንስ ይመርመር!?
------------------------//---------------------
በእምነት የተጣመርን ዘር የማናስቀድም፡
እኛ ሙስሊሞች ነን የሙስሊሞች ወንድም፡
ማንም ምንም ቢሆን በደልን አንወድም፡
ለሌሎች በማሰብ ኑረናል ስንወድም፡
እናም እባካችሁ ኢስላምን አትንኩ፡
ጥላቻ አውሯችሁ ውሸት አትፈብርኩ፡
ይሰማችሁ ፍትህ አስቡ ሰዋዊ፡
በአመራራችሁ ላይ ሁኑ ፍትሀዊ፡
---------------------///---------------
እምቢ ካላችሁ ግን እኛም እነሆ አለን፡
ሱጁድ እያደረግን እንገደላለን፡
የአሏህ ትዕዛዝ ነው ሶላት እንሰግዳለን፡
------------------///-----------------------
#ኑር

ህገ መንግስታዊ መብትን በመመሪያ መሸርሸር
❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄❄
ሙስሊም ተማሪዎች «በትምህርት ቤታችን መስጊድ ይሰራል» ብለው አልጠየቁም።አልያም ት/ቤቱ የመስገጃ ስፍራ ያዘጋጅልንም አላሉም።የተለየና አዲስም ጥያቄ አላነሱም።እንደየትምህር ቤታቸው ከፊሎቹ በአረፍት ሰዓት ሌሎች ተማሪዎች ሲጫወቱና ሲዝናኑ ከፊሎቹ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ጊቢ ሲሰግዱ ሌሎቹ ወጣ ብለው ሰግደው ይመለሱ ነበር። በዚህ ሁኔታ ሳሉ ትምህርት ቢሮው አዲስ ነገር አመጣባቸው። በትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ዉስጥም ሆነ ወጥቶ መስገድ አይቻልም የሚል መመሪያ አመጣ። ለመሆኑ መመሪያ ህገ መንግስታዊ መብትን የመሻር መብትስ እንዴት ይኖረዋል?
በሀገራችን ህገ መንግስት የህጎች የበላይ ህግ ህገ መንግስት ነው። ከርሱ ቀጥሎ የሚቀመጠው ፓርላማ የሚያወጣው ህግ ሲሆን በማስከተል ደግሞ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የሚያወጣው ደንብ ነው።ከደንብ ቀጥሎ ደግሞ አንድ ሚኒስተር መስሪያ ቤት የሚያወጣው መመሪያ በመጨረሻ ደረጃ ላይ ይገኛል።በደረጃ ካየን ህገ መንግስቱ በአንደኛ ደረጃ ላይ ሲገኝ መመሪያ ደግሞ በአራተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
በደረጃም ካየን ፓርላማ የሚያወጣው ህግ መንግስቱን መቃረን የለበትም።ደንብም አዋጅን መቃረን የለበትም። መመሪያም ደንብን መቃረን የለበትም። ከተቃረንም ዉድቅና ተቀባይነት የሌለው ይሆናል።ሆኖም በተደጋጋሚ ጊዜያት የትምህርት ሚኒስቴር ራሱ በሚያወጣው መመሪያ ከደንብና ከአዋጅ አልፎ ህገ መንግስቱን በመቃረን የሙስሊሞችን መብትን ለመሸራረፍ ሲፈልግ ተስተውሏል።
በተደጋጋሚ ጊዜያት መመሪያዎችን ሲያወጣ ለሙስሊሞች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ተማሪዎች ነው ብሎ ሲያስተባብል ይደመጣል። በተግባር ግን ሁሌም ኢላማ ሲያደርግና ለማገድ ሲጥር የሚታየው ሙስሊም ተማሪዎችን ነው። ነገሩን በምሳሌ ከገለጽነው በረመዳን ወር ዉስጥ በቀን ትምህርት ቢሮ መመሪያ በማውጣት "በየትምህርት ቤቱ በሚዘጋጀው የምገባ ሂደት ለሁሉም ተማሪ ተገኝቶ መመገብ ግዴታ ነው።" ብሎ መመሪያ እንደማውጣት ነው። በዚህ ምሳሌ መመሪያው ለሁሉም ነው ቢባልም በረመዳን በቀኑ ጊዜ እየጾሙ መመገብ የማይችሉትን ሙስሊሞችን በተለየ ኢላማ ኢንደሚያደርግ እሙን ነው።
ለማንኛው የአሁኑን የትምህርት ቢሮ መመሪያን ባላየውም በ1999 የትምህርት ሚ/ር አዘጋጅቶ በነበረው መመሪያ ላይ በጊዜው በሠለፊያ ጋዜጣ ላይ በብዕር ስም አስነብቤ ከነበርኳቸው ጽሁፎች መካከል ቀጣዩን በጉዳዩ ላይ ግንዛቤ አንዲኖረን ዘንድ እንዳለ ቀርቧል። መልካም ንባብ።
ኃይማኖትዊ መብትን የሚፃረረው የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
በየዘመኑ የነበሩ የኢትዮጵያ መሪዎች ህገ መንግስት ቢኖራቸውም ህገ መንግስቱን እንዳሻቸውም በመተርጐም ባሰኛቸው መንገድ ሲጠቀሙበት ቆይተዋል። ይህ እንዳይሆን በ1987 የጸደቀው ዘመነኛው ሕገ መንግሥት ከቀድሞዎቹ በተሻለ መልኩ ማብራሪያ ተቀምጦለታል።ሕገ መንግሥቱን በወቅቱ ያፀደቁ አካላት በእያንዳንዱ አንቀፅ ምን ማለት እንደ ፈለጉ በቃለ ጉባኤ አስፍረዋል።ማንኛውም ግለሰብ ይሁን የመንግስት መሥሪያ ቤት አንቀፁን ብቻ ወስዶ ለራሱ የሚመቸውን ትርጉም የመስጠት መብት የለውም።
ኾኖም ትምህርት ሚኒስቴር ልክ እንደ ቀደምት ጊዜ የሕገ መንግስቱ ማብራሪያ እና ቃለ ጉባኤ ወደ ጐን ትቶ ለአንቀፆች አዲስ ትርጓሜ አበጅቶ ለሙስሊሙ የታለመ የሚመስል መምሪያ አዘጋጀ።
የሕገ ወጡ መመሪያ ችግር ከርእሱ ይጀምራል።ርዕሱ "በትምህርት ተቋማት የአምልኮ ሥርዓት የሚመለከት የወጣ መመሪያ" ይላል።ይህም ማለት በአንድ እምነት ውስጥ ጣልቃ በመግባት መንግስት የአምልኮት ሥርዓት አወጣ ማለት ነው።ይህ ደግሞ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 11 ንዑስ አንቀፅ 3 ላይ"መንግስት በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም ሃይማኖትም በመንግስት ጉዳይ ጣልቃ አይገባም" የሚለዉን በቀጥታ ይቃረናል።ዐዋጅ ቁጥር 471/98 ትምህርት ሚኒስቴር እንዲህ ያለዉን ፀረ ሕገ መንግስታዎ መመሪያ እንዲዘጋጅ ሥልጣን ይሰጠዋልን? ዐዋጁ ትምህርት ሚኒስቴር አወጣዋለሁ የሚለውን ከሕገ መንግስቱ ጋር የሚቃረን መመሪያ የማዘጋጀት ሥልጣን ተሰጥቶኛል" ሊል አይችልም።
መመሪያዉ በክፍለ አንድ አንቀፅ 4 "የመመሪያው አስፈላጊነት" በሚለው ርዕስ ሥር "በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት በአንቀፅ 25 በሃይማኖቶች ምክንያት አድልዎ እንደማይፈፀም የተደነገገውን እና በአንቀፅ 27 የተደነገገዉ የሃይማኖት ነፃነት በትምህርት ተቋማት ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም በዚሁ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀፅ 90 (2) የተመለከተውን "ትምህርት በማንኛውም ረገድ ከሃይማኖት፣ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተፅዕኖዎች ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት የሚለዉ ተፈፃሚ ማድረግ" ይላል።
ይህ የሕገ መንግስት አንቀፅ ሁሉም ሰዎች እኩል መሆናቸዉን እንጂ እኩል ስለሆኑ ልዩነት እንዳ ይደረግባቸው ሃይማኖታዊ ነፃነታቸውን ንጠቁ ይላልን? ሁሉንም ያለልዩነት በእኩልነት ማስተናገድ እና በሕግ ፊት እኩልነታቸዉን ማረጋገጥ ወይስ ሌላ ዓላማ አለው? በመመሪያው አስፈላጊነት ሥር "በአንቀፅ 27 የተደነገገዉን የሃይማኖት ነፃነት በትምህርት ተቋማትም ተግባራዊ ማድረግ" ይላል።
ሕገ መንግስቱ በአንቀፅ 27 ሥር የፈቀዳቸውን የሃይማኖት ነፃነት የምናስፈፅመዉ ተግባራዊ ማድረግ ወይስ የተፈቀደውን በመከልከል? ይህ መመሪያ በኅብረት ሰላትን ይከለክላል።
ሕገ መንግስቱ አንቀፅ 27(1) ግን ይፈቅዳል።ይህ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ በሕገ መንግስቱ የተረጋገጡትን የሃይማኖት መብቶች በማንኛውም ቦታ ለማረጋገጥ የወጣ ከሆነ ዓላማው ሊፈፀም የሚችለው በሌሎችም ቦታዎች ሲተገበሩ የነበሩ መብቶችን በማረጋገጥ እንጂ በመገደብ አይደለም። መመሪያው ግን መብትን የሚሸራረፍ ብሎም የሚያግድ ነው።
የሕገ መንግስቱ አንቀፅ 90(2) ከሃይማኖት ተፅዕኖ ነፃ መሆን ያለበት ትምህርቱ እንጂ ተማሪው አይደለም። ትምህርቱ ዓለማዊ ይሁን የሚለዉን ስርዓት ለማረጋገጥ የወጣ መመሪያ ከኾነ ይህ መርሕ ሊረጋገጥ የሚችል የአምልኮ ሥርዓቶችን በመገደብ ሳይሆን በትምህርት ሥርዓት ውስጥ የሃይማኖት ተፅዕኖን በመግታት ነው።
በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 25 መሠረት እንደ መመሪያው "የዚህ ወይም የዚያ እምነት ተከታይ ነኝ ወይም ነው/ናት" የሚል በተማሪዎች መካከል ምንም አይነት ልዩነት እንዳይኖር ማድረግ አግባብ አለመኾኑን ያስረዳል። ተማሪዎቹ መጀመሪያውኑ የተለያየ እምነት ስላላቸው በእምነታቸው መሠረት ልዩነት ይኖራቸዋል።ነገር ግን እንደ ሕገ መንግስቱ በዚህ ልዩነት ምክንያት አድልዎ እንዳይኖር ነው መደረግ ያለበት እንጂ ልዩነትን መናድ አይደለም። ተማሪዎቹ በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 27(1) የተረጋገጠላቸውን የፈለጉትን እምነት የመከተል እና የመተግበር መብታቸው ሲረጋገጥ እንደ እምነቱ ልዩነት በተማሪዉ መካከል ልዩነት ይኖራል።ይህ የመመሪያዉ ዓላማ ፀረ ሕገ መንግስት እና ሁሉንም ሃይማኖት ጨፍልቆ አንድ ወደ ማድረግ የሚሄድ ነው።ይህ ደግሞ የማይሞከር ቅዥት ነዉ።
የመመሪያዉ ዓላማ በሚለው ርዕስ ሥር ዓላማውን ለማሳካት ተብሎ ከስር የተዘረዘሩት እርምጃዎች አድልዎን ከማስቀረት ይልቅ የሃይማኖት ነፃነትን ለመገደቡ ያለሙ ናቸው።አድልዎን ማስቀረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ 25ን መተግበር ማለት ነው።ይህ ደግሞ ሁሉንም ሳያበላልጡና ለአንዱም ሳያዳሉ በእኩል ዐይን ማየት እንጂ የሃይማኖት ነፃነትን ማገድ አይደለም።

መመሪያው በዓላማ 5.3 ሥር የተቀመጡት ትክክለኛ ሕገ መንግስታዊ ናቸዉ።ነገር ግን ዓላማውን ለመተግበር የተደነገጉ ድንጋጌዎች ሁሉም ከዓላማው እጅጉኑ ተፃራሪ ናቸዉ።
በመመሪያዉ ክፍል ሁለት ሥር ሂጃብን ይፈቅድና ኒቃብን ይከለክላል። ይህ አገላለፅ በራሱ ችግር አለበት። በመጀመሪያ ደረጃ ሂጃብ ማለት የቱ ነው? ይህቺ ወንዶችን የሚያደጓት ጥምጣም ዓይነት ነች ሂጃብ? ወይስ ጅልባብ የሚባለዉ? አልያስ ዋጂብነቱ በከፊል ዑለሞች የሚታወቀው ኒቃብ? የቱ ነው? ትምህርት ሚኒስቴር በሃይማኖታዊ ጉዳይ ጣልቃ ገብቶ ይህ ይቻላል፤ይኸኛው ደግሞ አይቻልም ማለት ይችላልን? ሃይማኖቱን የመተርጎም ሥልጣን የመንግስት ወይስ የሃይማኖቱ ምሁራን? መመሪያው አለባበስ በሚል ርዕስ ሥር "የክርስትና እምነት ተከታይ መነኮሳት እና ካህናት እንዲሁም የእስልምና እምነት ተከታይ ሼኾች ብቻ በትምህርት ተቋማት ቆብ ሊያደርጉ ወይም ሻሽ ሊጠመጥሙ ይችላሉ።" ይላል።
ለመሆኑ ማን ነው መነኮሳት፥ ካህናት እና ሼኮች እንደ ሆኑ የሚለየዉ? ትምህርት ሚኒስቴር በምን መልኩ እና መመዘኛ ይህ ሊል ይሁን? ይህስ በሕገ መንግስት አንቀፅ 11(3) "መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም። ሃይማኖትም በመንግስ ጉዳይ ጣልቃ አይገባም።" የሚለውን አይጥስምን?
መመሪያው "በትምህርት ተቋማት ጊቢ በምንም መልኩ የማንኛውም ሃይማኖት ተከታዮች በቡድን የአምልኮ ሥርዓት መፈፀም አይችልም" ይላል።
ህገ መንግስቱ "ማንኛውም ሰዉ የማሰብ፣የኅሊና እና የሃይማኖት ነፃነት አለው።ይህ መብት ማንኛዉም ሰው የመረጠውን ሃይማኖት ወይም እምነት የመያዝ ወይም የመቀበል፣ ሃይማኖቱን እምነቱን ለብቻ ወይም ከሌሎች ጋር በመሆን በይፋ ወይም በግል የማምለክ፣የመከታተል ፣የመተግበር ፣የማስተማር ወይም የመግለፅ መብትን ያትታል።"ይላል። ስለሆነም የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ሕገ መንግስቱ በመግለፅ የሚቃረን በመሆኑ በመኾኑ ተፈፃሚነት አይኖረውም። ይህ የትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ ኢትዮጵያ ተቀብላ ያፀደቀችውን ዓለም አቀፍ ሕጎች በቀጥታ የሚቃረን ነው።
ለአብነት በዩኔስኮ የሰብአዊ መብት ስምምነት ላይ :- "እያንዳንዱ ሰዉ የሀሳብ፣የኅሊና እና የሃይማኖት ነፃነት መብት አለው።ይህም መብት ሃይማኖቱን ወይም እምነቱን የመለወጥ ፣ነፃነትን ብቻውን ወይም ከሌሎች ጋር በኅብረት በይፋ ወይም በግል ኾኖ ሃይማኖቱን ወይም እምነቱ የማስተማር፣በተግባር ለመግለፅ፣የማምለክ እና የማክበር ነፃነትን ይጨምራል።"ይላል። ታዲያ ትምህርት ሚኒስቴር ይህን የዩኒስኮን ዓለም አቀፍ ስምምነት የሚጥስ መመሪያ እንዴት አዘጋጀ?
በኢትዮጲያ ሕገ መንግሥት መሠረት ማንም አካል ስላሰኝው ብቻ የአንዱን ሃይማኖት ተግባር ማገድ እንደ ማይችል ተገልጿል።ሕገ መንግስቱ በአንቀፅ 27(5) ላይ "ሃይማኖትን እና እምነትን የመግለፅ መብት ሊገደብ የሚችለው የሕዝብ ደኅንነት፣ ሰላም፣ ጤና ፣ ትምህርት፣ የሕዝብ የሞራል ሁኔታ፣ የሌሎች ዜጎችን መሠረታዊ መብቶች፣ነፃነቶች እና መንግስት ከሃይማኖት ነፃ መሆኑን ለማረጋገጥ በሚወጡ ሕጎች ይሆናል።" ይላሉ።
ነገር ግን መመሪያው በድፍኑ የተከለከሉት ሃይማኖታዊ ድርጊቶች በሕገ መንግስቱ እንደ ተጠቀሰው አደገኛ ሁኔታ ስለመፍጠራቸዉ የቀረበ ነገር የለም።ገና ለገና ይሆናሉ ተብለው ሳይሆን ፈጥረው ሲገኙ ብቻ ነው።ይህም ቢሆን ዝም ተብሎ በአንድ መሥሪያ ቤት ፍላጎት ብቻ የሚሆን ሳይሆን በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 13(2) ላይ እንደ ተገለፀው ከዓለም አቀፍ መርሆች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም ይኖርበታል።
በዮኔስኮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ሰነድ አንቀፅ 29(2) እንዲህ ይላል፦
"እያንዳንዱ ሰዉ በመብቶቹ ፣በነፃነቶቹ በሚጠቀምበት ጊዜ የሚታገደው የሌሎችን መብቶች እና ነፃነቶች በሚገባ ለማስከበር ብቻ በተደነገጉ ሕጎች እና የግብረ ገብነት፣ የጠቅላላውን የሕዝብ ፀጥታ እና ደኅንነት በዴሞክራሲያዊ ፣ማኅበራዊ ኑሮ ትክክለኛ የኾነዉ ተፈላጊ ጉዳይ ለማርካት በተወሰነው ብቻ ነው።"
በመግቢያችን እንደገለፃነው ሕገ መንግስቱ መተርጎም ያለበት በማብራሪያው እና በወቅቱ ሲፀድቅ በነበረዉ ቃለ ጉባኤ አማካኝነት መኾን ይኖርበታል። ሃይማኖታዊ ተግባራት ላይ የሚጣል እገዳን በሚመለከት ለምሳሌ በ1948 በወጣው ሕገ መንግስት አንቀፅ 40 እንዲህ ተቀምጧል፦
"የሕዝብን መልካም ጠባይ ወይም ፀጥታን ወይም ፖለቲካ ረገድ የሚያውክ ካልሆነ በቀር በንጉሠ ነገሥቱ መንግስት ግዛት የሚኖሩ ሰዎች በሕግ የሃይማኖታቸው ሥርዓት አክብረው በነፃ ለመፈፀም አይከለክሉም።" ይላል። ይህ ገደብ ሕገመንግስቱ የነበረ መሆኑን ያስገነዝበናል።
እንደዚሁም በአላማው ስር በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 27(5) ሥር የተገለጹ ገደቦችን በሕግ አግባብ ገደብ ለመጣል መሟላት ያለበት ጉዳይ የተባለው ገደብ ህጋዊ (Legitimate) ያሁኑ ሕገመንግስት ውስጥ በግልጽ የተቀመጡ የኃብረተሰቡ ውስጥ ጥቅሞች ለማስጠበቅ "አድሏዊነትነው የሚያስከትል መሆን የለበትም" ከሚለው የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ማብራሪያ አንጻር ስንመለከተው መመሪያው አድሏዊ ውጤትን የሚያስከትል ነው።
ምንም እንኳ መመሪያው አንቀጽ 5·2 "አድሎን የማስወገድ አላማ አለኝ" ቢልም ዝርዝር ድንጋጌዎች ስንመለከት በአንድ ኃይማኖት በኢስላም ላይ ያነጣጠሩ ሆነው እናገኛቸዋለን። ከዚህም በላይ ሊነጻጸሩ የማይችሉ ነገሮች በአንድ ላይ መጨፍለቅ በራሱ አድሎዊ ነው።
ስለዚህ ጠቅላላ መመሪያው በሃይማኖት ላይ እንደተደረገ ገደብ ዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ድንጋጌዎች በተለይ( Iccpr) ቅድመ ሁኔታዎች ጋር የማይጣጣም ነው።
መመሪያ ረቂቅ ከሕገመንግስቱ ጋር በግለጽ ይጋጫል። ስለ ገደብ የሚያወሳውን የአገራችንን ሕገመንግስት አንቀጽ 27(5) በሕግ አተረጓጐም መሠረት የልዩ ሁኔታ (Exception) ሲሆን እንደነዚህ ያሉት የልዩ ሁኔታ አንቀጾች መተርጎም ያለባቸው በጠባቡ እና እና በጥብቅ ሁኔታ መሆን አለበት።

Untitled Project 4
🎙 للشيخ بندر بليلة
➤ጣፍጭ የቲላዋ ግብዣ!
▪አሳ በህይወት ለመኖር ውሀ እንደ ሚያስፈልገው ሁሉ ቀልባችን ህያው ይሆን ዘንድ ቁርአን ያስፈልገዋል!!

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Canadian Prime Minister Justin Trudeau
የእስልምናን ፍኖት እጋርዳለሁ ብለህ ከመጋጋጥ ይልቅ አምነህ ተቀብለህ ተገቢውን ድጋፍ ብታደርግ ነው የሚያዋጣው። ላይሳካልህ ነገር የምታተርፈው ነገር ሙስሊሞችን ማጠናከርና ራስህን ማስገመት ብቻ ነው። እስልምናን ለማስቆም መሞከር የጸሐይን ብርሃን በመዳፍህ ሸፍነህ ምድርን ጨለማ ለማድረግ እንደመሞከር ነው። አይደለም መዳፍህን ሙሉ ሰውነትህን ዘርግተህ ብትዘረር የጸሐይን ጮራ መሸፈን እንደማትችለው ሁሉ፤ ሶላትን አይደለም ት/ቤት ውስጥ መኖሪያ ቤታችሁ ውስጥም አትሰግዱም ብለህ ብታዝ ሙስሊሞችን ይባስ ታጠናክራቸዋለህ እንጂ ቅዠትህ ዕውን አይሆንም።
እንኳን አንተ ከአንተ በላይ ሴኪዩላር ነን ብለው ቃሉን ራሱ ያስተማሩህ ሃገራት መሪዎች እንዲህ እጅ ሰጥተው በሰላም ሙስሊሙ ጋር እየኖሩ ነው። የአንተ ግን የመሃይምነት ጥግ በሃገሪቱ ከግማሽ በላይ ከሆነ ህዝብ ጋር በህልውናው መጥተህ ቀይ መስመር ታልፋለህ። ተመከር ወዳጄ‼ የማትጨርሰውን ጉዞ አትጀምር፤ ወደ ኋላም መመለስ፣ ወደፊትም መገስገስ በማትችልበት ወጥመድ ገብተህ መካከል ላይ ሰምጠህ ትቀራለህ።
||

አንድ ሰው ጭንቀትና ትካዜ አጋጥሞት ይህንን ዱዓእ ካደረገ አላህ ያስወግድለታል ብለዋል ነቢያችን ﷺ። እናም ሐፍዙት።
«اللهم إني عبدك، ابن عبدك، ابن أمتك، ناصيتي بيدك، ماضٍ فيَّ حكمك، عدلٌ فيَّ قضاؤك، أسألك بكل اسمٍ هو لك، سميتَ به نفسَك، أو علَّمتَه أحدًا من خلقك، أو أنزلتَه في كتابك، أو استأثرتَ به في علم الغيب عندك؛ أن تجعل القرآنَ ربيع قلبي، ونور صدري، وجلاء حزني، وذهاب همِّي»

ﺍﻟﺤﻤﺪ ﻟﻠﻪ
# አልሀምዱ ሊላህ
# Alhamdu lilahe
ለሀይማኖታዊ መብቱ ሚታገልለት ህዝባዊ መጅሊስ የተነፈገው ትውልድ
በሰላማዊ መንገድ አንድነቱን ጠብቆ የሀይማኖቴን መብት መብቴን አትንኩብኝ
ብሎ የሚጠይቅ ታዳጊ ትውልድ ማየት በጣም ደስ ይላል አልሀምዱ ሊላህ

በ1990ዎቹ የአዲስ አበባ
ትምህርት ቤቶች የሰላት
ችግር ስለነበር የመጅሊሱ መሪ
ችግሩን ሊፈቱ ሄደው
«የመጣችሁት ለትምህርት
ነው፤ ሰላታችሁን ቤታችሁ
ሰብስባችሁ ስገዱ» የሚል
ፈተዋ ሰጥተው ነበር።
ዘንድሮስ?
ትምህርት ቤቶች የሰላት
ችግር ስለነበር የመጅሊሱ መሪ
ችግሩን ሊፈቱ ሄደው
«የመጣችሁት ለትምህርት
ነው፤ ሰላታችሁን ቤታችሁ
ሰብስባችሁ ስገዱ» የሚል
ፈተዋ ሰጥተው ነበር።
ዘንድሮስ?
ምን ቢበዛብህም የችግር መከራ:
ባንተ ላይ ቢዘንብም ባንተም ቢያባራ:
በትግስት ጠብቅ የፀሀዩዋን ጮራ:
ምንም ብትዘገይ አትቀር ተቀርቅራ።
ኢንሻአላህ
ባንተ ላይ ቢዘንብም ባንተም ቢያባራ:
በትግስት ጠብቅ የፀሀዩዋን ጮራ:
ምንም ብትዘገይ አትቀር ተቀርቅራ።
ኢንሻአላህ
ሙእሚን በዱንያ ለነገ አያውቅም:
ሀሳቡ ሌላ ነው በርካሽ አይወድቅም:
«––––––––––––––»
ዛሬ ላይ የሰጠው ነገ የትስ ሄዶ:
ቃሉን አያፈርስም ፅፉል ያኔ ማዶ:
«––––––––––––––––»
ሊስትሮም ወዛደር ቢበላም ነግዶ
ሁሌም አመስጋኝ ነው ለፈጣሪው ሰግዶ።
ሀሳቡ ሌላ ነው በርካሽ አይወድቅም:
«––––––––––––––»
ዛሬ ላይ የሰጠው ነገ የትስ ሄዶ:
ቃሉን አያፈርስም ፅፉል ያኔ ማዶ:
«––––––––––––––––»
ሊስትሮም ወዛደር ቢበላም ነግዶ
ሁሌም አመስጋኝ ነው ለፈጣሪው ሰግዶ።
"የኢኽላስ ኢባዳ"
ስራን ለአላህ ማጥራት፣
ከልብ የእውነት፣
ሪያእ የሌለባት፣
ሱምዓም የማይቀርባት፣
ኡጅብም የማይደፍራት፣
ዱንያ ማታታልላት፣
ለአላህ ያለች ፅድት፣
ሽርክ ሆነ ቢድዓ ከቶ የማይቀርባት፣
ምታስገባ ጀነት የምታርቅ ከእሳት፣
የኢኽላስ ኢባዳ የዝች አይነቷ ናት፣
ደግሞ ትንሽ ላውጋ የኢኽላስ ባልተቤት፣
እሱ ባልተቤት ነው የውዲቷ ጀነት፣
ስራውን ደባቂ አላህን አዋቂ፣
እጅግ ተጠንቃቂ፣
ልቡም የሚጠላ መሆንን ታዋቂ፣
በኢባዳ ላይም ዘውታሪ ዘላቂ፣
ነው እኮ አልቃሻ፣
ወርዶ ከትከሻ፣
አብዝቶ ሚኮንን መባልን በሻሻ፣
ነው የኢማን ዋሻ የተቅዋ መንገሻ፣
ቀን በፆም ይውላል፣
ሌሊቱን ይቆማል፣
ጌታውን አብዝቶ ከልቡ ይፈራል፣
ጀነትን ከጅሏል ፣
እሳትንም ፈርቷል፣
በእሳት ፍራቻም ሌት ቀኑን ያለቅሳል፣
በስራው ማይኮራ፣
አልፎ እንደው ሚፈራ፣
አሳነስኩኝ ብሎ ከሚገባው ስፍራ፣
ደስታው የቀነሰ ሀዘኑም ከራራ፣
ሳቅን ማያበዛ ያልሆነ ሞዛዛ፣
ሁሌም የሚለምን የጌታውን ጀዛ፣
ዱንያንም የናቀ ተቅዋው የረቀቀ፣
ከሸህዋ የራቀ ጀነት የናፈቀ፣
ወንድሙን መካሪ፣
ባለ ውድ ባህሪ፣
ስለርሱ ባወጋ ደርሼ አልጨርሰው፣
በአጭሩ ይህ ነው የዛ ውድ ባህሪው፣
አላህ ውለታውን አብዝቶ የሰጠው፣
ያራህማን አድርገን የሱ አይነት አምሳያው።
ስራን ለአላህ ማጥራት፣
ከልብ የእውነት፣
ሪያእ የሌለባት፣
ሱምዓም የማይቀርባት፣
ኡጅብም የማይደፍራት፣
ዱንያ ማታታልላት፣
ለአላህ ያለች ፅድት፣
ሽርክ ሆነ ቢድዓ ከቶ የማይቀርባት፣
ምታስገባ ጀነት የምታርቅ ከእሳት፣
የኢኽላስ ኢባዳ የዝች አይነቷ ናት፣
ደግሞ ትንሽ ላውጋ የኢኽላስ ባልተቤት፣
እሱ ባልተቤት ነው የውዲቷ ጀነት፣
ስራውን ደባቂ አላህን አዋቂ፣
እጅግ ተጠንቃቂ፣
ልቡም የሚጠላ መሆንን ታዋቂ፣
በኢባዳ ላይም ዘውታሪ ዘላቂ፣
ነው እኮ አልቃሻ፣
ወርዶ ከትከሻ፣
አብዝቶ ሚኮንን መባልን በሻሻ፣
ነው የኢማን ዋሻ የተቅዋ መንገሻ፣
ቀን በፆም ይውላል፣
ሌሊቱን ይቆማል፣
ጌታውን አብዝቶ ከልቡ ይፈራል፣
ጀነትን ከጅሏል ፣
እሳትንም ፈርቷል፣
በእሳት ፍራቻም ሌት ቀኑን ያለቅሳል፣
በስራው ማይኮራ፣
አልፎ እንደው ሚፈራ፣
አሳነስኩኝ ብሎ ከሚገባው ስፍራ፣
ደስታው የቀነሰ ሀዘኑም ከራራ፣
ሳቅን ማያበዛ ያልሆነ ሞዛዛ፣
ሁሌም የሚለምን የጌታውን ጀዛ፣
ዱንያንም የናቀ ተቅዋው የረቀቀ፣
ከሸህዋ የራቀ ጀነት የናፈቀ፣
ወንድሙን መካሪ፣
ባለ ውድ ባህሪ፣
ስለርሱ ባወጋ ደርሼ አልጨርሰው፣
በአጭሩ ይህ ነው የዛ ውድ ባህሪው፣
አላህ ውለታውን አብዝቶ የሰጠው፣
ያራህማን አድርገን የሱ አይነት አምሳያው።