La tehzen
94 subscribers
175 photos
111 videos
32 files
480 links
"አንብብ በዚያ(ሁሉን)በፈጠረው ጌታህ ሥም"
ቁርዓን96:1

"ከመልካም ተግባር ምንንም አሳነሰህ አትመልከት፤ ወንድምህን
በብሩህ ፈገግታ መገናኘትን እንኳን"
ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ)


ሀሳብ አስታየት ካላችሁ👉👉👉 @Oufeyret
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①④

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
Forwarded from Deleted Account
እንደዚህች አይነት ጀግና እህቶችን በዚህ ሁኔታ በማየት አይኔ እምባ ከማውረድ ልቤ ሀዘንን ከመፍረድ አዕምሮዬ በሲቃ ከመራድ አልተወገደም።

እህቶች ሆይ አድራሻዋን ፈልጋችሁ አግዟት

በስደት እያላችሁ ገንዘብ ቆጥቡ ቦታ ግዙ ቤት ስሩ እያልን የምንጨቃጨቀው ሀገር ቤት ስትገቡ ይህ አይነትና መሰል ችግር እንዳያጋጥማችሁ ነው።

መች ይሆን የሚነግሯችሁን የምትሰሙት

ያለ ገደብ ገንዘባችሁን እዚህ ግባ ለማይባል ነገር እያባከናችሁ ነገ መውደቂያችሁ የት ይሆን!?

የአረብ ገረድ የሆናችሁትኮ ለመቀየር ራሳችሁን ለመለወጥ እንጅ ለሌሎች እየረዳችሁ ራሳችሁን እንደዚህ አይነት ቦታ ላይ እንድትጥሉ አይደለም።

#እህቶቼ_እባካችሁ__!!

እንደምትመለከቱት ስደተኞች ወጀ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው ግን መመለሳቸውን እንጅ የት እንደሚወድቁ አልታወቀም ።

ምን እንዳላቸው ብሶታቸው ስሜታየው ምን እንደሆነ ችግራቸውን ማን ጠየቃቸውና ማን ያውቃል።
#ስለዚህ_እህቶች__!
እባካችሁ ገንዘባችሁን ጠብቁ፡
ለራሳችሁ ህይወት እወቁ፡
በአስተሳሰባችሁ ንቁ፡
የወደፊት ተስፋን ሰንቁ፡
➻ተመልከቷት እህታችሁን አታሳዝንም!?
በዚህ የኢስላማዊ የአለባበስ ስታይል እዚህ ቦታ የተገኘችው ተመችቷት ደልቷት መሰላችሁ የሚረዳት ጠፍቶ ተጨንቃ ችግር አስገድዷት ነው።
ገንዘባችሁን እስካልጠበቃችሁ እና እስካልቆጠባችሁ ድረስ ነገ የናንተም እጣ ፈንታ ይሄው ነው።
የምነግራችሁ ወላሒ ስለማስብላችሁ ስለምታሳዝኑኝ ነው እባካችሁ ተመከሩ።
የእህታችሁን አድራሻ ፈልጉና አይዞሽ ቀሏት ስብራቷን ተረዷት አለንልሽ በሏት።
እነዚያ የአሏህ ጠላቶች ሲያልፉ ያገድሙ ሲመለከቷት #እህቴን ምን እያሏት ይሆን !?
#አሏህ_ይድረስልሽ_ጀግናዬ
አሏል ከችግር ያውጣሽ እህቴ
ሙስሊም እህቶቼ መቼም ተቸግራችሁ አልያችሁ።
አሏህ ከችግር ይጠብቃችሁ
አሚን
صفات الزوج الصالح
ሸይኽ ፈውዛን (ሀፊዘሁላህን)
➤ወንዶች ጥሩ ሚስት እንደ ሚያስፈልጋቸው ሁሉ ሴቶችም ጥሩ ባል ያስፈልጋቸዋል.!!

➤በሁለቱም ወገን ትዳር ሲታሠብ ጥሩ ጓደኛ ወይም የህይወት አጋር የሚሆን ሰው ማግኘት ዋናው እና አሳሳቢው ጉዳዪ ነው.!!

➤ታዲያ የጥሩ ባል መገለጫ ባህሪዎች ምንድናቸው.!?

🎙ሸይኽ ሷሊህ አል~ፈዉዛን ሀፊዘሁሏህ



https://t.me/httpsLatahzen
https://t.me/httpsLatahzen
➧አላህ ሱበሃኑሁ ወተአላ እንድህ ይላል

▪️إِلَيْهِ يَصْعَدُ الْكَلِمُ اطَّيِّبُ وَالْعَمَلُ الصَّٰلِحُ يَرْفَعُهُ

➲መልካም ንግግር ወደ እሱ ይወጣል በጎ ስራንም ያነሳዋል። (ፋጢር 10)

ኢብኑ ጀሪር በዚህ አንቀፅ ስር እንድህ ይላል "የባሪያ አላህን ማውሳቱ እና ውዳሴው ወደ አላህ ይወጣል ቀጥለውም የተፍሲር ምሁራንም በዚህ መልኩ እንደተጓዙ ገልፀዋል። (ጀሚኡል በያን 29/444)
Forwarded from አህመድ ፈንታቢል (አህመድ ፈንታቢል)
ከላይ ያለዉ ቪድዬ ሙሉ ትርጉሙን ከቪድዬ ስር ሊያስቀምጥልኝ አልቻለም
ሙሉ ትርጉ ከታች ያለዉ ነዉ
👇👇👇👇👇
ሁለት አድስ ተጋቢዎች በመግባት(በግኑኙነት)ይጀመራል
ባል በሚስቱ ለግኑኙነት ባገባ ጊዜ ይወደዳል ሯሳን ሊያረጋጋት ሊያዝንላት ምክንያቱም ለእሱ አድሱ ናት እና ወደ እሷ በገባ ጊዜ የተለያዩ ፍርሀቶች አሉባት ሊያረጋጋት ትፈልጋለች ፍርሀቷ በሚወገድበት ነገር ሊሰራ ይገባል
ፍርሀቷን በሚጨምር ነገር ላይጀምር ነዉ ይሄ ከአደብ ስርዓት አይደለም
በባል እና ሚስት የሚደረጉ ነገሮችን ሊያሸሻት ይችላል
ምሳሌ ይወደዳል
የሚጠጣ ሊያቀርብላት ይገባል
ወተት ወይም አሲር ወይም ሌላ ነገር
ከዚያ ትንሽም ቢሆን ሊጠጣ ይገባል
አስማዑ አሽሀሊያ የምትባለዉ ሶሀባ አለች
እኔ አኢሻን ለረሡል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም አስዋቡኳት ከዚያ ረሱል ከጎኑዋ ተቀመጡ
ከዚያ ወተት ጠጡ እና ለአኢሻ ሰጧት ከዚያ አንገቷን ዝቅ አደረገች አፈረች ከዚያ አስማዕ ለአኢሻ አለቻት ከረሱል ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እጅ ያለዉን ማለትም ወተቱን ዉሰጅ አልኳት ከዚያ ያዘች ጠጣች ኢማሙ አህመድ አዉርተዉታል ሸህ አልባኒ በሁለት መንገድ ከፊሉ ከፊሉን ያጠናክረዋል ሻሂድ አለዉ
ባል ከሚስቱ እጁን ከራሷ ማስቀመጥ ይወደዳል በረካ እንድትሆንለት ዱዓ ማድረግ ነብያችን ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም እንድህ ብለዋል
አንዳቹሁ ሚስት ባገባ ጊዜ ወይም ሰራተኛ በገዛ ጊዜ እንድህ ይበል
ጌታየ ሆይ እኔ ኸይሯን እጠይቅሀለሁ ከሸሯ በአንተ እጠበቃለሁ አቡዳዉድ ዘግበዉታል አልባኒ ሀሰን ብለዉታል
نْ عَمْرِو بْنِ شُعَيْبٍ عَنْ أَبِيهِ عَنْ جَدِّهِ أَنَّ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ: "إِذَا تَزَوَّجَ أَحَدُكُمْ امْرَأَةً، أَوْ اشْتَرَى خَادِمًا، فَلْيَقُلْ: اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ خَيْرَهَا وَخَيْرَ مَا جَبَلْتَهَا عَلَيْهِ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّهَا وَشَرِّ مَا جَبَلْتَهَا عَلَيْهِ. 

وَإِن اشْتَرَى بَعِيرًا، فَلْيَأْخُذْ بِذِرْوَةِ سَنَامِهِ، وَلْيَقُلْ مِثْلَ ذَلِكَ".
በኢብኑ ማጃህ ዘገባ ጥምጣም(እሯሳ)ላይ አጅን ያድርግ እና
በኢብኑ ማጃህ ዘገባ በዱዓዉ መጨረሻ ላይ የተባረከች እንድትሆን ዱዓ ያድርግ
ለባል እና ለሚስት ይወደዳል ህይወታቸዉን በሶላት መጀመር ሚስት ለዚህ ነገር አመች ከሆነች ምሳሌ በዉዱዕ ከሆነች። ዉዱዕ የሌላት ከሆነች አይፈልግም የተዋበችን ዉበት ለዚህ ሶላት ብላ መታጠብ ዉዱዕ ማድረግ የለባትም
ከሶሀቦች አሏህ መልካም ስራቸዉን ይዉደድላቸዉ እና ተገኝቷል ይሄ የሚሰገድ ሶላት ኡለሞች እንዳወሱት ለኑሮ መመቸት ምክንያት ነዉ ቤት ዉስጥ በረከት ማገኛ ነዉ በባል እና ሚስቱ መካከል መዋደድ ምክንያት ይሆናል ከሶሀባ ሰዎች አለ ኢብኑ መስኡድ አቡ ዘር ለሁዘይፋ ለሆነ ወጣት ባገባ ገዜ ቤተሰቦችህ ከገቡ ቡኋላ ሁለት ረክዓ ስገድ ከዚያም እሷ ዘንድ ያለዉን ኸይር አሏህን ጠይቅ ከሸሯ ደግሞ በአሏህ ተጠበቅ
ተመልከቱ ይሄን አደብ ስርዓት
ባል ከሚስቱ ጋር ቶሎ ብሎ ግኑኙነት(ጅማዕ)መጀመር የለበትም ይዘንላት እጁን ከሯሳ ያስቀምጥ እና ዱዓ ያድርግላት ለራሱም ዱዓ ያድር
ከሚስቱጋ ሁለት ረክዓ ይስገድ ይሄ ሁሉ ለኸይር እና ለበረካ መቅደሚያ ነዉ ኢብኑ መስኡድ አሏህ መልካም ስራዉን ይዉደድለት እና ወደ ሚስትህ በመጣህ ጊዜ ከአንተ ቡኋላ ሁለት ረክዓ እንድትሰግድ እዘዛት አቡ ሸይባ እና አብዱ ረዛቅ አዉርተዉታል ሼህ አልባኒ ሶሂህ ብሎታል
👇👇👇
https://t.me/HuzeyfaAhmed
፨፨፨፨ ሳገባሽ ላፍቅርሽ ፨፨፨፨፨

የምን መጣደፍ ነው ቅጥ ያጣ ችኮላ
ከጋብቻ በፊት ቃል ኪዳን መሀላ
የዘመኑ ሰዎች ሰይጥነው ተራቀው
የፍቅር ጓደኛ ቅምጥ ቢጤ ይዘው
ሊጀምሩ ፍቅር ሊቀምሱ ስሜቱን
ምግቤ ተቀይሯል ልያቸው አይንሽን
ውበትሽ ማርኮኛል ፍቅረኛሽም ልሁን
ቢላት ባንደበቱ ቃላት በመደርደር
እሷም እንደ ወጉ ትንሽ በመግደርደር
ዘላ ገባችበት የጥፋቱን መንደር
Hello! ውዴ ፍቅሬ የት ነው ያለህው?
በጣም ናፍቀኸኛል አይኖችህን ልየው
ማለት ጀምራለች እሷም በተራዋ
የሀራሙ ወጥመድ ገብቶ በገላዋ
ቀን መሽቶ ሲነጋ ጊዜያት አለፉ
ሸህዋ ገረፋቸው አልጋ ላይ አረፉ
ዚናም ተፈፀመ ሀራም ተሸመተ
አላህን አስቆጡ ሸይጧን ተደሰተ
ተነነ ደረቀ ወረተኛው ፍቅር
ሲጀመር ያስጠላ ሲፈፀም አያምር
ሚስጥሩ የገባው የዘላቂ ፍቅር
መተሳሰብ ያለው የሞላው ቁምነገር
ያ የሱና ወጣት በዲኑ ቆፍጣናው
ምርጫሽ ከሆነ አላህን የፈራው
ግልፁን ይነግርሻል ምንም ሳይደብቅሽ
በአላህ መንገድ ላይ ስጓዝ ያገኘሁሽ
መሆን ያለበትን እቅጩን ልንገርሽ
ጥርጥር የሌለው ሙስሊም እህቴ ነሽ
ጊዜው አልደረሰም ሳገባሽ ላፍቅርሽ
♡አንተ ለሰዎች ያለህ አቀራረብ
እነሱ ላንተ የሚኖራቸውን አቀራራብ
ይወስነዋል ።
•••┈┈┈•✿🌾🌹🌾✿•┈┈┈•••


♡ጊዜህን ማብራሪያዎችን በማቅረብ
አታባክን፣ ሰዎች የሚሰሙት መስማት
የሚፈልጉትን ብቻ ነው ፡፡
•••┈┈┈•✿🌾🌹🌾✿•┈┈┈••


♡የህይወትህ ጊዜ ትንሽ
መሆኗን እወቅ
⇨ትላንት የዛሬ ትውስታ እንደሆነ
እና ነገ የዛሬ ህልም እንደሆነ
ተገንዝበህ ስራበት ፡፡
•••┈┈┈•✿🌾🌹🌾✿•┈┈┈•••


#አሏህ መወደድ የሚገባዉን ሰው እንድትወደው አድርጎ በህይወትህ ዉስጥ ካኖረልህ ብእርግጥም ትልቅን ውለታ ውሎልሃል

#ሁሉም ጥሩ ሚስት ይመኛል...ሴቷም ብትሆን ጥሩን ወንድ ትመርጣለች...ነገር ግን #ጥሩን ለማግኘት #ጥሩ መሆን እንዳለብን ዘንግተናል፡፡

"ጥሩዎቹን ለጥሩዎቹ" (አል-ቁርዓን)
ሰቆቃና ስቃይ በበዛባት አለም
ትግስት እንደ ፍርሀት በታየበት አለም
በዱላ ተዋቅተን ካልተያየንማ አልተከባበርንም።
//
መንግስትማ ይሄ ሁሉ ግፍ መቼ ጠፍቶት ዝም አለ።ይሄን የጀረጀሰ ሽማግሌስ ለምን ሰለጠብንና!?
//
መስጅዴን አቃጥሎ በእኔው እየሳቀ
መስጅድ እየዘጋ ወንድሜን በዱላ እያሸማቀቀ
ሰው "ሀብ ሀብ"ይመሰል በሰንጢ ተወግቶ
አዞ አይደል ከርከሮ በካራ ተመቶ
ይሄን ግፍ እያየሁ መተጋስ አልችልም።
በቆሻሾች በደል ጆሮዬ ተመልቶ።
//
መኖርን አልሻም ድሎትም ይቅርብኝ፤
አንተ ጀግና ወጣት በደልን ያዘልከው
ከአካባቢህ ወጣት ተደራጅተህ ጥራኝ
ከየትም በዬ በዬት ቀዬህ እመጣለሁ
የደረስኩም ለታ ጌታህ እንዲያሳይህ የአሕባሽን ገሰስ ኮተታም ጥርቅም
ምሌ እነግርሀለሁ በአላህ ታግዤ እስከሚወጣለት ሳልገርፍ አልተወውም።
//
መኖሬ ለዲኔ ካልሆነ ሞቴን እመርጣለሁ።

አቡ_ዑበይዳ ነኝ
https://t.me/AbuOubeida
Forwarded from Deleted Account
የጁሙዓ ግብዣዬ
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
الشيخ : ماهر المعيقلي
Al-Kahf | الكهف
قناة تلاوات الشيخ ماهر المعيقلي

🍀

ሱረቱል ካህፍ የቻለ ይቅራ 📖
ያልቻ ያዳምጥ 🎧
የጁምዓ ሱናዎች🌷🌷🌷🌷🌹🌹🌷🌷🌷🌷
* ሻውር መወሰድ አረፍ ምንለውን ልብስ መልበስ🥼👚👕👖👗👘

*ሽቶ መቀባት ለወንዶች
* ጥፍርን መቁረጥ
🌹🌹🌹🌹🌷🌷🌷🌷🌷
* የብብት ና የብልት ፀጉሮችን መቁረጥ
* በጊዜ መስጊድ መግባት🕋🕋🕌🕌🕌🕌🕌🕋🕋🕋🕋🕋🕋

* በነቢያች ሰ/ ወ ሰለዋት ማውረድ
* ሱረቱል ካህፍን ማንበበ

* ሰደቃን መስጠት🥓🥖🥐🥯🥞🥮 መፋቅያ መጠቀም
በአጠቃላይ በሀይር ስራ መሳተፍ ።🌟🌟🌟⭐️🌈🌈🌈🌈
ዛሬ April 1 ነው። ይህን ቀን ጠብቀው የሚጃጃሉ ሰዎች ስላሉ ጅል ጓደኞች ያሏችሁ እንዳያስደነግጧችሁ ወይም እንዳይጎዷችሁ ተጠንቀቁ።
=
https://t.me/IbnuMunewor
Audio
ሱረቱል ካህፍ
=========

የቻለ ይቅራ 📚📖

ያልቻለ ያዳምጥ ~🎧

ፏ ያለ. __ ጁማዓ!!!
🚿 يوم الجمعة
🚿የውመል ጁምዓ
_ اولاً : فضله:
عن ابي هريرة رضي الله عنه قال:قال رسول الله صلى الله عليه وسلم :(( خيرُ يوم طلعت عليه الشمسُ يوم الجمعة: فيه خلق آدم، وفيه أدخل الجنة، وفيه أخرج منها، ولا تقومُ الساعة إلاً يوم الجمعة)) [مسلم].
🍀 የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم እንዲህ ብለዋል.
🌅 " ፀሀይ ከወጣችበት ቀናቶች በላጯ ቀን የጁምአ ቀን ነው፡ በሷ (በጁምአ) አደም ተፈጥሯል ፡ ጀነት እንዲገባ ተደርገዋል ፡በሷም ቀን ከጀነት እንዲወጣም ተደርጓል ፡ ቂያማም አትቆምም በሷ ቀን ቢሆን እንጂ".
📚 [ ሙስሊም ዘግቦታል ].
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስለ ረመዿን ተከታታይ አጫጭር የሙሐደራ ግብዣ ከአማርኛ የህዳግ ትርጉም ጋር: ክፍል ①⑤

በሸይኽ ዶ/ር ዑሥማን አል-ኸሚስ
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من هجر أخاه سنةً، فهو كسفْكِ دَمِه﴾

«ወንድሙን አንድ አመት ያኮረፈ ደሙን እንዳፈሰሰው ነው።»

[ሶሒሑ-ል-ጃሚዕ: 6581]
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እውነት ለመናገር የድሮዎቹ ሱፍዮች ነብዩን (ﷺ) ለማየት ጉጉት እንዳላቸው ይገልፁ ነበር። ይህንን የሚጠቁሙ ስንኞች በመንዙማዎቻቸው ውስጥ በብዛት ይገኛሉ። ለምሳሌ ያክል፦

"የመዲናውን
ባየነው አይኑን።"
~
"እንዴት ነሁ
ምነው ባየነሁ"
~
"ሙፍቲው" ግን ነብያችንን ለማየት እንኳ ይህን ያክል ሱቅሱቃ የለኝም ይላል። ጉድ ነው። መጅሊስ አካባቢ የሚታየው ሱቅሱቃ ግን ለብዙዎች የሚተርፍ መዘዝ እንዳያስከትል ያሰጋል።
=
https://t.me/IbnuMunewor
ኤፕሪል ዘፉል
Sadat
April 1 የውሸታሞች ቀን

"በኡስታዝ ሳዳት ከማል ሀፊዘሁሏህ"
ፈገግ የሚያሰኘኝ ሐዲሥ‼️
====================
✍️ የሐዲሡ አስተላላፊ ግንባር ቀደም የሐዲሥ ዘጋቢ የሆነው የነቢያችን ﷺ ባልደረባ አቡ ሁረይራህ ነው። አላህ ሥራውን ይውደድለትና እንዲህ ይላል፦
" بيْنَما نَحْنُ جُلُوسٌ عِنْدَ النبيِّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ، إذْ جَاءَهُ رَجُلٌ فَقَالَ: يا رَسولَ اللَّهِ هَلَكْتُ."
«ነቢያችን ﷺ ዘንድ ተቀምጠን ሳለን ድንገት አንድ ሰው መጣና "የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ጠፋሁ! (የሚያጠፋ ወንጀል ላይ ወደቅኩ!)" አላቸው።»
እርሳቸውም፦
قَالَ: ما لَكَ؟
«ምን ሆንክ? (ምን አገኘህ?)» አሉት።

እርሱም፦
قَالَ: وقَعْتُ علَى امْرَأَتي وأَنَا صَائِمٌ،
«ጾመኛ ሆኘ ሳለሁ ባለቤቴ ላይ ወደቅኩ! (ባለቤቴ ጋር ግንኙነት አደረግን!)» አላቸው።

እርሳቸውም የአላህ መልዕክተኛ ﷺ፦

فَقَالَ رَسولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ: هلْ تَجِدُ رَقَبَةً تُعْتِقُهَا؟
«ነጻ የምታወጣው ባሪያ ታገኛለህን?» አሉት።

እርሱም፦
قَالَ: لَا،
"ኧረ! በጭራሽ! (አላገኝም!)" አለ።

እርሳቸውም፦
قَالَ: فَهلْ تَسْتَطِيعُ أنْ تَصُومَ شَهْرَيْنِ مُتَتَابِعَيْنِ،
«ሁለት ወራትን በተከታታይ መጾም ትችላለህን?»አሉት።
(አንድ ወር አላስችለው ብሎ ጭራሽ ሁለት ወርi)

እርሱም፦
قَالَ: لَا،
"ኧረ! በጭራሽ! (አልችልም!)" አለ።

እርሳቸውም፦
فَقَالَ: فَهلْ تَجِدُ إطْعَامَ سِتِّينَ مِسْكِينًا.

«ስድሳ (60) ሚስኪኖችን የምትመግበው ታገኛለህን?» አሉት።

እርሱም፦
قَالَ: لَا،
"ኧረ! በጭራሽ! (አላገኝም!)" አለ።

فَمَكَثَ النبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ، فَبيْنَا نَحْنُ علَى ذلكَ أُتِيَ النبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ بعَرَقٍ فِيهَا تَمْرٌ
ነቢዩ ﷺ በዚህ ሁኔታ ላይ ትንሽ እንደቆዩ ተምር ያለበት ዘንቢል ይዞላቸው ተመጣ።

እንዲህ አሉ፦

قَالَ: أيْنَ السَّائِلُ؟
«(የቅድሙ) ጠያቂ የት አለ?» አሉ።

እርሱም፦
فَقَالَ: أنَا،
"እኔ ነኝ!" አለ።

እርሳቸውም፦

قَالَ: خُذْهَا، فَتَصَدَّقْ به!
ያንን የተመጣላቸውን በተምር የተሞላ ዘንቢል "(እንካ!) ይህቺን ያዝና ሶደቃ ስጥ!" አሉት።

(ፈገግ የሚያሰኘኝ ነገር እዚህ ጋር ነው።)
እርሱም፦

فَقَالَ الرَّجُلُ: أعَلَى أفْقَرَ مِنِّي يا رَسولَ اللَّهِ؟ فَوَاللَّهِ ما بيْنَ لَابَتَيْهَا - يُرِيدُ الحَرَّتَيْنِ - أهْلُ بَيْتٍ أفْقَرُ مِن أهْلِ بَيْتِي،
«አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ከኔ የበለጠ እጅግ በጣም ድሃ ማን አለና ነው (ለሌላ የምሰድቀው)? በአላህ ይሁንብኝ! (በመዲና) ተራሮች መካከል ከኔ የበለጠ እጅግ በጣም ድሃ የለም!» አላቸው።

فَضَحِكَ النبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ حتَّى بَدَتْ أنْيَابُهُ، ثُمَّ قَالَ: أطْعِمْهُ أهْلَكَ.
ውዱና አዛኙ ነቢይም ረሱሉ-ል-ሁዳ ቀንጣጤዎቻቸው እስኪታዩ ድረስ ሳቁና "እሺ! ቤተሰብህን መግበው!" አሉት።

ተመልከቱ እስኪ አቦ እኚህን የእዝነት ነብይ‼️
ይህን የእዝነትና ልስላሴ እምነት‼️
ወንጀል ሠርቶ ተጨናንቆ ቢሄድ ጭራሽ እንደ መልካም ሠሪ ስጦታ ተሰጥቶት ተመለሰ።
አጂብ'ኮ ነው ዲናችን! ምንኛ ያማረ አዛኝ የሆነ አምላክ ባሮች ነን! ምንኛ የእዝነትና ርኅራሄ እምነት ተከታዮች ነን! ለአማኞች ርኅሩኅ የሆነ ነቢይ ተከታዮች ነን!

ከዚህ ሐዲሥ ከምንማራቸው ቁም ነገሮች፦
1) በረመዿን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ይህ አይነት ወንጀል ላይ የወደቀ ሰው፤
ከላይ ሐዲሡ ላይ በተቀመጠው ቅደም ተከተል መሠረት፤ መጀመሪያ ነጻ የሚያወጣው ባሪያ ካለ ያወጣል፣ ያንን ካላገኘ ሁለት ወራትን በተከታታይ ይጾማል፣ ይህን ካልቻለ ስድሳ ሚስኪኖችን እስኪጠግቡ ይመግባል።
.
2) ከፋራ ለማውጣት የተቸገረን ሰው መርዳት እንደሚገባ፣
.
3) በመገረም ወቅት በዚህ ልክ መሳቅ እንደሚቻል፣
.
4) የወዱ ነቢይ ﷺ የማስተማር ጥበብ፣ እዝነትና ርኅራሄ፣
.
5) የሚማረውም ግለሰብ አደብና የዲናችን ገርነት፣
.
6) በወንጀል መጸጸትና እንዲህ አይነት ማካካሻ የሚያስፈልገውን ወንጀል ከመደበቅ ይልቅ መፍትሄውን አዋቂዎችን መጠየቅ እንደሚገባ እንማራለን።

ወንጀል ሠርተህ ውስጥህን ከከፋህና ደስተኛ ካልሆንክ፣ ይህ የኢማን መኖርህ ምልክት ነው።
You know the guilt after committing a sin?
Don't ever lose that, its a sign of Imaan. ባይሆን ቶሎ ወደ ጌታህ ተመለስ። ሸይጧን አላህ አይምርህም እያለ ተስፋ አስቆርጦ እስከ መጨረሻው አላማውን እንዳይፈጽምብህ ተጠንቀቅ።

አላህ ረመዿን በሰላም ደርሰው ከሚጠቀሙበት ባሮቹ ያድርገን።
||
ወንድማችሁ፦ ሙራድ ታደሰ
======
ዕለተ ጁሙዓህ ሸዕባን 29, 1443 H.C
April 01, 2022 G.C
||
t.me/MuradTadesse
ከአርሹ በላይ የሚለው መፅሃፍ የመጀመሪያው ዙር መጥቷል እጄ ገብቷል

ማገኘት የምትችሉት
ቦታ ደሴ አራዳ ሰላም ህንፃ ግራውንድ 33 ቁጥር መምጣት ትችላላችሁ!
0933519871
0921119899
ወንድማችሁ ጀማል እንድሮ
@JemalEndro
ከጁመዓ በሇላ ነው እጄ የገባው ያዘገየሁባችሁ አፍወን
0933519871

https://t.me/daewaselefiyaArbaminch/11426
አንዲት እናት ወደ አንድ ሸይኽ ፈትዋ ለመጠየቅ ትመጣና ለሸይኹ
" ሸይኽ ሆይ የልጆቼ እንቅልፍ በጣም ከባድ ነው ፣ ለፈጅር ሰላት እነሱን መቀስቀስ ደከመኝና ምንድነው መፍትሄው? " በማለት ጠየቀች ።
๏ ሸይኹም " ሙቀት መቆጣጠሪያው ተቃጥሎ እሳት ቢተፋ ኖሮ ምን ታደርጊ ነበር? " አላት
๏ እናት " እቀሰቅሳቹኋለሁ " አለች
๏ ሸይኹ " ግንኮ እንቅልፋቸው ከባድ ነው " አላት
๏ እናት " በአላህ ይሁንብኝ አንገታቸውን እየጎተትኩ ቢሆንም እቀሰቅሳቸዋለሁ " አለች
๏ ሸይኹ " ይህን የምታደርጊው ከዱንያ እሳት ልታድኚያቸው ነው ፣ ልክ እንደዛውም ከአኺራ እሳት ለማዳን ቀስቅሺያቸው " አላት ።

(يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ)
" እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነች እሳት ጠብቁ ፡፡ በእርሷ ላይ ጨካኞች ፣ ኀይለኞች የሆኑ መላእክት አልሉ ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምጹም ፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሠራሉ ፡፡" [ተህሪም 6]

------------------