የአኺራ ስንቅ زاد الآخرة
34 subscribers
2 videos
1 file
12 links
ከቁርኣን እና ከሐዲሥ፣ እንዲሁም ከታማኝ ዑለማዎች ከትክክለኛ ቂያስ የተጠናከሩ
#አጫጭር የድምፅ ፋይሎች
#የተለያዩ አፕልኬሽኖች#
የተለያዩ ኢስላማዊ ግጥሞች #
ተከታታይና ወቅታዊ ፅሁፎች
ሁሉንም፤በተለይም ተማሪዎችን የሚመለከቱ ይለቀቅበታል።
ይቀላቀሉን
አስተያየት ሲኖራችሁ
⤵️⤵️⤵️⤵️⤵️
@NurAhend
 አሳውቁኝ
★ ጀዛኩሙልሏህ ኸይራ።
Download Telegram
💎አዎ ላንቺ ለውዷ እህቴ💎
🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙🌙

እህቴ ላንቺ ነው ባክሽ ተመከሪ፣
ልብሽም አይዋልል ልክ እንደ በራሪ፣
መሆን አይበጅሽም የሀራም አክራሪ፣
ይህ አያዋጣሽም በሀቁ ተመሪ፣

የምእራቡን አለም ሱና ተከትለሽ፣
አንቺም እንደነሱ በጣም ከልክ አልፈሽ፣
ጠባብና አጭር ስሱን ልብስም ለብሰሽ፣
ትወጫለሽ ከቤት ሀያኡ ሳይኖርሽ፣
መውጣትሽም ሳያንስ አጅነቢን አይተሽ፣
ማየትሽ ሳይበቃ እጁን ጨብጠሽ፣

አባክሽ ተመለሽ አውቀሽ ታርመሽ፣
ተበሩጅ መጥፎነው አባክሽ ልበሽ፣
ከጀሀነም እሳት እንዲጠብቅሽ፣

ከቤትም አትውጪ ሀጃ ሳይኖርሽ፣
ከወጣሽም ልበሽ ከአናት እስከ እግርሽ፣
ሜካፕና ሽቶ ሌላም ሳይነካሽ፣
ተውሂድና ሱናን አውቀሽ ተመርተሽ፣
የማንም ወጠጤ አንቺን ሳይነካሽ፣
ተከብረሽም ኑሪ እስከ እለተ ሞትሽ።


@Nurahend



https://t.me/httpsIBNumuhammed
#ጉዞ ወደ አብሬት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

 ﴿لا تُشَدُّ الرِّحالُ إلّا لِثَلاثَةِ مَساجِدَ: مَسجِدِ الحَرامِ، ومَسجِدي هذا، والمَسجِدِ الأَقصى.﴾

“ወደ ሶስት መስጂድ ካልሆነ በቀር ለአምልኮት እንዳትጓዙ። እነሱም፦ መስጂዱል ሐራም፣ መስጂዱል አቅሷ ይሄ መስጂዴ መዲና የሚገኘው የሳቸው መስጂድ ናቸው።”

📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 1189
💜 የአላህ ፍቅር ውስጥህ ሲኖር
ብርሃኑ ልብህን ያበራና ጀሰድህን
#ለፈጅር ሰላት ይቀሰቅስሃል ።

ፍቅሩን ይስጠን🤲🏻
━━━━━━✦✿✦━━━━━━
ነብዩ ﷺ በመሰደባቸው የተቆጣው ውሻ
━━━━━━✦✿✦━━━━━━

: ከሞጎላዊያን አንድ ባለስልጣን የክርስትናን ሃይማኖት ከተቀበለ ጥቂት ጊዜያት በኋላ ሀይማኖቱን መቀበሉን አስመልክቶ በተዘጋጀ ድግስ ከተወሰኑ ቄሳውስቶች ጋር ሰብሰብ ብለው ተቀምጠዋል። ከአቅራቢያቸው አንድ ለአደን የተዘጋጀ ውሻ ታስሯል።
: በወቅቱ ከነበሩ ቄሶች አንዱ ለዓለማት እዝነት የተላኩትን ታላቁን ነቢ ሙሀመድ ﷺ በመጥፎ ማንሳትና መተቸት ብሎም መሳደብ ጀምሯል። ታዲያ ይህንን ሲሰማና ሲታዘብ የነበረው ውሻ እጅግ ተቆጣ ፤ ወዲያውኑ በከፍተኛ ድምፅ እየጮኸ ተሳዳቢውን ቄስ ዘሎ ነከሰውና አቆሰለው ፤ በአቅራቢያው የነበሩ ሰዎችም ተረባርበው አዳኑት ። ሰዎቹም፦ "ውሻው የምትናገረው ነገር አልተስማማውምና ሰለ ሙሀመድ (ﷺ) መጥፎ ከመናገር ተቆጠብ" ይሉታል ፤ ሰውየው ግን ፦ "አይ ችግሩ ከምናገረው አይመስለኝም ባይሆን በምናገርበት ወቅት እጄን ስዘረጋና ሳንቀሳቅስ ስለነበር እሱ ላይ የጠቆምኩበት መስሎት ነው" በማለት ስድብና ትችቱን ቀጠለ። ውሻው ግን ከመጀመሪያው በከፋ መልኩ በከፍተኛ ቁጣና ንዴት ዘሎ ጉሮሮውን በመንከስ ሰውየውን ገደለው።

👉 ይህ ክስተት በጊዜው የነበሩ ሰዎችን በከፍተኛ መልኩ አስገርሞ ነበር ፤ በዚህም ውሻ ምክንያት በወቅቱ ወደ 40 ሺህ የሚደርሱ ሰዎች እስልምናን ተቀበሉ።

👉 ክስተቱን ታላቁ አሊም ኢብኑ ሀጀር "አዱረሩል ካሚናህ" በተባለው መፅሃፋቸው አስፍረውታል።

የአላህን ሰራዊቶች እርሱ እንጂ ማንም አያውቃቸውም


ﺍﻟﻠﻬﻢّ ﺻﻞِّ ﻋﻠﻰ ﻣﺤﻤّﺪ ﻋَﺒْﺪِﻙَ ﻭﻧَﺒِﻴِّﻚَ ﻭﺭﺳﻮﻟِﻚَ ﺍﻟﻨﺒﻲِّ
ﺍﻷمي"
ትኩረት የነፈግነው ሐቅ
~~
"ከናንተ በላጫችሁ ቁርኣንን ተምሮ ያስተማረ ነው" ብለዋል ነብያችን (ﷺ)። [ቡኻሪ]
ይሁን እንጂ ብዙ ቁርኣን ያልቀራ ወገን እያለን ለጉዳዩ የሰጠነው ትኩረት ግን ለችግሩ የሚመጥን አይደለም። ስለሆነም ችግሩን በመቅረፍ ላይ ከራሳችን ልንጀምር ይገባል። እና
* ቁርኣን ካልቀራን ለምን አንቀራም?
* ያልቀራ ቤተሰብ ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣ ወዘተ. ካለ ለምን አናቀራም?
* ይህም ካልሆነልን የሚያቀሩትን በምንችለው አቅም ለምን አናግዝም?
ዛሬ ዛሬ ቁርኣን ማስተማር የሰነፎች ወይም እውቀታቸው የደከሙ ሰዎች ስራ እየመሰለ ነው።
ቁርኣን ያልቀራህ ወገኔ ሆይ! የትኩረት ማነስ እንጂ እውነት ቁርኣን ማንበብ መቻል ይህን ያክል ከባድ ነገር ሆኖ ነው ወይ? እስከ መቼ ነው 28 የዐረብኛ ፊደላትን አገጣጥሞ ማንበብ ተራራ የሚሆንብህ? ወላሂ! ተገቢ ትኩረት ብንሰጠው ቁርኣን ፈፅሞ ዛሬ በሃገራችን የሚወስደውን የጊዜ መጠን የሚጠይቅ አልነበረም። ከልብ ካለቀሱ እምባ አይገድም ይባላል።
እና ወንድሜ ሆይ! በነፃ የሚያስተምርህ ካገኘህ እሰየው። ካልሆነ ግን በክፍያ የሚያስተምሩ ወንድም/እህቶች ካሉም ደስ እያለህ ከፍለህ ተማር። ለሚያሳንፉ ሰዎች ጆሮ አትስጥ። ቁርኣን መማር ዲግሪና ዲፕሎማ ከመማር በታች ነውንዴ? ቁርኣን መማር ቋንቋ፣ ኮምፒተር፣ ... ከመማር በታች ነውንዴ? እነዚህን ነገሮች ለመማር ስንትና ስንት እያወጣን ቁርኣን ለመማር የሚወጣው ላይ ለቅሶ ማብዛት ምንድነው?
ይልቅ በጊዜ ቁርጠኛ ውሳኔ ወስን። ከዜሮም ብትነሳ እሩቅ አይደለም ትደርሳለህ። ማረም ማስተካከል ከሆነም በአጭር ጊዜ ትጋት ሁነኛ ለውጥ ታያለህ። አላህ ያግዘን።
~
https://t.me/IbnuMunewor
ሐሜተኞችን እንጠንቀቃቸው

ሐሰኑል በስሪይ ረሒመሁሏህ እንድህ አሉ
"ወደ አንተ ወሬን ያመጣልህ ሰው ወደ ሌላ ሰውም ወሬህን እንደሚወስድ እወቅ "
[ተንቢሑል ጋፊሊን 130]
____ __
ሐሜት ታላቅ ወንጀል ነው ልንርቀውና ልንጠነቀቀው ይገባል።ጠላታችንን በምላሳችን የጎዳን ቢመስለንም የምንጎዳው ዙረን ራሳችንን ነው።ስንት ደክመን የሰገድንውን ሶላት፣የፆምንውን ፆም ወይም የሰጠንውን ሶደቃ ለጠላንው ሰው ከሀሰናችን በትንሽ ደቂቃ ወይንም በሰከንድ አሟጠን ማስረከብ ነው ትርፋችን።ይህ በአኼራ የምርመራው ጊዜ ሲሆን ነው።
ዱንያ ላይ ደግሞ አብሮ ሲያማ የነበረው ሰው ወዳጅ በመምሰል ከታሚው(ከሚታማው) ሰው ጋር እገሌ እንድህ እንድህ ብሎ አምቶሃል ብሎ ይነግረውና የመቀያየም ብሎም የነፍስ የመጠፋፋት አደጋን ሊያደርስ ይችላል።
አላህ ከሐሜት ይጠብቀን
◾️ወላጆቻችንን በዱአ አንርሳቸው


◾️‏قـال الشيخ ابن عثيمين - رحمه الله-:
💦ኢብኑ ኡሰይሚን አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ይላሉ።

【"دعـاؤك لوالدك في صلاة التراويح أو في صلاة التهجد أفضل بكثير من أن تذبح له عشـر نيـاق".】
(ለሞተው አባትህ) በተራዊህ ወይም በተሀጁድ ላይ ሆነህ ዱአ ማድረግህ አስር ግመል ከምታርድለት በብዙ እጥፍ የተሻለ ነው።
📔[ لقـاء البـاب المفتوح (١١٥) ]

🔻ለሞቱትም ሆነ በህይወት ላሉት ወላጆቻችን ስጁድ ላይ ሆነን፣ ከማሰላመታችን በፊት፣ የጅሙአ ቀን፣ ማፍጠሪያ አካባቢ፣ በአሽረል አዋኺር፣ በሌሊት ተነስተንና ሌሎችም ዱአ ተቀባይነት ባላቸው ወቅቶች በዱአ ልናስታውሳቸው ይገባል።

↪️ወደ አሔራ ለሄዱት

➲አላህ እንዲምራቸው
➲ወንጀላቸውን ይቅር እንዲላቸው
➲ቀብራቸው የጀነት ጨፌ እንዲያደርግላቸው
➲ቀብራቸው በብርሀንና በኑር እንዲሞላው
➲ከቀብር ቅጣት እንዲጠብቃቸው
🔘አላህን አጥብቀን ልንለምንላቸው ይገባል።

↪️በህይወት ያሉ እንደሆነ

➲አላህ ቅናቻውን መንገድ እንዲመራቸው
➲ከሽርክ ከቢድአና ከጥመቱ ሁሉ እንዲጠብቃቸው
➲ኻቲማቸው እንዲስተካከል
➲ከዱንያ ጭንቅና ጥበት አላህ እንዲጠብቃቸው
➲አላህ መልካሙን ሁሉ እንዲወፍቃቸው
➲እድሜያቸው ከመልካም ስራ ጋር እንዲያረዝመውና
🔘ሌሎችም መልካም ዱአዎች ልናደርግላቸው ይገባል።

።///።።።//።።።።//።።።።።።///።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የፍቅረኞች ቀን (የዝሙተኞች ቀን) ማክበር እንዴት ይታያል??
👇👇👇
https://t.me/httpsIBNumuhammed
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📽:ያ አላህ!!!! ወላሂ ነው የምላችሁ ይህን የቁርዐን ድምፅ ስሰማ እምባ እምባ ፣ የውስጥ እርካታ(በቃላት የማይገለፅ) ፣ የየውመል ቂያማ ምንነት በደንብ ይገባኛል።
🚩:እስኪ ዘፈን የምናዳምጥ ሰዎች ይህን የመሰለ የቁርዐን ቲላዋ እያለልን የማንረዳ ከሆነ በጣም ከባድ ነው አህባቦቼ!!! እስኪ መቅራት የማንችል ከሆን እንኳን ጊዜ ሰጠን እንስማው በአላህ. . . . . !!!
🔰🔰የዕለቱ ሀዲስ🔰🔰

"▪️ከአቡሁረይራ በተዘገበ ሀዲስ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፤

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ ﷺ : ”...احْرِصْ عَلَى مَا يَنْفَعُكَ وَاسْتَعِنْ بِاللهِ وَلَا تَعْجَزْ، وَإِنْ أَصَابَكَ شَرٌّ فَلَا تَقُلْ لَوْ أَنِّي فَعَلْتُ كَذَا وَكَذَا قُلْ قَدَّرَ اللهُ وَمَا شَاءَ اللهُ فَعَلَ، فَإِنَّ لَوْ تَفْتَحُ عَمَلَ الشَّيْطَانِ“ رَوَاهُ مُسْلِم
ٌ
«በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ፤ በአላህ ታገዝ፤ አትሰላች፤ መጥፎ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ፤ ‘ይህን ነገር እንዲህ ወይም እንዲያ ባደርገው ኖሮ…’ አትበል። ነገር ግን ‘አላህ የወሰነው ሆነ፤ አላህ የፈለገውን ይሰራል’ በል። ‘እንዲህ ቢሆን ኖሮ’ የሚለው ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል» ሙስሊም ዘግበዉታል


📝አላህ ተቅዋን እና መልካም ስራን ያግራልን!

وصلَّى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلَّم
«ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104)
🍁ረመዳን ሸህሩን ሙባረክ🍁
====================
★ ረመዳንን ከሌሎች ወሮች የሚለዮ 10 ነገሮች★


አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ሁላችንም እንደምናውቀው ውዱ የበረካ ወር የሆነው ረመዳን ለተጠቃሚዎች በበረካው ሊያምበሸብሻቸው አንድ ሁለት እያለነው ረመዳን በአመት ውስጥ ካሉ 12 ወራቶች አንዱ ነው እንዲሁም ቁርአን ውስጥ ከተጠቀሱት 4 የላቁ ወራትም አንዱ ነው። ረመዳን ከሌሎች ወሮች ለየት የሚያደርጉት ብዙ ነገሮች አሉ ከነዛም ዉስጥ
① ፆም መደንገጉ ፦ የረመዳንን ወር ለየት ከሚያደርጉት ነገሮች መሀከል አንዱና ዋነኛው ወሩን እንድንፆም መታዘዛችን ነው
ፆም አላህ ዘንድ በጣም ከፍተኛ ቦታ ካላቸው ኢባዳዎች መሀከል አንዱ ነው ፆም የሱና እና ዋጂብ የሚባሉ ክፍሎችም አሉት የሱና ፆም የሚባለው መፆም የተከለከለ ባቸው ጊዜያት ሲቀሩ በማንኛውም ቀን መፆም የሚቻል ሲሆን ዋጂብ ወይም ፈርድ(ግዴታ) የሚባለው ፆም ደግሞ አላህ በባሮቹ ላይ ግዴታ ያደረገው የፆም አይነት ነው አላህ ፆምን በኛላይ ግዴታ ማድረጉን ሲናገር እንዲ ይላል
(يا ايها الذن امن كتب عليكم اصيم كما كتب اللذين من قبلكم لعلكم تتقون)
(እናንተ ያመናችሁ ሆይ ፆም በናንተ ላይ ግዴታ ተደርጓል ልክ ከናንተ በፊት በነበሩት ግዴታ እንደተደረገው) ከዚ የቁርዓን አያ የምንማረው የመጀመሪያው ከኛበፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ መደንገጉን እና በኛም ላይ መደንገጉን ነው።
② የቁርአን መውረድ፦ ቁርአን ለሰውልጆች መመሪያና ማስተማሪያ ነው እንዲሁም ከዚበፊት የሆኑ ፣አሁን እየሆኑያሉና ወደፊት የሚሆኑ ለኛ አስተማሪና አስጠንቃቂ የሆኑ ነገሮችን የያዘ ነው። የዚህ ዉድ ቁርአን በረመዳን መውረድ ረመዳንን ከሌሎች ወሮች ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው። እና እኛ በዚ በረመዳን ቁርአንን ልንቀራ ይገባናል
ቀደምት ደጋግ ቀደምቶች በረመዳን እስከ 60 ጊዜ ያኸትሙ ነበር።አኛስ?
③ የሰይጣን መታሰር፦ በረመዳን ወርየጀነት በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ አመፀኛ ሰይጣናትም ይታሰራሉ። ነብያችን ሰ,ዐ,ወ እንዲህ ይላوغلقت السماء، ابواب فتحت رمضان إذا دخل إذا رواية وفي الشياطين وسلسلت جهنم،ابواب الجنة ابواب فتحت رمضان جاء

" ረመዳን ሲገባ የሰማይ በሮች ይከፈታሉ የጀሀነም በሮች ይዘጋሉ ሰይጣናትም ይቀፈደዳሉ ።’’ በሌላ ዘገባም” የጀነት በሮች ይከፈታሉ” ብለዋል(ቡኻሪና ሙስሊም)

④ የስራዎች ምንዳ መደራረብ፦ በረመዳን ወር የሐሰናት ወይም የመልካም ስራዎች ምንዳ እጥፍ ድርብ ይሆናል። ነብዩ ሰ,ዐ,ወ ተጠይቀው ከሰደቃዎች ሁሉ በላጩ የቱ ነው ተብለው "በረመዳን የሚሰጥ ነው ብለዋል"
⑤ ከአንድሺ ሌሊቶች በላጭ የሆነችው ለይለትል ቀድር፦ አላህ ከአንድ ሺህ ሌሊቶች ያስበለጣት ሌሊት ናት እንዲሁም የአመቱን ጉዳዩች የሚፅፍባት የተበረከች ሌሊት ናት "ليلة القدر خير من الف شهر"
" ሌሊቶችም በላጭመወሰኛይቱ ሌሊት ከሺህ ናት"

⑥ መላኢኮች በብዛት ወደ መሬት መውረድ፦ አላህ አንዲ ይላል ፦تنزل الملاإكة والروح فيها بإذن ربهم من كل أمر"
"በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ "
⑦ ሱሁር (የሌሊት ምግብ) ፦ ሱሁር ካለፍት ህዝቦች ፆም የኛን የሚለይና ብዙ በረካዎችን የያዘነው ነብዩ ሰ,ዐ,ወ እንዲህ ይላሉ "تسحروا فإن في السحور بركة"
"ሱሁርን ብሉ ሱሁር መብላት
በረካ አለውና "
⑧ የተራዊህ ሰላት፦በረመዳን ብቻ በጀማአ የሚሰገደው የሱና ሰላት የሆነው ተራዊህ አንዱ ረመዳንን ለየት ከሚያደርጉ ነገሮች መሀከል አንዱ ነው። ከረመዳን ውጭ ይህ ሰላት አይሰገድም ።
⑨ የኡምራ ትሩፋት፦በረመዳን ወር ኡመራ ማድረግ ከነብዩ ሰ,ዐ,ወ ጋር ሀጅ እንደ ማድረግ ነው።"عمرة في رمضان تعدل حجة او قال حجة معي"
"በረመዳን የሚደረግ ኡምራ ከሀጅ ጋር እኩል ነው ወይም ከኔጋር ከሚሰራ ሀጅ እኩል ነው"ብለዋል
¹⁰ ወንጀል ማበሻ፦ረመዳን ወንጀል እንዲታበሱ ከሚያደርጉ ነገሮች መሀል አንዱና መሰረታዊው ነው።
" الصلوات الخمس ولجمعة الى الجمعة ورمضان الى رمضان مكفرات لما بينهن إذا اجتنبت الكبائر"
"ታላላቅ ወንጀሎች ከተራቁ አምስት ወቅት ሰላቶች ከጁምአ እስከ ጁምአ ከረመዳን እስከ ረመዳን በመሀከላቸው ያለውን ወንጀል ያስምራሉ"

አላህ ካለ ከረመዳን ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዩች ላይ ክፍል ሁለት ይቀጥላል።

@Nurahend




https://t.me/httpsIBNumuhammed
🌿🌿🌿🍃ጥቆም🍃🌿🌿🌿

💫ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ:-

"አንድ ሰው ዕውር ካለ መሆኑም ጋ ዐይኖቹን ቢጨፍናቸው ምንም ነገር ማየት እንደ ማይችለው ሁሉ፤ቀልብም በሚሸፍናት የወንጀል ጨለማ ምክንያት ሐቅን መመልከት አትችልም።"

🔻አይን ኖሮን ከመታወር ቀልብ ኖሮን ከመደናበር እናስተውል።አላህም ይጠብቀን።
አላህን መፍራትና መልካም ስራ በመስራት ላይ መታጋገዝ ግዴታ ነው ፡፡

يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا اتَّقُوا اللَّهَ وَابْتَغُوا إِلَيْهِ الْوَسِيلَةَ وَجَاهِدُوا فِي سَبِيلِهِ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ

እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ ፡፡ ወደርሱም መቃረቢያን (መልካም ሥራን ) ፈልጉ ፡፡ ትድኑ ዘንድም በእርሱ መንገድ ታገሉ፡፡

وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ ۚ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۖ إِنَّ اللَّهَ شَدِيدُ الْعِقَابِ

በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡አላህንም ፍሩ ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
«ከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡» (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 104)
የአኺራ ስንቅ زاد الآخرة
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሁለት ➭በአላህ ፈቃድ ይህችን አጭር ማስታወሻ በውስጣቸው አርእስቶች የያዙ ሁለትዋና ክፍሎች አድርጌ አዘጋጅቻታለሁ። በክፍል አንድ መግቢያ እና መንደርደሪያ፣የተፈጠርንለትን አላማ (ተውሒድን)፣ እዚህ ምድር ላይ የሰው ልጆች እንዴት በአላህ ላይ ማጋራት እንደጀመሩ፣ በፍጡራን እና በፈጣሪ አላህ መሃል ያለው ታላቅ ልዩነት፣አምልኮ ለማን እንደሚገባው…
➲መንዙማ
➫➫➫➫➫

➧ክፍል ሶስት


➲ከሰው ልጆች ሁሉ አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም)እስከ መጀመሪያው መልእክተኛ ኑሕ(አለይሂ ሰላም)ድረስ አስር ክፍለ ዘመን ነበር።በዚህ ወቅት የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ሃይማኖት በእስልምና ውስጥ ነበሩ። ችግሩ የተፈጠረው አንድነቱ የፈረሰው ኑሕ(አለይሂ ሰላም) የተላኩባቸው ሰዎች በደጋጎች ላይ ድንበር አልፈው የባእድ አምልኮት ላይ ሲወድቁ ግዜ ነው።

🔁በዚህም የተነሳ አዛኙ አላህ እነዚያ ህዝቦች የተፈጠሩለትን አላማ ያውቁ ዘንድ የመጀመሪያውን መልእክተኛ ኑሕ (አለይሂ ሰላም)ወደ ተውሂድ እንዲጠሯቸው ላካቸው። ኑሕም(አለይሂ ሰላም) ዘጠኝ መቶ ሀምሳ አመት የተውሂድ ጥሪ እንዲቀበሉ ይህን የተቀበለም ብስራት እንዳለው ፣ከአላህ ውጭ ሌላ አካል እሚፈጽሙትን አምልኮ እንዲርቁ ይህን ካላደረጉ ከባድ አደጋ እንደሚያጋጥማቸው በማስጠንቀቅ ተጣሩ።

➠ልብ እንበል የሰይጣ ወጥመዱ ከባድ ነው። በአንድ ሀይማኖት ላይ የነበሩትን ህዝቦች በታተናቸው። አብዛሀኛዎቹ የመጀመሪያውን መልእክተኛ ኑሕ ጥሪ አንቀበልም ብለው ለጥፋት ተዳረጉ።

➧አላሁ(ሱብሀነሁተዓላ )የነዚህን አጋሪያን (መጥፎ ፉጡሮች) መጨረሻ ከባድ የሆነ ቅጣት ቀጥቷቸው ከባድ አደጋንም ተከናነቡ። ጥፋታቸው ከባድ ስለነበረ በአላህ ትእዛዝ ሰማይ የያዘችውን ውሃ ለቀቀች ።ምድር የያዘችውን ውሃ ተፋች፣ተራራ የሚያካክሉ ፣ማእበሎች ተነስተው እነዚህ ሁሉ አመጸኞች ውርደትን ቀመሱ። በሁለት አገርም ተዋረዱ።

📘ዝግጅት መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ።

°
°
°
ኢንሻአሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

✏️መጻፍ ካልቻልክ አንብብብ‼️ማንበብ የተሻለ ሰው ያድርጋል።

⤵️ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ ቀጣይ ክፍሎችን ይከታተሉ።

ጆይን በማለት ተጠቃሚይ ሁኑ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsIBNumuhammed
➊) ነብዪ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-
«አላህ መልካም ሚስትን የለገሰው ሰው፣ የሀይማኖቱን ግማሽ ክፍል አግዞታል፣ በቀሪው ደግሞ አላህን ይፍራ»።
ምንጭ:-📒📕📙ሶሒሁ ተርጊብ (1916)

➋) ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:-
«ለሁለት ለሚዎደዱ ጥንዶች ትዳርን የመሰለ መልካም ነገርን አልታየላቸውም»።
ምንጭ:-📒📙📕ሲልሲለቱ ሶሒሀህ (624)

➌) «የባሏን ሀቅ ያልጠበቀች ሴት የእምነትን ጣዕም አታገኝም»።
ረሱል (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒📕📙ሶሒሁ ተርጊብ (1939)
@guzo wede jenet
የአኺራ ስንቅ زاد الآخرة
➲መንዙማ ➫➫➫➫➫ ➧ክፍል ሶስት ➲ከሰው ልጆች ሁሉ አባት ነብዩላህ አደም (አለይሂ ሰላም)እስከ መጀመሪያው መልእክተኛ ኑሕ(አለይሂ ሰላም)ድረስ አስር ክፍለ ዘመን ነበር።በዚህ ወቅት የሰው ልጆች ሁሉ በአንድ ሃይማኖት በእስልምና ውስጥ ነበሩ። ችግሩ የተፈጠረው አንድነቱ የፈረሰው ኑሕ(አለይሂ ሰላም) የተላኩባቸው ሰዎች በደጋጎች ላይ ድንበር አልፈው የባእድ አምልኮት ላይ ሲወድቁ ግዜ ነው። 🔁በዚህም…
➲መንዙማ
እውነታው፣ አደጋዎችና መዘዞቹ
➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫➫

➻ክፍል አራት

➧በሌላ ጎኑ ድል ለአሏህ፣ ለመልክተኛው እና ለአማኛች ነውና አሏህ ለነብዩሏህ ኑሕን (አለይሂ_ሰላም) በጣም ጥቂት ከሆኑ ተከታዮቻቸው ጋር ከእንስሳት ጥንድ ጥንድ በመሆን እዛች መርከብ ላይ ተጭነው በዚህ ምድራዊ ህይወት ከመስመጥ ተጠበቁ። በአላህ ፍቃድ የሚቀጥለው አለም ላይ ካለው አሳማሚ ቅጣት ተጠብቀው የሰላም አገር የሆነችው ጀነት ውስጥ ይገባሉ። ይህ ከባድ የሆነ የሰይጣን ወጥመድ ትኩረት ይሻልና እስቲ ትንሽ ጠለቅ ብለን እንየው፦

➳የሰው ልጆች ከአንድነታቸው በኃላ የተበታተኑት በአሏህ ላይ በማጋራታቸው ነው። አሏህ ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል፦

كَانَ النَّاسُ أُمَّةً وَاحِدَةً فَبَعَثَ اللَّهُ النَّبِيِّينَ مُبَشِّرِينَ وَمُنذِرِينَ وَأَنزَلَ مَعَهُمُ الْكِتَابَ بِالْحَقِّ لِيَحْكُمَ بَيْنَ النَّاسِ فِيمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ ۚ وَمَا اخْتَلَفَ فِيهِ إِلَّا الَّذِينَ أُوتُوهُ مِن بَعْدِ مَا جَاءَتْهُمُ الْبَيِّنَاتُ بَغْيًا بَيْنَهُمْ ۖ فَهَدَى اللَّهُ الَّذِينَ آمَنُوا لِمَا اخْتَلَفُوا فِيهِ مِنَ الْحَقِّ بِإِذْنِهِ ۗ وَاللَّهُ يَهْدِي مَن يَشَاءُ إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ

➲ሰዎቹ ሁሉ አንድ ሕዝብ ነበሩ፤ (ተለያዩ)፡፡ አላህም ነቢያትን አብሳሪዎችና አስፈራሪዎች አድርጎ ላከ፡፡ ከእነርሱም ጋር መጻሕፍትን በሰዎቹ መካከል በዚያ በርሱ በተለያዩበት ነገር ይፈርድ ዘንድ በእውነት አወረደ፡፡ በእርሱም (በሃይማኖት) ግልጽ አስረጂዎች ከመጡላቸው በኋላ በመካከላቸው ለኾነው ምቀኝነት እነዚያው የተሰጡት እንጂ አልተለያዩበትም፡፡ አላህም እነዚያን ያመኑትን ሰዎች ለእዚያ ከእውነት በርሱ ለተለያዩበት በፍቃዱ መራቸው፡፡ አላህም የሚሻውን ሰው ወደ ቀጥተኛው መንገድ ይመራል፡፡ [አል-በቀራህ-213]

➧ከአድነት በኃላ የተለያዩት በሺርክ ነው። ወደ ሽርክ እነዚያ ኑሕ የተላኩባቸው ህዝቦች የፈፀሙት ደግሞ ይህን የበደሎች ሁሉ ታላቅ በደል በሆነው ሺርክ ነው። ወደሺርክ ደግሞ የወሰዳቸው ከአሏህ እዝነት የተባረረው ሸይጧን እነሱን ቢድዐን በማሰራት ነው።

وَقَالُوا لَا تَذَرُنَّ آلِهَتَكُمْ وَلَا تَذَرُنَّ وَدًّا وَلَا سُوَاعًا وَلَا يَغُوثَ وَيَعُوقَ وَنَسْرًا

አሉም «አምላኮቻችሁን አትተዉ፡፡ ወድንም፣ ሱዋዕንም፣ የጉሥንም፣ የዑቅንም ነስርንም አትተው፡፡ [ኑሕ -23]

➠እነዚህ አምስት "አማልክት" ተብለው የተጠሩ ግለሰቦች እንማን ናቸው? እነዚህ ግለሰቦች በታላቁ ሶሐባ አብደላህ ኢብኑ አባስ (ረዲየላሁ እንሁን) አንደበት "ሷሊሆች(መልካም የአሏህ ባሪያዎች)" መሆናቸው የተመሰከረላቸው ናቸው። እነዚህ አምስት ሷሊሆች ሲሞቱ ሸይጧን ለህዝቦቻቸው አዛኝ መስሎ “ይቀማመጡ የነበረበት ቦታ ላይ ሃውልት ብታደርጉላቸው” አላቸው። እነሱም እሺ ብለው ተቀበሉት።

📘ዝግጅት መንዙማ ከሚለው ከኡስታዝ ሳዳት ከማል ኪታብ የተወሰደ።

ኢንሻአሏህ ይቀጥላል◉◉◉◉◉

✏️መጻፍ ካልቻልክ አንብብብ!ማንበብ የተሻለ ሰው ያድርጋል።

ጆይን በማለት ወደ ቻናላችን ይቀላቀሉ
➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴
https://t.me/httpsIBNumuhammed