☦️ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ☦️
60 subscribers
30 photos
2 videos
1 file
2 links
@fnote abew የአቦቶች መንገድ መከተል
Download Telegram
☦️🕯ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት አጋርህን ፈልግ። ከመታመምዎ በፊት ሐኪምዎን ይፈልጉ; መከራም ሳይደርስባችሁ ጸልዩ በመከራችሁም ጊዜ ታገኙታላችሁ እርሱም ይሰማችኋል።🕯☦️

♰ ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ ♰
👏1
+++ወጣት ነህን? +++
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ወጣት ነህን ወጣት በመሆንህ ገና ብዙ ዘመን አለኝ ዕድሜዬ ገና ነው ብለህ አትተማመን ተለክቶ የታወቀ ቀሪ ጊዜ ያለህም አድርገህ አታስብ  ‹‹የጌታ ቀን ድንገት እንደ ሌባ በሌሊት ይመጣልና›› 1ኛ ተሰ5፤2 ስለዚህ ምክንያት የእድሜያችንን መጨረሻ አስቀድመን እንዳናውቀው አደረገ ከዛሬ ዕለት ጀምሮ በትጋት ዝግጅታችንን እንጀምር ዘንድ በለጋ ዕድሜያችን ሲቀጩ በየቀኑ አታይምን ስለዚህም አንዱ ሲመክር እንዲህ ብሏል “ወደ እግዚአብሔር ለመመለስ አትዘግይ ከዛሬ ነገ እመለሳለሁ እያልህ አትቁጠር” ሲራ 5፤8 ዛሬ ነገ እመለሳለሁ ስትል አንድ ቀን ባቋራጭ እንዳትወሰድ፤ ስለዚህ ሽማግሌውም ይህንን ምክር ልብ ይበል ወጣቱም ይህንን ነገር ተረድቶ ተግባራዊ ያርግ ዘንድ ይሁን ወይስ በምቾትና ሁሉ ነገር ተሟልቶልህ የምትኖር እስካሁን ችግር የሚባል ደርሶብህ የማታውቅ ባለጸጋ ነህን እንዲህም ቢሆን ቅዱስ ጳውሎስ የሚለውን ስማው “ሰላምና ደኅንነት ነው ሲሉ ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል” 1ኛ ተሰ 5፤3 የዚህ ዓለም ነገሮች ሁሉ ተለዋዋጮች ናቸው እኛ በራሳችን የወደፊት ሕይወትና ሁኔታ ላይ ማዘዝ የምንችልና የሰለጠን አይደለንም ነገር ግን በጽድቅ ሥራ ላይ የሰለጠንን እንሁን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቸርና ሰውን ወዳጅ ነውና››

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ሕይወቱና ትምህርቱ ገጽ 134
Forwarded from ቤቴል 💒
1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:10-11

10. በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁምል ያበረታችሁማል።
11. ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን።

ሰናይ ቀን ❤️❤️❤️
😢1
◈ኦርቶዶክሳውያን የሚድያ ተጠቃሚዎች መልእክቱ በትክክል ለአባቶች ይደርስ ዘንድ በየአቅራቢያችሁ ላሉ አባቶች ሁሉ እንድትልኩ  እንማጸናለን።
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 11


1. በእግዚአብሔር ታመንሁ፤ ነፍሴን። እንደ ወፍ ወደ ተራሮች ተቅበዝበዢ እንዴት ትሉአታላችሁ?
2. ኃጢአተኞች እነሆ ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።
3. አንተ የሠራኸውን እነሆ እነርሱ አፍርሰዋልና፤ ጻድቅ ግን ምን አደረገ?
4. እግዚአብሔር በተቀደሰው መቅደሱ ነው፤ እግዚአብሔር፥ ዙፋኑ በሰማይ ነው፤ ዓይኖቹ ወደ ድሃ ይመለከታሉ፥ ቅንድቦቹም የሰው ልጆችን ይመረምራሉ።
5. እግዚአብሔር ጻድቅንና ኅጥእን ይመረምራል፤ ዓመፃን የወደዳት ግን ነፍሱን ጠልቶአል።
6. ወጥመድ በኅጥኣን ላይ ያዘንባል እሳትና ዲን ዐውሎ ነፋስም የጽዋቸው እድል ፈንታ ነው።
7. እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፤ ቅንነት ግን ፊቱን ታየዋለች።
አቤቱ ከቁጣ የራቅህ ይቅርታህ የበዛ ጻድቅ ልበ ሰፊ መሐሪ ሆይ አከብርሃለሁ። ... ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ፈልገህ ከቦታቸው ልታገባ ልትመልስ የመጣህ አንተ ነህ የጎሰቆልሁ እኔንም ፈልገህ ከሚናጠቁ አንበሶች ወደ ምድንበት ያለ ድንጋፄም በጥላህ ዐርፌ ወደ ምኖርበት ወደማትፈርስ ቅጽርህ ልታገባኝ ምን ያህል ይገባህ ይሆን! አቤቱ በባርያህ በዳዊት ቃል የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ዘንድ ክቡር ነው ብለሃልና ጌታዬ ሆይ በኃጢአት ከሚመጣ ሞት አድነኝ ሕይወትና ሥርየትን ስጠኝ።

መዝሙር 94

(1) ኑ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለእግዚአብሔርም ለእድኃኒታችን እልል እንበል። (2) በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ በመዝሙርም ለእርሱ እልል እንበል። (3) እግዚአብሔር ታላቅ አምላክ በአማልክትም ሁሉ ላይ ታላቅ ንጉሥ ነውና። (4) የምድር ዳርቻዎች በእጁ ውስጥ ናቸውና የወንዞችም ራሶች የእርሱ ናቸው። (5) ባሕር የእርሱ ናት እርሱም አደረጋት የብሩህንም ምድር እጆቹ ፈጠሩአት። (6) ኑ እንስገድለት ለእርሱም እንገዛ በፈጠረን በእግዚአብሔር ፊት እንክበርከክ። (7) እርሱ አምላካችን ነውና እኛ የሜዳው ሕዝብ የማሰማሪያውም በጎች ነንና። (8) ዛሬ ቃሉን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ በምድረ በዳ በፈተና ቀን በማሳረር እንደ ሆነ። (9) አባቶቻችሁ የፈተኑኝ መረመሩኝም ሥራዬንም ያዩበት። (10) ያንን ትውልድ አርባ ዓመት ተቆጣሁት ልባቸው ሁልጊዜ ይስታል መንገዴንም አላወቁም አልሁ። (11) ወደ ማረፊያዬ እንዳይገቡ በቁጣዬ የማልሁት።
ተስፋ መቁረጥና ስንፍና እጅግ ክፉዎች ናቸውና ከእነዚህ እንራቅ፡፡

“ክፋታቸውስ እንደምን ያለ ነው?” ያልከኝ እንደ ኾነም እንዲህ ብዬ እመልስልሃለሁ፡- ተስፋ መቁረጥ የወደቀው ሰው እንደ ገና እንዲነሣ አይፈቅድለትም፤ ስንፍናም የቆመው ሰው እንዲወድቅ ያደርጓል፡፡ ስንፍና ገንዘብ ያደረግናቸውን መልካም ነገሮች ከማሳጣቱም በላይ ሊመጡ ካሉ ክፉ ነገሮች እንዳንጠበቅ ያደርገናል፡፡ ስንፍና ከሰማያትም ቢኾን ይጥለናል፤ ቀቢጸ ተስፋም ወደ ክፋት ዐዘቅት እንድንሰጥም ያደርገናል፡፡ በእውነት በቀቢጸ ተስፋ ካልተያዝን ከጽኑ ክፋት መመለስ ይቻለናል፡፡

እነዚህ ኹለቱ ምን ያህል ኃይል እንዳላቸው ይበልጥ ታውቅ ትረዳ ዘንድ ምሳሌ ጠቅሼ ልንገርህን? መልካም! ዲያብሎስ መጀመሪያ ላይ መልካም ነበር፤ ከስንፍናና ከቀቢጸ ተስፋ የተነሣ ግን እንደ ገና የማይነሣ ኾኖ ወደ ክፋት ወደቀ፡፡ ዲያብሎስ ጥንቱ መልካም እንደ ነበረ ሲናገር መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ያለውን አድምጥ፡- “ሰይጣን እንደ መብረቅ ከሰማይ ሲወድቅ አየሁ” (ሉቃ.10፡18)፡፡ መብረቅ የሚለው አገላለጽ ዲያብሎስ ከመውደቁ በፊት ምን ያህል ብሩህ ሕይወት እንደ ነበረውና በምን ያህል ቅጽበት እንደ ወደቀ የሚያመለክት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ ተሳዳቢ፣ አሳዳጅና ነውርን የማያውቅ ሰው ነበር (1ኛ ጢሞ.1፡13)፡፡ ነገር ግን ቀናተኛ ስለ ነበርና ተስፋ ስላልቈረጠ ተነሥቶ መላእክትን የሚተካከል ኾነ፡፡ ይሁዳ ሐዋርያ ነበር፤ ነገር ግን በስንፍና ምክንያት ጌታውን አሳልፎ ሰጠ፡፡ ፈያታዊ ዘየማን ደግሞ እንደዚያ እጅግ ክፉ የነበረ ሰው ቢኾንም ቅሉ ተስፋ ስላልቈረጠ ኹሉንም ቀድሞ ገነት ገባ፡፡ ፈሪሳዊው ሰው ራሱን ከፍ ከፍ ያደርግ ስለ ነበር ከምግባር ማማ ላይ ወደቀ፡፡ ቀራጩ ግን ተስፋ ስላልቈረጠ ከፈሪሳዊውም በልጦ ወደ ምግባር ሰገነት ወጣ፡፡
ስለዚህ ይህን ዐውቀን ዘወትር ከስንፍናና ተስፋ ከመቁረጥ እንራቅ!

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👏1
፧፧ እኔ ከሚስቀው ዓለም አይለሁም  ፧፧

በአንድ ወቅት ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ በግብፅ ፓርላማ ላይ እንዲገኙ ጥሪ ደረሳቸው። ታዲያ አንድ እሚያውቃቸው ሰው ከሰው ጋር እንዲመሳሰሉ ስብሰባው ላይ የክህነት ልብሳቸውን ልብስ ትተው ሱፍ ማድረግ እንዳለባቸው ነገራቸው አለበለዚያ ግን መሳቂያ ይሆናሉ አላቸው። ይህንን የሰሙት ብጹዕነታቸው "እኔ ያለሁት ከሚስቀው ዓለም ጋር ሳይሆን ከሚሳቅበት ከክርስቶስ ጋር ነው። ስለዚህ አይደንቀኝም ዓለም ምንም ይበል!!! አሉት ይባላል። ከክርስቶስ ጋር የሚኖር ሰው ስለምድራዊ ክብር አይጨነቅም ተሰደብኩ ተነቀፍኩ ተዋረድኩ አይልም ለምን? ሁልጊዜም ቀራንዮ በአይኑ አለ እኛም በዓለም ፊት ዓለምን በክርስቶስ ፊት ክርስቶስን ከመምሰል ከንቱ መመላለስ እንድን ዘንድ የቅዱሳን አበው ማስተዋሉን ያድለን የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍፁምም የሆነውን ነገር ምን እንደሆነ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህንን ዓለም አትምሰሉ። ሮሜ 12:2


የአባቶቻችን ጸጋ በረከት ይደርብን አሜን፫

❤️መልካም አዳር❤️
🥰1😢1
Forwarded from ቤቴል 💒
አንዳንድ  ጊዜ  ሰው  ብቻውን  የሚቀርበት  ጊዜ  አለ ፤ ብቻውን  ምንም  በቃ !
አንተን ሞቼም  አልተውህም   ያለህ ሰው ሁሉ ምንም ፤

የሰው  ልጅ  የልፋቱን  ዋጋ እግዚአብሔርን  ካደረገ  ሰው ምንም  ይነሰው  በሰላም  ይኖራል ፤
በዚህ  ዓለም  ከባዱ  ነገር  ልብን  ሰላም  ማድረግ  ነው ! ከሰው ጋር ለመኖር ዋሽቶም  ቀጥፎም አስመስሎም  ሰላም  ሆኖ ይኖራል!

ልብን  ግን ዋሽቶ ቀጥፎ  አስመስሎ  ሰላም  ማድረግ አይቻልም !ልብን  ሰላም  ለማድረግ  እግዚአብሔርን  ዋጋ  ማድረግ  ነው !!! 

+ሊቀ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን +

መልካም  ማለዳ ❤️❤️❤️
ወገኖቼ ብናውቅበት እግዚአብሄርን በትህትና እናመሰግነዋለን ራሳችንን ብቻ እየከሰስን የእግዚአብሄርን ምርጦች ደግሞ እየተመለከትን እንጓዛለን ብናስተውል ራሳችንን ከዚህ አለም ሃጢአት እንጠብቃለን፡ ብናስተውል የድሆች ወዳጅ፡ የተራቡ አጉራሽ እንሆናለን የእግዚአብሄር ልጆች ብንሆን ትእዛዙን እናከብራን፡ እርስ በእርሳችንም እንዋደዳለን፤ ዲያቢሎስን ብንክደው የእርሱንም ሃሳብ እናውቃለን እንክዳለንም፤ በስጋ ብንመላለስ ግን ክርክር ትቀርበናለች ስንፍና ትጠጋናለች ድሆች አይታዩንም ንፅህና አይገኝብንም፤ በስጋ ብንመላለስ ክርስቶስን ለሌሎች እንሰብካለን እኛ ግን ክርስቶስን አላወቅነውም ብርሃንን ለሌሎች እናመላክታለን እኛ ግን ውስጣችን ጨልሟል እውር ደግሞ ማንን መምራት ይችላል? ራሱንም ተመሪውንም ወደገደል ከመክተት ውጭ? ለክርስቲያን ግን ትህትና ምግቡ መጠጡ ናት፡ ትሁታን ዘወትር እግዚአብሄርን ያዩታልና፡ ትእቢተኞች ግን ራሳቸውን ከፍ አድርገው ሌሎቹን ሲተቹ ይታያሉ በዚህ ዲያቢሎስን ይመስሉታል፡፡ እግዚአብሔር ትእቢተኞችን ያዋርዳል የተዋረዱትን ደግሞ ከፍ ከፍ ያደርጋል፡፡

📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 12


1. አቤቱ፥ አድነኝ፤ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
2. እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።
3. የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ፤
4. ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።
5. ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር። አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።
6. በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
7. አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።
8. በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።
እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል።

— የዮሐንስ ራእይ 3:20
🌹🌼🌹🌹ሰቆቃወ ድንግል🌼🌹🌼🌹🌹
ምዕረ በዘባንኪ ወምዕረ በገቦኪ፤
ማርያም ብዙኃ በሐዚለ ሕፃን ደከምኪ፤
ሶበኒ የሐውር በእግሩ ከመ ትፁሪዮ ይበኪ፤
አልቦ እንበለ ሰሎሜ ዘያስተባርየኪ ለኪ፤
ወዮሴፍ አረጋዊ ዘይፀውር ስንቀኪ።

🌹🌼🌹🌼🌹🌼🌹🌼🌹🌼🌹🌼🌹
ትርጉም፦
ማርያም አንድ ጊዜ በጀርባሽ አንድ ጊዜ በጎንሽ ልጅሽን በማዘል በእጅጉ ደከምሽ፤ በእግሩ በሚሄድበት ጊዜም ትሸከሚው ዘንድ ያለቅሳል፤
ስንቅሽን ከሚሸከም ከሽማግሌ ዮሴፍና ከሰሎሜ በቀር አንቺን የሚያስተጋግዝሽ የለም።

🌹🌼🌹🌼🌹🌼🌹🌹🌼🌹🌹🌹🌹🌹
❤2
*ልጄ ሆይ፥ አእምሮህን በነገው ጭንቀት አትሙላው* ፤ ምክንያቱም *እግዚአብሔር* አስቀድሞ ስለ ነገ አስቦበታል። ውጫዊው ማዕበል ይናወጥ ይሆናል፤ ነገር ግን ልብህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ ከሰጠህ፤ በውስጥህ የሚኖር ሰላም ከዓለም ውካታ ሁሉ በላይ ይሆናል።


*አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ💙🦋*



ሰላም  ዕደሩ  የነገ  ሰው  ይበለን ❤️❤️❤️
❤1👏1
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ ምንባብ
መዝሙረ ዳዊት 26:1

1. እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?


ሰናይ እለተ ሰንበት ❤️❤️❤️
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 13
1. አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
2. እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ሁልጊዜ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይጓደዳል?
3. አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፤ ጠላቴ። አሸነፍሁት እንዳይል፥
4. የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።
5. እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል።
6. የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።
👏1
Forwarded from ቤቴል 💒
ገላትያ 5
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፥ ደስታ፥ ሰላም፥ ትዕግሥት፥ ቸርነት፥ በጎነት፥ እምነት፥ የውሃት፥ ራስን መግዛት ነው።
²³ እንደዚህ ያሉትን የሚከለክል ሕግ የለም።
²⁴ የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ።
²⁵ በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ።
²⁶ እርስ በርሳችን እየተነሣሣንና እየተቀናናን በከንቱ አንመካ።
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 14


1. ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
2. የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
3. ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
4. ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
5. ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤
6. ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
7. ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
👏1
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ ምንባብ

የዮሐንስ ወንጌል 16:20-21

20. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
21. ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።


ሰናይ ዕለተ ሰኞ ይሁንልን ❤️❤️❤️
👏1
እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤

— ትንቢተ ኢሳይያስ 55:6
👏1