☦️ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ☦️
60 subscribers
30 photos
2 videos
1 file
2 links
@fnote abew የአቦቶች መንገድ መከተል
Download Telegram
ወንድሞቼ "እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡

ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡ እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
❤1🥰1
መከራዋ በዝቶ በሀዘን ስትማስስ
ልጆቿን እያጣች ዘወትር ስታለቅስ
በደም ላይ ደም ብዝቶ ጎርፍ እየሆነባት
ኢትዮጵያዬ ሀገሬ ክረምቱ አለቅ አላት
ያለፈ ታሪኳን ፍቅሯን የሚያስታውስ
ያላንቺ ማን አለ እንባዋን የሚያብስ
ጌታን በጀርባ አዝለሽ ስትንከራተቺ
በውሀ ጥም ሀሩሩ በድካም ስትዝዬ
እጆቿን ዘርግታ እናቴ ነይ ያለች
ከሙሉ መሶቧ ማዓድ ያቀረበች
ያቺ ቅድስት ሀገር እምነቷን አጉድላ
ባዶዋን ቀርታለች እናቴ አንቺን ጥላ
ድረሺላት ባክሽ በጥላሽ ሸሽጊያት
የያዘችው መንገድ መጥፊያ ነው የሆናት
በዘር በሀይማኖት በክህደት አብዳለች
ልጆቿን በከንቱ ቀን በቀን ታጣለች
በመዓት ቸነፈር ብዙ ነው ስቃይዋ
አዛኝ ልብ ያጣ ነው የሚዘንብ እንባዋ
እናቴ አዛኝቷ ሀገሬን ተመልከች
የማህጸኗ ፍሬ መገኛዬ እሷ ነች
አይ ሀገሬ ኢትዮጵያ ይህም ያልፋል
😢1
Forwarded from ቤቴል 💒
*<<የብልጣ ብልጥ ጸሎት ሦስት ናቸው።*
"በአባ ገብረኪዳን ግርማ "
=============+++++


*☦፩ኛው* ፦ቤተክርስቲያን ሄዶ፦
እግዚአብሔርን ይህቺን አርግልኝ፣አርግልኝ:አርግልኝ ብሎ መመለስና

፠የጠየቀውንም ሰይጣን የሆነ ነገር ያደርገኛል ብሎ የሚፈራ(ፈሪ)ማለት ነው።

፠፠ጸሎቱን ወጪ እያደረገ ከእግዚአብሔርም ጥበቃ እየተቀበለ እንደ ዘበኛ እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ነው።
ምስኪን!

*☦፪ኛው* ፦የሆነ ነገር እንዲያደርግለት ብቻ እግዚአብሔርን የሚጠራ ማለት ነው።

፠ እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በአምላክነቱና በአባትነቱ የማይርበው ሰው ማለት ነው።

ጸሎቱን የሚጸልየው፦
#ወይ የሆነ ነገር እንዳይደርስበት
#አልያም የሆነ የጎደለውን እግዚአብሔር እንዲሞላለት ብቻ ነው።

☦ *፫ኛው* ፦"እስመ በአብዝኆ ንባቦሙ ይመስሎሙ ዘይሰምዖሙ እግዚአብሔር።

ቃላትን በመድርደር ብቻ እግዚአብሔር የሚሰማቸው የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው።

*ጸሎቱን ከጸለዩ በኋላ* ፦
እንደዚህ ሆኖ፣
እንደዚህ ሆኖ፣
እንደዚህ ሆኖ
፣እንደዚህ ሆኖ፣እያሉ እግዚአብሔርን ወግ እንደማውጋት የሚያስመስሉ ናቸው።

እግዚአብሔርን እንደ አባት ብናወጋው ችግር የለውም።
ነገር ግን እንትናን እንትን ብዬ፣
እነ እገሌም ጠላቶቼ ናቸው፣
እገሌን እኔ አልደረስኩበትም የደረሰብኝ እራሱ ነው
እያሉ መናገር ማለት ነው።

ይህንን እግዚአብሔር ሳያውቅ ቀርቶ ነው? ይህንንማ እግዚአብሔር ያውቀዋል።


ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን በምስጋና የጀመርነውን ቀን በምስጋና እንጨርስ እና ለሊቱን ለባለቤቱ አደራ እንስጥ 🙌🙌❤️❤️❤️
❤1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 25


1. አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2. አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ፤ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3. አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።
4. አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
5. አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
6. አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
7. የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፤ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
8. እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
9. ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
10. የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
11. አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
12. እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል።
13. ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14. እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
15. እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
16. እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም።
17. የልቤ ችግር ብዙ ነው፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18. ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19. ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
20. ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፤ አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21. አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
22. አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
❤1👏1
ወይቤሎሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን ለምንት ኢየሐውሩ አርዳኢከ በከመሠርዑ ረበናት ወዘእንበለይሐጸቡ እደዊሆሙ ይበልዑ እክለ

ወአወሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎሙ  መደልዋን ሠናየ ተነበየ ኢሳይያስ ላዕሌክሙ እንዘይብል ዝ ሕዝብ በከናፍሪሆሙ ያከብሩኒ ወበልቦመሰ ነዋኅ ይርኅቁ እምኔየ

ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ስርዓት ለምን አይሄዱም አሉት? እጃቸውንም ሳይታጠቡ ለምን ይበላሉ ?

ኢየሱስ ክርስቶስም አላቸው መለሰላቸው እናንተ ግብዞች ኢሳይያስ እኒህ ሕዝብ በከንፈራቸው ያከብሩኛል በልባቸው ግን ፈጽመው ከእኔ ይርቃሉ ብሎ ኢሳይያስ እውነት ተናግሮባቸኋል ።
❤2👏1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 25(26)

1. አቤቱ፥ እኔ በየውሃቴ ሄጃለሁና ፍረድልኝ፤ በእግዚአብሔርም አምኛለሁና አልናወጥም።
2. አቤቱ፥ ፍተነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፍተን።
3. ምሕረትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥ በእውነትህም ተመላለስሁ።
4. በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥ ከዓመፀኞችም ጋር አልገባሁም።
5. የክፉዎችን ማኅበር ጠላሁ፥ ከዝንጉዎችም ጋር አልቀመጥም።
6. እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፤ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
7. የምስጋናን ድምፅ እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
8. አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
9. ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ።
10. በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች።
11. እኔ ግን በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም።
12. እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፤ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
🥰1👏1👀1
እውቀትና ትዕቢት የድኅነት መንገድ አይደሉም
የሰው ልጅ በተፈጥሮው ለማወቅ ይጓጓል፤ ዕውቀትንም ሲገበይ የሕይወትን ምሥጢር የጨበጠ ይመስለዋል። ነገር ግን እውቀት በራሱ ፍጹም ባለመሆኑ፣ በትሕትና ካልተገራ ለባለቤቱ የውድቀት መንስኤ ይሆናል። ብዙዎች ባነበቡት መጽሐፍ፣ በተናገሩት ቋንቋና በሰበሰቡት ዕውቀት ተመክተው ከሌሎች በላይ የሆኑ ይመስላቸዋል። ሆኖም እውነተኛው የመንፈሳዊ ሕይወት ሚዛን የአእምሮ መሙላት ሳይሆን የልብ መሰበርና መታዘዝ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ «እውቀት ያስታብያል ፍቅር ግን ያንጻል» (1ኛ ቆሮንቶስ 8፡1) በማለት እንዳስተማረን፣ ከፍቅርና ከትሕትና የተለየ እውቀት ሰውን ከመገንባት ይልቅ በትዕቢት እንዲወጠር ያደርገዋል።
በእግዚአብሔር ፊት ተቀባይነትን የሚያስገኘው የጥበብ ብዛት ወይም የንግግር ችሎታ አይደለም። ይልቁንም የሰው ልጅ ድካሙን አውቆ በፈጣሪው ፊት ራሱን ዝቅ ማድረጉ ነው። ነቢዩ ኤርምያስም «ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፣ ኃያልም በኃይሉ አይመካ... ነገር ግን የሚመካው በዚህ ይመካ፤ እኔ እግዚአብሔር መሆኔን በማወቁና በማስተዋሉ ይመካ» (ኤርምያስ 9፡23-24) በማለት የሰው ልጅ መመኪያው ራሱ ሳይሆን ፈጣሪው ብቻ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥቶ ተናግሯል እውቀታችን የሌሎችን ድክመት መለኪያና መናቂያ ሆኖ ከተገኘ፣ ያ እውቀት ከብርሃንነት ይልቅ ወደ ጨለማነት ተለውጧል ማለት ነው።
መዳን የሚገኘው በምሁራዊ ክርክር ወይም በቃላት ጋጋታ ሳይሆን በንጹሕ ልብ፣ በእምነትና በበጎ ምግባር ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ይህንን እውነት ሲያጸና «አባት ሆይ፣ የሰማይና የምድር ጌታ፣ ይህን ከጥበበኞችና ከአስተዋዮች ሰውረህ ለሕፃናት ስለ ገለጥህላቸው አመሰግንሃለሁ» (ማቴዎስ 11፡25) ብሏል። እዚህ ላይ ሕፃናት የተባሉት በዕውቀታቸው የማይመኩ፣ ልባቸው የዋህና ቅን የሆኑ ሰዎች ናቸው ስለዚህ እውቀት የመግባቢያና የማገልገያ መሣሪያ እንጂ የድኅነት መስፈርት እንዳልሆነ ተረድተን፣ በዕውቀታችን ሌሎችን ከመናቅ ይልቅ በፍቅር ልናገለግልና በትሕትና ልንመላለስ ይገባል።

✍✍✍✍ta...
🤲ራስን ሳያዩ ሌላውን መክሰስ…✍
በሕይወት ውስጥ አንዳንድ ጊዜ እውነት እና እይታ ይጋጫሉ ራሱን ሁልጊዜ እንደ ተበዳይ እና ንጹሕ፣ ሌላውን ደግሞ እንደ በዳይ እና ጥፋተኛ አድርጎ የሚያይ ሰው በራሱ ዓይን ውስጥ ያለውን ግንድ ሳያይ በሌላው ዓይን ውስጥ ያለውን ጉድፍ ለማውጣት የሚጥር ነው። የገዛ ድርጊቱ ሌሎችን እየጎዳና እያቆሰለ ሳለ፣ የራሱን ስህተት ላለማየት እውነቱን ይገለብጣል።
መጽሐፍ ቅዱስ ይህንን ሲያስረዳ
📖 «አንተ ግብዝ፥ አስቀድመህ ከዓይንህ ምሰሶውን አውጣ፥ ከዚያም በኋላ ከወንድምህ ዓይን ጉድፉን ታወጣ ዘንድ አጥርተህ ታያለህ» ማቴዎስ 7፡5 ይላል።
የገዛ ጥፋትን አለመቀበል ራስን ከማታለል ውጪ ሌላ ትርፍ የለውም ቃሉም «በደል የለብንም ብንል ራሳችንን እናስታለን፥ እውነትም በእኛ ውስጥ የለም» 1ኛ ዮሐንስ 1፡8 በማለት ያስጠነቅቃል።
«የሰው መንገድ ሁሉ በዓይኑ ፊት ቅን ትመስለዋለች፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመዝናል» ምሳሌ 21፡2። እኛ ራሳችንን ብናጸድቅም እውነተኛውን ሚዛን የሚያውቀው ፈጣሪ ነው ሌላውን ከመወንጀል ይልቅ፣ በራሳችን ድርጊት የተጎዱትን ማሰብና ልባችንን በእውነት ብርሃን መመርመር የእውነተኛ ብስለት መገለጫ ነው።

✍✍ta...
❤3
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 27



1. እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
2. ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
3. ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም፤ ሰልፍም ቢነሣብኝ በዚህ እተማመናለሁ።
4. እግዚአብሔርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርስዋንም እሻለሁ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ፥ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውንም አይ ዘንድ፥ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ።
5. በመከራዬ ቀን በድንኳኑ ሰውሮኛልና፥ በድንኳኑም መሸሸጊያ ሸሽጎኛልና፥ በዓለት ላይ ከፍ ከፍ አድርጎኛልና።
6. እነሆ፥ አሁን በዙሪያ ባሉ በጠላቶቼ ላይ ራሴን ከፍ ከፍ አደረገ፤ በድንኳኑም የእልልታ መሥዋዕትን ሠዋሁ፥ ለእግዚአብሔር እቀኛለሁ እዘምርለትማለሁ።
7. አቤቱ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን ቃሌን ስማኝ። ማረኝና አድምጠኝ።
8. አንተ ፊቴን እሹት ባልህ ጊዜ። አቤቱ፥ ፊትህን እሻለሁ ልቤ አንተን አለ።
9. ፊትህን ከእኔ አትሰውር፥ ተቈጥተህ ከባሪያህ ፈቀቅ አትበል፤ ረዳት ሁነኝ፥ አትጣለኝም፥ የመድኃኒቴም አምላክ ሆይ፥ አትተውኝ።
10. አባቴና እናቴ ትተውኛልና፥ እግዚአብሔር ግን ተቀበለኝ።
11. አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ ስለ ጠላቶቼም በቀና መንገድ ምራኝ።
12. የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፈቃድ አትስጠኝ።
13. የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።
14. እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።
🤔1
Forwarded from ማዕዶት
''ልቤ ሆይ ለምን ትጨነቃለህ እግዚኣብሄር የማያውቀው ስቃይህ የማይሰማው ጩሀትህ እና የማያየው እንባህ የለም።

"ሰዎች ሊረዱህ ባይችሉም እግዚኣብሄር የልብህን ምስጢር ያውቃል። ሁሉም መንገዶች ተዘግተው ሲታዩህ፣ በፀሎት ወደ እርሱ ቅረብ።"

"ምክንያቱም ተስፋህ በሰዎች እጅ ብቻ ሳይሆን በእግዚኣብሄር ፍቅር ውስጥ አለ ።''

አቡነ ሽኖዳ ሳልሳዊ🧡
🥰2
......✍


በስሜት መነዳት በሰው ልጅ ሕይወት ውስጥ ከፍተኛ የሆነ መንፈሳዊ፣ ስነ-ልቦናዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ የሚያስከትል አደገኛ ባሕርይ ነው ስሜት በባሕርይው ተለዋዋጭና ጊዜያዊ በመሆኑ፣ በእርሱ ብቻ ተመርተን የምንወስናቸው ውሳኔዎች አብዛኛውን ጊዜ ወደ ጸጸትና ጥፋት ይመሩናል በቁጣ፣ በፍርሃት፣ በቅናት ወይም በሥጋዊ ፍላጎት ተገፋፍቶ የሚወሰድ እርምጃ ማስተዋልን ይጋርዳል። በዚህም ምክንያት ከቤተሰብ፣ ከጓደኞችና ከማኅበረሰቡ ጋር ያለንን መልካም ግንኙነት ያበላሻል፤ እንዲሁም ለዓመታት የገነባነውን መልካም ስምና ሕይወት በቅጽበት ያፈርሳል።
መጽሐፍ ቅዱስም በስሜት መነዳትን አጥብቆ የሚቃወም ሲሆን፣ ራስን መግዛትና በማስተዋል መመላለስ የጥበበኛ ሰው መገለጫ እንደሆነ ያስተምራል ለምሳሌ በመጽሐፈ ምሳሌ 25፡28 ላይ «መንፈሱን የማይገዛ ሰው እንደ ፈረሰና ቅጥር እንደሌለው ከተማ ነው» ይላል ቅጥር የሌለው ከተማ ለጠላት ጥቃት የተጋለጠ እንደሆነ ሁሉ፣ ስሜቱን መቆጣጠር የማይችል ሰውም በቀላሉ ለፈተናና ለጥፋት ይጋለጣል። በተጨማሪም በመጽሐፈ ምሳሌ 14፡17 ላይ «ቶሎ የሚቈጣ ሰው ስንፍናን ያደርጋል» በማለት ቁጣና ችኩል ስሜት ወደ ሞኝነት ተግባር እንደሚመራ ይገልጻል።
ስለሆነም በስሜት ከመነዳት ይልቅ፣ በእግዚአብሔር ቃልና በማስተዋል መመራት ከብዙ ጥፋት ይጠብቀናል ሐዋርያው ጳውሎስ በገላትያ 5፡16 ላይ «በመንፈስ ተመላለሱ፥ የሥጋንም ምኞት ከቶ አትፈጽሙ» እንዳለው፣ ስሜታችንን ለእግዚአብሔር መንፈስ በማስገዛት ሰላማዊና የተረጋጋ ሕይወት መምራት ይገባናል።
በዓለ ደብረ ቁስቋም

'ቁስቋም' የቦታ ስም ነው። ይኸውም እመቤታችን ከብዙ የስደት ውጣ ውረድ በኋላ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ከካይሮ በስተደቡብ ፫፻፳ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በላዕላይ ግብጽ በምትገኘው በደብረ ቍስቋም በመንገድ ጕዞ ካገኛቸው ድካም ፮ ወር ከ፲ ቀናት ሰንብተው ያረፉበት ተራራ ነው፡፡

ኅዳር ስድስት ቀን እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ልጇን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን አዝላ ከአረጋዊ ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ሦስት ዓመት ከመንፈቅ በስደት ከኖሩ በኋላ ቅዱስ ገብርኤል ለዮሴፍ:-
❝ሕፃኑን የሚሹት ሄሮድስና ሠራዊቱ ሞተዋልና እናቱንና ሕፃኑን ይዘህ ወደ ሀገርህ ተመለስ!❞

— ማቴ ፳፯ ባለው ጊዜ አረጋዊ ዮሴፍ እናትና ልጁን ይዞ ስሎሜን አስከትሎ ክስደት ወደ ኢየሩሳሌም ሲመለሱ ከደብረ ቁስቋም ገብተው በመንገድ ጉዞ ካገኛቸው ድካም ያረፉበት ተራራማ ቦታ ነው::

ይህቺንም የተቀደስች ቦታን ጌታችን ባርኳት ወደ ናዝሬት ተመልሰዋል። ከብዙ ዘመን በኋላ በኅዳር ስድስት ቀን:-
❝አስተጋብኦሙ እግዚእነ ለሐዋርያቲሁ ቅዱሳን ውስተ ዝንቱ ደብረ ቊስቋም ወቀደሰ ታቦተ ወቤተ ክርስቲያን ወሠርዐ ቍርባነ ወመጠዎሙ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ — በዚህ በደብረ ቊስቋም ጌታችን ቅዱሳን ሐዋርያቱን ሰበሰባቸው ታቦትንና ቤተ ክርስቲያንንም አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን አቀበሏቸዋል❞

— በማለት መዝገበ ታሪክ ይተርካል፡፡

ሰማይ ዙፋኑ ምድርም የእግሩ መረገጫ የሆነ፤ እዚህ ቦታ ይገኛል እዚህ ቦታ አይገኝም የማይባል፥ በቦታ፣ በሁኔታና በጊዜ የማይገታ ምሉዕ በኵለሄ የሆነ አምላክ በዚህ ተራራ ማደሩን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው እንዲህ ሲል ያደንቃል:-
❝ምንተ እነግር ወምንተ እዜኑ በእንተ ዝንቱ ደብር ምሥጢር እስመ ኀደረ ልዑል ውስተ ደብረ ቍስቋም ምስለ ማርያም ድንግል — ስለዚህ ተራራ ምሥጢር ምን እናገራለሁ? ምንስ አወራለሁ? ልዑል በቍስቋም ተራራ ውስጥ ከድንግል ማርያም ጋር አድሯልና❞
— በማለት ከማድነቅ በቀር እንዲህ ነው ብሎ መናገር እንደማይቻል መስክሯል፡፡ ኢሳ. ፷፮፥፩ ፤ መዝ. ፵፱፥፲፪

ዳግመኛም በመንበረ ጸባዖት በልዑል ዙፋኑ ተቀምጦ የሚመሰገን አምላክ በዚህ ተራራ አድሮ መመስገኑ የእግዚአብሔር ትሕትናውን፣ የተራራው ክብሩን ሊቁ እንዲህ ሲል ያደንቃል:-
❝መንክር ወመድምም ዘተገበረ በደብረ ቊስቋም መንክር ዘይሴባሕ በአርያም አምላክ ፍጹም ኀደረ ውስቴቱ መድኀኔ ዓለም ዘሀሎ እምቅድም ኀደረ ውስቴቱ ለዝንቱ ደብር ዘአብ ቃል ምስለ እሙ ድንግል ደመና ቀሊል — በቊስቋም ተራራ የተደረገው ነገር ዕፁብ ድንቅ ነው። በአርያም የሚመሰገን አምላክ ድንቅ ነው፤ ቅድመ ዓለም የነበረ የዓለም መድኀኒት በውስጡ ፍጹም አድሯልና፤ የአብ ቃል ፈጣን ደመና ከሆነችው ከድንግል እናቱ ጋር በዚህ ተራራ ውስጥ አደረ❞

— በማለት ክርስቶስ የረገጠውን አፈርና ምድር ማክበራችንና መሳለማችን ለፈጣሪያችን ለክርስቶስ ያለንን ክብር ያስረዳል::

ዛሬ ዛሬ ሰዎች ተራራን መውጣትና ገዳማትንና አድባራትን መሳለም እንደ ነውር ቆጥረው ይተቻሉ፤ ላያውቁት እንጂ እግዚአብሔር በጸጋ የሚያድርባቸውንና በረድኤት የሚገለጥባቸውን ቦታዎች አክብሮ የበረከት ምንጭ አድርጓቸዋል። በዚሁ መሠረት በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ያሉ አማኞች አምልኮት ለመፈጸም፣ ምስክርነት ለመስጠት፣ ለክብሩ ለመዘመር፣ ቀድሞ ለተደረገላቸውም ሆነ ወደ ፊት ለሚደረግላቸው የእግዚአብሔር ቸርነት ፈጣሪያቸውን ለማመስገንና ለመማጸን እግዚአብሔር ወደ አከበራቸው ተራሮች ይወጡ እንደነበር መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል። ዘጸ ፫፥፩ ፤ ሚክ ፬፥፪ ፤ ማቴ ፲፯፦፩ ፤ ሐዋ ፫፥፩  ስለዚህ የቁስቋም ተራራ እግዚአብሔር በጸጋ ብቻ ሳይሆን በአካል ስላረፈባት እርሱ ባለበት ሁሉ ደግሞ መላእክት ለምስጋና አይለዩምና ተመስግኖባታል። በዚሁ አንጻር ይህቺ ተራራ ዛሬም ድረስ በእናቱ በቅድስት ድንግል ማርያም አማካኝነት እየተመስገነባት ይገኛል::

ዳግመኛም ለመላእክት የማይደክም ብርታትን የሰጠ ድካም የማይስማማው እግዚአብሔር እንደ ደካማ ፍጡር ማረፊያ መፈለጉን ቅዱስ ያሬድ እንዲህ ሲል ያደንቃል:-
❝መንግሥቱ ሰፋኒት ዘእምቅድመ ዓለም ወልደ ቅድስት ማርያም ኀሠሠ ምዕራፈ ከመ ድኩም ንጉሥ ዘለዓለም ግሩም እምግሩማን ብርሃነ ሕይወት ዘኢይጸልም ኀደረ ደብረ ቁስቋም ኀይል ወጽንዕ ዘእምአርያም — የቅድስት ድንግል ማርያም ልጅ ዓለም ሳይፈጠር ዘመን ሳይቆጠር የነበረች ጌትነቱ ምልዕት ስፍሕት ናት (ቅድመ ዓለም የነበረች ፍጽምት የምትሆን ልጅነቱ የባሕርዩ ናት) የማይጨልም የሕይወት ብርሃን፣ ከግሩማን በላይ ግሩም፤ ዘለዓለማዊ ንጉሥ ሲሆን እንደ ድኩም ማረፈያን ፈለገ ከአርያም የሆነ ኀይል ጽንዕ ያለው እርሱ በቁስቋም ተራራ አደረ❞
— በማለት የማይደክም ሁሉን ቻይ አምላክ ድካም የሚስማማውን ሥጋ እንደለበሰ ለማጠየቅ ማረፊያ መፈለጉን መስክሯል፡፡

ደብረ ቁስቋምን የእስክንድርያ ቤተክርስቲያን ሊቃውንት 'በግብጽ የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን' ይሏታል። የግብጽ ኦርቶዶክስ ምእመናን በእጅጉ የሚወድዷት ገዳም ስትሆን በዚህችም ገዳም በርካቶች መነኮሳት ይገኙበታል። ከቦታዋ ክብር የተነሣ 'ዳግሚት ቤተልሔም'ም ይሏታል። በገዳሙም ታላቅ ቤተ-መጻሕፍት አለ። በጌታ በተባረከችው ይህቺ ቦታ ላይ በ፫ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ቅዱስ ጳኩሚስ ገዳም የገደመ ሲሆን የእስክንድርያ ፳፫ኛ ፓትርያርክ ቴዎፍሎስ በታናሿ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ምትክ ታላቅ ካቴድራል ለመሥራት ባሰበ ጊዜ እመቤታችን ተገልጻለት የልጇ የክርስቶስ ትሕትናው በገዳሙ እንዲታሰብበት ባለበት ሁኔታ እንዲሆን/እንዲተወዉ ነግራዋለች::

ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድም ጌታችን ከስደት ለተመለሰባት ከድካመ ሥጋ ላረፈባት ለደብረ ቁስቋም በዝማሬ እንዲህ ሲል ተቀኝቶላታል:-
❝ብጽዐን ለኪ ኦ ደብረ ቍስቋም፤ እምኵሎን አድያም እምናዝሬት እስከ ቤተልሔም፤ ዘተጸወነ ላዕሌኪ መድጎኔ ኵሉ ዓለም — ከናዝሬት እስከ ቤተልሔም ካሉ አውራጆች ሁሉ የዓለም ሁሉ መድኅኒት ወደ አንቺ የተጠጋ የቍስቋም ተራራ ሆይ ክብር ይገባሻል❞

— ሲል የዓለምን ፈጣሪ ያስተናገደች ደብረ ቁስቋም ክብር እንደሚገባት ተናግሯል፡፡

ዳግመኛም:-
❝በቃለ ውዳሴ ጥዑም ይደሉ ሰላም፤ ለዕበይኪ ፍጹም አድባረ ቍስቋም፤ ማኅደረ ልዑል ዘአርያም፤ በአርያም ያለ የልዑል ማደሪያው የሆንሽ የቊስቋም ተራራ ሆይ ፍጹም ለሚሆን ክብርሽ በሚጣፍጥ የምስጋና ቃል ሰላምታ ማቅረብ ይገባል❞
— ሲል አወድሷል።


እንኳን ለበዓለ ደብረ ቁስቋም (ለወርኃ ጽጌ ፍጻሜ) አደረሳችሁ/አደረሰን። ቢሰጥ ቢሰጥ አንዳች የማይጎድልበት ቸሩ መድኃኔዓለም አባታችን ከእናቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ከስደቷ ረድኤት በረከት ይክፈለን።
❤3🥰1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 28


1. አቤቱ፥ ወደ አንተ እጠራለሁ፤ ዝም ብትለኝ ወደ ጓድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል፥ አንተ አምላኬ፥ ዝም አትበለኝ።
2. ወደ መቅደስህ ማደሪያ እጄን ባነሣሁ ጊዜ፥ ወደ አንተ የጮኽሁትን የልመናዬን ቃል ስማ።
3. ከኃጥኣንና ከክፉ አድራጊዎች ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፤ ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላም ከሚናገሩት ጋር አትጣለኝ።
4. እንደ ሥራቸው እንደ አካሄዳቸውም ክፉት ስጣቸው፤ እንደ እጃቸውም ሥራ ስጣቸው፤ ፍዳቸውን ወደ ራሳቸው መልስ።
5. ወደ እግዚአብሔር ሥራ ወደ እጆቹም አደራረግ አላሰቡምና ያፈርሳቸዋል እንጂ አይሠራቸውም።
6. የልመናዬን ቃል ሰምቶኛልና እግዚአብሔር ይመስገን።
7. እግዚአብሔር ኃይሌና ጋሻዬ ነው፤ ልቤ በእርሱ ታመነ እኔም ተረዳሁ፤ ሥጋዬም ደስ ይለዋል፥ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ።
8. እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይላቸው ነው፥ ለቀባውም የመድኃኒቱ መታመኛ ነው።
9. ሕዝብህን አድን፥ ርስትህንም ባርክ፤ ጠብቃቸው፥ ለዘላለሙም ከፍ ከፍ አድርጋቸው።
እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ ትባላለች። ይህም፡-

"#ንጽሕት" ስንል፡-
ሌሎች ሰዎች (ቅዱሳን) ቢነጹ ከገቢር፣ ከነቢብ ኃጢአት ነው እንጂ ከኃልዮ ኃጢአት አይደለም፡፡ እርሷ ግን ከነቢብ፣ ከገቢር፣ ከኃልዮ ንጽሕት ናት፡፡ "ለመኑ ተውኅቦ ተደንግሎ ኅሊና ለመላእክትሂ ኢተክህሎሙ" ኃጢአትን ከማሰብ መጠበቅ ከሰው ልጆች ለማን ተሰጠው ይህስ ለመላእክትም አልተቻላቸውም" እንዲል፡፡ (ተአምረ ማርያም)

"#ጽንዕት" ስንል:-
ሴቶች ቢጸኑ ለጊዜው ነው እንጂ በኋላ በጊዜው ተፈትሆ አለባቸው:: እመቤታችን ግን ቅድመ ጸኒስ ጊዜ ጸኒስ ድኅረ ጸኒስ ቅድመ ወሊድ ጊዜ ወሊድ ድኅረ ወሊድ ድንግል ናትና:: "ጽንዕት በድንግልና አልባቲ ሙስና" እንዳላት ቅዱስ ያሬድ "ወትረ ድንግል ማርያም" ማርያም ዘለዓለማዊት ድንግል ናት" እንዳለ፡፡ (መጽሐፈ ቅዳሴ)

"#ክብርት" ስንል፡-
ሌሎች ሴቶች ቢከብሩ ጻድቃን ሰማዕታትን ነቢያት ሐዋርያትን ወልደው ነው እመቤታችንን ግን የምናከብራት "የአምላክ እናቱ" ብለን ነውና፡፡

"#ልዩ" ስንል፡-
ከእርሷ በቀር እናት ሆና ድንግል እመቤት ሆና አገልጋይ የሆነች በድንግልና ወልዳ ወተትን (ሐሊበ ድንግልናዌን) ያስገኘች ሌላ ሴት የለችምና፡፡

በዚህም እመቤታችንን ንጽሕት፣ ጽንዕት፣ ክብርት፣ ልዩ እንላታለን፡፡