አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።
ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?
እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል።
ከዲ/ን አቤል ካሳሁን
ሰናይ ምሽት ❤️❤️❤️

❤1
"በምድር ላይ ያለ ፍትሕ በግፍ የሚፈሰው የንጹሐን ደም መሬት ላይ ወድቆ የሚቀር አይደለም፤ ወደ ሰማይ አብሮ ይወጣል፣ ወደ ፈጣሪም ፊት ይጮኻል። ሰብአዊ ፍርድ ቢዘገይ ወይም ቢጓደል፣ መለኮታዊው ፍርድ ግን ፍጹም ነውና መቼም ቢሆን አይቀርም። በግፍ የተገደሉትን ሰዎች መከራና እንባ እግዚአብሔር በአይኑ ይመለከተዋል፤ ክፉዎችንም በሰዓቱ ይቀጣቸዋል።"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን🙏
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን🙏
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 19
1. ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
2. ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
3. ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።
4. ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
5. በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል።
6. አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙረቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
7. የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
8. የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
9. የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
10. ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
11. ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
12. ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
13. የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
14. አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።
Forwarded from ቤቴል 💒
ተወዳጆች እንዴት አደራችሁ 😍
የአለም የትልቅነት መገለጫ ምንድን ነው ካልን መናቅ ነው
፠ስልጣን ያለዉ ስልጣን የሌለውን ይንቀዋል
፠ሀብት ያለው ደሀውን ይንቀዋል
፠የተማረው ያልተማረው ይንቀዋል
የአለም የትልቅነት መገለጫ ይሄው ነው ።
በፍቅር ተባብረን ተዋደን እንኖር ዘንድ
እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን🙏
መልካም ቀን ❤️❤️❤️
የአለም የትልቅነት መገለጫ ምንድን ነው ካልን መናቅ ነው
፠ስልጣን ያለዉ ስልጣን የሌለውን ይንቀዋል
፠ሀብት ያለው ደሀውን ይንቀዋል
፠የተማረው ያልተማረው ይንቀዋል
የአለም የትልቅነት መገለጫ ይሄው ነው ።
እግዚአብሔር ግን
ኃያል ነው ማንንም አይንቅም ። መጽ.ኢዮብ ፴፮ ፥ ፭
በፍቅር ተባብረን ተዋደን እንኖር ዘንድ
እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን🙏
መልካም ቀን ❤️❤️❤️
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ
ሰናይ ውሎ ❤️❤️
3. ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
4. ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።
5. ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
6. አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤ ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ።
7. በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
8. እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፤ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።
መዝሙረ ዳዊት 41:3-8
ሰናይ ውሎ ❤️❤️
❤1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 20
1. በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።
2. ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።
3. ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ።
4. እንደ ልብህ ይስጥህ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።
5. በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።
6. እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፤ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፤ በቀኙ ብርታት ማዳን።
7. እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
8. እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
9. አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥ በጠራንህም ቀን ስማን።
👏2
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ
መልካም ዕለተ ሰንበት ❤️❤️❤️
16. ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
17. ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
19. መንፈስን አታጥፉ፤
20. ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤
22. ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።
23. የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:16-23
መልካም ዕለተ ሰንበት ❤️❤️❤️
👏2❤1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 21
ደህና እደሩ❤️
1. አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
2. የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
3. በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤ ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።
4. ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥ ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ።
5. በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
6. የዘላለም በረከትን ሰጥተኸዋልና። በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
7. ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥ በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
8. እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
9. በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ እግዚአብሔር በቍጣው ያጠፋቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።
10. ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
11. ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።
12. ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤ ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለህ።
13. አቤቱ፥ በኃይልህ ከፍ ከፍ በል፤ ጽናትህንም እናመሰግናለን እንዘምርማለን።
ደህና እደሩ❤️
👏2
"ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። "
ማቴ. 5÷43-47
የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። "
ማቴ. 5÷43-47
🔥3
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ
ሰናይ ቀን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️
4. እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
5. ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም።
6. ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7. የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
8. እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
9. የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።
10. ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉትን ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።
11. ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12. ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?
13. አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
14. ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።
15. የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
16. መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው።
መዝሙረ ዳዊት 33:4-16
ሰናይ ቀን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️
ወዳጄ
ሁለት ሃሳቦችን ተረድተህ ፍራቸው፡፡
አንዱ "አንተ ቅዱስ ነህ" ሲል ሌላው " አትድንም " ይላል።
እነዚህ ሁለቱም ሀሳቦች ከጠላት ናቸው,
እና በእነሱ ውስጥ እውነት የለም.
ነገር ግን በዚህ መንገድ አስቡ፡
እኔ ታላቅ ኃጢአተኛ ነኝ፡ ጌታ ግን መሐሪ ነው፡፡
እሱ ሰዎችን በጣም ይወዳል፣ እናም ኃጢአቴን ይቅር ይለኛል፡፡
ቅዱስ ሰሎዋን አቶናዊው
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን ❤️❤️❤️
ሁለት ሃሳቦችን ተረድተህ ፍራቸው፡፡
አንዱ "አንተ ቅዱስ ነህ" ሲል ሌላው " አትድንም " ይላል።
እነዚህ ሁለቱም ሀሳቦች ከጠላት ናቸው,
እና በእነሱ ውስጥ እውነት የለም.
ነገር ግን በዚህ መንገድ አስቡ፡
እኔ ታላቅ ኃጢአተኛ ነኝ፡ ጌታ ግን መሐሪ ነው፡፡
እሱ ሰዎችን በጣም ይወዳል፣ እናም ኃጢአቴን ይቅር ይለኛል፡፡
ቅዱስ ሰሎዋን አቶናዊው
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን ❤️❤️❤️
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 23
ደና እደሩ❤️🙏
1. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2. በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3. ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4. በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5. በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6. ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።
ደና እደሩ❤️🙏
❤1
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ
ሰናይ ቀን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️❤️
15. ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
16. እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
17. በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።
18. ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
19. እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
20. ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?
1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:15-20
ሰናይ ቀን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️❤️
💠አባ ዳዊት አንድ ጊዜ አርሳንዮስ የነገራቸውን ታሪክ እንዲህ ያወጉናል “እርግጥ አባ አርሳንዮስ ይህንን ታሪክ የተናገረው ሌላ ሰው አደረገው ብሎ ነው፡፡ በርግጥ ግን የታሪኩ ባለቤት እርሱ ራሱ ነው፡፡
⚜አንድ አረጋዊ መነኩሴ ከበኣቱ ወጥቶ ሳለ ‹የሰው ልጆችን ሥራ አሳይህ ዘንድ ና› የሚል ድምፅ ሰማ፡፡ እርሱም ከበኣቱ ወጥቶ የጠራውን ድምፅ ተከትሎ ተጓዘ፡፡ ያ ድምፅ ወደ አንድ ቦታ አደረሰውና አንድ .ኢትዮጵያዊ እንጨት እየፈለጠ ሲከምር አሳየው፡፡ ያ እንጨት የሚፈልጥ .ኢትዮጵያዊ ሊሸከመው ሞከረና አቃተው፤ ይሁን እንጂ በመቀነስ ፋንታ አሁንም እየቆረጠ መከመር ቀጠለ፡፡
⚜ጥቂት አለፍ ብሎ ደግሞ አንድ ሰው በሐይቅ አጠገብ ቆሞ በተሠበረ ማሰሮ ውኃ ሲቀዳ ተመለከተ፡፡ ማሰሮው የተሰበረ በመሆኑ ውኃው እንደገና ወደ ሐይቁ ይመለስ ነበር፡፡
⚜ ያ ድምፅ በድጋሚ ‹ና ሌላ ነገር ደግሞ አሳይሃለሁ› ብሎ ወሰደው፡፡
⚜በአንድ ሥፍራ ላይ መቅደስ አሳየው፡፡ ሁለት ሰዎች በፈረስ ጐን ለጐን ሆነው መጡ፡፡ በትከሻቸውም በትራቸውን ጫፍና ጫፍ ላይ አጋድመው ይዘውት ነበር፡፡ በበሩ ወደ ውስጥ ሊያልፉ ቢፈልጉም በትራቸውን አግድም ስለያዙት ያግዳቸው ነበር፡፡ አንዳቸውም ከሌላኛው ኋላ በመሆን በትሩን ፊትና ኋላ አድርገው ሊገቡ አልፈለጉም፡፡ስለዚህም በፉክክር ከውጭ ቀሩ፡፡
⚜ያ ድምፅ ለዚያ አረጋዊ አባት
እንዲህ አለው፡፡ ‹እነዚህ ሰዎች የጽድቅን ቀንበር በትዕቢት ተሸክመውታል፣ ራሳቸውን ዝቅ ዝቅ አላደረጉም፤ ራሳቸውን ለማረምና በክርስቶስ የትኅትና ጉዞ ለመጓዝ አልፈለጉም፣ ስለዚህም ከመንግሥተ ሰማያት በአፍኣ (በውጭ) ይቀራሉ፡፡
🌴እንጨት የሚቆርጠው ሰውም በኃጢአት ላይ ኃጢአት የሚጨምርን ሰው ይመስላል፡፡ ንስሐ ከመግባት ይልቅ ሌሎች ኃጢኣቶችን እንደገና ይጨምራል፡፡
💧 ውኃ የሚቀዳውም ሰው መልካም ሥራን የሚሠራ ሰውን ይመስላል፣ ነገር ግን መልካም ሥራው ከክፉ ሥራው ጋር የተቀላቀለ በመሆኑ ጥቂቱ መልካሙ ሥራው ይበላሽበታል ።
💥 ስለሆነም እያንዳንዱ ለሚሠራው ነገር ሊጠነቀቅና በከንቱ እንዳይደክም ሊያስብበት ይገባል› አለው፡፡ ”
⚜ከቅዱሱ አባታችን አባ አርሳንዮስ ረድኤት በረከት ይክፈለን!

#አንተ_አንቺ_ማለት ...
ፀሀይዋን ተመልከታት አታምርም ? ጨረቃዋስ ከዋክብቱስ ዛፎቹ ወንዙና ተራራውስ አያምሩም ? ያምራሉ እኚ ሁሉ ግን ያልፉሉ አንተ ግን በሞት ከዚህ አለም ብትለይ እንኳን በሰማይ ለዘላለም ትኖራለህ ፈጣሪ ፍጥረታትንን ሁሉ በቃሉ በመናገር እና በሀሳብ (በሀልዮ) ሲፈጥር አንተን ግን በእጁ አሽሞንሙኖ ፈጥሮሀል አንተ ማለት ክርስቶስ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለው ማንም ሚከፍትልኝ ቢኖር ገብቼ እራቴን ከእርሱ ጋር እበላለው ብሎ የተናገረልህ ነህ ፈጣሪ አለምን ከፈጠረበት ጥበብ ይልቅ አለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል ተብሎ የተነገረልህ ዋጋ የከፈለልህ የመንግስቱ ወራሽ ውድ ልጁ ነህ ምን አልባት ዛሬ በተለያየ ሱስ ተይዘህ ይሆናል ምን አልባት ስራ በማጣት ፍቅረኛ በማጣት ትሰቃይ ይሆናል ምን አልባት ቤተሰብህ ወገንህ ተስፉ ቆርጦብህ ይሆናል ምን አልባት ሞትህን እየተመኘህ ይሆናል ግን አይዞህ ፈጣሪ በአንተ የጀመረውን ስራ ሳይጨርስ አትሞትም
ሰው ተስፉ ቢቆርጥብህ እራስህም ተስፉ ብትቆርጥ የፈጠረህ በአንተ ላይ ተስፉ አይቆርጥብህምና አይዞህ 1 ጠጠር አንስተህ ተራራ ላይ ብትወረውር ተራራው ምንም አይሆንም ጠጠሩ ተንከባሎ እግሩ ስር ይሆናል ያን ጠጠር አንስተህ መስታወት ላይ ብትወረውረው ግን መስታወቱ ይሰባበራል ጠጠሩን በችግር እንመስለውና ችግር ወዳንተ ሲመጣ እንደ መስታወቱ አትሰባበር እንደ ተራራው በቁጥጥር ስር አውለው 1 የተለኮሰ የክብሪት እንጨት ጭድ ላይ ብትጥለው ይቀጣጠላል ውሀ ላይ ብትጥለው ግን ውሀው ያጠፉዋል የሚያቃጥሉ ነገሮች በህይወትህ ውስጥ ሲከሰቱ እንደ ጭድ አትቀጣጠል እንደ ውሃው አጥፉቸው
እህቴ ምን አልባት ለስራ ጉዳይ በተለያየ ሀገር ውስጥ ሆነሽ ይሆናል ያለሽው መፈጠርሽ ሴትነትሽም አስጠልቶሽ ይሆናል። ግን ክርስቶስ ወደ አለም ሲመጣ ምድራዊ እናት እንጂ አባት አላስፈለገውም የሴት ልጅ ተብሎ እስኪጠራ ድረስ ማርያም ብቻዋን ነው ያሳደገችው። በኛ ቤተክርስቲያን ህንፃ ቤተክርስቲያኑ ተሰርቶ አለቀ የሚባለው ጉልላቱ ተሰርቶ ሲያልቅ ነው ። ፈጣሪም ፍጥረትን ሁሉ ፈጥሮ ሲጨርስ አዳምን ፈጠረ በመጨረሻም ከጎኑ ሄዋንን ወይም አንቺን የስነ ፍጥረት ጉልላት አርጎ ፈጠረሽ ስለዚህ እህቴ ክብርት ፍጥረት ነሽና ደስ ይበልሽ

🔥1👏1
ወንድሞቼ "እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡ ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/። ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡
ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡ እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡ እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡

❤1🥰1
መከራዋ በዝቶ በሀዘን ስትማስስ
ልጆቿን እያጣች ዘወትር ስታለቅስ
በደም ላይ ደም ብዝቶ ጎርፍ እየሆነባት
ኢትዮጵያዬ ሀገሬ ክረምቱ አለቅ አላት
ያለፈ ታሪኳን ፍቅሯን የሚያስታውስ
ያላንቺ ማን አለ እንባዋን የሚያብስ
ጌታን በጀርባ አዝለሽ ስትንከራተቺ
በውሀ ጥም ሀሩሩ በድካም ስትዝዬ
እጆቿን ዘርግታ እናቴ ነይ ያለች
ከሙሉ መሶቧ ማዓድ ያቀረበች
ያቺ ቅድስት ሀገር እምነቷን አጉድላ
ባዶዋን ቀርታለች እናቴ አንቺን ጥላ
ድረሺላት ባክሽ በጥላሽ ሸሽጊያት
የያዘችው መንገድ መጥፊያ ነው የሆናት
በዘር በሀይማኖት በክህደት አብዳለች
ልጆቿን በከንቱ ቀን በቀን ታጣለች
በመዓት ቸነፈር ብዙ ነው ስቃይዋ
አዛኝ ልብ ያጣ ነው የሚዘንብ እንባዋ
እናቴ አዛኝቷ ሀገሬን ተመልከች
የማህጸኗ ፍሬ መገኛዬ እሷ ነች
አይ ሀገሬ ኢትዮጵያ ይህም ያልፋል
ልጆቿን እያጣች ዘወትር ስታለቅስ
በደም ላይ ደም ብዝቶ ጎርፍ እየሆነባት
ኢትዮጵያዬ ሀገሬ ክረምቱ አለቅ አላት
ያለፈ ታሪኳን ፍቅሯን የሚያስታውስ
ያላንቺ ማን አለ እንባዋን የሚያብስ
ጌታን በጀርባ አዝለሽ ስትንከራተቺ
በውሀ ጥም ሀሩሩ በድካም ስትዝዬ
እጆቿን ዘርግታ እናቴ ነይ ያለች
ከሙሉ መሶቧ ማዓድ ያቀረበች
ያቺ ቅድስት ሀገር እምነቷን አጉድላ
ባዶዋን ቀርታለች እናቴ አንቺን ጥላ
ድረሺላት ባክሽ በጥላሽ ሸሽጊያት
የያዘችው መንገድ መጥፊያ ነው የሆናት
በዘር በሀይማኖት በክህደት አብዳለች
ልጆቿን በከንቱ ቀን በቀን ታጣለች
በመዓት ቸነፈር ብዙ ነው ስቃይዋ
አዛኝ ልብ ያጣ ነው የሚዘንብ እንባዋ
እናቴ አዛኝቷ ሀገሬን ተመልከች
የማህጸኗ ፍሬ መገኛዬ እሷ ነች
አይ ሀገሬ ኢትዮጵያ ይህም ያልፋል
😢1
Forwarded from ቤቴል 💒
*<<የብልጣ ብልጥ ጸሎት ሦስት ናቸው።*
"በአባ ገብረኪዳን ግርማ "
=============+++++
*☦፩ኛው* ፦ቤተክርስቲያን ሄዶ፦
እግዚአብሔርን ይህቺን አርግልኝ፣አርግልኝ:አርግልኝ ብሎ መመለስና
፠የጠየቀውንም ሰይጣን የሆነ ነገር ያደርገኛል ብሎ የሚፈራ(ፈሪ)ማለት ነው።
፠፠ጸሎቱን ወጪ እያደረገ ከእግዚአብሔርም ጥበቃ እየተቀበለ እንደ ዘበኛ እኖራለሁ ብሎ የሚያስብ ነው።
ምስኪን!
*☦፪ኛው* ፦የሆነ ነገር እንዲያደርግለት ብቻ እግዚአብሔርን የሚጠራ ማለት ነው።
፠ እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በአምላክነቱና በአባትነቱ የማይርበው ሰው ማለት ነው።
ጸሎቱን የሚጸልየው፦
#ወይ የሆነ ነገር እንዳይደርስበት
#አልያም የሆነ የጎደለውን እግዚአብሔር እንዲሞላለት ብቻ ነው።
☦ *፫ኛው* ፦"እስመ በአብዝኆ ንባቦሙ ይመስሎሙ ዘይሰምዖሙ እግዚአብሔር።
ቃላትን በመድርደር ብቻ እግዚአብሔር የሚሰማቸው የሚመስላቸው ሰዎች ናቸው።
*ጸሎቱን ከጸለዩ በኋላ* ፦
እንደዚህ ሆኖ፣
እንደዚህ ሆኖ፣
እንደዚህ ሆኖ
፣እንደዚህ ሆኖ፣እያሉ እግዚአብሔርን ወግ እንደማውጋት የሚያስመስሉ ናቸው።
እግዚአብሔርን እንደ አባት ብናወጋው ችግር የለውም።
ነገር ግን እንትናን እንትን ብዬ፣
እነ እገሌም ጠላቶቼ ናቸው፣
እገሌን እኔ አልደረስኩበትም የደረሰብኝ እራሱ ነው
እያሉ መናገር ማለት ነው።
ይህንን እግዚአብሔር ሳያውቅ ቀርቶ ነው? ይህንንማ እግዚአብሔር ያውቀዋል።
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን በምስጋና የጀመርነውን ቀን በምስጋና እንጨርስ እና ለሊቱን ለባለቤቱ አደራ እንስጥ 🙌🙌❤️❤️❤️

📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 25
1. አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
2. አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ፤ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
3. አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።
4. አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
5. አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
6. አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
7. የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፤ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
8. እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
9. ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
10. የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
11. አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
12. እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል።
13. ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
14. እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
15. እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
16. እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም።
17. የልቤ ችግር ብዙ ነው፤ ከጭንቀቴ አውጣኝ።
18. ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
19. ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
20. ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ፤ አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
21. አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
22. አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
❤1👏1
ወይቤሎሙ ጸሐፍት ወፈሪሳውያን ለምንት ኢየሐውሩ አርዳኢከ በከመሠርዑ ረበናት ወዘእንበለይሐጸቡ እደዊሆሙ ይበልዑ እክለ
ወአወሥአ እግዚእ ኢየሱስ ወይቤሎሙ መደልዋን ሠናየ ተነበየ ኢሳይያስ ላዕሌክሙ እንዘይብል ዝ ሕዝብ በከናፍሪሆሙ ያከብሩኒ ወበልቦመሰ ነዋኅ ይርኅቁ እምኔየ
ጸሐፍት ፈሪሳውያንም ደቀ መዛሙርትህ እንደ ሽማግሌዎች ስርዓት ለምን አይሄዱም አሉት? እጃቸውንም ሳይታጠቡ ለምን ይበላሉ ?
ኢየሱስ ክርስቶስም አላቸው መለሰላቸው እናንተ ግብዞች ኢሳይያስ እኒህ ሕዝብ በከንፈራቸው ያከብሩኛል በልባቸው ግን ፈጽመው ከእኔ ይርቃሉ ብሎ ኢሳይያስ እውነት ተናግሮባቸኋል ።

❤2👏1