☦️ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ☦️
60 subscribers
30 photos
2 videos
1 file
2 links
@fnote abew የአቦቶች መንገድ መከተል
Download Telegram
ከመሮጥ ይልቅ ማስተዋል

​በየዕለቱ ከምንኖረው ፈጣን ሕይወት እና የዕለት ተዕለት ጫና ውስጥ ቆም ብሎ ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ብዙ ጊዜ አእምሯችን ከውጭ በሚመጡ ውጣ ውረዶች እና ጭንቀቶች ይወጥራል፤ ነገር ግን እውነተኛው ጥንካሬ የሚመነጨው ሁልጊዜ ከመሮጥ ሳይሆን፣ ራሳችንን አግልለን ከውስጣችን ጋር ከምንነጋገርበት ጸጥታ ነው።

​ለአብዛኛዎቹ የሕይወት ውጣ ውረዶች መፍትሔ የምናገኘው መጮህ ስንጀምር ሳይሆን፣ መረጋጋት እና ማጤን ስንችል ነው። ከዚህ ዓለም ጫጫታ ትንሽ ፈቀቅ ማለት፣ ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ እና የት እንዳለን ማየት ትልቅ ብስለት ነው።

​አንዳንዴ ዝምታ ከሺህ ቃል በላይ መልስ ይሰጠናል፤ ራስን ማዳመጥ ደግሞ ቀጣዩን እርምጃ በግልጽ ያሳየናል።

​መልካም አዳር ይሁንልን❤️
፠ ክፉ  ልብ 🖤 ያላቸው  ሰዎች  ልክ  በቤት  ውስጥ  የተቀመጠ  እንደ ብልቃጥ  ውስጥ  መርዝ  ናቸው ፤መቼ  ማንን  ባላሰበው  መንገድ  ሊገል  እንደሚችል  አይታወቅም  ክፉ  ልብ  ያላቸውም  እንዲሁ  ከላይ መልካምና  ለስላሳ  አዋቂና  ለሰው  አሳቢ  መስለው  ይታያሉ  ነገር  ግን  እያደር  ቀስ  በቀስ  መርዛቸው  የሆነ  ሰዎን  ሲገል   ይታያል ፤  መልካም  ነገርን  በፍፁም  ማየት  አይችሉም  ሁሌ  ስህተት   ይፈልጋሉ  ሁሌም  ሰውን  በራሳቸው  አይን  ስለሚያዩ   ጥሩ  ነገሮችን  ወደ መጥፎ  ቀይሮ  ለመረዳት  ይፈጥናሉ  በባልንጀራ  መሀል  ጥላቻንና  ክፋትን  ያሳድራሉ ነገር  ግን  ቀና  ልብ  ያላቸው  ሰዎች  በመጥፎ ነገር  ውስጥ  ጥሩ  ነገርን  ያወጣሉ!!!

ቀና  ልብ  ያድለን  ሰላም  እደሩ ❤️❤️
🔥2❤1👏1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 18


1. አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።
2. እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።
3. ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
4. የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤
5. የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
6. በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
7. ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።
8. ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።
9. ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።
10. በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ።
11. መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም ድንኳኑ፤ በደመናት ውስጥ የጨለማ ውኃ ነበረ።
12. በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።
13. እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
14. ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
15. አቤቱ፥ ከዘለፋህ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
16. ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።
17. ከብርቱዎች ጠላቶቼ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።
18. በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ።
19. ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።
20. እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።
21. የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁም።
22. ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።
23. በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።
24. እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።
25. ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤
26. ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።
27. አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።
28. አንተ መብራቴን ታበራለህና፤ እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።
29. በአንተ ከጥፋት እድናለሁና በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።
30. የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።
31. ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?
32. ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥
33. እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።
34. እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።
35. ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።
36. አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
37. ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።
38. አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ።
39. ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።
40. የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።
41. ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ አልሰማቸውም።
42. እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ።
43. ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።
44. በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤ የባዕድ ልጆች ደለሉኝ።
45. የባዕድ ልጆች አረጁ፥ በመንገዳቸውም ተሰናከሉ።
46. እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ አምላኬም ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።
47. በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል።
48. ከጠላቶቼ የሚታደገኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።
49. አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ።
50. የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይሰጣል።
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ


19. ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
20. ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤
21. መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
22. የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤
23. ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!
24. ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

ማቴዎስ ወንጌል 6:19-24


ሰናይ ቀን ❤️❤️❤️
አቤቱ ጌታዬና አምላኬ ሆይ! ከኃጢአቴ ብዛት የተነሣ ፊቴን ወደ አንተ ለማንሳት እጠራጠራለሁ፤ ነገር ግን እንደ ቸርነትህ ማረኝ
በዕለተ ዓርብ ስለ እኔ በፈሰሰው ክቡር ደምህና በተቆረሰው ሥጋህ ኃጢአቴን ደምስስልኝ። የደከመውን መንፈሴን በቅዱስ መስቀልህ ኃይል አድስልኝ አቤቱ ካገሣው አንበሳ (ከሰይጣን) ወጥመድና ከክፉዎች ተንኮል ሰውረኝ
አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ፍጠን፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጎስቁሉ፤ ክፉን የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም።እኔ ግን ችግረኛና ምስኪን ነኝ፤ አቤቱ፥ እርዳኝ፤ ረዳቴና መድኃኒቴ አንተ ነህ፤ አቤቱ፥ አትዘግይ አሜን 🙏
"ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሜተ፤ መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤ መድኃኔ ዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲኣነ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚኣከ ከመ ትቅትል ሞተ።"

(ምስጋናን የለመዱ የሰማይ መላእክት ምድራውያን [የአዳም ልጆች] ቅዱሳን አመስግነው ፍጻሜ ላላገኙለት የስምኽ መታሰቢያ ሰላም እላለኹ። በአንተ ሞት ሞትን ትገድል ዘንድ ስለ እኛ መራራ ከርቤን እና ሐሞትን የጠጣኽ የዓለም መድኀኒት ሆይ ያቀረበኹልኽን ትንሽ ምስጋና ተቀበል።)

#መልክአ_መድኃኔዓለም
👏1
ተዝካረ ጥንተ ስቅለቱ ለመድኃኒነ
❝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ "ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት ወአብ በዲበ ምድር — በሰማይ ያለ እናት ከአብ መወለዱን በምድርም ያለ አባት ከድንግል ማርያም መወለዱን እናምናለን" ይህንንም አባቶቻችን ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል፤ ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት መለወጥ ሳያገኘት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደ፤ 'ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወልደ አብ በትስብእቱ' ብለው አምልተው አስፍተው እንዲያስተምሩን "ከመ አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ውእቱ አምላክ ወሰብእ ኅቡረ" ትርጉሙም እርሱ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው❞

— ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ፴፭፥፳፩

መጋቢት ፳፯ በቃል መናገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው። ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያናት በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሳኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ «ስቅለት» ተብሎ እንዲከበር ሥርዐት ሠርተዋል። መጋቢት ፳፯ ቀን ደግሞ በዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል ያኔ ደግሞ ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ ወደ ጥቅምት ፳፰ ተዛውሮ ደስ ብሎን ጥንተ ስቅለቱን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዐት ሰርታለች።


ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተክርስቲያናችን ጌታችን ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ:-
❝በመስቀሉ ወበቃሉ አእበዮሙ ለአበዊነ — በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው❞

እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።

ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኃ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ:-
❝እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋህድ ዘምስለ ምህረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ❞
እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች።
❝እስመ አንተ ትክል አንጽሖትየ እግዚኦ ወበቃልከ እለ ለምፅ አንጻሕከ ወበጽጌያት ምድር አሠርጎከ ወበመስቀልከ ለጻድቃን አብራህከ — ልታነጻኝ ይቻልሃል አቤቱ ለምጻሞቹን በቃልህ አንጽተሃልና ... ❞
እያሉ አባቶቻችን በመስቀሉ ለጻድቃን ማብራቱን እያሰቡ በዓሉን በመዝሙርና በደስታ ያከብሩታል።
❝ወበከመ ሙሴ ሰቀሎ ለአርዌ ምድር በገዳም ከማሁ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይሰቀል — ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስም ይሰቀል አንድ አለው❞

— ዮሐ ፫፥፲፬ ብሎ እንደተናገረ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው። ክርስቶስ ስለ ስቅለቱ ሲናገር ምሳሌ የሚሆነውን ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለውን የነሐሱን እባብ ❝ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስም ይሰቀል ዘንድ አለው❞ ብሎ ምሳሌውን ተናግሯል።

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከጭንጫ ውኃ አፍልቆ ቢመግባቸው ከዚህ ምድሩ ብቅ፣ ሰማዩ ዝቅ ቢልለት፣ ከደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጂ 'ይክልኑ እግዚአብሔር ሠሪዓ ማዕድ በገዳም'። ቆላ በሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል። ጌታም ሊያስተምራቸው የርሱን ከሃሊነት የእነርሱንም ሐሰት ሊገልጥባቸው  ሙሴን 'ነቅዓ ማይ የሌለበት በረሐ ይዘሃቸው ውረድ' ብሎት ቢሄዱ መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል። ነገር ግን 'ነዘር' የሚባል ክፉ እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር። ከዚህ በኋላ እስራኤል ሙሴ ዘንድ ሄደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከሰው ስሕተት ኃጢአት አይታጣም 'በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል  እባቦችን ከኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን፥ አማልደን' አሉት። ሙሴም ስለሕዝቡ  ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ 'ጽሩዩን ብርት አርዌ አስመስለህ ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው' አለው። ሙሴም እባብን ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ —ኦሪት ዘኁ ፳፩፥፩-፱።
 
ይህንም ምሳሌ አባቶቻችን በትርጓሜ ወንጌል ቅዱስ እንዳስቀመጡልን አርዌ ምድር የዲያብሎስ፤ አርዌ ብርት የጌታ ምሳሌ ነው። በአርዌ ምድር(እባብ) መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት። በአርዌ ብርት ደግሞ መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም።

አርዌ ብርት በአርዌ ምድር አምሳል መሰቀሉ ጌታ በአምሳለ እኩያን እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ዳግመኛም  ❝ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን❞ እንዳለ ነቢዩ ኢሳይያስ ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና — ኢሳ  ፶፫፥፲፪  የሚለውን ትንቢት ፈጽሟል። ምሳሌውን አውቆ በሙሴ አስመስሏል ትንቢቱንም አውቆ በነቢያቱ አናግሯል።
 
ጲላጦስ አይሁድን 'ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ?' ቢላቸው 'በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው' አሉ። ጲላጦስም  'በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ' ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በእኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው — ማቴ ፳፯፥፳፭።
 
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ:-
❝ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢያትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት❞
—  እንዲል ክርስቶስን አይሁድ 'ስቀለው!' ብለው ፈረዱበት።
 
አክሊልን የሚያቀናጀውን የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን 'አነገስንህ' ብለውታልና ጭፍሮች በፍና ተሣልቆ የእሾህ አክሊል ታተው ደፉለት:- 
❝ወጸፈሩ ሐራ አክሊለ ዘሦክ ወአስተቀጸልዎ ዲበ ርእሱ — ወታደሮችም ከሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት❞

— ዮሐ ፲፱፥፪። ኢየሱስ ክርስቶስ  የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ዕፀ በለስን በልቶ 'ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች' ዘፍ  ፫፥፲፰ ብሎ የፈረደበትን አዳም ስለእርሱ ክሶ መርገሙን ደምስሶለታል ።
 
መጋቢት ፳፯ ቀን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ  የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተመቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀድዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯)፡፡
 
❝ኦ አእዳው እለ ለሐኳሁ ለአዳም ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል፤ ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል — አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ! በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ!❞
— እንዲል  ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ስቅለቱን በዲሜጥሮስ ቀመር አውጥተን የጌታን መከራውን አስበን በስግደት ህማማቱን እናስባለን። በዝክረ ጥንተ ስቅለቱ በጥቅምት ፳፯ ደግሞ በመስቀል የተደረገልንን አስበን እናመሰግነዋለን፡፡
 
እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን።


ዲ/ን ኃይለራጉኤል
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ  "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው  ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል።
      
   ከዲ/ን አቤል ካሳሁን


ሰናይ  ምሽት ❤️❤️❤️
❤1
​"በምድር ላይ ያለ ፍትሕ በግፍ የሚፈሰው የንጹሐን ደም መሬት ላይ ወድቆ የሚቀር አይደለም፤ ወደ ሰማይ አብሮ ይወጣል፣ ወደ ፈጣሪም ፊት ይጮኻል። ሰብአዊ ፍርድ ቢዘገይ ወይም ቢጓደል፣ መለኮታዊው ፍርድ ግን ፍጹም ነውና መቼም ቢሆን አይቀርም። በግፍ የተገደሉትን ሰዎች መከራና እንባ እግዚአብሔር በአይኑ ይመለከተዋል፤ ክፉዎችንም በሰዓቱ ይቀጣቸዋል።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሰላም  ዕደሩ  የነገ ሰው ይበለን🙏
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 19


1. ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
2. ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
3. ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።
4. ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
5. በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል።
6. አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙረቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
7. የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
8. የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
9. የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
10. ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
11. ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
12. ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
13. የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
14. አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።
Forwarded from ቤቴል 💒
ተወዳጆች እንዴት አደራችሁ 😍

የአለም የትልቅነት  መገለጫ ምንድን ነው ካልን መናቅ ነው

፠ስልጣን ያለዉ ስልጣን የሌለውን ይንቀዋል
፠ሀብት ያለው  ደሀውን ይንቀዋል
፠የተማረው ያልተማረው ይንቀዋል

የአለም የትልቅነት መገለጫ ይሄው ነው ።

እግዚአብሔር ግን
ኃያል ነው ማንንም አይንቅም ። መጽ.ኢዮብ ፴፮ ፥ ፭


በፍቅር ተባብረን ተዋደን እንኖር ዘንድ

እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን
🙏

መልካም ቀን ❤️❤️❤️
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ

3. ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
4. ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።
5. ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
6. አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤ ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ።
7. በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
8. እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፤ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 41:3-8



ሰናይ ውሎ
❤️❤️
❤1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 20

1. በመከራ ቀን እግዚአብሔር ይስማህ፤ የያዕቆብ አምላክ ስም ያቁምህ።
2. ከመቅደሱ ረድኤትን ይላክልህ፥ ከጽዮንም ያጥናህ።
3. ቍርባንህን ሁሉ ያስብልህ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትህን ያለምልምልህ።
4. እንደ ልብህ ይስጥህ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።
5. በማዳንህ ደስ ይለናል፤ በአምላካችን ስም ከፍ ከፍ እንላለን፤ ልመናህን ሁሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ።
6. እግዚአብሔር የቀባውን እንዳዳነው ዛሬ አወቅሁ፤ ከሰማይ መቅደሱ ይመልስለታል፤ በቀኙ ብርታት ማዳን።
7. እነዚያ በሰረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፤ እኛ ግን በአምላካችን በእግዚአብሔር ስም ከፍ ከፍ እንላለን።
8. እነርሱ ተሰነካክለው ወደቁ፤ እኛ ግን ተነሣን፥ ጸንተንም ቆምን።
9. አቤቱ፥ ንጉሥን አድነው፥ በጠራንህም ቀን ስማን።
👏2
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ
16. ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤
17. ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።
19. መንፈስን አታጥፉ፤
20. ትንቢትን አትናቁ፤ ሁሉን ፈትኑ መልካሙንም ያዙ፤
22. ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር ራቁ።
23. የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።

1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:16-23

መልካም  ዕለተ  ሰንበት ❤️❤️❤️
👏2❤1
Forwarded from ቤቴል 💒
ወደ እኔ ነይና ነፍሴን ነጻ አስወጪያት፤ ጠላቶቼን ከእግሬ በታች ጣያቸው፤ ነፍሴን እንዳያፍኗት የሲዖልን ደጃፍ በላያቸው ላይ ዝጊባቸው፤የእውነተኛው ሙሽራ ፍጹም ሙሽሪት አንቺ ነሽና፡፡›

አባ ታድሮስ
❤4🥰1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 21

1. አቤቱ፥ በኃይልህ ንጉሥ ደስ ይለዋል፤ በማዳንህ እጅግ ሐሤትን ያደርጋል።
2. የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።
3. በበጎ በረከት ደርሰህለታልና፤ ከክቡር ዕንቍ የሆነ ዘውድን በራሱ ላይ አኖርህ።
4. ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥ ለረጅም ዘመን ለዘላለሙ።
5. በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብርንና ምስጋናን ጨመርህለት።
6. የዘላለም በረከትን ሰጥተኸዋልና። በፊትህም ደስታ ደስ ታሰኘዋለህ።
7. ንጉሥ በእግዚአብሔር ተማምኖአልና፥ በልዑልም ምሕረት አይናወጥም።
8. እጅህ ጠላቶችህን ሁሉ ታግኛቸው፥ ቀኝህም የሚጠሉህን ሁሉ ታግኛቸው።
9. በተቈጣህም ጊዜ እንደ እሳት እቶን አድርጋቸው፤ እግዚአብሔር በቍጣው ያጠፋቸዋል፥ እሳትም ትበላቸዋለች።
10. ፍሬአቸውን ከምድር ዘራቸውንም ከሰው ልጆች ታጠፋለህ።
11. ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።
12. ወደ ኋላቸው ትመልሳቸዋለህ፤ ፍላጻን በፊታቸው ላይ ታዘጋጃለህ።
13. አቤቱ፥ በኃይልህ ከፍ ከፍ በል፤ ጽናትህንም እናመሰግናለን እንዘምርማለን።




ደህና እደሩ❤️
👏2
"ባልንጀራህን ውደድ ጠላትህንም ጥላ እንደ ተባለ ሰምታችኋል። እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ዋጋ አላችሁ? ቀራጮችስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? ወንድሞቻችሁንም ብቻ እጅብትነሡ ምን ብልጫ ታደርጋላችሁ? አሕዛብስ ያንኑ ያደርጉ የለምን? እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ። "

ማቴ. 5÷43-47
🔥3
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ

4. እግዚአብሔርን ፈለግሁት መለሰልኝም፥ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ።
5. ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም አያፍርም።
6. ይህ ችግረኛ ጮኸ፥ እግዚአብሔርም ሰማው፥ ከመከራውም ሁሉ አዳነው።
7. የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።
8. እግዚአብሔር ቸር እንደ ሆነ ቅመሱ እዩም፤ በእርሱ የሚታመን ሰው ምስጉን ነው።
9. የሚፈሩት አንዳችን አያጡምና ቅዱሳኑ ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፍሩት።
10. ባለጠጎች ደኸዩ፥ ተራቡም፥ እግዚአብሔርን የሚፈልጉትን ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።
11. ልጆቼ ኑ፥ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
12. ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?
13. አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ከንፈሮችህም ሽንገላን እንዳይናገሩ።
14. ከክፉ ሽሽ መልካምንም አድርግ፤ ሰላምን እሻ ተከተላትም።
15. የእግዚአብሔር ዓይኖች ወደ ጻድቃን ጆሮቹም ወደ ጩኸታቸው ናቸውና።
16. መታሰቢያቸውን ከምድር ያጠፋ ዘንድ የእግዚአብሔር ፊት ክፉን በሚያደርጉ ላይ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 33:4-16



ሰናይ ቀን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️
ወዳጄ

ሁለት ሃሳቦችን ተረድተህ ፍራቸው፡፡
አንዱ "አንተ ቅዱስ ነህ" ሲል ሌላው " አትድንም " ይላል።
እነዚህ ሁለቱም ሀሳቦች ከጠላት ናቸው,
እና በእነሱ ውስጥ እውነት የለም.
ነገር ግን በዚህ መንገድ አስቡ፡
እኔ ታላቅ ኃጢአተኛ ነኝ፡ ጌታ ግን መሐሪ ነው፡፡
እሱ ሰዎችን በጣም ይወዳል፣ እናም ኃጢአቴን ይቅር ይለኛል፡፡

ቅዱስ ሰሎዋን አቶናዊው

ሰላም  ዕደሩ  የነገ  ሰው  ይበለን ❤️❤️❤️
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 23


1. እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2. በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3. ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4. በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5. በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6. ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።



ደና እደሩ❤️🙏
❤1
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ

15. ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ በሚታመን ሁሉ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።
16. እኛም እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ፍቅር አውቀናል አምነንማል። እግዚአብሔር ፍቅር ነው፥ በፍቅርም የሚኖር በእግዚአብሔር ይኖራል እግዚአብሔርም በእርሱ ይኖራል።
17. በፍርድ ቀን ድፍረት ይሆንልን ዘንድ ፍቅር በዚህ ከእኛ ጋር ተፈጽሞአል፤ እርሱ እንዳለ እኛ ደግሞ እንዲሁ በዚህ ዓለም ነንና።
18. ፍጹም ፍቅር ፍርሃትን አውጥቶ ይጥላል እንጂ በፍቅር ፍርሃት የለም፥ ፍርሃት ቅጣት አለውና፤ የሚፈራም ሰው ፍቅሩ ፍጹም አይደለም።
19. እርሱ አስቀድሞ ወዶናልና እኛ እንወደዋለን።
20. ማንም። እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ ወንድሙን ቢጠላ ሐሰተኛ ነው፤ ያየውን ወንድሙን የማይወድ ያላየውን እግዚአብሔርን ሊወደው እንዴት ይችላል?

1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4:15-20

ሰናይ ቀን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️❤️