☦️ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ☦️
60 subscribers
30 photos
2 videos
1 file
2 links
@fnote abew የአቦቶች መንገድ መከተል
Download Telegram
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 16


1. አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
2. እግዚአብሔርን። አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።
3. ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው።
4. ወደ ሌላ ለሚፋጠኑት መከራቸው ይበዛል፤ የቍርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም፥ ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም።
5. እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ።
6. ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፥ ርስቴም ተዋበችልኝ።
7. የመከረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ ደግሞም በሌሊት ኵላሊቶቼ ይገሥጹኛል።
8. ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም።
9. ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤
10. ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።
11. የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።
👏1
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ ምንባብ

15. በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።
16. ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
17. የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።


2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:15-17
ሰናይ ቀን ❤️❤️❤️
🥰1
+ኃጢአተኛ ነው" የምትለውን ወንድምህን ውደደው+


"እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡

ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/።

ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡

ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡

እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡

እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡

     +ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ+
❤1🥰1
Forwarded from ቤቴል 💒
"ከሐሜተኛና ከቀናተኛ ባልንጀራ ፈጥነህ ሽሽ፤ ይህን ከምታደርግ ብቸኝነትን የምትፈጽምበት ብቸኝነት ይሻልሃልና፡፡
ልቡናው የጨለመ ምሥጢር የማይጠብቅ ዝርወ ልብ የሆነን ሰው አትምከር፡፡ ብዙ ባልንጀሮችን አታብዛ ይልቁንም ደግሞ ከሴቶች ጋር። በቤቴ ውስጥ ነኝ ብለህ ባለጸጎችን አትማ፤ ነገርህን ወፍ አውጥቶት በአፍኣ ይገኛልና፡፡

ስትበላ ከሰው ጋር ብላ፤ ስትጠጣ ግን ብቻህን ጠጣ፤ ከመጠጥ በኋላ አብዝተህ በመናገር በባልንጀሮችህ የተናቅህ የተነቀፍህ ትሆናለህና፤ ሰነፍን ብቻውን ብትነግረው በሰገነት ይሰብከዋል፡፡ ሰነፍ ሲዘሙት ጽድቅ የሚሠራ ይመስለዋል፤ ሐሜተኛም ሲያማ የሚጸልይ ይመስለዋል፡፡ ንዝኅላልም ለጸሎት የሚተጋ ይመስለዋል፡፡ ንፉግም ለነዳያን የሚሰጥ ይመስለዋል፤ ለሰነፎችም ጥበብ የላቸውም፤ ጥበባቸውም ከንቱ ነው፤ ከአላዋቂ ባለጸጋ ቁራሽ የሚለምን ድኻ ይሻላል፡፡

ሞኝ ለንጉሥ ባለሟል ወታደር ሆኖ በተመረጠ ጊዜ ሞት የሌለ ይመስለዋል፡፡ ሞኝ ሲሾም ቤቱን ከጎረቤት ከፍ አድርጎ ይሠራል፤ ሞኝ ባለጸጋ በሆነ ጊዜ ደግሞ በባልንጀሮቹ ይመካ ዘንድ በሚስቱ ላይ ሚስት ያገባል፡፡

ለአላዋቂ ድኽነት ይሻለዋል፤ ሀብት ባገኘ ቁጥር ስሕተትና ክፋትን ይጨምራል፡፡ ገንዘቡንም በኋላ መኳንንት ይቀራመቱታል።"

(መጽሐፈ ወግሪስ ገጽ 81-82)


መልካም  ቆይታ
❤️❤️❤️
🔥1
አንዳንዴ  እንደዚህ ፊት  ለፊት የምታወራኝ  ይመስለኛል🥹🥹  የእመቤታችን  በረከቷ  ይደርብን  🥰🥰

ሰላም  ዕደሩ   የነገ ሰው ይበለን❤️❤️
❤‍🔥4
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 17

1. አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጥ።
2. ፍርዴ ከፊትህ ይውጣ፥ ዓይኖችህም በቅንነት ይዩ።
3. ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
4. የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5. እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
6. አቤቱ፥ ሰምተኸኛልና ወደ አንተ ጠራሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ቃሌንም ስማ።
7. የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው፥ ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው።
8. እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፥
9. ከሚያስጨንቁኝ ከኃጢአተኞች፥ ነፍሴንም ከሚከብቡአት ከጠላቶቼ።
10. አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ፥ በአፋቸውም ትንቢትን ተናገሩ።
11. አሁንም እርምጃችንን ከበቡ፤ ዓይናቸውን ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
12. እርሱ ንጥቂያን እንደሚናፍቅ አንበሳ ተሸጕጦም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ደቦል ነው።
13. አቤቱ፥ ተነሥ፤ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፤ ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።
14. አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፤ ልጆቻቸው ብዙ ናቸው የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
15. እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
እንዴት  አደራችሁ  ቤተሰብ 😍

እግዚአብሔር  ባዶ  ሲያደርገን  ተስፋ  መቁረጥ  የለብንም  ምክንያቱም  ለሙላት  ነውና፤
ሙሴን  እስራኤልን  እንዲጠብቅ  ከማድረጉ  በፊት  ለ50 አመት  በግ  ጠባቂ  ነበር  ለእረኝነት  ሲያለማምደው  ቀድሞ የበግ  ጠባቂ  አደረገው ፤ቃና  ዘገሊላ  ላይ  የጣፈጠ  እና  ልዩ  የሆነውን  ወይን  ለመሙላት  ማሰሮው  ባዶ  እስኪሆን  እስኪያልቅ  ጠብቋል እናም  በባዶነት  ውስጥ  በፈተና  በዝቅታ  ውስጥ  እግዚአብሔር  ለሚፈልገው  ነገር  እያዘጋጀን  እንደሆነ  ማመን  የበለጠ  ተስፋ  ማድረግ  ይኖርብናል !!


ቀኑ  የተቀደሰ  የተባረከ  ይሁንልን  ቀናችሁን  በምስጋና  ጀምሩ ❤️❤️❤️
ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።

— ትንቢተ ኢሳይያስ 58:10
የሰው ልጅ ትልቁ ሀብት — ደግነት

​በሕይወት ጉዟችን ውስጥ ብዙ ነገሮችን እናከማቻለን፤ ሀብት እናንጸባርቃለን፣ ዕውቀት እንቀስማለን፣ ዝና እና ፍለጋ እንሮጣለን። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ከእኛ ጋር የሚቀረው እና ስማችንን በሰዎች ልብ ውስጥ የሚያኖረው ብቸኛው ነገር «መልካምነት» ነው።

​ሰው ማስታወስ የሚችለው የሰጠኸውን ገንዘብ ሳይሆን፣ በችግር ቀን የደረስክለትን አጋጣሚ፣ የፈጠርክለትን ፈገግታ እና ያሳየኸውን እውነተኛ ፍቅር ነው።

ማንም ሰው በደግነቱ ከሰሰ እንጂ በቸርነቱ ተጎድቶ አያውቅም። ዛሬ ለምናገኛቸው ሰዎች የምንሰጠው አዎንታዊ ኃይል እና ቅን ቃል የራሳችንን ሕይወት ጭምር ውብ ያደርገዋል።

​ለሰው ልጅ አክብሮት መስጠት፣ መደጋገፍ እና ካለን ትንሽ ነገር ላይ ችግር ላለው ማካፈል የሕይወታችን ትልቁ ስኬት ነው።

​ ሰላማዊ ምሽት
ከመሮጥ ይልቅ ማስተዋል

​በየዕለቱ ከምንኖረው ፈጣን ሕይወት እና የዕለት ተዕለት ጫና ውስጥ ቆም ብሎ ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ብዙ ጊዜ አእምሯችን ከውጭ በሚመጡ ውጣ ውረዶች እና ጭንቀቶች ይወጥራል፤ ነገር ግን እውነተኛው ጥንካሬ የሚመነጨው ሁልጊዜ ከመሮጥ ሳይሆን፣ ራሳችንን አግልለን ከውስጣችን ጋር ከምንነጋገርበት ጸጥታ ነው።

​ለአብዛኛዎቹ የሕይወት ውጣ ውረዶች መፍትሔ የምናገኘው መጮህ ስንጀምር ሳይሆን፣ መረጋጋት እና ማጤን ስንችል ነው። ከዚህ ዓለም ጫጫታ ትንሽ ፈቀቅ ማለት፣ ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ እና የት እንዳለን ማየት ትልቅ ብስለት ነው።

​አንዳንዴ ዝምታ ከሺህ ቃል በላይ መልስ ይሰጠናል፤ ራስን ማዳመጥ ደግሞ ቀጣዩን እርምጃ በግልጽ ያሳየናል።

​መልካም አዳር ይሁንልን❤️
፠ ክፉ  ልብ 🖤 ያላቸው  ሰዎች  ልክ  በቤት  ውስጥ  የተቀመጠ  እንደ ብልቃጥ  ውስጥ  መርዝ  ናቸው ፤መቼ  ማንን  ባላሰበው  መንገድ  ሊገል  እንደሚችል  አይታወቅም  ክፉ  ልብ  ያላቸውም  እንዲሁ  ከላይ መልካምና  ለስላሳ  አዋቂና  ለሰው  አሳቢ  መስለው  ይታያሉ  ነገር  ግን  እያደር  ቀስ  በቀስ  መርዛቸው  የሆነ  ሰዎን  ሲገል   ይታያል ፤  መልካም  ነገርን  በፍፁም  ማየት  አይችሉም  ሁሌ  ስህተት   ይፈልጋሉ  ሁሌም  ሰውን  በራሳቸው  አይን  ስለሚያዩ   ጥሩ  ነገሮችን  ወደ መጥፎ  ቀይሮ  ለመረዳት  ይፈጥናሉ  በባልንጀራ  መሀል  ጥላቻንና  ክፋትን  ያሳድራሉ ነገር  ግን  ቀና  ልብ  ያላቸው  ሰዎች  በመጥፎ ነገር  ውስጥ  ጥሩ  ነገርን  ያወጣሉ!!!

ቀና  ልብ  ያድለን  ሰላም  እደሩ ❤️❤️
🔥2❤1👏1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 18


1. አቤቱ ጕልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።
2. እግዚአብሔር ዓለቴ፥ አምባዬ፥ መድኃኒቴ፥ አምላኬ፥ በእርሱም የምተማመንበት ረዳቴ፥ መታመኛዬና የደኅንነቴ ቀንድ መጠጊያዬም ነው።
3. ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሔርን እጠራለሁ፥ ከጠላቶቼም እድናለሁ።
4. የሞት ጣር ያዘኝ፥ የዓመፅ ፈሳሽም አስፈራኝ፤
5. የሲኦል ጣር ከበበኝ፤ የሞት ወጥመድም ደረሰብኝ።
6. በጨነቀኝ ጊዜ እግዚአብሔርን ጠራሁት፥ ወደ አምላኬም ጮኽሁ፤ ከመቅደሱም ቃሌን ሰማኝ፥ ጩኸቴም በፊቱ ወደ ጆሮው ገባ።
7. ምድርም ተንቀጠቀጠች ተናወጠችም፥ የተራሮችም መሠረቶች ተነቃነቁ፥ እግዚአብሔርም ተቈጥቶአልና ተንቀጠቀጡ።
8. ከቍጣው ጢስ ወጣ፥ ከፊቱም የሚበላ እሳት ነደደ፤ ፍምም ከእርሱ በራ።
9. ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፥ ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ።
10. በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፥ በነፋስም ክንፍ በረረ።
11. መሰወሪያውን ጨለማ አደረገ፤ በዙሪያውም ድንኳኑ፤ በደመናት ውስጥ የጨለማ ውኃ ነበረ።
12. በፊቱ ካለው ብርሃን የተነሣ ደመናትና በረዶ የእሳት ፍምም አለፉ።
13. እግዚአብሔርም ከሰማያት አንጐደጐደ፥ ልዑልም ቃሉን ሰጠ።
14. ፍላጻውን ላከ በተናቸውም፤ መብረቆችን አበዛ አወካቸውም።
15. አቤቱ፥ ከዘለፋህ ከመዓትህም መንፈስ እስትንፋስ የተነሣ፥ የውኆች ምንጮች ታዩ፥ የዓለም መሠረቶችም ተገለጡ።
16. ከላይ ሰደደ ወሰደኝም፥ ከብዙ ውኆችም አወጣኝ።
17. ከብርቱዎች ጠላቶቼ ከሚጠሉኝም አዳነኝ፥ በርትተውብኝ ነበርና።
18. በመከራዬ ቀን ደረሱብኝ፤ እግዚአብሔር ግን ደገፋዬ ሆነ።
19. ወደ ሰፊ ስፍራም አወጣኝ፤ ወድዶኛልና አዳነኝ።
20. እግዚአብሔር እንደ ጽድቄ ይከፍለኛል፤ እንደ እጄ ንጽሕና ይመልስልኛል።
21. የእግዚአብሔርን መንገድ ጠብቄአለሁና፥ በአምላኬም አላመፅሁም።
22. ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።
23. በእርሱ ዘንድ ቅን ነበርሁ፥ ከኃጢአቴም ተጠበቅሁ።
24. እግዚአብሔርም እንደ ጽድቄ እንደ እጄም ንጽሕና በዓይኖቹ ፊት መለሰልኝ።
25. ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤
26. ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።
27. አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዓይን ግን ታዋርዳለህ።
28. አንተ መብራቴን ታበራለህና፤ እግዚአብሔር አምላኬ ጨለማዬን ያበራል።
29. በአንተ ከጥፋት እድናለሁና በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።
30. የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነጠረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።
31. ከእግዚአብሔር በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?
32. ኃይልን የሚያስታጥቀኝ መንገዴንም የሚያቃና፥
33. እግሮቼን እንደ ብሖር እግሮች የሚያረታ በኮረብቶችም የሚያቆመኝ እግዚአብሔር ነው።
34. እጆቼን ሰልፍ ያስተምራል፥ በክንዴም የናስ ቀስት እገትራለሁ።
35. ለደኅንነቴም መታመኛን ሰጠኸኝ፥ ቀኝህም ትረዳኛለች፥ ትምህርትህም ለዘላለም ታጠናኛለች፥ ተግሣጽህም ታስተምረኛለች።
36. አረማመዴን በበታቼ አሰፋህ፥ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
37. ጠላቶቼን አሳድዳቸዋለሁ እይዛቸዋለሁም፥ እስካጠፋቸውም ድረስ አልመለስም።
38. አስጨንቃቸዋለሁ መቆምም አይችሉም፥ ከእግሬም በታች ይወድቃሉ።
39. ለሰልፍም ኃይልን ታስታጥቀኛለህ፤ በበላዬ የቆሙትን ሁሉ በበታቼ ታስገዛቸዋለህ።
40. የጠላቶቼን ጀርባ ሰጠኸኝ፥ የሚጠሉኝንም አጠፋሃቸው።
41. ጮኹ የሚረዳቸውም አልነበረም፤ ወደ እግዚአብሔርም ጮኹ አልሰማቸውም።
42. እንደ ትቢያ በነፋስ ፊት እፈጫቸዋለሁ፥ እንደ አደባባይም ጭቃ እረግጣቸዋለሁ።
43. ከሕዝብ ክርክር ታድነኛለህ፥ የአሕዛብም ራስ አድርገህ ትሾመኛለህ፥ የማላውቀው ሕዝብም ይገዛልኛል።
44. በጆሮ ሰምተው ተገዙልኝ፤ የባዕድ ልጆች ደለሉኝ።
45. የባዕድ ልጆች አረጁ፥ በመንገዳቸውም ተሰናከሉ።
46. እግዚአብሔር ሕያው ነው፥ አምላኬም ቡሩክ ነው፥ የመድኃኒቴም አምላክ ከፍ ከፍ ይበል።
47. በቀሌን የሚመልስልኝ አምላክ አሕዛብን በበታቼ ያስገዛልኛል።
48. ከጠላቶቼ የሚታደገኝ እርሱ ነው፤ በእኔም ላይ ከቆሙ ከፍ ከፍ ታደርገኛለህ፥ ከግፈኛ ሰው ታድነኛለህ።
49. አቤቱ፥ ስለዚህ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ ለስምህም እዘምራለሁ።
50. የንጉሡን መድኃኒት ታላቅ ያደርጋል፥ ቸርነቱንም ለቀባው ለዳዊትና ለዘሩ ለዘላለም ይሰጣል።
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ


19. ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፤
20. ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሠርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፤
21. መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና።
22. የሰውነት መብራት ዓይን ናት። ዓይንህ እንግዲህ ጤናማ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ይሆናል፤
23. ዓይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!
24. ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።

ማቴዎስ ወንጌል 6:19-24


ሰናይ ቀን ❤️❤️❤️
አቤቱ ጌታዬና አምላኬ ሆይ! ከኃጢአቴ ብዛት የተነሣ ፊቴን ወደ አንተ ለማንሳት እጠራጠራለሁ፤ ነገር ግን እንደ ቸርነትህ ማረኝ
በዕለተ ዓርብ ስለ እኔ በፈሰሰው ክቡር ደምህና በተቆረሰው ሥጋህ ኃጢአቴን ደምስስልኝ። የደከመውን መንፈሴን በቅዱስ መስቀልህ ኃይል አድስልኝ አቤቱ ካገሣው አንበሳ (ከሰይጣን) ወጥመድና ከክፉዎች ተንኮል ሰውረኝ
አቤቱ፥ እኔን ለማዳን ፍጠን፤ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ተመልከት ነፍሴን የሚሹአት ይፈሩ ይጎስቁሉ፤ ክፉን የሚመክሩብኝ ወደ ኋላቸው ይመለሱ ይፈሩም።እኔ ግን ችግረኛና ምስኪን ነኝ፤ አቤቱ፥ እርዳኝ፤ ረዳቴና መድኃኒቴ አንተ ነህ፤ አቤቱ፥ አትዘግይ አሜን 🙏
"ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሜተ፤ መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤ መድኃኔ ዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤ ዘሰተይከ በእንቲኣነ ከርቤ ወሐሞተ፤ በሞተ ዚኣከ ከመ ትቅትል ሞተ።"

(ምስጋናን የለመዱ የሰማይ መላእክት ምድራውያን [የአዳም ልጆች] ቅዱሳን አመስግነው ፍጻሜ ላላገኙለት የስምኽ መታሰቢያ ሰላም እላለኹ። በአንተ ሞት ሞትን ትገድል ዘንድ ስለ እኛ መራራ ከርቤን እና ሐሞትን የጠጣኽ የዓለም መድኀኒት ሆይ ያቀረበኹልኽን ትንሽ ምስጋና ተቀበል።)

#መልክአ_መድኃኔዓለም
👏1
ተዝካረ ጥንተ ስቅለቱ ለመድኃኒነ
❝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ከሁሉ አስቀድሞ ሃይማኖትን መመስከር እንዲገባ "ከመዝ ነአምን ዘአልቦቱ እም በሰማያት ወአብ በዲበ ምድር — በሰማይ ያለ እናት ከአብ መወለዱን በምድርም ያለ አባት ከድንግል ማርያም መወለዱን እናምናለን" ይህንንም አባቶቻችን ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን ቅድመ ዓለም ከእግዚአብሔር አብ ያለ እናት አካል ዘእምአካል ባሕርይ ዘእምባሕርይ የተወለደ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አካላዊ ቃል፤ ድኅረ ዓለም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለአባት መለወጥ ሳያገኘት ዘር ምክንያት ሳይሆን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ የተወለደ፤ 'ወልደ እግዚአብሔር በመለኮቱ ወልደ አብ በትስብእቱ' ብለው አምልተው አስፍተው እንዲያስተምሩን "ከመ አሐዱ ውእቱ ባሕቲቱ ውእቱ አምላክ ወሰብእ ኅቡረ" ትርጉሙም እርሱ በተዋሕዶ ሰው የሆነ አምላክ ነው ማለት ነው❞

— ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮስ ፴፭፥፳፩

መጋቢት ፳፯ በቃል መናገሩ በልብ መታሰቡ ከፍ ይበልና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ቀን ነው። ይሁን እንጂ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያናት በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሳኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ «ስቅለት» ተብሎ እንዲከበር ሥርዐት ሠርተዋል። መጋቢት ፳፯ ቀን ደግሞ በዐቢይ ጾም ላይ ስለሚውል ያኔ ደግሞ ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ በዓል ማክበርም ስለማይፈቀድ ወደ ጥቅምት ፳፰ ተዛውሮ ደስ ብሎን ጥንተ ስቅለቱን እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዐት ሰርታለች።


ጥቅምት ፳፯ ዝክረ ጥንተ ስቅለቱን ቤተክርስቲያናችን ጌታችን ስለፈጸመልን የማዳን ሥራ:-
❝በመስቀሉ ወበቃሉ አእበዮሙ ለአበዊነ — በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው❞

እያለች እየዘመረች ታስበዋለች።

ከዚህም በተጨማሪ ጥቅምት ፳፯ በወርኃ ጽጌ ውስጥ ያለ በመሆኑ:-
❝እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን ስብሐተ ዋህድ ዘምስለ ምህረት በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ❞
እያለች የቅዱሳን ክብራቸው የጻድቃን መድኃኒት የሆነው ጌታ ምድርን በአበባ የሚያስጌጣት እንደሆነ በመመስከር ትዘምራለች።
❝እስመ አንተ ትክል አንጽሖትየ እግዚኦ ወበቃልከ እለ ለምፅ አንጻሕከ ወበጽጌያት ምድር አሠርጎከ ወበመስቀልከ ለጻድቃን አብራህከ — ልታነጻኝ ይቻልሃል አቤቱ ለምጻሞቹን በቃልህ አንጽተሃልና ... ❞
እያሉ አባቶቻችን በመስቀሉ ለጻድቃን ማብራቱን እያሰቡ በዓሉን በመዝሙርና በደስታ ያከብሩታል።
❝ወበከመ ሙሴ ሰቀሎ ለአርዌ ምድር በገዳም ከማሁ ሀለዎ ለወልደ እጓለ እመሕያው ይሰቀል — ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስም ይሰቀል አንድ አለው❞

— ዮሐ ፫፥፲፬ ብሎ እንደተናገረ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለው መጋቢት ፳፯ ቀን ነው። ክርስቶስ ስለ ስቅለቱ ሲናገር ምሳሌ የሚሆነውን ሙሴ በምድረ በዳ የሰቀለውን የነሐሱን እባብ ❝ሙሴ እባብ በምድረ በዳ እንደሰቀለ የሰው ልጅ ክርስቶስም ይሰቀል ዘንድ አለው❞ ብሎ ምሳሌውን ተናግሯል።

የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እስራኤልን ከደመና መና አውርዶ፣ ከጭንጫ ውኃ አፍልቆ ቢመግባቸው ከዚህ ምድሩ ብቅ፣ ሰማዩ ዝቅ ቢልለት፣ ከደጋ ላይ ቢሆንለት የውርጭ ሰደቃ እያበጀ፣ ውሀውን እያረጋ፣ መና መገብኳችሁ ይላል እንጂ 'ይክልኑ እግዚአብሔር ሠሪዓ ማዕድ በገዳም'። ቆላ በሆነማ ባልተቻለውም ነበር ብለዋል። ጌታም ሊያስተምራቸው የርሱን ከሃሊነት የእነርሱንም ሐሰት ሊገልጥባቸው  ሙሴን 'ነቅዓ ማይ የሌለበት በረሐ ይዘሃቸው ውረድ' ብሎት ቢሄዱ መናው ወርዶላቸዋል፣ ውሀውም ፈልቆላቸዋል። ነገር ግን 'ነዘር' የሚባል ክፉ እባብ እየነከሰ ይፈጃቸው ጀመር። ከዚህ በኋላ እስራኤል ሙሴ ዘንድ ሄደው ከጌታ ምህረት ቸርነት ከሰው ስሕተት ኃጢአት አይታጣም 'በእግዚአብሔርና በአንተ ላይ ተናግረን በድለናል  እባቦችን ከኛ ያርቅልን ዘንድ ወደ እግዚአብሔር አመልክትልን፥ አማልደን' አሉት። ሙሴም ስለሕዝቡ  ወደ እግዚአብሔር ቢጸልይ 'ጽሩዩን ብርት አርዌ አስመስለህ ሠርተህ ከሚገናኙበት አደባባይ ከእንጨት ላይ ስቀልላቸው' አለው። ሙሴም እባብን ሠርቶ በዓላማ ላይ ሰቀለ እባብም የነደፈችው ሰው ሁሉ የነሐሱን እባብ ባየ ጊዜ ዳነ —ኦሪት ዘኁ ፳፩፥፩-፱።
 
ይህንም ምሳሌ አባቶቻችን በትርጓሜ ወንጌል ቅዱስ እንዳስቀመጡልን አርዌ ምድር የዲያብሎስ፤ አርዌ ብርት የጌታ ምሳሌ ነው። በአርዌ ምድር(እባብ) መርዝ እንዳለበት በዲያብሎስም ፍዳ ኃጢአት አለበት። በአርዌ ብርት ደግሞ መርዝ እንደሌለበት በጌታም ፍዳ ኃጢአት የለበትም።

አርዌ ብርት በአርዌ ምድር አምሳል መሰቀሉ ጌታ በአምሳለ እኩያን እንደወንጀለኛ ተቆጥሮ ለመሰቀሉ ምሳሌ ነው። ዳግመኛም  ❝ተኈለቈ ምስለ ጊጉያን❞ እንዳለ ነቢዩ ኢሳይያስ ከዐመፀኞችም ጋር ተቈጥሯልና — ኢሳ  ፶፫፥፲፪  የሚለውን ትንቢት ፈጽሟል። ምሳሌውን አውቆ በሙሴ አስመስሏል ትንቢቱንም አውቆ በነቢያቱ አናግሯል።
 
ጲላጦስ አይሁድን 'ከሁለቱ ማናቸውን ላድንላችሁ ትወዳላችሁ?' ቢላቸው 'በርባንን ፍታልን ክርስቶስ የተባለ ኢየሱስን ግን ስቀለው' አሉ። ጲላጦስም  'በዚህ ሰው ደም ከመጣ ፍዳ ሁሉ ንጹሕ ነኝ' ብሎ ባደባባይ እጁን ታጠበ። አይሁድ ደሙ በእኛም በልጅ ልጆቻችንም ይሁን አሉ። እርሱም በርባንን ፈታላቸው ጌታንም አሳልፎ ሰጣቸው — ማቴ ፳፯፥፳፭።
 
ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ:-
❝ሊቃነ መላእክት በመፍራትና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤ ኃጢያትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤ በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት❞
—  እንዲል ክርስቶስን አይሁድ 'ስቀለው!' ብለው ፈረዱበት።
 
አክሊልን የሚያቀናጀውን የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ ክርስቶስን 'አነገስንህ' ብለውታልና ጭፍሮች በፍና ተሣልቆ የእሾህ አክሊል ታተው ደፉለት:- 
❝ወጸፈሩ ሐራ አክሊለ ዘሦክ ወአስተቀጸልዎ ዲበ ርእሱ — ወታደሮችም ከሾህ አክሊል ጐንጕነው በራሱ ላይ አኖሩ ቀይ ልብስም አለበሱት❞

— ዮሐ ፲፱፥፪። ኢየሱስ ክርስቶስ  የእሾኽ አክሊል በመቀዳጀቱ ዕፀ በለስን በልቶ 'ምድር እሾኽንና አሜከላን ታበቅልብኻለች' ዘፍ  ፫፥፲፰ ብሎ የፈረደበትን አዳም ስለእርሱ ክሶ መርገሙን ደምስሶለታል ።
 
መጋቢት ፳፯ ቀን ክርስቶስ ኢየሱስ በመስቀል በተሰቀለ ጊዜ  የተሰቀለው የክብር ባለቤት ሰማይን የፈጠረ ነውና ፀሐይ ጨልማለች፣ ጨረቃ ደም ሆኗል፣ ከዋክብት ረግፈዋል። የተሰቀለው የክብር ባለቤት ምድርንም የፈጠረ ነውና በምድር የቤተመቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀድዷል፤ ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤ መቃብራት ተከፍተዋል፤ ከ፭፻ በላይ ሙታን ተነሥተዋል (ማቴ ፳፯)፡፡
 
❝ኦ አእዳው እለ ለሐኳሁ ለአዳም ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል፤ ኦ አእጋር እለ አንሶሰዋ ውስተ ገነት ተቀነዋ በቅንዋተ መስቀል — አዳምን የፈጠሩ እጆች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ! በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖት ተቸነከሩ ወዮ!❞
— እንዲል  ቅዳሴ ዘዮሐንስ አፈወርቅ ስቅለቱን በዲሜጥሮስ ቀመር አውጥተን የጌታን መከራውን አስበን በስግደት ህማማቱን እናስባለን። በዝክረ ጥንተ ስቅለቱ በጥቅምት ፳፯ ደግሞ በመስቀል የተደረገልንን አስበን እናመሰግነዋለን፡፡
 
እንኳን አደረሳችሁ/አደረሰን።


ዲ/ን ኃይለራጉኤል
አንድ በጣም ትልቅ ቆሻሻ የጫነ ጋሪ የሚገፋ ሰው ወደ ቤትህ መጥቶ "እባክህ በርህን ክፈትልኝና ይህን ቆሻሻ አንተ ቤት ላራግፈው?" ቢልህ፣ "ውይ የሚጥልበት ቢያጣ ነው። ባይቸገር ወደ እኔ አይመጣም ነበር" ብለህ ደጅህን ከፍተህ ታስገባዋለህ? በፍጹም፤ እንደውም "እንዴት ብታስበኝ ነው? ምነው ስታየው ቤት አልመሰለህም? እንዴት ሰው በሚኖርበት ቤት ቆሻሻ ካልደፋሁ ትላለህ? ስትል ለጠብ ትጋበዛለህ። መደፈርህ እያንገበገበህ  "እምቢ!" ብለህ ትቆጣለህ። በእርግጥም ያስቆጣል።

ግን ሌላ የሚከፋ ሽታ ያለው ቆሻሻን ጭኖ ለመጣ ባላጋራ እኮ በፈቃድህ የከፈትከው  ቤት አለ። የምን ቤት? ልብህ ነዋ፤ ማን ይኖርበታል አልኸኝ? እግዚአብሔር ነዋ። አንተ ለመኖሪያ ቤትህ ጽዳት የምትጠነቀቀውን ያህል የያዕቆብ አምላክ ለሚያርፍበት ኅሊናህ ተጠንቅቀህ ታውቃለህ? ሰይጣን ጭኖ የሚያመጣውን የኃጢአት ቆሻሻ ሁሉ እሺ ብለህ ወደ ልብህ በማስገባት የፈጣሪህን መቅደስ ለምን ታቆሽሻለህ? ንጹሑ እግዚአብሔር የሚያድርበትን ቤት ሊያቆሽሽ በመጣ ሰይጣን ላይ እንዴት አልተቆጣህም? ድፍረቱ ለምን አላብከነከነህም?

እግዚአብሔር አንተ ልትኖርበት ከምትፈልገው ንጹሕ ቤት የበለጠ ጽዱ መቅደስ የማይፈልግ ይመስልሃል።
      
   ከዲ/ን አቤል ካሳሁን


ሰናይ  ምሽት ❤️❤️❤️
❤1
​"በምድር ላይ ያለ ፍትሕ በግፍ የሚፈሰው የንጹሐን ደም መሬት ላይ ወድቆ የሚቀር አይደለም፤ ወደ ሰማይ አብሮ ይወጣል፣ ወደ ፈጣሪም ፊት ይጮኻል። ሰብአዊ ፍርድ ቢዘገይ ወይም ቢጓደል፣ መለኮታዊው ፍርድ ግን ፍጹም ነውና መቼም ቢሆን አይቀርም። በግፍ የተገደሉትን ሰዎች መከራና እንባ እግዚአብሔር በአይኑ ይመለከተዋል፤ ክፉዎችንም በሰዓቱ ይቀጣቸዋል።"

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ሰላም  ዕደሩ  የነገ ሰው ይበለን🙏
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 19


1. ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።
2. ቀን ለቀን ነገርን ታወጣለች፥ ሌሊትም ለሌሊት እውቀትን ትናገራለች።
3. ነገር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።
4. ድምፃቸው ወደ ምድር ሁሉ፥ ቃላቸውም እስከ ዓለም ዳርቻ ወጣ።
5. በእነርሱም ውስጥ የፀሐይን ድንኳን አደረገ፥ እርሱም እንደ ሙሽራ ከእልፍኙ ይወጣል፤ እንደ አርበኛ በመንገዱ ለመሮጥ ደስ ይለዋል።
6. አወጣጡ ከሰማያት ዳርቻ ነው፥ ዙረቱም እስከ ዳርቻቸው ነው፤ ከትኩሳቱም የሚሰወር የለም።
7. የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው፤ ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ምስክር የታመነ ነው፤ ሕፃናትን ጠቢባን ያደርጋል።
8. የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው፥ ልብንም ደስ ያሰኛል፤ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ብሩህ ነው፥ ዓይንንም ያበራል።
9. የእግዚአብሔር ፍርሃት ንጹሕ ነው፤ ለዘላለም ይኖራል፤ የእግዚአብሔር ፍርድ እውነትና ቅንነት በአንድነት ነው።
10. ከወርቅና ከክቡር ዕንቍ ይልቅ ይወደዳል፤ ከማርና ከማር ወለላም ይጣፍጣል።
11. ባሪያህ ደግሞ ይጠብቀዋል፤ በመጠበቁም እጅግ ይጠቀማል።
12. ስሕተትን ማን ያስተውላታል? ከተሰወረ ኃጢአት አንጻኝ።
13. የድፍረት ኃጢአት እንዳይገዛኝ ባሪያህን ጠብቅ፤ የዚያን ጊዜ ፍጹም እሆናለሁ፥ ከታላቁም ኃጢአት እነጻለሁ።
14. አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።
Forwarded from ቤቴል 💒
ተወዳጆች እንዴት አደራችሁ 😍

የአለም የትልቅነት  መገለጫ ምንድን ነው ካልን መናቅ ነው

፠ስልጣን ያለዉ ስልጣን የሌለውን ይንቀዋል
፠ሀብት ያለው  ደሀውን ይንቀዋል
፠የተማረው ያልተማረው ይንቀዋል

የአለም የትልቅነት መገለጫ ይሄው ነው ።

እግዚአብሔር ግን
ኃያል ነው ማንንም አይንቅም ። መጽ.ኢዮብ ፴፮ ፥ ፭


በፍቅር ተባብረን ተዋደን እንኖር ዘንድ

እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን
🙏

መልካም ቀን ❤️❤️❤️
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት  ቃል ፦የዕለቱ

3. ዘወትር። አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።
4. ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፤ በዓል የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።
5. ነፍሴ ሆይ፥ ለምን ታዝኛለሽ? ለምንስ ታውኪኛለሽ? የፊቴን መድኃኒት አምላኬን አመሰግነው ዘንድ በእግዚአብሔር ታመኚ።
6. አምላኬ ሆይ፥ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ታወከች፤ ስለዚህ በዮርዳኖስ ምድር በአርሞንኤምም በታናሹ ተራራ አስብሃለሁ።
7. በፍዋፍዋቴህ ድምፅ ቀላይ ቀላይን ትጠራታለች፤ ማዕበልህና ሞገድህ ሁሉ በላዬ አለፈ።
8. እግዚአብሔር በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፤ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።

መዝሙረ ዳዊት 41:3-8



ሰናይ ውሎ
❤️❤️
❤1