*ልጄ ሆይ፥ አእምሮህን በነገው ጭንቀት አትሙላው* ፤ ምክንያቱም *እግዚአብሔር* አስቀድሞ ስለ ነገ አስቦበታል። ውጫዊው ማዕበል ይናወጥ ይሆናል፤ ነገር ግን ልብህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ ከሰጠህ፤ በውስጥህ የሚኖር ሰላም ከዓለም ውካታ ሁሉ በላይ ይሆናል።
*አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ💙🦋*
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን ❤️❤️❤️
*አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ💙🦋*
ሰላም ዕደሩ የነገ ሰው ይበለን ❤️❤️❤️
❤1👏1
Forwarded from ዐውደ_ቤተ መጽሐፍት✝
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ ምንባብ
ሰናይ እለተ ሰንበት ❤️❤️❤️
መዝሙረ ዳዊት 26:1
1. እግዚአብሔር ብርሃኔና መድኃኒቴ ነው፤ የሚያስፈራኝ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወቴ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠኝ ማን ነው?
ሰናይ እለተ ሰንበት ❤️❤️❤️
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 13
1. አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?
2. እስከ መቼ በነፍሴ እመካከራለሁ? ትካዜስ እስከ መቼ ሁልጊዜ ይሆናል? እስከ መቼ ጠላቴ በላዬ ይጓደዳል?
3. አቤቱ አምላኬ፥ እየኝ ስማኝም፤ ጠላቴ። አሸነፍሁት እንዳይል፥
4. የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው፥ ለሞትም እንዳልተኛ ዓይኖቼን አብራ።
5. እኔ ግን በቸርነትህ ታመንሁ፥ ልቤም በመድኃኒትህ ደስ ይለዋል።
6. የረዳኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፥ ለልዑል እግዚአብሔር ስምም እዘምራለሁ።
👏1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 14
1. ለመዘምራን አለቃ፤ የዳዊት መዝሙር።
2. የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
3. ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
4. ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
5. ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤
6. ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
7. ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
👏1
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ ምንባብ
ሰናይ ዕለተ ሰኞ ይሁንልን ❤️❤️❤️
የዮሐንስ ወንጌል 16:20-21
20. እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተ ታለቅሳለችሁ ሙሾም ታወጣላችሁ፥ ዓለም ግን ደስ ይለዋል፤ እናንተም ታዝናላችሁ፥ ነገር ግን ኀዘናችሁ ወደ ደስታ ይለወጣል።
21. ሴት በምትወልድበት ጊዜ ወራትዋ ስለ ደረሰ ታዝናለች፤ ነገር ግን ሕፃን ከወለደች በኋላ፥ ሰው በዓለም ተወልዶአልና ስለ ደስታዋ መከራዋን ኋላ አታስበውም።
ሰናይ ዕለተ ሰኞ ይሁንልን ❤️❤️❤️
👏1
እግዚአብሔር በሚገኝበት ጊዜ ፈልጉት፥ ቀርቦም ሳለ ጥሩት፤
— ትንቢተ ኢሳይያስ 55:6
👏1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 15
1. አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል?
2. በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር።
3. በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ።
4. ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም።
5. ገንዘቡን በአራጣ የማያበድር፥ በንጹሑ ላይ መማለጃን የማይቀበል። እንዲህ የሚያደርግ ለዘላለም አይታወክም።
👏1
ተወዳጆች እንዴት አደራችሁ 😍
በአለም ላይ ትልቁ መከራ ምንድን ነው ካላችሁ
እንደ ውሻ የሰው ፊት ማየት ነው።
የሰው ፊት እሳት ነው።
የእግዚአብሔር ፊት ብቻ ግን ብርሃን ነው ።
ለዛ ነው ፊቴን እሹ ያለው
ቅዱስ ዳዊት
አቤቱ ፊቴን እሹ ብለሃልና
አቤቱ ጌታ ሆይ ፊትህን እሻለሁ ይላል።
ተወዳጆች
👉የማያሳፍር
👉ብርሃን የሆነ
👉ደስታ የሆነ ፊት
የእግዚአብሔር ፊት ነው
መልካም ማለዳ መልካም ቀን ❤️❤️❤️
በአለም ላይ ትልቁ መከራ ምንድን ነው ካላችሁ
እንደ ውሻ የሰው ፊት ማየት ነው።
የሰው ፊት እሳት ነው።
የእግዚአብሔር ፊት ብቻ ግን ብርሃን ነው ።
ለዛ ነው ፊቴን እሹ ያለው
ቅዱስ ዳዊት
አቤቱ ፊቴን እሹ ብለሃልና
አቤቱ ጌታ ሆይ ፊትህን እሻለሁ ይላል።
ተወዳጆች
👉የማያሳፍር
👉ብርሃን የሆነ
👉ደስታ የሆነ ፊት
የእግዚአብሔር ፊት ነው
መልካም ማለዳ መልካም ቀን ❤️❤️❤️
❤1🥰1
☦️ሃሌሉያ ለአብ ሃሌሉያ ለወልድ ሃሌሉያ ለመንፈስ ቅዱስ☦️
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 15 1. አቤቱ፥ በድንኳንህ ውስጥ ማን ያድራል? በተቀደሰውም ተራራህ ማን ይኖራል? 2. በቅንነት የሚሄድ፥ ጽድቅንም የሚያደርግ፥ በልቡም እውነትን የሚናገር። 3. በአንደበቱ የማይሸነግል፥ በባልንጀራው ላይ ክፋትን የማያደርግ፥ ዘመዶቹንም የማይሰድብ። 4. ኃጢአተኛ በፊቱ የተናቀ፥ እግዚአብሔርንም የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ለባልንጀራው የሚምል የማይከዳም። 5. ገንዘቡን በአራጣ…
በማቴዎስ 5:34 ላይ “ፈጽሞ አትማሉ” ተብሎ ታዟል፤ በሌላ በኩል ደግሞ በብሉይ ኪዳን በመዝሙር 15:4 (በ1954 ትርጉም መዝሙር 14:4) ላይ በእግዚአብሔር ድንኳን ውስጥ የሚኖር ጻድቅ ሰው ሲገለጽ “ለባልጀራው የሚምል የማይከዳም” ይላል። እንዴት ?1. የኪዳናትና የዘመን ልዩነት ፦
• በብሉይ ኪዳን ፦ በብሉይ ኪዳን ዘመን መማል ሙሉ በሙሉ የተከለከለ አልነበረም። የተከለከለው በሐሰት መማል እና የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ ማንሳት ነበር (ዘጸአት 20:7)። ስለዚህ አንድ ሰው በእግዚአብሔር ስም ማልዶ ቃሉን ከጠበቀና ካልካደ እንደ ጻድቅ ይቆጠር ነበር። መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት የጠቀሰው ይህንን ታማኝነት ነው።
# በአዲስ ኪዳን የክርስቶስ ያዘዘው ፦
በማቴዎስ 5 ላይ ሕግን ሊያሻሽልና ሊፈጽም ሲመጣ የሰዎችን የጽድቅ ደረጃ ከፍ አደረገው። “ቃላችሁ አዎን ከሆነ አዎን፥ አይደለም ከሆነ አይደለም ይሁን” በማለት አማኞች መማል ሳያስፈልጋቸው በቃላቸው ብቻ የሚታመኑ ፍጹማን እንዲሆኑ አዘዘ።
2. የቃሉ ትክክለኛ ፍቺ እና አንድምታው ፦
በግዕዙ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ይህ ጥቅስ “ዘይመህል ለባልጀሩ ወኢይሔሱ” ይላል። ይህንን ሊቃውንት በሁለት መንገድ ይተረጉሙታል፦
፠ አንደኛው ትርጉም፦ “ለባልጀሩ የሚምል (የሚምልለት/የሚገዘትለት) የማይከዳውም” ማለት ሲሆን፥ ይህም ከላይ እንደተጠቀሰው በብሉይ ኪዳን ለሰው የገባውን ቃል ኪዳን በጥንካሬ የሚጠብቅ ሰውን ያሳያል።
# ሁለተኛውትርጉም፦ “መሐላ” ማለት በግዕዝ ማልዶ ቃል መግባት ብቻ ሳይሆን “ቃል ኪዳን መግባት/መረታት” ማለትም ነው። ስለዚህ “ለባልጀራው የሚምል” ማለት “ለጓደኛው፣ ለወንድሙ ወይም ለሰዎች ሁሉ በታማኝነት ቃል የሚገባና የገባውን ቃል የማያጥፍ፣ የማይዋሽ” ማለት ነው።
3.#ሁለቱም ጥቅሶች የሚያተኩሩት በአንድ ዋና ነገር ላይ ነው፤ እርሱም ታማኝነት ነው።
# መዝሙረኛው ማልዶም ቢሆን የገባውን ቃል የማይ አጥፍ የመሰከረለትን ሰው ታማኝነት ሲያደንቅ፥
፠ ክርስቶስ ደግሞ ክርስቲያኖች መማል እንኳን ሳያስፈልጋቸው በንግግራቸው ብቻ የታመኑና የማይዋሹ እንዲሆኑ አስተምሯል።
በአጠቃላይ፡ መዝሙሩ የብሉይ ኪዳንን የጽድቅ ደረጃ (የማይዋሽና መሐላውን የሚያከብር) ሲያሳይ፥ ወንጌል ደግሞ ፍጹም የሆነውን የአዲስ ኪዳን ሕግ (ከመሐላ የጸዳ ሙሉ ታማኝነትን) ይገልጻል።
@temsgn121619
🥰1👏1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 16
1. አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና ጠብቀኝ።
2. እግዚአብሔርን። አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ፤ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።
3. ፈቃድህ ሁሉ በምድር ባሉት ቅዱሳንና ክቡራን ላይ ነው።
4. ወደ ሌላ ለሚፋጠኑት መከራቸው ይበዛል፤ የቍርባናቸውን ደም እኔ አላፈስሰውም፥ ስማቸውንም በከንፈሬ አልጠራም።
5. እግዚአብሔር የርስቴ እድል ፈንታና ጽዋዬ ነው፥ ዕጣዬንም የምታጠና አንተ ነህ።
6. ገመድ ባማረ ስፍራ ወደቀችልኝ፥ ርስቴም ተዋበችልኝ።
7. የመከረኝን እግዚአብሔርን እባርካለሁ፤ ደግሞም በሌሊት ኵላሊቶቼ ይገሥጹኛል።
8. ሁልጊዜ እግዚአብሔርን በፊቴ አየዋለሁ፤ በቀኜ ነውና አልታወክም።
9. ስለዚህ ልቤን ደስ አለው ምላሴም ሐሴት አደረገች፤ ሥጋዬም ደግሞ በተስፋ ታድራለች፤
10. ነፍሴን በሲኦል አትተዋትምና፥ ቅዱስህንም መበስበስን ያይ ዘንድ አትተወውም።
11. የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።
👏1
Forwarded from ቤቴል 💒
የሕይወት ቃል ፦የዕለቱ ምንባብ
15. በብዙዎች በኩል የተትረፈረፈው ጸጋ ለእግዚአብሔር ክብር ምስጋናን ያበዛ ዘንድ፥ ሁሉ ስለ እናንተ ነውና።ሰናይ ቀን ❤️❤️❤️
16. ስለዚህም አንታክትም፥ ነገር ግን የውጭው ሰውነታችን ቢጠፋ እንኳ የውስጡ ሰውነታችን ዕለት ዕለት ይታደሳል።
17. የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ባንመለከት፥ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና፤ የሚታየው የጊዜው ነውና፥ የማይታየው ግን የዘላለም ነው።
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 4:15-17
🥰1
+ኃጢአተኛ ነው" የምትለውን ወንድምህን ውደደው+
"እገሌ እኮ እንዲህ እንዲህ ዓይነት ኃጢአት ሠርቷል" ብላችሁ የምታሙትን ወንድማችሁ ከዚያ ኃጢአቱ ነጻ እንዲወጣ ትፈልጋላችሁን? እንግዲያስ ስለ ኃጢአቱ አልቅሱለት፤ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩለት፤ ለብቻ ወስዳችሁም ምከሩት እንጂ አትሙት። ሐዋርያው ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ክርስቲያኖች እንዲህ ብሎ ጽፎላቸው ነበር፡- "ነገር ግን ወዳጆች! እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን። ስመጣ እንደምወደው ሳትሆኑ አገኛችሁ ይሆናል፤ እኔም እንደምትወዱት ሳልሆን ታገኙኝ ይሆናል ብዬ እፈራለሁና፡፡
ምናልባት ክርክር ቅንዓትም ቁጣም አድመኝነትም ሐሜትም ማሾክሾክም ኩራትም ሁከትም ይሆናሉ፡፡ እንደ ገና ስመጣ በእናንተ ዘንድ አምላኬ እንዲያዋርደኝ፥ አስቀድመውም ኃጢአት ከሠሩትና ስላደረጉት ርኵሰትና ዝሙት መዳራትም ንስሐ ካልገቡት ወገን ስለ ብዙዎች ምናልባት አዝናለሁ ብዬ እፈራለሁ" /2ቆሮ.12፥19-21/።
ስለዚህ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ በትልቁ ደግሞ እንደ ጌታችን "ኃጢአተኛ ነው" የምትሉትን ወንድማችሁ ውደዱት፡፡ ለብቻው አድርጋችሁ ስትነግሩትም አመጣጣችሁ እርሱን ለመምከርና ለመገሰጽ ደግሞም ከኃጢአቱ እንዲመለስ እንጂ እርሱን ከመጥላታችሁ የተነሣ እንዳልሆነ አስረዱት፡፡ ስለዚህ በትክክል ካለበት ደዌ እርሱን መፈወስ ስትፈልጉ ወደ እርሱ መሄድን አትፍሩ፤ ጥፋቱን ለመንገርም አትፈሩ፡፡
ሐኪሞችን አይታችሁ ከሆነ አንድ አስቸጋሪ ታማሚን ለማከም መጀመርያ ቀስ ብለውና ጊዜ ወስደው ታማሚዉን ያሳምኑታል፤ ከዚያም መራሩን መድኃኒት ይሰጡታል፡፡ ታካሚውም በሽታው የሚድን ከሆነ ይፈወሳል፡፡ ሐኪሙን የሚያመሰግነው ግን ሲድን ነው፡፡
እናንተም እንደዚህ ሐኪም መሆን አለባችሁ፡፡ ከምታሙት ይልቅ የወንድማችሁን ቁስል የበለጠ እንዳይመረቅዝ ፈጥናችሁ ወደ ሐኪም ቤት (ወደ ቤተክርስቲያን) ውሰዱት። ከዚያም ሐኪም (ካህን) እንዲያየው አድርጉ፡፡
እንዲህ ስታደርጉ እናንተም ወንድማችሁም በእጅጉ ትጠቀማላችሁ፡፡ እውነተኛ ጦም ጦማችሁ ማለትም እንዲህና ይህን የመሰለ መልካም ምግባር ስታደርጉ ነው፡፡
+ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ+

"ከሐሜተኛና ከቀናተኛ ባልንጀራ ፈጥነህ ሽሽ፤ ይህን ከምታደርግ ብቸኝነትን የምትፈጽምበት ብቸኝነት ይሻልሃልና፡፡ልቡናው የጨለመ ምሥጢር የማይጠብቅ ዝርወ ልብ የሆነን ሰው አትምከር፡፡ ብዙ ባልንጀሮችን አታብዛ ይልቁንም ደግሞ ከሴቶች ጋር። በቤቴ ውስጥ ነኝ ብለህ ባለጸጎችን አትማ፤ ነገርህን ወፍ አውጥቶት በአፍኣ ይገኛልና፡፡
ስትበላ ከሰው ጋር ብላ፤ ስትጠጣ ግን ብቻህን ጠጣ፤ ከመጠጥ በኋላ አብዝተህ በመናገር በባልንጀሮችህ የተናቅህ የተነቀፍህ ትሆናለህና፤ ሰነፍን ብቻውን ብትነግረው በሰገነት ይሰብከዋል፡፡ ሰነፍ ሲዘሙት ጽድቅ የሚሠራ ይመስለዋል፤ ሐሜተኛም ሲያማ የሚጸልይ ይመስለዋል፡፡ ንዝኅላልም ለጸሎት የሚተጋ ይመስለዋል፡፡ ንፉግም ለነዳያን የሚሰጥ ይመስለዋል፤ ለሰነፎችም ጥበብ የላቸውም፤ ጥበባቸውም ከንቱ ነው፤ ከአላዋቂ ባለጸጋ ቁራሽ የሚለምን ድኻ ይሻላል፡፡
ሞኝ ለንጉሥ ባለሟል ወታደር ሆኖ በተመረጠ ጊዜ ሞት የሌለ ይመስለዋል፡፡ ሞኝ ሲሾም ቤቱን ከጎረቤት ከፍ አድርጎ ይሠራል፤ ሞኝ ባለጸጋ በሆነ ጊዜ ደግሞ በባልንጀሮቹ ይመካ ዘንድ በሚስቱ ላይ ሚስት ያገባል፡፡
ለአላዋቂ ድኽነት ይሻለዋል፤ ሀብት ባገኘ ቁጥር ስሕተትና ክፋትን ይጨምራል፡፡ ገንዘቡንም በኋላ መኳንንት ይቀራመቱታል።"
(መጽሐፈ ወግሪስ ገጽ 81-82)
መልካም ቆይታ ❤️❤️❤️
🔥1
📖 መዝሙረ ዳዊት - Chapter 17
1. አቤቱ፥ ጽድቄን ስማ ጩኸቴንም አድምጥ፤ በተንኰለኛም ከንፈር ያልሆነውን ጸሎቴን አድምጥ።
2. ፍርዴ ከፊትህ ይውጣ፥ ዓይኖችህም በቅንነት ይዩ።
3. ልቤን ፈተንኸው በሌሊትም ጐበኘኸኝ፤ ፈተንኸኝ፥ ምንም አላገኘህብኝም።
4. የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፤ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
5. እግሮች እንዳይናወጡ አረማመዴን በመንገድህ አጽና።
6. አቤቱ፥ ሰምተኸኛልና ወደ አንተ ጠራሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ ቃሌንም ስማ።
7. የሚያምኑህን ከሚቃወሙ በቀኝህ የምታድናቸው፥ ቸርነትህን ድንቅ አድርገህ ግለጠው።
8. እንደ ዓይን ብሌን ጠብቀኝ፥ በክንፎችህ ጥላ ሰውረኝ፥
9. ከሚያስጨንቁኝ ከኃጢአተኞች፥ ነፍሴንም ከሚከብቡአት ከጠላቶቼ።
10. አንጀታቸውን በስብ ቋጠሩ፥ በአፋቸውም ትንቢትን ተናገሩ።
11. አሁንም እርምጃችንን ከበቡ፤ ዓይናቸውን ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደረጉ።
12. እርሱ ንጥቂያን እንደሚናፍቅ አንበሳ ተሸጕጦም እንደሚኖር እንደ አንበሳ ደቦል ነው።
13. አቤቱ፥ ተነሥ፤ ቀድመህ ወደ ታች ጣለው፤ ነፍሴን ከኃጢአተኛ በሰይፍህ አድናት።
14. አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፤ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፤ ልጆቻቸው ብዙ ናቸው የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።
15. እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፤ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
እንዴት አደራችሁ ቤተሰብ 😍
እግዚአብሔር ባዶ ሲያደርገን ተስፋ መቁረጥ የለብንም ምክንያቱም ለሙላት ነውና፤
ሙሴን እስራኤልን እንዲጠብቅ ከማድረጉ በፊት ለ50 አመት በግ ጠባቂ ነበር ለእረኝነት ሲያለማምደው ቀድሞ የበግ ጠባቂ አደረገው ፤ቃና ዘገሊላ ላይ የጣፈጠ እና ልዩ የሆነውን ወይን ለመሙላት ማሰሮው ባዶ እስኪሆን እስኪያልቅ ጠብቋል እናም በባዶነት ውስጥ በፈተና በዝቅታ ውስጥ እግዚአብሔር ለሚፈልገው ነገር እያዘጋጀን እንደሆነ ማመን የበለጠ ተስፋ ማድረግ ይኖርብናል !!
ቀኑ የተቀደሰ የተባረከ ይሁንልን ቀናችሁን በምስጋና ጀምሩ ❤️❤️❤️

ባታንጐራጕርም፥ ነፍስህንም ለተራበ ብታፈስስ፥ የተጨነቀውንም ነፍስ ብታጠግብ፥ ብርሃንህ በጨለማ ይወጣል ጨለማህም እንደ ቀትር ይሆናል።
— ትንቢተ ኢሳይያስ 58:10
የሰው ልጅ ትልቁ ሀብት — ደግነት
በሕይወት ጉዟችን ውስጥ ብዙ ነገሮችን እናከማቻለን፤ ሀብት እናንጸባርቃለን፣ ዕውቀት እንቀስማለን፣ ዝና እና ፍለጋ እንሮጣለን። ነገር ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ከእኛ ጋር የሚቀረው እና ስማችንን በሰዎች ልብ ውስጥ የሚያኖረው ብቸኛው ነገር «መልካምነት» ነው።
ሰው ማስታወስ የሚችለው የሰጠኸውን ገንዘብ ሳይሆን፣ በችግር ቀን የደረስክለትን አጋጣሚ፣ የፈጠርክለትን ፈገግታ እና ያሳየኸውን እውነተኛ ፍቅር ነው።
ማንም ሰው በደግነቱ ከሰሰ እንጂ በቸርነቱ ተጎድቶ አያውቅም። ዛሬ ለምናገኛቸው ሰዎች የምንሰጠው አዎንታዊ ኃይል እና ቅን ቃል የራሳችንን ሕይወት ጭምር ውብ ያደርገዋል።
ለሰው ልጅ አክብሮት መስጠት፣ መደጋገፍ እና ካለን ትንሽ ነገር ላይ ችግር ላለው ማካፈል የሕይወታችን ትልቁ ስኬት ነው።

ሰላማዊ ምሽትከመሮጥ ይልቅ ማስተዋል
በየዕለቱ ከምንኖረው ፈጣን ሕይወት እና የዕለት ተዕለት ጫና ውስጥ ቆም ብሎ ማሰብ እጅግ አስፈላጊ ነው። ብዙ ጊዜ አእምሯችን ከውጭ በሚመጡ ውጣ ውረዶች እና ጭንቀቶች ይወጥራል፤ ነገር ግን እውነተኛው ጥንካሬ የሚመነጨው ሁልጊዜ ከመሮጥ ሳይሆን፣ ራሳችንን አግልለን ከውስጣችን ጋር ከምንነጋገርበት ጸጥታ ነው።
ለአብዛኛዎቹ የሕይወት ውጣ ውረዶች መፍትሔ የምናገኘው መጮህ ስንጀምር ሳይሆን፣ መረጋጋት እና ማጤን ስንችል ነው። ከዚህ ዓለም ጫጫታ ትንሽ ፈቀቅ ማለት፣ ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ እና የት እንዳለን ማየት ትልቅ ብስለት ነው።
አንዳንዴ ዝምታ ከሺህ ቃል በላይ መልስ ይሰጠናል፤ ራስን ማዳመጥ ደግሞ ቀጣዩን እርምጃ በግልጽ ያሳየናል።
መልካም አዳር ይሁንልን❤️

፠ ክፉ ልብ 🖤 ያላቸው ሰዎች ልክ በቤት ውስጥ የተቀመጠ እንደ ብልቃጥ ውስጥ መርዝ ናቸው ፤መቼ ማንን ባላሰበው መንገድ ሊገል እንደሚችል አይታወቅም ክፉ ልብ ያላቸውም እንዲሁ ከላይ መልካምና ለስላሳ አዋቂና ለሰው አሳቢ መስለው ይታያሉ ነገር ግን እያደር ቀስ በቀስ መርዛቸው የሆነ ሰዎን ሲገል ይታያል ፤ መልካም ነገርን በፍፁም ማየት አይችሉም ሁሌ ስህተት ይፈልጋሉ ሁሌም ሰውን በራሳቸው አይን ስለሚያዩ ጥሩ ነገሮችን ወደ መጥፎ ቀይሮ ለመረዳት ይፈጥናሉ በባልንጀራ መሀል ጥላቻንና ክፋትን ያሳድራሉ ነገር ግን ቀና ልብ ያላቸው ሰዎች በመጥፎ ነገር ውስጥ ጥሩ ነገርን ያወጣሉ!!!
ቀና ልብ ያድለን ሰላም እደሩ ❤️❤️
ቀና ልብ ያድለን ሰላም እደሩ ❤️❤️
🔥2❤1👏1