Students channel
3.53K subscribers
721 photos
12 videos
178 files
723 links
Stay will be Positive Attitude 😎
Download Telegram
የጥሪ ማስታዎቂያ
#Wachamouniversity

በ2019 ዓ.ም አዲስ ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ እና በ 2018 ዓ.ም አቅም ማሻሻያ ( Remedial) በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ማለፊያ ያመጣችሁ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10 / 2019 ዓ.ም ነው።

በ2019 ዓ.ም የተመደባችሁ Remedial ተማሪዎች ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ይገለጻል።

https://t.me/httpentra
#MattuUniversity #ጥሪማስታወቂያ

በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ 1ኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች (Freshman) እና በ2018 ዓ.ም Remedial የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፤ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 9 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ እናሳስባለን።

ማሳሰቢያ :-

በ2018 ዓ.ም. በበደሌ ካምፓስ በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርታችሁን ስትከታተሉ የነበራችሁና በ2019 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር ተመድባችሁ ስማችሁ በፊደል A-B የሚጀምር የተፈጥሮ ሳይንስና የማኅበራዊ ሳይንስ ስትሪም ተማሪዎች፣ ምዝገባችሁ የሚካሄደው በበደሌ ካምፓስ መሆኑን እናሳስባለን።

👉የሌሎች ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ ይሆናል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

https://t.me/httpentra
❤2
#Arbaminchuniversity

​ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ Freshman እና የ 2018 Remedial ላለፋችሁ ተማሪዎች፡

➻ ​የቅበላ ቀን፡ ረቡዕ፣ ጥቅምት 4/2019 ዓ.ም

➻ ​የምዝገባ ቀናት፡ ሐሙስ እና ዓርብ፣ ጥቅምት 5 እና 6/2019 ዓ.ም

➻ ​ትምህርት የሚጀምርበት፡ ሰኞ፣ ጥቅምት 9/2019 ዓ.ም

​የተመደቡበትን ካምፓስ ለማወቅ፡
አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በ
https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement ገብታችሁ የ12ኛ ክፍል መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት ማወቅ ትችላላችሁ።

(የRemedial ተማሪዎች ቀደም ሲል በተማራችሁበት ካምፓስ ትመዘገባላችሁ)።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➻ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➻ የስፖርት ልብስ።

https://t.me/httpentra
#WolaitaSodoUniversity

በ2019 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ከዚህ በፊት የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በተማራችሁበት ካምፓስ እንደሆነ ተገልጿል።

በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደባችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ስማችሁ ከ A-S የሆነ ምዝገባ የሚካሔደው በዋናው ካምፓስ እና ከ T-Z የሆናችሁ ምዝገባ የሚካሄደው በዳውሮ-ታርጫ ካምፓስ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በ2019 ዓ.ም ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ይገለጻል ተብሏል፡፡

https://t.me/httpentra
#DambiDolloUniversity

በ2019 ዓ.ም ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ጥቅምት 11/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

በ2019 ዓ.ም ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።


https://t.me/httpentra
❤2
#JigjiggaUniversity

በ2019 ዓ.ም ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እና የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 9-11/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
● አራት የቅርብ ጊዜ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የአልጋ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

https://portal.jju.et/biography ላይ በመግባት ከላይ የተጠቀሱትን ሰነዶች እና አንድ የመታወቂያ ፎቶ የአድሚሽን ቁጥራችሁን በመጠቀም ማስገባት ይጠበቅባችኋል።

https://t.me/httpentra
#DireDawaUniversity

በ2019 ዓ.ም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

በተለያዩ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 10 እና 11/2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

https://t.me/httpentra
🔥2
#DebraBirhanUniversity

​በ2019 ዓ/ም ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች እና በ2018 ዓ/ም በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የሬሜዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 11 እና 12/2019 ዓ.ም ስለሆነ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ አሳውቋል ::

👉ጥቅምት 16/2019 ዓ/ም ትምህርት የሚጀመርበት ጊዜ መሆኑን እንገልፃለን።

​ማሳሰቢያ፡

​ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን አናስተናግድም።
​የ2018 ሬሜዲያል ትምህርት በዩኒቨርሲቲው ተከታትለው ማለፊያ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ትምህርቱን ሲከታተሉ በነበሩበት ካምፓስ ይሆናል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

https://t.me/httpentra
#InjibaraUniversity

በ2019 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 12 እና 13/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

በ2019 ዓ.ም እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ትምህርት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እንደሚደረግ ተገልጿል፡፡
 
https://t.me/httpentra
#WallaggaUniversity

በ2019 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 የትምህርት ዘመን Remedial Program ተከታትላችሁ ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 09 እና 10 2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ያሳውቃል።

የምዝገባ ቦታ፡-

👉​ በ2019 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በዋናው ግቢ፣ ነቀምት ካምፓስ፤

👉 ​በ2018 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው በ2018 የትምህርት ዘመን የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ስትማሩበት በነበረው ካምፓስ ይሆናል።

​ማሳሰቢያ፡-

​በ2019 ትምህርት ዘመን በአቅም ማሻሻያ ትምህርት ለመማር ወደ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት በሌላ ማስታወቂያ የሚነገር ይሆናል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
● አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

https://t.me/httpentra
#Wolkiteuniversity

​በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች፤ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሜዲያል ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲው ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ጥቅምት 9 እና 10 መሆኑን አውቃችሁ በተገለጸው ቀን በአካል ቀርባችሁ እንድትመዘገቡ ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● ስድስት 3X4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● የፋይዳ መታወቂያ፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ፡፡

https://t.me/httpentra
🥰3🔥2
#AssosaUniversity

በ2019 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ወደ 1ኛ ዓመት ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 16 እና 17/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
● የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
 
https://t.me/httpentra
🥰3❤2😡1
እስካሁን ጥሪ #ያላደረጉ ዩኒቨርስቲዎች ዝርዝር

1. አርሲ ዩኒቨርስቲ
2. ደብረማርቆስ ዩኒቨርስቲ
3. ወሎ ዩኒቨርስቲ
4. መቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ
5. ጂንካ ዩኒቨርስቲ
6. ሰመራ ዩኒቨርስቲ
7. አምቦ ዩኒቨርስቲ
8. መቐለ ዩኒቨርስቲ
9. አዲግራት ዩኒቨርስቲ
10. አክሱም ዩኒቨርስቲ
11. ጋምቤላ ዩኒቨርስቲ

https://t.me/httpentra
አብዛኛው የመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ጥሪ ተካሄዷል የቀሩት ጥቂት ጊቢዎች ናቸው


ከጥቅም መጨረሻ አንስቶ እስከ ህዳር መጀመሪያዎቹ የ 2019 የማካካሻ ትምህርት ለሚወስዱ ጥሪ ይደረጋል

እያንዳንዱ ጊቢ ጥሪ በ ቻናላችን በፍጥነት እና በቅልጥፍና ወደ እናንተ ይደርሳል

2019 ሪሜዲያል አላቹ ??!!!!!!!!
https://t.me/httpentra
❤3🥰3🙊1
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#Mekdela_Amba_University

የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 9 እና 10/2019

ይህ ማስታወቂያ ከትግራይ ክልል በመንግስት ወደ መቅደላ አምባ የተመደባችሁ ተማሪዎችንም ይመለከታል።

ተጨማሪ መረጃ በምስሉ ላይ ተያይዟል


https://t.me/httpentra
👍3🔥1🤷1
Wollo university
❤2👍2🥰1
እስካሁን  ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርስቲዎች ዝርዝር

1. ጅማ ዩኒቨርስቲ (ጥቅምት 4 እና 5)
2. ደባርቅ ዩኒቨርስቲ (መስከረም 28 እና 29)
3. ራያ ዩኒቨርስቲ (ከጥቅምት 16-18)
4. ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 12 እና 13)

NB: ቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ ጥሪ ያደረገው ለFreshman እና በ 2019 አዲስ ለተመደባችሁ ሬሜዲያል ተማሪዎች ነው

5. ሐረማያ ዩኒቨርስቲ (ከ ጥቅምት 5 እስከ 8)
6. ሐዋሳ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 3 እና 4)
7. ዲላ ዩኒቨርስቲ ( For Freshmans ጥቅምት 5-6) & For New Remedial Students( ጥቅምት 19 እና 20)
8. ጎንደር ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 4-5)
9. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 4 -5)
10.  ሰላሌ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 4 እና 5)
11. ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
12. ባህርዳር ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
13. ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
14. ቦንጋ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 5 እና 6)
15. ቦረና ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 4 እና 5)
16. ጂግጂጋ ዩኒቨርስቲ ( ከጥቅምት  9-11)
17. ዋቸሞ ዩኒቨርስቲ( ጥቅምት 9 እና 10)
18. መቱ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
19. አርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 4 )
20. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
21. ድሬደዋ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 7 እና 8)
22. ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
23. ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ (ጥቅምት 9 እና 10)
24. ወለጋ ዩኒቨርስቲ (ጥቅምት 9 እና 10)
25. እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 12 እና 13)
26. ደብረብርሃን ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 11 እና 12)
27. ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ጥቅምት 9 እና 10)
28. ወራቤ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 16 እና 17)
29. አሶሳ ዩኒቨርስቲ( ጥቅምት 16 እና 17)
30. ቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 16 እና 17)
31. ኬተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 5 እና 6)
32. መደ ወላቡ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 9 እና 10)
33. መቅደላ አምባ ( ጥቅምት 9 እና 10)
34. ወሎ ዩኒቨርስቲ ( ጥቅምት 14 እና 15)




https://t.me/httpentra
❤4🥰4🔥1
#ይነበብ

ከትግራይ ወደ አሶሳ ዩኒቨርስቲ ለተመደባቹ
❤3🔥2🥰2
ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ወደ ተቋሙ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎችን ለመቀበል በአዲስ አበባ እና በአዳማ ከተሞች አስተባባሪዎችን በመመደብ የትራንስፖርት አገልግሎት እገዛ ለተማሪዎቹ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡

ከላይ በምስሉ ላይ የተቀመጡት የስልክ ቁጥሮችን ብቻ በመጠቀም እገዛ ማግኘት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል፡፡

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርታቸውን በተቋሙ እንዲከታተሉ የተመደቡ አዲስ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ከጥቅምት 05-08/2019 ዓ.ም እንደሆነ መግለጹ ይታወቃል።

https://t.me/httpentra