Students channel
3.53K subscribers
721 photos
12 videos
178 files
723 links
Stay will be Positive Attitude 😎
Download Telegram
ለ ሁሉም የ freshman year students

✅  አንድ ነገር ግን በጣም ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው አሁን ወደ uv ግቡ ለተባላችሁ እና ምደባ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ University የሚያጋጥሟቹህ ነገሮች
👉  በደንብ አስቡበት university ከገባችሁ በሗላ especially first semester ላይ በጣም መጠንቀቅ የሚያስፈልገው time ነው በሂወታችሁ ውስጥ ሁሉ ነገር የሚበላሸውም የሚስተካከለውም በዚህ ወቅት ነው then ትንሽ second semester ልታስተካክሉት ትችላላችሁ first semester ያበላሻችሁትን በታምር ሂወታችሁን እንዳታበላሹት everything ከዚህ year በሗላ ይደርሳል focus on yourself and ur goal that's it ማለት university ከባድ year ልታሳልፉበት የምትችሉት በዚህ አመት ነው ምንም የምታቁት ነገር የለም ስለ አጠናን እስታይል፣ ስለ ፈተና አወጣጥ ፣ ምን ምን መምህራን እንደሚያጋጥማችሁ i swear they are totally different from highschool teacher . የ ሰው ልጅ በሁለት አይነት መንገድ እራሱን ያስተምራል አንድ በራሱ ሁለት ከሰው ይማራል እራሳቹን በተቻለ መጠን ከሰው ለመማር ሞክሩ አለበለዚያ መልሶ ያስከፍላችሗል ።
👉 University ውስጥ ብዙ ነገሮች ይወራሉ እነሱም ቶሎ ነው ወሬው የሚዛመተው ከነሱም መካከል ፈተና ሲደርስ ስለ ፈተና በጣም ብዙ ነገሮች ይወራሉ እዚህ ጋር don't be foolish እሽ በቃ በተቻላችሁ መጠን ቀድማችሁ ለመጨረስ ሞክሩ እያዳንዷን ነገር አጣርታችሁ አድርጉ እና just ያላመናችሁበትን social media ውስጥ አትሁኑ just በደንብ የምትጠቀሙበትን ለዩ እና በጣም ወሳኝ ነው አሪፍ ወይም የሚያስፈልግ መርጃ ይዞ መንቀሳቀስ like አንዳንዶች ተማሪን attract ለማድረግ even exam ሲለቁ አመተምህረት የተሳሳተ ሊለቁ ይችላሉ እና ብዙ .....  ስህተታችሁ ደግሞ የሚሆነው cgpa ላይ ነው then department አመራረጥ ላይ ነው ሁሉም ተያያዥነት አላቸው then ደግሞ NG መባል ሲወራ ቀላል ይመስላል ግን በቃ የልጅነት ህልማችሁን ነው የሚያጨልመው በተቻለን መጠን እናስረዳለን ግን የምንልከውን በደንብ የማያነብም አለ አምና ብዙ ተማሪ በ inbox የሚለኝ ነገር ነው ካለፈ በሗላ ነው ፁሁፉ እራሱ ምን እንደሚል የሚገባቸው በደንብ የተረዱኝ ግን they did great በሂወታቸው ላይ እና life ይቀጥላል ከስተታችሁ ቢሆን እየተማራችሁ ግን እንዳልኳችሁ ከሰው ተማሪ በቃ ተመሳሳይ ነው ትንሽ ብቻ ነው የሚቀየረው ሁሉም ነገር university ውስጥ
👉 ሴቶች please focus on ur goal እሽ እስኪ እዩት ስንት ተማሪ ነው በ inbox ያወራችሁ 😂 don't be foolish ማንም ወንድ ግድ አይሰጠውም ለናንተ ሲሰክሷቹሁ ነው 🫣 even you don't  believe me check it pp እየቀየራችሁ maybe the same man ልጀነጅናችሁ ይችላል ደግሞም ትደርሱበታላችሁ first cgpa እስከ ምትመረቁ ድረስ እሷን ነው የምትጠቀሙት so ሰቀል አድርጓት
👉 እና don't expect too much እራሳችሁንም ልታጡ ትችላላችሁ just as much as you can do it እና በምትከተሉት እምነት ጠንክሩ እሱ ይሞለዋል የቀረውን 🙏
👉 እና እንዳንኳችሁ first semester በጣም ወሳኝ ነው ከዚያ በሗላ እየከበደ ነው የሚመጣው so በደንብ ለመስራት ሞክሩ ። ምን ምን ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ምን ምን ማጥናት እንዳለባችሁ በተቻለ መጠን እናሳውቃለን🙏🙏

https://t.me/httpentra
❤7
ዘንድሮ ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሪሚዲያል ተማሪዎች ተቀብለዋል

ዘንድሮ የትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች በግዚያዊነት አገልግሎት ስላማይሰጡ ይሆናል jimma እና Haramaya university ምደባ የተካሄደው


ሀዋሳ የደረሳቹ አላቹ ??????

https://t.me/httpentra
📢 ማስታወቂያ
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
 
1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
 
የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉
https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡
https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።
 
2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
 
👉
https://student.ethernet.edu.et/view-placement  
3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ
https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።
 
#ትምህርት_ሚኒስቴር

https://t.me/httpentra
❤1👍1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!
❤7🥰2
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና መመዝገቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።

የኦንላይን መመዝገቢያ ቁጥር እና የይለፍ ኮድ በመግቢያ ፈተና ወቅት በተሰጣችሁ ኢሜይል የተለካላችሁ መሆኑ ተገልጿል።

የተመደባችሁበትን የማደሪያ ህንጻ ቁጥር እና የዶርም ቁጥር
estudent.astu.edu.et ላይ በመግባትና የተሰጣችሁን Username እና Password በመጠቀም መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

https://t.me/httpentra
❤4👍1🔥1🦄1
ቀን፡ 21/01/2019 ዓ.ም
የተራዘመ ማስታዎቂያ
በ 2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ 2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመትና የአቅም ማሻሻያ  ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ስም ዝርዝራችሁ ስላልደረሰን የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ነው፡፡

  የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

https://t.me/httpentra
❤4👍2🦄1
#MoE

በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

https://t.me/httpentra
🔥3🥰2😘1
#InjibaraUniversity

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የ2ኛ ዲግሪ (በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች) እንዲሁም የ3ኛ ዲግሪ (በመደበኛ መርሐግብር) ትምህርት ለመከታተል ያመለከታችሁ በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 25-27/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ የተባለ ሲሆን፣ ትምህርት መስከረም 28/2019 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡


https://t.me/httpentra
🔥4😱1🙊1
🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ #የጥሪ_ማስታወቂያ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ሁሉም የፍሬሽማን ተማሪዎች

📅 የምዝገባ ቀን፦ ጥቅምት 4–5፣ 2019 ዓ.ም.

📍 በተመደባችሁበት ካምፓስ ምዝገባችሁን ያካሂዱ። ማለትም

👉 የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Sciences) ተማሪዎች በInstitute of Technology ይመዘገባሉ

👉የማህበራዊ ሳይንስ (Social Sciences) ተማሪዎች በCollege of Agriculture and Veterinary Medicine, Jimma University ይመዘገባሉ

የመግቢያ ቁጥራችሁን (Admission Number) በመጠቀም ወደ ዩኒቨርሲቲው ፖርታል በመግባት የዶርሚተሪ፣ ካፍቴሪያ እና ሴክሽን ምደባችሁን ማየት ትችላላችሁ። መረጃው በቀጣይ ቀናት በፖርታሉ ላይ ይጫናል
https://portal.ju.edu.et

📄 ይዘው የምትመጡት :

የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት/ሰርተፊኬት
4 የፓስፖርት ፎቶ
የአልጋ ልብስ እና የስፖርት ልብስ

⚠️ Remedial ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ወደፊት ይገለጻል።

https://t.me/httpentra
👍3🥰2🙉1
#የጥሪ_ማስታወቂያ #RayaUniversity

ለራያ ዩኒቨርሲቲ ነባርና የሪሚዲያል ፈተና ያለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ
ራያ ዩኒቨርሲቲ እንኳን ለ2019 ዓ.ም በሰላም አደረሳችሁ እያለ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ1ኛ ወሰነ ትምህርት የነባር እና በ2018 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል መርሃ-ግብር ወስዳችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 16-18/2019 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጂስትራር ጽሕፈት ቤት በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ ያሳውቃል።

ማሳሰቢያ፦

👉1) ከላይ ከተጠቀሱት የመመዝገቢያ ቀናት በፊትም ሆነ በኋላ የሚመጡ ተማሪዎችን የማናስተናግድ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

👉2) ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ እና ሌሎች ለመማር የሚያገለግሉ የትምህርት ቁሳቁስ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን።

የራያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጂስትራር ጽሕፈት ቤት

https://t.me/httpentra
🥰4🤝3👍1
#የጥሪ_ማስታወቂያ

ቀብሪደሃር ዪኒቨርሲቲ በ2019 አዲስ የተመደቡ (freshman) ተማሪዎች ፣ በ2018 ሪሚድያል ፕሮግራም ተከታትለዉ ማለፊያ ዉጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እንዲሁም በ 2019 ዓ.ም በሪሚድያል ፕሮግራም ወደ ዩኒቨርስቲው የተመደቡ ተማሪዎች ወደ ጊቢ የሚገቡበት ቀናት ጥቅምት 2 እና 3 /2019 መሆኑን አሳዉቀዋል።

ሙሉ መረጃው ከላይ በምስሉ ላይ ተያይዟል።

https://t.me/httpentra
🔥4😁2👍1👌1
የጥሪ_ማስታወቂያ #Haramaya_univ

በ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርታችሁን በሀረማያ ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ የተመደባችሁ አዲስ ቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፣ ከጥቅምት 05 እስከ 08፣ 2019 ዓ.ም. ሀረማያ በሚገኘው የዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ በአካል ተገኝታችሁ ሪፖርት እንድታደርጉ እናሳውቃለ

ማሳሰቢያ፦
1ኛ) ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ፡ አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎችንና ቁሳቁሶች፦
የ8ኛ ክፍል ሰርቲፍኬት ካርድ፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት እና የ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ሰርቲፍኬት (ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ)፣
6 ፓስፖርት መጠን ያላቸው ኑርድ ፎቶግራፎች፣
የግል መጠቀሚያ ብርድልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ።

2ኛ) በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱትን የትምህርት ማስረጃዎችና ፎቶግራፍ ስካን (Scan) በማድረግ በሶፍት ኮፒ (Soft Copy) ይዛችሁ መምጣት ይኖርባቸኋል።

3ኛ) ተማሪዎች የመኝታ ክፍል ድልድላችሁን የ12ኛ ክፍል መለያ ቁጥራችሁን (Admission Number) በዩኒቨርሲቲው ድረ-ገጽ (
www.haramaya.edu.et⁠�) በመግባት ማወቅ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

4ኛ) ዩኒቨርሲቲው ጥሪ ካደረገባቸው ቀናት በፊትም ሆነ ዘግይተው የሚመጡ ተማሪዎችን የማያስተናግድ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል።

https://t.me/httpentra
🔥3🥰2❤1🤷‍♂1👍1👌1
ለመጀመሪያ አመት ተማሪዎች ጥሪ ያደረጉ ዩኒቨርስቲዎች

1,Jimmaa University ጥቅምት 4 እና 5

2,Hawassa University ጥቅምት 3 እና 4

3,Haramaya University ጥቅምት 5-8

4,Kabridahar University ጥቅምት 2 እና 3

5,Raya University ጥቅምት 16-18

6,Debark University- መስከረም 28-29


https://t.me/httpentra
🔥5✍2👍1🙈1
ተራዝሟል❗️#Debark_University

በ 2019 በደባርቅ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ከመስከረም  28-29/2019 መሆኑን ዩኒቨርስቲው የገለጸ  ቢሆንም የ ሬሜዲያል ተማሪዎች መረጃ ከትምህርት ሚኒስቴር ያልተላከ በመሆኑ ጥሪው ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ዩኒቨርስቲው ዛሬ ባወጣው ማስታወቂያ አሳውቋል።


https://t.me/httpentra
🥰2👍1🔥1
Students channel
https://t.me/httpentra
#UoG

በ2019 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በተመሳሳይ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥቅምት 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
● ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
● የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
● አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

የምዝገባ ቦታ፡-
● ለማኅበራዊ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በማራኪ ግቢ
● ለተፈጥሮ ሳይንስ መስክ መደበኛ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ
● ለድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች በግቢው ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች

አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሰቲው ከመሔዳችሁ በፊት በኦንላይን (
Registration.uog.edu.et) ምዝገባችሁን እንድትፈጸሙ ተብሏል። (የምዝገባ ሒደቱ ቅደም ተከተልን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)

https://t.me/httpentra
🥰2🔥1
#DillaUniversity

ለዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በሙሉ፡-

​ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን የድህረ-ምረቃ፣ ቅድመ-ምረቃ እና የሪሜዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች የመመዝገቢያ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 

⚡️በ 2019 ዓ.ም አዲስ ሪሚዲያል ተማሪዎች ጥቅምት 19-20/2019 ዓ.ም

⚡️ በ 2018 ዓ.ም ሪሚድያል ተከታትላችሁ ማለፊያ ነጥብ ያመጣችሁ እና በ 2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ Freshman ተማሪዎች ጥቅምት 5-6/2019 ዓ.ም

⚡️ 2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ ለመማር ተቀባይነት ያገኛችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥቅምት 5-6/2019 ዓ.ም

https://t.me/httpentra
🔥1🥰1😡1
የጥሪ ማስታወቂያ
#Odabultum_University

ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ በ2019 የትምህርት ዘመን  የፍሬሽማን ተማሪዎች እና በ2018 ሪሜድያል ተምራችሁ ያለፉችሁ ተማሪዎች  የመመዝገቢያ ጊዜ ጥቅምት4 እና 5 መሆኑን እሳውቋል።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማያስተናግድ መሆኑን ገልፆል።

ተጨማሪ መረጃዎች ምስሉ ላይ ተያይዟል።

https://t.me/httpentra
🔥2❤1
✅Selale University

1. በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ ፕሮግራም የተመደባችሁ

2. በ2018 ዓ.ም በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የረሜዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡

እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ እያልን ምዝገባ የሚካሄደው ጥቅምት 4 እና 5/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን።

ሌሎችም እንዲጠቀሙ Share አርጉላቸዉ!

https://t.me/httpentra
🔥2😁1
#MizanTepiUniversity

በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሃ-ግብር ተማሪዎች እና በ 2018 በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲያችን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች በሙሉ
​የ2019 የትምህርት ዘመን ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 09 እና 10 መሆኑን እየገለጽን፤

የመመዝገቢያ ቦታ :-

​1ኛ. ማህበራዊ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ሚዛን-አማን በሚገኘው ዋናው ግቢ

​2ኛ. ተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት መስክ ለተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

ማሳሰቢያ

​በዩኒቨርሲቲያችን በሪሜዲያል/እርምጃ "ማሻሻያ"ፕሮግራም ለተመደባችሁ ተማሪዎች መመዝገቢያ ወቅት ወደፊት ሌላ ጥሪ ማስታወቂያ የምናሳውቃችሁ መሆኑን እየገለጽን፤

ለምዝገባ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➻ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➻ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➻ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
➻ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።

https://t.me/httpentra
🔥2✍1❤1🥰1