Students channel
3.54K subscribers
721 photos
12 videos
178 files
723 links
Stay will be Positive Attitude 😎
Download Telegram
ተራዝሟል❗️

ጂንካ ዩኒቨርስቲ በ 2018 በጂንካ ዩኒቨርስቲ በሬሜዲያል ሲማሩ ለቆዩና አዲስ ለተመደቡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎቹ አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

https://t.me/httpentra
👍2
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የፍሬሽማን ተማሪዎች ወደ ግቢ የቅበላ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡

ተማራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 14 እና 15/2019 ዓ.ም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የ2019 ትምህርት ዘመን ካሌንደር ያሳያል፡፡

https://t.me/httpentra
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደቡ እንዲሁም ለነባር ተማሪዎች በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይገለጻል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በጠየቁት መሠረት፣ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ፣ የትምህርት ሒደታችሁ እንዳይስተጓጎል እና ደኅንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል በጊዜያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ" ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

"ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን" ብሏል ሚኒስቴሩ ባጋራው አጭር መልዕክት፡፡

በተለያየ ምክንያት ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል የሚፈልጉ
#ነባር እና #አዲስ ተማሪዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የጠቆመው ትምህርት ሚኒስቴር፤ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ከ5 ሺህ በላይ ነባር ተማሪዎች የዝውውር ማመልከቻ እንዳስገቡ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/httpentra
#MoE
 
የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇
https://student.ethernet.edu.et/preferences
 
https://t.me/httpentra
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የተቋሙ ነባር የቅድመ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 28 እና 29/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት (Freshman) እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

https://t.me/httpentra
#የጥሪ_ማስታወቂያ #ASTU

ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የ 2019 መደበኛ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ አዲስ ገቢ  እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ

ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን መስከረም 20 እና 21/2019 ሲሆን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ግቢው ስትሄዱ

የ 12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፍኬት
ከ 9-12 የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
4 ፓስፓርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ
አንሶላ እና  ብርድ ልብስ
የስፖርት ትጥቅና ጫማ ይዛችሁ እንድትመጡ አስታውቋል።

ማሳሰቢያ: ከመግቢያ ቀን ቀድሞም ዘግይቶም የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም።


https://t.me/httpentra
🥰3
መልካም ዜና ለወላጆች
ብርሃን የጥናት ማዕከል እንደተለመደው በ2019 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የሚሆን የኢንተራንስ ማዘጋጃ ቲቶር በመደበኛ መርሐ ግብር ከሰኞ እስከ አርብ እና በቅዳሜና በእሑድ መርሐግብር አዘጋጅቷል ።
ያለን ቦታ የተወሰነ በመሆኑ አስቀድመው ልጆችዎን ያስመዝግቡ ።
አድራሻ ፦ ከአጠና ተራ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ ያለ ሕንጻችን

ለበለጠ መረጃ ፦ 0986777407
                          0937329987 ይደውሉ
የቴሌግራም አድራሻ ፦ @MWYSMGK
                             ፦ @mogeswy
❤4🔥1
"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስ

ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡

ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡

ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም።

ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል።

የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ (ሰርኩላሩ ከላይ ተያይዟል፡፡)

https://t.me/httpentra
❤5🔥1
ለ ሁሉም የ freshman year students

✅  አንድ ነገር ግን በጣም ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው አሁን ወደ uv ግቡ ለተባላችሁ እና ምደባ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ University የሚያጋጥሟቹህ ነገሮች
👉  በደንብ አስቡበት university ከገባችሁ በሗላ especially first semester ላይ በጣም መጠንቀቅ የሚያስፈልገው time ነው በሂወታችሁ ውስጥ ሁሉ ነገር የሚበላሸውም የሚስተካከለውም በዚህ ወቅት ነው then ትንሽ second semester ልታስተካክሉት ትችላላችሁ first semester ያበላሻችሁትን በታምር ሂወታችሁን እንዳታበላሹት everything ከዚህ year በሗላ ይደርሳል focus on yourself and ur goal that's it ማለት university ከባድ year ልታሳልፉበት የምትችሉት በዚህ አመት ነው ምንም የምታቁት ነገር የለም ስለ አጠናን እስታይል፣ ስለ ፈተና አወጣጥ ፣ ምን ምን መምህራን እንደሚያጋጥማችሁ i swear they are totally different from highschool teacher . የ ሰው ልጅ በሁለት አይነት መንገድ እራሱን ያስተምራል አንድ በራሱ ሁለት ከሰው ይማራል እራሳቹን በተቻለ መጠን ከሰው ለመማር ሞክሩ አለበለዚያ መልሶ ያስከፍላችሗል ።
👉 University ውስጥ ብዙ ነገሮች ይወራሉ እነሱም ቶሎ ነው ወሬው የሚዛመተው ከነሱም መካከል ፈተና ሲደርስ ስለ ፈተና በጣም ብዙ ነገሮች ይወራሉ እዚህ ጋር don't be foolish እሽ በቃ በተቻላችሁ መጠን ቀድማችሁ ለመጨረስ ሞክሩ እያዳንዷን ነገር አጣርታችሁ አድርጉ እና just ያላመናችሁበትን social media ውስጥ አትሁኑ just በደንብ የምትጠቀሙበትን ለዩ እና በጣም ወሳኝ ነው አሪፍ ወይም የሚያስፈልግ መርጃ ይዞ መንቀሳቀስ like አንዳንዶች ተማሪን attract ለማድረግ even exam ሲለቁ አመተምህረት የተሳሳተ ሊለቁ ይችላሉ እና ብዙ .....  ስህተታችሁ ደግሞ የሚሆነው cgpa ላይ ነው then department አመራረጥ ላይ ነው ሁሉም ተያያዥነት አላቸው then ደግሞ NG መባል ሲወራ ቀላል ይመስላል ግን በቃ የልጅነት ህልማችሁን ነው የሚያጨልመው በተቻለን መጠን እናስረዳለን ግን የምንልከውን በደንብ የማያነብም አለ አምና ብዙ ተማሪ በ inbox የሚለኝ ነገር ነው ካለፈ በሗላ ነው ፁሁፉ እራሱ ምን እንደሚል የሚገባቸው በደንብ የተረዱኝ ግን they did great በሂወታቸው ላይ እና life ይቀጥላል ከስተታችሁ ቢሆን እየተማራችሁ ግን እንዳልኳችሁ ከሰው ተማሪ በቃ ተመሳሳይ ነው ትንሽ ብቻ ነው የሚቀየረው ሁሉም ነገር university ውስጥ
👉 ሴቶች please focus on ur goal እሽ እስኪ እዩት ስንት ተማሪ ነው በ inbox ያወራችሁ 😂 don't be foolish ማንም ወንድ ግድ አይሰጠውም ለናንተ ሲሰክሷቹሁ ነው 🫣 even you don't  believe me check it pp እየቀየራችሁ maybe the same man ልጀነጅናችሁ ይችላል ደግሞም ትደርሱበታላችሁ first cgpa እስከ ምትመረቁ ድረስ እሷን ነው የምትጠቀሙት so ሰቀል አድርጓት
👉 እና don't expect too much እራሳችሁንም ልታጡ ትችላላችሁ just as much as you can do it እና በምትከተሉት እምነት ጠንክሩ እሱ ይሞለዋል የቀረውን 🙏
👉 እና እንዳንኳችሁ first semester በጣም ወሳኝ ነው ከዚያ በሗላ እየከበደ ነው የሚመጣው so በደንብ ለመስራት ሞክሩ ። ምን ምን ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ምን ምን ማጥናት እንዳለባችሁ በተቻለ መጠን እናሳውቃለን🙏🙏

https://t.me/httpentra
❤7
ዘንድሮ ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሪሚዲያል ተማሪዎች ተቀብለዋል

ዘንድሮ የትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች በግዚያዊነት አገልግሎት ስላማይሰጡ ይሆናል jimma እና Haramaya university ምደባ የተካሄደው


ሀዋሳ የደረሳቹ አላቹ ??????

https://t.me/httpentra
📢 ማስታወቂያ
 
በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የመግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ እና በ2019 ዓ.ም በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
 
1. በ2018 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በሪሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
 
የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
👉
https://student.ethernet.edu.et/view-placement
ቅሬታ ለማቅረብ፡
https://student.ethernet.edu.et/complaints ተጠቀሙ።
 
2. በዝውውር በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በሚከተለው ማስፈንጠሪያ (Link) በመግባት መመልከት ትችላላችሁ፦
 
👉
https://student.ethernet.edu.et/view-placement  
3. በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች፡ በጊዜያዊነት የተመደባችሁበትን ዩኒቨርሲቲ በ
https://student.ethernet.edu.et/university-transfer/ ማስፈንጠሪያ በመግባት የራሳችሁን ፋይዳ (የመለያ ቁጥር) በመጠቀም መመልከት የምትችሉ መሆናችሁን እንገልጻለን።
 
#ትምህርት_ሚኒስቴር

https://t.me/httpentra
❤1👍1
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ!!!
❤7🥰2
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#ASTU

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ አዲስ ገቢ የቅድመ-ምረቃ ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና መመዝገቢያ ቀናት መስከረም 20 እና 21/2019 ዓ.ም መሆኑ ይታወቃል።

የኦንላይን መመዝገቢያ ቁጥር እና የይለፍ ኮድ በመግቢያ ፈተና ወቅት በተሰጣችሁ ኢሜይል የተለካላችሁ መሆኑ ተገልጿል።

የተመደባችሁበትን የማደሪያ ህንጻ ቁጥር እና የዶርም ቁጥር
estudent.astu.edu.et ላይ በመግባትና የተሰጣችሁን Username እና Password በመጠቀም መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።

https://t.me/httpentra
❤4👍1🔥1🦄1
ቀን፡ 21/01/2019 ዓ.ም
የተራዘመ ማስታዎቂያ
በ 2018 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁና በ 2019 ዓ.ም አዲስ ከትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ የ1ኛ ዓመትና የአቅም ማሻሻያ  ተማሪዎች ምዝገባ መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ይከናወናል ተብሎ የነበረ ቢሆንም ስም ዝርዝራችሁ ስላልደረሰን የምዝገባ ቀኑ ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡- የሌሎች ነባር መደበኛ ተማሪዎች ምዝገባ ከዚህ ቀደም በተገለፀው መሰረት መስከረም 26 እና 27/2019 ዓ.ም ነው፡፡

  የወልድያ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጅስትራር ጽ/ቤት

https://t.me/httpentra
❤4👍2🦄1
#MoE

በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ስትማሩ የነበራችሁ ነባር ተማሪዎች እና አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎችን በጊዜያዊነት ከክልሉ ውጪ ወዳሉ ዩኒቨርሲቲዎች ከመመደብ ጋር ተያይዞ የተነሱ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ እየሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በምደባው ሒደት የቀረቡ ቅሬታዎችን የማጥራት ሥራ ተጠናቆ ተማሪዎቹ በጊዜያዊነት ወደተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች የሚገቡበት ቀን ይፋ እስከሚደረግ ድረስ፣ ተማሪዎቹ ባሉበት ሆነው በትዕግስት እንዲጠብቁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

https://t.me/httpentra
🔥3🥰2😘1
#InjibaraUniversity

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም የ2ኛ ዲግሪ (በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች) እንዲሁም የ3ኛ ዲግሪ (በመደበኛ መርሐግብር) ትምህርት ለመከታተል ያመለከታችሁ በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ከመስከረም 25-27/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ የተባለ ሲሆን፣ ትምህርት መስከረም 28/2019 ዓ.ም የሚጀመር መሆኑ ተገልጿል፡፡


https://t.me/httpentra
🔥4😱1🙊1
🎓 ጅማ ዩኒቨርሲቲ #የጥሪ_ማስታወቂያ

በጅማ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ ሁሉም የፍሬሽማን ተማሪዎች

📅 የምዝገባ ቀን፦ ጥቅምት 4–5፣ 2019 ዓ.ም.

📍 በተመደባችሁበት ካምፓስ ምዝገባችሁን ያካሂዱ። ማለትም

👉 የተፈጥሮ ሳይንስ (Natural Sciences) ተማሪዎች በInstitute of Technology ይመዘገባሉ

👉የማህበራዊ ሳይንስ (Social Sciences) ተማሪዎች በCollege of Agriculture and Veterinary Medicine, Jimma University ይመዘገባሉ

የመግቢያ ቁጥራችሁን (Admission Number) በመጠቀም ወደ ዩኒቨርሲቲው ፖርታል በመግባት የዶርሚተሪ፣ ካፍቴሪያ እና ሴክሽን ምደባችሁን ማየት ትችላላችሁ። መረጃው በቀጣይ ቀናት በፖርታሉ ላይ ይጫናል
https://portal.ju.edu.et

📄 ይዘው የምትመጡት :

የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት/ሰርተፊኬት
4 የፓስፖርት ፎቶ
የአልጋ ልብስ እና የስፖርት ልብስ

⚠️ Remedial ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ወደፊት ይገለጻል።

https://t.me/httpentra
👍3🥰2🙉1