Students channel
3.53K subscribers
722 photos
12 videos
178 files
724 links
Stay will be Positive Attitude 😎
Download Telegram
#GonderUniversity

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛና ተከታታይ መርሐግብር ነባር ተማሪዎች (2ኛ ዓመት እና በላይ) የ2019 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት መስከረም 20/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

https://t.me/httpentra
🥰1
#የጥሪ_ማስታወቂያ #DebreMarkosUniversity

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የአንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የነበራችሁ ነባር የዋናው ግቢ እና የቡሬ ካምፓስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም ብቻ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

https://t.me/httpentra
❤3
#የጥሪ_ማስታወቂያ#Woldia_University

ለወልዲያ ዩኒቨርስቲ ለአዲስ ገቢና በ 2018 ሬሜዲያል ለነበራችሁ፤ በ 2019 በሬሜዲያል ወደ ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ለምትመደቡ እና ለነባር መደበኛ (Senior) ተማሪዎች የወጣ የጥሪ ማስታወቂያ

የመግቢያ ቀን መስከረም 26 እና 27

ተጨማሪ መረጃ በ ምስሉ ላይ ተያይዟል
🔥2
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አድርጓል።

የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ይመልከቱ 👇
https://student.ethernet.edu.et/view-placement

በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንድታቀርቡ ተብሏል።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇
https://student.ethernet.edu.et/complaints

በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመሔድ የሚቀርብ የምደባ ቅሬታን የማያስተናገድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቅሬታ በምታስገቡበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

https://t.me/httpentra
Placement ያያቹህ የት ደረሳቹህ????
ተራዝሟል❗️

ጂንካ ዩኒቨርስቲ በ 2018 በጂንካ ዩኒቨርስቲ በሬሜዲያል ሲማሩ ለቆዩና አዲስ ለተመደቡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎቹ አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

https://t.me/httpentra
👍2
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የፍሬሽማን ተማሪዎች ወደ ግቢ የቅበላ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡

ተማራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 14 እና 15/2019 ዓ.ም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የ2019 ትምህርት ዘመን ካሌንደር ያሳያል፡፡

https://t.me/httpentra
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደቡ እንዲሁም ለነባር ተማሪዎች በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይገለጻል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በጠየቁት መሠረት፣ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ፣ የትምህርት ሒደታችሁ እንዳይስተጓጎል እና ደኅንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል በጊዜያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ" ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

"ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን" ብሏል ሚኒስቴሩ ባጋራው አጭር መልዕክት፡፡

በተለያየ ምክንያት ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል የሚፈልጉ
#ነባር እና #አዲስ ተማሪዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የጠቆመው ትምህርት ሚኒስቴር፤ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ከ5 ሺህ በላይ ነባር ተማሪዎች የዝውውር ማመልከቻ እንዳስገቡ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/httpentra
#MoE
 
የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇
https://student.ethernet.edu.et/preferences
 
https://t.me/httpentra
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የተቋሙ ነባር የቅድመ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 28 እና 29/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት (Freshman) እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

https://t.me/httpentra
#የጥሪ_ማስታወቂያ #ASTU

ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የ 2019 መደበኛ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ አዲስ ገቢ  እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ

ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን መስከረም 20 እና 21/2019 ሲሆን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ግቢው ስትሄዱ

የ 12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፍኬት
ከ 9-12 የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
4 ፓስፓርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ
አንሶላ እና  ብርድ ልብስ
የስፖርት ትጥቅና ጫማ ይዛችሁ እንድትመጡ አስታውቋል።

ማሳሰቢያ: ከመግቢያ ቀን ቀድሞም ዘግይቶም የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም።


https://t.me/httpentra
🥰3
መልካም ዜና ለወላጆች
ብርሃን የጥናት ማዕከል እንደተለመደው በ2019 ዓ/ም 12ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የሚሆን የኢንተራንስ ማዘጋጃ ቲቶር በመደበኛ መርሐ ግብር ከሰኞ እስከ አርብ እና በቅዳሜና በእሑድ መርሐግብር አዘጋጅቷል ።
ያለን ቦታ የተወሰነ በመሆኑ አስቀድመው ልጆችዎን ያስመዝግቡ ።
አድራሻ ፦ ከአጠና ተራ ወደ አዲስ ሰፈር በሚወስደው መንገድ ላይ ያለ ሕንጻችን

ለበለጠ መረጃ ፦ 0986777407
                          0937329987 ይደውሉ
የቴሌግራም አድራሻ ፦ @MWYSMGK
                             ፦ @mogeswy
❤4🔥1
"ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፡፡ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት"፡፡ - ትምህርት ሚኒስ

ትምህርት ሚኒስቴር "የተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር አፈጻጸምን" አስመልክቶ በቀን 07/01/2019 ዓ.ም ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) የተፈረመ ሰርኩላር ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ልኳል፡፡

ሰርኩላሩ፤ ዩኒቨርሲቲዎቹ ከተማሪዎች ቅበላ፣ የትምህርት መስክ ምደባ እና የተማሪዎች ዝውውር ጋር በተያያዘ ሊከተሏቸው የሚገቡ አሠራሮችን አስቀምጧል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች በሚኒስቴሩ ከተላለፈ የምደባ ውጤት ውጭ ተማሪን በራሳቸው ተነሳሽነት መቀበል፣ የተመደበበትን ተቋም መቀየር ወይም በሌላ ተቋም የተመደበን ተማሪ ያለአግባብ መመዝገብ እንደማይችሉ ተገልጿል፡፡

ተቋማቱ ከተቀመጠው የምደባ መስፈርት ውጭ በግለሰብ ጥያቄ፣ በልዩ ትዕዛዝ ወይም ለአንድ ተማሪ ብቻ በሚደረግ ልዩ አሠራር የትምህርት መስክ ምደባ መቀየር አይችሉም።

ከአንድ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሌላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪ ዝውውር የሚፈፀመው የላኪው እና የተቀባዩ ዩኒቨርሲቲ ስምምነት ሲኖር ብቻ ሲሆን፣ ዝውውሩ ሲፈፀም ትምህርት ሚኒስቴር በደብዳቤ እንዲያውቀው መደረግ አለበት ተብሏል።

የዝውውር ጥያቄ የሚስተናገደው ተማሪው በተመደበበት ተቋም ቢያንስ አንድ ሴሚስቴር የተማረ እና ከፕሮግራሙ 50 በመቶ በላይ ያላጠናቀቀ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡

በሌላ በኩል ከመንግሥት ወደ ግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዝውውር ሊፈፀም የሚችል ሲሆን፣ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ወደ መንግሥት ዩኒቨርሲቲ ዝውውር ማድረግ እንደማይቻል ተገልጿል፡፡ (ሰርኩላሩ ከላይ ተያይዟል፡፡)

https://t.me/httpentra
❤5🔥1
ለ ሁሉም የ freshman year students

✅  አንድ ነገር ግን በጣም ማስጠንቀቂያ ለመስጠት ነው አሁን ወደ uv ግቡ ለተባላችሁ እና ምደባ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ University የሚያጋጥሟቹህ ነገሮች
👉  በደንብ አስቡበት university ከገባችሁ በሗላ especially first semester ላይ በጣም መጠንቀቅ የሚያስፈልገው time ነው በሂወታችሁ ውስጥ ሁሉ ነገር የሚበላሸውም የሚስተካከለውም በዚህ ወቅት ነው then ትንሽ second semester ልታስተካክሉት ትችላላችሁ first semester ያበላሻችሁትን በታምር ሂወታችሁን እንዳታበላሹት everything ከዚህ year በሗላ ይደርሳል focus on yourself and ur goal that's it ማለት university ከባድ year ልታሳልፉበት የምትችሉት በዚህ አመት ነው ምንም የምታቁት ነገር የለም ስለ አጠናን እስታይል፣ ስለ ፈተና አወጣጥ ፣ ምን ምን መምህራን እንደሚያጋጥማችሁ i swear they are totally different from highschool teacher . የ ሰው ልጅ በሁለት አይነት መንገድ እራሱን ያስተምራል አንድ በራሱ ሁለት ከሰው ይማራል እራሳቹን በተቻለ መጠን ከሰው ለመማር ሞክሩ አለበለዚያ መልሶ ያስከፍላችሗል ።
👉 University ውስጥ ብዙ ነገሮች ይወራሉ እነሱም ቶሎ ነው ወሬው የሚዛመተው ከነሱም መካከል ፈተና ሲደርስ ስለ ፈተና በጣም ብዙ ነገሮች ይወራሉ እዚህ ጋር don't be foolish እሽ በቃ በተቻላችሁ መጠን ቀድማችሁ ለመጨረስ ሞክሩ እያዳንዷን ነገር አጣርታችሁ አድርጉ እና just ያላመናችሁበትን social media ውስጥ አትሁኑ just በደንብ የምትጠቀሙበትን ለዩ እና በጣም ወሳኝ ነው አሪፍ ወይም የሚያስፈልግ መርጃ ይዞ መንቀሳቀስ like አንዳንዶች ተማሪን attract ለማድረግ even exam ሲለቁ አመተምህረት የተሳሳተ ሊለቁ ይችላሉ እና ብዙ .....  ስህተታችሁ ደግሞ የሚሆነው cgpa ላይ ነው then department አመራረጥ ላይ ነው ሁሉም ተያያዥነት አላቸው then ደግሞ NG መባል ሲወራ ቀላል ይመስላል ግን በቃ የልጅነት ህልማችሁን ነው የሚያጨልመው በተቻለን መጠን እናስረዳለን ግን የምንልከውን በደንብ የማያነብም አለ አምና ብዙ ተማሪ በ inbox የሚለኝ ነገር ነው ካለፈ በሗላ ነው ፁሁፉ እራሱ ምን እንደሚል የሚገባቸው በደንብ የተረዱኝ ግን they did great በሂወታቸው ላይ እና life ይቀጥላል ከስተታችሁ ቢሆን እየተማራችሁ ግን እንዳልኳችሁ ከሰው ተማሪ በቃ ተመሳሳይ ነው ትንሽ ብቻ ነው የሚቀየረው ሁሉም ነገር university ውስጥ
👉 ሴቶች please focus on ur goal እሽ እስኪ እዩት ስንት ተማሪ ነው በ inbox ያወራችሁ 😂 don't be foolish ማንም ወንድ ግድ አይሰጠውም ለናንተ ሲሰክሷቹሁ ነው 🫣 even you don't  believe me check it pp እየቀየራችሁ maybe the same man ልጀነጅናችሁ ይችላል ደግሞም ትደርሱበታላችሁ first cgpa እስከ ምትመረቁ ድረስ እሷን ነው የምትጠቀሙት so ሰቀል አድርጓት
👉 እና don't expect too much እራሳችሁንም ልታጡ ትችላላችሁ just as much as you can do it እና በምትከተሉት እምነት ጠንክሩ እሱ ይሞለዋል የቀረውን 🙏
👉 እና እንዳንኳችሁ first semester በጣም ወሳኝ ነው ከዚያ በሗላ እየከበደ ነው የሚመጣው so በደንብ ለመስራት ሞክሩ ። ምን ምን ነገሮች እንደሚያስፈልጓችሁ ምን ምን ማጥናት እንዳለባችሁ በተቻለ መጠን እናሳውቃለን🙏🙏

https://t.me/httpentra
❤7
ዘንድሮ ጅማ ዩኒቨርስቲ እና ሀረማያ ዩኒቨርስቲ ሪሚዲያል ተማሪዎች ተቀብለዋል

ዘንድሮ የትግራይ ክልል ዩኒቨርስቲዎች በግዚያዊነት አገልግሎት ስላማይሰጡ ይሆናል jimma እና Haramaya university ምደባ የተካሄደው


ሀዋሳ የደረሳቹ አላቹ ??????

https://t.me/httpentra