Students channel
3.53K subscribers
722 photos
12 videos
178 files
724 links
Stay will be Positive Attitude 😎
Download Telegram
ADDIS ABABA UNIVERSITY
SELF SPONSORSHIP CUT OFF POINT

ለ Natural

1. Medicine 81
2. Dental Medicine 79.08
3. Software Engineering 77.67

ለ Social

1. BAIS 72.33
2. Law 71. 92
3. Political science 71.5

ውጤታችሁን ለማየት👇

https://admission.aau.edu.et/dashboard

https://t.me/httpentra
😁1
#GonderUniversity

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛና ተከታታይ መርሐግብር ነባር ተማሪዎች (2ኛ ዓመት እና በላይ) የ2019 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

ትምህርት መስከረም 20/2019 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

https://t.me/httpentra
🥰1
#የጥሪ_ማስታወቂያ #DebreMarkosUniversity

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የአንደኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ተማሪዎች የነበራችሁ ነባር የዋናው ግቢ እና የቡሬ ካምፓስ መደበኛ የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን የምዝገባ ጊዜ መስከረም 18 እና 19/2019 ዓ.ም ብቻ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

https://t.me/httpentra
❤3
#የጥሪ_ማስታወቂያ#Woldia_University

ለወልዲያ ዩኒቨርስቲ ለአዲስ ገቢና በ 2018 ሬሜዲያል ለነበራችሁ፤ በ 2019 በሬሜዲያል ወደ ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ለምትመደቡ እና ለነባር መደበኛ (Senior) ተማሪዎች የወጣ የጥሪ ማስታወቂያ

የመግቢያ ቀን መስከረም 26 እና 27

ተጨማሪ መረጃ በ ምስሉ ላይ ተያይዟል
🔥2
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ወስደው ውጤት ያመጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባን ይፋ አድርጓል።

የተመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ ይመልከቱ 👇
https://student.ethernet.edu.et/view-placement

በምደባው ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ቅሬታችሁን ይህ ምደባ ይፋ ከሆነበት ጀምሮ በአምስት ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን መረጃና ማስረጃ በማያያዝ እንድታቀርቡ ተብሏል።

ቅሬታ ለማቅረብ 👇
https://student.ethernet.edu.et/complaints

በአካል ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በመሔድ የሚቀርብ የምደባ ቅሬታን የማያስተናገድ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቅሬታ በምታስገቡበት ወቅት የሐሰት መረጃ፣ የተሳሳተ ማስረጃ ወይም የተጭበረበረ ሰነድ ማቅረብ በፍጹም የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

https://t.me/httpentra
Placement ያያቹህ የት ደረሳቹህ????
ተራዝሟል❗️

ጂንካ ዩኒቨርስቲ በ 2018 በጂንካ ዩኒቨርስቲ በሬሜዲያል ሲማሩ ለቆዩና አዲስ ለተመደቡ የመጀመሪያ አመት ተማሪዎቹ አድርጎት የነበረውን ጥሪ አራዝሟል።

https://t.me/httpentra
👍2
#EthiopianDefenceUniversity

የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የፍሬሽማን ተማሪዎች ወደ ግቢ የቅበላ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን ገልጿል፡፡

ተማራቂ ያልሆኑ ነባር ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ መስከረም 14 እና 15/2019 ዓ.ም እንደሆነ ዩኒቨርሲቲው ያወጣው የ2019 ትምህርት ዘመን ካሌንደር ያሳያል፡፡

https://t.me/httpentra
በትግራይ ክልል በሚገኙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አዲስ ለተመደቡ እንዲሁም ለነባር ተማሪዎች በጊዚያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይገለጻል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር

በትግራይ ክልል ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች በጠየቁት መሠረት፣ በክልሉ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ እስኪስተካከል ድረስ በጊዜያዊነት ከትግራይ ክልል ውጪ ወደሚገኙ ሌሎች የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እንድትመደቡ የሚደረግ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል፡፡

"በዚህ ጉዳይ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ሚኒስቴር በአካል መሔድ ሳይጠበቅባችሁ፣ የትምህርት ሒደታችሁ እንዳይስተጓጎል እና ደኅንነታችሁ ተጠብቆ ትምህርታችሁን በመደበኛነት እንድትቀጥሉ ለማስቻል በጊዜያዊነት የምትመደቡበትን ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ ይፋ እንደሚያደርግ" ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

"ያለው ነባራዊ ሁኔታ ሲስተካከል፣ መጀመሪያ በተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ተመልሳችሁ ትምህርታችሁን የምትቀጥሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን" ብሏል ሚኒስቴሩ ባጋራው አጭር መልዕክት፡፡

በተለያየ ምክንያት ትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መቀጠል የሚፈልጉ
#ነባር እና #አዲስ ተማሪዎችን በተመለከተ ከዩኒቨርስቲዎቹ ጋር እየተነጋገረ መሆኑን የጠቆመው ትምህርት ሚኒስቴር፤ ተማሪዎቹ በትዕግስት እንዲጠብቁ ጠይቋል፡፡

ከ5 ሺህ በላይ ነባር ተማሪዎች የዝውውር ማመልከቻ እንዳስገቡ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

https://t.me/httpentra
#MoE
 
የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምርጫ አድርጉ ተብሏል፡፡
 
በ2018 ዓ.ም የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምደባ ምርጫችሁን ከመስከረም 7-11/2019 ዓ.ም ድረስ እንድታደርጉ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመምረጥ 👇
https://student.ethernet.edu.et/preferences
 
https://t.me/httpentra
#DebreTaborUniversity

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሁሉም የተቋሙ ነባር የቅድመ እና የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው መስከረም 28 እና 29/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በ2019 ዓ.ም ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት (Freshman) እና የሪሚዲያል ተማሪዎች እንዲሁም በ2018 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን ምዝገባ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ የሚደረግ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

https://t.me/httpentra
#የጥሪ_ማስታወቂያ #ASTU

ለአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ የ 2019 መደበኛ ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ አዲስ ገቢ  እና ነባር ተማሪዎች በሙሉ

ምዝገባ የሚከናወንበት ቀን መስከረም 20 እና 21/2019 ሲሆን አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደ ግቢው ስትሄዱ

የ 12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፍኬት
ከ 9-12 የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት
4 ፓስፓርት ሳይዝ ፎቶ ግራፍ
አንሶላ እና  ብርድ ልብስ
የስፖርት ትጥቅና ጫማ ይዛችሁ እንድትመጡ አስታውቋል።

ማሳሰቢያ: ከመግቢያ ቀን ቀድሞም ዘግይቶም የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም።


https://t.me/httpentra
🥰3