Students channel
3.54K subscribers
723 photos
12 videos
178 files
725 links
Stay will be Positive Attitude 😎
Download Telegram
Remedial Result are now out
Check out everyone
ሰበር ዜና የ2018 ሪሜዲያል ውጤት ተለቋል

የ ሬሜዲያል ዉጤት Officially ተለቋል


https://t.me/httpentra
በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም Result https://result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት Remedial Examination ከሚለው ስር View Results የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤታቸውን ማየት የቻላሉ።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ " ሙሉ ውጤታችን Disqualified ተደርጓል " ያሉ በርካታ ተማሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል።

ተማሪዎቹ " ይፋ በተደረገው የፈተና ውጤት ላይ የገጠመን ከፍተኛ ችግር እንዲሰማልን እንፈልጋለን " ብለዋል።

ቅሬታቸውን ካቀረቡት መካከል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳንይንስ ተማሪዎች ውጤታቸው " ሙሉ በሙሉ Disqualified " የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ፥ በደብረ ብርሃን፣ ወሎ፣ አርባ ምንጭ፣ ሚዛን ቴፒ፣ ሰመራ፣ ባህርዳር፣ ወልቂጤ፣ ኦዳ ቡልቱም፣ ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የተለያዩ ተማሪዎች ውጤት ላይ ተመሳሳይ ችግር እንደገጠማቸው አመልክተዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር ቅሬታቸውን ተመልክቶ ምክንያቱን በመለየትና በማሳወቅ እንዲሁም በመመርመር አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።

https://t.me/httpentra
 
            Share share🙏🙏
❤1
🔔 Universty Placement

የ2018 ዓ.ም. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሀገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው የትምህርት መርሃ ግብር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግቢያ ውጤት ላስመዘገባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡-
 
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና የትምህርት መስክ ምርጫችሁን ከነሐሴ 28 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ከታች የተቀመጠውን ማስፈንጠሪያ (Link) በመጠቀም ምርጫችሁን ት/ቤት መሄድ ሳይጠበቅባችሁ ባላችሁበት ቦታ እራሳችሁ በመሙላት እንድታሳውቁ እንገልጻለን።

ማስፈንጠሪያ (Link)  
https://student.ethernet.edu.et/

ማሳሰቢያ፡- የህክምና፣ የአካል ጉዳተኝነት፣ ተመሳሳይ ጾታ ያላቸው መንትያዎች እና ከ6 ወር በታች ህፃን የሚያጠቡ እናቶች አስፈላጊውን ሕጋዊ ማስረጃ ማያያዝ ይኖርባችኋል።

https://t.me/httpentra
❤1
አንዳንዶቻቹ  ሪሜዲያል  ብማር ይሻላል ወይስ  diploma  ወይስ private ብሞላ ይሻላል  ብላቹ እየጠየቃቹ ነበር

የኔ ምክር  ሪሜዲያል እየተማራቹ  private  ሞልታቹ   መፈተን ትችላላቹ

https://t.me/httpentra
🫡3🔥1
✅ የጥሪ ማስታወቂያ

🔰 መቱ ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች ወደ ጊቢ የሚመለሱባቸዉ ቀናት መስከረም 7 እና 8 /2018 መሆኑን አሳዉቀዋል።

ትምህርት ሚጀመረው  መስከረም 11/2019 ዓ.ም

ሙሉ መረጃው ከላይ በምስሎቹ ላይ ተያይዘዋል።

https://t.me/httpentra
😢4
#Attention

ከዚህ ብኃላ የነባር ተማሪዎች ማለትም ሁለተኛ አመት እና እና ከዛ በላይ ያሉ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ ጥሪ በስፋት  ስለሚኖር በንቃት ቻናላችን ይከታተሉ ለሌሎች ሼር አድርጉ
  ‼️


♡        ❍ㅤ      ⎙       ⌲
ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ     ˢʰᵃʳᵉ

https://t.me/httpentra
#የጥሪ_ማስታወቂያ
#Debrebrehan_University

-በደብረ ብርሃን ዋናው ግቢ እና መሃል ሜዳ ካምፓስ ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ለነበራችሁ  ነባር ተማሪዎች በሙሉ

- የምዝገባ ጊዜ መስከረም 7 እና 8/ 2019ዓ.ም

- የአንደኛ አመት ተማሪዎች ጥሪ ለወደፊት እስኪገለፅ ድረስ በትዕግስት ጠብቁ

https://t.me/httpentra
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ የነባር የቅድመ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት መስከረም 09 እና 10/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በመሆኑም ነባር ተማሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ሪፖርት እንዲያደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

https://t.me/httpentra
❤1
✅የጥሪ ማስታወቂያ

ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ነባር  ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

1) የቅድመ ምረቃ  3ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ እንዲሁም የነባር  የድህረ ምረቃ ተማሪዎች ፤

2) የትምህርት ክፍል ምደባቸውን ያወቁ 2ኛ አመት ተማሪዎች(Anesthesia, Comprehensive Nursing, , Law, Midwifery, Pharmacy, Pre-medicine and Veterinary Medicine)
የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የመጀመሪያው ወሰነ ትምህርት ምዝገባ የሚካሄደው ከመስከረም 07-08/2019 ዓ.ም መሆኑን እየገለጽን ምዝገባ የሚካሄደው ፕሮግራሙ በሚገኝበት ካምፓሶች መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማንቀበል መሆኑን እናሳውቃለን



https://t.me/httpentra
የጥሪ ማስታወቂያ
ለሰላሌ University ለነባር (2ኛ ዓመት እና ከዚያ በላይ) የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ

እንኳን ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን አደራሳችሁ እያልን ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 7-8/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ
1. ማንኛውም ተማሪ “National ID” ይዞ መምጣት ያለበት መሆኑን፣፤
2. ከተጠቀሰው ጊዜ አስቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሬጅስትራር ጽ/ቤት

https://t.me/httpentra
ለነባር  ተማሪዎች ጥሪ ያቀረቡ ዩኒቨርስቲዎች

1 Mattu university መስከረም 7 እና 8
2 Debrebrehan university መስከረም 7 እና 8
3 Mekelle university  መስከረም 9 እና 10
4 Bahirdar university መስከረም 7 እና 8
5 Salale university መስከረም 7 እና 8
6 Oda bultum university መስከረም 7 እና 8



https://t.me/httpentra
✅BongaUniversity

በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ ለሆናችሁ የመደበኛ መርሃግብር ተማሪዎች በሙሉ

🔰ምዝገባ የሚካሄደው መስከረም 7 እና 8/2019 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን።

1ኛ ዓመት ለምትገቡ የመግቢያ ጊዜ ወደፊት እናሳውቃለን።


https://t.me/httpentra
#WolloUniversity

ወሎ ዩኒቨርሲቲ የ2ኛ ዓመትና በላይ ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች የ2019 ትምህርት ዘመን የመግቢያ ጊዜ መስከረም 11 እና 12/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል።

በተጠቀሱት ቀናት በምትማሩበት ግቢ (በደሴ ግቢ፣ በኮምቦልቻ ግቢ እና በልዕለ ህክምና ግቢ) ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።

መስከረም 13/2019 ዓ.ም በቅጣት ምዝገባ ሲሆን፣ ትምህርት መስከረም 13/2019 ዓ.ም እንደሚጀመር ተገልጿል።

በ2019 ዓ.ም ወደ ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለምትመደቡ የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች፣ የሪሚዲያል ተማሪዎች እና በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተምራችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ጥሪ ወደፊት ይደረጋል ተብሏል።

https://t.me/httpentra
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሁሉም ነባር የቅድመ-ምረቃ እና የድኅረ-ምረቃ መደበኛ እና ተከታታይ መርሐግብር ተማሪዎች የመመዝገቢያ ቀናት መስከረም 04 እና 05/2019 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በሀትምህርት ሚኒስቴር የምትመደቡ አዲስ ገቢ መደበኛ እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተከታተላችሁና የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች መግቢያ መስከረም 07 እና 08/2019 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

https://t.me/httpentra
            Share share🙏🙏
https://t.me/httpentra
❤1😁1
#AmboUniversity ተማሪዎች

ለሁሉም የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንዲያውቁት የሚፈለገው፦
የመመዝገቢያ ሂደቱ በኦንላይን (Online) እና በአካል (Face-to-Face) እንደሚካሄድ ሲሆን፣ ምዝገባው ሰኞ፣ መስከረም 18 እስከ ማክሰኞ፣ መስከረም 19፣ 2019 ዓ.ም. ይካሄዳል።
መልካም አዲስ የትምህርት ዘመን!


https://t.me/httpentra
✅የ ጥሪ ማስታወቂያ


የቦረና ዩኒቨርሲቲ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ምዝገባ በመስከረም 7 እና 8 ቀን 2019 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን እያሳወቅን፤ በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጅስትራር ጽሕፈት ቤት በአካል በመገኘት ምዝገባችሁን እንድታጠናቅቁ በጥብቅ እሳስቧል።

በተጨማሪም በ2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሬሚዲያል (Remedial) መርሃ ግብር ሲከታተሉ ለነበሩና በ2019 ዓ.ም ወደ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ለሚገቡ ተማሪዎች፤ የመግቢያውን ጊዜ ወደፊት የምናያሳውቅ መሆኑን ገልጷል።

ማሳሰቢያ  : Fayda/id መያዝ ግዴታ ነው

https://t.me/httpentra
ለአርሲ ዩኒቨርሲቲ ነባር ቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

የምዝገባ ጊዜ መስከረም 9-10/2019 ዓ.ም እና ትምህርት የሚጀምረው መስከረም 12/2019 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እናሳውቃለን።

📣 1ኛ ዓመት ለምትገቡ በቀጣይ ማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል።
📣 በ 2018 ዓ.ም በቆጂ ካምፓስ የነበራችሁ ተማሪዎች ወደ ዋናው ካምፓስ (Main Campus) የምትመጡ ሲሆን ፤ ሌሎች ተማሪዎች በሙሉ ባለፈው ዓመት ስትማሩ ወደነበረበት ካምፓስ የምትገቡ መሆኑን እናሳውቃለን።


https://t.me/httpentra
📣#የጥሪ_ማስታወቂያ

       
ለአክሱም ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ነባር ተማሪዎች በሙሉ፤

የዩኒቨርሲቲያችን ነባር መደበኛ ተማሪዎች፤ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት መስከረም 14 እና 15 2019
ዓ/ም ባለው የጊዜ ሰሌዳ መሆኑን አውቃችሁ፤ ከዚህ ቀደም ስትማሩበት በነበራችሁት ግቢ በአካል በመገኘት ሪፖርት በማድረግ ምዝገባችሁን እንድታከናውኑ እያሳወቅን፤ ከዚህ ውጭ ምንም ዓይነት ምዝገባ በውክልና የማይቻል መሆኑን ለማሳሰብ እንወዳለን።

✔ በ2018 ዓ.ም በአክሱም ዩኒቨርሲቲ በሬሜዲያል (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁ ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች፤ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን የምትገቡበት የመግቢያ ቀናት፤ በ2019 ዓ.ም አዲስ ከሚመደቡልን ተማሪዎች ጋር አብረን የምንጠራችሁ መሆናችንን አውቃችሁ በትዕግስት እንድትጠብቁ ለማሳሰብ እንወዳለን።

የአክሱም ዩኒቨርሲቲ ዋናው ሬጅስትራር ፅ/ቤት!


https://t.me/httpentra
❤1