“ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ (ኤፌ. 5፡16)።
ዕድሜ ለንስሓ እየሰጠ፤ አገልግሎታችንን እየባረከ፤ በአባትነት ፍቅሩ ከዘመን ወደ ዘመን የሚያሸጋግረን ልዑል እግዚአብሔር እንኳን ከዘመነ ቅዱስ ማርቆስ 2018 ዓ.ም ወደ ዘመነ ቅዱስ ሉቃስ 2019 ዓ. ም በሰላም አሸጋግራችሁ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በስብከተ ቃሉ ላመኑ፣ በሞተ እስጢፋኖስ በዓለም ሁሉ ለተበተኑ ምእመናን በላከላቸው መልእክት ውስጥ ያለፉበትን የኃጢአት ዘመን ትተው፣ በንስሓ ታጥበው፣ ዘመኑን እየተመለከቱ በማስተዋል በሃይማኖት እንዲኖሩ የጻፈላቸው የሕይወት ቃል ነው።
የተወደዳችሁ የልዑል እግዚአብሔር ልጆች! ዘመን ተለውጦ አዲስ ዘመን ሲተካ ለንስሓ አዲስ ጊዜ እየተሰጠን መኾኑን መዘንጋት የለብንም። እንግዲህ እንደ ጥበበኞች እንጅ ጥበብ እንደሌላቸው ሳይሆን እንደት እንድትመላለሱ በጥንቃቄ ተጠበቁ “ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና ዘመኑን ዋጁ (ኤፌ. 5፡16) እንድል ቅዱስ መጽሐፍ በዚህ ከፉ ዘመን ራስን በመግዛትና በመቆጣጠር ቸግርን መጋፈጥና ማለፍ የክርስትና ግደታችን መሆኑን መዘንጋት የለብንም።
የሰው ልጅ ያለፈ ሕይወቱን እየገመገመ፣ መተው ያለበትን እየተወ፣ ከስሕተቱ ተምሮ ንስሓ እየገባ፣ በምክረ ካህን ራሱን እየለወጠ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኘውን ነገር ፈትኖ እየመረጠ ክርስቲያናዊ ሥርዓትን ጠብቆ እንዲኖር በእግዚአብሔር ታዝዟል።
ነቢዩ ዳንኤል “ጥበብና ኃይል ለእርሱ ነውና የእግዚአብሔር ስም ከዘላለም እስከ ዘላለም ይባረክ፤ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል” (ዳን 2፥20) በማለት እግዚአብሔር በጥበቡ ጊዜያትንና ዘመናትን እንደሚለውጥ ነግሮናል። አምላካችን በጥበቡ ዘመንን ሲለውጥ የሰው ልጅም ከቆመበት ሥፍራ እግዚአብሔርን ደስ ወደሚያሰኝ ተግባር እንዲቀርብና በተሰጠው ዘመን ሰውንም እግዚአብሔርንም እንዲያገለግል እንጂ የዚህ ዓለም ምርኮኛ እንዲሆን አይደለም።
በመጽሐፍ እንደተነገረን የሰው ልጅ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኙት ነገሮች ማለትም ፍቅርን፣ በጎነትን፣ የዋሕነትን፣ ከኃጢአት ርቆ በንስሐ ጸንቶ መኖርንና በጥበብ መመላለስን የማንነቱ መገለጫ ያደርግ ዘንድ ነው። በአዲሱ ዓመትም በልባችን መታደስ ተለውጠን ከኃጢአት ርቀን በንስሐ ጸንተን ሕገ እግዚአብሔርን እየጠበቅን ዘመኑን መስለን ሳይሆን ዘመኑን ዋጅተን የእግዚአብሔር መንግሥት ወራሾች ለመሆን መዘጋጀት ይኖርብናል።
የተወደዳችሁ በሩቅም በቅርብም የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያዊያት “በሰላም ማሰሪያ የመንፈስን አንድነት ለመጠበቅ ትጉ”(ኤፌ 4፥3) ብሎ እንደተናገረው በአዲሱ ዓመት አሮጌውን የመለያየት የዘረኝነት፣ የምንደኝነት፣ የጸብ፣ የመወሻሸት፣ የመገፋፋት፣ የመጠፋፋት፣ ወዘተ... አመል ፀባያችንንና ልምዳችንን በማስወገድ ለአንድነት፣ ለፍቅር ለሰላም፣ ለይቅርታ፣ ለእውነት፣ ለበረከት የተዘጋጀን የክርስቶስ መለእክተኞች መሆን እንደሚገባን በአጽናዖት ለማሳሰብ እወዳለሁ። አዲሱ ዓመት የንስሓ፣ የይቅርታ፣ የሰላም፣ የደስታ፣ የፍቅር ይሁንልን!
አባ ፊልጶስ
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት፤
የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
መስከረም 1 ቀን 2019 ዓ.ም

🙏4❤3
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምዕመናን በሙሉ!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርስቲ በ2018 ዓ.ም በርቀት እና በኦንላይን ዘርፍ በዲግሪ መርሐ ግብር የነገረ መለኮት ትምህርትን ለማስተማር ከነሐሴ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 19 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ የአዲስ ተማሪዎችን ምዝገባ እያካሄደ ይገኛል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ በዩኒቨርስቲው የርቀት እና በይነ መረብ ኮሌጅ በአካል ወይም በወኪል በመቅረብ ዋናውን የትምህርት ማስረጃችሁንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ በማቅረብ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ ሁሉም አመልካቾች ከሚኖሩበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲን የሰበካ አባልነት የድጋፍ ደብዳቤ እና 4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251949000333 እና +251949000777 ይደውሉ፡፡
በቴሌግራም ቻናላችን @HTUCODEE ይከታተሉን

❤7
በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) መሪነት ለቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ መምህራን የሥልጠናና የምክክር ጉባኤ ተካሔደ
___
(ቅ.ሥ.ዩ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም)
በብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ (ተባባሪ ፕሮፌሰር) የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት፣ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ መሪነት፣ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በማስመልከት ለዩኒቨርሲቲው መምህራን የተዘጋጀ የአንድ ቀን ሥልጠናና ምክክር ጉባኤ ዛሬ መስከረም 26 ቀን 2019 ዓ.ም በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ።
መርሐ ግብሩ ብፁዕ ዶ/ር አቡነ ፊልጶስ Educational Eco System in E.O.T.C በሚል ርእስ ሥልጠና የሰጡ ሲሆን ብፁዕነታቸው በመማር ማስተማር ሂደት፣ መምህራኑ ሊኖራቸው በሚገቧቸው ኃላፊነቶችና ተማሪዎችን በማገልገል ዙሪያ ለመምህራኑ ሰፊ ሥልጠናና መመሪያ ሰጥተዋል።
ከሰዓት በኋላ በቀጠለው የመምህራን ጉባኤ ብፁዕነታቸው ሥልጠና በሰጡበት ርእሰ ጉዳይ መነሻነት መምህራኑ በስምንት ቡድኖች ተከፋፍለው በተለያዩ የውይይት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በጋራ የተወያዩ ሲሆን፣ ከውይይቱ በኋላም እያንዳንዱ ቡድን የደረሰበትን ሐሳብና የውይይቱን ውጤት ለተሳታፊዎች አቅርበው ተወያይተውበታል።
ስምንቱ ቡድኖችም በቤተ ክርስቲያኒቱ ታላላቅ አባቶች ስም ሰይመው የአንድ ሙሉ ቀን ወርክሾፕ መምህራኑ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በተሻለ መንፈስና በጋራ ትብብር እንዲወጡ የሚያግዝ የምክክርና የልምድ ልውውጥ መድክ ላይ በንቃት ተሳትፈዋል።
ብፁዕነታቸው ከውይይቱ የተገኙ ግብአቶችን መነሻ አድርገው ለመማር ማስተማሩ አጋዥ የሚኾኑ ግብአቶችን አክለው በቅርብ ቀን ቀጣይ ውይይት እንደሚደረግ ቃል ገብተውዋል።
የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ሕዝብ ግንኙነት