Holy Spirit Revival
373 subscribers
81 photos
8 videos
17 files
37 links
The End Time Holy Spirit and Gospel Revival...
Download Telegram
ቅርበት(Intimacy)
It's all about intimacy...ወደ ደረቱ በመጠጋት ኢየሱስን በጥልቀት ማወቅ። ኢየሱስን አውቆ የሚጨርስ ማንም የለም። ነገር ግን ኢየሱስ ራሱን የሚገልጥበት level  ይለያያል። በቅርበታችን ልክ ነው ኢየሱስን የምናውቀው። casual ክርስቲያን ኢየሱስን በስም እና በሰላምታ፥ close የሆኑ ደግሞ በግማሽ፥ best level ያሉ ደግሞ እጅግ ያውቁታል። exceptional በሆነ መልኩ ለኢየሱስ ቅርብ የሆኑ እና ኢየሱስን የሚያውቁ ደግሞ አሉ። ከብዙሃኑ ህዝብ ይልቅ 70ው ደቀመዛሙርት፥ ከ70ው 12ቱ፥ ከ12ቱ 3ቱ፥ ከ3ቱ ደግሞ ዮሐንስ ከኢየሱስ ጋር ያላቸው ቅርበት እየተጠጋ የሚሄድ ሲሆን በቅርበታችው ልክ ኢየሱስን የሚረዱበት እና ስለ ኢየሱስን የሚያውቁበት ልክ ይለያያል። ከሁሉም ይልቅ ዮሐንስ የኢየሱስን ልብ ቀርቦ ያውቅ ነበር። ለሌላው ሚስጥር የሆነ ለእሱ ግን እጅግ ይገለጥ ነበር። ኢየሱስ ይወደው ነበር የተባለውም እሱ ነው። ጉዳዩ የማጋፋት እና የመጋፋት ሳይሆን ወደ ኢየሱስ ደረት የመቅረብ ጉዳይ ነው። it's all about intimacy...



https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
https://t.me/holyspiritrevival
Channel photo updated
Forwarded from Deleted Account
ሼር አርጉ ወገኖች ተቃውሞአችሁን አሰሙ ዝም አትበሉ
***********
#ሰዶማዊነትን_እቃወማለሁ_challenge_ሁላችሁም_በፈጣሪያችሁ_ስም_ልለምናችሁ_ተቀላቀሉ

👉“የሰዶም ሰዎች ግን ክፉዎችና በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ኃጢአተኞች ነበሩ።”
— ዘፍጥረት 13፥13

👉“እግዚአብሔርም በሰዶምና በገሞራ ላይ ከእግዚአብሔር ዘንድ ከሰማይ እሳትና ዲን አዘነበ፤”
— ዘፍጥረት 19፥24
ግብረ ሰዶማዊነትን እቃወማለው 🙅‍♀️🙅‍♀️🙅‍♀️

☝️መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ግብረ-ሰዶማዊነት በዚህ መልክ ጋብቻን አስቀምጧል ።

👉 መጽሐፍ ቅዱስ ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደ ኢ-ሞራላዊና ተፈጥሯዊ እንዳልሆነ ኃጢአት ይኮንናል። ሌዋውያን
18፡22 ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደ ርኩሰት ይወስደዋል፣ እንደ ጸያፍኃጢአት። ሮሜ 1፡26-27 የግብረ-ሰዶማዊነት ሐሳብና ድርጊትንእንደ አሳፋሪ፣ ተፈጥሯዊ እንዳልሆነ፣ ሴሰኝነት፣ እና ወራዳነትአድርጎ ይገልጸዋል። አንደኛ ቆሮንቶስ 6፡9 እንደሚያስቀምጠውግብረ-ሰዶማውያን ርኩሶች ናቸው እናም የእግዚአብሔርን
መንግሥት አይወርሱም።

🤔ሁለቱም የግብረ-ሰዶማዊነት ሐሳብና
ድርጊቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ተኮንነዋል፣ የግብረ-ሰዶማውያን“ጋብቻ” የእግዚአብሔር ፍቃድ አለመሆኑ ግልጽ ነው፣ እናም
በእውነቱ ኃጢአት ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ በሚጠቅስበት ጊዜ ሁሉ፣ በወንድና በሴት መካከል ነው። በመጀመሪያ የተጠቀሰው ጋብቻ፣ ዘፍጥረት
2፡24፣ ሰው ወላጆቹን በመተው ከሚስቱ ጋር እንደሚተባበር ይገልጻል።
ጋብቻን በተመለከተ መመሪያ የሚሰጡ ምንባቦች፣ እንደ 1ቆሮንቶስ 7፡2-16 እና ኤፌሶን 5፡23-33 ያሉት፣ መጽሐፍ ቅዱስ
በግልጽ ያስቀመጠው ጋብቻ በወንድና በሴት መካከል መካሄዱንነው።

😥 እንደ መጽሐፍ ቅዱስ አባባል፣ ጋብቻ የሕይወት ዘመንኅብረት ነው፣ በወንድና በሴት መካከል፣ በቅድሚያ ቤተሰብን ለመገንባትና ለእዚያ ቤተሰብ አመቺ የሆነ አካባቢ ለመስጠት።
ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይህንን የጋብቻ መረዳት ለመፈጸም ጥቅም ላይ የሚውል አይደለም።

የመጽሐፍ ቅዱስ የጋብቻ አተያይ
ሁለንተናዊ የሆነ የጋብቻ አተያይ ሆኗል፣ በእያንዳንዱ የሰዎች ሥልጣኔ፣ በዓለም ታሪክ ላይ። ታሪክ የግብረ-ሰዶማዊነትን ጋብቻ
ተቃውሞ ይሞግታል። ዘመናዊው ሃይማኖታዊ ያልሆነው ሥነ-ልቦና እውቅና እንደሰጠው ወንድና ሴት በሥነ-ልቦናም ሆነ በስሜት
የተፈጠሩት እርስ በርሳቸው እንዲቀባበሉ ነው።

ቤተሰብን በተመለከተ፣ የሥነ-ልቦና ሰዎች የሚሉት በወንድና በሴት መካከል
የሚደረግ ኅብረት፣ ሁለቱ ተጋቢዎች መልካም የሆነውን ጾታዊ ሚናቸውን እንዲወጡ ያስችላቸዋል፣ በተሻለ ስፍራ በመልካም
የተቀረጹ ልጆችን ለማሳደግ። ሥነ-ልቦና የግብረ-ሰዶማዊ ጋብቻን ተቃውሞ ይሞግታል። በተፈጥሮ/በአካል፣ ወንድና ሴት የተፈጠሩት
በግብረ-ሥጋ ግንኙነት አንድ ላይ “እንዲገጥሙ” መሆኑ ግልጽ ነው።

🤯በግብረሰዶማውያን-ሥጋ ግንኙነት “ተፈጥሯዊ” አሠራር ልጆችንለመውለድም ፣ በግልጽ የተቀመጠው ብቸኛ መንገድ በወንድና በሴት መካከል የሚደረግ የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ነው ይሄንን ዓላማ የማያሳካ።

☝️ተፈጥሮ የግብረ-ሰዶማዊነትን ጋብቻ ተቃውሞ ይሞግታል። ስለዚህ እኛም ኢትዮጵያን ግብረ ሰዶምን እንቃወማለን ።
Forwarded from URIM🔥 (✞ቃለ-አብ✞)
"ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል!"

ብዙ አማኝ ወደ ቤተ ክርስቲያን የሚመጣው ለመዝናናት ነው። ሌላውም ሰው ጆክ ሲያምረው፣ መሳቅ ሲፈልግ የእኛን ቪዲዮዎች ነው የሚያየው። በኢየሱስ ስም፣ በልሳን፣ በጸሎት ከት ከት ብሎ ይስቃል። እኛም አብረን እንስቃለን። ምንም ስለማይመስለን ቪዲዮውን እየተቀባበልን እንስቃለን። የእግዚአብሔር ስም መቀለጃ ስለሆነ የሚያየው አይፈራው፣ የሚሰማን አይፈራው። እኛም አላከበድነው በሚገባ አላሳየነው፣ አልገለጥነው፣ አላመጣነው...።

የአብዛኞቻችን አገልጋዮች ዓላማ ራሱ ሰውን ማዝናናት ነው፤ "ምን ብናገር አዝናናዋለሁ ነው።" የብዙ ምዕመናን የቤተ ክርስቲያን፣ የስብከትና የአገልግሎት ምርጫ "የት ብሄድ ያልተካበደ ነገር እሰማለሁ"፣ "መዝናናት አገኛለሁ" የሚል ነው። ቤተ ክርስቲያን ቴአትር ቤት፣ እኛም ኮሜዲያን ሆነናል።

ተዉ እንጂ ብዙም ሩቅ ባልሆኑ ዓመታት፣ የዛሬ ሰልሳ ዓመት ወደ ኃላ "ሪዋይንድ" ብታደርጉ አማኞች የሚፈራ ምገስ ነበራቸው። ሰዎቹ ዛሬም በሕይወት ስላሉ ሄዳችሁ ጠይቋቸው። በቤተ ክርስቲያናቸው ደጃፍ ማለፍ እንኳ ያስፈራ ነበር። ሕይወታቸው ግርማ ነበረው። መልዕክታቸው አስደንጋጭ ነበር። ለማስደንገጥ ብለው ሳይሆን እግዚአብሔር በመካከላቸው ነበር።

እዚያ ለመቀለድ አትሄድም፤ ንሰሐ እንጂ  ጆክ ትዝ አይልህም። አጋንንት ይወጣል፣ ሰዎች ይፈወሳሉ። የእግዚአብሔር ቃል፣ የክርስቶስ ወንጌል ይሰበካል። ይኼ ሁሉ የሚሆነው ፐርፌክት ፍጹማን ክርስቲያኖች ስለሆኑ  አይደለም። ግን የኢየሱስን ስም    አስከባሪዎች ነበሩ።

አሁን ቢያንስ ስሙ በሆነ መንገድ ይከበር ዘንድ ብንጸልይስ? ቢያስፈልግ ኮሜዲያኖቹን በጊዜ ቢወስደን፤ ይኼም እኮ አንዱ መንገድ ነው። ወይም ደግሞ ጥግ አስይዞን የሆኑ ሌሎች ሰዎች ቢያመጣ፣ እኛ ዕድሉን አልጠቀም ስላልን ሌላን ትውልድ ቢያስነሳልን፣ ስላላየናቸው እንጂ እግዚአብሔር ስሙን የሚያስከብሩለት ልጆች አሉታ!...

በዚህ ዘመን ወንጌል የምንሰብክበት ብዙ መድረክ አግኝተን፣ ሚዲያ ተመቻችቶልን አልተጠቀምንበትም። በየሰዉ ቤት የጌታን ስም ተሸክመን ለመግባት እንደዚህ ዘመን ዕድል ተሰጥቶን ያውቃል እንዴ? እኛ ግን ጆካችንን ይዘን ገባንበት፤ እግዚአብሔርን መሳለቂያ አደረግነው። ስለዚህ ወገኖቼ በአሕዛብ መካከል የተነቀፈው ማንነቱ የቀለለው ስሙ መልሶ እንዲከብድ በየትኛውም መንገድ ምክንያት ለመሆን መጸለይ አለብን።

ዶ/ር ማሙሻ ፈንታ

@oraclekb
Forwarded from #KALTUBE
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Read Bible

“አቤቱ፥ የሥርዓትህን መንገድ አስተምረኝ፥ ሁልጊዜም እፈልገዋለሁ።”
       መዝሙር 119፥33

#read #bible #kaltube #saka
💐💐💐💐
@KALTUBE
@KALTUBE
@KALTUBE
Forwarded from REVEAL JESUS
#አስቸኳይ
#በአፋር_ የታሰሩ_ ሰላማዊ_ አገልጋዮች_ እንዲፈቱ_ ድምፅ_ እንሁን_!!!

#ጥር 19/5/2016 በአፋር ሎጊያ ቤተክርስቲያን 19 ወጣቶች ለአገልግሎት ከደቡብ ከኦሮሚያ የተወጣጡ አገልጋዮች የሄዱ ሲሆን እዛ ያሉ ቅዱሳንን በማገልገል እና ለሀገራችንን ሰላም እና አንድነት በመፀለይ ያሳለፉ ሲሆን ጥር23/5/2016 ሐሙስ ከሰአት ሰመራ ሄደው ከተማዋን እየጎበዩ በእግረኛ መንገድ ላይ ወክ በማድረግ መንፈሳዊ ነገር እተነጋገሩ ሲሄዱ ሲቪል የለበሰ ፖሊስ አስቆማቸው

እንዴት እዚህ ምድር ላይ መጣችው በማለት አፍሶ ወደ እስር ቤት አራት ወጣቶች አስገብቷል ዛሬ ሰባተኛ ቀናቸው ሲሆን በተደጋጋሚ ነገ እንለቃቸዋለን እያሉ እየደበደቡ ከአራቱ ሁለቱ በፀና የታመሙ ሲሆን ዛሬ ችራሽ ወደ አሳይታ ማረሚያ ቤት ተወስደዋል እንዴት በሰላማዊ ሰዎች ላይ እንዲህ ይደረጋል ጉዳዩ በአንዳንድ ፅንፍ በተሞሉ አካላት እንዲህ ሲደረግ ይሄ የመጀመሪያው አይደለም በአፋር የክርስቲያኖች ስደት እየተበራከተ ነው የማምለኪያ አዳራሾች እየተዘጉ ነው አሁን ለአፋር ክልላዊ መንግስት እንዲደርስ እና ወንድሞቻችን ፍትህ እንዲያገኙ ድምፅ እንሁን #የታሰሩት_ ልጆች_ ስም_ ስርዝር

#አብነት_ ኢሳያስ
#ኤርሚያስ_ ካሳሁን
#ተከተል_ ደበበ
#ቾምቤ _አሰፋ

@revealJesus
Saved for Good Works, Not by Good Works.

We believe that we are SAVED BY GRACE, not by works.

"For by grace you have been saved through faith, and that not of yourselves; it is the gift of God, not of works, lest anyone should boast." Ephesians 2:8-9

Salvation by good works doesn’t work. Our good works are not enough to earn salvation. If that would’ve been possible, then Jesus died in vain.

We are SAVED FOR GOOD WORKS, not by good works.

"For we are His workmanship, created in Christ Jesus for good works, which God prepared beforehand that we should walk in them." Ephesians 2:10

Faith without works is dead. True faith always produces good works (James 2:14-26).

Grace is not a license to sin but a power to live a holy life (Titus 2:11-12).
Forwarded from Eyasu